Telegram Web Link
አንቺ ካለሺኝ
@Mgetem

ማርያም ብዬ ፤ ማንን እፈራለሁ
አባ ጊዮርጊስ ፤ ሲቀኝ እንዳለው ።
እኔን ለመፍጨት፤
ምድርም ወፍጮ ፤ ሰማይ መጅ ቢሆን
አንቺ ካለሺኝ ፤ ከቶ ምን ልሆን።
የጥፋት ውሃን ፤ ዛሬም ለማውረድ
እንደ ኖኅ ዘመን ፤ ሰማይ ቢቀደድ
በቅድስናሽ መርከብ ተርፌ
እሻገራለሁ ሞትን አልፌ።
በሰዶምና በገሞራ ላይ
እንደ ዘነበው ፤ እሳት ከሰማይ
ቢዘንብብኝስ ፤ ምን እሆናለሁ
ባንቺ ልመና ፤ አምኜ ሳለሁ።

✍️ አቤል ታደለ


https://www.tg-me.com/Mgetem
https://www.tg-me.com/Mgetem
https://www.tg-me.com/Mgetem
ለአስተያየት : @abeltadele
ናና አማኑኤል
ዘማሪት ሲ/ር ሕይወት ተፈሪ
ናና አማኑኤል | ዘማሪት ሲስተር ሕይወት ተፈሪ
@MMezmur

ናና አማኑኤል ና መድኃኒቴ
ጽድቅህን አልብሰኝ ይቅር መራቆቴ

የመዝሙር ቻናላችንን ይቀላቀሉ 🙏

https://www.tg-me.com/MMezmur
https://www.tg-me.com/MMezmur
https://www.tg-me.com/MMezmur
መነነ ዮሐንስ
@Mgetem

የድንግሊቱን ድምፅ ፤
ከእናቱ ማፀህን ፤ ከጠባቡ አልጋው
ዮሐነስ ሲሰማ ፤ ለመውጣት አጓጓው።
ወደ እኔ እንድትመጪ ፤ የጌታዬ እናቱ
እኔ ማነኝ ማለት ፤ ባይችል ባንደበቱ ።
ወቶም ሊቀበላት ፤ ባይታደል እንኳ
የእናቱን ማህፀን ፤ ከውስጥ ሆኖ አንኳኳ።
በእግዚአብሔር መንፈስ ፤ ልቡናው ተቃኝቶ
ደስታውን ለመግለፅ ፤ ባይችል ቃል አውቶ።
በአማናዊት ታቦት ፤ በድንግል ማርያም ፊት
በእናቱ ማህፀን ፤ ዘለለ እንደ ዳዊት።
የድንግሊቱን ድምፅ ፤ ከሰማ ጀምሮ
አስጠላው የአለም ፤ ጩኸት አምባኋሮ።
ተወልዶም አልቆየ ፤ ሌላ አልሰማም ብሎ
መነነ ዮሐንስ ፤ ይህን አለም ጥሎ ።
ዘወትር ሃጢያትን ፤ ለጊዜያዊ ደስታ
እኛም እንደ ውሃ ፤ ጠዋትና ማታ
ከዚህ አለም ጉድጓድ ፤ መቅዳት እንዲበቃን
ድምጿን እንሰማ ዘንድ ፤ ድንግሊቱ ታብቃን።

አቤል ታደለ

https://www.tg-me.com/Mgetem
https://www.tg-me.com/Mgetem
https://www.tg-me.com/Mgetem

ለአስተያየት : @abeltadele
​ዮሐንስ
 
በሠላሳ ክረምት ጌታን ላጠመቀ፤
የየወር ሠላሳ እየተጠበቀ፤
የብዙዎች ደስታ ፤
የሆነ ልደቱን ካለንበት ቦታ፤
ተውጣጥተን ስናስብ በደብረ መቅደሱ፤
ሻማ እንዳትለኩሱ፤
በተወደደ ማር ጧፍም አትጨርሱ፤
ሚነድ የሚያበራ መብራት ነው ራሱ!!                                  
    
©ከሣቴ ብርሃን
____
www.tg-me.com/andkelem
www.tg-me.com/andkelem
2025/07/08 02:20:46
Back to Top
HTML Embed Code: