Telegram Web Link
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ሃሳቦንና ውስጣዊ ማንነቶን አእምሮዋዊ ህይወቶን በመለወጥ አለሞን ይለውጡ፡፡

ለእርሶ ለማይረባዎት ውስጦን ለሚያደማዎት ውስጦንና ስሜቶን ለሚረብሽና ለሚያቆሽሽ የእርሶን ማንነትና አቅም ጥያቄ ውስጥ ከሚከትቦትና እርሶንና ማንነቶን የሚያጎድፍ ሀሳቦችን በውስጦ አያብሰልስሉ፡፡ የእርሶን አለምና ህይወት ለምን ለነገሮች ለሁኔታዎችና ሌሎች ለሚናገሮት ነገሮች አሳልፈው ይሰጣሉ?

እርሶ ሰው በመሆኖ ብቻ ጥያቄ ውስጥ የማይገባ ብቁ ፍጥረት ነዎት፡፡ መሆንና ማድረግ መድረስ ከሚፈልጉት ለመድረስ እርሶን ሊያቆምና ሊገታ የሚችል አንድም የለም ከሃሳቦ በቀር! ሃሳቦን ይምረጡ!

ለውጤት እናስብ!
ሃሳቦን ወደ ውጤት ይለውጡ!
ለውጤት ማሰብ ይማሩ፡፡
ካሊድ ሰኢድ፤ በኢትዮጵያ የቦብ ፕሮክተር ስልጠና አሰልጣኝና አማካሪ
Kalid Proctor Gallagher Consultant
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ምን እያሰብክ ነው?

ሀሳቦን የመምረጥ አቅሞን ይጠቀሙ! እናም ማንነቶንና ስሜቶን ህይወቶንና ኑሮዎን ይለውጡ፡፡ ይህ ለእርሶ የተሰጦት ታላቅ ጸጋ እና እምቅ አቅሞ ነው፡፡ ደስ ሲል!!

ከምርጥ ሃሳብ ምርጥ ግዜን ለእርሶ፡፡ ድንቅ ቀን ይሁንሎ!

ለውጤት እናስብ!
ሃሳቦን ወደ ውጤት ይለውጡ!
ለውጤት ማሰብ ይማሩ፡፡
ካሊድ ሰኢድ፤ በኢትዮጵያ የቦብ ፕሮክተር ስልጠና አሰልጣኝና አማካሪ
Kalid Proctor Gallagher Consultant
አባይን ማን ገነባው?

ለዚህ ጥያቄ መልሳቹህ ምንድን ነው? የእኔን መልስ በቅድሚያ ልንገራቹህ፡፡ መልሴ “የሃሳብ ለውጥ” ነው፡፡

ለዘመናት አባይ የማይገነባበትን መንገዶችና ሁኔታዎች ስናብሰለስል እና ስንተነትን፣ ስንቆዝም፤ የአለም ፍትሃዊ አለመሆንን ስናዜም እና ስናማርር ከዘመናት ቆይታ ቡሆላ ሀሳብ ሲቀየር ስሜታችን ተቀየር፡፡ ስሜታችን ሲቀየር እምነታችን እና ድርጊታችን ተቀየረ፡፡ ድርጊታችን ሲቀየር ውጤታችን ተቀየር፡፡

እናም ዛሬ በአባይ ላይ ያለን ሃሳባችን ተለውጦ በአባይ ላይ ያለን አቆምና ባህሪያችን ተግባራችን እርምጃችን እና ፉከራችን ተቀይሮ እዚህ ደርሶዋል፡፡

አለምና ሃገራት የሚለወጡት ሃሳባቸው ሲለወጥ ብቻ ነው!

እስቲ የእርሶን ምላሽ ኮሜንት ላየ ያጋሩን ወይስ በኔ ሃሳብ ይስማማሉ?

ለውጤት እናስብ!
ሃሳቦን ወደ ውጤት ይለውጡ!
ለውጤት ማሰብ ይማሩ፡፡
ካሊድ ሰኢድ፤ በኢትዮጵያ የቦብ ፕሮክተር ስልጠና አሰልጣኝና አማካሪ

Kalid Proctor Gallagher Consultant
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የሰው ልጅ የሃሳቡ ድምር ውጤት ነው።

ኤመርሰን “የሁሉም ሰው ቁልፉ ሃሳቡ ነው” ይላል። እናም አንተ በሰዎች ሀሳብና አስተያየት በሁኔታዎች ተገዚ መሆን አቁመህ በራስህ በውስጥህ ሀሳብ መኖር እስካልጀመርክ ድረስ አንተ ሁሌም የነገሮች የሰዎች ሀሳብና አስተያየቶች ባርያ ነው የምትሆነው።

ታላቅ ሰው ከታላቅ ሀሳብ ነው የሚወለደው መልካም ሀሳብ፣ መልካም ቀን ይሁንሎ!

ለውጤት እናስብ!
ሃሳቦን ወደ ውጤት ይለውጡ!
ለውጤት ማሰብ ይማሩ፡፡
ካሊድ ሰኢድ፤ በኢትዮጵያ የቦብ ፕሮክተር ስልጠና አሰልጣኝና አማካሪ
Kalid Proctor Gallagher Consultant
ሰላም የሚገኘው በሰላማዊ ሃሳብ ብቻ ነው።

በውጭ የምታየው ምንም ይሁን ምን እርሶ ሀይል እስካልሆኑት ድረስ ክስተት ሆኖ ይቀራለ። እርሶ በአእምሮዎና በሃሳብ ዉስጥ የሚገኙ የሃይል ማእከል ኖት። በዚህ የሀይል ማእከል ውስጥ ሆነው የሚያብሰለስሉት ሀሳብ ምንም ይሁን ምን ስሜቶን ይቆጣጠራል እርሶን ድርጊቶን በመግዛት የማይታየው ውስጣዊ አለሞ ወደ መሬት ይወርድና ወደ ሚታየው አለማዊ ክስተት ይፈጸማለ። ይህ የተፈጥሮ ህግ ነወ!

እኔ አንተ አንቺ ሁላችንም ሰላም እድገት ብልጽግና ባገራችን ሲሰፍን በአይነ ህሊናችን አሻግረን በማለም በአንድነት የሰላም ሀይል ማእበል እንፍጠር። ያስቡበት! አይሸወዱ ካለንበት ሁኔታ በላይ ማሰብ ካልቻልን በቀር ካለንበት ሁኔታና ክስተት በላይ መሻገር አንችልም።

ከሰላም ሀሳብ ሰላም ቀን ይሁንሎ። ምርጥ ሀሳብ።

ለውጤት እናስብ!
ሃሳቦን ወደ ውጤት ይለውጡ!
ለውጤት ማሰብ ይማሩ፡፡
ካሊድ ሰኢድ፤ በኢትዮጵያ የቦብ ፕሮክተር ስልጠና አሰልጣኝና አማካሪ
Kalid Proctor Gallagher Consultant
ህጻናት ልጆቻችን በአእምሮና በአካል የሚበለጽጉት በጫወታ ነው።

ህጻናት ልጆችህን ገና ናቸው ብለህ አትናቃቸው አእምሮቸው ለማወቅና የመቀበል አቀሙ ከአዋቂ በላይ አቅም አለው። ልጆች ምታስተምረው ካደጉ ቡሆላ ሳይሆን ገና በህጻንነታቸው ነው።

ትንሽ ከፍ ካሉ ማስተማር ከባድ ይሆናል ምክያቱም ከፍ ባሉ ቁጥር አእምሮዎቸው ፕሮግራምድ ሆኖ ስለሚጠብቅህ ያንን ለመፋቅ እና ሌላ ፕሮግራም ለመጫን ገና ብዙ ስራ ይጠይቅሃል ስለዚህ አስቀድመህ የምትፈልገውን ፕሮግራም ገና በልጅነታቸው አእምሮ ውስጥ ጫንላቸው። ታድያ ይህንን ለማድረግ ገና ናቸው አልደረሱም ብለህ እንዳታስብ ምታስተምራችው መንገድ ብቸኛው በጫወታ ነው። አጫውታቸው!

ለውጤት እናስብ!
ሃሳቦን ወደ ውጤት ይለውጡ!
ለውጤት ማሰብ ይማሩ፡፡
ካሊድ ሰኢድ፤ በኢትዮጵያ የቦብ ፕሮክተር ስልጠና አሰልጣኝና አማካሪ
Kalid Proctor Gallagher Consultant
የእርስዎ መልስ የቱ ነው?

ለውጤት እናውራ፣ ለውጤት እናስብ፣ ለውጤት እንስራ!

ለውጤት እናስብ!
ሃሳቦን ወደ ውጤት ይለውጡ!
ለውጤት ማሰብ ይማሩ፡፡
ካሊድ ሰኢድ፤ በኢትዮጵያ የቦብ ፕሮክተር ስልጠና አሰልጣኝና አማካሪ
Kalid Proctor Gallagher Consultant 👇👇👂
ብታውቅስ? ትከተለው ነበር? ሚስጥሩንስ ማወቅ ትፈልጋለህ?
Anonymous Poll
65%
ተገኝቶ ነው
0%
ሚኖር አይመስለኝም
15%
እንጃ
20%
እስቲ
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የእርሶ ህይወት ሙቀት መለኪያ ስንት ዲግሪ ላይ ነው? 📟

ምንድን ነው ሚያወራው ካላቹሁኝ ይህችን ቪዲዮ 2ደቂቃ ወስዳቹህ ይመልከቱ የማወራውን ይረዳሉ ብዙ ቁም ነገሮችን ይሸምታሉ።

ለእርሶ ቀኖን በድንቅ ሀሳብ ድንቅ ቀን ያርግሎት!

ለውጤት እናስብ!
ሃሳቦን ወደ ውጤት ይለውጡ!
ለውጤት ማሰብ ይማሩ፡፡
ካሊድ ሰኢድ፤ በኢትዮጵያ የቦብ ፕሮክተር ስልጠና አሰልጣኝና አማካሪ
Kalid Proctor Gallagher Consultant
ውድ ነገር በነጻ

አእምሮዎችንን ያገኘንው ከኛ ጋር ስንፈጠር አብሮን የተሰጠን መሳሪያ እና በነጻ ነው፡፡ ሰው ደግሞ በነጻ የሚያገኘውን ነገር ሁላ ርካሽ ነው የሚያረገው፡፡ እውነታው ግን የተገላቢጦሽ ነው፡፡ በገንዘብ የምናገኘው ነገር ሁሉ ርካሽ ናቸው፡፡ ቤትህ ቢወድም መልሰህ ትገነባዎለህ፣ ገንዘብህን ብታጣና ብትከስር መልሰህ ታገኘዋለህ፡፡ እነዚህን ነገሮች ደጋግመህ እንኮን ብታጣ መልሰህ መላልሰህ እንደገና ማግኘት ትችላለህ፡፡

ቤተሰባችን አገራችን ልጆቻችን ህልሞቻችን ሁሉ በነጻ ያገኘናቸው ናቸው፡፡ እነዚህን በነጻ ያገኘናቸውን ነገሮች ግን አንዴ ካጣን በምንም ደግመን አንመልሳቸውም፡፡

በዚህ ሀሳብ ከተስማሙ እስማማለው ብለው ቴክስት ያርጉ፡፡


ውድ ሃሳብ! አንቂ ሃሳብ! ንቁ ቀን ተመኘንሎ
ሃሳቦን ወደ ውጤት ይለውጡ!
ለውጤት ማሰብ ይማሩ፡፡
ካሊድ ሰኢድ፤ በኢትዮጵያ የቦብ ፕሮክተር ስልጠና አሰልጣኝና አማካሪ
Kalid Proctor Gallagher Consultant
በውስጧ ያለውን ታላቅ ሀሳብ አስበውት ያውቃሉ? በእያንዳንዳችን የዕለት ተዕለት ህይወት ውስጥ ያልታለሙ ህልሞችና አጋጣሚዎች በውስጣችን አሉ: በእኛ ለመጠራት ዝግጁ ሆነዉ እየጠበቁ ያሉ አጋጣሚዎች፡፡ በየእለቱ በህይወትህ በኑሮህ የሚገጥሙህ ችግሮች ሁሉ አንተን ወደዚህ የእድገት መስመር ለመምራትና ከነገሮች ከሁኔታዎች በሰዎች ተገዥ መሆን አቁመህ በውስጥህ ለመጠራት ዝግጁ ሆኖ እየጠበቀ ያለ ታላቅ ሀሳብ እንድታወጣ የሚመሩህ የመንፈስ ጥሪዎች ናቸው፡፡

ጆሴፍ መርፊ "በትኬሻህ ላይ ያለው ችግር ከሰማይ በረከት ነው" ያለበት ምክንያትም ለዚሁ ነው፡፡ ምንም ነገር ዉስጥ ብትሆን ሁሌም በውስጥህ ታላቅ ነገር ብቻ አስብ። እንደዛ እስካላሰብክ ድረስ ታላቅ ሰው ልትሆን አትችልም!

ሃሳቦን ወደ ውጤት ይለውጡ!

ካሊድ ሰኢድ፤ በኢትዮጵያ የቦብ ፕሮክተር ስልጠና አሰልጣኝና አማካሪ
Kalid Proctor Gallagher Consultant
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ስኬታማ አልሆንኩም ብለው ተጨንቀዋል? በቪዲዮ ድንቅ ምላሽ።

አብዛኛው ሲነገረን ያደግነው ምናሰባቸው ነገሮች ሁሉ እውነት አይደሉም። መደበኛ ትምርት ከሌለህ ስኬታማ መሆን አንችልም ብለን እንድናምን ነው ያደግንው... የንግድ ልምድ ከሌለን ስኬታማ መሆን አንችልም ብለን እንድናምን ነው ያደግንው...ይህ ሁሉ ግን ውሸት ነው። በአለም ላይ የነበሩ ታላላቅ ሰዎች እነዚህ ነገሮች ስለነበራቸው አይደለም ስኬታማ የሆኑት።

የተቀርጽንባቸው ሀሳቦች ማንነታችንንና የህይወት ደራጃ ይወስናሉ። ህይወታችንን ለመለወጥ ሲነገረን ካደግንባቸው ውስን እምነቶችና ሃሳቦች መለወጥ ይገባል።

ለውጤት እናስብ!
ካሊድ ሰኢድ፤ በኢትዮጵያ የቦብ ፕሮክተር ስልጠና አሰልጣኝና አማካሪ
Kalid Proctor Gallagher Consultant
አለምና ሌሎች ካልተቀየሩ አንተ ላትቀየር ነው?

ልብ ብለው አስበውት ያወቃሉ ግን? ትዳር ደስተኛ ለማድረግ ባል ሚስቱን፣ ሚስት ደግሞ ባልዎን እንዲቀየር ይጠብቃሉ፡፡ አባትና ልጅ ለመግባባት አባት ልጅን፣ ልጅ ደግሞ አባት እንዲቀየር ይጠብቃል፡፡ አገር እንዲቀየር መንግስት ህዝብን፣ ህዝብ መንግስት እንዲቀየር ይጠብቃሉ፡፡

እስቲ በቅድሚያ የራሶን ውስጣዊ አለም አመለካከትና እይታ እንዲሁም አስተሳሰቦን ቀድመው ይለውጡና ይሞክሩት፡፡

ሃሳቦን ወደ ውጤት ይለውጡ!
ካሊድ ሰኢድ፤ በኢትዮጵያ የቦብ ፕሮክተር ስልጠና አሰልጣኝና አማካሪ
Kalid Proctor Gallagher Consultant
ድርጊት (ተግባር) ሁለተኛው የሀሳብ ፎርም ነው፡፡

በውሰጥህ ስለራስህ ሰለማንነትህና ስለህይወትህ ሁሉ አሁን በህይወትህ ባለህ ደረጃና ሁኔታዎች እናም ሰዎች ላንተ በሚሰጡህ ቦታ ልክ ከሆነ የምታስበው አንተ ሁሌም እራስህን የምታገኘው ደከማ እና ለምንም ነገር ብቁ አለመሆንህን ነው፡፡

የምተፈልገው ነገር ሁሉ እውን ሆኖ ከማየትህ በፊት በቅድሚያ በውስጣዊ ማንነትህ ስለራስህና ስለህይወትህ ካለህበት ሁኔታና ደረጃ በላይ ከፍ ብለህ ስታስብ እና ውስጥህን በታላቅ ሃሳቦች ስትሞላው ብቻ ነው።

ለውጤት ማሰብ ይማሩ፡፡
ካሊድ ሰኢድ፤ በኢትዮጵያ የቦብ ፕሮክተር ስልጠና አሰልጣኝና አማካሪ
Kalid Proctor Gallagher Consultant
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ለምን ስለራሶ ዝቅታ በገዛ ሀሳቦ እራሶን ዝቅ አርገው ያስባሉ? ለምን?

በራስህ በገዛህ አእምሮ ውስጥ የተቀረጸ የአንተ ምስል አለ። በአንተው በራስህ ውስጥ እኮ ነወ። አይገርምም? ደግሞም እኮ በሃሳቦቻችን ነው የቀርጻናቸው። ታዲያ እያንዳንዳችን ውስጥ የቀረጽነው ምስል በፊልም ቢወጣ ሁላችንም የምርጥ ተዎናኝ ተሸላሚ እንሆን ነበር።

እስቲ ልጠይቅህ ባንተ ውስጥ የተቀረጸው የራስ ምስል ልብ ወለድ ፊልም ምን አይነት ነው? በራስህ ውስጥ ምርጥ አስደሳች ታላቅ ምስል እየቀረጽክ ነው ወይስ....? በሉ በቪዲዮ ላይ ነገሩን በደም ያብላሉት።

ከምርጥ ሃሳብ ደስ በሚል ስሜት ውብ ቀን ይሁንሎት!

ሃሳቦን ወደ ውጤት ይለውጡ!
ካሊድ ሰኢድ፤ በኢትዮጵያ የቦብ ፕሮክተር ስልጠና አሰልጣኝና አማካሪ
Kalid Proctor Gallagher Consultant
ለሚያስበው የሌለውና የማይሆነው ይሆንለታል፡፡ ለማያስበው እያለውም የለውም፡፡

ደስተኛ ሆነህ ደስታ እንዲሰማህ የግድ ውጫዊ ሚያሳስደስቱህ ነገሮች እስኪመጡልህ መጠበቅ አያስፈልግህም፡፡ ፍቅር እንዲሰማህ የግድ አፍቃሪ መጠበቅ አያስፈልግህም፡፡ ሀብታም ባለጸጋ ሆነህ እንድታይና እንዲሰማህ የግድ ሀብት እስኪኖርህ መጠበቅ የለብህም። ስኬታማ ውጤታማ ሆነህ እንድትገኝና እንዲሰማህ የግድ ስኬት እስኪመጣ መጠበቅ አያስፈልግህም፡፡

መሆንና ማግኘተት የምትፈልገውን ነገር ሁሉ ከመሆናቸውና ከመከሰታቸው በፊት አስቀድመህ በአእምሮህ ውስጥ ስታስብ ያለህ ያህል ይሰማሀል እናም ባንተ ውስጥ ያለው የማይታይ የሀሳብ-ቅርጽ/ጽንሰ-ሃሳብ ስሜትህን አንተነትህንና ስብእናህን ገዝቶ ወደ ሚታይ ቁሳዊ እውነታ ይለወጣል፡፡

ሃሳቦን ወደ ውጤት ይለውጡ!
ካሊድ ሰኢድ፤ በኢትዮጵያ የቦብ ፕሮክተር ስልጠና አሰልጣኝና አማካሪ
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
አሁን ያሎት የራስ-ምስል (Self-Image) ካልወደዱት እንዴት መለወጥ ይችላሉ?

አሁን ያሎት የራስ-ምስል የተቀረጸው በአብዛኛው እርሶ በመረጡትና የእርሶ እውነተኛ ማንነት ሳይሆን በህይወቶ ውስጥ በደረሰቦት ውጫዊ ሁኔታና ክስተቶች እንዲሁም ሌሎች ሰዎች ስለእርሶ በሰጦት አስተያየት ትችትና ወቀሳ በተደጋጋሚ በውስጦ ባስገቡት ሃሳብ በአእምሮዎ ውስጥ የተቀረጸ ነው። ታዲያ ምንበወጣህ ለምን ተብሎ የርሶን ውድ ማንነተና ህይወት ለሁኔታዎች ለሌሎች ሰዎች ለማንም አሳልፈው ይሰጣሉ?

ያው እንግዲህ መልሰው የሚፈልጉትን የራሶን ማንነትና ህይወት ለመቅረጽ ይህንን ከባለፈው ሳምንት አጠር ተደርጎ የተቆረጠውን ቪዲዮ ደግመው ይመልከቱ።

ከውድ ሃሳብ ውድ ቀን ለእርሶ!

ሃሳቦን ወደ ውጤት ይለውጡ!
ካሊድ ሰኢድ፤ በኢትዮጵያ የቦብ ፕሮክተር ስልጠና አሰልጣኝና አማካሪ
Kalid Proctor Gallagher Consultant
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
እራሶን ሰብሰብ አርገው በሰከነ መንፈስ ለመዋል.....ምን?

ቀኖን ግዜዎን ሁሌም በየቀኑ ተረጋግተው ለማሳለፍ እራሶንና ውስጦን ሰብሰብ አርገው በሰከነ መንፋስ ለመዋል ሚያስችሎትን ውሳኝ ነገር እስቲ ሹክ እንበሎት። መልሱን በዚህች 2ደቂቃ ቪዲዮ ውስጥ በጥልቅ ያገኙታል።

ከውብ ሃሳብ የተረጋጋ መንፋስ ውብ ቀን ለእርሶ ይሁንሎት!

ለውጤት እናስብ!
ሃሳቦን ወደ ውጤት ይለውጡ!
ለውጤት ማሰብ ይማሩ፡፡
ካሊድ ሰኢድ፤ በኢትዮጵያ የቦብ ፕሮክተር ስልጠና አሰልጣኝና አማካሪ
Kalid Proctor Gallagher Consultant
2025/07/07 22:28:33
Back to Top
HTML Embed Code: