#እሰይ_እሰይ_ተወለደ

እሰይ እሰይ ተወለደ (፪)
ከሰማየ ሰማያት ወረደ (፪)
ከድንግል ማርያም ተወለደ
እሱ ባይወለድ እሰይ እሰይ
ቸሩ አባታችን "
መች ትገኝ ነበረ "
ገነት ምድራችን "
ብርሃን ወጣላቸው እሰይእሰይ
ለመላ ሕዝቦቹ "
በጨለማው ጉዞ "
እንዲያሲሰላቹ "
እንደ ጠል ወረደ እሰይ እሰይ
ከሰማይ ወደ እኛ "
ወገኖቹን ሊያድን "
ከኃጢአት ቁራኛ "
እግዚአብሔር አብ ላከ እሰይ እሰይ
አንድያ ልጁን "
እርሱ ወዷልና "
እንዲሁ ዓለሙን "


@MEZMURA
#አንቺ የወይን ሐረግ
አንቺ የወይን ሐረግ ድንግል ልምላሜሽ የበዛ /፪/
ምግብ ሆኖ /፪/ ተሰጠን ፍሬሽ ለእኛ ቤዛ /፪/
ኸኸ
አዝ. . .
በአንቺ ሰማይነት ድንግል የወጣው ፀሐይ /፪/
ብርሃን ነው/ ፪/ ለጻድቃን ስሙም አዶናይ /፪/ ኸኸ
አዝ . . .
ፊደል ትመስያለሽ ድንግል ወንጌል ትወልጃለሽ /፪/
ለመላእክት /፪/ የማይቻል ነበልባሉን የቻልሽ /፪/ ኸኸ
አዝ . . .
የመሶብ ምሳሌ ድንግል የኮከብ መገኛ/፪/
በሥጋችን በነፍሳችን እንዳንራብ አንቺ አለሽን ለእኛ /፪/ ኸኸ
አንቺ የወይን ሐረግ ድንግል ልምላሜሽ የበዛ /፪/
ምግብ ሆኖ /፪/ ተሰጠን ፍሬሽ ለእኛ ቤዛ /፪/ ኸኸ
#የጽድቅ በር ነሽ
የጽድቅ በር ነሽ የሙሴ ጽላት
አክሊለ ሰማእታት ምእራገ ጸሎት
የጌታዬ እናት ንጹሕ አክሊላችን
ሐመልማለ ሲና እመቤታችን /፪/
አዝ . . .
እመቤታቸን ለእኛ መርኩዝ ነሽ
እመቤታቸን ከለላም ሆንሽን
እመቤታቸን የእሳት ሙዳይ
እመቤታቸን እሳት ታቀፍሽ
እመቤታቸን በብርሃን ተከበሽ
እመቤታቸን ወርቅ ለብሰሽ
እመቤታቸን ከሴቶች ሁሉ
እመቤታቸን አብ መረጠሸ
አዝ . . .
እመቤታቻን ድንግል ሆይ ልጆችሽ
እመቤታቸን ዘወትር ይጠሩሻል
እመቤታቸን ስምሽን ለልጅ ልጅ
እመቤታቻን ያሳስቡልሻል
እመቤታቻን በተሰጠሸ ጸጋ
እመቤታቻን በአማላጅነትሽ
እመቤታቻን ምሕረትን አሰጪን
እመቤታቻን ከመሐሪው ልጅሽ
አዝ . . .
እመቤታችን ያልታረሰች እርሻ
እመቤታቻን ዘር ያልተዘራባት
እመቤታቻን የሕይወትን ፍሬ
እመቤታቻን ሰጠችን የእኛ እናት
እመቤታቻን የተሠዋው መሲህ
እመቤታቻን እናቱን ወደዳት
እመቤታቻን በቀኙ ቆማለች
እመቤታቻን ድንግል እመቤት ናት
አዝ . . .
እመቤታችን የእውነት ደመና
እመቤታቻን ዝናብ የታየባት
እመቤታቻን ወዳናለች ድንግል
እመቤታቻን የታተመች ገነት
እመቤታቻን ክብር ለሆነችው
እመቤታቻን ኑ እንዘመርላት
እመቤታቻን ደስ ይበልሽ እንበል
እመቤታቻን ለብርሃን እናት
#ታማልደናለች
ታማልደናለች /፬/
ማርያም /፪/ቤዛዊተ ዓለም/፪/
አዝ . . .
ሚካኤል መልአከ ሊቀ መላእክት /፪/
ዘአውረድከ /፪/ መና ከደመና/፪/
አዝ . . .
ገብርኤል መልአክ አብሣሬ ትስብእት/፪/
ዘአብሠራ /፪/ ለማርያም ንጽሕት/፪/
አዝ . . .
ሩፋኤል መልአክ ሊቀመላእክት/፪/
ዘአብርሀ /፪/ዓይኑ ለጦቢት/፪/
አዝ . . .
ኡራኤል መልአክ ለእዝራ ነቢይ/፪/
ዘአስተዮ/፪/ ጽዋአ ልቡና/፪/
አዝ . . .
ሰሎሞን ይቤላ /፬/
ርግብየ ሠናይትየ ሰሎሞን ይቤላ /፪/
አዝ . . .
ገብረ መንፈስ ቅዱስ /፬/
ሐዋርያ /፪/ ዘእስክንድርያ/፪/
አዝ . . .
ተክለሃይማኖት /፬/
ሐዋርያ /፪/ ዘኢትዮጵያ /፪/
አዝ . . .
ብርሃናተ ዓለም ጴጥሮስ ወጳውሎስ
አእማደ /፪/ ቤተ ክርስቲያን /፪/
#በሐዘኔ
በሐዘኔ ደራሽ ነሽ በጭነቀቴ
በችግሬ ደራሽ ነሽ
የአምላኬ እናት የጌታዬ እናት
ድንግል እመቤቴ ወላዲተ ቃል/፪/
አዝ . . .
መላካሚቱ ርግብ ድንግል እመቤቴ
ማርያም እናቴነሽ ድንግል እመቤቴ
ከፍጥረታት ሁሉ ድንግል እመቤቴ
ገናና ነው ክብርሽ ድንግል እመቤቴ
የሐዘኔ መጽናኛ ድንግል እመቤቴ
እንባን አባሽነሽ ድንግል እመቤቴ
አዝ . . .
ዋሻ መጠለያ ድንግል እመቤቴ
የዘለዓለም ቤቴ ድንግል እመቤቴ
መንገድ ስሄድ ስንቄ ድንግል እመቤቴ
መጠነሽ ምግቤ ድንግል እመቤቴ
እምአምላክ ስጠራሽ ድንግል እመቤቴ
ይጠፋል ረሀቤ ድንግል እመቤቴ
አዝ . . .
የእናትነትሽ ድንግል እመቤቴ
ፍቅርሽን አየሁት ድንግል እመቤቴ
ጎጆዬን ስትሞይው ድንግል እመቤቴ
ባዶ የሆነውን ድንግል እመቤቴ
አንቺ እያለሽልኝ ድንግል እመቤቴ
ምን እሆናለሁኝ ድንግል እመቤቴ
#ለውዳሴሽ ልትጋ
ለውዳሴሽ ልትጋ ስምሽ ግርማ ያለው/፪/
እመቤቴ ኸኸ እመቤቴ ስልሽ እውላለሁ
አዝ. . .
ከልቤ አቀርባለሁ ምስጋና ለስምሽ
መለመኛዬ ነው ጽኑእ ቃል ኪዳንሽ
በሰላምታ ድምጽሽ ያልጸና ማን አለ
ጽንሱ በማኅፀን በደስታ ዘለለ
አዝ. . .
ማርና ወተት ነው የስምሽ ስያሜ
እመቤቴ ስልሽ ይቀላል ሽክሜ
ቅኔ ማኀሌቴ ሰዓታት መዝሙሩ
ያመሰግኑሻል ምድርና ጠፈሩ
አዝ. . .
እናቱ ነሽና አንቺ ለአዶናይ
ማለድኩኝ ከፊትሽ ይቅርታውን እንዳይ
ሰአሊነ ብዬ ይኸው ተምሬአለሁ
በአንቺ ተደግፌ ነገም እኖራለሁ
አዝ. . .
ነይ ነይ እልሻለሁ አንደ ካህናቱ
በሰዓታት ጸሎት ቆሜ በሌሊቱ
ዝም አልልም እኔ አወድስሻለሁ
የዓለምን መከራ እረሳብሻለሁ
#ስለማይነገር ስጦታው
ስላማይነገር ስጦታው እግዚአብሔር ይመስገን
ቸል ያላላን አምላክ ስንጓዝ ማእበሉን አቋርጠን
ስለማይነገረው ስጦታው እግዚአብሔር ይመስገን
አዝ . . .
የሕይወት እስትንፋስ ዘራብን ሕያው እንድንሆን
ይህን ያደረገ አምላካችን እግዚአብሔር ይመስገን
ስለማይነገር ስጦታው እግዚአብሔር ይመስገን
አዝ . . .
ንፋሱን ገስፆ ማእበል አቁሞ የሚያሻግር
የዓለም ፈተና ሲበዛ እርሱ መጠጊያችን
ሰለማይነገር ስጦታው እግዚአብሔር ይመስገን
አዝ . . .
ዳግሞ እንዳንሞት በሞቱ ሞትን የረታልን
የምንመካበት ትንሣኤ ሰላምን ለሰጠን
ሰለማይነገር ስጦታው እገዚአብሔር ይመስገን
አዝ . . .
ከሲኦል እሥራት ተፈተን ነጻ የወጣንበት
መስቀሉን ለሰጠን ለአምላካችን እንዘምር በእውነት
ስለማይነገር ስጦታው እግዚአብሔር ይመስገን
#አንትሙሰ
አንትሙስ ንበሩ ሀገረ ኢየሩሳሌም/፪/
እስከትለብሱ ኃይለ እምአርያም /፬/
እናንተ ግን ቆዩ በኢየሩሳሌም ሀገር /፪/
እስክምታገኙ ኃይል ከሰማይ /፬/
#ዓረገ በስብሐት
ዓረገ በስብሐት ዓረገ በእልልታ በስብሐት
በእልልታ አረገ በስብሐት በእልልታ/፪/
ሞትን ድል አድረጎ የሠራዊት ጌታ
አረገ አረገ በእልልታ/፪/
#መንፈስ ቅዱስ ወረደ
መንፈስ ቅዱስ ወረደ ላዕለ ሐዋርያት/፪/
ተመሲሎ /፭/ በነደ እሳት /፪/
ትርጉም፡- መንፈስ ቅዱስ በሐዋርያት ላይ በእሳት
አምሣል ወረደ

@MEZMURA
#ወላዲተ አምላክ
ወላዲተ አምላክ ማርያም ድንግል(፪)
ልዩ ነው ክብርሽ(፪)ከፍጥረት መሀል
በቃሉ ዓለማትን ሣይፈጥራቸው ገና
ታስበሽ የነበርሽ በእግዚአብሔር ሕሊና
ከሐና ማህጸን ከኢያቄም አብራክ
እናት እንድትሆኝው መረጠሽ አምላክ
ከመላክት በክብር አንች ትበልጫለሽ
ከሰዎች ልጆችም የለም የሚመስልሽ
በእግዚአብሔር ዘንድ ስምሽ የገነነ
አልተገኘም ድንግል እንዳንች የከበረ
ነውር የሌለብሽ ንፅሕት ሙሽራ
የመመኪያችን ዘውድ ርህርይተ ሕሊና
እናትና ድንግል ወላዲተ ቃል
የማትለወጭ የኃይማኖት በትር

@MEZMURA
#የአምላክ ዐቃቤ ሕግ

ገባሬ መንክራት በገድሉ ያወቅነው
የእግሮቹ ትቢያ የአራዊት ስንቅ ነው
ገብረ መንፈስ ቅዱስ
የአምላክ ዐቃቤ ሕግ
የኢትዮጵያ ዋስ ነው ፈጥኖ የሚታደግ

ፀሐይ(2) የምድራችን ፀሐይ
በገድሉ ያበራል እስከ ጥልቁ ቀላይ
የመላዕክት ወዳጅ/2/
ገብረሕይወት ሰማይ

አዝ__________

መብረቅ/2/ሰረገላው መብረቅ
የቃልኪዳኑ ወንዝ ቢጠጣ የማይደርቅ
የፍጥረቱ ደስታ/2/
ገብረሕይወት ፃድቅ

አዝ__________

ኮከብ/2/ክብረ ገድላን ኮከብ
ዓለምን የሚያስንቅ መዐዛው የሚስብ
አርከ ሥሉስ ቅዱስ/2/
ገብረሕይወት ኪሩብ

አዝ___________

ስኂን /2/ ፄና ልብሱ ስኂን
የነፍስን አዳራሽ በገድል የሚሸፍን
የሚነበብ መፃፍ/2/
ገብረሕይወት ድርሳን

አዝ__________

መቅረዝ/2/ የማኅቶት መቅረዝ
ምድረከብድ ዝቋላን ያለመለመ ወንዝ
የዝጊቲው ፈዋሽ/2/
ገብረሕይወት ምርኩዝ

@MEZMURA
#ጽርሐ አርያም
ጽ ርሐ አርያም/4/
ክብርሽ ገናና ነው ለዘለዓለም
አዝ.....
በመላዕክት ሀገር በሦስቱ ከተማ
በኤረር በኢዮር እንዲሁም በራማ
ውዳሴ ቀረበ ለሰማይ ንግሥት
የአምላክን እናት በክብር አየናት
አዝ.....
በበረሀ ያሉ ዓለምን የናቁ
ውዳሴሽን ደግመው ስምሽን የሰነቁ
አንቺን ስንጠራ ጠላት ገለል ይላል
ማርያም በግርማሽ ከ ሳሻችን ያፍራል
አዝ.....
ከእግሮቿ በታች ጨረቃን ተጫምታ
የክብርን አክሊል በራሶቿ ደፍታ
በቅዱሳን ሁሉ ትመሰገናለች
ዓለም የዳነባት ድንግል ማርያም ነች
አዝ.....
ብርሀንን ለብ ሳ በንጽሕና አጊጣ
ፍጥረትን ስትባርክ በክብር ተገልጣ
ነፍ ሳት ተቀደሱ በእምነት ከበዋት
ከበሮን አንስተን እንዘምርላት

@MEZMURA
#ሃሌ ሃሌሉያ
ሃሌ ሃሌሉያ/፪/
በ ሰማይ በምድር ምህረት ሆኗልና
ሃሌ ሃሌሉያ አሜን ሃሌሉያ
አዝ.....
መላዕክት ዘመሩ አመ ሰገኑት
እየተደነቁ በአምላክ ቸርነት/፪/
ስ ብሐት ለእግዚአብሔር በሰማያት አሉ
እረኞችም አብረው እርሱን አከበሩ/፪/
አዝ.....
ዓለምን ለመፍጠር ከተጠበበት
ይበልጣል ከሁሉ እኛን ያዳነበት/፪/
ከዳግማዊት ሔዋን ከእመቤታችን
በረቂቅ ጥበቡ ተወልዶ አዳነን/፪/
አዝ.....
ሁላችሁም ሂዱ ከቤተልሔም
ታገኙታላችሁ በከብቶች ግርግም/፪/
ኢየሱስ ክርስቶስ ወሃቤ ሰላም
ሞታችንን ወስዶ ህይወቱን ሰጠን/፪/

@MEZMURA
#በበረሃው በሀሩሩ

በበረሃው በሀሩሩ
በሚያስፈራው በባህሩ
እስራኤልን የታደገው
በክንፎቹ የጋረደው ሚካኤል ነው
=======================

ሚካኤል ነው አፅናኝ ደጋፊዬ
" " በዱር በበረሃ
" " ነፍሴን ያረካልኝ
" " ከአለቱ ውሃ
የፊቴ ፈገግታ የውስጤ ፍስሐ
ከአምላክ የተሰጠኝ በረከት አምሐ
======================

ሚካኤል ነው መብረቅ ያወረደው
" " ጠላት ድል የነሳው
" " የባህራን ወዳጅ
" " ሀዘኑን ያስረሳው
ቤቱን የሰራለት በእግሮቹ ያቆመው
እንደ እናት እንደ አባት ደግሶ የዳረው

= = = = = = = =
ሚካኤል ነው ክሴን ያስቀደደ
" " የበደሌን እዳ
" " በአማላጅነቱ
" " ያዳነኝ ከፍዳ
በመንገዴ ሁሉ እኔን እየረዳ
ፍቅሩን ጽፎት አልፏል በልቤ ሰሌዳ

@MEZMURA
#የራማው ልዑል

የራማው ልዑል ገብርኤል /2/
ተመላለስ መሀላችን ስምህን ጠርተን ና ስንል/2/

ብርሃን ልብሱ እሳታዊ መልአክ
አንተ አማልደን ከመሃሪው አምላክ/2/
አዝ =====
የምስራች ነጋሪ ድንቅ ልደትን አብሳሪ 
የጽድቅ ፋና የድህነትት ጎዳና /2/
አዝ=====
ላመኑብህ ለተማጸኑብህ
ፈጥኖ ደራሽ አለኝታቸው ነህ /2/
አዝ=====
የአናንያ የአዛርያ የሚሳኤል ከለላቸው 
ከእሳት ነበልባል ያዳንካቸው /2/
አዝ =====
ተስፋ አምባችን መጠጊያችን
ቅዱስ ገብርኤል ጠባቂያችን /2/
አዝ =====
ዕለት ዕለት የምንማልድህ
ልጀችህን ይምላን መንፈስህ/2/

@MEZMURA
#ሃያል_ነህ_አንተ

ሃያል ነህ አንተ ሃያል
ደጉ መልአክ ገብርኤል
ይውደቅ ይሸነፍ ጠላት
አንተ ተራዳን በእውነት
#አዝ
በዱራ ሜዳ ላይ - ገብርኤል
ጣኦት ተዘጋጅቶ - ገብርኤል
ሊያመልኩት ወደዱ - ገብርኤል
አዲስ አዋጅ ወጥቶ - ገብርኤል
ሲድራቅ እና ሚሳቅ አብደናጎ ፀኑ፤
ጣኦቱን እረግጠው በእግዚያብሄር አመኑ
#አዝ
ተቆጣ ንጉሱ - ገብርኤል
በሶስቱ ህፃናት - ገብርኤል
ጨምሯቸው አለ - ገብርኤል
ወደ እቶን እሳት - ገብርኤል
ከሰማይ ተልኮ ወረደ መላኩ፤
ከሞት አዳናቸው በሳት ሳይነኩ።
#አዝ
ከእቶኑ ስር ሆነው - ገብርኤል
ዝማሬ ተሞሉ - ገብርኤል
ገፍተው የጣሏቸው - ገብርኤል
በእሳቱ ሲበሉ - ገብርኤል
አልተቃጠለችም የራሳቸው ፀጉር፤
አዩ መኩአንንቱ የእግዚአብሄርን ክብር።
#አዝ
ናቡከደነፆር - ገብርኤል
እጁን ባፉ ጫነ - ገብርኤል
ሰለስቱ ደቂቅን - ገብርኤል
ከእሳት ስለአዳነ - ገብርኤል
ይክበር ጌታ አለ የላከ መላኩን፤
ሊአመልከው ወደደ ስላየ ማዳኑን

@MEZMUR
#ለጣዖት_አንሰግድም

ለጣዖት አንሰግድም ብለው
ሶስቱ ህፃናት እምቢ አሉ
የምናመልከው አምላክ
ከእሣት ያወጣል እያሉ
#አዝ
በንጉሱ ቁጣ ልባቸው ሳይርድ
አንዳችም ሣይፈሩ በእሣቱ መንደድ
በእምነት በርትተው መከራን ታገሱ
የታመኑት ጌታ ፈረደ ለነሱ
#አዝ
በመካከል ታየ ከእነሱ ጋር
መላኩ ገብርኤል ታዞ ከእግዚአብሔር
በእሳቱ መካከል ምስጋናን ጀመሩ
ስቡህኒ ብለው ለስሙ ዘመሩ
#አዝ
የእሳቱን ነበልባል ውሀ እያደረገ
የእግዚአብሔር መላክ ነብሳቱን ታደገ
አንዳች ሳይነኩ ከእሳቱ ወጡ
የእግዚአብሔርን ክብር ለዓለም ገለጡ
#አዝ
ተመላልሰው ታዩ በእሳቱ መሀል
ከራሳቸው ፀጉር አንዲቶአ ሳትጎል
የከለዳውያን የእሳት ምድጃቸው
ህፃናቱን ትቶ እነሱን በላቸው

@MEZMURA
#ገብርኤል ስለው ሰምቶ


ገብርኤል/2/ ሰለው ሰምቶ መጣ ወደኔ ፈጥኖ
ሰንሰለቴን በጠሰው የአንበሶቹን አፍ ዘግቶ

ገብርኤል ስጋዬ ሳይረግፍ በአናብስቹ ጥፍር
ገብርኤል ታድጎኛል ምልጃው የመላኩ ፍቅር
ገብርኤል በረሐብ ለነደዱ አናብስት ሲጥሉኝ
ገብርኤል አንተ አለኸኝና ክንፎችህ ከለሉኝ

አዝ_______________

ገብርኤል ከአፎቱ ሲመዘዝ የጠላቴሰይፍ
ገብርኤል አጽንቶ ይዞኛል ፍሬዬ ሳይረግፍ
ገብርኤል አደገድጋለሁ አለኝና ፍቅሩ
ገብርኤል በእሳት ክንፉ ታጥራል የደጄ ድንበሩ

አዝ_______________

ገብርኤል በሰይፍ ተመትራል የክፉዎች ብክነት
ገብርኤል ሐብሉ ተበጣጥሷል ያመጡት ሰንሰለት
ገብርኤል ከቅድሱ ድንጋይ ሕይወት ከሚያፈልቀው
ገብርኤል እንዳልለይ ረዳኝ ክብሬን ከፍ አረገው

አዝ_______________

ገብርኤል አለው ልዩ ስልጣን በአምላክ የተሰጠው
ገብርኤል ይመጣል ወደኛ እሳቹን ሊያጠፋው
ገብርኤል እኛም እናምናለን ሰምተናል አይተናል
ገብርኤል የመላክት አለቃ ከአምላክ ያማልዳል

አዝ_______________

ገብርኤል ስጋዬ ሳይረግፍ በአናብስቹ ጥፍር
ገብርኤል ታድጎኛል ምልጃው የመላኩ ፍቅር
ገብርኤል በረሃብ ለነደዱ አናብስት ሲጥሉኝ
ገብርኤል አንተ አለኸኝና ክንፎችህከለሉኝ

@MEZMURA
✞ ​ቡሄ_በሉ

ቡሄ በሉ /2/ ሆኦ ልጆች ሁሉ ሆ
የኛማ ጌታ ሆኦ የዓለም ፈጣሪ ሆ
የሰላም አምላክ ሆ ትሁት መሀሪ ሆ
በደብረ ታቦር ሆ የተገለጠው ሆ
ፊቱ እንደ ፀሐይ ሆ በርቶ የታየው ሆ
ልብሱ እንደብርሃን ሆ ያንፀባረቀው ሆ

ድምጽህን ሰማና በብህሩ ደመና/2/
የቡሄው ብርሃን ለኛ መጣልን/2/

ያዕቆብ ዮሐንስሆ እንዲሁም ጴጥሮስ ሆ
አምላክን አዩት ሆ ሙሴ ኤልያስ ሆ
አባቱም አለ ሆ ልጄን ስሙት ሆ
ቃሌ ነውና ሆ የወለድኩት ሆ


ታቦር አርሞንኤም ሆ ብርሃን ታየባቸው ሆ
ከቅዱስ ተራራ ሆ ስምህ ደስ አላቸው ሆ
ሰላም ሰላም ሆ የታቦር ተራራ ሆ
ብርሀነ መለኮት ሆ ባንቺ ላይ አበራ ሆ


በተዋህዶ ሆ ወልድ የከበረው ሆ
የእግዚአብሔር አብ ልጅ ሆ ወልደማርያም ነው ሆ
ቡሄ በሉ ሆ ቡሄ በሉ ሆ
የአዳም ልጆች ሆ ብርሃንን ሆ ተቀበሉ ሆ


አባቴ ቤት ሆ አለኝ ለከት ሆ
እናቴ ቤት ሆ አለኝ ለከት ሆ
ከአጎቴም ቤት ሆ አለኝ ለከት ሆ
አክስቴም ቤት ሆ አለኝ ለከት ሆ
ተከምሯል ሆ እንደ ኩበት ሆ


የዓመት ልምዳችን ሆ ከጥንት የመጣው ሆ
ከተከመረው ሆ ከመሶቡ ይውጣ ሆ
ከደብረ ታቦር ሆ ጌታ ሰለመጣ ሆ
የተጋገረው ሆ ሙልሙሉ ይምጣ ሆ


ኢትዮጵያውያን ሆ ታሪክ ያላችሁ ሆ
ባህላችሁን ሆ ያዙ አጥብቃችሁ ሆ
ችቦውን አብሩት ሆ እንዳባቶቻችሁ ሆ
ምስጢር ስላለው ሆ ደስ ይበላችሁ ሆ


አባቶቻችን ሆ ያወረሱን ሆ
የቡሄን ትርጉም ሆ ያሳወቁን ሆ
እንድንጠብቀው ሆ ለእኛ የሰጡን ሆ
ይህን ነውና ሆ ያስረከቡን ሆ


ለድንግል ማርያም ሆ አሥራት የሆንሽ ሆ
ቅዱሳን ጻድቃን ሆ የሞሉብሽ ሆ
በረከታቸው ሆ ያደረብሽ ሆ
ሁሌም እንግዶች ሆ የሚያርፉብሽ ሆ
ሀገረ እግዚአብሔር ሆ ኢትዮጵያ ነሽ ሆ


ለሐዋርያት ሆ የላከ መንፈስ ሆ
ዛሬም ለኢትዮጵያ ሆ ጸጋውን ያፍስስ ሆ
በበጎ ምግባር ሆ እንድንታነጽ ሆ
በቅን ልቦና ሆ በጥሩ መንፈስ ሆ
በረከተ ቡሄ ሆ ለሁላችንይድረስ ሆ

ዓመት ዓውዳመት ድገም እና ዓመት ድገም እና
በጋሽዬ ቤ ድገም እና ዓመት ድገም እና
ያውርድ በረከት ድገም እና ዓመት ድገም እና
ወርቅ ይፍሰስበት ድገም እና ዓመት ድገም እና
በእማምዬ ቤት ድገም እና ዓመት ድገም እና
ይግባ በረከት ድገም እና ዓመት ድገም እና
ማርና ወተት ድገም እና ዓመት ድገም እና
ይትረፍረፍ በእውነት ድገም እና ዓመት ድገም እና


እንዲሁ እንዳላችሁ በምነት አይለያችሁ በምነት
ላመቱ በሰላም በምነት ያድርሳችሁ በምነት
ክርስቶስ በቀኙ በምነት ያቁማችሁ በምነት
የመንግስቱ ወራሽ በምነት ያድርጋችሁ በምነት
እንዲሁ እንዳለን በምነት አይለየን በምነት
ለዓመቱ በሰላም በምነት ያድርሰን በምነት
አማኑኤል በቀኙ በምነት ያቁመን በምነት
የመንግስቱ ወራሽ በምነት ያድርገን በምነት


የቅዱሳን መላክት የፃድቃን ሰማዕታት
ረድኤት በረከት ይግባ በሁሉም ቤት
በሁሉም ቤት/2/ ይግባ በረከት/2/
እንቁም በሃይማኖት ፀንተን በትጋት
የአስራት አገር የአበው ቀደምት
የቅዱሳን አባቶች ትውፊት
ይገባልና ልንጠብቅ በእውነት
ባህላችንን የአባቶች ትውፊት /3/

@MEZMURA
#ሰውነቴ
ሰውነቴ በአንተ ፍቅር ተጠምዳለች
ውለታህን እያሰበች ታለቅሳለች
መከራው ተረሳ ትካዜም ቀረልኝ
ገብረመንፈስ ቅዱስ ፈጥነህ ደርሰህልኝ


ደጅህን ለመርገጥ መንገድ ስጀምር
ተፈቶ አየዋለው የልቤ ችግር
ወዳጅ እና አባቴ ሚስጥሬ ተስፋዬ
ቀና እንድል አረከኝ በነፍስ በስጋዬ

/አዝ=====

በሚመጥን ፊደል በሚያምሩ ቃላት
ነፍሴ ትጠማለች ስምክን ለመጥራት
እንባዬ ይፈሳል አንደበት ያጥረኛል
ውለታህን ሳስብ ልቤ ይቀልጥብኛል

/አዝ =====

ልዩ እኮ ነህ ለእኔ መተኪያ የሌለህ
ልጅህን ሳሰለች ዛሬም ትሰማለህ
ዚጊቲ ልገስግስ ከደጅህ ልውደቅ
ገብረህይወት እንዳልኩ ዘመኔ ይለቅ

/አዝ =====

ስለቴን ስሰማኝ ሲጠብቀኝ ምልጃህ
ሳጉረመርምብህ ትታገሰኛለህ
የጭንቄ ማረፊያ የህመሜ ፈውስህ
አርከ እግዚአብሔር ገብረመንፈስ ቅዱስህ

/አዝ =====

ልዩ እኮ ነህ ለእኔ መተኪያ የሌለህ
ልጅህን ሳሰለች ዛሬም ትሰማለህ
ዚጊቲ ልገስግስ ከደጅህ ልውደቅ
ገብረህይወት እንዳልኩ ዘመኔ ይለቅ

@MEZMURA
#እናቴ እመቤቴ

እናቴ እመቤቴ/ የማትጠፊው ከአፌ/2/
በረከቴ አንቺ ነሽ/ የመስቀል ስር ትርፌ /2/
አምላኬ ሸልሞኝ ለዘላለም ያዝኩሽ
ጌታን የማይብሽ ብሌኔ አደረኩሽ


በልቤ ላይ ይፍሰስ የፍቅርሽ ፀዳሉ
የሚጣፍጥ ስምሽ መድኃኒት ለሁሉ
ተወዳጁ ልጅሽ ፀጋውን ያብዛልኝ
እድሜዬ እስኪ ፈፀም ለክብርሽ እንድቀኝ

/አዝ====

ነፍሴ እንዳትጎዳ እንዳትቀር ባክና
ብርታት ሆኖልኛል የስምሽ ምስጋና
እኖራለሁ ገና ንኢ ንኢ ስልሽ
ክብሬ ነሽ ጌጤ ነሽ ከአፌ የማልነጥልሽ

/አዝ =====

ሲነጋም ጠራሁሽ ሲመሽም ጠራሁሽ
ስዕልሽ ፊት ቆሜ ሰአሊ ለነ እያልኩሽ
አሜን የምልብሽ መነጋገሪያዬ
የአማኑኤል እናት አንቺ ነሽ ቋንቋዬ

/አዝ=====

መች በስጋ ጥበብ ሰው ለአንቺ ይቀኛል
ከአምላክ ከአልተላከ ከፊትሽ ይቆማል
አንቺን ማመስገኔ አንቺን ማወደሴ
በልቡ ያሰበሽ ፈቅዶ ነው ስላሴ

/አዝ=====

ብዙ ተቀብዬ ጥቂት አልዘምርም
ለእናትነት ፍቅርሽ ከቶ ዝም አልልም
እኔን በእደ ፍቅርሽ የምትባርኪ
ኦ ምልዕይተ ፀጋ ድንግል ሰላም ለኪ

@MEZMURA
#ማር ሊቀ ሰማዕት

ማር ሊቀ ሰማዕት ገባሬ መንክር
ጊዮርጊስ ኃያል(፪)

የዱድያኖስ አምላክ - - ጊዮርጊስ ኃያል
ያንን ደራጎን - - ጊዮርጊስ ኃያል
አምላክ እንዳልሆነ - - ጊዮርጊስ ኃያል
ገድለህ አሳየኸን - - ጊዮርጊስ ኃያል
የቤሩት ኮከብ ነህ - - ጊዮርጊስ ኃያል
የልዳ ፀሐይ - - ጊዮርጊስ ኃያል
ለባሴ ሞገስ ነህ መክብበ ሰማዕት(፪)
አዝ= = = = =
መከራና ስቃይ - - ጊዮርጊስ ኃያል
እያጸኑብህ - - ጊዮርጊስ ኃያል
ትናገር ነበረ - - ጊዮርጊስ ኃያል
ስለ አምላክህ - - ጊዮርጊስ ኃያል
ሥጋህን ፈጭተው - - ጊዮርጊስ ኃያል
ይድራስ ሲበትኑት - - ጊዮርጊስ ኃያል
ዳግመኛ አስነሳህ አምላከ ምሕረት(፪)
አዝ= = = = =
አንገትህ ሲታረድ - - ጊዮርጊስ ኃያል
ምድር ተናወጠች - - ጊዮርጊስ ኃያል
ወተትና ውሃ - - ጊዮርጊስ ኃያል
ደምም አፈለቀ - - ጊዮርጊስ ኃያል
ሰብዐ ነገሥታት - - ጊዮርጊስ ኃያል
እስኪደነቁብህ - - ጊዮርጊስ ኃያል
ሰባት አክሊላትን ጌታ አቀዳጀህ(፪)
አዝ= = = = =
የዚህን ዓለም ጣዕም - - ጊዮርጊስ ኃያል
ንቀኸው ጥቅሙን - - ጊዮርጊስ ኃያል
በፍቅር ተቀበልክ - - ጊዮርጊስ ኃያል
መራራ ሞትን - - ጊዮርጊስ ኃያል
ሰማይና ምድር - - ጊዮርጊስ ኃያል
ሳርና ቅጠሉ - - ጊዮርጊስ ኃያል
ሰማዕተ ክርስቶስ ቅዱስ ጊዮርጊስ አሉ(፪)

@MEZMURA
#ሁሉም ነገር ሆነ

ሁሉም ነገር ሆነ በግሸን ማርያም
በደብረ ከርቤ በጊሸን ማርያም
በእግዚአብሔር ፈቃድ ሁሉም ነገር ሆነ

መስቀሌን በመስቀል - በግሸን ማርያም
እንዳለ በቃሉ - በግሸን ማርያም
በግሸን አደረ - በግሸን ማርያም
ግማደ መስቀሉ - በግሸን ማርያም
ክርስቲያኖች ሁሉ - በግሸን ማርያም
እንጓዝ ከደጅዋ - በግሸን ማርያም
ትኖራለችና -በግሸን ማርያም
ድንግል ከነልጅዋ - በግሸን ማርያም
አዝ= = = = =
በገነት መስሎ - በግሸን ማርያም
ጌታ ያስቀመጠው - በግሸን ማርያም
ዙሪያሽ ገደል ሁኖ - በግሸን ማርያም
አንድ መግቢያ ያለሽ - በግሸን ማርያም
ግሸን ደብረ ከርቤ - በግሸን ማርያም
የታቦር ተራራ - በግሸን ማርያም
ሁነሽ የተመረጥሽ - በግሸን ማርያም
የመስቀል ማደሪያ - በግሸን ማርያም
አዝ= = = = =
እንማፀናለን - በግሸን ማርያም
ከደጅሽ ላይ ሆነን - በግሸን ማርያም
ባንቺ አማላጅነት - በግሸን ማርያም
ጌታ እንዲለመነን - በግሸን ማርያም

@MEZMURA
#እግዚአብሔር እኛን ይወደናል

እግዚአብሔር እኛን ይወደናል
መላዕክቱን ለኛ ልኮልናል
እንዲረዱን እንዲጠብቁን/2/
መላዕክቱ እንዲታደጉን/2/
አዝ.............
መንገደኛ መስሎ መላኩ ሲራራ
በሐሞት መስሎ በዚያ በተራራ
የጦቢትን አይኑን ያበራ/2/
ሩፋኤል ነው ለኛ የሚራራ/2/
አዝ........
ጦቢያና ጦቢት ይናገሩ
የመላዕኩን ታአምር ይዘርዝሩ
ይናገሩ ይገለጥ ክብሩ /2/
የታወሩ ሁሉ እንዲበሩ /2/
አዝ.............
ወለተ ራጉኤል ተናገሪ
የጫጉላ ቤትሽን ታሪክ አውሪ
ተናገሪ ለህዝብ አብስሪ /2/
ታምራቱን ምንም ሳፈሪ /2/
አዝ...........
ሰባቱ ባሎችሽ መሞታቸው
የሚያሳዝነ ነበር ታሪካቸው
ሩፋኤልም ደረሰልሽ/2/
ጎጆሽንም ባረከልሽ/2/
አዝ...........
እንግዲህ ተደሰች እልል በይ
አስማንዲዮስ ወቷል ከአንቺ ላይ
ህይወትሽን ሩፋኤል ዋጀው/2/
ሰላምሽን ለአለም አወጀው /2/
አዝ...........
ጦቢያም ይናገር በተራው
ያደረገለትን አለኝተው
ወዲያው ደሞ አባት ሆነው/2/
ሽማግሌ ሆኖ ዳረው /2/
አዝ.............
እኔም ልናገር በተራዬ
ቀሎልኛልና መከራዬ
ሩፋኤል ነው እናት አባቴ/2/
እለዋለሁ ወንድም እህቴ/2/
አዝ.......
እኔም ልናገር በተራዬ
ያደረገልኝን አለኝታዬ
ህይወቴን ሁሉ ቀይሮታል/2/
ልቦናዬ ፍቅሩ ማርኮታል/2/

@MEZMURA
#ገሊላ_እትዊ

እመቤቴ እሰከ መቼ
በባዕደ ሀገር ትኖርያለሽ /2/
ገሊላ ግቢ/4/ ሐገርሽ ገሊላ ግቢ/2/

ገሊላ እትዊ/4/ ሐገርኪ ገሊላ እትዊ/2/

እመቤቴ ማርያም ገሊላ እትዊ
ሰደቱ ይበቃሽል ገሊላ እትዊ
ሄሮድስ ሞቱልብሉ ገሊላ እትዊ
ገብርኤል ነገሮሽል ገሊላ እትዊ
በእሳት ሰርገላ ገሊላ እትዊ
ዑራኤል የምራሻል ገሊላ እትዊ

ሐገርኪ ገሊላ እትዊ/2/

የዝናቡን ጌታ ገሊላ እትዊ
እናቱ ሁነሽ ሳለ ገሊላ እትዊ
ሰይጣን በሰው አደሩ ገሊላ እትዊ
ውሃ ጥም ፅንቶብሽ ገሊላ እትዊ
አፈሽ ደርቁ ዋል ገሊላ እትዊ
ይብቃል እናቴ ገሊላ እትዊ
ርሀብ ጥማትሽ ገሊላ እትዊ
ሂጅ ወደ ገሊላ ገሊላ እትዊ
ወደ ዘመድችሽ ገሊላ እትዊ

ሐገርኪ ገሊላ እትዊ/2/

የሰማዕታት ገሊላ እትዊ
የፃድቃን እናት ገሊላ እትዊ
ባርክሽ ሰጠሽቸው ገሊላ እትዊ
መክራን ሰድት ገሊላ እትዊ
እኛም ይታደገን ገሊላ እትዊ
የአንቺው ብርክት ገሊላ እትዊ

ሐገርኪ ገሊላ እትዊ/2/

ገፃሽ ብሩህ መልካም ገሊላ እትዊ
ልክ እንደ ፀሐይ ገሊላ እትዊ
እግዚትነ ማርያም ገሊላ እትዊ
እሙ ለአዶናይ ገሊላ እትዊ
አይገባም ለአንቺ ገሊላ እትዊ
መክራ ስቃይ ገሊላ እትዊ

ሐገርኪ ገሊላ እትዊ /2/
ገሊላ ግቢ /4/ አገርሽ ገሊላ ግቢ/2/

@MEZMURA
#አክሊለ ፅጌ

አክሊለ ፅጌ ማርያም አክሊለ ፅጌ
አክሊለ ፅጌ ማርያም አክሊለ ፅጌ

ስሟ ማርያም ነው አክሊለ ፅጌ
የጌታ እናት "
እናት አባቷ "
ያወጡላት "
ከምድር ማር "
ከሰማይ ያም "
ብለው ሰየሟት "
ድንግል ማርያምን "
አዝ......
የስሟ ጣህም አክሊለ ፅጌ
ከማር ይበልጣል "
እንደሷ ያለ "
ከየት ይገኛል "
የፍቅር መዝገብ "
ነቅህ የሌለባት "
ለክብሯ ወደር "
ማን አግኝቶላት "
አዝ......
የከበረ ዘውድ አክሊለ ፅጌ
የወርቅ ሙዳይ "
የሽቱ ብልቃጥ "
የነፍሴ ሲሳይ "
ከጥፋት ውሀ "
ኖህ የዳነብሽ "
የሰላም መርከብ "
ቤቱ አንቺ ነሽ "
አዝ......
በቤተ መቅደስ አክሊለ ፅጌ
ስትኖር ተመርጣ "
ምግቧን ይዞላት "
ፋኑኤል መጣ "
አስራ አምስት ዓመት "
ሲሆናት ድንግል "
በገብርኤል ብስራት "
ተፀነሰ ቃል "

@MEZMURA
#አዘክሪ

አዘክሪ ድንግል አዘክሪ
ለልጅሽ አሳስቢ አዘክሪ
ለኃጥአን አኮ ለጻድቃን

ከአንቺ መወለዱን - - - አዘክሪ
በቤተልሔም - - - አዘክሪ
በጨርቅ መጠቅለሉን - - - አዘክሪ
መኝታው ግርግም - - - አዘክሪ
ለኃጥአን አኮ ለጻድቃን
አዝ= = = = =
በዚያ በብርድ ወራት - - -አዘክሪ
የገበሩለትን - - - አዘክሪ
የአድግና የላህም - - - አዘክሪ
እስትንፋሳቸውን - - - አዘክሪ
ለኃጥአን አኮ ለጻድቃን
አዝ= = = = =
በግብጽ በረሃ - - - አዘክሪ
መሰደድሽን - - - አዘክሪ
የአሸዋውን ግለት - - - አዘክሪ
ረሃብና ጥሙን - - - አዘክሪ
ለኃጥአን አኮ ለጻድቃን
አዝ= = = = =
በመቃብሩ ዘንድ - - - አዘክሪ
ባለቀሽው እንባ - - - አዘክሪ
አሳስቢ ድንግል ሆይ - - - አዘክሪ
ገነት እንድገባ - - - አዘክሪ
ለኃጥአን አኮ ለጻድቃን

@MEZMURA
2024/05/03 01:15:49
Back to Top
HTML Embed Code: