Telegram Web Link
እውን እስቲ አስተውል በህይወትህ ውስጥ በምታያቸውና በምታገኛቸው ነገሮች፣ ሰዎች ላንተ በሚሰጡህ ቦታ ልክ፣ በህይወት ያለፍክባቸው መንገዶች ልክ፣ በድክመቶችህና በስህተቶችህ ልክ፣ በህይወትና ኑሮህ በሚገጥሙ ሁኔታዎችና ክስተቶች ስለራስህ ማንነትና ስለህይወትህ በአእምሮህ ምታስበው ሃሳቦች ብቻ በህይወት እየባከኑ መሆኑን ልብ ብለዋል? በዚህም የተነሳ እርሶ ለራሶና ለህይወቶ የሚሰጦቸው ትሩጋሜና እሳቤዎች (Assumptions) አብዛኛው ውሸት መሆኑንስ ያውቃሉ? የነዚህን ነገሮች መንስኤ፣ መፍትሄና ይህን ሰብሮ በመውጣት ወደፊት ለመራመድ መደረግ ያለባቸውንና እርሶ በህይወቶና በነጻነቶ ውስጥ ለመኖር የሚያግዞትን እውቀት በቅርቡ ቀን...
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
እራሳችንን ማግኘትና ወደ እራሳችን ማንነት በመመለስ በህይወት ወደፊት መራመድ ያስፈልገናል
በውስጥህ ሰው የመሆንህ አቅም አለህ። ይህ በእርገጥ እውነት ነው! ነገር ግን በራሶ በመመራመር እውነታውን በራሶ ማወቅና መረዳት ያስፈልጋል። እራሶ በራሶ ላይ የሚሰለጥኑበት እና የሚያግዞትን እውቀትና ትምህርታዊ መረጃዎችን በኛ በኩል ይዘንሎት እንመጣለን። በቅርብ ቀን ይጠብቁን...
የምንኖርበትን ሁኔታና አካባቢያችንን ካልወደድነው እኛው እራሳችን ነን መለወጥና እንዲኖረን የምንፈልገውን ሁኔታና አካባቢያችንን መቅረጽ ያለብን። ይሁንና የማንወደውን ሁኔታና አከባቢያችንን ከጎን ትተን ትኩረታችንና ሃሳባችንን የምንወደውና መቀረጽ የምንፈልገውን አለም ለመቅረጽ ከመራመድ ይልቅ ያለንበት ሁኔታና አካባቢያችንን እንዲሁም የውጩ አለምን በማየትና በመመልከት ብቻ የምንኖር ከሆነ ግን የሃሳባችንን ትኩረትና የማንነታችንን ስሜት አጠቃላይ ህይወታችንንና የእኛን አለም ውጫዊ ሁኔታዎች ስለሚቆጣጠሩት ውጫዊ ሁኔታዎችና አከባቢያችን የእኛን ህይወትና አለም ይቀርጻሉ። የዚህን ሂደት አመለካከትና አስተሳሰብ በመለወጥ በራሶና በህይወቶ ለውጥ ማምጣት ለይ ለመስራት አጋዠ እውቀትና መረጃዎች ካስፈለጎ በቅርብ ቀን...
ለውጥ ለማምጣት አንዴ ወደ ተግባር ከገቡ ቡሆላ ያለማቆረጥ Motivation እና በፍላጎት/Desire ውስጥ መቆየት ባለንበት ቆመን እንድንቀርና ቀድሞ የነበርንበት ማንነት ይበልጥ እንዲያገረሽብን የሚያረግ መሆኑን ጥናቶች ያመላክታሉ። እርሶ ይህ አይነት ሁኔታ ደርሶቦታል? ይህንን ሃሳብስ ይጋራሉ? የእርሶ ምላሽ የቱ ነው? ምላሾን ያጋሩን።
Anonymous Poll
40%
አዎ ይህንን ሃሳብ እውነታ እኔም እጋራለው።
60%
አይ እኔ ይህን ሃሳብ እቃወማለው።
በራሳችን ማንነትና በስብዕናችን ላይ ለውጥ ማምጣት እና በህይወታችንና በኑሮዎችን ውስጥ ማደግ አለብን። ምንም እንኮን በዙሪያችን ያለንበት ሁኔታና ደረጃ፣ የማሃበራዊና ኢኮኖሚያዊ ተግዳሮቶቻችን የቱንም ያህል ቢሆኑም በነዚህን ውጫዊ ሁኔታዎች በመዋጥ ያለንባቸው ሁኔታዎች የኛን ማንነትና ህይወት እንዲቀርጽና እንዲቆጣጠሩን ከመፍቀድ ይልቅ ያለንበትን ሁኔታ፣ አካባቢያችንን፣ እና ዙሪያችንን መለወጥና መቅረጽ ያለብን እኛው እራሳችን ነን። ለዚህ ደግሞ ከምናያቸውና ከሚገጥሙን ውጫዊ ሁኔታዎች/ክስተቶች ሃሳባችንንና ስሜታችንን በመግዛት እና እራሳችንን በመቆጣጠር መለወጥ የምንፈልገውን ነገር ለመቅረጽና ለመፍጠር ወደ ፊት መራመድ ግድ ነው።
ሃሳባችንን በመግዛት ተግባራችንን ተቆጣጥረን እራሳችንን መምራት የሚያስችለንን የግንዛቤ እውቀት ማግኘትና መረዳት ማለት ያለማቆረጥ በየቀኑ ወደፊት በመራመድ መቅረጽና መፍጠር የምንፈልገውን የራሳችንን ማንነት እና በህይወት መድረስ የምንፈልገው ቦታ ላይ ለመድረስ የሚያስችለንን መንገድና አቅም ማግኘት ማለት ነው። ይህንን አጋዥ እውቀትና ትምህርታዊ ስልጠና በቅርብ ቀን...
በገዛ አእምሮዎ የሚያስቡት ሃሳቦች እራሶንና ማንነቶን ሲያጠቁ አስተውለዋል? ይህ ሃሳቦ በምትኩ ስሜቶን ሲቅጣጠሮትስ ልብ ብለዎል? በሚሰማዎት ስሜት ምክንያት ደግሞ መሆንና ማድረግ የሚፈልጉትን ነገሮች ለማድረግ የሚወስዱትን እርምጃዎችና ተግባሮች እየገደቦት እርሶ በልማድ የሚወስዶቸውን እርምጃዎችና ተግባሮች ስር ብቻ ማንነቶን ሲቆጣጠሮትስ አስተውሎዋል? የዚህን ጉዳይ ሂደት እንዴትና ለምን ይህ ይሆናል? እንዴት ነው የምንለውጠው ለሚለው ጥያቄዎች በሳይንሳዊ ጥናት ምርምር ጋር በጥልቀት በቅርብ ቀን...
ብዙ ሰዎች ትልቅ ነገር ለማድረግ ሲነሱ ግባችንን ከመጀመራችን በፊት ወይም በመጀመሪያዎ እርምጃ በምትገጥመን እንቅፋት ከመጀመራችን በፊት አስቀድመን እንሸነፋለን፡፡ ለምን? ምክንያቱም ቀድመን በሃሳብ ስለምንሸነፍ፡፡ በሰዎች አስተያየት በነገሮችና በሁኔታዎች ተነስተን በማይሆነውና በማይቻለው መንገድና ሀሳብ ተብሰልስለን መንገዳችንን ከመጀመራችን በፊት በሃሳብ ደክመን ትልቅ ማለም አድክሞንና አስንፎን እንዴት የሚለው ሃሳብ አስጨንቆን የያዝነውን የጀመርነውን እርግፍ አርገን ትተን የነበርንበት ቦታና ስፍራ ቆመን እንቀራለን፡፡ አይገርምም ግን? በሀሳብ ብቻ መሸነፍ፡፡ ሀሳብ ሀያል ሀይል ነው፡፡ ለውጤት ማሰብ ይማሩ።
ታላቅ ለውጥና እድገት የምታመጣው ዋነኛው ያለህ ትምህርት/ዲግሪና ዶክትሬት ሳይሆን በማንነትህ ውስጥ በምታደርጋቸው ድርጊቶችና ተግባሮችህ ነው። ስለዚህ ያለህን እውቀትና ትምህርት በተጨባጭ ለማውረድ አንተነትህ የተገነባበትንና ተግባሮችህን የሚመራው አእምሮህ አስቀድሞ የተቀረጸበትን ጽንሰ ሃሳብና ምስሎች በመለወጥ እራስህንና ማንነትህን መጠቀም ስትችል ብቻ ነው። ይህንን ሃሳብ ይጋራሉ? 1. አዎ፣ ግን እንዴት የሚለው ነው ዋናው ጥያቄ። 2. አልስማማም፣ ሁሉም በፎርማል ትም/ት የሚገኙ ናቸው።
በልጅነት አስተዳደጋችንና በህይወት እድገታችን ውስጥ በውስጣችን ስለራሳችንና ስለህይወት ያለንን አመላካከትና አስተሳሰብ በተለያዩ ሃሳቦችና ምስሎች፣ በሰዎችና በአከባቢያችን ሁኔታዎች በተቀረጽንባችው ጽንሰ ሃሳቦች ስር የማንነታችንና የህይወታችን እሳቤዎች (Assumptions) አጥር ውስጥ ተቀርጸናል። እናም እነዚህ የተቀረጽንባቸው ጽንሰ ሃሳቦችና ምስሎች አብዛኛዎቹ ለእኛ የማይረቡን እና የእኛ እውነተኛ ማንነት አልያም እኛ መሆናን ማድረግ የምንችለው አቅም ልክ ፈጽሞ አይደሉም። የአስተሳሰብ ለውጥ ለዘላቂ ለውጥና እድገት ሂደት የሚያግዞትን እውቀት በቅርብ ቀን...
አእምሮዎዊና ውስጣዊ አለማችንን ሃሳባችንን በመቆጣጠርና በመምራት ሰው በመሆናችን ብቻ ብቁ የመሆናችንን ውስጣዊ አቅም እና ተፈጥሮዋዊ እውነተኛ ማንነታችንን መልሰን በማግኘትና በመጠቀም ነው ታላላቅ ነገር ከእኛ ውስጥ ሊገኝ የሚችልበትና ታላቅ ለውጥ የምናገኝበት ብቸኛው አማራጭ። ይህንን ሃሳብ እርሶ ይጋራሉ? 1. አዎ ሙሉ ለሙሉ 2. ሃሳብ በመቆጣጠር ይህንን ያህል ነገር ሊገኝ አይችልም የማይመስል ነገር ነው። 3. አዎ በከፊል እጋራለው።
አብዛኛዎቹ ስለእኛነታችን ያለን አስተሳሰባችንና ምልከታችን እኛ የተቀረጽንባቸው በአእምሮዎችን የተመዘገቡ የመረጃዎች ስብስብ የሆኑ ጽንሰ ሃሳቦችና ምስሎች ናቸው እናም አብዛኛዎቹ ለእኛ የማይረቡን የውሸት የአእምሮ እሳቤዎች ብቻ ናቸው። በዛው ልክ ስለራሳችን የሚሰማን ስሜቶችና ልማዳዊ ተግባራችንም የዚሁ የተቀረጽንባቸው ጽንሰ ሃሳብ ውጤት ብቻ ናቸው።
2025/07/04 18:07:31
Back to Top
HTML Embed Code: