This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
አረጋዊው ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ መልከ ጼዴቅ ዐረፉ!!!

የብፁዕ አቡነ መልከ ጼዴቅ አጭር ዜና ሕይወት።

ልደት፡-

ብፁዕ አቡነ መልከ ጼዴቅ፣ በጎንደር ክፍለ ሀገር፣ በደብረ ታቦር አውራጃ በፋርጣ ወረዳ ልዩ ስሟ መገንታ ቍስቋም በተባለች ደብር፣ ከቄስ ወርቅነህ ትኩ እና ከወይዘሮ አንጓች አታሌ በ1916 ዓ.ም. ተወለዱ፡፡

መንፈሳዊ እና ዘመናዊ ትምህርት፡-

በሕፃንነት ዕድሜያቸው፥ ከደጉ አባታቸው ከቄስ ትኩ ፊደል ቈጥረው፣ ንባብ ለይተው፣ ዳዊት ከደገሙ በኋላ የቃል ትምህርት ጀመሩ፡፡ በአቅራቢያቸው ከሚገኘው ድድም ጊዮርጊስ ከመሪጌታ ወንድም ጾመ ድጓ እና ምዕራፍ ተማሩ። ቀጥሎም በዝነኛዋ ደብር አዛውር ኪዳነ ምሕረት ከታላቁ የዜማ መምህር መሪጌታ ጀንበር የዜማ ትምህርታቸውን አጠናከሩ። ከዚያም ወደ ሌላኛው ዝነኛ ደብር አትከና ጊዮርጊስ ከመሪጌታ ፈቃዱ ድጓ ተምረዋል። ቅኔ ቈጥረው የተቀኙት ደግሞ በታላቁ ደብር ቆማ ፋሲለደስ ከሚገኙት ከሊቁ መምህር መሪጌታ ዓምደ ብርሃን ነበር። ቀጥሎም፣ ወደ አማራ ሳይንት ገርት አቡነ አቢብ ተጉዘው ከመሪጌታ አበበ፣ ገርቲ ቅኔያቸውን ከነአገባቡ አጠናክረው ተቀኝተዋል።

ከታላቁ ሊቅ መምህር ሰይፈ ሥላሴ በአዲስ አበባ መንበረ መንግሥት ቅዱስ ገብርኤል ገዳም፣ የመጻሕፍተ ሐዲሳትን ትርጉም ተምረው፣ በመምህርነት በመመረቅ ወንበር ዘርግተው አስተምረዋል። ከሌላው ሊቅ ከመምህር ፊላታዎስ ደግሞ የአምስቱን ብሔረ ኦሪት ትርጓሜ፣ መዝሙረ ዳዊትን፣ መጽሐፈ ኢሳይያስን በሚገባ አጠናቀው ተምረዋል። ብፁዕ አቡነ መልከ ጼዴቅ፣ ከፍተኛ የሃይማኖት ትምህርትን፣ በአገር ውስጥ እና በውጭ ሀገር ተምረዋል።
🔔🔔 ዜና ዕረፍት 🔔🔔
ታላቁ የቤተ ክርስቲያናችን ሊቅ ብፁዕ አቡነ ኤጲፋንዮስ ዐረፉ!!!

• የቀብር ሥነ ሥርዐታቸው ነገ ጠዋት በ3፡00 በመንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል ይፈጸማል!!!

የቀድሞው የምዕራብ ሸዋ ሀገረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ የነበሩት፣ ብፁዕ አቡነ ኤጲፋንዮስ፣ ዛሬ ጠዋት ዐርፈዋል፡፡
ከሓላፊነታቸው ተገልለው በመንበረ ፓትርያርኩ በሚገኘው ማረፊያቸው ለረጅም ጊዜ በሥጋ ሕመም የቆዩት ብፁዕነታቸው፣ ዛሬ ረቡዕ፣ ኅዳር 2 ቀን 2013 ዓ.ም. ጠዋት በሞተ ሥጋ ተለይተውናል፡፡
ብፁዕ አቡነ ኤጲፋንዮስ፣ በአምስተኛው ፓትርያርክ ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ አንብሮተ እድ፣ ሐምሌ 5 ቀን 1991 ዓ.ም. ኤጲስ ቆጶስነት ከተሾሙት 16 ብፁዓን አባቶች አንዱ ነበሩ፡፡ በፊት ስማቸው አባ አምኃ ሥላሴ ይባሉ የነበሩ ሲኾን፣ ብፁዕ አባ ኤጲፋንዮስ ተብለው ለከፋ ሸካ ሀገረ ስብከት ተመድበው ነበር ሐዋርያዊ አገልግሎታቸውን የጀመሩት፡፡
የብፁዕ አቡነ ኤጲፋንዮስ የቀብር ሥነ ሥርዐት፣ ነገ ኀሙስ፣ ኅዳር 3 ቀን 2013 ዓ.ም. ከጠዋቱ በ3፡00፣ በመንበረ ጸባኦት ቅድስት ሥላሴ ካቴድራል፣ ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ፣ ብፁዓን አበው ሊቃነ ጳጳሳት፣ የጠቅላይ ቤተ ክህነት የመምሪያ ሓላፊዎች እና የድርጅቶቹ ሓላፊዎች፣ የአዲስ አበባ አድባራት እና ገዳማት ሓላፊዎች፣ ወዳጅ ዘመዶቻቸው በተገኙበት እንደሚፈጸም፣ የጠቅላይ ቤተ ክህነት ሕዝብ ግንኙነት መምሪያ በፌስቡክ ገጹ አስታውቋል፡፡
ውድ የቻናላችን ተከታታዮች እንኳን ለቅዱስ ጊዮርጊስ ዓመታዊ ክብረ በዓል በሠላምና በጤና አደረሳችሁ!
እንኳን ለ ጾመ ነቢያት(የገና ጾም) በሠላም እና በጤና አምላካችን ልዑል እግዚአብሔር ጠብቆ አደረሰን። ጾሙን የበረከት ጾም ያድርግልን በረከት የምናገኝበት የኃጢአት መደምሰሻ የዲያብሎስ ድል መንሻ ያድርግልን። አብዝተን ስለ ሃገራችን እና ስለ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ዕምነታችን እንጸልይ በጆሯችን የምንሰማውን በዓይናችን አያሳየን።

መልካም የጾም ወቅት ይሁንልን::
የዕለቱ ምስባክ

ታህሣሥ ፲፬

💚💛

መዝሙረ ዳዊት መዝሙር ፻፴፰÷፲፪

"ወሌሊትኒ ብሩህ ከመ መዓልት
በአምጣነ ጽልመታ ከማሁ ብርሃና
እስመ አንተ ፈጠርከ ኩልያትየ እግዚኦ"
++++++++
ወንጌል
ማቴ ፲÷፲፮ - ወናሁ አነ እፌንወክሙ

@LkdusYared
የዕለቱ ምስባክ

ታህሣሥ ፲፭

💚💛❤️

መዝሙረ ዳዊት መዝሙር ፴÷፲፪

"ቀብፁኒ እም ልብ ከመ ዘሞተ
ወኮንኩ ከመ ንዋይ ዘተኀጉለ
እስመ ሰማዕኩ ድምፀ ብዙኃን እለ ዐገቱኒ ዐዉድየ
+++++++++++++
ትርጉም
እንደ፡ሞተ፡ሰው፡ከልብ፡ተረሳኹ፥እንደ፡ተበላሸ፡ዕቃም፡ኾንኹ።
የብዙ፡ሰዎችን፡ስድብ፡ሰምቻለኹና፤በዙሪያው፡ፍርሀት፡ነበረ::
++++++++
ወንጌል

ሉቃ ፲፭÷፲፩ - ወይቤ ፩ ብእሲ ቦቱ ፪ ደቂቅ

ቅዳሴ - ግሩም (ሠለስቱ ደቂቅ )

@LkdusYared
'ጌራ ወርቅ ክበበ ጌራ ወርቅ(2)
አክሊለ ጽጌ ማርያም አክሊለ ጽጌ(2)

💚 💛 ❤️

😇 @LkdusYared 😇
🛑🛑የምስራች እንኳን ደስ አላችሁ የተዋህዶ ልጆች አክሊል ሚዲያ ተተኪ ዘማርያን የምናፈራበት መዝሙራት ኦርቶዶክሳዊ ትምህርቶች ወቅታዊ የቤተክርስቲያን መረጃዎች የተለያየ መንፈሳዊ አገልግሎቶች የሚተላለፍበት መንፈሳዊ ሚዲያ ተከፈተ አሁኑኑ ሰብስክራይብ ያድርጉ ለሌሎችም ሼር ያድርጉ ለነፍስዎ ብዙ ነገር ያተርፋሉ@aklil media


https://youtu.be/-S_ZG86A9Bc?si=0HlMPv5UnuqJ9Vv4
🤑💵 🇫 🇴 🇷 🇪 🇽 𝗧𝗿𝗮𝗱𝗶𝗻𝗴 መማር የምትፈልጉ አንድ የሚገርም የ Forex  ቻናል ያውቃሉ

💶  𝗖𝗶𝘁𝘆 𝗙𝗼𝗿𝗲𝘅 𝗘𝘁𝗵𝗶𝗼𝗽𝗶𝗮 💶

@City_Forex_Ethiopia ይባላል ።
ተመዝገባችሁ መማር የምትፈልጉ አናግሯቸው እስከ 𝟰𝟬% Discount የሚደርስ ቅናሽ አድርገዋል !

    ☎️   +251977338586       🇪🇹
    ☎️   +251977338586       🇪🇹

ይህን ይጫኑ የ Telegram ቻናላቸውን ለማግኝት  👇👇


https://www.tg-me.com/City_Forex_Ethiopia
https://www.tg-me.com/City_Forex_Ethiopia
https://www.tg-me.com/City_Forex_Ethiopia
https://www.tg-me.com/City_Forex_Ethiopia

🎯 𝗔𝗱𝗱 𝗬𝗼𝘂𝗿 𝗖𝗵𝗮𝗻𝗻𝗲𝗹
2024/05/02 11:31:52
Back to Top
HTML Embed Code: