Telegram Web Link
Audio
#እመቤታችን #መድኃኒት #ስትባል


🎥ዲያቆን ያረጋል አበጋዝ


✝️ #የእስራኤልም #ልጆች ወደ #እግዚአብሔር ጮኹ #እግዚአብሔርም #ብንያማዊውን የጌራን ልጅ ናዖድን ግራኙን ሰው አዳኝ #አስነሣላቸው #የእስራኤልም ልጆች በእርሱ እጅ ወደ ሞዓብ ንጉሥ ወደ #ዔግሎም ግብር ላኩ።

*♥️ #ቤዛነት


3 ✝️እኔ #የእስራኤል #ቅዱስ አምላክህ #እግዚአብሔር #መድኃኒትህ ነኝ #ግብጽን #ለአንተ ቤዛ አድርጌ፥ #ኢትዮጵያንና ሳባንም ለአንተ ፋንታ ሰጥቻለሁ።*

3 #For I am the #Lord thy God, the #Holy #One of #Israel, thy Saviour: I gave Egypt for thy #ransom, Ethiopia and Seba for thee.



@KIRSTOSIYESUS
"የተወለደው የአይሁድ ንጉሥ ወዴት ነው?" የሚለውን ጽሑፍ ምክንያት አድርጋችሁ ብዙዎቻችሁ ብዙ መልእክት ልካችሁልኛል::

መልእክቶቻችሁ አደፋፍረውኝ ለዛሬ ማታ ይህንን ሞክረኛ (challenge) ከፍቻለሁ::

የዛሬዋን ምሽት የት ሊያሳልፉ አስበዋል?

የተወለደው ክርስቶስ ነው:: ልደቱም የጌታ ነው::
ሕፃኑና እናቱ በሌሉበት ቦታ ማሳለፍ ትልቅ ጥፋት ነው::

የተወለደውን ሕፃን ከብበው በትንፋሻቸው ካሞቁት እንስሳት እኔና አንተ እንዴት እናንሳለን? በሥራ ላይ ያላችሁ ዛሬ ማታ እንደ እረኞቹ በጎቻችሁን ትታችሁ ወደ ተወለደው ሕፃን ገስግሱ:: ሰውና መላእክት አብረው በዘመሩበት ሌሊት ስትዘፍን አትደሩ::
አምላክና ሰው አንድ በሆኑበት ቀን ነፍስና ሥጋችሁን በሁለት ፈቃዶች ስትለዩ አትደሩ::

ባለ ሥልጣኖች በዚህች ሌሊት ቤተ መንግሥት ውስጥ ምንም አትሠሩም:: ሰብአ ሰገልን ሆናችሁ አሳልፉ:: ለተወለደው ሕፃን ስትዘምሩ እደሩ::
በሥራ ቦታ ላይ ያላችሁ ሁሉ ከእረኞቹ ጋር በሜዳችሁ የመላእክትን ዝማሬ ዘምሩ::

በዚህ ቻሌንጅ ሁለት ነገር እንድናደርግ ተጋብዘናል :-

Challenge 1 ዛሬ ማታ የት ሊያሳልፉ አስበዋል? ከቻሉ ኮሜንት ላይ ይጻፉ

Challenge 2
በብርድ ወራት በከብቶች ግርግም የተወለደው ሕፃን ምንኛ ሊበርደው እንደሚችል አስቡት? ድንግል ማርያም በጨርቅ የጠቀለለችውና የከለለችው ድንቅ ሕፃን የተወለደው እንስሳት አዝነው ያሞቁት በብርዳማ ሌሊት ነበር::

የሰሞኑን ብርድ መቼም እያያችሁት ነው:: ደራርበን ወጥተንም እንዴት እንደሚያንገበግብ ግልጽ ነው:: በዚህ የብርድ ወቅት ሌሊቱን ሙሉ ደጅ የሚያድሩ የጎዳና አዳሪዎች ብዙ ናቸው:: መንገድ ላይ ወልደው ማደሪያ ስላጡ መንገድ ላይ የተኙ እናቶች ዛሬ አሉ::

እነሱ ብርድ ላይ ተኝተው እኛ ስለተወለደው ሕፃን በዓል ብናከብር አያምርብንም::

ይህንን የምታነቡ ሁሉ ዛሬ ማታ ወደ ቤተ ክርስቲያን ስትሔዱ ትርፍ ልብስ ይዛችሁ በደጅ ያገኛችሁትን አንድ ሰው አልብሱ:: የተወለደውን ሕፃን ክርስቶስ እንዳለበሳችሁት ይቆጠራል::

ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ ስለ ዛሬዋ ምሽት እንዲህ ይላል :-

‹‹ይህች ምሽት ንጹሕ የሆነውና እኛን ሊያነጻን የመጣው (አምላክ) የተገለጠባት ንጽሕት ምሽት ናት፡፡

ጆሮአችን ንጹሕ ይሁን ፤ ዓይኖቻችንም ወደ ንጹሕ ነገር ይመልከቱ ፤ የልባችን ስሜት ቅዱስ ይሁን! ንግግራችንም አክብሮትን ይሞላ!

ይህች ምሽት የዕርቅ ምሽት ናት ፤ ስለዚህ ማንም ሰው ወንድሙን ተቆጥቶ እንዳያስቀይም!

ይህች ምሽት ለዓለም ሁሉ ሰላምን ያስገኘች ምሽት ስለሆነች ማንም ሰው አይሸበርባት፡፡
ይህች ምሽት የደግነት ምሽት ስለሆነች ማንም ሰው ክፉ አይሁን!
ይህች ምሽት የትሕትና ምሽት ናትና ማንም ሰው
እንዳይታበይባት!
ይህች ምሽት የደስታችን ቀን ስለሆነች የበደሉንን
አንበቀልባት!

የበጎ ፈቃድ ቀን ናትና የጭካኔ ቀን አናድርጋት!
የጸጥታ ቀን ናትና በቁጣ የምንነድባት ቀን አናድርጋት!

ዛሬ እግዚአብሔር ወደ ኃጢአተኞች የመጣበት ቀን ነው ፤ ስለዚህ ጻድቅ ሰው በኃጢአተኞች ላይ አይኩራባቸው!

ዛሬ እጅግ ባለጠጋ የሆነው አምላክ ስለ እኛ ደሃ የሆነበት ቀን ነው፤ ስለዚህ ሀብታም ሰው ድሆችን ወደ ገበታው ይጥራቸው፡፡

ዛሬ ያልጠየቅነውን ሥጦታ የተቀበልንበት ዕለት ነው፡፡ ስለዚህ እጆቻቸውን ዘርግተው እየጮኹ ለሚለምኑን ሰዎች የእርዳታ እጃችንን እንዘርጋ!

የዛሬዋ ዕለት ለጸሎቶቻችን የሰማያትን በር ከፍታልናለች ፤ እኛም ይቅርታን ለሚጠይቁን ሰዎች በራችንን እንክፈት!

ዛሬ አምላክ የሰውነትን ማኅተም በራሱ ላይ አተመ ፤ ሰውም የአምላክነትን ማኅተም ተጎናጸፈ!››

#ዛሬ_ማታ_የት_ነኝ
#የተወለደው_ንጉሥ_ወዴት_ነው
#የት_ቤተ_ክርስቲያን_ነን
#አንድ_ሰው_እናልብስ

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
ታኅሣሥ 28 2015 ዓ.ም.
+ የሕዝብ ቆጠራ መዝገብ +

ጌታችን በቤተልሔም ለመወለዱ ምክንያት የሆነው ለሕዝብ ቆጠራ ሲሉ ወደ ይሁዳ አውራጃ በመምጣታቸው ነበር:: ለቆጠራ መጥተው ከመቆጠራቸው በፊት ጌታችን ተወለደ:: ወደ ናዝሬት ከመመለሳቸው በፊት ግን ሁለት ሆነው ሊቆጠሩ የመጡበትን የሕዝብ ቆጠራ ሦስት ሆነው አድርገው ተቆጥረዋል::

እባካችሁ ያንን የቆጠራ መዝገብ ያለበትን ቦታ የምታውቁ የሮማውያን ታሪክ መርማሪዎች ካላችሁ ብትነግሩኝ ደስ ይለኛል:: ደግሞ የሕዝብ ቆጠራ መዝገብ ምን ያደርግልሃል? ካላችሁ መዝገቡ ይገኝ እንጂ እኔ ግን የምፈልገው አንድ ስም አለ:: ከብዙ የይሁዳ ተወላጆች ስም መካከል ሰሎሜ ዮሴፍ ማርያም ከሚሉ ስሞች አጠገብ አንድ ዓለም የዳነበት ስም በሕዝብ ቆጠራው መዝገብ ሥር ተጽፎአል::

ጉልበት ሁሉ የሚሰግድለት ስም : ከሰማይ በታች እንድንበት ዘንድ የተሠጠን ስም : ከስም በላይ የሆነ ስም : ቅዱስ ገብርኤል በክብር ይዞት የወረደና ለድንግሊቱ የነገራት ስም : አጋንንት ሲሰሙት የሚንቀጠቀጡለት ስም : ሙታንን የሚያስነሣ ድውያንን የሚፈውስ ስም በዚያ የሕዝብ ቆጠራ መዝገብ ላይ እንደዋዛ እንዲህ ተብሎ ተጽፎአል::

ኢየሱስ ✍🏽

አንተ የሕዝብ ቆጠራ ሠራተኛ ሆይ ይህንን ስም እዚያ መዝገብ ላይ ስትጽፈው ብዕርህ አልተሰበረም ወይ? ቀለሙስ አልሸሸም ወይ? እጆችህስ አልተንቀጠቀጡም ወይ?

ጌታችን በዚያ መዝገብ ላይ ተጻፈ:: በዚያ መዝገብ ከጌታ ጋር የተጻፉት ንጽሕት ድንግልና ጻድቁ ዮሴፍ ብቻ አልነበሩም:: በዚያች ግዛት ያሉ ሰዎች ሁሉ አብረው ተጽፈዋል:: ጥሩ ሰዎች ክፉ ሰዎች ወንጀለኞች ነፍሰ ገዳዮች ሰካራሞች አመንዝሮች በዚያ መዝገብ ላይ ስማቸው ተጽፎአል::

ክርስቶስም ገና ከመወለዱ ከኃጢአተኞች ጋር ተቆጠረ:: በሕይወት ዘመኑ የኃጢአተኞች ወዳጅ የሚል ቅጽል ስም የወጣለት ጌታ በዕለተ አርብም በግራና ቀኙ ከወንበዴዎች ጋር አብሮ የተሰቀለው ጌታ አሁንም በልደቱ ጊዜ "ከዓመፀኞች ጋር ተቆጠረ" (ኢሳ 53:12)

እኛን ከቅዱሳን ጋር ሊደምረን እሱ ከኃጢአተኞች ጋር ተቆጠረ:: እኛን "ስማችሁ በሰማይ ስለተጻፈ ደስ ይበላችሁ" ለማለት እርሱ በምድር መዝገብ ላይ ተጻፈ::

ወዳጄ ክርስቶስ ስለ አንተ ሲል ከኃጢአተኞች ጋር ተቆጠረ:: አንተ ስለ እርሱ ከንጹሐን ጋር ተቆጠርለት:: በተወለደበት ጊዜ ከሰካራሞችና ዘራፊዎች ስም ዝርዝር ጋር ለአንተ ሲል አብሮ ተቆጠረ:: እስቲ አንተ ልደቱን አስበህ ከሚሰክሩት ሰዎች ስም ዝርዝር ውስጥ ውጣ:: ከዘራፊዎችም መካከል ተለይ:: ክርስቶስ ወደ አንድ ነገር የሚገባው የሚገቡትን ሊያወጣ ነው:: ወደ ሞት የገባው ሙታንን ሊያወጣ ነው:: ወደ ሲኦል የወረደው ነፍሳትን ከሲኦል ሊያወጣ ነው:: ወደ ሮማውያን የሕዝብ ቆጠራ የኃጢአተኞች መዝገብ ስሙ የገባውም የሁላችንን በደል ተሸክሞ እኛን ከዚያ መዝገብ ሊያስወጣን ነው::

"ስማችሁ ግን በሰማያት ሰለ ተጻፈ ደስ ይበላችሁ"
ሉቃ 10:20

ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
ታኅሣሥ 28 2013 ዓ.ም.

ለተጨነቀች ነፍስ ዕረፍት የሆነው የእግዚአብሔር ቃል ለሁሉ ይዳረስ ዘንድ :: እኔም ለእናንተ ከሰበክሁ በኁዋላ የተጣልሁ እንዳልሆን አጥብቃችሁ ስለ እኔ ጸልዩልኝ!
በኮሜንት መስጫው ሥር "ለሚሰሙት ጸጋን ይሰጥ ዘንድ፥ እንደሚያስፈልግ ለማነጽ የሚጠቅም ማናቸውም በጎ ቃል እንጂ ክፉ ቃል ከአፋችሁ ከቶ አይውጣ" (ኤፌ 4:29)
ሰማይን ያለ ባላ ምድርን ያለ ካስማ ያጸና፣ ብቻውን ታላላቅ ነገሮችን ያደረገ፣ በማኅጸን ደም አርግቶ አጥንት ሰክቶ ጽንስ የሚፈጥር ሠዓሌ ሕፃናት ዛሬ ሥጋ ማርያምን መሰወሪያው አድርጎ ወደ ፈጠራት ምድር በትሕትና ገባ። አዳምን የሚናገር የሠላሳ ዓመት ጎልማሳ አድርጎ የፈጠረው ጌታ ዛሬ አፍ ያልፈታ የአንድ ቀን ልጅ ሆኖ ከእናቱን ወተት እየለመነ እንደ ሕፃናት ሲያለቅስ ታየ። ስፍራ የማይወስኑት አምላክ ወደ ዓለም ሲገባ ስፍራ ስላልተገኘለት በከብቶች ማደሪያ በረት ተወልዶ እንስሳት ትንፋሽ ሲገብሩለት አደረ። ሲያሟሙቁት።

የእግዚአብሔር አብ ቸርነቱ ምን ይደንቅ?! ቀድሞ የፈጠረው አዳም በበደል ቢወድቅበት እርሱን አጥፍቶ በምትኩ አዲስ ሰው መፍጠር እየቻለ፣ ነገር ግን ለወደቀ ባሪያው ምትክ የሌለው አንድያ ልጁን ሞቶ ተሰቅሎ እንዲያድነው ወደ ዓለም ላከ። ስለ ባሪያ ፈንታ ልጅን ቤዛ አድርጎ የሚሰጥ ከአብ በቀር ማን አለ? አብርሃም ልጁን ሳያቅማማ ሊሠዋ የተነሣው ፈጥሮ ላኖረው ከሁሉ ለሚበልጥበት አምላኩ ነበር። አብ ግን ልጁን የሰጠው በኃጢአት ምክንያት ጠላቶቹ ለነበርነው ለእኛ ነው።

ይህ ሁሉ የሆነው ስለ ሰው ቢሆንም ሰው ግን የተደረገለትን ቸርነት አላወቀም። አምላክ የገባውን "የአድንኃለሁ" ቃል ጠብቆ ወደ ምድር ሲወርድ፣ ሰው ግን "የሚመጣውን አምላክ" ረስቶ የሚወለድበት እንኳ ስፍራ አሳጣው። መላእክት መጥተው እስኪያነቁት ሰው በሜዳ በዋሻ አንቀላፋ። በዚያን ጊዜ የተኙት እረኞችስ መላእክት ቀስቅሰዋቸው ተነሡ። እኔ ግን እስከ አሁን ተኝቻለሁ። ኃጢአት እያባከነኝ አንተ ከተወለድህበት ርቄ ከሜዳ ቀርቻለሁ። መልአክህን ልከህ በምሥራች ቃል የምትቀሰቅሰኝ መቼ ነው? ሕይወቴ መወለድህን እንዳልሰማ ሰው ሆኗል። የበደል እንቅልፍ ከብዶባቸው ዓይኖቼ ማዳንህን ማየት ተስኗቸዋል። ቀስቅሰኝና ልደትህን እንደ አዲስ ተወልጄ ላክብር? አንቃኝና እስከ ቤተልሔም ሄጄ ለእኔ ስትል የሆንከውን አይቼ እያመሰገንኹ ልመለስ?!

ዲያቆን አቤል ካሳሁን
[email protected]
ታኅሣሥ 28/ 2015 ዓ.ም.

Church of Nativity
ቤተልሔም
(ፍልስጥኤም)

ድረ ገጹን ይጎብኙ
https://dnabel.com

ቴሌግራም
https://www.tg-me.com/Dnabel
*🌹 #የጌና #ማሕሌት* #በረከት👏🏿👏🏿👏🏿 *እንኴን አደረሳችሁ አደረሰን #በግርግም #የተወለደው አምላካችን #በልቦናችን #እንዲወለድ ልቦናችንን ለጌታ የተመቸ ያድርግልን*
አስተያየት

ግን.. ግን.. በየከተማው አደባባይና በየመንገዱ የሚደረገው የጎዳና ላይ ስብከት ከመጠን ያለፈ፣ ከተገቢነትም የተሻገረ፣ ከትክክለኛነትም በተቃራኒ እየተጓዘ አይመስላችሁም..? ማንም ሰው እምነቱን በፈለገ መንገድ የመግለፅና ለሌላው የማስተዋወቅ መብት እንዳለው አምናለሁ። ይህ ግን ቆመንለታል ከሚሉት ዓላማ፣ ከሌላው ወገን መብትና ክብር እንዲሁም ከአካባቢ ጸጥታ አንጻር መገምገም ይኖርበታል። አሊያ ዘርፈ ብዙ ችግር እንዳያሰከትል ያሠጋል።

የጎዳና ላይ ሰባኪዎች ዓላማቸው ኢየሱስን መስበክ፣ ለሌሎች ወገኖችም የሕይወትን መንገድ ማመላከት ከሆነ በቅድሚያ ሰው እንዲሰማቸው ማድረግ ነበር የሚጠበቅባቸው። ተግባራቸው ግን ተቃራኒውን ነው የሚመስለው። ጥረታቸው በጎዳና ከሚያልፈው የራሳቸው ወገን አሜንታ ፍለጋ አሊያም በአለቆቻቸው እንደ ጀግና ለመቆጠር ከሆነ ከአዳራሾቻቸው መውጣት አያስፈልጋቸውም። አቢይ ምክንያታቸው ሌላው ሰው ላይ መድረስ ከሆነ ግን በትንሹ አክብሮትና የለዘብታ ቃል መገለጫቸው መሆን አለበት። እንደሚታወቀው ብዙው ሰው እርጋታ የተሞላበት የፍቅር ቃል እንጂ ጩኸት አይሰማም። ጯኺዎች ራሳቸውን እንደ ወንጌል ሰባኪ ቢቆጥሩም አላፊ አግዳሚውን እያደነቆሩት እንጂ እየሰበኩት እንዳልሆነ ቢያውቁት መልካም ነው። ለዚህም አነስተኛ ጥናት ቢሠሩ ደግ ነበር። በእርግጥ እዚያ አካባቢ በስሜት እንጂ በጥናት የመመራት ነገር የሚታሰብ አይደለም።

ብዙ ሰው በተግባራቸው ከመበሳጨቱ የተነሳ የሚጠሩትን ክቡር ስም እንዳያሰድቡ ይጠነቀቁ ዘንድ የሚያሳስባቸው ቢኖር እንዴት ደግ ነበር..? የአንዳንዶቹ ሰባኪያን ሁኔታ ደግሞ ይገርማል። ወንጌል በእልህ ይሰበክ ይመስል እየተንቀጠቀጡ ወጪ ወራጁ ላይ ሲጮሁ የውስጣቸውን የሰላም እጦት ሕዝቡ ላይ ለማራገፍ የሚጥሩ ነው የሚመስሉት። በቀደምለት ሜክሲኮ ጋር በተመሳሳይ እልህ ሲሰብክ የነበረ ወጣት ከጠቀስኩት ነገሮች ሁሉ አልፎ ሄዶ ፀብ ጫሪ ጩኸት ሲያሰማ ነበር። ከጩኸቱ ውስጥ "... ኦርቶዶክስ፣ ካቶሊክ፣ ፕሮቴስታንት... የትኛውም ሃይማኖት አያድንም፤ የሚያድነው ኢየሱስ ነው... በሃይማኖት ገመድ የተተበተባችሁ ስሙ.. ሃይማኖታችሁ አያድናችሁም" የሚል ይገኝበታል። ከንግግሩ ጋር የድምፁ መጠንና የሚታይበት እልህ የጥላቻውን መጠን ያሳያል። ብዙ መንገደኞች እየተሳደቡ፣ ሌሎችም መሰላቸታቸውን በምልክት እየገለጡ ሲያልፉ ነበር።

ይህ ድርጊት በዚሁ ከቀጠለ ሩቅ ባልሆኑ ቀናት ውስጥ የፀብና የአምባጓሮ መነሻ እንደሚሆን መገመት ስህተት አይሆንም። ስለሆነም የሚመለከተው አካል መፍትሄ ሊያበጅለት ይገባል። የተረጋጉና ጨዋ ፕሮቴስታንቶችን ስለዚህ ጉዳይ እንዲመክሩ ማሳሰብ ጠፍቶኝ አይደለም። ሆኖም ግን እንዳለመታደል ሆኖ በዚያ ክበብ ውስጥ ምክር ቀርቶ ውግዘት የሚገታው እንቅስቃሴ እንደሌለ የታወቀ በመሆኑ ነው ያለፍኩት። ይህን አስተያየት "የክርስቶስ ስም እንዳይነገር" የተሠጠ አድርጋችሁ የምትቆጥሩ ወፈፌ ጴንጤዎች ካላችሁ ግን መልሴ በክርስቶስ ኢየሱስ ሆኖ፥ በፍቅር የሚሠራ እምነትና ምሥክርነት እንጂ ጩኸት ወንጌል ሆኖ አያውቅም የሚል ነው። ካስፈለገም የአስቄዋ ልጆችን ድርጊትና ውጤት አስታውሳችኋለሁ። የጌታ የኢየሱስ ስም የተከበረው እነርሱ ስሙን እየጠሩ በመጮኻቸው ሳይሆን አጋንንት ያደረበት ሰው ስለዘለለባቸው፣ ቆስለውም ራቁታቸውን እስኪሸሹ ድረስ ስለበረታባቸውና ስላሸነፋቸው ነው (ሐዋ፡19፥14-17)። እናም በቃሉ ላይ መራቀቁን ትታችሁ ይሄን የዕብድ ድርጊት አስቁሙ አሊያም በልክ አርጉት..!።
Audio
እኛው እናቡካ እኛው እንጋግር


🎥መምህር ያረጋል አበጋዝ



አንዲት ቤተክርስትያን

✝️
#አንድ #ሲኖዶስ

♥️
#አንድ #ፓትርያርክ

*ማኅበረ ቅዱሳን የስብከት ወንጌል



@KIRSTOSIYESUS
Audio
የነነዌ ሰዎችን እንባ የተቀበለ አምላክ ይህንን እንባ አይቀበልምን*


🎥መምህር እዮብ ይመኑ



አንዲት
#ቤተክርስትያን

✝️አንድ
#ሲኖዶስ

♥️አንድ
#ፓትርያርክ

ማኅበረ ቅዱሳን ወቅታዊ ጉዳይ


@KIRSTOSIYESUS
ቀሚሴን አስወልቆ ሊደፍረኝ ነበር
Voice changer with effects - https://thevoicechanger.com
ፓሊሱ ቀሚሴን አስወልቆ ሊደፍረኝ ነበር

🎥አባ ገብረ ሚካኤል ፈንቴ♥️

⚖️አባታችን በሕግ አስከባሪ ነን ባሉ ግፈኞች የደረሰባቸው ግፍ



*አንዲት
#ቤተክርስትያን

*✝️አንድ
#ሲኖዶስ

*♥️አንድ
#ፓትርያርክ

ማኅበረ ቅዱሳን ወቅታዊ ጉዳይ አባቴ የኔ እንባ ይፍሰስ


@KIRSTOSIYESUS
2025/07/04 20:32:14
Back to Top
HTML Embed Code: