Telegram Web Link
Forwarded from Kesatebirhan Ze Tewahdo (Channels)
​​ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ- እግዚአብሔር እንዴት ይፈርዳል? -

“ይኼ ሁሉ በዓለም እየሆነ እየተደረገ ግን እግዚአብሔር እንዴት ዝም ይላል?እውን የሠራዊት ጌታ በመንበሩ አለ?” የሚል የራሔል ጥያቄ ለአፍታ ጎብኝቶት ከሆነ ይኼ ቪድዮ የማያዳግም መልስ አለው።

👇👇👇👇👇
https://youtu.be/s9xfl8nCk14
https://youtu.be/s9xfl8nCk14
Forwarded from Kesatebirhan Ze Tewahdo (Channels)
​​“እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል አላልኩም" የሆሣዕናዋ አህያ

በአእምሮ ስቱዲዮ ሃሳብ በተባለ ፕሮግራም ላይ የሆሣዕናዋን አህያ ጠርቼ ቃለ መጠይቅ አድርጌላታሁ። አስገራሚና አዝናኝ ትዝታዋንን እንዲህ አካፍላኛለች።ስሟት እስቲ።

ከሆሣዕናዋ አህያ ጋር የተደረገ ቃለመጠይቅ - ክፍል 1

👇👇👇👇👇👇👇👇
https://youtu.be/e_G9GiRdVDc
https://youtu.be/e_G9GiRdVDc
👍21
Forwarded from Kesatebirhan Ze Tewahdo (Channels)
​​“እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል አላልኩም" የሆሣዕናዋ አህያ

በአእምሮ ስቱዲዮ ሃሳብ በተባለ ፕሮግራም ላይ የሆሣዕናዋን አህያ ጠርቼ ቃለ መጠይቅ አድርጌላታሁ። አስገራሚና አዝናኝ ትዝታዋንን እንዲህ አካፍላኛለች።ስሟት እስቲ።

ከሆሣዕናዋ አህያ ጋር የተደረገ ቃለመጠይቅ - ክፍል 1

👇👇👇👇👇👇👇👇
https://youtu.be/e_G9GiRdVDc
https://youtu.be/e_G9GiRdVDc
1👍1
​​“እኔ ከሞትኩ ሰርዶ አይብቀል አላልኩም" የሆሣዕናዋ አህያ

በአእምሮ ስቱዲዮ ሃሳብ በተባለ ፕሮግራም ላይ የሆሣዕናዋን አህያ ጠርቼ ቃለ መጠይቅ አድርጌላታሁ። አስገራሚና አዝናኝ ትዝታዋንን እንዲህ አካፍላኛለች።ስሟት እስቲ።

ከሆሣዕናዋ አህያ ጋር የተደረገ ቃለመጠይቅ - ክፍል 1

👇👇👇👇👇👇👇👇
https://youtu.be/e_G9GiRdVDc
https://youtu.be/e_G9GiRdVDc
👍2
Forwarded from Kesatebirhan Ze Tewahdo (Channels)
​​📌 #ክፍል2
ምናባዊ ቆይታዬ ቀጥሏል። “የማወጣው ድምጽ ለእናንተ ማናፋት ለእኔ ግን ስብሐት ነው።” ታለናለች የሆሣዕናዋ አህያ

ከሆሣዕናዋ አህያ ጋር የተደረገ ቃለ መጠይቅ ክፍል - 2

👇👇👇👇👇👇
https://youtu.be/1Qsdjo9LpAY
https://youtu.be/1Qsdjo9LpAY
👍1
Forwarded from Kesatebirhan Ze Tewahdo (Channels)
​​📌 #ክፍል2
ምናባዊ ቆይታዬ ቀጥሏል። “የማወጣው ድምጽ ለእናንተ ማናፋት ለእኔ ግን ስብሐት ነው።” ታለናለች የሆሣዕናዋ አህያ

ከሆሣዕናዋ አህያ ጋር የተደረገ ቃለ መጠይቅ ክፍል - 2

👇👇👇👇👇👇
https://youtu.be/1Qsdjo9LpAY
https://youtu.be/1Qsdjo9LpAY
👍1
Forwarded from Kesatebirhan Ze Tewahdo (Channels)
​​📌 #ክፍል2
ምናባዊ ቆይታዬ ቀጥሏል። “የማወጣው ድምጽ ለእናንተ ማናፋት ለእኔ ግን ስብሐት ነው።” ታለናለች የሆሣዕናዋ አህያ

ከሆሣዕናዋ አህያ ጋር የተደረገ ቃለ መጠይቅ ክፍል - 2

👇👇👇👇👇👇
https://youtu.be/1Qsdjo9LpAY
https://youtu.be/1Qsdjo9LpAY
Forwarded from Kesatebirhan Ze Tewahdo (Channels)
​​“የጻድቁ ዮሐንስ ሕገ መንግሥት ይከበር!!" - ከሆሣዕናዋ አህያ ጋር የተደረገ ቃለ መጠይቅ - የመጨረሻው ክፍል

እነሆ በበዓለ ሆሣዕናው የቃለ መጠይቃችንን የመጨረሻ ክፍል ይዘንላችሁ ቀርበናል። አህያይቱ ከበድ ያለ
መልእክትና ጥያቄም በማቅረብ ትዘጋዋለች።
👇👇👇👇👇
https://youtu.be/o6NkpAD8en4
https://youtu.be/o6NkpAD8en4
Forwarded from Kesatebirhan Ze Tewahdo (Sol)
🌿እንኳን ለሆሣዕና በዓል አደረሳችሁ🌿

በአእምሮ ስቱዲዮ ሃሳብ በተባለ ፕሮግራም ላይ የሆሣዕናዋን አህያ ጠርቼ ቃለ መጠይቅ አድርጌላታሁ። አስገራሚና አዝናኝ ትዝታዋንን እንዲህ አካፍላኛለች።ስሟት እስቲ።

1⃣ ከሆሣዕናዋ አህያ ጋር የተደረገ ቃለ መጠይቅ ክፍል - 1
👇👇👇
https://youtu.be/e_G9GiRdVDc

2⃣ ከሆሣዕናዋ አህያ ጋር የተደረገ ቃለ መጠይቅ ክፍል - 2
👇👇👇
https://youtu.be/1Qsdjo9LpAY

3⃣ ከሆሣዕናዋ አህያ ጋር የተደረገ ቃለ መጠይቅ - የመጨረሻው ክፍል
👇👇👇
https://youtu.be/o6NkpAD8en4

@kesatebirhanzetewahdo
@kesatebirhanzetewahdo
👍4
በእንተ እለተ ስቅለት
?????^^^ድንግልን እንዴት ላጽናናት^^^??? (እንጉርጉሮ)
@Mgetem

ጨረቃ ደምሆነች ጸሐይም ጨለመ
ከዋክብት ረገፉ፡ ሐኪሙ ታመመ
ልዑል ተዋረደ ጌታ ሎሌ ሆነ
በገዛ ፈጣሪው ፍጡሩ በየነ
ያችን ብላቴና እንደምን ላጽናናት?
አንድያዋን አጥታ፡ ዛሬ ሀዘን ላይ ናት
እንደምን ላባብላት፡ እንዴት ትረጋጋ
ችንካር የልጇን እጅ፡ ሀዘን ልቧን ወጋ
ይምጡ እስቲ ጥሯቸው፡ በሰማያት ያሉ
ሚካኤልገብርኤል፡ መላእክትበሙሉ
አንድያ እህታቸው፡ አንድልጇንአጥታ
ታለቅሳለችና፡ ከግሩሥርተደፍታ፡፡
የሆሳእና ሰው፡ ወዴት ተበተነ?
ከምኔው“ንጉስ”ባይ፡ “ልስቀልህ” ባይ ሆነ?
ከምኔው ሰጋጁ፡ በፍርድ መሰከረ?
እንዴት ከእጁ በልቶ፡ ደርሶ ዘነተረ?
አንዱችግረኛ፡-
በኢያሪኮ መንገድ፡ጽድቅን ያረቀቀ
ዛሬ በግፈኞች፡ እጅ ላይ ወቀደቀ
25 ጊዜ ዱላ አረፈበት፡ አፍንጫው ነሠረ
የዓለሙ መዓዛ፡ የደስታችን እጣን፡ ሽታው ደም ነበረ
ከጌቴሴማኒ፡ እስከነ ሐና ቤት
25 ጊዜ ሲደፋ ሲጎተት
አስረውት በገመድ፡ ኋለኞች ሲስቡት፡ ፊተኞች ለቀቁት፡ ወደ ኋላ ወደቀ
ፊተኞች ሲስቡት፡ ኋለኞች ለቀቁት፡ ወደ ፊት ወደቀ
እኛ ስንጮህበት፡ እሱ አረመመ፡ እኛ ስንወዛ፡ እሱ ግን ደቀቀ
ያችን ብላቴና:እንደምን ላጽናናት?
አንድያዋን አጥታ: ዛሬ ሀዘን ላይ ናት
በጎች ሆነን ሳለ፡ እሱ ግን እረኛ
ተክቶን ሊታረድ፡ በግ ሊሆን ስለኛ
40 ጊዜ ጡጫ፡ ሳይናገር ባ’ፉ
ጨክነው ፍጡራን፡ ፈጣሪ ላይ ተፉ
22 ጊዜ በጅንፎ ደረቱን
22 ጊዜ በአለን ጋልቡን
ክቡራን እጆቹ፡ ንዑዳን እግሮቹ፡ 65 ጊዜ
ተመቱ፡ ተላጡ፡ ሆኑ እንደ አዋዜ
ከካህናት አለቃ፡ ታስሮተ ወሰደ፡ ከሐናቀያፋ
ካፉ ምራቅ አልቆ፡ ወደቀ ደም ተፋ
ግርፋቱን አይተው፡ ‘ንዳያሳዝናቸው፡ ልባቸው እንዳይራራ
አንዱ እየገረፈ፡ ሌሎች በገበጣ፡ ሲረሱ ቆጠራ
ያለልማዳቸው፡ ብዙ ተገረፈ
አንዱ ተገራፊ፡ለሺህ ገራፊዎች፡በቃቸው፡ ተረፈ
ያችን ብላቴና፡እንደምን ላጽናናት?
አንድያዋን አጥታ:ዛሬ ሀዘን ላይ ናት
300 እሾህ ያለው፡ በከበረው ራሱ፡ሥረወፅ ደረበ
የእሾህ አክሊል ደፋ፡ 73 ቦታ፡ ደም ከርሱ ነጠበ
ተሸከመ ሄደ፡ ተሳለቁገ ፉት
በልባቸው ጠሉት፡ ባፋቸውዘለፉት፡፡
በዚያልቶስጥራ፡ በዚያ የእንጨት ሀገር
በ8 እጽዋት መስቀል ሆኖ ነበር፡፡
እጸ-ዘይትና እንዲሁ እጸ-ከርካዕ
እጸ-በለስ፡ እጸ-ወይራ፡ እጸ-ሥርናይ
ልቡን በአዴራ፡ በታላላቅ ችንካር
ደረቱን በሮዳስ፡ ቀኝ እጁን በሳዶር
እግሮቹን በዳናት፡ ግራ እጁን በአላዶር
ሆኖ ባየች ጊዜ፡ ልጇ ተሰቅሎባት
ያችን ብላቴና፡ ምን ብዬ ላጽናናት?
አንድያዋን አጥታ፡ ድንግል ሀዘን ላይ ናት
ብርሃንን የፈጠረ፡ ዓይኖቹን ሸፈኑ
ያንን ርህሩሁን ፊት፡ ሊመቱ ጨከኑ
እንደ ተቸገረ፡ 'ሚያዝንለት እንዳጣ
እንደ ተረገመመም፡ በሁሉ እንደ ተቀጣ
እንደ ምስኪን ደሀ፡ ቀን እንደራቀው ሰው
ምድርን ያስጌጣት፡ አጣሳ ይለብሰው?
ንገረኝ ጌታዬ፡ በእጅህ ከፈጠርከው
ማንን ልብስ ነሳህ፡ ማንን አራቆትከው?
ይህን ጊዜ እናቱን: ምን ብዬ ላጽናናት?
የደስታ ምንጭ ሆና፡ ሀዘንተኛዋ ናት፡፡
እንደ ቀማ ወንበዴ፡ ዱር እንዳለ ሽፍታ
ሀገር እንዳጠፋ፡ ተሰቀለ ጌታ
እንደ ትንቢቱ ቃል፡ እንደ ተነገረው
ረዳት እንደ ሌለው፡ ሆነ እንደ ቸገረው
ባየነውም ጊዜ፡ አላከበርነውም
እንወደውም ዘንድ: ደም ግባት የለውም
እኛ ግን መታነው፡ እሱ ታገሰልን
እኛው አደማነው፡ ደምን ለበሰልን
ልብን የሚጠግን፡ ልቡ ላይ ወጋነው
በችንካር ቸንክረን፡ በዋንጫ ቀዳነው
አቤቱ አምላኬ፡ ታማኙ መድኅኔ
እሽ ብለህ የሞትክ፡ ለሰቀልኩህ እኔ
ስለ ኃይል ትርጉም፡ በብርታ ትስጠብቅ
አንተ በትህትና፡ መጣህ ልታሳውቅ
ስህተት በሞላበት፡ የኃይ ልግንዛቤ
ትዕቢት በገነባው፡ እንዳይገኝ ልቤ
አቤት ያንተ ፍቅር፡ አቤት ያንተነገር
በዚያች ጭንቅ ሰዓት፡ ስለ ሰቃዮችህ፡ መዳን ታስብ ነበር፡፡
ያ ስደት የኔነው፡ የኔ ነው ሰንበሩ
ጩሀትህም ጩሀቴ፡ የኔ ነው ችንካሩ
በደሌን ቻልክልኝ፡ ሆነህ በኔ ቦታ
ሞትህ ሞቴ ነበር፡ መድኃኒቴ ጌታ
ልኖር ተወልጄ፡ ሞት ስላሸነፈኝ፡ ልጄ በርታ እያልከኝ
አንተ ልትሞት መጥተህ፡ ማሸነፊያ ሆንከኝ
ግን
ያችን የሀዘን እናት
ያችን ብላቴና ምን ብዬ ላጽናናት
ድንግል ስለ ልጇ: ዛሬ ሀዘን ላይ ናት፡፡
(አክሊሉ ደበላ..ሚያዝያ 2007ዓ.ም
@Mgetem
@Mgetem
@Solasc12
👍2815😢10
"በአትክልቱ ሥፍራ"
+++++++
@Mgetem

የጌታ መቃብር - የተቀበረበት፣
ያትክልት ሥፍራውም - ትንሣኤ የታየበት፣
ምልክቶች ናቸው - ለኤደን ለገነት፣
አዳም ሥውር ሞትን ሞቶ ለጠፋበት።

አዳም ሲሞትማ-በዛፎቹ መኻል-ራሱን ደበቀ፣
በለስ ቀጥፎ በልቶ-በመተላለፉ-ከፈጣሪ ራቀ።
መቃብር ውስጥ ገብቶ-እንደ ተዘጋበት-ይመስላል ሽሽጉ፣
በዛፎች ከለላ-መሠወር ማሰቡ-ያ አዳም ያ ዝንጉ።

አንዴ የተቀበረው - ሕያው አምላካችን
በአትክልቱ ሥፍራ - ተነሥቷል ጌታችን።

በአትክልት ሥፍራ ውስጥ-ዛፎች በበዙበት-ወድቆ የነበረው፣
የሞተውን አዳም-ጌታችን ሲነሣ-አንሥቶ አከበረው።

ይህ ያትክልት ሥፍራ - መቃብር ያለበት፣
የከበረው አዳም - ስለማይኖርበት፣
ሰርግ ወዳለበቱ-በገነት ወዳለው-የአትክልት ቦታ፣
ክርስቶስ አዳምን ወሰደው በእልልታ።

(ጌታችን ከትንሣኤው በኋላ ለማርያም መግደላዊት በአትክልቱ ሥፍራ መታየቱን ቅዱስ ኤፍሬም ሶርያዊ በውዳሴ ስቅለት (Hymns on crucifixion /8:13/ በውብ ግጥሙ ያመሰጠረውን እንደተረጎምኩት)
++++++
ዲ/ን ሕሊና በለጠ
__________________
@Mgetem
@Mgetem
@solasc12
👍153
በአእምሮ ስቱዲዮ ሃሳብ በተባለ ፕሮግራም ላይ የሆሣዕናዋን አህያ ጠርቼ ቃለ መጠይቅ አድርጌላታሁ። አስገራሚና አዝናኝ ትዝታዋንን እንዲህ አካፍላኛለች።ስሟት እስቲ።

1⃣ ከሆሣዕናዋ አህያ ጋር የተደረገ ቃለ መጠይቅ ክፍል - 1
👇👇👇
https://youtu.be/e_G9GiRdVDc

2⃣ ከሆሣዕናዋ አህያ ጋር የተደረገ ቃለ መጠይቅ ክፍል - 2
👇👇👇
https://youtu.be/1Qsdjo9LpAY

3⃣ ከሆሣዕናዋ አህያ ጋር የተደረገ ቃለ መጠይቅ - የመጨረሻው ክፍል
👇👇👇
https://youtu.be/o6NkpAD8en4

@kesatebirhanzetewahdo
@kesatebirhanzetewahdo
👍1
Forwarded from Kesatebirhan Ze Tewahdo (♚sσια❛¹²❜)
#መድኃኔዓለም_ወይስ_የግል_አዳኝ - ግጥም

ዲ/ን ከሣቴብርሃን ገ/ኢየሱስ

ይህ መንፈሳዊ ግጥም የክርስቶስን የዓለም መድኃኒትነት በመጽሐፍ ቅዱስ ታሪኮች በማስረገጥ "የግል አዳኝ" ባዮችን ይሞግታል።

እኛም ይኼን ድንቅ የሥንኝ ቋጠሮ ወርሀዊ መታሰቢያውን በማስታከክ ጀባ ብለናችኋል።
👇👇👇👇
https://youtu.be/2T9kWYsC7w0
https://youtu.be/2T9kWYsC7w0

______________________
Please Subscribe and share
@kesatebirhanzetewahdo
👍1
Forwarded from Kesatebirhan Ze Tewahdo (♚sσια❛¹²❜)
#የማንነት_ጥያቄ - ግጥም

ዲ/ን ከሣቴብርሃን ገ/ኢየሱስ

ይህ የሥንኝ ቋጠሮ ከየትኛው ብሔር ነህ ለሚል የቸከ ዘመነኛ ጥያቄ የማያዳግም ኦርቶዶክሳዊ ምላሽ ይሰጣል። የአቋም መግለጫው የተወረሰው ቅዱስ ሚካኤል ለኢያሱ ጥያቄ ከመለሰለት መልስ ነው። ተጋበዙልን።
👇👇👇👇👇
https://youtu.be/4ZWRKw-TpyM
https://youtu.be/4ZWRKw-TpyM
___________
ሰብስክራይብ | Subscribe 👇 Kesatebirhan Ze Tewahdo

🔔
👍1
እናቱ እናቴ - ልደትሽ ልደቴ !
(በመላኩ አላምረው)
@Mgetem

+ + +
ለእናትነት ክብር - እርሱ ከመረጠሽ
በዮሐንስ በኩል - ለእኔ ከተሰጠሽ
እኔም እርሱን ጌታ - ብዬ ከተቀበልሁ
ማዳኑን አምኜ - በሕጉ ስር ከዋልሁ
እናቱን እናቴ - ብየ ለመቀበል...
ጥያቄ ልደርድር? ለምን? እንዴት? ልበል?
+ + +
ልጅሽ በምድር ላይ - ሥጋሽን በመልበስ
አዳምን ሊያድነው - ለእኛም ጽድቅን ሊያወርስ
የረገጠው መሬት - የቆመበት ቦታ
ከቤተልሄም ዋሻ - እስከ ጎለጎታ
ቅዱስ ከተባለ - ውሎ ያደረበት
ልዩ ክብር ካለው - የተሰቀለበት...
አንችማ እናቱ - ማህፀን ዓለሙ
የሰውነት ልኩ - ሥጋውና ደሙ
እንዴት አትከብሪ!? እንዴት አትቀደሽ!?
እንዴት አትወደጅ!? እንዴት አትወደሽ!?
+ + +
እንኳንስ ለእኔና...
ለእርሱም ለጌታችን - ፈጣሪ ለሆነ
እናቱ መባልሽ - ይህ እውነት ከሆነ
እናቴ መሆንሽ - እንዴት አልታመነ???
+ + +
በሥጋ ያይደለ - በረቀቀ መንፈስ
እናቴ ሆነሽኝ - ያንችን ክብር ብወርስ
ይሄንን መታደል - እንዴት እገፋለሁ?
እናቱ እናቴ ነሽ! - ተቀብየሻለሁ!!!
+ + +
ፈጣሪን ልትወልጅው - አምላክን ልታ’ዥው
ሰማይና ምድር የማይወስኑትን - በእቅፍሽ ልትይዥው
ከድንግልና ጡት - ወተት ልታጠቢው
የዓለሙን መጋቢ...
ከደኃ ማጀትሽ - ሲራብ ልትመግቢው
እናት አባትሽን - ከእስር ልታስፈቺ
የክፋትን አባት - በፍቅር ልትረቺ
ከሀና ከኢያቄም - የተወለድሽ አንቺ
እናትና ድንግል - ንግሥትና አገልጋይ
ሰማየ ሰማያት - ጽርሐ አርያም ሆይ!
የአንቺ ግሩም ልደት - ለእኔም ነው ልደቴ
የጥምቀት መሥራቹ - ልጅሽ ነው አባቴ
ዳግም የተወለድሁ - ከውኃና መንፈስ
ባንቺ መወለድ ነው - የአዳም ተስፋው ሲደርስ
ሕይወት የሆነልን - የልጅሽ ሥጋና ደም
ከአንቺው ነው የነሳው - ከላይ አልወረደም
ዝም ማለት ያልቻልኩት - ለዚህ ነው ድፍረቴ
ልጅሽ ሕይወቴ ነው !
እናቱ እና ነሽ - ልደትሽ ልደቴ
+ + +
+
ቅድስተ ቅዱሳን - ንጽሒተ ንጹሐን
ማሕጸኑ ለጽድቅ - እናቱ ለብርሃን
ሰማየ ሰማያት - ታናሽ ብላቴና
ከእያቄም ወሀና - ተወለደሻልና
ዓለም ብርሃን አየ - ውስጥሽ ባለው ፀሐይ
አዳም ቀና አለ - ተስፋ ብርሃኑን ሊያይ
ፍጥረታት በሙሉ - ከሰማይ ከምድር
በደስታ ተመሉ - ልደትሽ ሲነገር
ተወለደሻልና - የፀሐይ እናቱ
ጽርሃሐ-አርያም ሆንሽ - ብላቴናይቱ !
+ + +
+
(፡›አበው ስለክብርሽ - ቃላት አጠራቸው
ስለ ደም ግባትሽ - ምሳሌ ጠፋቸው
እኔ ግን ደፋሩ - እዘባርቃለሁ
ባልበሰለ ብዕር - ቃላት እመርጣለሁ
በተንሸዋረረ ዓይን - ክብርሽን አያለሁ
ምልጃሽን እያሰብሁ - በተስፋ እኖራለሁ‹፡)
+ + +
የብርሃን እናቱ - የፀሐይ ምሥራቁ
የአዳም ሙሉ ተስፋ - የሰይጣን መብረቁ
ስለ አንቺ መወለድ - ዓለም ተፈጠረ
ስለ አንቺ መወለድ - የሰው ልጅ ከበረ
አዳምና ዘሩ - በኃጢአት ቢረክሱ
በአንቺ መወለድ - ግን በክብር ነገሡ
በአንቺ ልዩ ልደት - አዳም አምላክ ሆነ
በአንቺ ልዩ ልደት - ክብራችን ገነነ
በአንቺ ልዩ ልደት - ዲያብሎስ ታሰረ
በአንቺ ልዩ ልደት - ባሪያ መሆን ቀረ
እኔም ደፋር ሆንኩኝ - ፍርሃት ተሰወረ
ባዶው አዕምሮዬ - ክብርሽን ነገረ፡፡
+ + +
ሰማይና ምድር - ልደትሽን ሲያከብሩ
ሊቃውንት ሲቀኙ - መላእክት ሲዘምሩ
ክብርሽን ተማምነው - በምልጃሽ ያደሩ
በምህረት ቃል ኪዳን - ለክብር ሲጠሩ
እንደልጅነቴ ለእኔም - እንዲደርሰኝ
እንባሽን አስታውሶ - ልጅሽ እንዲምረኝ
ዝም ማለት ያልቻልኩት - ለዚህ ነው ድፍረቴ
የአንቺ መወለድ ነው - የጽድቅ መሠረቴ
ልጅሽ ሕይወቴ ነው !
እናቱ እናቴ ነሽ - ልደትሽ ልደቴ፡፡
+ + +
@Mgetem
@Mgetem_Group
@Solasc12
👍6314👏9🥰3
​​ቅርብኝ ቅርብኝ
@Mgetem

ራስ እኔነቴን ካዋረደ፤
እፍረትን በእኔ ላይ ካንጓደደ፤
እኔስ እንዴት ላክብረው ራሴን?
ቁልቁል ከጣለው ማንነቴን?
እረ ወዲያ በቃኝ ራስነቱ ይቅርብኝ፤
ጡረተኛን ጣሪ አካል ካደረገኝ፤
ካልጠቀመኝ ራስነቱ፤
ካልረባን አክሊልነቱ፤
እረ ወዲያ ይቅርብኝ፤
ራሱ ገምቶ አካሌን አያግማው፤
ራሱ ያመጣውን ራሱ ይወጣው፤
በሕሊናዬም አይታሰብ ስም አጠራሩም አይታወስ፤
ሰላሜን አይንሳ ብስጭቴን አይቀስቅስ፡፡
ግና እግዚአብሔር በእርሱ ከነገሠ ፤
ነፍሱን ለጌታው ፈቃድ ካፈሰሰ፤
ይምጣ ይግባ ራስም ይሁነኝ፤
በርቶ ያድምቀኝ ሞቆ ያሙቀኝ፤
ሕያው ሆኖ ያኑረኝ ብርሃንን ያልብሰኝ፤
ያለበለዚያ ወዲያ ወዲያ ክላልኝ አትምጣብኝ፡፡
ጫንቃዬ ሰልችቶአል ጡረተኛን ማዘል፤
እሹሩሩ ማለት ጡጦ እየሰጡ ማባበል፡፡

@Mgetem
@Mgetem_group
@SoLaSc12
👍195
Forwarded from Kesatebirhan Ze Tewahdo (Channels)
​​ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ- እግዚአብሔር እንዴት ይፈርዳል? -

“ይኼ ሁሉ በዓለም እየሆነ እየተደረገ ግን እግዚአብሔር እንዴት ዝም ይላል?እውን የሠራዊት ጌታ በመንበሩ አለ?” የሚል የራሔል ጥያቄ ለአፍታ ጎብኝቶት ከሆነ ይኼ ቪድዮ የማያዳግም መልስ አለው።

👇👇👇👇👇
https://youtu.be/s9xfl8nCk14
https://youtu.be/s9xfl8nCk14
👏2👎1
Forwarded from Bereket Gudisa
የመጀመሪያው የዳረጎት የወረቀት ህትመት መጽሔት ለአንባቢዎች ሊቀርብ ነው።

''አለቃ መሠረት'' የተሰኘውና የዳረጎት ሚዲያ አባላትን ጨምሮ በርካቶችን በማስተማር መሠረት በሆኑት መጋቤ ምሥጢር መሠረት ተሰማ የሕይወት ታሪክ፤ የጿፏቸውን የሥነ-ጹሑፍ ሥራዎች፤ የተደረሱላቸውን ቅኔያት፤ የልጆቻቸውን ምስክርነትን የያዘ መጽሔት ተዘጋጅቶ ለአንባቢያን ሊቀርብ ነው።

በመጽሔቱ የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ መንበረ ፓትርያሪክ ጠ/ጽ/ቤት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ የሰበካ ጉባኤ ማደራጃ መምሪያ ኃላፊና የአርሲና የምሥራቅ ጎጃም አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ያሬድ ጨምሮ የሀገረስብከቱ ከፍተኛ አመራሮችና አባቶች መልዕክት አስተላልፈዋል።

በ48 ገጾች የተዘጋጀው የዳረጎት ዘተዋህዶ መጽሔት ልዩ ዕትም ስለ መጋቤ ምሥጢር አለቃ መሰረት ተሰማ ተነግረው የማይጠገቡና ለጆሮ አዲስ የሆኑ ታሪኮችን በውስጡ አካቷል።

በጽሔቱ በ700 ቅጂ ለህትመት የሚበቃ ሲሆን ከፊታችን አርብ ጀምሮ በአሰላ ደብረ መድኃኒት መድኀኔዓለም ቤተክርስቲያን የአባታችንን የ፵ ቀን መታሰቢያ አስመልክቶ በተዘጋጀው ጉባኤ ላይ በይፋ ተመርቆ ለአንባቢያን ይቀርባል።

በዚህ የመታሰቢያ ጉባኤ ላይ ታላላቅ መምህራነ ወንጌልና ዘማሪያን እንዲሁም ተማሪዎቻቸው ይገኛሉ። በህይወት ታሪካቸው ላይ ያተኮረ አጭር ዶክመንተሪም ለዕይታ ይበቃል። ዳረጎት ሚዲያ በአሰላ ከተማና አከባቢዋ ለሚገኙ ቤተሰቦቹ በዚህ ትልቅ ጉባኤ ላይ ተገኝተው የበረከቱ ተካፋይ እንዲሆኑ ጥሪ ያቀርባል።
👍61
2025/07/08 23:09:20
Back to Top
HTML Embed Code: