“እነሆም ከዋነኞቹ አለቆች አንዱ ሚካአል ሊረዳኝ መጣ” (ዳን. ፲፥፲፫). ሚካኤል ማለት በዕብራይስጥ “መኑ ከመ አምላክ፤ ማን እንደ እግዚአብሔር” ማለት ነው፡፡
https://www.tg-me.com/Mesle_Fikur_Welda
https://www.tg-me.com/Mesle_Fikur_Welda
❤3
#የመስከረም_16_ግጻዌ
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
#መስከረም_16_ቀን_በቅዳሴ_ሰዓት_የሚነበቡት_መልእክታት👇
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
1ኛ ቆሮንቶስ 3
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹⁰ የእግዚአብሔር ጸጋ እንደ ተሰጠኝ መጠን እንደ ብልሃተኛ የአናጺ አለቃ መሠረትን መሠረትሁ፥ ሌላውም በላዩ ያንጻል። እያንዳንዱ ግን በእርሱ ላይ እንዴት እንዲያንጽ ይጠንቀቅ።
¹¹ ከተመሠረተው በቀር ማንም ሌላ መሠረት ሊመሠርት አይችልምና፥ እርሱም ኢየሱስ ክርስቶስ ነው።
¹² ማንም ግን በዚህ መሠረት ላይ በወርቅ ቢሆን በብርም በከበረ ድንጋይም በእንጨትም በሣርም ወይም በአገዳ ቢያንጽ፥ የእያንዳንዱ ሥራ ይገለጣል፤
¹³ በእሳት ስለሚገለጥ ያ ቀን ያሳያልና፥ የእያንዳንዱም ሥራ እንዴት መሆኑን እሳቱ ይፈትነዋል።
¹⁴ ማንም በእርሱ ላይ ያነጸው ሥራ ቢጸናለት ደመወዙን ይቀበላል፤
¹⁵ የማንም ሥራ የተቃጠለበት ቢሆን ይጎዳበታል፥ እርሱ ራሱ ግን ይድናል ነገር ግን በእሳት እንደሚድን ይሆናል።
¹⁶ የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ እንደ ሆናችሁ የእግዚአብሔርም መንፈስ እንዲኖርባችሁ አታውቁምን?
¹⁷ ማንም የእግዚአብሔርን ቤተ መቅደስ ቢያፈርስ እግዚአብሔር እርሱን ያፈርሰዋል፤ የእግዚአብሔር ቤተ መቅደስ ቅዱስ ነውና፥ ያውም እናንተ ናችሁ።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
ያዕቆብ 1
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹⁹ ስለዚህ፥ የተወደዳችሁ ወንድሞቼ ሆይ፥ ሰው ሁሉ ለመስማት የፈጠነ ለመናገርም የዘገየ ለቍጣም የዘገየ ይሁን፤
²⁰ የሰው ቍጣ የእግዚአብሔርን ጽድቅ አይሠራምና።
²¹ ስለዚህ ርኵሰትን ሁሉ የክፋትንም ትርፍ አስወግዳችሁ፥ ነፍሳችሁን ማዳን የሚችለውን በውስጣችሁም የተተከለውን ቃል በየዋህነት ተቀበሉ።
²² ቃሉን የምታደርጉ ሁኑ እንጂ ራሳችሁን እያሳታችሁ የምትሰሙ ብቻ አትሁኑ።
²³ ቃሉን የሚሰማ የማያደርገውም ቢኖር የተፈጥሮ ፊቱን በመስተዋት የሚያይን ሰው ይመስላል፤
²⁴ ራሱን አይቶ ይሄዳልና፥ ወዲያውም እንደ ምን እንደ ሆነ ይረሳል።
²⁵ ነገር ግን ነጻ የሚያወጣውን ፍጹሙን ሕግ ተመልክቶ የሚጸናበት፥ ሥራንም የሚሠራ እንጂ ሰምቶ የሚረሳ ያልሆነው፥ በሥራው የተባረከ ይሆናል።
²⁶ አንደበቱን ሳይገታ ልቡን እያሳተ እግዚአብሔርን የሚያመልክ የሚመስለው ማንም ቢኖር የእርሱ አምልኮ ከንቱ ነው።
²⁷ ንጹሕ የሆነ ነውርም የሌለበት አምልኮ በእግዚአብሔር አብ ዘንድ ይህ ነው፤ ወላጆች የሌላቸውን ልጆች ባልቴቶችንም በመከራቸው መጠየቅ፥ በዓለምም ከሚገኝ እድፍ ሰውነቱን መጠበቅ ነው።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
ሐዋርያት 15
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹³ እነርሱም ዝም ካሉ በኋላ ያዕቆብ እንዲህ ብሎ መለሰ፦ ወንድሞች ሆይ፥ ስሙኝ።
¹⁴ እግዚአብሔር ለስሙ የሚሆንን ወገን ከአሕዛብ ይወስድ ዘንድ አስቀድሞ እንዴት እንደ ጐበኘ ስምዖን ተርኮአል።
¹⁵ ከዚህም ጋር የነቢያት ቃል ይሰማማል፥ እንዲህ ተብሎ እንደ ተጻፈ፦
¹⁶-¹⁷ ከዚህ በኋላ የቀሩት ሰዎችና በስሜ የተጠሩት አሕዛብ ሁሉ ጌታን ይፈልጉ ዘንድ እመለሳለሁ፥ የወደቀችውንም የዳዊትን ድንኳን እንደ ገና እሠራታለሁ፥ ፍራሽዋንም እንደ ገና እሠራታለሁ እንደ ገናም አቆማታለሁ ይላል ይህን የሚያደርግ ጌታ።
¹⁸ ከጥንት ጀምሮ ሥራው ሁሉ በእግዚአብሔር ዘንድ የታወቀ ነው።
¹⁹ ስለዚህ ከአሕዛብ ወደ እግዚአብሔር የዞሩትን እንዳናስቸግራቸው፥
²⁰ ነገር ግን ከጣዖት ርኵሰትና ከዝሙት ከታነቀም ከደምም ይርቁ ዘንድ እንድንጽፍላቸው እቈርጣለሁ።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
#መስከረም_16_ቀን_በቅዳሴ_ሰዓት_የሚነበበው_የሚዜመው_የቅዳሴ_ምስባክ👇
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
"ዕቤ አዐቅብ አፋየ ከመ ኢይስሐት በልሳንየ። ወአንበርኩ ዐቃቤ ለአፉየ። ሶበ ይትቃወሙኒ ኀጥአን ቅድሜየ"። መዝ. 38(39)፥1-2
#ትርጉም፦ "በአንደበቴ እንዳልስት መንገዴን እጠብቃለሁ፤ ኃጢአተኛ በፊቴ በተቃወመኝ ጊዜ በአፌ ላይ ጠባቂ አኖራለሁ አልሁ።
ከዝምታ የተነሣ እንደ ዲዳ ሆንሁ፥ ለበጎ እንኳ ዝም አልሁ፥ ቍስሌም ታደሰብኝ"። መዝ. 38(39)፥1-2
ወይም👇
"አሠንያ እግዚኦ በሥምረትከ ለጽዮን። ወይትሐነፃ አረፋቲሃ ለኢየሩሳሌም። አመ ትሠምር መሥዋዕተ ጽድቅ"። መዝ. 50(51)÷18-19
#ትርጉም፦ "አቤቱ፥ በውዴታህ ጽዮንን አሰማምራት፤ የኢየሩሳሌምንም ቅጽሮች ሥራ። የጽድቁን መሥዋዕት መባውንም የሚቃጠለውንም መሥዋዕት በወደድህ ጊዜ፥ ያን ጊዜ በመሠዊያህ ላይ ፍሪዳዎችን ይሠዋሉ"። መዝ. 50(51)÷18-19
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
#መስከረም_16_ቀን_የእለቱን_ወንጌል_እናንብብ📖👇
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
ዮሐንስ 9
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
¹ ሲያልፍም ከመወለዱ ጀምሮ ዕውር የሆነውን ሰው አየ።
² ደቀ መዛሙርቱም፦ መምህር ሆይ፥ ይህ ሰው ዕውር ሆኖ እንዲወለድ ኃጢአት የሠራ ማን ነው? እርሱ ወይስ ወላጆቹ? ብለው ጠየቁት።
³ ኢየሱስም እንዲህ ብሎ መለሰ፦ የእግዚአብሔር ሥራ በእርሱ እንዲገለጥ ነው እንጂ እርሱ ወይም ወላጆቹ ኃጢአት አልሠሩም።
⁴ ቀን ሳለ የላከኝን ሥራ ላደርግ ይገባኛል፤ ማንም ሊሠራ የማይችልባት ሌሊት ትመጣለች።
⁵ በዓለም ሳለሁ የዓለም ብርሃን ነኝ።
⁶ ይህን ብሎ ወደ መሬት እንትፍ አለ በምራቁም ጭቃ አድርጎ በጭቃው የዕውሩን ዓይኖች ቀባና።
⁷ ሂድና በሰሊሆም መጠመቂያ ታጠብ አለው፤ ትርጓሜው የተላከ ነው። ስለዚህ ሄዶ ታጠበ እያየም መጣ።
⁸ ጐረቤቶቹም ቀድሞም ሲለምን አይተውት የነበሩ፦ ይህ ተቀምጦ ይለምን የነበረ አይደለምን? አሉ።
⁹ ሌሎች፦ እርሱ ነው አሉ፤ ሌሎች፦ አይደለም እርሱን ይመስላል እንጂ አሉ፤ እርሱ፦ እኔ ነኝ አለ።
¹⁰ ታድያ፦ ዓይኖችህ እንዴት ተከፈቱ? አሉት።
¹¹ እርሱ መልሶ፦ ኢየሱስ የሚባለው ሰው ጭቃ አድርጎ አይኖቼን ቀባና፦ ወደ ሰሊሆም መጠመቂያ ሄደህ ታጠብ አለኝ፤ ሄጄ ታጥቤም አየሁ አለ።
ወይም👇
ዮሐንስ 10
¯¯¯¯¯¯¯¯¯¯
²² በኢየሩሳሌምም የመቅደስ መታደስ በዓል ሆነ፤
²³ ክረምትም ነበረ። ኢየሱስም በመቅደስ በሰሎሞን ደጅ መመላለሻ ይመላለስ ነበር።
²⁴ አይሁድም እርሱን ከበው፦ እስከ መቼ ድረስ በጥርጣሪ ታቆየናለህ? አንተ ክርስቶስ እንደ ሆንህ ገልጠህ ንገረን አሉት።
²⁵ ኢየሱስም መለሰላቸው፥ እንዲህ ሲል፦ ነገርኋችሁ አታምኑምም እኔ በአባቴ ስም የማደርገው ሥራ ይህ ስለ እኔ ይመሰክራል፤
²⁶ እናንተ ግን እንደ ነገርኋችሁ ከበጎቼ ስላልሆናችሁ አታምኑም።
²⁷ በጎቼ ድምፄን ይሰማሉ እኔም አውቃቸዋለሁ ይከተሉኝማል፤
²⁸ እኔም የዘላለም ሕይወትን እሰጣቸዋለሁ፥ ለዘላለምም አይጠፉም፥ ከእጄም ማንም አይነጥቃቸውም።
²⁹ የሰጠኝ አባቴ ከሁሉ ይበልጣል፥ ከአባቴም እጅ ሊነጥቃቸው ማንም አይችልም።
³⁰ እኔና አብ አንድ ነን።
³¹ አይሁድ ሊወግሩት ደግመው ድንጋይ አነሡ።
³² ኢየሱስ፦ ከአባቴ ብዙ መልካም ሥራ አሳየኋችሁ፤ ከእነርሱ ስለ ማናቸው ሥራ ትወግሩኛላችሁ? ብሎ መለሰላቸው።
³³ አይሁድም፦ ስለ መልካም ሥራ አንወግርህም፤ ስለ ስድብ፤ አንተም ሰው ስትሆን ራስህን አምላክ ስለ ማድረግህ ነው እንጂ ብለው መለሱለት።

³⁴ ኢየሱስም እንዲህ ብሎ መለሰላቸው፦ እኔ፦ አማልክት ናችሁ አልሁ ተብሎ በሕጋችሁ የተጻፈ አይደለምን?
³⁵ መጽሐፉ ሊሻር አይቻልምና እነዚያን የእግዚአብሔር ቃል የመጣላቸውን አማልክት ካላቸው፥
³⁶ የእግዚአብሔር ልጅ ነኝ ስላልሁ እናንተ አብ የቀደሰውን ወደ ዓለምም የላከውን፦ ትሳደባለህ ትሉታላችሁን?
³⁷ እኔ የአባቴን ሥራ ባላደርግ አትመኑኝ፤
³⁸ ባደርገው ግን፥ እኔን ስንኳ ባታምኑ አብ በእኔ እንደ ሆነ እኔም በአብ እንደ ሆንሁ ታውቁና ታስተውሉ ዘንድ ሥራውን እመኑ።
³⁹ እንግዲህ ደግመው ሊይዙት ፈለጉ፤ ከእጃቸውም ወጣ።
⁴⁰ ዮሐንስም በመጀመሪያ ያጠምቅበት ወደ ነበረው ስፍራ ወደ ዮርዳኖስ ማዶ እንደ ገና ሄደ በዚያም ኖረ።
⁴¹ ብዙ ሰዎችም ወደ እርሱ መጥተው፦ ዮሐንስ አንድ ምልክት ስንኳ አላደረገም፥ ነገር ግን ዮሐንስ ስለዚህ ሰው የተናገረው ሁሉ እውነት ነበረ አሉ።
⁴² በዚያም ብዙዎች በእርሱ አመኑ።
✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️✝️
የሚቀደሰው ቅዳሴ #ቅዳሴ_እግዚእነ ነው። መልካም የቅዱስ ዕፀ መስቀል የደመራ በዓል ለሁላችንንም ይሁንልን።

❤1
Rich:
የጨረስነው የጽድቅ አኗኗር ያለና መጉደል እንደሌለ እኮ ነው በኃጢአት ዘምተን የምንኖረው ያስገርማል።
ያለን ጊዜ እንኳን ኃጢአትና ክፋት በራሳችን እና በሰው ላይ ሰርተን ቀርቶ የምንናፍቀውን ብዙ መልካም ነገር አድርገን እንኳን ለመኖር በቂ አይደለም።
ይብቃን!
የተሸከምነውን መስቀል ይበልጥ እንዲከብደን ካደረጉት አንዱ ይኸው ነው!
“መንግስተ እግዚአብሔርን የምትወርሰው የክርስቶስን መስቀል አንተ ተሸክመህ ሌላው እንዲጥሉ አድርገህ አይደለም”
አባ አርምሞ
https://www.tg-me.com/Mesle_Fikur_Welda
የጨረስነው የጽድቅ አኗኗር ያለና መጉደል እንደሌለ እኮ ነው በኃጢአት ዘምተን የምንኖረው ያስገርማል።
ያለን ጊዜ እንኳን ኃጢአትና ክፋት በራሳችን እና በሰው ላይ ሰርተን ቀርቶ የምንናፍቀውን ብዙ መልካም ነገር አድርገን እንኳን ለመኖር በቂ አይደለም።
ይብቃን!
የተሸከምነውን መስቀል ይበልጥ እንዲከብደን ካደረጉት አንዱ ይኸው ነው!
“መንግስተ እግዚአብሔርን የምትወርሰው የክርስቶስን መስቀል አንተ ተሸክመህ ሌላው እንዲጥሉ አድርገህ አይደለም”
አባ አርምሞ
https://www.tg-me.com/Mesle_Fikur_Welda
Telegram
ምስለ ፍቁር ወልዳ
Zion, My Mother – Never Leave Me
✨ Heavenly words for a hurting world ✨
“The entrance of Your words gives light; it gives understanding to the simple.” – Psalm 119:130
🎶 Mezmur | 📖 Sermons | 🕊️ Holy Days | 📚 Spiritual Stories
📬 @Mesle_Fikur_Welda_Bot

††† እንኳን ለግሼን ደብረ ከርቤ: ለብዙኃን ማርያምና ለቅዱሳኑ ዓመታዊ በዓል በሰላም አደረሳችሁ፤ አደረሰን። †††
††† በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን! †††
††† ግሼን ደብረ ከርቤ †††
††† ሃገራችን ኢትዮዽያ ሃገረ እግዚአብሔር መሆኗን ታላቁ ቅዱስ መጽሐፍ ይመሰክራል:: (መዝ. 67, አሞጽ. 9:7) ሕዝቦቿም የድንግል ማርያምና የቅዱሳን አሥራት ናቸው:: የኢትዮዽያውያንን ያህል ድንግል ማርያምን የሚወድ: ለቅዱስ መስቀሉ ክብርን የሚሰጥ: ቅዱሳንንም የሚዘክር ያለ አይመስለኝም:: "እመ ብርሃንም ፈጽማ ትወደናለች:: ለዚህ ደግሞ ቅንጣት ታህል አንጠራጠርም::"
ለዓለም እስከ አሁን ድረስ የሁለቱ (የታቦተ ጽዮንና የቅዱስ ዕፀ መስቀሉ) መገኛ እንቆቅልሽ ነው:: ለእኛ ግን ሁለቱም ያሉት በቤታችን ውስጥ ነውና እንመሠክራለን:: ክብር ለቀደምት አበው ይድረሳቸውና አስፈላጊውን መንፈሳዊና ሥጋዊ ዋጋ ከፍለው ታቦተ ጽዮንን እና ቅዱስ ዕፀ መስቀሉን አምጥተውልናል::
በዚህች ዕለትም የጌታችንና የመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል በደብረ ከርቤ ግሼን ማረፉን አስበን በዓልን እናከብራለን:: ይኸውም ደጉ አፄ ዳዊት በሠይፈ አርዕድ የተጀመረውን ጥረት ቀጥለው: በኃይለ እግዚአብሔር አሕዛብን አስደንግጠው: እመ ብርሃንንም በጸሎት ጠየቁ::
የአምላክ እናትም ረድታቸው ቅዱስ ዕፀ መስቀሉን ከኩርዓተ ርዕሡ: ወንጌላዊ ቅዱስ ሉቃስ ከሳላት ምስለ ፍቁር ወልዳ እና ከብዙ ንዋያተ ቅዱሳት ጋር ተላከላቸው:: እርሳቸው መስከረም 10 ቀን መስቀሉን ተቀብለው: በዓሉን በተድላ አክብረው በመንገድ በ1396 ዓ/ም ዐርፈዋል::
አፄ ዳዊት ካረፉ በኋላ ቅዱስ መስቀሉ ለ30 ዓመታት ተቀምጧል:: አፄ ዘርዓ ያዕቆብ እስከ ነገሠበት 1426 ዓ/ም ድረስም ከ6 በላይ ነገሥታት አልፈዋል::
††† አፄ ዘርዓ ያዕቆብ ከነገሠ ከጥቂት ዓመታት በኋላ ለቅዱስ መስቀሉ በመካነ ንግሡ ደብረ ብርሃን ቤተ ክርስቲያንን ለማነጽ ሲያስብ ጌታችን በራዕይ "አንብር መስቀልየ በዲበ መስቀል" አለው:: ከዚህ ቀን ጀምሮ ደጉ ንጉሥ የመካነ መስቀሉን ቦታ ይፈልግ ዘንድ ከሠራዊቱ ጋር ብዙ ደክሟል::
በመጨረሻም በነገሠ በ10 ዓመታት ግሼንን አምባሰል (ወሎ) ውስጥ አግኝቷት ሐሴትን አድርጓል:: ቦታዋ በሥላሴ ፈቃድ በትእምርተ መስቀል የተፈጠረች ናትና እግዚአብሔር አብ ቤተ ክርስቲያንን አንጾ መስቀሉን በብረት: በመዳብ: በናስ: በብር: በወርቅ ለብጦ: ዐፈር እንዳይነካውም አድርጐ አኑሮታል::
በቦታውም ተአምራት ተደርገዋል:: ጻድቁ ዘርዓ ያዕቆብም 'ጤፉት' የሚባል መጽሐፍን ጽፎ እዚያው አኑሮታል:: መጽሐፉ እንደሚለው በሃገራችን ያለው ግማደ መስቀሉ (የቀኝ እጁ) ብቻ ሳይሆን ሙሉው ዕፀ መስቀል ነው:: ይህ የተደረገውም መስከረም 21 ቀን ነው::
††† ብዙኃን ማርያም / ጉባኤ ኒቅያ †
††† ዳግመኛ ይህች ዕለት 'ብዙኃን ማርያም' ትባላለች:: በቁሙ ሲታይ ድንግል ማርያም የብዙ ቅዱሳን የጸጋ እናት መሆኗን ያመለክታል:: በምሥጢሩ ግን በዚህች ዕለት በሃገረ ኒቅያ በእመቤታችን እና በአምላክ ልጇ የሚያምኑ 318ቱ ቅዱሳን ሊቃውንት መሰብሰባቸውን የሚያጠይቅ ነው::
የሊብያው ሰው አርዮስ ጌትነት ገንዘቡ የሆነ ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን ክዶ ሊያስክድ ሲሯሯጥ በፈቃደ እግዚአብሔር: በጻድቁ ንጉሥ ቆስጠንጢኖስ ጥሪ: 2348 ምሑራን ከመላው ዓለም ተሰበሰቡ::
ጥሪው የተላለፈው በወርኀ ሚያዝያ ሲሆን በመንገድ ችግር ሁሉም ተጠቃለው ኒቅያ የገቡት በዚህ ቀን ነበር:: ከተሰበሰበው ብዙ ሰው መካከል የአበውን ደቀ መዛሙርት ሳንቆጥር ሃይማኖታቸው የቀና: ምግባራቸው የጸና 318ቱ አበው ሊቃውንት ተገኙ::
እነዚህ አባቶች 'ሊቃውንት' ሲባሉ እንዲሁ በእውቀት ብቻ የበሰሉ እንዳይመስሉን:: 318ቱ አበው እኩሎቹ በዘመነ ሰማዕታት እጅና እግራቸውን የተቆረጡና ለሃይማኖታቸው ብዙ ዋጋ የከፈሉ ናቸው:: እኩሎቹ ደግሞ በገዳማዊ ሕይወት ያጌጡ: ፍቅረ ክርስቶስ በውስጣቸው የሚነድ: የመንፈስ ቅዱስ ቤት ናቸው:: የጉባኤውን ዜና ግን ሕዳር 9 ቀን የምንመለከት ነንና የዚያ ሰው ይበለን:: ይህች ቀን ለአባቶቻችን የሱባኤ መጀመሪያ ናት::
††† ቅዱሳን ቆዽርያኖስ እና ዮስቴና †††
††† ቆዽርያኖስ ማለት አገር ያስጨነቀ የሶርያ ጠንቅ ዋይ (መተተኛ) የነበረ ሰው ነው:: ከሥራዩ ብዛት የተነሳ አጋንንትን የሚፈልገውን ያዛቸው ነበር:: በዚያ ሰሞን ታዲያ ወደ አንጾኪያ ሔዶ የለመደውን ሊሠራ አሰበ:: እንዳሰበውም ሔደ::
በአንጾኪያ ደግሞ ስም አጠራሯ የከበረ: ክርስትናዋ የሠመረ: ድንግልናዋ የተመሠከረና ደም ግባቷ ያማረ አንዲት ወጣት ነበረች:: ስሟም ዮስቴና (የሴቶች እመቤት) ትባላለች:: እንዲህ ነው ስምና ሥራ ሲገጣጠሙ::
በወቅቱ ደግሞ የእርሷ ጐረቤት የሆነ አንድ ሰው በቁንጅናዋ ተማርኮ 'ላግባሽ' ቢላት 'አይሆንም' አለችው:: ምክንያቱም እርሷ መናኝ ናትና:: በጥያቄ አልሳካልህ ቢለው በሃብት ሊያታልላት: 'እገድልሻለሁ' ብሎ ሊያስፈራራት: በሥራይ (በመስተፋቅር) ሊያጠምዳት ሞከረ:: ነገር ግን አልተሳካለትም:: ምክንያቱም ሟርት በእሥራኤል ላይ አይሠራምና:: በመጨረሻ ግን ወደ ቆዽርያኖስ ሔዶ "አንድ በለኝ" አለው:: ቆዽርያኖስም "ይሔማ በጣም ቀላል ነው" ብሎ ወዲያው አጋንንትን ጠራቸው:: "ሒዳችሁ ያችን ወጣት አምጡልኝ" ሲልም ላካቸው::
አጋንንቱ ወደ ቅድስት ዮስቴና ሲሔዱ ግን መላእክት ወርደው ቤቷን በእሳት አጥረውታል:: ተመልሰው "አልቻልንም" አሉት:: እርሱም "አንዲት ሴት ካሸነፈቻችሁማ እኔም ክርስቲያን እሆናለሁ" ብሎ አስፈራራቸው:: አጋንንቱም በማታለል አንዱ ሰይጣን እርሷን መስሎ ሌሎቹ ደግሞ አስረውት መጡ::
ቆዽርያኖስ ይህን ሲያይ ደስ ብሎት "ሠናይ ምጽአትኪ ኦ ዮስቴና እግዝእቶን ለአንስት-የሴቶች እመቤት ዮስቴና እንኳን ደህና መጣሽ" ሲል: ስሟ ገና ሲጠራ ደንግጠው አጋንንት እንደ ጢስ ተበተኑ:: "ለዛቲ ቅድስት በኀበ ጸውዑ ስማ: ከመ እንተ ጢስ ተዘርወ መስቴማ" እንዳለ መጽሐፍ::
ቆዽርያኖስም በሆነው ነገር ተገርሞ "ስሟን ሲጠሩ እንዲህ የራዱ ወደ እርሷማ እንዴት ይቀርባሉ" ብሎ ተነሳ:: መጽሐፈ ሥራዩን በሙሉ አቃጠለ:: ሃብቱንም ለነዳያን አካፍሎ ሒዶ ክርስቲያን ሆነ:: የሚገርመው ድንግል ነበርና ከብዙ ተጋድሎ በኋላ ዲቁናና ቅስናን ተሾመ::
አምላክ መርጦታልና የቅርጣግና ዻዻስ ሆኖ ተመርጦ የክርስቶስን መንጋ በትጋት ጠብቋል:: ቅድስት ዮስቴናም ገዳም አንጻ: ደናግሉን ሰብስባ ንጽሕናን ስታስተምር ኑራለች:: በመጨረሻም በዚህ ዕለት ንጉሡ ዳኬዎስ ክርስቶስን ካልካዳችሁ በሚል ብዙ አሰቃይቶ አንገታቸውን አሰይፏል::
††† ቸር አምላክ በኃይለ መስቀሉ ሃገራችንን ከክፉው ሁሉ ይጠብቅልን:: የቅዱሳኑን ጸጋ ክብርም አይንሳን::
††† መስከረም 21 ቀን የሚከበሩ ዓመታዊ የቅዱሳን በዓላት
1.ቅድስት ግሼን ደብረ ከርቤ
2.ብዙኃን ማርያም
3."318ቱ" ቅዱሳን ሊቃውንት
4.ቅዱስ ቆዽርያኖስ ሰማዕት
5.ቅድስት ዮስቴና ድንግል
6.ቅዱስ ጢባርዮስ ሐዋርያ

††† ወርኀዊ በዓላት
1.ቅድስት ድንግል እግዝእትነ ማርያም ወላዲተ አምላክ
2.አበው ጎርጎርዮሳት
3.አቡነ ምዕመነ ድንግል
4.አቡነ አምደ ሥላሴ
5.አባ አሮን ሶርያዊ
6.አባ መርትያኖስ ጻድቅ
††† "እግዚአብሔር ትዕቢተኞችን ይቃወማል:: ለትሑታን ግን ጸጋን ይሰጣል ይላል:: እንግዲህ ለእግዚአብሔር ተገዙ:: ዲያብሎስን ግን ተቃወሙ:: ከእናንተም ይሸሻል:: ወደ እግዚአብሔር ቅረቡ:: ወደ እናንተም ይቀርባል::"(ያዕ ፬፥፮)
✝ ወስብሐት ለእግዚአብሔር ✝