Telegram Web Link
"ዝክረ ኒቅያ" ጀምሯል። የቅኔ መምህሬን መጋቤ ምሥጢር ኃይለ ልዑል ገነትን የፊት መስመር ተሰላፊ ሆነው በማየቴ ካሁኑ ደስ ደስ እያለኝ ነው። ዳሩ ግን "ዝክረ ኒቅያ" አርዮሳዊ መነኮሳትን ፣ ንስጥሮሳዊ ጳጳሳትን የሚያወግዝ ፣ ምን ዋና ፣ ምን አጋዥ ፣ ምን ተወጋዥ መጽሐፍ እንደሆነ የሚያነጽር ጸሎተ ሃይማኖታዊ ረቂቅ የሚያረቅ ፣ 81ዱዋዊ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጓሜና ቀኖና ውዝግብን የሚያጠራ ሕጋዊ ውሳኔ የሚወስን ካልሆነ የአበል ወጪ የከሰርንበት ኪሳራ ፣ ቁና ሰፍታ እንደለበሰችው "ስም እንዲጠራ" ነው ሚሆነው። የልብ ሕመም ለያዛት ቤተ ክርስቲያን ማስታገሻ የሚወጋ ጉባኤ እንደማይሆን እጠብቃለሁ።

ከሣቴ ብርሃን
___
www.tg-me.com/andkelem
www.tg-me.com/andkelem
#ይድራስ
@Mgetem

በገድል የፀና የእምነት ገበሬ
የሃይማኖት ጀግና የትሩፋት ፍሬ
ኮከበ ፋርስ ቅዱስ ጊዮርጊስ
የቴዎስብታ ልጅ የአንስጣሲዎስ
በወጣትነቱ ወንጌል ለማዳረስ
አለማትን ቢዞር በነጩ ፈረስ
በኢየሱስ ስም አታስተምር ብለው
መከራ ቢያፀኑ በእርሱ ላይ ጨክነው
የፈጠረውን አምላክ ለጥቅም እንዲሸጠው
በሃብት ንብረት ሹመት ጌታን እንዲለውጠው
ክርስቶስን ትቶ ለጣኦት እንዲሰግድ
ምርጫ ቢያቀርቡለት ከበው በአራት አምድ
እኔ ክርስቲያን ነኝ ብሎ በአደባባይ
አምላኩን ቢጠራ ቢያደርሱበት ስቃይ
በእምነት ስለፀና ለስጋው ሳይሳሳ
በዛ ሁሉ መከራ ከፍቅሩ የተነሳ
አምላኩን በመጥራት ስላናደዳቸው
ለጣኦት እንዲሰግድ ቢታገሉ ፀንተው
በጋለ ብረት ላይ አስረውት ገርፈው
በደሙ ነጠብጣብ እሳቱን ቢያጠፋው
በዚ ባይበቃቸው ሰውነቱን ፈጭተው
በይድራስ ተራራ ቢነዙት በትነው
እፅዋት አራዊቱ ሳርና ቅጠሉ
እያመሰገኑ ጊዮርጊስ ጊዮርጊስ ሲሉ
ከፅናቱ ብዛት ሰማዕት በመሆን
እስከሞት ተጋድሎ ያጠመቀ ሁሉን
የሰማዕታት አለቃ ከስጢፋኖስ በኋላ
ጊዮርጊስ ሰማዕት የእምነት ጀግና
አለ ወይ ዛሬ ላይ በእምነቱ የፀና
ጊዮርጊስ ጊዮርጊስ ጊዮርጊስ እያለው
ወደ ኋላው ፈርቶ ያላፈገፈገው
እኮ ማነው ታድያ ዛሬ ላይ የፀናው
ከአንገቱ ደም ውሃ ወተት ያዘነበው
ሦስቴ ሞቶ ሰባት አክሊል የቀዳጀው
ኮከብ ነው ፀሃይ ነው ስሙን ለሚጠራው
አያፍርም ተማፅኖት ጊዮርጊስ ጊዮርጊስ ለሚለው (2×)

https://www.tg-me.com/Mgetem
https://www.tg-me.com/Mgetem
https://www.tg-me.com/Mgetem
ሆናዋለች #ቤዛ
@Mgetem

በአምላኳ ተመርጣ ፤ ያውም ለናትነት
ባሪያው ነኝ እያለች ፤ የምታዘዝለት
በሄዋን ትእቢት ፤ የተዘጋው ገነት
ዳግም ተከፈተ ፤ በማርያም ቅንነት።
እንግዳ የሆነን ፤ የሥጋዌ ሚስጥር
አምና ተቀብላ ፤ በሄዋን ጥርጥር
ዳቢሎስ ካስገባን ፤ የገሀነምወህኒ
ማርያም አሶጣችን ፤ ብላ ይኩነኒ።
ዳግሚት ሰማዩ ፤ ዙፋኑ ለመሆን
የተገባች ሆና ፤ ልጁ ልጇ እንዲሆን
ሄዋን ያጣችውን ፤ ቅድስና ይዛ
ማርያም ለዓለሙ ፤ ሆናዋለች ቤዛ።

አቤል ታደለ

https://www.tg-me.com/Mgetem
https://www.tg-me.com/Mgetem
https://www.tg-me.com/Mgetem

ለአስተያየት : @abeltadele
ጉባኤ ቃና
~
ኦ ማርቆስ ረስየኒ አንበሳ፥
ለላህም ትካዘ ዓለም ከመ እስብር ጥርሳ።

ውርስ ትርጉም

ማርቆስ ማርቆስ አድርገን አንበሳ፥
የዓለም ሃሳብ ላምን ድል እንድንንነሳ።

__
www.tg-me.com/andkelem
www.tg-me.com/andkelem
፪ቱ አእሩግ አመ በከዩ ብካየ፥
ረከቡ ወለተ ዘታስተሠሪ ጌጋየ፥
ለወንጌላውያን ኵልነ ዘኮነተነ ምጒያየ፥
ኢያቄም ወሐና ወለዱ ሰማየ፥
ወሰማዮሙኒ አሥረቀት ፀሐየ።

ነግሥ
____
www.tg-me.com/andkelem
www.tg-me.com/andkelem
ማርያም ተወለደች
@Mgetem

በዚች እለት
ከሐናና ከኢያቄም ፤ እድሜያቸው ካረጀ
ልዑል ለማደሪያው ፤ መቅደስ አዘጋጀ
ከዕሰይ የዘር ግንድ ፤ እቤቱን አነፀ
ከማይነቅዝ እንጨት ፤ ታቦቱን ቀረፀ።
በዚች እለት
እንደ እንግዳ ደራሽ ፤ ድንገት ያላየናት
አስቀድሞ ትንቢት ፤ የተነገረላት
በሊባኖስ አድባር ፤ ተወለደች ሴት ልጅ
ፊቷ የሚያበራ ፤ ከፀሐይ ሰባት እጅ ።
በዚች እለት
በነፍስም በሥጋ ፤ ነውር የሌለባት
መልካና ደም ግባት ፤ የተባበረላት
ጸጋን የተመላች ፤ በዕንቁ ያጌጠች
የመመኪያችን ዘውድ ፤ ማርያም ተወለደች።
ታዲያ ይህችን እለት ፤
እንዴት እናክብራት ፤ በምን ያህል ድምቀት
አይደለም የሌላ ፤ የተራ ሰው ልደት
እንዴት ባለ ቅኔ ፤ ጠቢቡስ ያገልግል
ልደቷ ብቻውን ፤ ድንቅ ነው የድንግል።

https://www.tg-me.com/Mgetem
https://www.tg-me.com/Mgetem
https://www.tg-me.com/Mgetem

እንኳን አደረሳችሁ!
✍️ አቤል ታደለ
@abeltadele
ዘተወለድኪ ማርያም እምነ ቡርክት ማኅፀን፥
አድኅንኒ እምነገሮሙ ለሰብአ ዓማፂት ዘመን፥
እለ ይትናገሩ በክልኤ ልሳን።
-----------
ከተባረከች ማኅፀን የተወለድሽ ማርያም ሆይ:- በሁለት ቢላ ከሚበሉ የዐመፃ ዘመን ሰዎች አድኚኝ!

እም መልክዐ ልደታ
__
www.tg-me.com/Andkelem
www.tg-me.com/andkelem
ገና በማለዳ
ይንቦገቦጋል ልቤ በሀሴት
ማን ቀርፎ ጣለ የኑሮዬን ምሬት?
ቆይ ምን ተፈጥሮ ወረረኝ ደስታ?
ድብርት ማያጣው
ጭፍግጉ ፊቴ እንዴት ተፈታ?

ሳቅ ሳቅ ይለኛል ደርሶ መፈገግ
ማንባት አልነበር የህይወቴ ወግ?
ማዘን መከፋት መጥላት ሁሉንም
ዛሬን ምን ለየው?
                ... እንጃ! አልገባኝም!

ብቻ
ከአፌ ይሾልካል የመዝሙር ግጥም
ምሬት አልነበር የምቆረጥም?
ብሶት አይደል ወይ የማኝክ ሁሌ
ተመስገን ቃልን ማን ሰጠ ለኔ?
ከየት አፈስኩት በዚህ ጠዋት
ሞት እኮ ነበር የኔስ ምኞት

ብቻ
ወጣሁ ከቤቴ
ፍልቅልቅ ሳቄ ሐዘኔን ረቶት
ዐይኔ ታዘበ
ነጠላ ለባሽ መንገዱን ሞልቶት
አሰብኩ በብርቱ አጤንኩ ጠልቄ
ቀኑ ምን ነበር?
               ... እንጃ! ምን አውቄ!

ጠየቅኩ መንገደኛ ሰማሁ ከአላፊ ሴት
ልደቷ ነው ለካ የአለሟ እመቤት
ለዛ ነው የፈካው ጽልመታም ቀኔ
ለዛ ነው የሸሸው አቃፊ ሐዘኔ
ማርያም እናቴ
በእለተ ውልደቷ ሆናኝ መድኅኔ

#ኤልዳን - 1/9/17
https://www.tg-me.com/Mgetem
https://www.tg-me.com/Mgetem
https://www.tg-me.com/Mgetem
ደጅህ ስመላለስ
ነጠላ አደግድጌ የልቤን ማን ያውቃል
የሚመለከተኝ
ብርቱ ሰው መስየው በእኔ ይደነቃል
.
እሱማስ ይሉኛል ስሜን እያነሱ
ውሎና አዳሩ ከቤተመቅደሱ
እሱማስ ይሉኛል እየተደነቁ
ዕላዬን ነው እንጂ ውስጤን መች አወቁ
!

https://www.tg-me.com/Mgetem
https://www.tg-me.com/Mgetem
https://www.tg-me.com/Mgetem
[ ጥሩቤል ]
@tirrubel
ፅልመትን መጋፋት ፤
ላያድን ከእንቅፋት ፤
ቆመህ አትታገል ፤ እንደ አለም የዋሃን
ጭለማውን ቅደድ ፤ ፈንጥቀህ ብርሃን ።
ለሊቱን ከመርገም ፤ ተጠጋ ከጀንበር
በሚገፉህ ሁሉ ፤ ወድቀህ እንዳትሰበር።


https://www.tg-me.com/Mgetem
https://www.tg-me.com/Mgetem
https://www.tg-me.com/Mgetem
አቤል ታደለ


ለአስተያየት : @abeltadele
ይድረሰኝ በረከትሽ ❤️
@Mgetem

ይድረሰኝ በረከትሽ የጌታ እናት የጭንቅ ቀን ደራሽ
ልንበርከክ በጉልበቴ ድንግል ለክብርሽ
አባ ጊዮርጊስ እንዳመሰገነሽ
አባህርያቆስ እንዳወደሰሽ
አባ ኤፍሬም እንደተቀኘልሽ እኔም ላመስግንሽ
የጌታዬ እናት ይጣፍጣል ስምሽ
የራቤ መና ነሽ የመጠጤ ዉሐ ነሽ
የድክሜ ብርታት የህመሜ ፈዉስ ነሽ
ደግሜ ደጋግሜ ድንግል ላመስግንሽ

ባይገባኝም እንኳን የአንቺን ስም መጥራት
በምን ላመስግንሽ የአምላኬ እናት
ኃጢአቴ የበዛ ብሆንም ደካማ አልሸሸግም የአንቺን ስም ከመጥራት
የጭንቅ ቀን ደራሽ የጌታዬ እናት
ላመስግንሽ ድንግል ልንበርከክ ከስዕልሽ ፊት እንዳገኝ ምህረት
ዉዳሴሽን ልድገም ልጠጣ ፀበልሽን ትሰጫለሽና ለነብሴ እረፍት
ይሆነኛልና ለህመሜ ፈውስ ለመዳኔ ምክንያት
ቃል ኪዳን አገኘሽ ኪዳነምህረት

ዕዉርን ያበራሽ ሳለሽ በማህፀን
ምንኛ ድንቅ ነዉ አንቺን የፀነሰ የሐና ማህፀን
ላመስግንሽ ድንግል ልቀኝልሽ በእዉነት
ይህ ያንስሻልና የአማኑኤል እናት
ይድረሰኝ በረከትሽ የአምላክ እናት የአለም ሁሉ እናት

የፃድቃን የሰማዕታት ማረፊያ እቅፍ
አኑሪኝ ድንግል ሆይ በቅዱሳን እቅፍ
ይድረስልሽ በይኝ ሚካኤል በክንፍ
መኖርን እሻለሁ በአምላክ እቅፍ

አሳስቢልኝ ድንግል ከልጅሽ ከአማኑኤል
ኃጢአቴን ደምስሶ ይቅር እንዲለኝ
አማልጂኝ ድንግል ሆይ ከአምላክ ከልዑል
ከእሱ ዉጪ ማን አለ ይቅር የሚል

የቅድስት ሃና የኢያቄም ብሩክት
እኛንም አሳስቢን በሰርክ በፀሎት
_________
መልካም ሰንበት

https://www.tg-me.com/Mgetem
https://www.tg-me.com/Mgetem
https://www.tg-me.com/Mgetem
ልዩ ምሥክር ናት
@Mgetem

እንደ ከዚህ ቀደም ፤ አብሳሪው መልአክ
ለሌሎች እንዳለው ፤ ከአርያም ሲላክ
ሠምቶሻል እግዚአብሔር ፤ የልብሽ መሻቱን
አላለም ለድንግል ፤ ሲጀምር ብሥራቱን ።

ምክንያቱም እሷ ፤
ለምና አታውቅም ፤ ሥለትም ተስላ
የፈጣሪ እናት ፤ እኔ ልሁን ብላ ።

ምክንያቱም እሷ ፤
እንደ ደናግላን ፤ ድንገት አሁን ካሁን 
ጠብቃ አታውቅም ፤ ለመውለድ መሲሁን ።

ምክንያቱም እሷ ፤
እንደነ ኤልሳቤጥ ፤ ወይም እንደ ሐና
ልጅ እንኳን ለማግኘት ፤ አታውቅም ተማፅና ።

ምክንያቱም እሷ ፤
መሆኑ አልገባት ፤ እንድትሆን እልፍኙ
ገና በልጅነት ፤ ያረጋት መናኙ ።

ምክንያቱም እሷ ፤
በልቧ ጸንሳው ፤ መኖርን ነው እንጂ
መባል አታስብም ፤ አምላክን ውለጂ ።

ምክንያቱም እሷ  ፤
ምረጠኝ ሳትለው ፤ ወዶ የመረጣት
አንዳችም ሳትሻ ፤ ሁሉ የተሰጣት
የእርሱ ድንቅ ሥራ ፤ ልዩ ምሥክር ናት ።

https://www.tg-me.com/Mgetem
https://www.tg-me.com/Mgetem
https://www.tg-me.com/Mgetem
አቤል ታደለ


ለአስተያየት : @abeltadele
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
2025/07/04 20:30:15
Back to Top
HTML Embed Code: