Telegram Web Link
Forwarded from ስለፍትሕ (Talk To Lawyer)
ከተጨማሪ እሴት ታክስ ነፃ በተደረገ ግብር ከፋይ ላይ የሚፈፀም የታክስ ተመላሽ ሥርዓት

— የተጨማሪ እሴት ታክስ ነፃ መብት ያለው ሰው በአገር ውስጥ ታክስ የሚከፈልበት ግብይት ሲያከናውን ታክሱን ከፍሎ በተመላሽ እንዲስተናገድ ይደረጋል፡፡
— የታክስ ነፃ ባለመብቱ ለአቅራቢው ክፍያ የፈፀመው በባንክ በኩል መሆኑን የሚያስረዳ ማስረጃ ካቀረበ የተመላሽ ጥያቄው በቀረበ በሰባት ቀናት ውስጥ ተመላሽ ይደረጋል፡፡
— የታክስ ነፃ ባለመብቱ ለአቅራቢው ክፍያ የፈፀመው በባንክ በኩል ካልሆነ በአነስተኛ ኦዲት ተጣርቶ የተመላሽ ጥያቄው በቀረበ በአንድ ወር ጊዜ ውስጥ ተመላሽ ይደረጋል፡፡
https://www.tg-me.com/AboutJustices
@AboutJustices
#Ethiopia

ማንኛውንም ሰው #ከሀገር_እንዳይወጣ የማገድ ስልጣንን የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት መስሪያ ቤትን በዋና ዳይሬክተርነት ለሚመራ ኃላፊ የሚሰጥ የአዋጅ ማሻሻያ ለህ/ ተ/ ም/ ቤት  ቀርቧል።

የአዋጅ ማሻሻያው ምን ይዟል ?

ማሻሻያው ማንኛውንም ሰው ከሀገር እንዳይወጣ የማገድ ስልጣን ለኢሚግሬሽን እና ዜግነት አገልግሎት መስሪያ ቤት ዋና ዳይሬክተርነት ይሰጣል።

ነባሩ ህግ ምን ይላል ?

" ማንኛውም ሰው #ከኢትዮጵያ_እንዳይወጣ ሊታገድ የሚችለው በህግ መሰረት #በፍርድቤት ሲታዘዝ ብቻ ነው " ይላል።

ዛሬ ለህዝብ ተወካዮች ም/ቤት የቀረበው የአዋጅ ማሻሻያ በነባሩ ህግ ላይ የተቀመጠውን የፍርድ ቤትን " #ብቸኛ_ስልጣን " የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት መስሪያ ቤትን በዋና ዳይሬክተርነት ለሚመራ ኃላፊ በተጨማሪነት #ያጋራ ነው።

ማሻሻያው የአገልግሎቱ ዋና ዳይሬክተር ፦

⚫️ ከሚመለከታቸው የደህንነት አገልግሎት እና ህግ አስከባሪ አካላት ከሚያገኘው መረጃ ወይም አገልግሎቱ በራሱ ከሚያገኘው መረጃ በመነሳት ፤

⚫️ በብሔራዊ ጥቅምና ደህንነት ላይ ሊቀለበስ የማይችል ግልጽና ድርስ የሆነ ከፍተኛ ጉዳት የሚያስከትል ሁኔታ መኖሩን ሲያምን፤ ማንኛውም ሰው ከሀገር እንዳይወጣ ማገድ ይችላል ሲል ደንግጓል። 

የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ፤ " ከሀገር እንዳይወጣ ያገደውን ሰው ይዞ የሚያቆይ ከሆነ ፍ/ቤት መቅረቡን ማረጋገጥ አለበት "ም ይላል የአዋጅ ማሻሻያው። 

ዜጎች ከሀገር እንዳይወጡ የማገድ ስልጣን ላይ ማሻሻያ የተደረገው ፤ በነባሩ ድንጋጌ ምክንያት እየደረሰ ያለውን " ከፍተኛ ጉዳት " ለመቅረፍ እንደሆነ በማሻሻያው ላይ ሰፍሯል።

አሁን በስራ ላይ ባለው አዋጅ መሰረት " ከፍርድ ቤት የእግድ ትዕዛዝ እስኪገኝ ድረስ በብሔራዊ ጥቅምና ደህንነት ላይ ከፍተኛ ጉዳት ያደረሱ ወይም ሊያደርሱ የሚችሉ ሰዎች ከሀገር እየወጡ ከተጠያቂነት እያመለጡ በሀገራችን ብሔራዊ ጥቅምና ደህንነት ላይ ከፍተኛ ጉዳት እያደረሱ ነው " ሲል የረቂቅ አዋጁ ገልጿል።

በሌላ በኩል ፦

ማሻሻያ አዋጁ " #አስተዳደራዊ_ቅጣት " አንቀጽ ይዟል።

" ከጊዜ ወደ ጊዜ በህገ ወጥ መንገድ በሀገራችን ውስጥ የሚኖሩ የውጭ ሀገር ዜጎች እየተበራከቱ፤ በህገ ወጥ ድርጊቶች እየተሳተፉ ከፍተኛ ችግር እየፈጠሩ በመሆኑ በአስተዳደራዊ ቅጣት በመቅጣት ከህገ ወጥ ድርጊታቸው እንዲቆጠቡ ማድረግ አስፈላጊ ነው " ሲል ያስረዳል።

በዚህም በኢትዮጵያ የሚንቀሳቀሱ የውጭ ሀገር ዜጎችን " በጥቁር መዝገብ እንዲመዘገቡ እና ከሀገር እንዲወጡ ማድረግ ወደ ህጋዊ ስርዓት እንዲመጡ በማድረግ ረገድ ከፍተኛ የሆነ ሚና " እንዳለው ተብራርቷል።

#የሚኒስትሮች_ምክር_ቤት በሚያወጣው ደንብ አማካኝነት፤ የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት መ/ቤት አስተዳደራዊ ቅጣት እንዲጥል በአዋጅ ማሻሻያው ስልጣን ተሰጥቶታል።

" ይህን አዋጅ አሊያ በዚህ አዋጅ መሰረት የወጣ ደንብ ወይም መመሪያን የጣሰ ማንኛውም ሰው ፤ የሚኒስትሮች ምክር ቤት በሚያወጣው ደንብ መሰረት አስተዳደራዊ እርምጃ ይወሰድበታል " ይላል ማሻሻያው።

Credit:
#EthiopiaInisider 
#JournalistTesfalemWoldeyes

@tikvahethiopia
ሟችን የግብረ-ስጋ ግንኙነት በመፈፀም ሕይወቷ እንዲያልፍ ያደረገው ግለሰብ በጽኑ እስራት ተፈረደበት

ከሟች መኖሪያ ቤት በመግባት አፏን በጨርቅ ጠቅጥቆ፣ አንገቷን አንቆ በመያዝ የግብረ-ስጋ ግንኙነት በመፈፀም ሕይወቷ እንዲያልፍ ያደረገው ግለሰብ በጽኑ እስራት ተፈረደበት

አላዩ ሞገስ ደሳለኝ የተባለ ተከሳሽ ጥር 29 ቀን 2015 ዓ.ም ከጠዋቱ በግምት 1፡30 ሲሆን በጉለሌ ክፍለ ከተማ ወረዳ 02 ሽሮ ሜዳ አዲስ ተስፋ ትምህርት ቤት አካባቢ የ14 ዓመት የሆነችውን የግል ተበዳይ የምትኖርበት መኖሪያ ቤት በመግባት በጥፊ በመምታት፣ እንዳትጮህ አፏ ውስጥ ጨርቅ በመጠቅጠቅ እና አንገቷን በሁለት እጁ አንቆ በመያዝ በኃይል የግብረ-ስጋ ግንኙነት የፈጸመባትና አፏ ውስጥ ጨርቅ በመጠቅጠቁ እና አንገቷን በማነቁ ምክንያት ትንፋሽ አጥሯት ሕይወቷ እንዲያልፍ በማድረጉ በአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን ምርመራ ተጣርቶ በፍትህ ሚኒስቴር የጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ ዘርፍ በሴቶችና ህጻናት ላይ የሚፈፀሙ ወንጀሎች ዐቃቤ ሕግ ዳይሬክቶሬት በወ/ሕ/አ/620/2/ሀ/ እና /3/ መሰረት በፌዴራል የመጀመሪያ ደረጃ ፍርድ ቤት አራዳ ምድብ 11ኛ ወንጀል ችሎት ክስ ቀርቦበት ክርክር ሲደረግ ቆይቷል፡፡

በክርክሩ ሂደትም የዐቃቤ ሕግ ማስረጃ ከተሰማ በኋላ ተከሳሽ እንዲከላከል ብይን ተሰጥቶ የመከላከያ ምስክሮችን ያሰማ ቢሆንም የቀረበበትን ክስ ሊከላከል ባለመቻሉ ፍርድ ቤቱ በተከሳሽ ላይ የጥፋተኛነት ፍርድ በመስጠት በ19 ዓመት ፅኑ እስራት እንዲቀጣ ሲል ውሳኔ ሰጥቷል፡፡

(ፍትህ ሚኒስቴር)
#የሞት_ፍርድ👉 #Adama

ተከሳሽ ቶሎሳ ወይም ፍቅሩ አሸናፊ ይባላል።

በአዳማ ከተማ ቦሌ ክፍል ከተማ በተለምዶ ደካ አዲ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ ሚያዝያ 21 ቀን 2016 ዓ.ም እናቱን በአሰቃቂ ሁኔታ ገድሏል።

ተከሳሹ እናቱን በስለት (ቢላዋ) በአሰቃቂ ሁኔታ ወግቶ ነው ህይወታቸውን እንዲያጡ ያደረገው።

ተከሳሹ ድርጊቱን የፈጸመው #በቁማር_የተበላዉን ገንዘብ እናቱ ያላቸውን ንብረት በመሸጥ እንዲተኩለት ለማድረግ ሲል እየደበደበ ያሰቃያቸው እንደነበር ዐቃቤ ሕግ በማስረጃ አረጋግጧል።

በዚህ ብቻ ያላበቃው ተከሳሽ ሚያዚያ 21/ 2016 ዓ/ም ጠዋት በአሰቃቂ ሁኔታ የእናቱ ህይወት እንዲያልፍ በማድረጉ ከባድ የግድያ ወንጀል ክስ ቀርቦበታል።

ጉዳዩን የተመለከተው የአዳማ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ዛሬ በዋለው ችሎት በሞት እንዲቀጣ ወስኗል።

በተከሳሹ ላይ የተጣለው #የሞት_ፍርድ በአገሪቱ ርዕሰ ብሔር ሲጸድቅ ነው ተፈጻሚ የሚሆነው። #ኤፍቢሲ
@tikvahethiopia
አማራጭ የሕግ እውቀት
👉Telegram👈
https://www.tg-me.com/lawsocieties

👉Facebook Page 👈
https://www.facebook.com/lawsocieties/

👉 LinkedIn 👈
https://www.linkedin.com/company/lawsocieties/

👉YouTube 👈
https://youtube.com/@Ale_Hig
ፍቺ ከፍርድ ቤት ውጭ፡- የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ሰሚ ችሎት እና የፌዴሬሽን ምክር ቤት ውሳኔዎች አጭር ዳሰሳ
በ፦ ተክለኃይማኖት ዳኜ በላይ

ይህ ጽሑፍ የሰበር ሰሚ ችሎት በኮ/መ/ቁ 14290፣ በ31891 እና 102662 ጋብቻ ከተፈጸመ በኋላ ለረጅም ጊዜ ተለያይቶ መኖር እና በዚህ ጊዜ ውስጥ ሌላ ጋብቻ መስርቶ መኖር ፍርድ ቤት መቅረብ ሳያስፈልግ ጋብቻውን ለማፍረስ በቂ እንደሆነ የሰጣቸው ውሳኔዎች የፌዴሬሽን ምክር ቤት የሰበር ችሎቱ ውሳኔዎች ከሕገ-መንግሥቱ አንቀጽ 50(5)፤ አንቀጽ 55 እንዲሁም አንቀጽ 79(3) ጋር የሚቃረን ነው በማለት ሽሯቸዋል።

ጸሐፊው የሰበር ውሳኔዎቹን እና የፌዴሬሽን ምክር ቤት ውሳኔን ከቤተሰብ ሕጉ ከሕገ መንግሥቱ እና ከሌሎች አግባብነት ካለቸው ሐሳቦች ጋር በማገናዘብ የራሱን ሐሳብ ያሰፍራል።

መልካም ንባብ!
https://www.abyssinialaw.com/blog/divorce-out-of-court-a-brief-survey-of-federal-supreme-court-decisions-and-federal-council-decisions
የመኖሪያ ቤት  አከራይ ተከራይ የውል ስምምነት ምዝገባ ሰኔ አንድ ይጀምራል

የመኖሪያ ቤት  አከራይ ተከራይ የውል ስምምነት ምዝገባ ሰኔ አንድ እንደሚጀምር የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ አስታወቀ፡፡

የአዲስ አበባ ቤቶች ልማት እና አስተዳደር ቢሮ የመኖሪያ ቤት ኪራይ ቁጥጥር እና አስተዳደር አዋጅ 1320/2016 ን ለመፈፀም የአከራይና ተከራይ ውል ከሰኔ አንድ ጀምሮ በየወረዳዎቹ ምዝገባ እንደሚጀመር ገልጿል።

የቢሮ ኃላፊዋ  ወ/ሮ ቅድስት ወ/ጊዮርጊስ ምዝገባውን ለማካሄድ ከሚመለከታቸው አካላት ጋር በመቀናጀት አስፈላጊውን ዝግጅት አድርገናል ብለዋል።

አከራዮች ከተከራዮቻቸው ጋር በመሆን  ከሰኔ አንድ ጀምሮ በየወረዳቸው በመገኘት መመዝገብ እንደሚችሉ ተናግረዋል። 

ምዝገባውን ከስራ ሰአት ውጭ ለማከናወን እንደታቀደም ጠቁመዋል።

አዋጁና መመሪያው የአከራይ እና ተከራይን ሚዛናዊ ተጠቃሚነት የሚያስጠብቅ መሆኑንም ተናግረዋል።

ይህንኑ ተግባራዊ ለማድረግ የመኖሪያ ቤት ኪራይ ቁጥጥር እና አስተዳደር አዋጅ ላይ እና የማስፈፀሚያ መመሪያ ላይ ውይይት መካሄዱን አስረድተዋል።
አማራጭ የሕግ እውቀት
👉Telegram👈
https://www.tg-me.com/lawsocieties

👉Facebook Page 👈
https://www.facebook.com/lawsocieties/

👉 LinkedIn 👈
https://www.linkedin.com/company/lawsocieties/

👉YouTube 👈
https://youtube.com/@Ale_Hig
#ሞት_ተፈርዶበታል !

ከአባቱ ጋር በገባበት " #የጥቅም_ግጭት " መላው ቤተሰቦቹን በጥይት ገድሎ ሊጨርስ የነበረው ግለሰብ በሞት ተቀጣ።

ተከሳሽ ከፍታ ካፋላ ይባላል።

በጋርዱላ ዞን የሃይበና ቀበሌ ነዋሪ ነው።

ግለሰቡ ቤተሰቦቹ በሚኖሩበት በኮንሶ ዞን ሠገን ዙሪያ ወረዳ ሠገን ገነት ቀበሌ በመሄድ በ4 ቤተሰቦቹ ላይ የጥይት እሩምታ ይከፍታል።

በዚህም ሶስቱን ሲገድል አንዱን አቁስሏል።

በጥይት እሩምታ የገደላቸው ፦
- #አባቱ
- #እናቱ
- #አጎቱ ሲሆኑ የመቁሰል አደጋ የደረሰበት የ9 አመት ታናሽ ወንድሙ ነው።

ግለሰቡ ይህን ፈጽሞ ከአካባቢዉ ቢሰወርም የጸጥታ ኃይሉ ከማህበረሰቡ ጋር ተባብሮ ባደረገዉ ክትትል ከ5 ወራት በኋላ ሊያዝ ችሏል።

ፖሊስም ስራውን አጠናቆ ለፍርድ ቤት አቅርቧል።

ተከሳሹም ፤ ከወላጅ #አባቱ ጋር በገባበት ' የጥቅም ግጭት ' ምክኒያት ወንጀሉን እንደፈጸመ ለፍርድ ቤቱ አምኖ ቃሉን ሰጥቷል።

ይህም ቃሉም ከቀረበበት የሰውና የሰነድ ማስረጃ ጋር ተዳምሮ የፍርድ ሂደቱን ቀላል እንዳደረገዉ ቲክቫህ ኢትዮጵያ ሰምቷል።

በዚህም በኃላ ጉዳዩን ሲመረምር የነበረዉ የኮንሶ ዞን ከፍተኛ ፍርድ ቤትም ተከሳሽ ከፍታ ካፋላ #በሞት እንዲቀጣ ወስኗል።

#TikvahEthiopiaFamilyHW

@tikvahethiopia
ለባህላዊ የዳኝነት ሥርዓቶች እውቅና የሚሰጥና ከዘመናዊ የፍትህ ሥርዓት ጋር እንዲጣጣሙ የሚያስችል ሞዴል ረቂቅ አዋጅ ተዘጋጀ

አዲስ አበባ፤ ግንቦት 26/2016፦ በኢትዮጵያ ለሚገኙ ባህላዊ የዳኝነት ሥርዓቶች እውቅና የሚሰጥና ከዘመናዊ የፍትህ ሥርዓት ጋር እንዲጣጣሙ የሚያስችል ሞዴል ረቂቅ አዋጅ መዘጋጀቱን የፍትህ ሚኒስቴር ገለጸ።

የፍትህ ሚኒስቴር "ማኅበረሰብ አቀፍ የፍትህ አገልግሎት ሚና በኢትዮጵያ የፍትህ ዘርፍ" በሚል መሪ ኃሳብ ባለድርሻ አካላትን ያሳተፈ ውይይት አካሂዷል።

በመርኃ ግብሩ የፌደራልና የክልል የፍትህ ዘርፍ አመራሮች እንዲሁም የሲቪል ማኅበረሰብ ድርጅት ተወካዮች ተገኝተዋል።

የፍትህ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቲዮስ (ዶ/ር) በዚሁ ጊዜ እንደገለጹት፤ ባህላዊ የዳኝነት ሥርዓት ግጭቶችን ለማርገብና የተረጋጋ ማኅበረሰብ ለመፍጠር አይነተኛ ሚና አላቸው።

ይሁንና ዘርፉ በፍትህ ሥርዓቱ ማኅበረሰቡን ተጠቃሚ እንዲያደርግ ከዘመናዊ የፍትህ ሥርዓቱ ጋር የተጣጣመ በማድረግ ረገድ ክፍተት መኖሩን ነው ያስረዱት።

ይህንን ችግር ለመቅረፍና ዘርፉ ለፍትህ ሥርዓቱ መጎልበት ያለውን ሚና ከግምት በማስገባት የባህላዊ የዳኝነት ሥርዓቶችን ለማጠናከር እየተሰራ ነው ብለዋል።

ይህንንም ተከትሎ አሁን ላይ ዘመናዊው የአዋጅ ሥርዓትን ከባህላዊ የፍትህ ሥርዓት ጋር ማሰናሰን የሚያስችል ሞዴል ረቂቅ አዋጅ መዘጋጀቱን ጠቁመዋል።

ሞዴል ረቂቅ አዋጁ የፍትህ ሥርዓቱን በማሳለጥ ረገድ አገራዊ አበርክቶው የላቀ መሆኑን አብራርተዋል።

የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝዳንት ቴዎድሮስ ምህረት በበኩላቸው በኢትዮጵያ መደበኛ ፍርድ ቤቶች የሚሰጡት አገልግሎት ከፍላጎት ጋር መጣጣም አለመቻሉን ገልጸዋል።

ፍርድ ቤቶች ከሰው ሃይል፣ ከመሰረተ ልማትና ከኃብት አኳያ ውስንነት ያለባቸው በመሆኑ በአግባቡ ተደራሽ መሆን እንዳልቻሉ ጠቁመው መሰል ችግሮችን ለመፍታት ባህላዊ የዳኝነት ሥርዓቶች ቁልፍ ሚና አላቸው ብለዋል።

ባህላዊ ፍርድ ቤቶች በመደበኛው ፍርድ ቤቶች ላይ የሚፈጠረውን ጫና እንዲቀንስ ከማስቻላቸውም በላይ ዜጎች በቋንቋቸውና በነባራዊ ሁኔታቸው እንዲዳኙ የሚያስችል መሆኑንም አስረድተዋል።

በመሆኑም ዘርፉን ማጠናከር የሁሉም ባለድርሻ አካል ድርሻ ሊሆን እንደሚገባ ጠቁመው የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤትም ከዚህ አኳያ የሚጠበቅበትን ሚና እንደሚጫወት አረጋግጠዋል።

በፍትህ ሚኒስቴር የተቋም ግንባታና ሪፎርም ዘርፍ ሚኒስትር ዴኤታ አማካሪ አማኑኤል ታደሰ በበኩላቸው በኢትዮጵያ ለሚገኙ የባህላዊ የዳኝነት ሥርዓቶች እውቅና ለመስጠት የተዘጋጀው ሞዴል ረቂቅ አዋጁ ክልሎች ለሚያዘጋጁት ረቂቅ ሕግ መነሻ እንደሚሆን ተናግረዋል።

ሞዴል ረቂቅ አዋጁ በተለይም ባህላዊ የዳኝነት ሥርዓቶች ከመሰረታዊ የሰብዓዊ መብት መርህ ጋር እንዳይጣረሱ ለማድረግ ያለመ መሆኑም አክለዋል።

ሞዴል ረቂቅ አዋጁ ባህላዊ የዳኝነት ሥርዓቶች ለአገራዊ የፍትህ ሥርዓቱ ተጨማሪ አቅም እንዲሆኑና የበለጠ ውጤታማ እንዲሆኑ ለመደገፍ ያለመ መሆኑም ተናግረዋል።

በውይይት መድረኩ የሲዳማ ባህላዊ የዳኝነት ሥርዓት "አፊኒ" በተሞክሮነት ቀርቦ ውይይት ተደርጎበታል።(ኢዜአ)
አማራጭ የሕግ እውቀት
      👇👇👇👇👇👇👇👇
https://www.tg-me.com/lawsocieties
1322 SEZ Technical Correction final መማ 21.pdf
1.8 MB
አዋጅ ቁጥር ፩ሺ፫፻፳፪/፪ሺ፲፮
የልዩ ኢኮኖሚ ዞን አዋጅ
Proclamation No 1322/2024
Special Economic Zone Proclamation
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
According to Labour Proclamation No. 1156/2019, what is the minimum working age?
Anonymous Poll
23%
18
76%
15
5%
17
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
Forwarded from ስለፍትሕ (Lawyer Mikias Melak 🔊 ጠበቃና የሕግ አማካሪ ሚኪያስ መላክ)
አስደሳች ዜና!
🔴🔴 የአጭር ጊዜ ስልጠና!🔴🔴
ሳያመልጥዎ ቶሎ ይመዝገቡ!
👇👇👇👇👇👇👇
https://forms.gle/HthGiWNazet4tMBF7

መስራት በተሰኘው በገበያ ፣ ማስተርካርድ ፋውንዴሽን እና በአጋሮቻቸው ጥምረት ለተመሠረተው ፕሮግራም ከዘ-ኢንስፓየርድ ኢትዮጵያን ዪዝ አሶሲዬሽን ጋር በመተባበር ነፃ ስልጠና አዘጋጅተዋል
ስልጠናውም በቀላሉ በስልኮ ቴለግራም ቦት (TELEGRAM BOT) ላይ የሚሰጥ ሲሆን ሲጨርሱ ባጅና ሰርተፍኬት ያገኛሉ !

ይህ እድል ለኢትዮጵያ ወጣቶች

በነፃና ባሉበት ቦታ ሆነው እንዲከታተሉት የቀረበ ሲሆን የዲጂታል ችሎታዎን ለማሻሻል እና የ ኢ-የመማሪያ ምህዳር እንዲያገኙ ዕድል ይሰጣል፡፡

መርጃውን ከየት አገኙት?👇👇👇

ከዘ-ኢንስፓየርድ ኢትዮጵያን ዩዝ አሶሲዬሽን

ሪፈራል ኮድዎን  ያስገቡ:- 👉 0103

ስልጠናውን እና በሰርተፊኬት የሚያገኙት
በዚህ ፎርም ሲመዘገቡ ብቻ እንደሆነ ማሳወቅ እንፈልጋለን!!

ሲመዝገቡ ለሚጠይቅዎት ለሚከተሉት ጥያቄዎች ከዚህ በታች የተሰጠውን መልስ ያስገቡ፣

መርጃውን ክየት አገኙት?
መልስ👇👇👇👇
ከዘ-ኢንስፓየርድ ኢትዮጵያን ዩዝ አሶሲዬሽን

ሪፈራል ኮድዎን በ IEYA**** ቅርጸት ያስገቡ:-
መልስ👉👉 0103


እጅግ በጣም ጠቃሚ እና የስራ እድል የሚፈጥር ስልጠና ነው ተጠቀሙበት።

Your referral code is 0103.

Here is the link👇👇👇👇

https://forms.gle/HthGiWNazet4tMBF7


በጎግል (Google) እና ቴሌግራም (Telegram) ቦት ላይ መመዝገብ አለቦት።
መረጃዎን በጎግል(Google) ከሞሉ በኋላ ወደ ቴሌግራም ቦት የሚመራዎትን አገናኝ ሊንክ (Link) ያገኛሉ እና ኮርሱን ይውሰዱ።
2024/06/11 11:55:07
Back to Top
HTML Embed Code: