Telegram Web Link
ይነበብ! ይነበብ!

ትብብር!
በኢ/ኦ/ተ/ቤተ-ክርስቲያን በጉራጌ ዞን ሀገረ ስብከት በእዣ ወረዳ በቦዥባር ለሚሠራው ቤተክርስቲያን፥ የቤተክርስቲያኑ ልጆቿ እሑድ ሰኔ 9/2016ዓ.ም ኮልፌ ገነት አዳራሽ የምክክር ጉባኤ አዘጋጅቷል።

በዚህ መርሐግብሩ በተለያየ ምክንያት መታደም ለምይችሉ ወይም ከአዲስ አበባ ውጪ ያሉ ይከታተሉ ዘንድ
Live ለማስተላለፍ ተፈልጓል።

በዚህም መሠረት ቀና የቤተክርስቲያን ልጆች ሙሉ ወይም በከፊል  መሳርያ ያላችሁ ዩቱዩበሮች በዚህ ቀን መርሐግብሩ እንድታስተላልፉ በቅዱስ አማኑኤል ስም እንጠይቃለን።

መስፈርት!
የኦርቶዶክሳዊት ተዋሕዶ ቤተ-ክርስቲያን ሚዲያ መሆን አለበት!

በውስጥ አውሩኝ👇

www.tg-me.com/Proud24
ተማሪዎች ከፈተና በፊት ምን ብለው ይጸልዩ?

ቅዱስ ቄርሎስ ሳድሳዊ ከሚታወቁባቸው በርካታ በጎ ነገሮች አንዱ ለተማሪዎች የነበራቸው ልዩ ፍቅርና ቅርበት ነበረ፡፡ አባ ሚናስ ተብለው ይጠሩ ከነበረበት የምንኩስናቸው ዘመን ጀምሮ አቡኑ በተማሪዎች የተከበቡ ነበሩ፡፡ ከልዩ ልዩ ክፍለ ሀገራት ካይሮ ዩኒቨርሲቲ ሊማሩ ለሚመጡ ተማሪዎች የማደሪያ አገልግሎት በቅዱስ ሚናስ ቤተ ክርስቲያን ውስጥ ይሰጡ ነበር፡፡ ይህ አገልግሎታቸውም በግብፅ ለዘመናዊው ቤተ ክርስቲያንን የሚያካትት የማደሪያ አገልግሎት(church- affiliated dormitory) መወለድ ምክንያት ሆኗል፡፡ የዚህ የማደሪያ አገልግሎት ተጠቃሚዎች የነበሩ ተማሪዎችም ቀሳውስትና ጳጳሳት የቤተ ክርስቲያን መሪዎች ለመሆን በቅተዋል፡፡(ሊቀ ጳጳሱ አቡነ ሳሙኤልና ቅዱስነታቸው አቡነ ሺኖዳ ሣልሳዊተጠቃሽ ናቸው፡፡) በወቅቱ መነኩሴ የነበሩት አባ ሚናስ (አቡነ ቄርሎስ) ለእያንዳንዱ የቤተ ክርስቲያኑ ካህን በተማሪዎቹ መኖሪያ ውስጥ የሥራ ድርሻ ሰጥተው ነበር፡፡ የእርሳቸውን የሥራ ድርሻ ምን እንደነበረ ግን ማንም ሰው አላወቀም ነበር፡፡ በሌሊት በድብቅ የሚሠሩት ሥራ ካህናቱና በቤተ ክርስቲያኑ የሚኖሩ ተማሪዎች የሚጠቀሙበትን መጸዳጃ ቤት ማጽዳት ነበር፡፡

ይህ ለተማሪዎች ያላቸው በጎ አመለካከት በፓትርያርክነት ዘመናቸው አልተለያቸውም፡፡ ተማሪዎች ፈተና ሲደርስባቸው ወደ እርሳቸው እየመጡ ጸልዩልን ይሉአቸው ነበር፡፡ አንዳንድ ተማሪዎች ደግሞ የሚያጠኑበትን መጽሐፍ ይዘው መጥተው ያስባርኩ ነበር፡፡ ቅዱስ አባ ቄርሎስ አንዳንዴ መጽሐፉን ገለጥ ያደርጉና ‹ይህንን አጥኑ› ብለው ይሠጡ ነበር፡፡ የፈተናውም አብዛኛው ጥያቄ ከዚያ ገጽ ይወጣ ነበር፡፡ እንዲሁም ለተማሪዎች ፈተና በሚፈተኑበት ጊዜ የሚገጥማቸውን የመንፈስ ጭንቀትና የአእምሮ ውጥረት በመረዳት የሚከተለውን ከፈተና በፊት የሚጸለይ ጸሎት አዘጋጅተውላቸዋል፡፡

+ ጸሎት +

‹‹ጌታዬ ኢየሱስ ክርስቶስ

‹‹በችግርህ ቀን ጥራኝ ፤ አድንሃለሁ አንተም ታከብረኛለህ›› ብለህ የአንተን መጠጊያነት መፈለግን ስላስተማርከኝ አመሰግንሃለሁ!

አሁንም ጌታ ሆይ! በዚህ የፈተና ሰዓት ጥበብና ማስተዋልን ትሰጠኝ ዘንድ እማጸንሃለሁ፡፡

ይህን ፈተና በሰላም አልፍ ዘንድ ጸጋን (ሞገስን) ስጠኝ፡፡ ፈተናውን በምሠራ ጊዜ ጥልቅ የሆነ ሰላምህንና በረከትህን ስጠኝ፡፡

ጌታዬ ኢየሱስ ውጤት በሚሰጡኝ ጊዜ በመምህራኖቼ ዓይን መወደድን ትሰጠኝና ልባቸውን ታለሰልስልኝ ዘንድ እለምንሃለሁ፡፡ የከበርከው ጌታእኔ ኃጢአተኛ ነኝ ፤ ዓመቱን ሙሉ አንተን ደስ አላሰኘሁህም ፤ ውስጤንም ጭምር ፤ ነገር ግን ከልቤ ደንዳናነትና ከኃጢአቶቼ የተነሣ ሳይሆን ከምሕረትህ እና ከርኅርኄህ የተነሣ እንደትረዳኝ እለምንሃለሁ፡

ጌታ ሆይ ‹‹ለምኑ ይሰጣችኋል፣ እሹ ታገኛላችሁ፤ አንኳኩ ይከፈትላችኋል›› ብለሃል፡፡ እናም እነሆኝ እየለመንኩ ነው፤ የምሕረትህንም ደጅ እያንኳኳሁ ነው፡፡  ‹‹ወደ እኔ የሚመጣውን ከቶ ከእኔ አላወጣውም›› ብለሃልና ጸሎቴን አትናቅ፡፡በቅድስት ድንግልና በመላእክትህ ሁሉ አማላጅነት መልስልኝ!! አሜን!"

ለዘንድሮ ተፈታኝ ተማሪዎች እግዚአብሔር ከእናንተ ጋር ይሁን! የልባችሁን ዓይን ያብራላችሁ! ያጠናችሁትን ይባርክላችሁ

JOIN @MekuriyaM
Forwarded from ቤተ_ልሔም~Bethelhem (፩ Mekuriya Murashe=M²)

🌿 #ንነጽር_፲፩

“ጌታ ቅርብ ነው። በነገር ሁሉ በጸሎትና በምልጃ ከምስጋና ጋር በእግዚአብሔር ዘንድ ልመናችሁን አስታውቁ እንጂ በአንዳች አትጨነቁ።”
  — ፊልጵስዩስ 4፥6

ሐዋርያው "አትጨነቁ" ሲል ምን ማለቱ ነው? እንዴት ነው አለመጨነቅ የምንችለው ብሎ የሚጠይቅ አይጠፋም።
:
በእርግጥ ምንም እሚያስጨንቅ ነገር የለም ማለት አንችልም። ምክንያቱም
#ጭንቀት ባይኖር ኖሮ #አትጨነቁ ባልተባልን ነበር።

እንዲሁ
#አትጨነቁ ብቻ ብሎ ዝም ቢለን፤ ታድያ ምን እናድርግ ማለታችን አይቀርም ነበር። ነገር ግን ከእነ መፍትሔው ስለተቀመጠልን #ጭንቀትን የማስወገድ አቅማችን እጅግ እንዲጨምር ያደርገዋል።

እኛ ለጌታ ሩቅ ብንሆንም እርሱ ለእኛ ቅርብ እንደሆነ ገና ከጅምሩ ተስፋችንን እንዲለመልም አበሠረን። ቀጠለና በክፉም በደጉም ወደ ፈጣሪያችን መጮህ እንዳለብን ነገረን። ምክንያቱም እርሱ ለእኛ ቅርብ ነውና።

#የሚያስጨንቃችኹን ነገር እስኪ ለአንዳፍታ ቆም ብላችኹ አስቡት..... ይሄኔ'ኮ በአላፊ ጠፊ ነገር ትጨነቁ ይሆናል። ግዴ'ለም በጸሎትና በምልጃ ከምስጋናም ጋር ወደ እግዚአብሔር ጩኹ እንጅ በአ ን ዳ ች #አትጨነቁ
አንድ ሰው ሲጨነቅ እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር መሆኑን እየተጠራጠረ ነው ወይም አያምንም ማለት ነው።

አንድ ሰው ሲጨነቅ በእግዚአብሔር ቃል ይጠራጠራል ወይም ማመን ከብዶታል ማለት ነው። ብዙ ጊዜ ተጨንቀን እናውቃለን። ይህን ቃል ሥናስታውስ ግን ጭንቀታችን እንደሚቀል 100% እርግጠኛ ነኝ።

ይህን በመሰለው ግን
#መጨነቅ ይገባናል እላለኹ👇

“በብዙ መከራና ከልብ ጭንቀት በብዙም እንባ ጽፌላችሁ ነበርና፤ ይህም እናንተን አብዝቼ የምወድበትን ፍቅር እንድታውቁ እንጂ እንዳሳዝናችሁ አይደለም።”
  — 2ኛ ቆሮ 2፥4

JOIN
@MekuriyaM
ተቀባበሉ እኮ😂

"ብዙ ሰዎች "Facebook" ን የሚጠቀሙት ትምህርት አዘል ጽሑፎችን ከማንበብ ይልቅ Photo ብቻ ዓይተው ለመውጣት ነው። እኔ "Telegram'ን" የሚጠቀሙኝ ግን ከ Photo ይልቅ ትምህርት አዘል ጽሑፎችን ለማንበብ እንደሆነ ጓደኛዬ "WhatsApp" በቂ መረጃዬ ነው።"

👉 "WhatsApp" "አዎ እውነት ነው በዚህ ሐሳብ እኔም እስማማለኹ፤ የእኔም ዕይታ ነው የተናገርሺው። ግን እስኪ "Instagram" የተለየ ሐሳብ ካላት ትጠየቅ።"

👉 "Instagram" " ኧረ ምንም የተለየ ሐሳብ የለኝም "Telegram" ያነሣችው ሐሳብ እኔንም ያስማማኛል።" ምናልባት ግን "Imo" ሐሳቤን አልተጠየቅኩም ብላ ለ "Fb" እንዳታደላ እሷም ትጠየቅ።"

👉 "Imo" "ኧረ በጭራሽ አላዳላም እንደ "Telegram" ዓይነት ያለ ድንቅ ነገር ከየት ተገኝቶ ነው ጓድ?" ልሎች ጓደኞቻችን በሌላ ጊዜ ሐሳባቸውን ይስጡ እስኪ አሁን እራሷ "Facebook" ትጠየቅ።"

👉"Facebook" "እሺ ዕድሉ ስለተሰጠኝ አመሰግናለሁ በመጀመርያ ደረጃ ሁላችሁም ሐሳብ ስትሰጡ እኔስ ምንድነኝ ብላችሁ አመዛዝናችሁ የሚመለከታችሁን መልስ ለመስጠት ሞክሩ። ሲቀጥል "ወ/ሪት "Telegram" ያነሳሽው ጉዳይ ጥሩ ነው። ነገር ግን ጓደኞችሽን ከመጠየቅሽ በፊት እኔን ብትጠይቂኝ ከእኔ አንቺ እንደምትሻዪኝ እነግርሽ ነበር። ስለዚህ እኔም የአንቺ ትልቅነት እመሰክራለሁ ማንም አይደርስብሽም። ሌሎቹን ግን እንደ እኔ አቅም ሳይኖራቸው፤በእኔ ላይ የሚደነፉት ነገር ብታቆሚልኝ መልካም ነው።"

😍"Telegram" እሺ አቶ "Facebook" ጥሩ ተናግረሃል ከጓደኞቼ ግን እንደ እኔ እንደ እኔ አንተ የምትሻል ይመስለኛል። ግን ከ "Photo" ይልቅ ጽሑፍ ላይ ብትሠራ ይሻልሃል። አስተማሪውም አስተማሪ ያልሆነውንም "Photo" ከሚለቀቅብህ መልካም መልካሙን እንዲለቀቅብህ ብታደርግ እላለሁ። በሌላ ጊዜ ደግሞ በሌላ ርዕስ የምንገናኝ ይሆናል። በሰላም ግቡ።

Join us on telegram
www.tg-me.com/MekuriyaM
Dn Mekuriya Murashe4
<unknown>
#አምላክ_የጠራቸው

ከተለያየ መስክ አምላክ የጠራቸው
በቃሉ የጸኑ ሐዋርያት ናቸው
ትቷቸው ሲያርግ የተደናገጡ
ወደ ተዘጋ ቤት ገብተው ተቀመጡ
መሄጃችን የት ነው ብለው ሲረበሹ
አጽናኙ መንፈስ ወርዷል ወደ እነርሱ
ኹሉም ተዘጋጁ ታጥቀው በወንጌሉ
በዓለሙ ቋንቋ ዞረው ሊያስተምሩ
አምላክም አላቸው ኁሩ ወመሀሩ
ሱባኤውም ገቡ እንዲጠነክሩ
ጾማቸው ጨርሰው በዓለም ተበተኑ
አልጫውን ዓለም በወንጌል አቀኑ
ዞረው ሲያስተምሩ መከራን ታገሱ
ደማቸው አፍሰው ምድሪቷን ቀደሱ
ዛሬም በመንፈስ ከጎናችን አሉ
በቃል ኪዳናቸው ትውልድ ያጽናናሉ

Dn Mekuriya Murashe
“አምላክ በእልልታ፥ እግዚአብሔር በመለከት ድምፅ ዐረገ።”
— መዝሙር 47፥5

“ጌታ ኢየሱስም ከእነርሱ ጋር ከተናገረ በኋላ ወደ ሰማይ ዐረገ በእግዚአብሔርም ቀኝ ተቀመጠ።”
— ማርቆስ 16፥19

“ሲባርካቸውም ከእነርሱ ተለየ ወደ ሰማይም ዐረገ።”
— ሉቃስ 24፥51

Join us on telegram
www.tg-me.com/MekuriyaM

❝አንዱ ፈረንጅ ነው አሉ...አንድ ጥናት ሊያጠና ወደ ኢትዮጵያ ይመጣል ጥናቱን እያጠናም ኢትዮጵያውያን ለድንግል ማርያም ያለን ፍቅር በጣም ያስገርመው ነበር፤

በየሔደበት የሀገራችን ክፍል ሁሉ ሕፃናት በጨዋታ መኻል 'የማርያም መንገድ ስጠኝ' ሲሉ፣ እናቶች ሲወልዱ 'ማርያም ማርያም' ሲሉ፣ የወላድ ጠያቂዎችም 'እንኳን ማርያም ማረችሽ' ሲሉ፣ የኔ ቢጤ ሲለምን 'በእንተ ማርያም' ሲል፣ ሰውነት ላይ ያለ ጥቁር ምልክት ሲታይ 'ማርያም የሳመችኝ' ተብሎ ሲገለጽ....ይሰማል  ያያል።

እናም 'እነዚህ ሰዎች ለማርያም ምን ያክል ፍቅር ቢኖራቸው ነው' እንዲህ የሚሉትና የሚያደርጉት ብሎ ተደነቀ።

በመጨረሻም ጥናቱን አጠቃሎ ወደ መጣበት ሲመለስ፦ "ኢትዮጵያውያን ከአካል ክፍላቸው አንዱ ቦታ ቢቆረጥና ቢደማ በደማቸው ውስጥ 'ማርያም ማርያም ማርያም' የሚል ጽሁፍ ተጽፎ ይገኛል" አለ ይባላል፡፡❞

●●●Join us on telegram
@MekuriyaM
Forwarded from አቴርሳታ ፕሮሞሽን 📢
💕ከዘማሪያን የማንን መዝሙር ማዳመጥ ይ ፈ ል ጋ ሉ ? 🔔 💕

┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕 ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ 💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
[┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕 ሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉ💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕 ሊቀ መዘምራን ኪነጥበብ 💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕 ዘማሪ አቤል መክብብ 💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕ዘማሪት ሲስተር ህይወት ተፈራ💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕ዘማሪ ዲያቆን ሙሉቀን ከበደ💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕 ቀሲስ ምንዳዬ ብርሃኑ 💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕 ዘማሪት ፋሲካ ድንቁ 💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛

🌷 👥 የሁሉንም ዘማሪያን መዝሙር ለማግኘት 🔔 👇
🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧
Forwarded from አቴርሳታ ፕሮሞሽን 📢
💕ከዘማሪያን የማንን መዝሙር ማዳመጥ ይ ፈ ል ጋ ሉ ? 🔔 💕

┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕 ሊቀ መዘምራን ቴዎድሮስ ዮሴፍ 💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
[┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕 ሊቀ መዘምራን ይልማ ኃይሉ💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕 ሊቀ መዘምራን ኪነጥበብ 💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕 ዘማሪ አቤል መክብብ 💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕ዘማሪት ሲስተር ህይወት ተፈራ💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕ዘማሪ ዲያቆን ሙሉቀን ከበደ💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕 ቀሲስ ምንዳዬ ብርሃኑ 💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛
┏•••••••••••••••••••••••••••••••┓
💕 ዘማሪት ፋሲካ ድንቁ 💕
┗•••••••••••••••••••••••••••••••┛

🌷 👥 የሁሉንም ዘማሪያን መዝሙር ለማግኘት 🔔 👇
🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧🫧
2024/06/16 00:42:09
Back to Top
HTML Embed Code: