Telegram Web Link
ለሶስተኛ (PhD) ዲግሪ ትምህርት ፈላጊዎች በሙሉ
======================== ሐምሌ 14 ቀን 2013 ዓ.ም
ለሶስተኛ (PhD) ዲግሪ ትምህርት ፈላጊዎች በሙሉ
የባሕር ዳር ዩኒቨርስቲ በሳይንስና ከፍተኛ ሚኒስቴር በተነደፈዉ አገር በቀል ዲግሪ የትብብር ፕሮግራም በመደበኛ ፕሮግራም በ30 የተለያዩ የ3ኛ ዲግሪ ትምህርት መስኮች ተማሪዎችን ተቀብሎ ማሰልጠን ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም በተጠቀሱት የ3ኛ ዲግሪ የትምህርት መስኮች መማር የምትፈልጉ እስከ ነሐሴ 17/2013 ዓ/ም ድረስ በሚከተለዉ ድረ ገጽ ኦን ላይን (Online) ማመልከት የምትችሉ መሆኑን እንገልጻለን ፡፡ https://www.bdu.edu.et/hcppreg/
ማሳሰቢያ
1. የፈተና ቀን ነሐሴ 26/2013 ይሆናል
2. ለማመልከት የምትልኳቸው ማንኛውም ዶክመንቶች በጥራት የሚነበቡ መሆን አለባቸው
3. ኦፊሻል ትራንስክርቢት ከነሐሴ 25/2013 በፊት መድረስ አለበት
4. ኦፊሻሉ ያልደረሰለት አመልካች ለመግቢያ ፈተና አይቀመጥም
5. ኦፊሻል የምትልኩት በፖስታ ሳጥን ቁጥር 79 ነው
6. የማመልከቻ ክፍያ ብር 200 ሲሆን በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ አካውንት ቁጥር
1. 1000013094563 ለባሕር ዳር ቴክኖሎጂ ኢንስትቲዩት ትምህርት ዘርፎች
2. 1000096185007 ለኢትዮጵያ ቴክስታይልና ፋሽን ቴክኖሎጂ ኢንስትቲዩት ትምህርት ዘርፎች
3. 1000013099522 ለሌሎች ኮሌጆች ትምህርት ዘርፎች
ገቢ ማድረግና ደረሰኙን በድረ ገጹ መላክ ያስፈልጋል፡፡
ጀማሪ ንግዶችን ከኢንቨስተሮች ጋር ለማገናኘት "የጋራ" የተሰኘ ፖርታል ተዘጋጀ

የሥራ ዕድል ፈጠራ ኮሚሽን ከማስተርካርድ ፋውንዴሽን እና ፒያሳ ኮሚኒኬሽን ጋር በመተባበር ጀማሪ ንግዶችን ከኢንቨስተሮች ጋር ለማገናኘት አገር አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ "የጋራ" የተባለ ፖርታል አዘጋጀ ።

"የጋራ" ፖርታል ሥነ ጥበብን፣ ቴክኖሎጂን እንዲሁም ከፍተኛ ተነሳሽነት ያለውን የወጣት ኃብት በመጠቀም የፋይናንስ አማራጭ አገልግሎትን ለማቅረብ ተልዕኮ ያለው ነው።

የሥራ ዕድል ፈጠራ ኮሚሽን የግሉን ዘርፍ ልማት ለመደገፍ የፋይናንስ ዘዴዎችን ለይቶ ማወቅና ጥቅም ላይ እንዲውል የማስተባበር ሥራዎችን የሚሠራ ሲሆን ይህንንም ከግሉ ዘርፍ ጋር በማስተሳሰር ለሥራ ፈጣሪዎች ማነቆ የሆነውን የፋይናንስ አቅርቦት ችግር የመፍትሔ ኃሳቦችን ያቀርባል።

በማስተርካርድ ፋውንዴሽን የገንዘብ ድጋፍ የተደረገለት ይህ ፕሮጀክት ሥራ ፈጣሪዎችን ለመርዳት ሁሉንም የሥራ ሥነ ምህዳራዊ ባለድርሻዎች የሚያገናኝና የኢንቨስትመንት ልምድን ለማሳደግ መሠረት የሚጥል ነው።

በዚህ ፖርታል ጀማሪ ንግዶች ስለራሳቸው መግለጫዎችን በመስጠት ለባለሀብቶች ራሳቸውን ያስተዋውቃሉ ፤ ባለሀብቶችም ለአጋርነት የሚፈልጓቸውን ጀማሪ ሥራ ፈጣሪዎችን እንዲመርጡ ያስችላል።

በፖርታሉ ውስጥ ለመመዝገብ ምንም አይነት ክፍያ የማይጠየቅ ሲሆን፣ የንግድ ኃሳቦች ወይም የተደራጀ ኢንተርፕራይዝ ያላቸው ወጣቶች www.yegara.org ላይ በመግባት የሚጠየቁ መረጃዎችን ሞልተው ይልካሉ።

ከዚያም በኢሜል ማረጋገጫ በሚላክላቸው መሰረት አስፈላጊ ሰነዶችን አዘጋጅተው በመመለስ መመዝገብ ይችላሉ። ኢንቬስተሮችም በተመሳሳይ ሁኔታ ተመዝግበው አባል ይሆናሉ።

መረጃው የሥራ ዕድል ፈጠራ ኮሚሽን ነው።
ክፍት የሥራ ቦታ ማስታወቂያ

ማስታወቂያው የወጣበት ቀን ነሐሴ 11 ቀን 2013 ዓ.ም

Dire Dawa University
ተፈላጊ የሰው ኃይል ብዛት :
116 - ቦታዎች በ0አመት

መረጃውን #Share /ሸር/ በማድረግ ለሌሎችም በስራ ፍለጋ ለሚንከራተቱ እና የተሻለ ስራ ለሚፈልጉ ወገኖቻችን እናካፍል። መልካምነት ለራስ ብቻ ሳይሆን ለሌሎችም ማሰብ ነው።

@jobcome
2025/07/08 11:33:43
Back to Top
HTML Embed Code: