Forwarded from አንድ ቀለም ከከሡ ጋር
ለፃድቃን ከጻፍኳቸው የመዝሙር ግጥሞች በብዙ ቁጥር በመመዝገብ የአቡዬ ሥራዎች ግንባር ቀደሙ ነው። ወደ 10 አይጠጉም ብላችሁ ነው? ስላሳደጉኝ ነው መሰል ለአቡየ አደላለሁ። እሳቸው እሳቸውንም የጠየቅኋቸውን ሲሰሙ አይጣል ነው። በተለይ እሄዳለሁ ብዬ ባላሰብኩበት ሁኔታ መካነ መቃብራቸው ምድረ ከብድ ዕለተ እረፍታቸውን እዚያ እንዳከብር በአንዳች ተአምራዊ መንጀድ እንድሄድ ባደረጉበት 2015 እና 2016 የሚታይና የሚዳሰስ ተአምራትና ድንቅ በሕይወቴ ሲያደርጉ ነበር ብዬ እመሰክራለሁ። የፃድቁንም ሆነ ለሌሎች ቅዱሳን የተጻፉ ሙሉ ሥራዎቼን የ"እዩት" የመዝሙር ግጥም መድብል ቅጽ ሁለት የሆነው "ጉባኤያችን ማርያም" መጽሐፍ የፍልሰታ ሰሞን ሲወጣ አስነብባችኋለሁ። ለዕለተ ቀኑ ፣ ለበረከት ከዘማሪት ሕይወት ወልዴ ጋር አምና የሠራነውን ቆንጆ ሥራ ጋበዝኳችሁ።
ዝክረ ፃድቅ ለዓለም ይሄሉ!
https://youtu.be/YXEbsNVBKN0?si=w9is8WAEhdDH32eQ
ዝክረ ፃድቅ ለዓለም ይሄሉ!
https://youtu.be/YXEbsNVBKN0?si=w9is8WAEhdDH32eQ
YouTube
❤️ አዲስ ዝማሬ “ አቡነ ንብሎ “ ዘማሪት ሕይወት ወልዴ @-mahtot
❤️ አዲስ ዝማሬ “ አቡነ ንብሎ “ ዘማሪት ሕይወት ወልዴ @-mahtot
👍18❤4
🔔#ዝማሬ_ተዋሕዶ
💠" ሰብሕዎ ለእግዚአብሔር ስብሐተ ሐዲሰ ፣
እግዚአብሔርን በአዲስ ምስጋና አመስግኑት "
🗓 ግንቦት ፲፮ ቀን፣ ቀዳሚት
May 24, Saturday
⛪️ ብፁዕ አቡነ ዲዮናስዮስ የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ፣ ሊቃውንተ ቤ/ክ፣ ካህናት፣ የአጥቢያ ሰንበት ት/ቤቶች መዘምራን እና መላው ምእመናን በሚገኙበት
📍Eissporthalle Frankfurt
Am Bornheimer Hang 4
60386 Frankfurt am Main
የጀርመንና አካባቢው ሀገረ ስብከት
የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት ጉባኤ
📌https://www.facebook.com/share/1FRmn3x9RW/
✅
https://vm.tiktok.com/ZNdJuM8V9/
🖌ዲዛይን፦ በሀገረ ስብከቱ ሚድያ
💠" ሰብሕዎ ለእግዚአብሔር ስብሐተ ሐዲሰ ፣
እግዚአብሔርን በአዲስ ምስጋና አመስግኑት "
🗓 ግንቦት ፲፮ ቀን፣ ቀዳሚት
May 24, Saturday
⛪️ ብፁዕ አቡነ ዲዮናስዮስ የሀገረ ስብከቱ ሊቀ ጳጳስ፣ ሊቃውንተ ቤ/ክ፣ ካህናት፣ የአጥቢያ ሰንበት ት/ቤቶች መዘምራን እና መላው ምእመናን በሚገኙበት
📍Eissporthalle Frankfurt
Am Bornheimer Hang 4
60386 Frankfurt am Main
የጀርመንና አካባቢው ሀገረ ስብከት
የሰንበት ትምህርት ቤቶች አንድነት ጉባኤ
📌https://www.facebook.com/share/1FRmn3x9RW/
✅
https://vm.tiktok.com/ZNdJuM8V9/
🖌ዲዛይን፦ በሀገረ ስብከቱ ሚድያ
👍6❤4
መጻጕዕ
@Mgetem
(የዐቢይ ጾም አራተኛው ሳምንት ‹መጻጒዕ› ይባላል)
ልክ እንደ መጻጕዕ
እያየው ከሆንኩኝ ፥ የአለምን ነውር፤
በሥጋ ተመልካች ፥ በነፍስ ግን እውር፤
በአካል ከደጅህ ፥ ቆሜ ከሰው እኩል፤
እግረ ልቡናዌ ፥ ከሆነብኝ ስንኩል፤
በመውደቄ ብዛት ፥ ሀይሌ ከደከመ፤
ዘመናት ብቆጥርም ፥ ነፍሴ ከታመመ፤
ገዝተኸኛልና ፥ ከፍለህ የደም ዋጋ፤
መጥተህ እክታስነሳኝ ፥ ከኃጢአቴ አልጋ፤
ልክ እንደ መጻጕዕ ፥ ከፀበሉ ገንዳ፤
አፅናኝ እንዳሎጣ ፥ ከቤተ ሳይዳ ።
✍ አቤል ታደለ
https://www.tg-me.com/Mgetem
https://www.tg-me.com/Mgetem
https://www.tg-me.com/Mgetem
@Mgetem
(የዐቢይ ጾም አራተኛው ሳምንት ‹መጻጒዕ› ይባላል)
ልክ እንደ መጻጕዕ
እያየው ከሆንኩኝ ፥ የአለምን ነውር፤
በሥጋ ተመልካች ፥ በነፍስ ግን እውር፤
በአካል ከደጅህ ፥ ቆሜ ከሰው እኩል፤
እግረ ልቡናዌ ፥ ከሆነብኝ ስንኩል፤
በመውደቄ ብዛት ፥ ሀይሌ ከደከመ፤
ዘመናት ብቆጥርም ፥ ነፍሴ ከታመመ፤
ገዝተኸኛልና ፥ ከፍለህ የደም ዋጋ፤
መጥተህ እክታስነሳኝ ፥ ከኃጢአቴ አልጋ፤
ልክ እንደ መጻጕዕ ፥ ከፀበሉ ገንዳ፤
አፅናኝ እንዳሎጣ ፥ ከቤተ ሳይዳ ።
✍ አቤል ታደለ
https://www.tg-me.com/Mgetem
https://www.tg-me.com/Mgetem
https://www.tg-me.com/Mgetem
👍28❤14🥰6
#ውሸት_እናተንኮል
@Mgetem
ውሸትና ተንኮል ፣ ጓደኞች ነበሩ ፣
እውነትን ለማጥፋት ፣ እንዲህ ተማከሩ ።
እውነት የተባለው ፣ ይሄ ጠላታችን ፣
መጥፋት አለበት ፣ ጭራሽ ከዓለማችን ።
እኛ እየተጠላን ፣ እሱ እየተወደደ ፣
ብዙ ጊዜ አለፈ ፣ ዘመንም ነጎደ ።
የኛ ብቻ ይሁን ፣ መላው ሀገር ምድሩ ፣
ውሸትና ተንኮል ፣ እንዲህ ተማከሩ ።
ከዕለታት በአንዱ ቀን ፣ ተንኮል እያደባ ፣
ከውሸት ጋር ሆኖ ፣ ከእውነት ቤት ገባ ።
እውነት ከጓደኞቹ ፣ ሠላምና ፍቅር ፣
በደስታ በሀሴት ፣ ይጫወቱ ነበር ።
ተንኮልም በድንገት ፣ እውነትን ተማታ ፣
ፍቅርም አዘነ ፣ ሠላምም ተቆጣ ።
ውሸት ብቅ አለና ፣ ከተደበቀበት ፣
ከተንኮል ጋር ሆኖ ፣ እውነትን ገደሉት ።
ሠላምና ፍቅር ፣ እጅግ እያዘኑ ፣
እንቅበረው ዘንድ ፣ ስጡን አስከሬኑን ።
ብለው ተማጸኑ ፣ ውሸትን በእምባ ፣
እውነት ተቀበረ ከመቃብር ገባ ።
ዓለምን የመግዛት ፣ ብርቱ ዓላማችው ፣
ውሸትና ተንኮል ፣ ሞላ የልባቸው ።
አንድ ቀን ፣ አቶ ውሸት ተነስቶ በጧት ፣
የሰፈሩን ሰዎች ፣ ደስታ ሲመለከት ።
ተጠራጠረና ፣ ወደ ቀብሩ ሮጠ ፣
ልክ እንደደረሰ ፣ በጣም ደነገጠ ።
እውነት ተፈልጎ ፣ መቃብሩ ሲታይ ፣
ምንም ነገር የለም ፣ አንዳችም የሚታይ ።
አወይ ልፋታችን ፣ ተንኮል መጥተህ ብታይ ፣
እውነት ከቶ አልሞተም ፣ ዓርጎ ነው ሰማይ ።
እውነትና ዘይት ምንግዜም ከላይ ናቸው ✔
https://www.tg-me.com/Mgetem
https://www.tg-me.com/Mgetem
https://www.tg-me.com/Mgetem
@Mgetem
ውሸትና ተንኮል ፣ ጓደኞች ነበሩ ፣
እውነትን ለማጥፋት ፣ እንዲህ ተማከሩ ።
እውነት የተባለው ፣ ይሄ ጠላታችን ፣
መጥፋት አለበት ፣ ጭራሽ ከዓለማችን ።
እኛ እየተጠላን ፣ እሱ እየተወደደ ፣
ብዙ ጊዜ አለፈ ፣ ዘመንም ነጎደ ።
የኛ ብቻ ይሁን ፣ መላው ሀገር ምድሩ ፣
ውሸትና ተንኮል ፣ እንዲህ ተማከሩ ።
ከዕለታት በአንዱ ቀን ፣ ተንኮል እያደባ ፣
ከውሸት ጋር ሆኖ ፣ ከእውነት ቤት ገባ ።
እውነት ከጓደኞቹ ፣ ሠላምና ፍቅር ፣
በደስታ በሀሴት ፣ ይጫወቱ ነበር ።
ተንኮልም በድንገት ፣ እውነትን ተማታ ፣
ፍቅርም አዘነ ፣ ሠላምም ተቆጣ ።
ውሸት ብቅ አለና ፣ ከተደበቀበት ፣
ከተንኮል ጋር ሆኖ ፣ እውነትን ገደሉት ።
ሠላምና ፍቅር ፣ እጅግ እያዘኑ ፣
እንቅበረው ዘንድ ፣ ስጡን አስከሬኑን ።
ብለው ተማጸኑ ፣ ውሸትን በእምባ ፣
እውነት ተቀበረ ከመቃብር ገባ ።
ዓለምን የመግዛት ፣ ብርቱ ዓላማችው ፣
ውሸትና ተንኮል ፣ ሞላ የልባቸው ።
አንድ ቀን ፣ አቶ ውሸት ተነስቶ በጧት ፣
የሰፈሩን ሰዎች ፣ ደስታ ሲመለከት ።
ተጠራጠረና ፣ ወደ ቀብሩ ሮጠ ፣
ልክ እንደደረሰ ፣ በጣም ደነገጠ ።
እውነት ተፈልጎ ፣ መቃብሩ ሲታይ ፣
ምንም ነገር የለም ፣ አንዳችም የሚታይ ።
አወይ ልፋታችን ፣ ተንኮል መጥተህ ብታይ ፣
እውነት ከቶ አልሞተም ፣ ዓርጎ ነው ሰማይ ።
እውነትና ዘይት ምንግዜም ከላይ ናቸው ✔
https://www.tg-me.com/Mgetem
https://www.tg-me.com/Mgetem
https://www.tg-me.com/Mgetem
👍89❤58👏17🥰4😢3
ደብረ ዘይት
@Mgetem
(የዐቢይ ጾም አምስተኛው ሳምንት ‹ደብረ ዘይት› ይባላል፡፡)
ወዮ የዛን ለታ
ወዮ የዛን ለታ ፤ ሲመጣ ሙሽራው
ዘይቱን ላልገዛ ፤ ላጣ የሚያበራው ፤
ወዮ የዛን ለታ ፤ ሲነፋ መለከት
ንስሐ ላልገባ ፤ በዚ ሁሉ ስብከት ፤
ወዮ የዛን ለታ ፤ ለሠነፍ ገበሬ
ሊዘራ በክረምት ፤ ላጠመደ በሬ ፤
ወዮ የዛን ለታ ፤ በጌታ ምጽአት
ወልዶ ላሳደገ ፤ ፀንሶ ኃጢአት ፤
ሰብሉን ሰብሳቢ ፤ በአንድ ጎተራ
ቡቃያው ሲደርስ ፤ የዘራው አዝመራ
ፍሬ ላላፈራ ፤ ወዮ የዛን ለታ
አጫጁን ሲልከው ፤ የመከሩ ጌታ ።
✍️ አቤል ታደለ
https://www.tg-me.com/Mgetem
https://www.tg-me.com/Mgetem
@Mgetem
(የዐቢይ ጾም አምስተኛው ሳምንት ‹ደብረ ዘይት› ይባላል፡፡)
ወዮ የዛን ለታ
ወዮ የዛን ለታ ፤ ሲመጣ ሙሽራው
ዘይቱን ላልገዛ ፤ ላጣ የሚያበራው ፤
ወዮ የዛን ለታ ፤ ሲነፋ መለከት
ንስሐ ላልገባ ፤ በዚ ሁሉ ስብከት ፤
ወዮ የዛን ለታ ፤ ለሠነፍ ገበሬ
ሊዘራ በክረምት ፤ ላጠመደ በሬ ፤
ወዮ የዛን ለታ ፤ በጌታ ምጽአት
ወልዶ ላሳደገ ፤ ፀንሶ ኃጢአት ፤
ሰብሉን ሰብሳቢ ፤ በአንድ ጎተራ
ቡቃያው ሲደርስ ፤ የዘራው አዝመራ
ፍሬ ላላፈራ ፤ ወዮ የዛን ለታ
አጫጁን ሲልከው ፤ የመከሩ ጌታ ።
✍️ አቤል ታደለ
https://www.tg-me.com/Mgetem
https://www.tg-me.com/Mgetem
❤31👍19😢13🥰4👎1
ተጨማሪ የደብረዘይት ግጥሞች እና ጽሑፎች እንዲሁም ጥቅሶችን ለቀናል!
👇👇👇👇👇👇👇
https://www.tg-me.com/Ortho_Quotes
https://www.tg-me.com/Ortho_Quotes
https://www.tg-me.com/Ortho_Quotes
👇👇👇👇👇👇👇
https://www.tg-me.com/Ortho_Quotes
https://www.tg-me.com/Ortho_Quotes
https://www.tg-me.com/Ortho_Quotes
Telegram
ኦርቶዶክሳዊ ጥቅሶች ብቻ
በዚህ ቻናል ኦርቶዶክሳዊ ጥቅሶችን በሚያምር ዲዛይን ያገኛሉ፡፡ ቻናላችንን በመቀላቀል ቤተሰብ ይሁኑን
🥰10👏8👍5
መንፈሳዊ ግጥም ብቻ
ገብር ኄር . . .
የገብርሄር ግጥም ከፎቶ ጋር ለቀናል
👇👇👇👇👇👇👇👇
https://www.tg-me.com/Ortho_Quotes/12
https://www.tg-me.com/Ortho_Quotes/12
https://www.tg-me.com/Ortho_Quotes/12
https://www.tg-me.com/Ortho_Quotes/12
👇👇👇👇👇👇👇👇
https://www.tg-me.com/Ortho_Quotes/12
https://www.tg-me.com/Ortho_Quotes/12
https://www.tg-me.com/Ortho_Quotes/12
https://www.tg-me.com/Ortho_Quotes/12
Telegram
ኦርቶዶክሳዊ ጥቅሶች ብቻ
ገብር ኄር
@Ortho_Quotes
(ስድስተኛው የዐቢይ ጾም ሳምንት ‹ገብር ኄር› የሚል ስያሜ አለው፡፡ ‹ገብር ኄር› ማለት ‹በጎ፣ ታማኝ አገልጋይ› ማለት ነው፡፡)
ኑ በሉ እንጠይቅ
ቆፍረን ቀበርነው ፤ እስኪያጠፋው ዝገት ፤
ወይስ ነገድንበት ፤
ስንት አተረፍንበት ?
ኑ በሉ እንጠይቅ ፤ እግዜር ለፍጥረቱ
አካልም ገንዘብ ነው ፤ የሰጠው መክሊቱ ፤
ዓይናችን ቅዱሱን ፤ ያያል እንደ ጻድቃን? …
@Ortho_Quotes
(ስድስተኛው የዐቢይ ጾም ሳምንት ‹ገብር ኄር› የሚል ስያሜ አለው፡፡ ‹ገብር ኄር› ማለት ‹በጎ፣ ታማኝ አገልጋይ› ማለት ነው፡፡)
ኑ በሉ እንጠይቅ
ቆፍረን ቀበርነው ፤ እስኪያጠፋው ዝገት ፤
ወይስ ነገድንበት ፤
ስንት አተረፍንበት ?
ኑ በሉ እንጠይቅ ፤ እግዜር ለፍጥረቱ
አካልም ገንዘብ ነው ፤ የሰጠው መክሊቱ ፤
ዓይናችን ቅዱሱን ፤ ያያል እንደ ጻድቃን? …
👍22❤6
ኒቆዲሞስ
@Mgetem
(ሰባተኛው የዐቢይ ጾም ሳምንት ‹ኒቆዲሞስ › ይባላል)
ነበር ኒቆዲሞስ
የእስራኤል መምህር ፤ ሳለ ሊቀ ኦሪት
ወንጌል የተማረ ፤ ከክርስቶስ ለሊት
ቀለም በመዝለቁ ፤ በእውቀቱ ምጥቀት
እንደ ምሁር ነኝ ባይ ፤ የማይቃጣው ንቀት ።
ነበር ኒቆዲሞስ
ባለሥልጣን ሆኖ ፤ ያገኝ ሞገስን
ማጎንበስ ያልፈራ ፤ እንደ ሀገር መስፍን
የልጅነት ሥልጣን ፤ ከሌለው ተጠመቆ
በሸንጎ ቢሰየም ፤ እንደማይድን አውቆ።
ነበር ኒቆዲሞስ
ባለጸጋም ሆኖ ፤ በጥሪቱ ንኡስ
አብልጦ የሻተ ፤ ሀብተ መንፈስ ቅዱስ
ተረድቶ በሰማይ ፤ ስሙ እንደሌለ
ዓለሙን አትርፎ ፤ ነብሱን ያጎደለ።
https://www.tg-me.com/Mgetem
https://www.tg-me.com/Mgetem
https://www.tg-me.com/Mgetem
✍️ አቤል ታደለ
@Mgetem
(ሰባተኛው የዐቢይ ጾም ሳምንት ‹ኒቆዲሞስ › ይባላል)
ነበር ኒቆዲሞስ
የእስራኤል መምህር ፤ ሳለ ሊቀ ኦሪት
ወንጌል የተማረ ፤ ከክርስቶስ ለሊት
ቀለም በመዝለቁ ፤ በእውቀቱ ምጥቀት
እንደ ምሁር ነኝ ባይ ፤ የማይቃጣው ንቀት ።
ነበር ኒቆዲሞስ
ባለሥልጣን ሆኖ ፤ ያገኝ ሞገስን
ማጎንበስ ያልፈራ ፤ እንደ ሀገር መስፍን
የልጅነት ሥልጣን ፤ ከሌለው ተጠመቆ
በሸንጎ ቢሰየም ፤ እንደማይድን አውቆ።
ነበር ኒቆዲሞስ
ባለጸጋም ሆኖ ፤ በጥሪቱ ንኡስ
አብልጦ የሻተ ፤ ሀብተ መንፈስ ቅዱስ
ተረድቶ በሰማይ ፤ ስሙ እንደሌለ
ዓለሙን አትርፎ ፤ ነብሱን ያጎደለ።
https://www.tg-me.com/Mgetem
https://www.tg-me.com/Mgetem
https://www.tg-me.com/Mgetem
✍️ አቤል ታደለ
Telegram
መንፈሳዊ ግጥም ብቻ
በዚህ ቻናል ላይ በየቀኑ ኦርቶዶክሳዊ ግጥሞችን ያገኛሉ
ለአስተያየትና ግጥም እንዲፖሰትላችሁ የምትፈልጉ ለመላክ
@Solasc12
@Solasc13
@Mgetem_group
ኦርቶዶክሳዊ ጥቅሶች ብቻ
@Ortho_quotes
ለአስተያየትና ግጥም እንዲፖሰትላችሁ የምትፈልጉ ለመላክ
@Solasc12
@Solasc13
@Mgetem_group
ኦርቶዶክሳዊ ጥቅሶች ብቻ
@Ortho_quotes
🥰12👍10❤4
Forwarded from Daregot Media
የኒቆዲሞስ ታላቅነት
በዚያ “አልቦ ዘመድ በጊዜ ተዋርዶ” በተባለበት ፣ ሐዋርያቱ እንኳ ጥለው በሸሹበት ዕለተ ዓርብ የልጇን መለኮት የተዋሐደው ሥጋ ከአርማትያሱ ሰው ከዮሴፍ ጋር ከመስቀል አውርዶ በቀበረ ጊዜ እመቤታችን ለኒቆዲሞስ የመረቀችው ምርቃት “ታላቅ ያድርግህ!”(1) የሚል ነበር።
ይኸውም ሲደርስ ሲፈጸም ሊቁ ቅዱስ ያሬድ የታላቁ አቢይ ጾም ፯ተኛ ሳምንት መጠሪያ አድርጎት ፤ በጾመ ድጓውም “ወሀሎ አሐዱ ብእሲ እምፈሪሳውያን ዘስሙ ኒቆዲሞስ ፣ዘሖረ ኀቤሁ ቀዲሙ ሌሊተ ፣ ወይቤሎ ለኢየሱስ እጓለ አንበሳ ሰከብከ ወኖምከ ፣ አንሥአኒ በትንሣኤከ” (2) እያለ ዘምሮለት በዓመቱ ታሪኩ ሲነገር ታላቅነቱ ሲወሳ ይኖራል።
ሙሉ ጹሑፉን ያንብቡ https://telegra.ph/ዲረጎት-04-05
Join us @daregot
በዚያ “አልቦ ዘመድ በጊዜ ተዋርዶ” በተባለበት ፣ ሐዋርያቱ እንኳ ጥለው በሸሹበት ዕለተ ዓርብ የልጇን መለኮት የተዋሐደው ሥጋ ከአርማትያሱ ሰው ከዮሴፍ ጋር ከመስቀል አውርዶ በቀበረ ጊዜ እመቤታችን ለኒቆዲሞስ የመረቀችው ምርቃት “ታላቅ ያድርግህ!”(1) የሚል ነበር።
ይኸውም ሲደርስ ሲፈጸም ሊቁ ቅዱስ ያሬድ የታላቁ አቢይ ጾም ፯ተኛ ሳምንት መጠሪያ አድርጎት ፤ በጾመ ድጓውም “ወሀሎ አሐዱ ብእሲ እምፈሪሳውያን ዘስሙ ኒቆዲሞስ ፣ዘሖረ ኀቤሁ ቀዲሙ ሌሊተ ፣ ወይቤሎ ለኢየሱስ እጓለ አንበሳ ሰከብከ ወኖምከ ፣ አንሥአኒ በትንሣኤከ” (2) እያለ ዘምሮለት በዓመቱ ታሪኩ ሲነገር ታላቅነቱ ሲወሳ ይኖራል።
ሙሉ ጹሑፉን ያንብቡ https://telegra.ph/ዲረጎት-04-05
Join us @daregot
❤19👍10🤬1
ኒቆዲሞስ
@Mgetem
(ሰባተኛው የዐቢይ ጾም ሳምንት ‹ኒቆዲሞስ › ይባላል)
ነበር ኒቆዲሞስ
የእስራኤል መምህር ፤ ሳለ ሊቀ ኦሪት
ወንጌል የተማረ ፤ ከክርስቶስ ለሊት
ቀለም በመዝለቁ ፤ በእውቀቱ ምጥቀት
እንደ ምሁር ነኝ ባይ ፤ የማይቃጣው ንቀት ።
ነበር ኒቆዲሞስ
ባለሥልጣን ሆኖ ፤ ያገኝ ሞገስን
ማጎንበስ ያልፈራ ፤ እንደ ሀገር መስፍን
የልጅነት ሥልጣን ፤ ከሌለው ተጠመቆ
በሸንጎ ቢሰየም ፤ እንደማይድን አውቆ።
ነበር ኒቆዲሞስ
ባለጸጋም ሆኖ ፤ በጥሪቱ ንኡስ
አብልጦ የሻተ ፤ ሀብተ መንፈስ ቅዱስ
ተረድቶ በሰማይ ፤ ስሙ እንደሌለ
ዓለሙን አትርፎ ፤ ነብሱን ያጎደለ።
https://www.tg-me.com/Mgetem
https://www.tg-me.com/Mgetem
https://www.tg-me.com/Mgetem
✍️ አቤል ታደለ
@Mgetem
(ሰባተኛው የዐቢይ ጾም ሳምንት ‹ኒቆዲሞስ › ይባላል)
ነበር ኒቆዲሞስ
የእስራኤል መምህር ፤ ሳለ ሊቀ ኦሪት
ወንጌል የተማረ ፤ ከክርስቶስ ለሊት
ቀለም በመዝለቁ ፤ በእውቀቱ ምጥቀት
እንደ ምሁር ነኝ ባይ ፤ የማይቃጣው ንቀት ።
ነበር ኒቆዲሞስ
ባለሥልጣን ሆኖ ፤ ያገኝ ሞገስን
ማጎንበስ ያልፈራ ፤ እንደ ሀገር መስፍን
የልጅነት ሥልጣን ፤ ከሌለው ተጠመቆ
በሸንጎ ቢሰየም ፤ እንደማይድን አውቆ።
ነበር ኒቆዲሞስ
ባለጸጋም ሆኖ ፤ በጥሪቱ ንኡስ
አብልጦ የሻተ ፤ ሀብተ መንፈስ ቅዱስ
ተረድቶ በሰማይ ፤ ስሙ እንደሌለ
ዓለሙን አትርፎ ፤ ነብሱን ያጎደለ።
https://www.tg-me.com/Mgetem
https://www.tg-me.com/Mgetem
https://www.tg-me.com/Mgetem
✍️ አቤል ታደለ
Telegram
መንፈሳዊ ግጥም ብቻ
በዚህ ቻናል ላይ በየቀኑ ኦርቶዶክሳዊ ግጥሞችን ያገኛሉ
ለአስተያየትና ግጥም እንዲፖሰትላችሁ የምትፈልጉ ለመላክ
@Solasc12
@Solasc13
@Mgetem_group
ኦርቶዶክሳዊ ጥቅሶች ብቻ
@Ortho_quotes
ለአስተያየትና ግጥም እንዲፖሰትላችሁ የምትፈልጉ ለመላክ
@Solasc12
@Solasc13
@Mgetem_group
ኦርቶዶክሳዊ ጥቅሶች ብቻ
@Ortho_quotes
❤14👍9😢2
Forwarded from አንድ ቀለም ከከሡ ጋር
አንዳንድ ነገሮች ስለ “እዩት” መጽሐፍ
(Birthday Special)
1. ወረቀት አልባ መጽሐፍ ነው።
መቼም ጣራ በነካ የኅትመት ዋጋ ፣ የመጽሐፍ ማከፋፈያ ያላቸው ጸሐፍት ሳይቀሩ ከማሳተም ሲያፈገፍጉ ፣ አከፋፋዮችም 40% እየቆረጡ የጸሐፍትን ጥቅም ሲነፍጉ ፣ አንባብያንም በዋጋው ውድነትና በሕይወት ዘይቤ ለውጥ (life style modification)ምክንያት ከመጻሕፍት ዓለም ወጥተው ወደ ፖስት ንባብ ሲሸሸጉ ዘመኑን የዋጀ አዲስ መላ መምታት አስፈልጓል። ወረቀት አልባ መጽሐፍ ማሳተም ወይም Ebook/ Audiobook print ወይም ዲጂታል ፕሬስ። በርግጥ እንደ ቱባ መጻሕፍት ፣ አፍሮ ቡክስ የመሳሰሉ ቀድመው ታትመው የተነበቡና አሁንም ገበያ ላይ ያሉ መጻሕፍትን ለዲጂታል ንባብና መሰማት ያበቁ Appoch አሉ። ለኦርቶዶክሳዊውም ዓለም ይኼን አዲስ ግን ዘመኑን የዋጀ መንገድ ደፍሮ መጀመር ነው የአንድ ቀለም ፕሬስ ተልእኮ። ስለዚህ “እዩት”/ቅጽ 1 በቅርብ ቀናት ፣ “ጉባኤያችን ማርያም”/ ቅጽ 2 የፍልሰታ ሰሞን ፣ “ዘመን ፣ ብርሃን ፣ ዜማ”/ ቅጽ 3 በቀጣዩ አዲስ ዓመት በEBOOK/AUDIO BOOK ይለቀቃሉ። ያኔ ክፍለ ሃገር አሊያ ባሕር ማዶ መሆን ሳይገድብዎ ሞባይልዎን ወይም ላፕቶፕዎን ብቻ በመጠቀም ገዝተው አሊያም ተከራይተው ማንበብ ይችላሉ። የግጥም ስብስብ መሆኑ የሚያጎናጽፈው አጭር አቀራረብ እንደ epub ካለ ቁጥብ presentation ጋር እንዳይሰለች ያደርገዋል።
ይቀጥላል!
__
http://www.tg-me.com/Andkelem
http://www.tg-me.com/Andkelem
http://www.tg-me.com/Andkelem
(Birthday Special)
1. ወረቀት አልባ መጽሐፍ ነው።
መቼም ጣራ በነካ የኅትመት ዋጋ ፣ የመጽሐፍ ማከፋፈያ ያላቸው ጸሐፍት ሳይቀሩ ከማሳተም ሲያፈገፍጉ ፣ አከፋፋዮችም 40% እየቆረጡ የጸሐፍትን ጥቅም ሲነፍጉ ፣ አንባብያንም በዋጋው ውድነትና በሕይወት ዘይቤ ለውጥ (life style modification)ምክንያት ከመጻሕፍት ዓለም ወጥተው ወደ ፖስት ንባብ ሲሸሸጉ ዘመኑን የዋጀ አዲስ መላ መምታት አስፈልጓል። ወረቀት አልባ መጽሐፍ ማሳተም ወይም Ebook/ Audiobook print ወይም ዲጂታል ፕሬስ። በርግጥ እንደ ቱባ መጻሕፍት ፣ አፍሮ ቡክስ የመሳሰሉ ቀድመው ታትመው የተነበቡና አሁንም ገበያ ላይ ያሉ መጻሕፍትን ለዲጂታል ንባብና መሰማት ያበቁ Appoch አሉ። ለኦርቶዶክሳዊውም ዓለም ይኼን አዲስ ግን ዘመኑን የዋጀ መንገድ ደፍሮ መጀመር ነው የአንድ ቀለም ፕሬስ ተልእኮ። ስለዚህ “እዩት”/ቅጽ 1 በቅርብ ቀናት ፣ “ጉባኤያችን ማርያም”/ ቅጽ 2 የፍልሰታ ሰሞን ፣ “ዘመን ፣ ብርሃን ፣ ዜማ”/ ቅጽ 3 በቀጣዩ አዲስ ዓመት በEBOOK/AUDIO BOOK ይለቀቃሉ። ያኔ ክፍለ ሃገር አሊያ ባሕር ማዶ መሆን ሳይገድብዎ ሞባይልዎን ወይም ላፕቶፕዎን ብቻ በመጠቀም ገዝተው አሊያም ተከራይተው ማንበብ ይችላሉ። የግጥም ስብስብ መሆኑ የሚያጎናጽፈው አጭር አቀራረብ እንደ epub ካለ ቁጥብ presentation ጋር እንዳይሰለች ያደርገዋል።
ይቀጥላል!
__
http://www.tg-me.com/Andkelem
http://www.tg-me.com/Andkelem
http://www.tg-me.com/Andkelem
👍15❤9🥰1
Forwarded from አንድ ቀለም ከከሡ ጋር
አንዳንድ ነገሮች ስለ “እዩት” መጽሐፍ
(Part 2)
2. የመዝሙር ግጥም መድብል ነው።
እንኳን የመዝሙር ግጥም መድብል ፣ የመንፈሳዊ ግጥም መድብል አቅርቦት እንኳ በጣት ሚቆጠር ነው። በግሌ ከዲያቆን መኩሪያ ጉግሣ የቀደሙ ኅትመቶችና የአሁን “የእኔ መክሊት” የመዝሙር ግጥም ውጭ የታተመ የአንጋፋና አዳዲስ ጸሐፍት መዝሙር ሥራ አልሰማሁም። የመዝሙር ግጥሞች ያለ ዜማቸው ራቁታቸውን ሲቀርቡ የሚነበቡ ፣ የሚስቡ ፣ የሚያስገነዝቡ መሆን አለባቸው ፤ እንደ ቅኔ አባታቸው ብዬ በጽኑ አምናለሁ። በዚህ አንጻር የእኔ የ5 ዓመት የብርዕ ምርት ምን ያህል አጥጋቢ ነው የሚለውን በሕዝባዊና ሙያው ሂስ ሚዛንነት ማስገምገም ስላስፈለኝ 81 የጌታ ሥራዎች ፣ በመጀመሪያው ቅጽ/ ቅጽ ስብሐተ እግዚአብሔር ለንባብ ብርሃን ይበቃሉ። ሌሎቹም ቅጾች ይቀጥላሉ።
__
http://www.tg-me.com/Andkelem
http://www.tg-me.com/Andkelem
http://www.tg-me.com/Andkelem
(Part 2)
2. የመዝሙር ግጥም መድብል ነው።
እንኳን የመዝሙር ግጥም መድብል ፣ የመንፈሳዊ ግጥም መድብል አቅርቦት እንኳ በጣት ሚቆጠር ነው። በግሌ ከዲያቆን መኩሪያ ጉግሣ የቀደሙ ኅትመቶችና የአሁን “የእኔ መክሊት” የመዝሙር ግጥም ውጭ የታተመ የአንጋፋና አዳዲስ ጸሐፍት መዝሙር ሥራ አልሰማሁም። የመዝሙር ግጥሞች ያለ ዜማቸው ራቁታቸውን ሲቀርቡ የሚነበቡ ፣ የሚስቡ ፣ የሚያስገነዝቡ መሆን አለባቸው ፤ እንደ ቅኔ አባታቸው ብዬ በጽኑ አምናለሁ። በዚህ አንጻር የእኔ የ5 ዓመት የብርዕ ምርት ምን ያህል አጥጋቢ ነው የሚለውን በሕዝባዊና ሙያው ሂስ ሚዛንነት ማስገምገም ስላስፈለኝ 81 የጌታ ሥራዎች ፣ በመጀመሪያው ቅጽ/ ቅጽ ስብሐተ እግዚአብሔር ለንባብ ብርሃን ይበቃሉ። ሌሎቹም ቅጾች ይቀጥላሉ።
__
http://www.tg-me.com/Andkelem
http://www.tg-me.com/Andkelem
http://www.tg-me.com/Andkelem
👍9❤2
ዳግም ምን አሏቸው?
/መነባንብ/
✞**
እናታለም ተዋህዶ
ባንችነትሽ የሚኮራ
በስምሽ ስም የሚጠራ
ዛሬ ጠፋ የሚያበራ
ስለፍቅርሽ ቀልጠው ነደው
ስለ አምላካቸው ተማግደው
በሃይማኖት ፍቅር እጅጉን ተነክተው
ካንቺ ጉያ በኖሩ
እግሮችሽ ስር በተማሩ
ለምን/2/ ተዋህዶ ጠላቸው መንደሩ
ምን አሏቸው ደግሞ ቅዱሳን አበውን
አንቺን እናት እምነት ከዚህ ያበቁትን
ምን አሏቸው ደግሞ አበው ሊቃውንትን
አንድምታውን ፈተው ባመሰጠሩልን
ሚስጢርን መሰጥርው ለኛ ባኖሩልን
ብራና ወጥረው አምድ በፃፉልን
ውለታቸው ታዲያ ይህ ነው?
ስላደረጉልን የምንከፍለው
ጭራሽማ አምላክ ባከበራቸው
አክሊሉን በደፋላቸው
በሀሴት በተቀበላቸው
ልባችን ለምን አመፀ ለምንድን ማይቀበል
ተፈትኖ ያለውን የተፃፈላቸውን የህይወት ገድል
ለምንድን! የማናምን በምልጃቸው
እሱ እግዚአብሔር በሰጣቸው
ደግሞስ ምን አሏቸው?
እሄ......./በለቅሶ/
ሁሌም እውነት ነው
መልከ መልካም ሙሽራዋ
የፀናች በድንግልናዋ
ማን አለ እንደዝች እንደ ቅድስት እናት
ያልተረታ በነገስታት
አንገቷን ለሰይፍ የሠጠች
ክርስቶስን ብላ የኖረች
እኮስ ምን አሏት ይህችን እናት
የስጋ ፋላጎት ያልሠበራት።
ተዋህዶ እናት አለም
እንደድሮ ፀንቶ የሚኖር ልጆችሽ ፈርተዋል የሉም
የምልጃ ታላቅ ስራ
ለህዝቦቿ እያበራ
እየለመኑ ምህረት
ሲያስተዳድሩ አናብርቱ አናብስቱን
ከባህር ውስጥ የፀለዩ
በስራቸው የተለዩ
ገብረ መንፈስ ቅዱስ ታላቅ አባት
ምን አሏቸው ይሆን አንቺ ምስኪን እምነት
አይደል እንዴ ተዋሕዶ
ስጋቸውን የገበሩ
በእርኩሳን መናፍስት የተፈሩ
በእግዜር ጥበብ የከበሩ
ምን አሏቸው ቅዱሳንን ሰማዕታት ፃድቃናትን
የክርስቶስ ደቀመዝሙር ሃዋርያት
ትንቢት ፀሀፊ ነቢያት
ተዋህዶ ውዷ እናቴ ምን አሏቸው?
በዕቶን ውስጥ ማግደዋቸው
እንደ እንስሳ አረደዋቸው
በቁም ቆመው ቆዳቸውንገፈዋቸው
ላንቺ ቋሚ ልጆችሽን ምን አሏቸው
አይ ተዋህዶ....
በአንድ እግራቸው ሰባት ዓመት የፀለዩ
ባንቺ የፍቅር መግቦትሽ ከዓለም ላይ የተለዩ
የተክለሃይማኖት እናት አንቺ ቅድስት እምነት
አያማልዱም ሲላቸው ልጆችሽን
ዛሬ ምን ተሰማሽ ንገሪኝ በእውነት
የልጆችሽን ምልጃ ሊያስታርቅ ሊቃትት
መቻል ደጉ....
ስንቱን ቻልሽው እናታለም....
እሄ......
የእመብርሃን አስራት ኢትዮጵያ
የቅዱሳን የፃድቃን መፍለቂያ
አንቺስ ጋር ምን አሏቸው
መሠረቶችሽን ሲገፏቸው
ምን አልሻቸው ይሆን እንደው ዝም አልሻቸው
የመኖሬ ምስጢር
የመኖሬ ዘመን እምነቴ እሷናት ብለሽ ሳትነግሪያቸው
የቅዱሳንን ምልጃ የፃድቃንን ምልጃ ሳታሰተምሪያቸው
ለዚህ ይሆን አማላጅ አይደሉም ብለው የናቋቸው
ለነገሩ አይደለም
ስንቴ አስተማርሻቸው
በግልጽ አሳይተሽ አስቀምጠሽላቸው
ሰብከሻቸው ነበር ጊዜ ነጎደና በመናፍቅ እስር
የማማላዳቸው ያን ሁሉ ምስክር
ቀበሩት ከአፈር
እና ተዋህዶ ያንቺን ጓዳ የሚያውቁ
በፍቅርሽ ማነቆ የታነቁ
ቀስ በቀስ ወጡ እያለቁ
አሁንማ እናቴ
ባንቺ ጉያ እየኖሩ
አንቺንም እያሳፈሩ
ፈሉብሽ እንደ አሸን ቅዱሳንሽን እየካዱ
አያማልዱም ብለው ረግጠው እየሄዱ
ታዲያ ምን አሏቸው
ያንቺን ልጆች በቤታቸው
ዛሬስ ምን አሏቸው???
https://www.tg-me.com/Mgetem
https://www.tg-me.com/Mgetem
https://www.tg-me.com/Mgetem
/መነባንብ/
✞**
እናታለም ተዋህዶ
ባንችነትሽ የሚኮራ
በስምሽ ስም የሚጠራ
ዛሬ ጠፋ የሚያበራ
ስለፍቅርሽ ቀልጠው ነደው
ስለ አምላካቸው ተማግደው
በሃይማኖት ፍቅር እጅጉን ተነክተው
ካንቺ ጉያ በኖሩ
እግሮችሽ ስር በተማሩ
ለምን/2/ ተዋህዶ ጠላቸው መንደሩ
ምን አሏቸው ደግሞ ቅዱሳን አበውን
አንቺን እናት እምነት ከዚህ ያበቁትን
ምን አሏቸው ደግሞ አበው ሊቃውንትን
አንድምታውን ፈተው ባመሰጠሩልን
ሚስጢርን መሰጥርው ለኛ ባኖሩልን
ብራና ወጥረው አምድ በፃፉልን
ውለታቸው ታዲያ ይህ ነው?
ስላደረጉልን የምንከፍለው
ጭራሽማ አምላክ ባከበራቸው
አክሊሉን በደፋላቸው
በሀሴት በተቀበላቸው
ልባችን ለምን አመፀ ለምንድን ማይቀበል
ተፈትኖ ያለውን የተፃፈላቸውን የህይወት ገድል
ለምንድን! የማናምን በምልጃቸው
እሱ እግዚአብሔር በሰጣቸው
ደግሞስ ምን አሏቸው?
እሄ......./በለቅሶ/
ሁሌም እውነት ነው
መልከ መልካም ሙሽራዋ
የፀናች በድንግልናዋ
ማን አለ እንደዝች እንደ ቅድስት እናት
ያልተረታ በነገስታት
አንገቷን ለሰይፍ የሠጠች
ክርስቶስን ብላ የኖረች
እኮስ ምን አሏት ይህችን እናት
የስጋ ፋላጎት ያልሠበራት።
ተዋህዶ እናት አለም
እንደድሮ ፀንቶ የሚኖር ልጆችሽ ፈርተዋል የሉም
የምልጃ ታላቅ ስራ
ለህዝቦቿ እያበራ
እየለመኑ ምህረት
ሲያስተዳድሩ አናብርቱ አናብስቱን
ከባህር ውስጥ የፀለዩ
በስራቸው የተለዩ
ገብረ መንፈስ ቅዱስ ታላቅ አባት
ምን አሏቸው ይሆን አንቺ ምስኪን እምነት
አይደል እንዴ ተዋሕዶ
ስጋቸውን የገበሩ
በእርኩሳን መናፍስት የተፈሩ
በእግዜር ጥበብ የከበሩ
ምን አሏቸው ቅዱሳንን ሰማዕታት ፃድቃናትን
የክርስቶስ ደቀመዝሙር ሃዋርያት
ትንቢት ፀሀፊ ነቢያት
ተዋህዶ ውዷ እናቴ ምን አሏቸው?
በዕቶን ውስጥ ማግደዋቸው
እንደ እንስሳ አረደዋቸው
በቁም ቆመው ቆዳቸውንገፈዋቸው
ላንቺ ቋሚ ልጆችሽን ምን አሏቸው
አይ ተዋህዶ....
በአንድ እግራቸው ሰባት ዓመት የፀለዩ
ባንቺ የፍቅር መግቦትሽ ከዓለም ላይ የተለዩ
የተክለሃይማኖት እናት አንቺ ቅድስት እምነት
አያማልዱም ሲላቸው ልጆችሽን
ዛሬ ምን ተሰማሽ ንገሪኝ በእውነት
የልጆችሽን ምልጃ ሊያስታርቅ ሊቃትት
መቻል ደጉ....
ስንቱን ቻልሽው እናታለም....
እሄ......
የእመብርሃን አስራት ኢትዮጵያ
የቅዱሳን የፃድቃን መፍለቂያ
አንቺስ ጋር ምን አሏቸው
መሠረቶችሽን ሲገፏቸው
ምን አልሻቸው ይሆን እንደው ዝም አልሻቸው
የመኖሬ ምስጢር
የመኖሬ ዘመን እምነቴ እሷናት ብለሽ ሳትነግሪያቸው
የቅዱሳንን ምልጃ የፃድቃንን ምልጃ ሳታሰተምሪያቸው
ለዚህ ይሆን አማላጅ አይደሉም ብለው የናቋቸው
ለነገሩ አይደለም
ስንቴ አስተማርሻቸው
በግልጽ አሳይተሽ አስቀምጠሽላቸው
ሰብከሻቸው ነበር ጊዜ ነጎደና በመናፍቅ እስር
የማማላዳቸው ያን ሁሉ ምስክር
ቀበሩት ከአፈር
እና ተዋህዶ ያንቺን ጓዳ የሚያውቁ
በፍቅርሽ ማነቆ የታነቁ
ቀስ በቀስ ወጡ እያለቁ
አሁንማ እናቴ
ባንቺ ጉያ እየኖሩ
አንቺንም እያሳፈሩ
ፈሉብሽ እንደ አሸን ቅዱሳንሽን እየካዱ
አያማልዱም ብለው ረግጠው እየሄዱ
ታዲያ ምን አሏቸው
ያንቺን ልጆች በቤታቸው
ዛሬስ ምን አሏቸው???
https://www.tg-me.com/Mgetem
https://www.tg-me.com/Mgetem
https://www.tg-me.com/Mgetem
Telegram
መንፈሳዊ ግጥም ብቻ
በዚህ ቻናል ላይ በየቀኑ ኦርቶዶክሳዊ ግጥሞችን ያገኛሉ
ለአስተያየትና ግጥም እንዲፖሰትላችሁ የምትፈልጉ ለመላክ
@Solasc12
@Solasc13
@Mgetem_group
ኦርቶዶክሳዊ ጥቅሶች ብቻ
@Ortho_quotes
ለአስተያየትና ግጥም እንዲፖሰትላችሁ የምትፈልጉ ለመላክ
@Solasc12
@Solasc13
@Mgetem_group
ኦርቶዶክሳዊ ጥቅሶች ብቻ
@Ortho_quotes
❤39👍29👏2
እስትንፋስ ሥጋ
@Mgetem
አካላቴ ፥ሳይጎዳ እስካለሁ፤
አልፎም ባልሆንም ጤና
አልቀርም መጥቼ አይሻለሁ፤
ተሰናክዬም ቢሆን
በህመም ተጎድቼ፤
ባጣም እራመድበት
እመጣ እጄን ተጫምቼ፤
በእጄ ተጉዤ፥ አልቀርም
ጠብቂኝ ፥አይሻለሁ መጥቼ፤
ሰው ባያግዘኝም ቢከፋብኝ
እመጣለሁ ድኬ ተጎትቼ፤
ከሆነ፥አንደበቴ ብቻ ደህና
አመሰግናለሁ ጮኬ አሰምቼ፤
አካላት አንደበቴ ቢያዝ
አልቀርም ካለች ነፍሴ፤
በእዝነ ህልናዬ ላመሰግን
አልቀር ከደጅሽ መድረሴ፤
ከሚያውደው ቤተ መቅደስ
ልቆም ልቀመጥ ለቅዳሴ፤
የፈለገው ይምጣ ላልቀር
ለማርያም
በማርያም፥ቃል ገባሁ ለራሴ፤
ልጅሽን፣አንቺንና እኔን የሚለይ
የለም አንዳች ኃይል፤
ሁሌም በረከቴን ላፍስ
ከደጅሽ ከስርሽ እውል።
እናም እመቤቴ እያለ
የሚለምናት በለቅሶ፤
አማኙ ልቤ፥ ሺ ጊዜ ቢቸገር
የፈለገው ቢሆን ደርሶ፤
አይቀር ከደጇ ይሄዳል
ሊመለስ ሰንቆ፥በረከቱን አፍሶ።
https://www.tg-me.com/Mgetem
https://www.tg-me.com/Mgetem
https://www.tg-me.com/Mgetem
@Mgetem
አካላቴ ፥ሳይጎዳ እስካለሁ፤
አልፎም ባልሆንም ጤና
አልቀርም መጥቼ አይሻለሁ፤
ተሰናክዬም ቢሆን
በህመም ተጎድቼ፤
ባጣም እራመድበት
እመጣ እጄን ተጫምቼ፤
በእጄ ተጉዤ፥ አልቀርም
ጠብቂኝ ፥አይሻለሁ መጥቼ፤
ሰው ባያግዘኝም ቢከፋብኝ
እመጣለሁ ድኬ ተጎትቼ፤
ከሆነ፥አንደበቴ ብቻ ደህና
አመሰግናለሁ ጮኬ አሰምቼ፤
አካላት አንደበቴ ቢያዝ
አልቀርም ካለች ነፍሴ፤
በእዝነ ህልናዬ ላመሰግን
አልቀር ከደጅሽ መድረሴ፤
ከሚያውደው ቤተ መቅደስ
ልቆም ልቀመጥ ለቅዳሴ፤
የፈለገው ይምጣ ላልቀር
ለማርያም
በማርያም፥ቃል ገባሁ ለራሴ፤
ልጅሽን፣አንቺንና እኔን የሚለይ
የለም አንዳች ኃይል፤
ሁሌም በረከቴን ላፍስ
ከደጅሽ ከስርሽ እውል።
እናም እመቤቴ እያለ
የሚለምናት በለቅሶ፤
አማኙ ልቤ፥ ሺ ጊዜ ቢቸገር
የፈለገው ቢሆን ደርሶ፤
አይቀር ከደጇ ይሄዳል
ሊመለስ ሰንቆ፥በረከቱን አፍሶ።
https://www.tg-me.com/Mgetem
https://www.tg-me.com/Mgetem
https://www.tg-me.com/Mgetem
Telegram
መንፈሳዊ ግጥም ብቻ
በዚህ ቻናል ላይ በየቀኑ ኦርቶዶክሳዊ ግጥሞችን ያገኛሉ
ለአስተያየትና ግጥም እንዲፖሰትላችሁ የምትፈልጉ ለመላክ
@Solasc12
@Solasc13
@Mgetem_group
ኦርቶዶክሳዊ ጥቅሶች ብቻ
@Ortho_quotes
ለአስተያየትና ግጥም እንዲፖሰትላችሁ የምትፈልጉ ለመላክ
@Solasc12
@Solasc13
@Mgetem_group
ኦርቶዶክሳዊ ጥቅሶች ብቻ
@Ortho_quotes
👍26❤20