Telegram Web Link
ተወለደችልኝ

🌹🌹🌹🌹🌹🌹

ከዘላለም ህይወት በኃጥያት ተለይቼ
በመከራ ስኖር እውነትን ጠልቼ
ጌታዬ አምላኬን ዘወትር ሳሳዝነው
ሰላምን አጥቼ ነፍሴን አንገላታው
ድክመቴን ያወቀ የፈጠረኝ እሱ
ሊያድነኝ ወደደ መሀሪ ቅዱሱ
ከሴቶች መሀከል በንጽህና መርጧት
በፍጹሙ ፍቅሩ በልዕልና ወዷት
ዳግም ሰው ሊያደርገኝ በቃል አደረባት

ታድያ እቺ ልዕልት እርሷ የኔ ጸሀይ
ሰንሰለት ሆነችኝ ከእርሱ እንዳልለያይ
ከቅድስት እናቷ ከቅዱስ አባቷ
ለአለም አብርቶ ውበት ደምግባቷ
ወላዲተ አምላክ ድንግል እመቤቴ
ተወለደችልኝ ሆነችኝ ህይወቴ

እናቴ ይህ የአንቺ ብቻ አይደለም የኔም የልደት ቀኔ ነው። ከአንቺ ተለይቶ የሚቆጠር ዘመን የለኝም። አንቺ ባትኖሪልኝ እኔ ምንም ነበርኩ። ሰው የሆንኩት፣ አምላኬን ያወቅኩትና ነፍሴን ያሳረፍኳት በአንቺ ነው።

ዛሬ ነፍሴ ልደቷ ነው። ከአንቺ ተወልዳለችና። ያደረግሽልኝን ለመናገር ቃል አጥቻለሁ። ደግሞስ ከየት ጀምሬ የት አቆመዋለሁ። ብቻ በምድር አብሬሽ መኖሬ አይደለም በሰማይም ከእግርሽ ስር መኖሬ እጅጉን ደስተኛ ያደርገኛል።

ደስተኛይቲ ሆይ ደስ ይበልሽ

◦◉◉Join us on telegram
@MekuriyaM
Forwarded from አቴርሳታ ፕሮሞሽን 📢
የተወለዱበትን ቀን በመምረጥ ፣ ስለራሶ እና ስለቤተሰቦ እንዲሁም ስለ ሀይማኖቶ ይወቁ ፣
Forwarded from አቴርሳታ ፕሮሞሽን 📢
💁‍♂ስለ ሀይማኖቴ ማወቅ ግዴታዬ ነው የሚል የማንኛውም ኦርቶዶክስ ሊቀላቀለው የሚገባ ቻናል።  ጥያቄ ይጠየቃል ምዕመኑም ይሳተፋል ቻናሉን ለመቀላቀል

     🔐ከስር ክፈት የሚለውን
     በመጫን ይቀላቀሉ👇👇👇
Forwarded from አቴርሳታ ፕሮሞሽን 📢
የተወለዱበትን ቀን በመምረጥ ፣ ስለራሶ እና ስለቤተሰቦ እንዲሁም ስለ ሀይማኖቶ ይወቁ ፣
Forwarded from አቴርሳታ ፕሮሞሽን 📢
"እድሜዎ ስንት ነው" ፣ ምን ማረግ አለብኝ በዚ እድሜ?
Forwarded from አቴርሳታ ፕሮሞሽን 📢
የተወለዱበትን ቀን በመምረጥ ፣ ስለራሶ እና ስለቤተሰቦ እንዲሁም ስለ ሀይማኖቶ ይወቁ ፣
Forwarded from ቤተ_ልሔም~Bethelhem (፩ M²)
ይወዳት ነበር። በደንብ አድርጎ ያፈቅራት ነበር። ቀን በቀን እቤቷ ሲመላለስ አየው ስለነበር እቀናበት ነበር። እኔም እጅግ አድርጌ አፈቅራት ነበር። ግን አንድም ቀን እቤቷ ሄጄ አላውቅም። በቃ ይጨንቀኝ ነበር። የእርሱ ብቻ የሚያደርጋት እየመሰለኝ ሌላ ሌላ ነገር ማሰብ ጀምሬ ነበር።

እሚገርማችሁ ነገር፥ ገና ጩጬ እያለኹ ነበር ከእሷ ጋር ፍቅር የያዘኝ። ጓደኛዬም እንደ እኔው ገና ፈላ እያለ ነበር እቤቷ መመላለስ የጀመረው። ይመላለስ እንጂ አንድም ቀን በአካል አይቷት አያውቅም። እንዲሁ በተስፋ ይመላለስ ነበር።

ከዕለታት አንድ ቀን ጓደኛዬ ይዞን ወደ ቤቷ ይወስደኛል። ገና የውጭ መግቢያው ጋር ስደርስ የእርሷ ቤት መሆኑን እንዲሁ ታወቀኝ። ደስ የሚል መዓዛ ይሸትተኝ ጀመር፤ ሰዎች ድምፃቸውን ከፍ አድርገው የእርሷን ስም ሲጠሩ ሰማኹ። ለካ ወዳጇ እኔ ብቻ አልነበርኩም። ከእኔም በላይ አብልጠው የሚሿት ሰዎችም እንደ ነበሩ ገባኝ።

ከዚያማ እኔም ወደ ቤቷ መገስገስ ጀመርኳ! ማን ሊያስቆመኝ? ስለ እርሷ ማወቅ(መማር) ተያያዝኩት። ቀን በቀን ስሟን መጥራት ጀመርኵ። ከትንሽ ዓመታት በኋላ በሌላ አነጋገር ስለ እሷ አወሳ ዘንድ አንደኛው ሰውዬ ነገረኝ። "ምን ብሎ?" አትሉኝም?

"ምን ብሎ?" "ስለ እርሷ መማር በዚህ ብቻ አይደለም። በዜማም ተቀኝተዉላታልና በዜማም ስሟን ጥራት አለኝ።" ጀመርኳ!

ለዚያም ነው... "ማርያም መሠረተ ሕይወት" ብዬ ያዜምኩላት!
ቅኔ ይቀኛሉ መላእክት ከራማ
ተሰጥቶሻልና የመወደድ ግርማ
በእግዚአብሔር ቀኝ የምትቆሚ
ዕጸ ጳጦስ ልመናችንን ስሚ

◦◎● Join us on telegram
@MekuriyaM

Dn Mekuriya Murashe
ዘማሪት ማርያማዊት
ክራር፥ ዲ/ን መኩሪያ

◉◎●Join us on telegram
www.tg-me.com/MekuriyaM
ዘማሪት ምሕረት
ክራር፥ ዲ/ን መኩሪያ

◉◎●Join us on telegram
www.tg-me.com/MekuriyaM
ዘማሪት ማርያማዊት

የአንቺስ ጸጋ የጉድ ነው😍

◉◎●Join us on telegram
    
www.tg-me.com/MekuriyaM
Mastewal
<unknown>
ንነጽር_፸ ||
ስለ ማስተዋል ||
Join us @MekuriyaM
Marfed
<unknown>
⚡️ ንነጽር_፸፩ ||
⚡️ ስለ ማርፈድ ||
⚡️ Join us @MekuriyaM ||
Afelaleg
<unknown>
💫 ንነጽር_፸፪ ||
💫 ስለ አፈላለግ
💫 Join us @MekuriyaM
አመለካከት=Attitude
<unknown>
💫 ንነጽር_፸፫ []
💫 ስለ አመለካከት []
💫 ◦●● Join us
@MekuriyaM []
2024/05/18 08:17:24
Back to Top
HTML Embed Code: