Telegram Web Link
በጋ መቅረቡን፥ ከበለስ ተምሬ።
ጣፋጭ አድርጎልኝ፥ የዘመኔን ፍሬ፤
ከማሰናከያው፥ አምልጣለች ነፍሴ፤
በምህረት መክሮኛል፥ አባቴ ንጉሴ።
የደሙ ግርግዳ፥ ቅጥሬን እያሰፋ፤
የልቤን መባዘን፥ አስታጥቆታል ተስፋ።
+++++++
©ታዜና
#መንፈሳዊ_ግጥሞች
www.tg-me.com/Menfesawigetmoch
እጅግ በርቻለሁ፥ ከትናንቱ ዛሬ
ቅኔ ሞልቶት ልቤን፥ ለስምህ ዘምሬ።
የምፈራው ሁሉ፥ ፈርቶህ እያለፈ፤
ያመንኩበት ስምህ፥ ሞቴን አሸነፈ።
አዲስ ሆኖልኛል፥ የህይወት ጎዳና፤
ክንድህ ነው ብርታቴ፥ ጉልበቴን ያፀና።
ቅጥልጥል ሀሳቤን፥ በአንድ የጠቀለልከው፤
አይን አልባ ግንባሬን፥ ብርሀን የሸለምከው።
አንተ ነህ በቃልህ፥ አልጋዬን ያስያዝከኝ፤
ርግማኔን ሽረህ፥ ከድንጋይ ያዳንከኝ።
መስቀልህ መስቀሌን፥ ሲሰቅልኝ ጌታ፤
ይኖራል ሲገርመኝ፥ የፍቅርህ ውለታ።
የሰላሜ አለቃ፥ የልቤ ንጉስ፥
የድንግል ማርያም፥ ልጅ ክበር ኢየሱስ።
+++++++
©ታዜና
#መንፈሳዊ_ግጥሞች
www.tg-me.com/Menfesawigetmoch
ማዳኑ ቀድማ፥ ቁጣው ዘገየ፤
ህይወታችንን፥ በምህረት አየ።
የሚጠበቀን፥ ቀስት የወጠረ፤
አሳጃችን፥ ፈርኦን አፈረ።
ፍርሀታችንን፥ እምነት ውጦታል፤
ኩነኔያችንን፥ ሞቱ ሰቅሎታል።
+++++++
©ታዜና
#መንፈሳዊ_ግጥሞች
www.tg-me.com/Menfesawigetmoch
Forwarded from እልመስጦአግያ+++ (Tazena /ታዜና/)
የሰማዩ ጌታ፥ የምድር ባለቤት፤
ከኔጋራ ባይሆን፥ ባይገባ በኔ ቤት።
ከፅድቁ ጎዳና፥ ህይወቴ ተረስታ፤
አልኖርም ነበረ፥ ነፍሴ ነፍሷን አጥታ።
+++++++++++++++++++++++
#መንፈሳዊ_ግጥሞች ©ታዜና
www.tg-me.com/Menfesawigetmoch

@JohnDPT27
@Learn_with_John
የፀሀይን መውጫ፣እዩ ምስራቅን፤
ቀራንዮ ውሎ፣ገልጧል ወንጌሉን
ገነትን አሳየን፣ቤተክርስቲያን ሰርቶ፤
አምስቱን ምስራቆች፥እንዳትረሱ ከቶ
+++++++++++++++++++++++
#መንፈሳዊ_ግጥሞች ©ታዜና
www.tg-me.com/Menfesawigetmoch
@JohnDPT27
@Learn_with_John
+++እንኳን ለቅዱስ ሚካኤል
ክብረ በአል አደረሳችሁ+++

——ሚካኤል——
ዳንኤል ተናገር፣ ባህራን ተናገር፤
ሚካኤል ሲመጣ፣ የሆነውን ነገር፡፡
የአንበሳውን ጉድጓድ፣ ምሰጋና ሞልቶታል፤
የሞቱን ደብዳቤ፣ ህይወት ዘርቶበታል፡፡

የሞት ጽሁፍ ይዤ፣ ወደ ሀገሬ ስሄድ፤
የሚታደግ መላክ፣ ጠበቀኝ ከመንገድ፡፡
ሚካኤል ወዳጄ፣ ፍርዴን ለውጦታል፤
የሞቴን ቀዶ ጥሎ፣ ሰርጌን ደግሶታል፡፡

የዳንኤል ወዳጅ፣ ለኔም ወዳጄ ነው፤
የአንበሶቹን አፍ በሰይፍ የዘጋ ነው፡፡
የኔንም ነካሾች፣ አጥፍቶ በሰይፉ፤
የተራቡ አንበሶች፣ ሳይነኩኝ አለፉ፡፡

+++++++++++++++++++++++
#መንፈሳዊ_ግጥሞች
©ታዜና
https://www.tg-me.com/Menfesawigetmoch
ጸልዩ
ለሰው የሚበቃ፥ ተስፋ እንዳልነበረ
በሚያልፍ ፈተና፥ልብህ ተሰበረ
ፀሎትህ ከቆመ፥ ብዙ ቀን አለፈ፤
ውስጥህ የነበረው፥ ጽናት ተሸነፈ።
ሰላምህ ወጣና፥ ስጋት ያዘቦታ፤
አይምሮህ ተቃኘ፥ ዓለም ከፍታ።

ሰላም የሚመልስ፥ የሚሰጥ ጽናት
ውዳሴ ማርያም ነው፥ መዝሙረ ዳዊት
ቁመህ ፀልይና፥ ልብህን መልሰው፤
የቆሰለን ተስፋ፥ በቃሉ ፈውሰው።
+++++++++++++++++++++++
“ወደ ፈተና እንዳትገቡ ትጉና ጸልዩ።”
— ማቴዎስ 26፥41
+++++++++++++++++++++++
©ታዜና
#መንፈሳዊ_ግጥሞች
www.tg-me.com/Menfesawigetmoch

@JohnDPT27
@Learn_with_John
በስደት ኑሮ፥ በምድረ በዳ፤
ምርኩዝ የሆነኝ፥ ልጁን የረዳ፡፡
እንባዬን ጠርጎ ፥ቢያለቅሱ አይኖቼ፤
በርትቷል ልቤ፥ ጎኑን አይቼ፡፡

ይመጣል እግሬ፥ አይቀርም ሄዶ፤
አይረሳም ቤቱን፥ ሌላ ቤት ለምዶ፡፡
ብለይ ከቤቴ፥ ከወዳጅ ዘመድ፤
እጅግ ርቆ፥ እግሬ ቢሰደድ፡፡
ያባቴ ወንጌል፥ ያበረታኛል ፤
ከማውቃት ሀገር፥ ይመልሰኛል፡፡
+++++++++++++++++++++++
©ታዜና
#መንፈሳዊ_ግጥሞች
Telegram👇👇👇👇
www.tg-me.com/Menfesawigetmoch
ኪዳነምህረት፲፮
በእሾህ የታጠረው፥ ተከፍቶ መንገዱ፤
የሀሰት ዳኝነት፥ ተለውጦ ፍርዱ።
በረዳትነቷ፥ ወጣሁኝ በደህና፤
ኪዳነ ምህረት ፥ዋስ ጠበቃ ሆና።
+++++
©ታዜና #መንፈሳዊ_ግጥሞች
በቴሌግራም ይከታተሉን
www.tg-me.com/Menfesawigetmoch
መንገድ ላይ እንዳልቀር፥ በረሀ ተርቤ፤
ተስፋን እየሞላ፥ በታካቹ ልቤ፤
አለቱን በበትር፥ ሰኝጥቆ አፈለቀ፤
የሚያስጨንቁኝን፥ በውሀ አስጨነቀ።
+++++
©ታዜና #መንፈሳዊ_ግጥሞች
በቴሌግራም ይከታተሉን
www.tg-me.com/Menfesawigetmoch
የንጉስ ጭካኔ ፥ ክንዱ ቢበረታ፤
ለጣዖት ሳንሰግድ፥ እኛ ሳንረታ፡፡
የምናምነው አምላክ፥ ሊያድነን ወደደ፤
ገብርኤል መጣና፥ እሳቱ በረደ፡፡

ፍላፃና ሠይፉን፥ አጠፈው መላኩ፤
ሰላም ይዞ መጣ፥ ባለም ለታወኩ፡፡
አትጠራጠሩ፥ ምልጃው ያስምረናል፤
የሚነደው እሳት፥ ሳይነካን ወተናል፡፡

የሰልስቱ ደቂቅ፥ የእጠሉጣ ብርታት፤
የድንግል አብሳሪ፥ የቂርቆስ ረዳት፡፡
በሚመጣው አለም፥ እንዳይበላኝ እሳት፤
አማልደኝ ከጌታ፥ ነፍሴን እንዲምራት፡፡

የነገርኩህ ሁሉ፥ በቀኑ ደረሰ ፤
በዘብር ገብርኤል፥ እንባዬ ታበሰ፡፡
ና ልጄ ስትለኝ፥ አልልህም እንቢ፤
ስለቴን ተቀበል፥ አባቴ ቁልቢ፡፡

የልቤን ነግሬህ፥ የቁልቢው ገብርኤል፤
ሳትረሳ ፈፀምከው፥ ስለቴን ተቀበል፡፡
ለንግስ እንመጣለን፥ አንተ አትረሳምና፤
ደሞ የዛሬ አመት፥ አድርሰን በደህና፡፡
+++++++
©ታዜና
#መንፈሳዊ_ግጥሞች
www.tg-me.com/Menfesawigetmoch
የንጉስ ጭካኔ ፥ ክንዱ ቢበረታ፤
ለጣዖት ሳንሰግድ፥ እኛ ሳንረታ፡፡
የምናምነው አምላክ፥ ሊያድነን ወደደ፤
ገብርኤል መጣና፥ እሳቱ በረደ፡፡

ፍላፃና ሠይፉን፥ አጠፈው መላኩ፤
ሰላም ይዞ መጣ፥ ባለም ለታወኩ፡፡
አትጠራጠሩ፥ ምልጃው ያስምረናል፤
የሚነደው እሳት፥ ሳይነካን ወተናል፡፡

የሰልስቱ ደቂቅ፥ የእጠሉጣ ብርታት፤
የድንግል አብሳሪ፥ የቂርቆስ ረዳት፡፡
በሚመጣው አለም፥ እንዳይበላኝ እሳት፤
አማልደኝ ከጌታ፥ ነፍሴን እንዲምራት፡፡

የነገርኩህ ሁሉ፥ በቀኑ ደረሰ ፤
በዘብር ገብርኤል፥ እንባዬ ታበሰ፡፡
ና ልጄ ስትለኝ፥ አልልህም እንቢ፤
ስለቴን ተቀበል፥ አባቴ ቁልቢ፡፡

የልቤን ነግሬህ፥ የቁልቢው ገብርኤል፤
ሳትረሳ ፈፀምከው፥ ስለቴን ተቀበል፡፡
ለንግስ እንመጣለን፥ አንተ አትረሳምና፤
ደሞ የዛሬ አመት፥ አድርሰን በደህና፡፡
+++++++
©ታዜና
#መንፈሳዊ_ግጥሞች
Join👇👇👇👇👇👇👇👇
www.tg-me.com/Menfesawigetmoch
ሀጢያትን ለመተው ዛሬ ለመወሰን
ለመስበር ድንበሩን የበደልን ወሰን
የትናንት ታሪክ ታሪክ ሆኖ እንዲቀር
የሀጢያትን ሽቶ በፊቱ ለመስበር
አንድ ነው መንገዱ
ከመንገዶቹ አንዱ
ራስን ለካህን በደንበ አሳይቶ
እንደገና ማበብ በንሰሀ ፈክቶ
ሁሉን ለትጠቀልል መንግስቱ ቀርባለች
ንሰሀ ገብታችሁ ጠብቁኝ ትላለች
+++++++
©ታዜና
#መንፈሳዊ_ግጥሞች
Join👇👇👇👇👇👇👇👇
www.tg-me.com/Menfesawigetmoch
አልጠራጠርም
ሰማይን መዘርጋት ምድርን መፍጠርህን
አካሌን ከአፍር ማበጃጀትህን
አልጠራጠርም አምላኬ ስራህን

አጥንቶቼ ባንተ ፀንተው መቆማቸው
አይኖቼ በተስፋ ነገን ማየታቸው
ጆሮቼ መልካሙን ወሬ መስማታቸው
አልጠራጠርም ያንተ ስራ ናቸው

የእድሜ ቀኖቼ በሰላም ቢቀኑ
አልጠራጠርም ባርከህ ነው ዘመኑን
ደግሞ ስለፍቅር መሞት መቁሰልህን
በደሌን ልትሽር ቤዛ መሆንህን
መቃብርን ዘግተህ እኔን ማዳንህን
አልጠራጠርም አምላኬ ፍቅርህን
+++++
©ታዜና #መንፈሳዊ_ግጥሞች
በቴሌግራም ይከታተሉን
www.tg-me.com/Menfesawigetmoch
2025/07/01 00:46:38
Back to Top
HTML Embed Code: