Telegram Web Link
◾️ በጦርነት ጊዜ የአዕምሮ ጤንነትዎን መረዳት!

በሀገራችን ላይ ጦርነት እና የጦር ወሬ መስማት ከጀመርን ሰነባብተናል። ጦርነቱን ተከትሎ በተፈጠሩ ቀዉሶች እና መፈናቀሎች፣ አብዛኛዎቹ ሰዎች ፣ የጭንቀት ፣ የሀዘን ፣ እና የንዴት ስሜቶችን ማስተናገዳቸዉ ጤናማ እና ተገቢ ናቸው። ነገር ግን አንዳንድ ሰዎች ለጦርነቱ የበለጠ ጥልቅ እና ደካማ ምላሽ ሊኖራቸው ይችላል።

ሁሉም ሰው በአሰቃቂ ሁኔታ ላይ በተለያየ መንገድ ምላሽ እንደሚሰጥ እና እያንዳንዱ ሰው ለከባድ ስሜቶች የራሱ የሆነ የመቻቻል ደረጃ እንዳለው ማስታወስ አስፈላጊ ነው። እነዚህን ስሜቶች ለመቋቋም ለራስህ እና ለሌሎች ልታደርጋቸው የምትችላቸው አንዳንድ ነገሮች አሉ። በዓለማችን ውስጥ መሰማራታችን ፣ ከሰዎች ጋር መገናኘታችን እና ከፊታችን ስላሉ ፈተናዎች ብሩህ አመለካከት መያዝ ሌሎች አሰቃቂ ጊዜያትን ለማለፍ ቁልፍ ናቸው ይላሉ። በእርግጥ ፣ በችግር ጊዜ፣ ሰዎች ህይወታቸውን እና የህይወት እርካታን የሚያሻሽሉ ለውጦችን ማድረግ ይችላሉ።

ለተዛባ ሁኔታ መደበኛ ምላሽ ምን እንደሆነ እና ምን ምልክቶች የበለጠ ከባድ ችግር እንዳለቦት ማወቅ ከአእምሮ ጤና ባለሙያ እርዳታ መቼ እንደሚፈልጉ ለማወቅ ይረዳዎታል።
Continue Reading
◾️ እየወደቀ ያለው የአሜሪካ ኢምፔሪያሊዝም 
(BRI፣ B3W እና Global Gateway) (የዐዲስ ኢኮኖሚ ሥርዐት ውልደት መባቻ (?)


 ( በ ዶ/ር ፀደይ ወንድሙ )

የኮሚውኒስቱ ጎራ አሜሪካንን ኢምፔሪያሊስት ናት ሲላት ቆይቷል (ከነአባባሉም "ኢምፔሪያሊዝም ይውደም" ነበር)። ለአሜሪካዊያን ግን ራሳቸውን እንደ ኢምፔሪያሊስት ማሰብ ሩቅ ነበር (“Americans are not in the habit of speaking of themselves as imperialistic” ሲል ይገልጸዋል ፖል ቫርግ “Imperialism and the American Orientation toward World Affairs” በተሰኘ መጣጥፉ (እ.አ.አ. በ1966 የተጻፈ ነው))። የአሜሪካንን ኢምፔሪያሊስትነት በተመለከተ በአሜሪካን ምሁራን መካከል ጥቂት ክርክሮች የነበሩ ቢኾንም፣ በአሜሪካ የትምህርት ሥርዐት ውስጥ ከመጀመሪያ ዲግሪ የፖለቲካ ሳይንስ ጥናት ጀምሮ አሜሪካንን እና ኢምፔሪያሊዝምን ማገናኘት ከ"ሙሁራዊ" ክበብ ማፈንገጥ ተደርጎ ይታያል። ይኽንን የሚነግረን ሚካኤል ፓረንቲ፣ እ.አ.አ. በ1995 አንድ መጽሓፍ አሳተመ፣ Against Empire የተሰኘ። ይኽ መጽሓፍ ከወጣ በኋላ የብዙዎች ዐይን የተከፈተ ይመስላል። 
እንደፓረንቲ ከኾነ የኢምፔሪያሊዝም አስተሳሰብ እና ድርጊት ለረጅም ጊዜ በሰው ልጅ ታሪክ ውስጥ የዘለቀ ቢኾንም፣ ከአሜሪካ ጋር እንዳይያያዝ በተለያዩ አገላለጾች ሲሸፋፈን ቆይቷል፦ ለምሳሌ በግዛትነት የተያዙ አገራትን ("empires"ን)፣ "commonwealth"፣ "dominion" ወይም "territory" ብሎ በመጥራት፤ ወይም ደግሞ ግዛት ለማድረግ ጦርነት ሲደረግ ሰበቡን "አገር ለመከላከል"፣ ለ"ብሔራዊ ደኅንነት"፣ እና "መረጋጋትን ለማስጠበቅ" በማድረግ።
የአሜሪካ ኢምፔሪያሊዝም ከመቶ ዓመታቶች በፊት ከነበሩት ኢምፓየሮች የሚለየው ካፒታሊስት መኾኑ ነው። ከረጅም ጊዜ በፊት የሚደረጉ የግዛት ማስፋፋቶች ሃብት ለመዝረፍ፣ ለማስገበር፣ የወርቅ ማዕድን ለመሰብሰብ ወይም ለክብር የሚደረግ ነበር። ካፒታሊስታዊውን የሚለየው ግን፣ በሚስፋፋባቸው አገሮች ላይ በአነስተኛ ክፍያ ጉልበትን በመበዝበዝ እና በገበያ ሥርዓታቸው ውስጥ ሰርፆ በመግባት ካፒታልን ወደራሱ ስለሚያከማች ነው። ካፒታል የሚያከማቸውም በሚይዛቸው አገሮች ላይ ኢንቨስት በማድረግ፣ በኢኮኖሚያቸው፣ በባህላቸው እና በፖለቲካ ሥርዓታቸው ላይ የበላይ በመኾን የምርት ሥርዓታቸውን ከዓለም ዓቀፍ ገበያ ጋር በማስተሳሰር ነው።  
Continue Reading
ተስፋ . . .
Greed's are corrupted human hearts - 'Charlie Chaplain'

አኗኗራችን ነፃና ውብ መሆን ይችላል ግን መንገዳችንን ስተናል ስስት የሰውን ልብ በክሏል አለምን በጥላቻ ከፋፍሏል ሞኞች ደም መፋሰስ ውስጥ ከተውናል , በፍጥነት መጉዋዝ ችለናል ግን በራሳችን ውስጥ ተቀብረናል , ብዙ መስጠት የሚችለው ጥበባችን ፈላጊዎች አድርጎ አስቀርቶናል እውቀታችን ተጠራጣሪ ጉብዝናችን ጨካኝና ክፉ አድርጎናል , ብዙ አሳቢዎች ግን ስሜት አልባዎች ሆነናል ከማሽን ይበልጥ ሰብአዊነት ያስፈልገናል ከጉብዝና ይልቅ ደግነትና ሩህሩህነት ያስፈልገናል ያለነዚህ ብቃቶች ሕይወት ቀውስ ውስጥ ትሆንና ሁሉንም እናጣለን ::
ለናንተም ለምትሰሙኝ እላችሁዋለሁ የወረደብን መከራ ምንም አይደለም የሚያልፍ ስስት ነው የሰውን ልጅ ዕድገት የሚፈሩ ሰዎች ጭካኔ ነው, የሠዎች ጭካኔ ያልፋል አትጥሉ ብዙ ፍቅርና ተስፋ በእናንተ ውስጥ አለ ::
ይህንን ሕይወት ነፃ ውብ የተሻለ የማድረግ ኃይል አላችሁ
አዲስ ስለሆነ ዓለም, ቀና ለሆነ ዓለም, የመስራት ዕድል ለሰው ስለሚሰጥ ዓለም እንልፋ ! ለወጣቱ መፃኢ ተስፋ ለአዛውንቱ እፎይታና ዕረፍትን ስለሚሰጥ ዓለም እንልፋ ጥላቻና አለመቻቻልን ለመጣል ምክንያት ስለሆነች ዓለም እንልፋ , ልፋታችን ለመልካም ብቻ ይሆን ዘንድ እንልፋ . . .

' Charline Chaplain as the 'Major General '

'

Hope . . .

Our lives can be free and beautiful, but we have lost our way. Greed has corrupted human hearts, divided the world with hatred. We need more humanity. We need kindness and compassion instead of courage. Without these qualities, life will be in crisis and we will lose everything.
I say to you who hear me: The suffering we have suffered is nothing but greed. People who are afraid of human progress are cruel.
You have the power to make this life free and beautiful
Let's move on to a new world, a new world of opportunity, a new world for a better life, a new world of HOPE for all !

"Charlie Chaplain as the Major General "
@kendelM
ውድ የቅንድል ዲጂታል መፅሔት ተከታታዮች በማህበራዊ፣ ሀገራዊ፣ ስነ ልቦናዊ፣ ቴክኖሎጂ፣ ባህል፣ ጥበብና ጤና ነክ ጉዳዮች ዙሪያ የሚያተኩር ዲጂታል መፅሔታችንን ከቅንድል የትስስር ገፆች እና ከTikvahmagazine በተጨማሪ በየወሩ በኢሜይል አድራሻችሁ ወደ እናንተ እንድትደርስ ለምትፈልጉ ከታች ያለውን አጭር ፎርም በመሙላት ቋሚ ተከታታይ መሆን ይችላሉ፡፡

#ቅንነት_ድል_ያደርጋል!

https://surveyheart.com/form/61bc7020e462f47da4c7e778
"Harnessing the Potential of Human Mobility"

አቤት የሰው ብዛት ሚገባ ሚወጣ
መች ቦታ ቢኖረው ሌላ ቦታ መጣ!

ዛሬ አለማቀፍ የፍልሰተኞች ቀን ነው።
መሽቶ እኪነጋ በብዙ ሰቆቃ ውስጥ የሚኖሩ በብዙ ችግር ከአራቱም የአም ክፍል የተሰደዱ እልፎችን ማሰብ እና መጠበቅ ያስፈልጋል።
ሰፊው ለሰው ልጆች ሁሉ በቂ ነው!

#KeepWordSafe
#InternationalMigrantsDay
#ኢሰመኮ

@KendelM
የአለም ውበት የሚገለጠው በሁሉም ያሉ የሰው ልጆች አቃፊ ፣ ለሰላም ዝቅ የሚሉ ሆነው አንድ የሚሆኑበት ፍቅር ህያው ሲሆን ነው፡፡
ባንዲት ህይወት ባንዲት አለም
አብረን እንሁን ሩህ ለማለምለም
አለም ባንድ ጎኗ
ይኅው በዳር ዳሯ እሳት እናያለን
ምስክር ይሆን ዘንድ በሲኦል እንዳለን
ተፈጥሮ ሳይነሳን - ውበት ሳያጎለን
በአንድነት ለመኖር ለምን እንፈራለን?
የምንከተላቸው አያዩንም ዞረው
ምንኖረውን ችግር አያይቱም ዞረው
ታዲያ
ውሀ ለተጠማ
ምግብም ለራበው
መልበስ ለጠፋበት - ሰላም ለናፈቀው
በአንድ አለም በአንድነት መቼ ነው ምንደርሰው?

#InternationalSolidarityDay
#UnityInDiversity
#KeepWordSafe
#ጤናማቃላት

@kendelM
@kendelM
how lucky am i to be seen as a colour of my self
a proud Ethiopian
i am not labeled as black
or not called white
when ever i am asked of my colour
i am proudly saying green, yellow and red
i am Ethiopian
best known for my humanity
love, forgiveness and prosperity
of my circles whom are known people
not just as others to be cold people of colour
this are people of respect along with their duty
people of integrity
with in the proud soul
people of truth and trust
but untouchable for the evil
one mind set one soul
one heart for their country’s survival
ethiopia is people of man
generations of heroes
an eyes for the blind
a hand and leg for the disable
a soul for the dead
and one and only soldiers for their peace
ethiopia is an example of all kind
a living truth
©rj

@kendelM
@kendelM
ቅንድል ኢትዮጵያ pinned «ቃለመጠይቅ ከክቡር ዶ/ር ኦባንግ ሜቶ ጋር ክፍል - 1 "....የሀገር ፍቅር ማለት እንደተስቦ በሽታ ሁላችንም ጋር ያለን ብሄርተኝነት የሚባል በሽታን ወደጎን በመተው ኢትዮጵያዊነታችን ላይ የጋራ ታሪኮቻችንን በማሰብ በፍቅርና በሰላም መኖር መቻል ማለት ነው። ...." (በነፃነት ጌታቸው) 👇👇👇👇👇 https://telegra.ph/KENDEL---ARCHIVE-12-24»
#ቅንድል_ዲጂታል_መፅሔት

በልዩ የበዓል እትም ይጠብቁን፡፡

@kendelM
እንኳን ለገና በዓል በሰላም አደረሳችሁ!

አንቺ ቤተልሔም፥የይሁዳ ምድር፥ከይሁዳ ገዢዎች ከቶ አታንሺም ሕዝቤን እስራኤልን የሚጠብቅ መስፍን ከአንቺ ይወጣልና፥ ተብሎ በነቢይ እንዲህ ተጽፏልና፥በይሁዳ ቤተልሔም የአለም መድሀኒት ፣ የፍጥረታት ጌታ ፣ የሀያላን ሀያል ፣ የጌቶች ጌታ ፣ የንጉሶች ንጉስ የስጋም የነፍስም ፈጣሪ እርሱ መድሐኒት እየሱስ ክርስቶስ ከድንግል ማርያም ተወልዷል።
የገና በዓል አምላክ በፈጠራት ምድር አንድያ ልጁን ለአዳም መድሀኒት እንዲሆን ስጋ ለብሶ የተወለደበት እንደመሆኑ በልባችን ፍቅር ፣ ሰላም ፣ ቅንነት ፣ ምክንያታዊነት እና በጎነትን በልባችን ፀንሰን እንድንወልድ እድል የተሰጠን ነው።
በዓሉን ስናከብር በቅንነት ስራ ፣ በበጎ ተግባር መሆን ይገባዋል። የፍቅርና የይቅርታ አምላክ የተወለደበት ቀን ነውና ሁላችንም ልባችንን በፍቅር ህይወታችንን በይቅርታ እንመራ ዘንድ አደራ እያልን ቅንድል ለሁሉም የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ እንኳን ለበዓሉ በሰላም አደረሳችሁ በመላት መልካም ምኞቷን ትገልፃለች።

ቅንድል ዲጂታል መፅሔት
ቅንነት ድል ያደርጋል!

@kendelM
@kendelM
ከትሕትና የበለጠ መልካም ነገር የለም። ሌሎችን መረዳት የመጀመርያው ንቃት እና ዕውቀት ነው፣ መንፈሳችንንም ወደ ላይ ክፍ ከፍ ያደርገዋል።

@kendelM
@kendelM
💜የሕይወት ግንድ ብዙ ቅርንጫፎች ነን!!

አንድ ውቅያኖስ ላይ ነን ‘የአንተ’ ታንኳ ሲናጥ ‘የእኔው’ ደንገል መንቀጥቀጥ ይጀምራል… ‘የእርሷ’ ጀልባ ሲቀዝፍ የባሕሩ ለመምቴ ይናጣል… የሰላምህ እርግብግቢት የሰላማችንን ንፋስ ይጠቅሳል… የሕመማችን ትንፋሽ የደስታ መንፈሷን ይበርዛል… ስለምን - ‘እኔም’፣ ‘አንተም’፣ ‘እርሷም’፣ ‘ሁላችንም' አንድ ነንና...

🔶መምህሩ ማሃርሺ… “How are we Supposed to treat others?” ብለው ቢጠይቁት…
“There are no others” ሲል የመለሰው ለዚህ ነበር...

በተገበርከው ክፋት ብቻ ሳይሆን በተብሰልስሎትህ ሂደት ነገር ዓለማችን ይታወካል። በተነፈስከው በጎ ቃል አይደለም ባሰላሰልካት ደግነትም መውጣት መግባታችን ይዋባል… ብቻህን አይደለህምና የብቻ ሰላም የለህም… አልተነጣጠልንምና የብቻ ሕመምም አይኖርህም

🔷የግዙፍ ውቅያኖስ አካል ነን… እኛም ሆንን በዙሪያችን ያለው የተፈጥሮ ስንክሳር የውቅያኖሱ አንድ ጠብታ ነው… አንዲት ጠብታ የምትፈጥረው ለመምቴ /Ripple/ የሌላውን ለመምቴ ትነካለች… እኒህ የሃሳብ፣ የስሜትና የድርጊት ለመምቴዎች በሌላኛው ተፈጥሮ ላይ ቀጥተኛ ተጽዕኖ አላቸው… በበጎም በክፉም… ተመልሰው ግን ወደ ምንጫቸው ይመጣሉ… በመዋኛ ገንዳ ውስጥ የፈጠርከው የውሃ ለመምቴ የገንዳውን ግድግዳ ገጭቶ ወዳንተ እንዲመለስ ማለት ነው…

ከኔ ቤት ላይ የረጨኸው እሳት ከሆነ ነበልባሉ ያንተን ቤት ይነካል… ሽቶ ስትረጨኝ የመዓዛው ቅንጣቶች ለአፍንጫህ ውብ ጠረን ይለግሳል… “You reap what you saw” … ሰው የዘራውን ያንኑ ደግሞ ያጭዳል… ይህን ምስራቃውያኑ Karma ሲሉት ሌሎች ደግሞ Boomerang ይሉታል… Boomerang አውስትራሊያኖቹ አቦርጂኒስቶች ከእንጨት የሚሰሩት ደጋን ቅርጽ ያለው የአደን መሳሪያ ሲሆን ወርዋሪው ዘንድ ተመልሶ እንዲመጣ ተደርጎ የሚነደፍ ነው… ለሃሳብ፣ ለስሜትና ድርጊትህ መጠንቀቅ የሚኖርብህ ወላፈኑ ‘ለእኔም’፣ ‘ለእርሷም’፣ ‘ለእነርሱም’ እንደሚተርፍ በማሰብ ነው… ምክንያቱም … We are all One!

🔷በ ዕውቀቱ በአንድ ድንቅ ግጥሙ ላይ እንዲህ ብሏል👇
ይችላል ይሉሃል ፍልሚያ ማዘጋጀት፣
ያባት አጥንት ወስዶ ስሎ ጦር ማበጀት፣
አንተው ጦር ወርውረኽ አንተው ቀድመኽ ወደቅኽ፣
አካሌ ደረቴ መኾንህን መች አወቅኽ?፣

🔶ሰው ብቻ ሳይሆን ከዋክብቱ፣ ሕዋው፣ ምድሪቱ፣ እንስሳው… በሚታየውና በማይታየው ዓለም ያለው ነገር ሁሉ በአንዳች ተፈጥሯዊ ክር የተሳሰረ ነው… ማሰሪያው ስላልታየ መተሳሰሩ የለም አይባልም… “Invisible threads are the strongest ties.” ― Friedrich Nietzsche

‘እዚያ ቤት ሲንኳኳ እኛ ቤት ይሰማል’ ‘ከወዲህ አንተን ሳማ እዚያ ከንፈር ትነክሳለህ’፣ ‘እከሊት ስታነሳኝ በስቅታዬ አውቀዋለሁ’፣ ‘የሰፈር ውሻ ሲያላዝን አንዱ አዛውንት ሊያልፉ ነው ማለት ነው’… ‘ውስጥህ ሲረባበሽ ራቅ ካለ ቤተሰብህ አልያም ወዳጅህ ቤት አንድ አደጋ አለ ማለት ነው’... 'ቅንድብህ ሲርገበገብ እንግዳ ሰው ልታይ ነው' … የጥንቶቹ ይሄ እውነት ስለገባቸው ይመስለኛል መሰል አባባሎች ያቆዩልን

በረከት በላይነህ "የመንፈስ ከፍታ" ላይ እንዲህ ይለናል👇

“የግልህ ወንዝ ስለሌለህ ብቻህን የምትሰራው ድልድይ የለም! የሰማዩ ርቀት፣ የምድሪቱ ስፋት በ’እኛ’ እንጂ በ’እኔ’ አይለካም፡፡ ውዱ ‘እኔ’ ከ’እኛ’ የተሰራው ነውና!”

🔷እዚህ ጋ ነው ስለ ዝምድናና ባዳነት ያለን ግንዛቤ መፈተሸ ያለበት፣ ስለ ዘርና ቀለም ያለን መረዳት መጤን ያለበት፣
Peter Russell “The Global brain” ብሎ ባሰናዳው ቪዲዮው ላይ አንድ በጨረቃ ላይ የተጓዘ የጠፈር ሳይንስ ተመራማሪ የተናገረውን ውብ ቃል ትሰማላችሁ “When you are up there you are no longer an American citizen or a Russian citizen. Suddenly those boundaries disappear. You are a planetary citizen.”

🔑ኑረዲን ዒሳ በአንድ ግጥሙ.

“ባዳውን አፍቅሮ፣
ከባዳው ልጅ ፈጥሮ፣
እኔን ባዳዬ አለኝ - ሰባት ቤት ቆጥሮ፣
ልጁን ዘመዴ አለው - በፍቅር ታውሮ፡፡
ቅጠሉ ነኝና ለረጂሙ ሃረግ፣
እኔም ዘመዱ ሆንኩ - መቼስ ምን ይደረግ?” ብሏል…

ፍቅር ሲገባን የልዩነት ቅዠት ይተናል… ማንነት ሲገባን ሕብራችን ይታያል… ጥበብ ሲያጥጠን ግን ልዩነት ያዜምልናል…

ጃፓንን ያጥለቀለቀው የሱናሚ ማዕበል የጠፋው አንድ ሚሊየን ሕፃናት ተሰብስበው “We pray for you” በማለታቸው ነው… ከየልቦቻቸው ቅንነት የተፈጠረው የፍቅር እርግብግቢት - የአንድነት ሞገድ ነው የጃፓንን ሕመም ያከመው… በዙሪያችን ያለው ተገልጦ የሚመላለስበት እንቅብ /field/ ምናችንን ተቀበለ ነው ቁምነገሩ

❤️ ፍቅር ስንሰጥ በዙሪያችን ባሉት ላይ እርግብግቢቱ ፍቅርን ይወልዳል፣ክፉ ስናስብ ደግሞ በተቃራኒው ክፋት ይጠነሰሳል፣ከፊልዱ ውጭ እስካልሆንን ድረስ ከምላሹ ተጽዕኖ ልናመልጥ አንችልም።
ደምስ ሰይፉ

We are all One!
ውብ አሁን❤️

@kendelM
@kendelM
ለመላው የኦርቶዶክስ እምነት ተከታይ ቤተሰቦቻችን እንኳን ለከተራ በዓል በሰላም አደረሳችሁ።
@kendelM
@kendelM
ባለጊዜ

ዘመን ሲያልፍ፥ ዘመን ሲተካ
ጊዜዬ መጣ ስል፥ ልደሰት ልረካ
ደረሰልኝ ያልኩት፥ ልቤን የጣልኩበት
አጠገቤ ሲደርስ፥ ሳየው በቅርበት
ቀልሎ አገኘዋለሁ፥ አጣለሁኝ ደስታ
ዓይኔ ሌላ ይሻል፥ ይሆናል ከርታታ
ደ'ሞ ሌላ ጊዜ፥
ቅጠሏ የሚያምር፥ በለሲት አይቼ
ጊዜዬ የደረሰ፥ መስሎኝ ተደስቼ
ቀረብ ብዬ ሳያት፥ ምጓጓለት ፍሬ
በውስጧ አልነበረም፥ ቀረሁ ተማርሬ
ግና 'ሞክራለሁ፥ ተስፋዬን አልቆርጥ
እገኛለሁ ሁሌ፥ ጊዜየን ፍለጋ፥ ተራራ ስቧጥጥ
ደሞም ይመስለኛል፥ ጊዜዬ የመጣ
ፖለቲክስ ሳወራ፥ ስልጣን ላይ ስወጣ
ግና እኩይ ሳስብ፥ ሌላውን ስገፋ
እቡይ ማንነቴን፥ ም'ዳሩን ሳሰፋ
ድንገት ብልጭ ብሎ፥ የክስረት መብረቅ
'' ጊዜህ እንዳልሆነ፥ ጠንቅቀህም አታውቅ''
እንዲያ ሲለኝ ታዲያ
ሲተቸኝ ይህ ውስጤ
መጠየቅ ጀመርሁ፥ ምንድነው ግን ምጤ?
ይሄው ጠይቃለሁ
እመራመራለሁ
'መቼ ይሆን ጊዜዬ?'፥ በሚል ብርቱ ሙግት፥ እወዛወዛለሁ..
ግና አንድ ነገር እንዲሁ ይገባኛል
መልካምን ካደረግሁ
ተንኮልን ካላሰብሁ
ዘር ቋንቋ ሳ'ለይ፥ ሁሉን እኩል ካየው(ሁ)
አልጠራጠርም፥ ጊዜዬ ያኔ ነው

ስለዚህ
ለምን ልንከራተት ፥ ልቤን የትም ጥዬ
ቅን ስሆን ነውና፥ ሚደርሰው ተራዬ
ጊዜዬን ፍለጋስ፥ ለምን ልሁን ሚዜ
ይሄው አገኘሁት፥ ቀና ልሁን በቃ
ቅንነት ነው ጊዜ።

ግጥም:- ቀለዮጳ ደስታ

@KendelM
ጥምቀት በታሪካዊቷ የጎንደር ከተማ
@kendelM
@kendelM
2025/06/27 17:45:49
Back to Top
HTML Embed Code: