Telegram Web Link
የደረቁ ዓይኖች
@Mgetem

እሷ
ከቤተመቅደሱ በር ላይ ቆማለች፣
ፊት ለፊቷ ካለዉ የጌታ ስዕል ላይ ዐይኖቿን ተክላለች፣
እጆቿን ዘርግታ ፡
የማይቆም እምባዋን ቁልቁል ታፈሳለች፡፡

እኔ
በኃጢአት ደክሜ
ካንዱ አፀድ አጠገብ ታክቶኝ ቁጭ ብያለሁ፣
እንባን ባልታደሉ በደከሙ ዓይኖቼ
ዝም ብዬ አያታለሁ፡፡

ይፈሳል እምባዋ ይወርዳል አይቆምም፣
አሷም ልክ እንደኔ በዓለም ስትሸነፍ
ያዳናትን ጌታ ሳትክደው አትቀርም፡፡
 
እምባ ጥቁር እምባ ፀፀት ያከሰለው፣
እምባ ትኩስ እምባ ሀጢያት ያቃጠለው፣
እምባ መንታ እምባ ከአይኖቿ ይወርዳል፣
ምህረትን ፍለጋ ይጮሀል ይጣራል፡፡
 
ተቸገረች መሠል አልቻለችም መሠል እንባዋን ለመግታት፣
ፀፀቷ ገብቶኛል፡
እልፍ ሀዘኗ ፊት ስንት ቃል ደርድሬ ምን ብዬ ላበርታት፡፡

እንዴት ቀናሁባት እንዴት ታድላለች፣
የበዛ በደሏን በበዛ እምባዋ ታጥባ ትነፃለች፡፡
ይብላኝ እንጂ ለኔ ዓይኔ ለደረቀ፣
ልቤ ደንድኖብኝ
በኃጢአት በርኩሰት ነፍሴ ለደቀቀ፡፡
ይብላኝ እንጂ ለኔ ፀፀት ላላደለኝ፣
ካባቴ ቤት ርቄ መንገድ ለጠፋብኝ፡፡
ይብላኝ እንጂ ለኔ
ልጄ ነሽ እያለኝ ልጁ ላልሆንኩለት፣
ለፈወሰኝ አምላክ ጥፊ የመለስኩለት፣
ባፌ ማረኝ እንዳልልህ ልቤ መቼ አለቀሰ፣
ከንቱ ሆኜ ቀረሁብህ ነፍሴ ባለም እያነከሰ፡፡

ያዳንከኝ ሆይ...

እምባ ስጠኝ የጴጥሮስን ተፀፅቼ ማረኝ እንድል፣
እምባ ስጠኝ የጳውሎስን ማሳደዴን ትቼ እንድድን፣
የሚፈውስ ስጠኝ እምባ፣
የዓይኖቼን መባ አቅርቤልህ፡
የምህረት ደጅህ እንድገባ፡፡

ገጣሚ እሌኒ መኮነን

ሼር እያደረጋችሁ

https://www.tg-me.com/Mgetem
https://www.tg-me.com/Mgetem
https://www.tg-me.com/Mgetem
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
2025/07/03 20:11:45
Back to Top
HTML Embed Code: