Forwarded from ISLAMINDSET
አንዳከም፣አንሳነፍ...አላህ ቃል የገባልን እሱን ብቻ ካመለክን የዘላለም የስኬት ህይወት ነው። ለምንስ ተስፋ እንቅርጣለን...ሽይጧን የዘላለም ቅጣት ቃል ተገብቶለት ዱንያ ላይ እስካለ ድረስ ተስፋ አይቆርጥም፤ እኛ የአላህ ባርያ ሆነን ያውም የነብዩ(ሰ.ዐ.ወ)ህዝቦች ሆነን ጀነት ቃል ተገብቶልን ለምንስ ተስፋ እንቆርጣለን!!!?...በኢባዳ በርቱ.
ISLAMINDSET
Forwarded from ISLAMINDSET
የሆነ ቀን ነበር እኛ የማናውቀው ግን ወደዚህ አለም የመጣንበት፤የሆነ ቀን ነበር የፈተናን ምሬት የቀመስንበት፤የሆነ ቀን ነበር የደስታን ጥግ ያጣጣምንበት። የነበረን ቀን ማስታወስ ግማሽ ሰውነትን የሚጠይቅ ሲሆን ነገር ግን የሆነ ቀን እና ግዜ እንደሚመጣ ተገንዝቦ መዘጋጀት ሙሉ ሰውነትን ይጠይቃል። ይህም የሆነ ቀን አለ ሳናውቀው እንደተወለድነው ድንገት ሳናውቀው የምንሞትበት፤ የሆነ ግዜ አለ አላህ ያለ አስተርጓሚ ስራችንን እያወቀ የሚጠይቅበት...!
...ለሆነ ቀን እና ግዜ ዛሬውኑ ዝግጅት እናድርግ! አይቀርምና ጉዞው.

ISLAMINDSET.
Forwarded from ISLAMINDSET
የሸይኽ ሙሐመድ አል-አንሲ ፕሮግራም ነገ ማለትም እሁድ ከሰዓት በ11:30 በISLAMINDSET ዩትዩብ ቻናላችን ይለቀቃል..ኢንሻአላህ!

ISLAMINDSET.
Forwarded from ISLAMINDSET
አጫጭር እና ጠቃሚ ቪዲዮዎችን ወደናንተ ስንለቅ እንዲደርሶዎ የቲክቶክ ፔጃችንን ፎሎው ያድርጉ!
የቲክቶክ username ➙ islamindset
ሙሉ ቪዲዮውን ለመመልከት ከላይ የለቀቅነውን የዩትዩብ ማስፈንጠሪያ ሊንክ ይጫኑ....ጀዛኩሙላህኸይረን.
ISLAMINDSET.
Forwarded from በሲራ ስቱዲዮ
የሆነ ቀን ነበር እኛ የማናውቀው ግን ወደዚህ አለም የመጣንበት፤የሆነ ቀን ነበር የፈተናን ምሬት የቀመስንበት፤የሆነ ቀን ነበር የደስታን ጥግ ያጣጣምንበት። የነበረን ቀን ማስታወስ ግማሽ ሰውነትን የሚጠይቅ ሲሆን ነገር ግን የሆነ ቀን እና ግዜ እንደሚመጣ ተገንዝቦ መዘጋጀት ሙሉ ሰውነትን ይጠይቃል። ይህም የሆነ ቀን አለ ሳናውቀው እንደተወለድነው ድንገት ሳናውቀው የምንሞትበት፤ የሆነ ግዜ አለ አላህ ያለ አስተርጓሚ ስራችንን እያወቀ የሚጠይቅበት...!
...ለሆነ ቀን እና ግዜ ዛሬውኑ ዝግጅት እናድርግ! አይቀርምና ጉዞው.

                   @besira
Forwarded from ISLAMINDSET
መሽቶ ሲነጋ እንዲሁም ነግቶ ሲመሽ አላህ ወደ ጀነት እንድንገባ ዘንድ ተጨማሪ አድል እየሰጠን እንደሆነ ስንቶቻችን እናስተውል ይሆን?! ..አሁን አሁንማ እያስፈራኝ መጥቷል, ለምን? ብትሉ አላህ ያዘነለት ሰው ካልሆነ በቀር መሽቶ ሲነጋ በውስጣችን " ጤነኛ ስለሆኩ ጥሩ እንቅልፍ ተኝቼ ተነሳሁ" ብለን የአላህን ሀይል እና ሁሉን ቻይነት የምንረሳ እየመሰለኝ ነው።በተቃራኒው ነግቶ ሲመሽ ደግሞ ምናልባችም ያሳካነው ነገር ካለ በአላህ ፍላጎት ተሳካልኝ ሳይሆን ልክ እንደ ቃሩን "እኔ ኮ እንደዚህ ነኝ በዕውቀቴ አሳካሁ!" የምንል እየመሰለኝ ነው! ...አላህ ይጠብቀንና!

ISLAMINDSET.
Forwarded from ISLAMINDSET
" እኔ በዱንያ ላይ ልክ እንደ አንድ መንገደኛ ዛፍ ስር እንደተጠለለ እንጂ ሌላ አይደለሁም!"

ነብዩ ሙሐመድ(ሰ.ዐ.ወ)
➙ እኛ ግን እንደ ረሱል(ሰ.ዐ.ወ) የሆን አይመስለኝም። ስራችን ሁሉ መንገደኛ ሳንሆን ኗሪ የሆን ነው የሚመስለው!..አላህ ይዘንልን🙏

ISLAMINDSET.
Forwarded from ISLAMINDSET
አላህ በተለያዩ ግዜ እና ሰዓታቶች ባሮቹ የሚጠይቁትን የትኛውም ነገር ከትሩፋቱ ይቸራል።በየትኛውም የህይወት ደረጃ ላይ እንሁን የአላህ እዝነቱ በኛ ላይ አይቋረጥም።ነገር ግን ሰዎች ነን እና በዱንያ ስንኖር በኛ አስተሳሰብ ጎደለን ብለን የምናስባቸው ነገሮች አይጠፉም።ለዚህም በተለያዩ ሀዲስ ዘገባዎች እንደሚያመላክቱት በጁሙዓ ቀን ጥቂት ሰዓታቶች አሉ አላህ ባሮቹ የትኛውንም የሚያስፈልጋቸውን ነገር ቢጠይቁት የሚሰጥበት, ይህም ከአሱር ሶላት በኋላ እስከ መግሪብ ሶላት ሰዓት ድረስ እንደሆነ ረሱል(ሰ.ዐ.ወ) አመላክተዋል። ጉዳይ ካላችሁ አላህን ጠይቁ...ኢንሻአላህ ይሰጣችኋል! በዱዓችሁም ወንድማችሁንም አትርሱት!🤲

[ አላሁመ ሶሊ አላ ሙሐመድ ወአላ አሊ ሙሐመድ..!]

ISLAMINDSET.
Forwarded from ISLAMINDSET
መፈፀም ያለበት ነገር አላህ በሚፈልገው ሰዓት እና ቦታ በውስጥ ፍላጎት ካልፈፀምን, መፈፀም ለሌለበት ነገር ነፍሳችን ተስባለች ማለት ነው! ራሳችንን እንመልከት። ራሳችንን ለመመልከት ደግሞ ያሳለፍነውን ህይወታችንን ማስታወስ በቂ ነው።
ISLAMINDSET.
Forwarded from ISLAMINDSET
ሁሉም ነገሮች በአላህ ውሳኔ ነው የሚፈፀሙት! ነገር ግን እኛም ሰበብ እንድናደርስ ታዘናል። ሰበብ ስናደርስ ግን ውጤቱን ለአላህ ሰጥተን መሆን አለበት። አላህ ፈቅዶ ከተሳካልን አላህን እናመስግን። እናም ፈተና መሆኑን እንወቅ ...ፈተናውም (
አላህ ፈቅዶ ተሳካልን እንል ይሆን.. ወይስ በጉልበቴ አልያም በአስተሳሰቤ አሳካሁት እንላለን!)

የሚል ነው! ...እንዲሁ ሰበብ አድርሰን ካልተሳካም ፈተና ውስጥ መሆናችንን እናስተንትን ...ፈተናውም
አላህ የፈለገውን ሰራ እንል ይሆን ወይስ እድለ ቢስ ነኝ እኔ

!?)
እንል ይሆን..ራሳችንን በሁሉም ተግባራችን ዘወር ብለን እንመልከት።

➙ መልካም የጁሙዓ ቀን ይሁንልን🤲

ISLAMINDSET.
Forwarded from ISLAMINDSET
"
የሰው ልጅ አላህ ምኞቱን ሁሉ እንዲሰጠው ይፈልጋል። መሽቶ ሲነጋም ለህልሙ ይሮጣል እንዲሳካለትም ይታገላል። ነገር ግን አላህ ጤናን ሲያሳጣው ምኞቱ ፣ ህልሙ፣ ትግሉ ሁሉ ጤነኛ መሆን ብቻ ይሆናል።"

...አይ እኛ!!!

➙ ጤነኛ ሆነን የምናስበው ነገር ጤናችንን ስናጣው የምንረሳው ከሆነ አይጠቅመንም..!

ISLAMINDSET.
Forwarded from ISLAMINDSET
"መጪው አለም ወደኛ ቀረበ, በህይወት ምንኖርበት አለም ላይመለስ ጀርባውን ሰጥቶ ወደኋላ ሄደ... የመጪው አለም(የአኺራ)ልጆች ሁኑ!, የአሁኗ አለም(ዱንያ)ልጆች እንዳትሆኑ፤ በዚህ ህይወት ላይ ስንኖር አላህን መገዛት ብቻ ነው ስራችን! በመጪው አለም የሰራነው ምንዳ ብቻ ነው ምናገኘው ስራ አይኖርም!"


አሊ ኢብን አቡጧሊብ (ረ.ዐ)

ISLAMINDSET.
Forwarded from ISLAMINDSET
የጧት እና የማታ ዚክሮችን ማለት ይለማመዱ። እነዚህ ከላይ የምትመለከቷቸው ዚክሮች ረሱል(ሰ.ዐ.ወ) በህይወት ዘመናቸው ሲሏቸው የነበሩ ሲሆኑ ጧት ከሱብሂ በኋላ እና ማታ ከአሱር ሶላት በኋላ ማለትን ይልመዱ!

አላሁመ ሶሊ አላ ሙሐመድ ወአላ አሊ ሙሐመድ
__ መልካም ጁሙዓ __
ISLAMINDSET.
Forwarded from ISLAMINDSET
"
የቀን ምግቡ የተሟላለት በቤቱ ውስጥ, እንዲሁም በሰውነቱ ጤነኛ የሆነ ሰው, ዱንያ ለሱ ጥቅልል ብላ ገብታለታለች

" አሉ ነብዩ ሙሐመድ(ሰ.0.ወ) ...

ለእያንዳንዳችን ከዱንያ የምንፈልገው ይሄንን ይመስለኛል። ነገር ግን እንዳለመታደል ሆኖ አላህ ያዘነለት ሰው ካልሆነ በስተቀር ትርፍን ነገር ከአላህ እየተመኘ ዱንያ እንዳልተሰጠችው ፣ እንደጠበበችበት ያስባል። ...አላህ ይዘንልን🤲

ISLAMINDSET.
2025/10/19 04:54:49
Back to Top
HTML Embed Code: