Telegram Web Link
እንደበፊቱ አብረን እንዳንስቅ ,እንዳናወራ ያደረገን የሆነ ነገር አለ ይች አለም በኛ አንድ መሆን ደብሯታል ለዛም ነጣጠለችን..😒😞
🦋ኪያብ
           ⭐️ኮከብ ቆጠራ🌟

በጀርባዬ ሆኜ በጀርባሽ ተንጋለሽ ደልቶን የመስኩ ሳር
ሽቅብ እያስተዋልን የሞላውን ህዋ በብርሃን ጠጠር
ሰማዩን ለሁለት ተካፍለን በፍቅር

ግማሹን ለራሴ ግማሹን ለራስሽ ኮከብ ልንቆጥር
ሃገር ስጠኝ ብለሽ ሃገር ስጪኝ ብዬሽ
ከትልቁ ኮከብ ወዲህ ግዛት የኔ ከትልቁ ኮከብ ወዲያ ማዶ ያንቺ ብለን በህዋ ላይ አበጅተን ድንበር
እንደጠፈርተኛ በአይን መንኮራኩር

ከዋክብቱን ሁሉ ዳሰን ለቅመን አፍሰን
ለፍተን ቆጥረን ስፍራቸውን ሳናውቅ በቁጥር ለይተን
ቀልቤ ይምራኝ ቀልብሽ ባላወኩት
ሰዓት ድንገት ዞር ስትይ ዞር ብል በድንገት
በዓይን ንጥቀት ፍጥነት
የቆጠርናቸውም ያልቆጠርናቸውም ትንሹም ትልቁ
ከዋክብቱ ሁሉ ተደበላለቁ
ከንፈሮቻችን ላይ እሳት አፈለቁ
ከዛ የሆነውን እኛም አላወቅን እነሱም አልነቁ እነሱም አያውቁ


- ከነቢል መኮንን 👏
እኔ ነኝ ዳግም ህይወት🙋‍♀

💏

💆ስላንተ ማሰብ እየጀመርኩኝ ነው
ገና በጠዋቱ አንተን መናፈቅ፣
ስላንተ መጨነቅ ፣ያደረከውን ያወራከኝን እያሰብኩ ሳይታወቀኝ ፈገግ ማለት
እየጀመርኩኝ ነው።😁

የሂዊ ማስታወሻዋች 👱‍♀
☺️ @itsmedagihiwi ❤️
👫 @itsmehiwihabsawit
🎤Hሀበሻman

መልካም የአባቶች ቀን 👨‍🍼👨‍🍼👨‍🍼👨‍🍼👨‍🍼👨‍🍼👨‍🍼👨‍🍼
📚ከብዕረኛው.....

            ጠበኛ እውነቶች
                      ~ በሜሪ ፈለቀ

✏️ ሰዎች ሊያወድሱህ ከፈለጉ ከፈጣሪ ታናሽ፥ ሊዘልፉህ ከፈለጉ ደግሞ ሳጥናኤል የሚቀናበት ክፉ ያደርጉሀል፤ ከሰማሃቸው ራስህን የመሆን እድል አይሠጡህም፥ ሁሉም በፈለጉት መንገድ ሊቀርፁህ መጥረቢያ ይስላሉ። ልብህን ከከፈትክላቸው የየድርሻቸውን ጠርበውህ ቅርፅ አልባ ያደርጉሀል………
✏️ ስህተት በስህተት ቢባዛ ቢደመርም ውጤቱ የትየለሌ ጥፋት ነው………
✏️ ሁሉም በልቡ ለማንም የማያሳየው ቆሻሻ ይኖረዋል፥ ጥላቻ ክፋት ግልፍተኝነት ራስን መውደድ… አንዱ ይኖርበታል፤ ልዩነቱ ብዙዎቻችን ያ ባህሪያችን በአስገዳጅ ሁኔታ ፈንቅሎ ካልተገለጠ በቀር ንፁህ ቅን እና ፍፁም እንደሆንን እናስመስላለን………
✏️ ሲገባኝ ሁሉም ሰው የሆነች "የለውጥ ኩርባ" አለችው፥ አስተሳሰቡ ስሜቱ ወይ ድርጊቱ የሚቀየርባት፥ ወደ አዲስ ምዕራፍ የሚታጠፍባት፥ ከወደቀበት መቀመቅ የሚስፈነጠርባት ወይም ለዛለው ጉልበቱ አቅም የሚያገኝበት………
✏️ ለህይወት መጨረሻ ብሎ ነገር የለም፥ የአንዱ ቀን መጨረሻ የሌላው ቀን መጀመሪያ ነውና፤ የሰኞ ማለቅ የማክሰኞ መጀመር እንደሆነው፥ የምድር መጠቅለል ለሰማያዊ ህይወት መጀምር እንደሚሆነው………
✏️ ከእያንዳንዱ ክፋት ጀርባ መሪር የሆነ በደል አለ፥ ጥያቄው በደልን ይቅር ያለ በጎነት አለ? ካለም በደልን ይቅር ለማለት የሚያስችል ትልቅ በጎነት የሚፈጥር 'ፍቅር'ን የሚጠይቅ ይመስለኛል………
✏️ ሁሌም ዛሬ ላይ ቆመህ ሁለት ምርጫ አለህ፥ ትናንት ወይም ነገ፤ ትዝታ ወይም ተስፋ!………
✏️ ብሩህ ነገ የሚባል ቀን የለም፥ ማንም ቢሆን ነገን ኖሮ የሚያውቅ የለም፤ ምክንያቱም ነገን መኖር ስንጀምር ዛሬ ተብሏል………
✏️ እኔና አንተ አንድ ቦታ ላይ በተለያየ አቅጣጫ ፊታችንን አዙረን ብንቆም የእኔ ቀኝ ላንተ ግራ ነው፥ ያንተ ግራ የኔ ቀኝ ነው፤ ቀኝ ይሄ ነው ግራ ይሄ ነው ብዬ ብከራከርህ ቂል ነኝ። እንዳንተ አቋቋም ያንተ እውነት ይሆናል.. ባንተ እውነት ለማመን ያንተን ጫማ መዋስ አለብኝ………

         ...❤️ #ዮቶራዊት ❤️...

            @ItsMeMadi👩‍💻
       @Mahder_Kasahun🦋
ለምን ወደዋል

🎤Hሀበሻman

@Abusha_13
@KeFilimona
የኔ ብቻ እንድትሆን ሳይሆን እኔም ያንተ እንድሆን ነበር ፍላጎቴ እኔን የአንተ ማድረግ ባልችልም አንተን ግን የእኔ አድርጌ እየኖርኩ ነው ። ከተለያየን ብዙ ጊዜ ሆነን አይደል ? እኔ ግን አሁንም ላንተ እፅፋለሁ በእየለቱ የማወራህ ያክል ይሰማኛል ። ምን እንደሆንክ           ምን እንደምትሰራ       ምን እንደምታስብ አላውቅም...... ግን እንደ ድሮ ክፉ እንዳይነካብኝ እፀልይልኀለሁ ፤ የኔ ባላረግህም ያንተ መሆንን ስላልከለከለኝ ፈጣሪዬን አመሰግነዋለሁ ። ግን ደግሞ ሰሞኑን ናፍቀኸኛል ......ይሄንን ብፅፈው ለውጥ የለውም አይደል ?........ እንደድሮው አቅፈኸኝ ረጅሙን መንገድ በእግራችን አንዞርም አይደል ? ..........በሀይቁ ውስጥ እግራችንን አርገን የልባችንን አናወራም አይደል ? ..........በባዶ መሸታ ቤት ገብተን የራሳችንን ዘፈን አስከፍተን አንቀውጠውም አይደል ? ......ሁሉንም ተወዉ አትደውልልኝም አይደል ?      ሁሌ ያሰብኩትን ሳልነግርህ የምትቀድመኝ ወፍ የት ሄደች ? ዛሬም ትንገርልኝ ናፍቀኸኛል የምር ናፍቀ.....

B19 🍷
እንደዚህ ነው ፍቅር
🎤Hሀበሻ man
@Abusha_13
@KeFilimona
🔥🔥🔥🔥🔥 miki
.
.
  ብ ዙ  የተበደለ የመሰለው፣ ፍትህን በጉልበት ለማግኘት የታገለ፣ "ሰማይ _ ንጉስ_" የሚለውን ብሂል ያልሰማ የሚመስል፣ ፈጣሪን የከሰሰ ''ምስኪኑ ዛፍ ቆራጭ''፤ የልቡ መሻት ሞልቶ ያስቀጣዋል? ቀጪው ማን ሆኖ?? እግዜር ምን ተቀጣ???😳🤔🤷‍♀

በ   #ደራሲ_ሄኖክ_በቀለ የተፃፈ በ'5' ክፍል የሚቀርብ፥ ተጋበዙልኝ🙏 በእርግጠኝነት ትወዱታላቹ።
       
           #ዮቶራዊት 🦋🦋..
       @Mahder_Kasahun🦋
ክፍል ፩

        በ #ሄኖክ_በቀለ

     እዚህ ሀገር ውስጥ መቃብራቸው ሊማስ አንድ ሐሙስ የቀራቸው፤ ሕይወትን በዓይናቸው ቂጥ ገላምጠው የጨረሱ፤ “ፍርድና ርትዕ ዘልቋቸዋል” የተባሉ አዛውንት የሚፈርዱበት በሰንበት አንዴ የሚቆም ሸንጎ አለ። በዳይና ተበዳይ ተጠፍረው ይቀርቡና ይካሰሳሉ። በዳይም፣ ተበዳይም የመጡበትን ተናግረው የተሰጠውን ፍርድ ተቀብለው አመስግነው ይሄዳሉ።

     ዕድሉ ቀና “ሰማይ አይታረስ ንጉሥ አይከሰስ!” በሚል ማኅበረሰብ መሃል እየኖረ —ሰማይ ሊያርስ ንጉሥ ሊከስ እንባውን እያዘራ ደረሰ። ነታባ ጋቢ የለበሱ ዳኞች በሸንጎው መሃል ተሰይመዋል። ተከሳሽና ከሳሽ፤ ወሬ ሊያጦለጡል የመጣ የሀገር ሰው፤ ከወደቀው ዋርካ ጀርባ ተንቋጠው አሰፍስፈው ገቢር የሚቀላውጡ ሕፃናት ቦታውን ሞልተውታል።

     ሸንጎውን የሚመሩት ሽማግሌ ከተቀመጡበት ብድግ ብለው ሁሉም ዝም እንዲል እጃቸውን እያወዛወዙ ምልክት ሰጡ። ሽማግሌው ፊታቸው በሽብሽባት የተፈሰፈሰ አሮጌ ቦርሳ የመሰለ፤ ድክም ፍዝዝ ብለው ዓይኖቻቸው ብቻ የነቁ፤ ጭብጥ የምታህል አናታቸው ላይ ግራና ቀኝ ትላልቅ ጆሮዎቻቸው ተሰፍተው ሦስት ፊት እንዳላቸው ነገር የሚያስቱ፤ ከወገባቸው ጎበጥ ያሉ ሰው ናቸው።

     “ክስ ያለህ ቅረብ ተብለሃል!” አሉ ባለች በሌለች አቅማቸው ጅንን ብለው። ከልባቸው አበጥ ስላሉ ይሆን ከወገባቸው ጎበጥ ያሉት?

     ዕድሉ ተንደርድሮ ከሳሽ የሚቆምበት ጉብታ ላይ ተሰየመ። “ይህ ሁሉ ነሆለል የተሰበሰበው “ሚስቴን ወሸሙብኝ”፤ “በሬዬን ነዱብኝ”፤ “አጥሬን ደፈሩብኝ” ሊል አይደል? እንደእኔ የተበደለ በድፍን ሀገሩ ቢታሰስ አንድ ይገኛል? ...ኧረ እንዲያውም!”

     ዕድሉ ቀና ለወትሮው ክስና ክርክር ባለበት የማይደርስ፤ ከምድርም ከሰማይም የተስማማ፤ ቢበድሉት ውጦ ቢወጉት ደምቶ ዝም የሚል ጭምት ነበር። ዛሬ የከሳሽ ጉብታ ላይ ቆሞ ሲታይ የሸንጎው ታዳሚ ጸጥ እረጭ ብሎ አፈጠጠ። ሸንጎውን የሚመሩት ሽማግሌ ብቻ ደስ አላላቸውም ። ዕድሉ በዕድሜ የሚበልጡትን ከሰሾች ገፈታትሮ መቅደሙ አበሳጭቷቸው ይሁን፤ ወይ የስልጣናቸውን  አቅም የሚያሳዩበት ምቹ ጊዜ ጠብቀው ስላገኙ ይሁን..

“ተከሳሾችህን ወደ ፊት ጥራ ተብለሃል!”

     ዕድሉ ቀና ከከሳሽ መደቡ ላይ ፈንጠር ብሎ ወረደ።
ለተከሳሽ የተዘጋጀው ክብታ ላይ ደርሶ በእጁ የያዛትን መጥረቢያ አስቀመጣት። የተሰበሰበው የሀገር ሕዝብ ሁኔታውን በግራ መጋባት ይከታተላል።

   “ተከሳሾቼ ሁለት ናቸው። አንዱ ይኸው! ይሄ መጥረቢያ ነው። ሁለተኛውን እንኳ የት እንዳለ አላውቅም። ብጠራው አይመጣም። ብቆጣው አይፈራም። በሰው ሕግ አይመራም። “ተወኝ! ስለው ይስቅብኛል። ምን እንደበደልሁት እንጃ ብቻ ሰባት ሰማያዊ ጋቢ ለብሶ እያደፈጠ ያጠቃኛል። ባለክንፍ አሽከሮች፣ የገዘፉ አዝማቾች፣ እልፍ ነጫጭ ሎሌዎች አሉት...”

   “ማሸሞሩን ትተህ ምናል ብትናገር?” ሽማግሌው ትዕግስት አጥተው ይቅበዘበዛሉ።

“እንደውም ሁለተኛው ተከሳሽ ፈጣሪ ነው።”

           ይቀጥላል........
   @Mahder_Kasahun🦋
ክፍል ፪

        በ #ሄኖክ_በቀለ

     ዙሪያውን ከቦ የተዘለለው የሀገር ሰው ቦታውን በቱማታ አተረማመሰው። እዚያም እዚህም የተቆጡ ሰዎች በዕድሉ ድፍረት ተለኩሰው መንቦግቦግ ጀመሩ። አንዳንዱ ፈጣሪ ለእዚህ የንቀት ንግግር እዚያው በመብረቅ እንዳያደባያቸው ይለምናል። እስከነተረቱስ “ለኃጥአን የመጣ ለጻድቃን ይተርፋል!” ይሉ የለ? አንዳንዱ “ዕድሉ መወገሩ አይቀርም!” በሚል ተስፋ ሹል ባልጩት ፍለጋ በዓይኑ ይማትራል። አንዳንዱ ዓይናቸው ሥር ላበደው ዛፍ ቆራጭ ከንፈር ይመጥጣል። ከዋርካው ጀርባ ያደፈጡ አመዳም ሕፃናት ምን እንደተከሰተ ለመቅለብ ጆሮዎቻቸውን ዘርግተው ይቀላጠፋሉ።

     ዕድሉ ድምፁ በጩኸት ማዕበል ተውጦ ምን እንደሚል አልተሰማም እንጂ፤ የሀገር ሰው ቁጣ ምንም ሳይመስለው ኃይለቃል እያወራ ይውረገረጋል።

     ሽማግሌው ሕዝቡን እንደምንም ዝም አሰኝተው ወደ ዋናው ዳኛ ዞሩ። ፊታቸው ላይ ወፍራም ቁጣና ቀጭን ደስታ እኩል ተሸርቧል። በሰው ፊት ያዋረዳቸው ይህ ሰው አፍታ ሳይቆይ የሞቱን መግነዝ በራሱ እጅ ስለፈተለ ከንፈራቸው ላይ የታፈነ ፈገግታ ያጣጥራል።

   “ምን ይላሉ እርስዎ?”

     ዋናው ዳኛ ፊታቸው ላይ የተጋደመውን ጠባሳ ቆርጣ የምትስለመለም ዓይናቸውን አጨንቁረው “እስቲ እንስማው?! መቼም አይገድለን...” አሉ። ቁጣ ያደበላለቀው ሸንጎ ከዕድሉ ድፍረት በላይ በዳኛው ውሳኔ ተደናገጠ። ፊቶች ወዛቸው ተመጦ ተቁለጨለጩ። እንኳን ፈጣሪን ያህል ነገር ተከሶ ወትሮም ግራና ቀኝ ማገናዘብ አልተለመደም። ዋናው ዳኛ ከእዚህ በፊት ሸንጎ ረግጠው የማያውቁ ለሄላ-ገነት በቀረበው ሀገር በኩል የሚኖሩ ሽማግሌ ናቸው። በሰው በሰው ጠቢብነታቸው የሀገር ሸንጎ ጠሪዎች ጋር ደርሶ ተፈልገው የተገኙ ስለነበሩ ሕዝቡ እያጉረመረመም ቢሆን ትዕዛዛቸውን ተቀበለ።

     ሽማግሌው እየቀፈፋቸው ወደ ዕድሉ ዞረው “ቀጥል ተብለሃል!” አሉ። የጎበጠ ጀርባቸው ተቃና። ያበጠች ልባቸው ፈርጣ ይሆን?
ዕድሉ ጉሮሮውን ጠራርጎ፤ ለፍልሚያ እንደሚዘጋጅ ሰው ሰውነቱን አፍታቶ ቀጠለ።

     “እንግዲህ ክሴን ስሙት። ይህቺ መጥረቢያና ፈጣሪ በደካማ ጉልበቴ ገብተው በድለውኛል። በማይመጣ መጥተውብኛል። ካደፈጠ አውሬ፤ ከተሰበቀ ጦር፣ በክፉ ከሚያይ ጎረቤት ሸሽጌ ለወግ ትብቃ ያልኳት ልጄን ገድለውብኛል። እውነት እዚህ ሀገር ፍትሕ ካለ በእዚህ እንዲጠየቁልኝ ነው የምሻው።”
አንዱ ቁጣው ያልበረደ ወጣት ብድግ ብሎ...

     “ምነው? ምነው ዕድሉ ምነው? ሰብሉ ሰምሮ፤ አዝመራው አሽቶ፤ ጠላት ደሞ በደጅ ቆሞ እያጓራ እያየህ ሲሆን ሲሆን ማመስገን ሳይሆን በንስሓና በጸሎት መትጋት ሲገባህ፤ ደረትህን ገልብጠህ ከአምላክ ጋር እኩል ቤት ትገጥማለህ? ምናል መቅሰፍት ባትጠራብን?!!”

   ዕድሉ ቀና የወጣቱ መልስ እንደ አንዳች እያደረገው ከአፉ ላይ ነጥቆ ቀጠለ።

     "ዝ ም በ ል!"
“ያልተነካ ግልግል ያውቃል! ማለት እንደአንተ ዓይነቱን ነው። የራስህ ጉዳይ! የልጄን ደም ጠጥቶ የበቀለ አዝዕርት ምን ይረባኛል? ለምን ያሸተውን ጠራርጎ ነቀዝ አያነቅዘውም። ለምን አንበጣና ተምች አያደብነውም?! ሆድ ቢሞላ የልጄን ክብልል ዓይን ይሆነኛል? ጠግቤ ባገሳ የአንገቷን ሽታ የአንገቷን ሽታ ይለኛል? ምነው ደኅና ሰው ነህ ስልህ እንዲህ ቀለልህ?!”

          ይቀጥላል.........
  @Mahder_Kasahun🦋
ክፍል ፫

        በ #ሄኖክ_በቀለ

     “መቼም አልሰማ ብለህ ክሴን እቀጥላለሁ” ካልክ የሆንከውን አብራርተህ ተናገር! አታደናግር!” ሽማግሌው ጮኸ።

     “ነገሩ እንዲህ ነው። የሆነ ቀን አለልማዴ ዓለሜን አስከትዬ ዛፍ ቆረጣ ሄድሁ። በእኔ ቤት ዛፍ ቆርጬ ገንዘብ ላገኝ ነው እንግዲህ። አዬ! ...ምነው በቀረብኝ። ዓለሜን አርቄ አስቀምጬ መጥረቢያዬን ይዤ ዛፉ ላይ ወጣሁና መተግተግ ጀመርሁ። ምን የተረገመው ቀን እንደሆነ እንጃ ከዛፉ ላይ አንዲት ሰላላ ቅርንጫፍ ብላት ብሠራት አልቆረጥ አለችኝ። ዛሬ ደግሞ የምን ተአምር ነው የገጠመኝ? እያልሁ ደጋግሜ ብመታት ጭራሽ እንደድንጋይ መጥረቢያዬን አንጥራ ትመልሳለች እንጂ ፍንክችም አትልም። ሠላሳ ዓመት ዛፍ ስቆርጥ እንዲህ ዓይነት ነገር ገጥሞኝም አያውቅም። የዚህ ሀገር እንጨት እንደምታውቁት ገራም ነው፤ እንኳን ቅርንጫፍ ግንዱም አስሬ ደኅና ካገኙት ይበቃዋል። ተንጋልሎ ያርፋል። የትንግርቴን ተፋጥጬ ሳነሣ ስለው፣ ሳነሣ –ስለው ...እልህ ይዞኝ እንጂ እጄ ዝሎ ኖሮ መጥረቢያው አምልጦኝ ቁልቁል ተምዘገዘገ። በዓይኔ ስከተለው...

   ዕድሉ ቀና ሳግ አንቆ አላናግር ስላለው አቀርቅሮ ጊዜ ወሰደ።

   “ለቅሶህን ተውና ቀጥል ተብለሃል!”

   “በዓይኔ ስከተለው እንደ ኪሩብዔል ሰይፍ ሲገለባበጥ ወርዶ ከየት መጣች ያላልኳት የልጄ አናት ላይ ሰመጠ። ይታያችሁ! ለእንጨት የሰነፈ መጥረቢያ ለልጄ ሲሆን በረታ። ለካ ዓለሜን አርቄ ባስቀምጣትም አሳዝኛት ሥሬ መጥታ ሽቅብ ስታየኝ ነበር። እኔ አፈር ልብላላት ...ሞት ሲጠራት እኮ ነው! ታዲያ ፈጣሪ ቢለው አይደል ሠላሳ ዓመት ሙሉ ገጥሞኝ የማያውቀውን የእዚያ ቀን መጥረቢያ ያመለጠኝ? ታዲያ ፈጣሪ ቢለው አይደል አድርጌ የማላውቀውን መጥረቢያ የሚያመልጠኝ ቀን ልጄን ይዤ የመጣሁት? ታዲያ ፈጣሪ ቢለው አይደል ከዓመት እስከ ዓመት የሚያሰቃያት ንዳድ ያንን ቀን ጋብ ያለላት? ታዲያ ፈጣሪ ቢለው አይደል ለእጅ የምትሰንፍ ቅርንጫፍ በስል መጥረቢያ የለገመቸው? ለምን “እንቢ! ስትለኝ አልተውኋትም? ምነው መጥረቢያውስ ካልጠፋ አውላላ መዳፍ የማታህል የልጄን አናት የመረጠው? ፈጣሪ ቢለው አይደል?”

    አዝማሪው ሐዋዝ ተነሣ
“መቼም እንደሰው ልጅ ጉድ የትም የለም። ጠማማ ዕድሉንም፣ ስንፍናውንም በፈጣሪ ማሳበብ ይወዳል። አንተ የአርባ ዓመት ጎልማሳ ስትሆን ምነው ልጅህን መጠበቅ አላወቅህበት? እጅህ እስኪዝል አንድ ቅርንጫፍ ቀጥቅጥ ያለህ ፈጣሪ ነው? ከእጅህ አሽቀንጥረህ ስትጥለውም ወደወረወርክበት ይሄዳል እንጂ መጥረቢያ እግር የለው፤ ዓይን የለው፤ ምን አድርግ ነው የምትለው? ይህን ድፍረት ለተናገርህበት ራሱ ቅጣት ይገባሃል። ኧረ ምነው! ስንት ነገር ጥለን ነው የመጣነው፤ ጊዜያችንን ባንፈጅ...?”

     ዕድሉ ቀና ክሱን ሰምቶ የሚደግፈው አለማግኘቱ አንገበገበው። ኀዘኑ እጥፍ ድርብ ሆነ። መናገሩ እንደማይጠቅም ሲሰማው ልቡ አመነታ። ቢሆንም የተበደለው አላለቀም። ቢያንስ “ተናግሬ ይውጣልኝ!” ብሎ ተቀበለ።

     “አይ ሐዋዝ! አንተ ጎረቤቴ ሆነህ የደረሰብኝን ሁሉ ስታውቅ እንዲህ ማለትህ አሳዝኖኛል። ጊዜ የተፈጀብህ ለምኑ ነው? አናውቅም የት ውለህ የት እንደምታነጋ? ሌላ ምንም አልልህም አንተም ሴት ልጅ አለችህ። በልጅ የመጣ እንዴት እንደሚያንሰፈስፍ ደርሶብህ እየው።” ንግግሬ እንዳልጠቀመ አይቼያለሁ። ቢሆንም ልናገረውና የመጣው ይምጣ...”

   ዋናው ዳኛ አንካሳ እግራቸውን በእጆቻቸው እያመቻቹ የሚሆነውን በዝምታ ይሰማሉ።

“ይቅር ብዬ አልፌው እንጂ የተበደልሁትስ ይህ ብቻ አልነበረም። ከሆነ አይቀር ግን ይኸው ስሙት።

             ይቀጥላል.........
      @Mahder_Kasahun🦋
የሰካራም ግጥም


🎤Hሀበሻman
ክፍል ፬

        በ #ሄኖክ_በቀለ

    ታላቁ ልጄ እንደምታውቁት የቀኝ እጁ አራት ጣቶች ቆራጣ ናቸው። የእርሱ ታናሽ ደግሞ እጁም እግሩም ላይ ስድስት ስድስት ጣት አለው። ይህ እንዴት ሆነ? ሲቀለድብኝ መሆኑ ነዋ! .....አንድ ቀን ጠዋት የጀመርሁ ሥራ ፍለጋ ስንከራተት ውዬ ሰውነቴ ዝሎ አመሻሽ ላይ ቤት ደረስኩ። ምንም ምንም ሳልል፤ እህልም ሳልቀምስ፤ ልብሴንም ሳላወልቅ መጥረቢያዬን ቆጥ ላይ ሳልሰቅል ተኛሁ። ብዙም አልቆየ ታላቅ ልጄና ነፍሰጡር ሚስቴ በጩኸት ቤቱን ሲያናጉት ብትት ብዬ ተነሣሁ። ሳይ ከልጄ መዳፍ ላይ ደም እንደወራጅ ውኃ ይንዠቀዠቃል። ዘልዬ አፈፍ ሳደርገው አራት ጣቶቹ ተራ በተራ ጠብ፣ ጠብ ብለው እንደጉድፍ መሬት ላይ ወደቁ። ያ መጥረቢያ ከንፈሩ ደም ጠግቦ ተጋድሟል። የሆነው ወዲያው ገባኝ። ታዲያ ምን ዋጋ አለው? ከረፈደ ዕውቀት የቀደመ ጠርጣራነት እንደሚበልጥ ማን አስተምሮኝ  ያኔ? ደንቆሮ፣ የደንቆሮ ዘር አይደለሁ። አንድ ቀን መጥረቢያዬን ማራቅ ብረሳ... ። ዛሬም ድረስ አውራ ጣቱ በመዳፉ ላይ ብቻዋን ፍርፍር ስትል ሳያት እንባዬ ይመጣል። ጠማማ ዕድሌን መግራት ተስኖኝ እንዳጎደልሁት ይሰማኛል!”

    "ይበቃል ተብለሀል።"

     “አይበቃኝም ገና መች ጀመርኩትና?! ኋላ ስንቀዠቀዠ ቤቱ ሄድኳ። ምነው ፈጣሪ ምነው ሳምንህ ጉድ ሠራኸኝ? ስል አለቀስሁ። ስለትህን አጉድዬ አውቃለሁ? የምበላው ባጣ እንኳ አሥራትና መባህን ነክቼ አውቃለሁ? ውለታ አታውቅም? አምላክ አይደለህም ተንደርድረህ ከሰው ልታንስ ነው? ምነው እኔን እንዳሻህ ብታደርገኝ? ምነው ልጆቼን ብትተውልኝ?” አልኩት። ሞኝ፣ የሞኝ ዘር አይደለሁ? ...የሰማኝ መሰለኝ። “አይዞህ ያለኝ መሰለኝ። “ይቅርታህን! የዛሬን ብቻ እለፈኝ ትቼሃለሁ” ያለኝ መሰለኝ። “ታርቀናል” ብዬ እንባዬን ጠርጌ ተነሣሁ። ቤት ስደርስ ያቺ ወረግቡ ሚስቴ ስታምጥ ደረስኩ። ቀበቶዬን አላልቼ የምትሰጥም አንተ፤ የምትነሣም አንተ ተመስገን!” አልሁት። ክፋቱን ረሳሁለት። ሚስቴ ምጥዋ ሳይጠና ተገላገለች። ቆንጅዬ ወንድ ልጅ በጨርቅ ጠቅልለው አሳቀፉኝ። ሳይደግስ አይጣላም!” ይሉ የለ የእኛ ሀገር ሰዎች? ...ደጋጎቹ። “መከራዬን አይተሃልና ኀዘኔን በሳቅ፣ ለቅሶዬን በደስታ ቀይረሃልና” ስል ስሙን ካሣ አልኩት። የካሠኝ መስሎኝ! አይ ደንቆሮ፣ የደንቆሮ ዘር ...ቶሎ አይነቃም እኮ።

     ያዋለደችው ሴት በደስታ የምሆነውን ሲያሳጣኝ ፊቷን ጨምታ ስታየኝ ጠረጠርኩና ጨርቁን ገለጥሁት። በእጆቹ በእግሮቹም ላይ ስድስት ስድስት ጣቶች አሉ። ስድስተኛ ሆነው የበቀሉት እንደሌሎቹ ጠንካራ ስላልሆኑ ወዲያና ወዲህ ተንከርፍፈዋል። ደነገጥሁ። ከማዘን ማበድ ቀረበኝ። ጣቱ ስድስት መሆኑ አይደለም፤ ነገረ-ሥራው ገርሞኝ እንጂ። የታላቁን አራት ጣት ነሳኸኝ ብዬ “ምነው?” ስላልኩት ካሣ ላይ መመለሱ ነው? ይሄ ቀልድ እንጂ ሌላ ምን ይሆናል? ድርቅ በጎርፍ ይካሣል? ሥርጉዳት በእባጭ ይሣሳል? ኧረ እንዲህም አድርጎ ቀልድ የትም የለ!

     ሽማግሌው የግራ ጆሯቸውን፤ ከፊቶች አንዱን እያከኩ ተነሡ።

     “እንግዲህ ሰማንህ 'ዕድሉ'። ለሰሚ የቸገረ ነገር ነውና የሸንጎውን ሐሳብ አድምጠን ፍርዱን ለዋናው ዳኛ እንሰጣለን። 
ወደ ሸንጎው ዞረው  ፈጣሪና መጥረቢያ አጥፍተዋል። ፍርድ ይገባቸዋል? የምትል እጅህን አውጣ ተብለሃል!”

           ይቀጥላል.........
    @Mahder_Kasahun🦋
;
የተሰላቸ ስሜት ይሰማኛል አዲስ ነገር ማጣት: ከደስታ መራቅ..
ከሰዎች ጋር ማውራት መሳቅ መጫወት እነዚ እኔጋ አለመኖራቸው ስልቹ አድርጎኛል..ራሴን መሸወድ ላይም የተካንኩ እንድሆንኩ ታዝቢያው.....

ከጠፋችው ኪያብ🍂
2024/05/21 07:51:08
Back to Top
HTML Embed Code: