Telegram Web Link
ግንቦት_16

አንድ አምላክ በሆነ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም ግንቦት ዐሥራ ስደስት በዚችም ቀን የወንጌላዊ ቅዱስ ዮሐንስ መታሰቢያው ነው።

በእስያና በኤፌሶን በዙሪያቸው በአሉ አገሮች ሁሉ ስለ መስበኩና ከባሕር በመስጠምም ወደ ፈጣሪያቸው እግዚአብሔር እስከ መለሳቸውና የክብር ባለቤት ጌታችን በእጆቹ ላይ የሚያደርገው ተአምራት በትምህርቶቹም ከሰይጣን ወጥመድ እስከ አዳናቸው ድረስ ጣዖታትን ከሚያመልኩ ከክፉዎች ሰዎች ስለደረሰበት መከራ ነው።

በሸመገለም ጊዜ ወንጌልን ጻፈላቸው ሦስቱ ወንጌላውያን ያስቀሩትን እስከሚጽፍ መንፈስ ቅዱስ አነሣሥቶታልና የወልድንም አኗኗሩንና ሰው መሆኑን ዓለም የማይወስነውንም ተአምራቱን። ከዚህ በኋላም ወደ ሰማይ እንደ ወጣና በሰማይ የሚኖሩ የመላእክት ሠራዊት ሥርዓታቸውን አይቶ አቡቀለምሲስ የሚባለውን ጻፈ።

ለስብከቱም የበዓሉ መታሰቢያ ሊሆን ግብጻውያን ይህን ሠሩ ዳግመኛም በእስክንድርያ አገር ውስጥ ቤተ ክርስቲያኑ የከበረችበት ቀን ነው። (ስንክሳር ዘወርኀ ግንቦት 16)
_
www.tg-me.com/andkelem
www.tg-me.com/andkelem
እስቲ ደሞ ህጄ
ነጠላ አደግድጌ ልንበርከከው ደጁን፤
አፍ እንደሆን አፍ ነው
  የጎረሰበትን አይረሳም  ወዳጁን፤

ዳግም ተመልሼ  እስከምበድልህ
በል ቁጥር ንገረኝ ስንት ልስገድልህ?

/እንካ ንስሀዬን/

ትላንት ሀሙስ ለታ
ልቤን የቀደደ  መገለጥ ተሰማኝ፣
አስገደፈችልህ /በጧሚ አፏ ስማኝ/

አወይ ባትጀምረኝ
ወይ መሳሟን ባትተው ፣
ከርቤ ከርቤ አለችኝ
  ከንፈሯን ብትከፍተው!

መብረቅ ዳብሳለች ወይ
እስከማርያም ጣቷ?
አንዘረዘረችኝ
አቤት ሀጢያቴ_አቤት ሃጢያቷ!

/ሳመችኝ ነው ምልህ/ 

ምላሷን አውጥታ  ጥርሴን አነጣችው
ባፍንጫዬ ዘልቃ ጀሮዬን ሳመችው

እስቲ ምናለበት
ጉሮሮዬን አልፋ ውስጤ ብትቀበር፤
ድምፄን ያመኝ ነበር?
  ልቤን ያመኝ ነበር?

ይመመኝ ይመመኝ
ተስፋ ቆርጦ ይሂድ አስታማሚ ደክሞት
/ፍታት አይቀርብኝ/
እንኳን በሷ ምላስ_ወባ ነድፋኝ ብሞት።

በል ቁጥር ንገረኝ ስንት ልስገድልህ
ዳግም ተመልሼ እስከምበድልህ

ከተናደድኽብኝ 
መሰንዘር ከወድድኽ እጅህን ለበቀል
ሀዘንህ ጎርፍ ይሁን ቁጣህ ሁሉን ይንቀል

እንባችን ወንዝ ይሙላ
ባይነት በግፍ በግፍ
በልምጭ ካቃትንህ
ከሰማይ ቀስት አርግፍ

ሰው ምርጫው ካረገ ስሜትና ሆዱን
ክፍትፍቱን ክደን የመዳን መንገዱን

  አጥፋው ሁሉን ፍጡር 
ጨለማን አታንጋው፤
  ዋ ብቻ አደራህን
/ከንፈሯን/ አትዝጋው::

ዳግም ተመልሼ እስከምበድልህ
...........ስንት ልስገድልህ
!

━━━━━━━━✦🖤✦━━━━━━━━
ምርጫዎ ስለሆነ እናመሰግናለን  ❤️

https://www.tg-me.com/Mgetem
https://www.tg-me.com/Mgetem
https://www.tg-me.com/Mgetem
"የምኲራቡ"

https://youtube.com/shorts/6aR3zk8TlyM?si=UFOrUs_KOsK2S47-

ከ"እዩት" የመዝሙር ግጥም መድብል የተወሰደ
መጽሐፉን ከAndkelem mobile app በቅርብ ቀን ያገኙታል።
___
www.tg-me.com/andkelem
www.tg-me.com/andkelem
ልክ እንደ ገብርኤል
@Mgetem

ልክ እንደ ገብርኤል ፤ ውስጡ ደስ ያላለው
እውነተኛ ሰላም ፥ በልቡ የሌለው
ባለበት ያልጸና ፤ ፍፁም የማያምን
ሰላም ለኪ ይበል ፤ እንደምን ማርያምን ።

ልክ እንደ ገብርኤል ፤ ፀሎትን ለማድረስ
ከፈጣሪው ታርቆ ፤ በእግዚአብሔር መቅደስ
በፊቱ የማይቆም ፤ ያለ አንዳች ማቋረጥ
ማርያም ፊት ለመቆም ፤ እንደምን ይመረጥ ።

ልክ እንደ ገብርኤል ፤ በቀንና በሌት
ዘወትር ሳያስታጉል ፤ የማይቆም ማህሌት
አብሮ የማይሰለፍ ፤ ከመላእክት ወገን
እንደምን ይችላል ፤ ማርያምን ማመስገን።

አቤል ታደለ


https://www.tg-me.com/Mgetem
https://www.tg-me.com/Mgetem
https://www.tg-me.com/Mgetem
ለአስተያየት : @abeltadele
Forwarded from Kesatebirhan Ze Tewahdo (መንፈሳዊ ግጥም ብቻ)
​​📌ኤላም ቤተ ስብሐት

ጥሩ የዝማሬ ጸጋ ኖሮት ፣ መዝሙር የማውጣት ምኞት ይዘው ግጥምና ዜማ ከየት አገኛለሁ ብለው ከተጨነቁ ወደ ኤላም ቤተ ስብሐት ይደውሉ።

በንባብም ሆነ በምሥጢር ኦርቶዶክሳዊ ደረጃቸውን የጠበቁ መንፈሳዊ የመዝሙር ግጥምና ዜማ ያገኛሉ።

💎ምን ምን ያገኛሉ?

👉 መደበኛ የምስጋና መዝሙራት
👉 የንስሐ መዝሙራት
👉 የበገና መዝሙራት
👉 የመዲናና ዘለሰኛ መዝሙራት
👉 የእማሆይ መዝሙራትን ያገኛሉ።

✍️ በተጨማሪም በመረጡት የትኛውም ርእሰ ጉዳይ በትእዛዝ እንጽፍልዎታለን።

ቅንብሩን ጨርሰው የግራፊክስ ዲዛይን ሥራ ካስፈለገም እንሠራልዎታለን። 📷

ኑ! ስብሐተ እግዚአብሔርን እናስፋ!
ኤላም ቤተ ስብሐት

📱ስልክ ቁጥር
+251912239783
+251912831494
📩 በቴሌግራም @kebras @solasc12
#ድረስ_ቶሎ_ና_ገብርኤል
@Mgetem

ድረስ ቶሎ ና ገብርኤል ከላይ ከራማ
ትሻለች ነፍሴ ተጨንቃ ጠፍቶ ሰላሟ
መንገዴን በሾህ አጥሮታል አዳኝ ጠላቴ
ድረስ ቶሎ ና ገብርኤል ቅደም ከፊቴ
ተቆጥቶ ዘንዶ በኔ ተነሳስቶዋል
ጎዳናዬን ባሀር ወርሶት አውኮኛል
ብርቱ መልአክ ድረስና ተዋጋልኝ
ገዳዬን ጣልልኝ
ጉልበተኛው ችሎ አይቆምም ባለህበት
እንደ ውሀ ቀዝቃዛ ነው የቶን እሳት
አይዞህ በለኝ እሳቶኑን እንዳልፈራ
ሆነህ ከኔ ጋራ
እንደ ጋራ ላይ የወጣው ነበልባል   
አያቃጥለኝ ፈጥነህ ድረስ ገብርኤል
ትሽሀለች ነፍሴ ጨንቋት በፈተና
ገብርኤል ቶሎ ና
ድረስ ቶሎ ና ገብርኤል ከላይ ከራማ
ትሻለች ነፍሴ ተጨንቃ ጠፍቶ ሰላማ
መንገዴን በሾህ አጥሮታል አዳኝ ጠላቴ
ድረስ ቶሎ ና ገብርኤል ቅደም ከፊቴ

https://www.tg-me.com/Mgetem
https://www.tg-me.com/Mgetem
https://www.tg-me.com/Mgetem
እስኪ ሼር በማድረግ ጓደኞቻችሁን ወደ ቻናላችን ጋብዟቸው
👇👇👇👇
https://www.tg-me.com/Mgetem
https://www.tg-me.com/Mgetem
መምህር መግስቱ ጥላሁን  የባህል_ህክምና 09-29-66-76-26
#ትክክለኛዉን_እና_የቀደምት_ሊቃውንት_የአባቶቻችንን #ጥበብ_ይሻሉ_ወይም_ይፈልጋሉ_እንግዲያውስ #ከምንሰጣቸው_የጥበብ አገልግሎቶች በትንሹ ከታች ተዘርዝረዋል
1  ለሀበት
2  ለመፈትሄ ስራ
3  ለመስተፋቅር
4  ለስንፈተ ወሲብ
5  ለበረከት
6   ለገቢያ
7   ለትዳር እንቢ ላላቹሁ
8  ለአይነ ጥላ
9   ለስልጣን
10 ገንዘብ አልበረክት ላላችሁ
11 ለግርማ ሞገስ
12 ገንዘባቹሁን የተወሰደባቹሁ እንዲመለስላቹሁ የሚያደርግ
13 አፍዝ አደንግዝ
14 ለትዳር የሚሆን ኮኮብ ቆጠራ
15 ለሁሉ መስተፍቅር
16 ለድምፅ
17 ለብልት
18 ለውጭ እድል
19  ወንድ ልጅ ብቻ እየወለዱ ሴት ልጅ መዉለድ ለተሳናቸዉ
20 ለደም ግፊት
21 ለመካንነት
22  ለህመም
09-29-66-76-26
23 ኢቃማ ሳይኖራቹሁ ለምትንቀሳቀሱ እንዳትያዙ የሚያደርግ
24 ሴት ልጅ ብቻ እየወለዱ
ወንድ ልጅ መዉለድ ለተሳናቸዉ
25 ለጥይት መከላከያ ወይም ጥይት እዳይመታ የሚያደርግ
26 እፀ መሰዉር
ከምንሰጣቸዉ
በትንሹ  ይህን ይመስላል
በአካል መምጣት ለማትችሉ ወይም መዳኒቱን ለምትፈልጉ ከአገር  ውጭም  ሆነ  ከአገር ውስጥ  ባሉበት ቦታ እናደርሳለን  
ልብ ይበሉ  ትክክለኛዉን የባህል መዳህኒት ለማግኘት እኛጋ ይምጡ
ለጥያቄ ይደውሉልን
⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️
☎️09-29-66-76-26
☎️09 29 66  76 26
Whatsapp
Talagram
imo
ማናገር ይችላሉ
ዐረገ በእልልታ
@Mgetem

የተዋሐደውን ሥጋ ፤
የከፈለበትን ዋጋ ፤
አልተወውም በመቃብር ፤
ከፍ አደረገው በክብር ፤
የአዳምም ፀጋ ፤ ከቀድሞ በለጠ
በዘባነ ኪሩብ ፤ ሰው ልጅ ተቀመጠ ።
ዛሬ በደመና ፤ ሰማይ ተቀበለው
ትላንትና ዮሴፍ ፤ እንደ ጠቀለለው ።
ዛሬ በአባቱ ቀኝ ፤ ከበረ ክርስቶስ
ትላንት እንደ ቆመ ፤ በቅጥረ ጲላጦስ።
ዛሬ በመለከት ፤ ዐረገ በእልልታ
ትላንትና ህማም ፤ የዋለበት ጌታ።
ዛሬ ዘመሩለት ፤ መላእክት አጅበው
ትላንትና ጭፍሮች ፤ ያፌዙበት ከበው።
ዛሬም ቢሆን ፥ ወደ ሰማይ ፤ ነገም ቢሆን ትላንትና
እንደ ኢየሱስ ፥ ከፍ አይልም ፤ ዝቅ ያላለ በትህትና ።

https://www.tg-me.com/Mgetem
https://www.tg-me.com/Mgetem
https://www.tg-me.com/Mgetem

አቤል ታደለ

ለአስተያየት : @abeltadele
ዓርገ ሰማያተ በዓምደ ደመና፥
ለድንግል ተፈትሐ ማኅፀና፥
ለደቂቀ እስራኤል ዘአውረደ መና፥
ዓርገ ሰማያተ በአምደ ደመና።

ውርስ ትርጉም

በድንግል ማኅፀን፥
ያን ሥጋ አዳምን፥
ወደ አምላክነት ልዕልና ያሳረገ፥
በአምደ ደመና ወደ ሰማይ አረገ፥
ለእስራኤል ልጆች ያወረደ መና፥
ዐረገ በስብሐት በዐምደ ደመና።

ዚቅ

እንኳን ለብርሃነ ዕርገቱ በሰላም አደረሳችሁ!

____
www.tg-me.com/andkelem
www.tg-me.com/andkelem
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
#ቅድስት_እናት
@Mgetem

ይቺ ቅድስት እናት _ ቃልን ወሰነችው
በከብቶቹ ግርግም_ ወልዳ ታቀፈችው
በመጠቅለያም_ጠቀለለችው።

ለደቱንም ዘር_ አልቀደመውም
የዳዊት ሥር ነው_መድኃኒአለም
በመወለዱም ድንግልናዋን_አልለወጠውም
የተዘጋች ደጃፍ_እናታችን ማርያም።

ቃል ከአብ _ ያለ ድካም ወጣ
የአዳም ልደቱ_ ደረሰለት ዕጣ
ከድንግልም ያለ _ሕማም ተወለደ
በእውነተኛው ብርሃን_ከሳሽ ተሰደደ።

ምጥ ሳያገኛት_ተሰማ እልልታ
ሰበአ ሰገል መጡ_ሊሰግዱ ለጌታ
እረኞች _ ዘመሩ ተሞልተው ደስታ።

ለአምላክነቱ አመጡለት _ዕጣን
ለንጉሥነቱ _ አቀረቡ ወርቁን
መድኃኒት ነውና _ ገለጡት ትንቢቱን
እነሆ አየነው_ ምስዋዕት ከርቤውን።

ግርማ ያለሽ_ድንግል የአሮን በትር
እናደንቅሻለን _ የሁላችን ክብር
ገናንነትሽን _ልንዘረዝር
በያሬድ ውብ ዜማ_ በዳዊት መዝሙር
ቆመናል ከደጅሽ_ ልንደረድር።

እንደ መልአኩ ገብርኤል_ ከላይ እንደመጣው
ልናመሰግንሽ _ ማርያም ግድ ነው
የባሕሪያችን መዳን_ካንቺ ተገኘልን
በማሕጸንሽ ፍሬ_ሞት ተቀበረልን።

እንደ ሠርግ _ቤት ጉድፍ የሌለብሽ
መንፈስ ቅዱስ _ ያደረብሽ
የልዑል ኃይልም ማርያም ጸለለበሽ ።

ዘለአለም ነዋሪ_የነገስታት ንጉስ
ከኃጢአት ያዳነን_ ይመስገን ኢየሱስ
የልባችን ሰላም_ፍቅርህ በኛ ይንገስ።

ከአብ የተወለደ _ከአለም በፊት የነበረ
አንዱ ቃል እራሱን ( ባሕሪዩን) ሰወረ
እንደምን ይረቃል_የሰማዩ ምስጢር
የሱ ያደረገን_ ይመስገን እግዚአብሔር።

የኪዳን ጽላት_ያለብሽ
የተሰወረ መና_የተሸከምሽ
የወርቅ መሶብ_ የምንልሽ
ደብተራ ድንኳን _አንቺ ነሽ
የጥበብን ወንጌል_ በክንድሽ የታቀፍሽ
አሳስቢ ድንግል ሆይ_ ለመሃሪው ልጅሽ
እናምናለንና _ ሁሉ እንደሚቻልሽ

https://www.tg-me.com/Mgetem
https://www.tg-me.com/Mgetem
https://www.tg-me.com/Mgetem
# መስክር
https://www.tg-me.com/Mgetem

ልጨክን እልና....
ላልጨክን  ተዋለው :
የእውነት ለመኖር....
የውሸት ኖራለው:

ክርስቲያን ነኝ  ብልም 
ግብሬ ግን ሌላ ነው :
ላልጨክን መጨከን
ለኔ  አይነት አዳ ነው ::
  
       ወይ እውነት ወይ ሐሰት :
       ወይ ድፍረት ወይ ሃፍረት :
       መመስከር ግድ ነው
        አኔ በማምንበት::

https://www.tg-me.com/Mgetem
https://www.tg-me.com/Mgetem
https://www.tg-me.com/Mgetem
ማርያም እስካለ
@Mgetem

የበግ ለምድ ለበሶ ፤ አስመሳዩ ተኩላ
ከእናታችን ነጥቆ ፤ እኛንም ሊበላ
መስሎ ተቆርቋሪ ፤ የእውነት ጠበቃ
ፀሀይን ጋረደች ፤ ይለናል ጨረቃ ።
ደካማ ነው ብሎ ፤ ሺ ጊዜ ቢወድቅም
ማርያም እስካለ ፤ ሰይጣን ሰው አይንቅም።
የጥላቻ መርዙን ፤ በወንጌል አስታኮ
የኛንም ምስጋና ፤ ይለዋል አምልኮ ።
ደግነቷ እንጂ ፤ የጌታዬ እናቱ
ከክፉ ጠማማ ፤ ከእንደኛ አይነቱ
አለም ካሰመጠን ፤ በኃጢያት ማእበል
ባልተገባት ነበር ፤ ምስጋና መቀበል።

https://www.tg-me.com/Mgetem
https://www.tg-me.com/Mgetem
https://www.tg-me.com/Mgetem
✍️ አቤል ታደለ

ለአስተያየት : @abeltadele
እንደምን አይገርም
@Mgetem

አምላክን መጽነሷን ፤ እመብርሃን አውቃ
ዘመዷን ኤልሳቤጥ ፤ ሄዳ መጠየቋ
እንደምን አይገርም ።
ከሴቶች መካከል ፤ ከፃድቃኑም ጎራ
አንቺ ብርክት ነሽ ፤ ተብላ ሳትኮራ
ወደ ተራራማው ፤ የይሁዳ ከተማ
ፈጥና መነሳቷ ፤ ጥቂት ሳታቅማማ
እንደምን አይገርም ።
ታላቅ የምስራች ፤ ሆኖ የእሷ ጉዳይ
ከታናሹ ደስታ ፤ ልትሆን ተካፋይ
አማናዊ ፀሀይ ፤ በማህፀኗ ይዛ
የኮከቡን እናት ፤ ልትጎበኝ መጓዟ
እንደምን አይገርም ።
የንጉሦች ንጉስ ፤ ፈጣሪን ጸንሳ
ትእቢት ሳይኖርባት ፤ ዘመድ ማስታወሷ
ክብሯን ሳትነፃፅር ፤ ከኤልሳቤጥ ጋራ
አጃቢ ሳትሻ ፤ መንገድ መጀመሯ
እንደምን አይገርም።

https://www.tg-me.com/Mgetem
https://www.tg-me.com/Mgetem
https://www.tg-me.com/Mgetem
አቤል ታደለ
ለአስተያየት :
@abeltadele
ንሸጣ፦የብርሃን እናት (ዲያቆን ሄኖክ ሃይሌ)
2025/07/05 19:27:37
Back to Top
HTML Embed Code: