Telegram Web Link
Forwarded from Kesatebirhan Ze Tewahdo (♚sσια❛¹²❜)
#የማንነት_ጥያቄ - ግጥም

ዲ/ን ከሣቴብርሃን ገ/ኢየሱስ

ይህ የሥንኝ ቋጠሮ ከየትኛው ብሔር ነህ ለሚል የቸከ ዘመነኛ ጥያቄ የማያዳግም ኦርቶዶክሳዊ ምላሽ ይሰጣል። የአቋም መግለጫው የተወረሰው ቅዱስ ሚካኤል ለኢያሱ ጥያቄ ከመለሰለት መልስ ነው። ተጋበዙልን።
👇👇👇👇👇
https://youtu.be/4ZWRKw-TpyM
https://youtu.be/4ZWRKw-TpyM
___________
ሰብስክራይብ | Subscribe 👇 Kesatebirhan Ze Tewahdo

🔔
እናቱ እናቴ - ልደትሽ ልደቴ !
(በመላኩ አላምረው)
@Mgetem

+ + +
ለእናትነት ክብር - እርሱ ከመረጠሽ
በዮሐንስ በኩል - ለእኔ ከተሰጠሽ
እኔም እርሱን ጌታ - ብዬ ከተቀበልሁ
ማዳኑን አምኜ - በሕጉ ስር ከዋልሁ
እናቱን እናቴ - ብየ ለመቀበል...
ጥያቄ ልደርድር? ለምን? እንዴት? ልበል?
+ + +
ልጅሽ በምድር ላይ - ሥጋሽን በመልበስ
አዳምን ሊያድነው - ለእኛም ጽድቅን ሊያወርስ
የረገጠው መሬት - የቆመበት ቦታ
ከቤተልሄም ዋሻ - እስከ ጎለጎታ
ቅዱስ ከተባለ - ውሎ ያደረበት
ልዩ ክብር ካለው - የተሰቀለበት...
አንችማ እናቱ - ማህፀን ዓለሙ
የሰውነት ልኩ - ሥጋውና ደሙ
እንዴት አትከብሪ!? እንዴት አትቀደሽ!?
እንዴት አትወደጅ!? እንዴት አትወደሽ!?
+ + +
እንኳንስ ለእኔና...
ለእርሱም ለጌታችን - ፈጣሪ ለሆነ
እናቱ መባልሽ - ይህ እውነት ከሆነ
እናቴ መሆንሽ - እንዴት አልታመነ???
+ + +
በሥጋ ያይደለ - በረቀቀ መንፈስ
እናቴ ሆነሽኝ - ያንችን ክብር ብወርስ
ይሄንን መታደል - እንዴት እገፋለሁ?
እናቱ እናቴ ነሽ! - ተቀብየሻለሁ!!!
+ + +
ፈጣሪን ልትወልጅው - አምላክን ልታ’ዥው
ሰማይና ምድር የማይወስኑትን - በእቅፍሽ ልትይዥው
ከድንግልና ጡት - ወተት ልታጠቢው
የዓለሙን መጋቢ...
ከደኃ ማጀትሽ - ሲራብ ልትመግቢው
እናት አባትሽን - ከእስር ልታስፈቺ
የክፋትን አባት - በፍቅር ልትረቺ
ከሀና ከኢያቄም - የተወለድሽ አንቺ
እናትና ድንግል - ንግሥትና አገልጋይ
ሰማየ ሰማያት - ጽርሐ አርያም ሆይ!
የአንቺ ግሩም ልደት - ለእኔም ነው ልደቴ
የጥምቀት መሥራቹ - ልጅሽ ነው አባቴ
ዳግም የተወለድሁ - ከውኃና መንፈስ
ባንቺ መወለድ ነው - የአዳም ተስፋው ሲደርስ
ሕይወት የሆነልን - የልጅሽ ሥጋና ደም
ከአንቺው ነው የነሳው - ከላይ አልወረደም
ዝም ማለት ያልቻልኩት - ለዚህ ነው ድፍረቴ
ልጅሽ ሕይወቴ ነው !
እናቱ እና ነሽ - ልደትሽ ልደቴ
+ + +
+
ቅድስተ ቅዱሳን - ንጽሒተ ንጹሐን
ማሕጸኑ ለጽድቅ - እናቱ ለብርሃን
ሰማየ ሰማያት - ታናሽ ብላቴና
ከእያቄም ወሀና - ተወለደሻልና
ዓለም ብርሃን አየ - ውስጥሽ ባለው ፀሐይ
አዳም ቀና አለ - ተስፋ ብርሃኑን ሊያይ
ፍጥረታት በሙሉ - ከሰማይ ከምድር
በደስታ ተመሉ - ልደትሽ ሲነገር
ተወለደሻልና - የፀሐይ እናቱ
ጽርሃሐ-አርያም ሆንሽ - ብላቴናይቱ !
+ + +
+
(፡›አበው ስለክብርሽ - ቃላት አጠራቸው
ስለ ደም ግባትሽ - ምሳሌ ጠፋቸው
እኔ ግን ደፋሩ - እዘባርቃለሁ
ባልበሰለ ብዕር - ቃላት እመርጣለሁ
በተንሸዋረረ ዓይን - ክብርሽን አያለሁ
ምልጃሽን እያሰብሁ - በተስፋ እኖራለሁ‹፡)
+ + +
የብርሃን እናቱ - የፀሐይ ምሥራቁ
የአዳም ሙሉ ተስፋ - የሰይጣን መብረቁ
ስለ አንቺ መወለድ - ዓለም ተፈጠረ
ስለ አንቺ መወለድ - የሰው ልጅ ከበረ
አዳምና ዘሩ - በኃጢአት ቢረክሱ
በአንቺ መወለድ - ግን በክብር ነገሡ
በአንቺ ልዩ ልደት - አዳም አምላክ ሆነ
በአንቺ ልዩ ልደት - ክብራችን ገነነ
በአንቺ ልዩ ልደት - ዲያብሎስ ታሰረ
በአንቺ ልዩ ልደት - ባሪያ መሆን ቀረ
እኔም ደፋር ሆንኩኝ - ፍርሃት ተሰወረ
ባዶው አዕምሮዬ - ክብርሽን ነገረ፡፡
+ + +
ሰማይና ምድር - ልደትሽን ሲያከብሩ
ሊቃውንት ሲቀኙ - መላእክት ሲዘምሩ
ክብርሽን ተማምነው - በምልጃሽ ያደሩ
በምህረት ቃል ኪዳን - ለክብር ሲጠሩ
እንደልጅነቴ ለእኔም - እንዲደርሰኝ
እንባሽን አስታውሶ - ልጅሽ እንዲምረኝ
ዝም ማለት ያልቻልኩት - ለዚህ ነው ድፍረቴ
የአንቺ መወለድ ነው - የጽድቅ መሠረቴ
ልጅሽ ሕይወቴ ነው !
እናቱ እናቴ ነሽ - ልደትሽ ልደቴ፡፡
+ + +
@Mgetem
@Mgetem_Group
@Solasc12
​​ቅርብኝ ቅርብኝ
@Mgetem

ራስ እኔነቴን ካዋረደ፤
እፍረትን በእኔ ላይ ካንጓደደ፤
እኔስ እንዴት ላክብረው ራሴን?
ቁልቁል ከጣለው ማንነቴን?
እረ ወዲያ በቃኝ ራስነቱ ይቅርብኝ፤
ጡረተኛን ጣሪ አካል ካደረገኝ፤
ካልጠቀመኝ ራስነቱ፤
ካልረባን አክሊልነቱ፤
እረ ወዲያ ይቅርብኝ፤
ራሱ ገምቶ አካሌን አያግማው፤
ራሱ ያመጣውን ራሱ ይወጣው፤
በሕሊናዬም አይታሰብ ስም አጠራሩም አይታወስ፤
ሰላሜን አይንሳ ብስጭቴን አይቀስቅስ፡፡
ግና እግዚአብሔር በእርሱ ከነገሠ ፤
ነፍሱን ለጌታው ፈቃድ ካፈሰሰ፤
ይምጣ ይግባ ራስም ይሁነኝ፤
በርቶ ያድምቀኝ ሞቆ ያሙቀኝ፤
ሕያው ሆኖ ያኑረኝ ብርሃንን ያልብሰኝ፤
ያለበለዚያ ወዲያ ወዲያ ክላልኝ አትምጣብኝ፡፡
ጫንቃዬ ሰልችቶአል ጡረተኛን ማዘል፤
እሹሩሩ ማለት ጡጦ እየሰጡ ማባበል፡፡

@Mgetem
@Mgetem_group
@SoLaSc12
Forwarded from Kesatebirhan Ze Tewahdo (Channels)
​​ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ- እግዚአብሔር እንዴት ይፈርዳል? -

“ይኼ ሁሉ በዓለም እየሆነ እየተደረገ ግን እግዚአብሔር እንዴት ዝም ይላል?እውን የሠራዊት ጌታ በመንበሩ አለ?” የሚል የራሔል ጥያቄ ለአፍታ ጎብኝቶት ከሆነ ይኼ ቪድዮ የማያዳግም መልስ አለው።

👇👇👇👇👇
https://youtu.be/s9xfl8nCk14
https://youtu.be/s9xfl8nCk14
Forwarded from Bereket Gudisa
የመጀመሪያው የዳረጎት የወረቀት ህትመት መጽሔት ለአንባቢዎች ሊቀርብ ነው።

''አለቃ መሠረት'' የተሰኘውና የዳረጎት ሚዲያ አባላትን ጨምሮ በርካቶችን በማስተማር መሠረት በሆኑት መጋቤ ምሥጢር መሠረት ተሰማ የሕይወት ታሪክ፤ የጿፏቸውን የሥነ-ጹሑፍ ሥራዎች፤ የተደረሱላቸውን ቅኔያት፤ የልጆቻቸውን ምስክርነትን የያዘ መጽሔት ተዘጋጅቶ ለአንባቢያን ሊቀርብ ነው።

በመጽሔቱ የኢ/ኦ/ተ/ቤ/ክ መንበረ ፓትርያሪክ ጠ/ጽ/ቤት ዋና ሥራ አስኪያጅ፣ የሰበካ ጉባኤ ማደራጃ መምሪያ ኃላፊና የአርሲና የምሥራቅ ጎጃም አህጉረ ስብከት ሊቀ ጳጳስ ብፁዕ አቡነ ያሬድ ጨምሮ የሀገረስብከቱ ከፍተኛ አመራሮችና አባቶች መልዕክት አስተላልፈዋል።

በ48 ገጾች የተዘጋጀው የዳረጎት ዘተዋህዶ መጽሔት ልዩ ዕትም ስለ መጋቤ ምሥጢር አለቃ መሰረት ተሰማ ተነግረው የማይጠገቡና ለጆሮ አዲስ የሆኑ ታሪኮችን በውስጡ አካቷል።

በጽሔቱ በ700 ቅጂ ለህትመት የሚበቃ ሲሆን ከፊታችን አርብ ጀምሮ በአሰላ ደብረ መድኃኒት መድኀኔዓለም ቤተክርስቲያን የአባታችንን የ፵ ቀን መታሰቢያ አስመልክቶ በተዘጋጀው ጉባኤ ላይ በይፋ ተመርቆ ለአንባቢያን ይቀርባል።

በዚህ የመታሰቢያ ጉባኤ ላይ ታላላቅ መምህራነ ወንጌልና ዘማሪያን እንዲሁም ተማሪዎቻቸው ይገኛሉ። በህይወት ታሪካቸው ላይ ያተኮረ አጭር ዶክመንተሪም ለዕይታ ይበቃል። ዳረጎት ሚዲያ በአሰላ ከተማና አከባቢዋ ለሚገኙ ቤተሰቦቹ በዚህ ትልቅ ጉባኤ ላይ ተገኝተው የበረከቱ ተካፋይ እንዲሆኑ ጥሪ ያቀርባል።
#አልችልም_አስችለኝ
@Mgetem

እየደነገጠ እየፈራ ልቤ
አንድነት አቅቶት ቅጥልጥል ሃሳቤ
ኮሽ ባለ ቁጥር እየፈራች ነፍሴ
አስጨንቀዋለሁ ራሴን በራሴ
አይኖቼ ተስፋዬን ማየት ተስኗቸው
እግሮቼ ጉዞዬን መጓዝ አቅቷቸው
ይቅበዘበዛሉ መሪ ጠፍቶባቸው
ዝም ባለ ጎጆ ጭጭ ባለ ሌሊት
ጩኸት ይሰማኛል ምንም በሌለበት
የሚያሳርፍ ጌታ እንዳለኝ ይወቀው
የሚያስጨንቀኝን አምላኬ አስጨንቀው
አንተ ድረስና የጭንቄን ውል ፍታ
አልችልም አስችለኝ እንዳልጠፋ ጌታ !

👇👇👇
https://app.golinks.io/twitter
https://app.golinks.io/twitter
Forwarded from Kesatebirhan Ze Tewahdo (መንፈሳዊ ግጥም ብቻ)
​​📌ኤላም ቤተ ስብሐት

ጥሩ የዝማሬ ጸጋ ኖሮት ፣ መዝሙር የማውጣት ምኞት ይዘው ግጥምና ዜማ ከየት አገኛለሁ ብለው ከተጨነቁ ወደ ኤላም ቤተ ስብሐት ይደውሉ።

በንባብም ሆነ በምሥጢር ኦርቶዶክሳዊ ደረጃቸውን የጠበቁ መንፈሳዊ የመዝሙር ግጥምና ዜማ ያገኛሉ።

💎ምን ምን ያገኛሉ?

👉 መደበኛ የምስጋና መዝሙራት
👉 የንስሐ መዝሙራት
👉 የበገና መዝሙራት
👉 የመዲናና ዘለሰኛ መዝሙራት
👉 የእማሆይ መዝሙራትን ያገኛሉ።

✍️ በተጨማሪም በመረጡት የትኛውም ርእሰ ጉዳይ በትእዛዝ እንጽፍልዎታለን።

ቅንብሩን ጨርሰው የግራፊክስ ዲዛይን ሥራ ካስፈለገም እንሠራልዎታለን። 📷

ኑ! ስብሐተ እግዚአብሔርን እናስፋ!
ኤላም ቤተ ስብሐት

📱ስልክ ቁጥር
+251912239783
+251912831494
📩 በቴሌግራም @kebras @solasc12
Forwarded from Kesatebirhan Ze Tewahdo (መንፈሳዊ ግጥም ብቻ)
​​📌ኤላም ቤተ ስብሐት

ጥሩ የዝማሬ ጸጋ ኖሮት ፣ መዝሙር የማውጣት ምኞት ይዘው ግጥምና ዜማ ከየት አገኛለሁ ብለው ከተጨነቁ ወደ ኤላም ቤተ ስብሐት ይደውሉ።

በንባብም ሆነ በምሥጢር ኦርቶዶክሳዊ ደረጃቸውን የጠበቁ መንፈሳዊ የመዝሙር ግጥምና ዜማ ያገኛሉ።

💎ምን ምን ያገኛሉ?

👉 መደበኛ የምስጋና መዝሙራት
👉 የንስሐ መዝሙራት
👉 የበገና መዝሙራት
👉 የመዲናና ዘለሰኛ መዝሙራት
👉 የእማሆይ መዝሙራትን ያገኛሉ።

✍️ በተጨማሪም በመረጡት የትኛውም ርእሰ ጉዳይ በትእዛዝ እንጽፍልዎታለን።

ቅንብሩን ጨርሰው የግራፊክስ ዲዛይን ሥራ ካስፈለገም እንሠራልዎታለን። 📷

ኑ! ስብሐተ እግዚአብሔርን እናስፋ!
ኤላም ቤተ ስብሐት

📱ስልክ ቁጥር
+251912239783
+251912831494
📩 በቴሌግራም @kebras @solasc12
እምዋ እናናዬዋ!
...
ምን ብዬ ደጁ ቆማለሁ
ፈራሁት የልጅሽ መልኩን፤
እልፍ አዕላፍ ስራዊት አለው
አውቃለሁ የስልጣን ልኩን
.
ዮሀንስ በድንገት ቢያየው
በቅፅበት ተንከባለለ፤
እንግዲህ እኔን አስቢኝ
ፃድቅ ሰው እቺን ታከለ
.
ከሞቴ እንደምን ልዳን
ቀሚሱን ቤት በኩል ልንካው፤
እንኳንስ ቀርበው ሊያዋዩት
እሳት ነው የራቀ ዱካው
..
.(አንቺ ግን እናናዬዋ)
.
አንቺ ግን ወለል አረግሽው
ቀለለ የገነት መስኮት፤
ፍም አቅፈሽ እሹሩሩ ያልሽ
አጃኢብ ስነ መለኮት

..
(አንቺማ እምዬን መሳይ)
.
የየዋህ የምስኪን ገፅሽ
የሀገሬ የእናቶች አምሳል፤
ምን ነበር ቆዳ ባረገኝ
ይህ መልክሽ በብሩሽ ሲሳል..
..
እምዬ _እታባሆዬ
እናዬ----ዋሻ ምርኩዜ፤
ማን አለኝ ካንቺ በስተቀር
የከፋኝ ችክ_ ያለኝ ጊዜ
.
እምዋ እናናዬዋ
..
.
ስንት አለት ስንት መከራ
ቁልቁለት ሲያንከባልለኝ፤
እሩጬ የማስጨንቅሽ
ቀሚስሽ እንዲከልለኝ
..
እምዋ እናናዬዋ
..
.
ምንገዱ ሁኖ አሜኬላ
ሲነድለኝ የህይወት ስንኩል፤
"ቅም" አርገሽ እቅፍ አረግሽኝ
ጉያሽ ስር ከልጅሽ እኩል.
.
እናዋ እናናዬዋ
እምዋ እናቴን መሳይ
______________
(አስቱ)
@Mgetem
@Mgetem
@Mgetem_group
አባ የትናንቱ
ዲያቆን ሄኖክ ኃይሌ
@Mgetem

ያለ ማወቅ ጽልመት ሀገሩን ሲወርሰው
ማን ነበር ትውልዱን በወንጌል ያረሰው?

አባ ተክለ ሃይማኖት አባ የትናንቱ
ትዝ አለኝ ተጋድሎው ውል አለኝ ሕይወቱ

በቆላ በደጋ የተንከራተትኸው
የሃይማኖትን ተክል ዞረህ የተከልኸው

የኢትዮጵያ ፀሐይ አባ ተክለ አብ
እስቲ መለስ ብዬ ሥራህን ላስብ

የክህደት ጨለማ በአንተ ሲርቅ
የሃይማኖት ብርሃን ሲያንጸባርቅ

በቀንና ሌሊት ከላይ ታች ዞረህ
ሕዝቡን አደረስከው አስተምረህ መክረህ

ስንት ነበር አባ ‹የጉዞ አበልህ›?
ያረፍህበት ስፍራ የተዘጋጀልህ

የት ነበር መኝታው ጎን ማሳረፊያህ?
ንገረኝ እባክህ ማን ነበር የሸኘህ?
እሳት አባቴ ሆይ እኔ አመድ ልጅህ

በዘመኔ ቋንቋ እስኪ ልጠይቅህ?
@Mgetem
@Mgetem
@Mgetem_group
መድኃኔዓለም - መንፈሳዊ ግጥም
👇
https://youtu.be/2T9kWYsC7w0

_____________________
@KesatebirhanZetewahdo
መንፈሳዊ ግጥም ብቻ pinned «መድኃኔዓለም - መንፈሳዊ ግጥም 👇 https://youtu.be/2T9kWYsC7w0 _____________________ @KesatebirhanZetewahdo»
2025/07/04 04:14:52
Back to Top
HTML Embed Code: