Telegram Web Link
ልክ እንደ ገብርኤል
@Mgetem

ልክ እንደ ገብርኤል ፤ ውስጡ ደስ ያላለው
እውነተኛ ሰላም ፥ በልቡ የሌለው
ባለበት ያልጸና ፤ ፍፁም የማያምን
ሰላም ለኪ ይበል ፤ እንደምን ማርያምን ።

ልክ እንደ ገብርኤል ፤ ፀሎትን ለማድረስ
ከፈጣሪው ታርቆ ፤ በእግዚአብሔር መቅደስ
በፊቱ የማይቆም ፤ ያለ አንዳች ማቋረጥ
ማርያም ፊት ለመቆም ፤ እንደምን ይመረጥ ።

ልክ እንደ ገብርኤል ፤ በቀንና በሌት
ዘወትር ሳያስታጉል ፤ የማይቆም ማህሌት
አብሮ የማይሰለፍ ፤ ከመላእክት ወገን
እንደምን ይችላል ፤ ማርያምን ማመስገን።

አቤል ታደለ


https://www.tg-me.com/Mgetem
https://www.tg-me.com/Mgetem
https://www.tg-me.com/Mgetem
ለአስተያየት : @abeltadele
👍2620🥰5👎1
Forwarded from Kesatebirhan Ze Tewahdo (መንፈሳዊ ግጥም ብቻ)
​​📌ኤላም ቤተ ስብሐት

ጥሩ የዝማሬ ጸጋ ኖሮት ፣ መዝሙር የማውጣት ምኞት ይዘው ግጥምና ዜማ ከየት አገኛለሁ ብለው ከተጨነቁ ወደ ኤላም ቤተ ስብሐት ይደውሉ።

በንባብም ሆነ በምሥጢር ኦርቶዶክሳዊ ደረጃቸውን የጠበቁ መንፈሳዊ የመዝሙር ግጥምና ዜማ ያገኛሉ።

💎ምን ምን ያገኛሉ?

👉 መደበኛ የምስጋና መዝሙራት
👉 የንስሐ መዝሙራት
👉 የበገና መዝሙራት
👉 የመዲናና ዘለሰኛ መዝሙራት
👉 የእማሆይ መዝሙራትን ያገኛሉ።

✍️ በተጨማሪም በመረጡት የትኛውም ርእሰ ጉዳይ በትእዛዝ እንጽፍልዎታለን።

ቅንብሩን ጨርሰው የግራፊክስ ዲዛይን ሥራ ካስፈለገም እንሠራልዎታለን። 📷

ኑ! ስብሐተ እግዚአብሔርን እናስፋ!
ኤላም ቤተ ስብሐት

📱ስልክ ቁጥር
+251912239783
+251912831494
📩 በቴሌግራም @kebras @solasc12
👍92🤬1
#ድረስ_ቶሎ_ና_ገብርኤል
@Mgetem

ድረስ ቶሎ ና ገብርኤል ከላይ ከራማ
ትሻለች ነፍሴ ተጨንቃ ጠፍቶ ሰላሟ
መንገዴን በሾህ አጥሮታል አዳኝ ጠላቴ
ድረስ ቶሎ ና ገብርኤል ቅደም ከፊቴ
ተቆጥቶ ዘንዶ በኔ ተነሳስቶዋል
ጎዳናዬን ባሀር ወርሶት አውኮኛል
ብርቱ መልአክ ድረስና ተዋጋልኝ
ገዳዬን ጣልልኝ
ጉልበተኛው ችሎ አይቆምም ባለህበት
እንደ ውሀ ቀዝቃዛ ነው የቶን እሳት
አይዞህ በለኝ እሳቶኑን እንዳልፈራ
ሆነህ ከኔ ጋራ
እንደ ጋራ ላይ የወጣው ነበልባል   
አያቃጥለኝ ፈጥነህ ድረስ ገብርኤል
ትሽሀለች ነፍሴ ጨንቋት በፈተና
ገብርኤል ቶሎ ና
ድረስ ቶሎ ና ገብርኤል ከላይ ከራማ
ትሻለች ነፍሴ ተጨንቃ ጠፍቶ ሰላማ
መንገዴን በሾህ አጥሮታል አዳኝ ጠላቴ
ድረስ ቶሎ ና ገብርኤል ቅደም ከፊቴ

https://www.tg-me.com/Mgetem
https://www.tg-me.com/Mgetem
https://www.tg-me.com/Mgetem
21👍6
እስኪ ሼር በማድረግ ጓደኞቻችሁን ወደ ቻናላችን ጋብዟቸው
👇👇👇👇
https://www.tg-me.com/Mgetem
https://www.tg-me.com/Mgetem
16👍13🥰4
መምህር መግስቱ ጥላሁን  የባህል_ህክምና 09-29-66-76-26
#ትክክለኛዉን_እና_የቀደምት_ሊቃውንት_የአባቶቻችንን #ጥበብ_ይሻሉ_ወይም_ይፈልጋሉ_እንግዲያውስ #ከምንሰጣቸው_የጥበብ አገልግሎቶች በትንሹ ከታች ተዘርዝረዋል
1  ለሀበት
2  ለመፈትሄ ስራ
3  ለመስተፋቅር
4  ለስንፈተ ወሲብ
5  ለበረከት
6   ለገቢያ
7   ለትዳር እንቢ ላላቹሁ
8  ለአይነ ጥላ
9   ለስልጣን
10 ገንዘብ አልበረክት ላላችሁ
11 ለግርማ ሞገስ
12 ገንዘባቹሁን የተወሰደባቹሁ እንዲመለስላቹሁ የሚያደርግ
13 አፍዝ አደንግዝ
14 ለትዳር የሚሆን ኮኮብ ቆጠራ
15 ለሁሉ መስተፍቅር
16 ለድምፅ
17 ለብልት
18 ለውጭ እድል
19  ወንድ ልጅ ብቻ እየወለዱ ሴት ልጅ መዉለድ ለተሳናቸዉ
20 ለደም ግፊት
21 ለመካንነት
22  ለህመም
09-29-66-76-26
23 ኢቃማ ሳይኖራቹሁ ለምትንቀሳቀሱ እንዳትያዙ የሚያደርግ
24 ሴት ልጅ ብቻ እየወለዱ
ወንድ ልጅ መዉለድ ለተሳናቸዉ
25 ለጥይት መከላከያ ወይም ጥይት እዳይመታ የሚያደርግ
26 እፀ መሰዉር
ከምንሰጣቸዉ
በትንሹ  ይህን ይመስላል
በአካል መምጣት ለማትችሉ ወይም መዳኒቱን ለምትፈልጉ ከአገር  ውጭም  ሆነ  ከአገር ውስጥ  ባሉበት ቦታ እናደርሳለን  
ልብ ይበሉ  ትክክለኛዉን የባህል መዳህኒት ለማግኘት እኛጋ ይምጡ
ለጥያቄ ይደውሉልን
⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️⬇️
☎️09-29-66-76-26
☎️09 29 66  76 26
Whatsapp
Talagram
imo
ማናገር ይችላሉ
9😢5👎4👍3🥰2
ዐረገ በእልልታ
@Mgetem

የተዋሐደውን ሥጋ ፤
የከፈለበትን ዋጋ ፤
አልተወውም በመቃብር ፤
ከፍ አደረገው በክብር ፤
የአዳምም ፀጋ ፤ ከቀድሞ በለጠ
በዘባነ ኪሩብ ፤ ሰው ልጅ ተቀመጠ ።
ዛሬ በደመና ፤ ሰማይ ተቀበለው
ትላንትና ዮሴፍ ፤ እንደ ጠቀለለው ።
ዛሬ በአባቱ ቀኝ ፤ ከበረ ክርስቶስ
ትላንት እንደ ቆመ ፤ በቅጥረ ጲላጦስ።
ዛሬ በመለከት ፤ ዐረገ በእልልታ
ትላንትና ህማም ፤ የዋለበት ጌታ።
ዛሬ ዘመሩለት ፤ መላእክት አጅበው
ትላንትና ጭፍሮች ፤ ያፌዙበት ከበው።
ዛሬም ቢሆን ፥ ወደ ሰማይ ፤ ነገም ቢሆን ትላንትና
እንደ ኢየሱስ ፥ ከፍ አይልም ፤ ዝቅ ያላለ በትህትና ።

https://www.tg-me.com/Mgetem
https://www.tg-me.com/Mgetem
https://www.tg-me.com/Mgetem

አቤል ታደለ

ለአስተያየት : @abeltadele
🥰2415👍6
ዓርገ ሰማያተ በዓምደ ደመና፥
ለድንግል ተፈትሐ ማኅፀና፥
ለደቂቀ እስራኤል ዘአውረደ መና፥
ዓርገ ሰማያተ በአምደ ደመና።

ውርስ ትርጉም

በድንግል ማኅፀን፥
ያን ሥጋ አዳምን፥
ወደ አምላክነት ልዕልና ያሳረገ፥
በአምደ ደመና ወደ ሰማይ አረገ፥
ለእስራኤል ልጆች ያወረደ መና፥
ዐረገ በስብሐት በዐምደ ደመና።

ዚቅ

እንኳን ለብርሃነ ዕርገቱ በሰላም አደረሳችሁ!

____
www.tg-me.com/andkelem
www.tg-me.com/andkelem
28👍3🥰3👏1
ምክንያት ስላለኝ ነው
ዘማሪት ምርትነሽ ጥላሁን
ምክንያት ስላለኝ ነው
https://www.tg-me.com/MMezmur

ምክንያት ስላለኝ ነው የምዘምርልሽ
ምክንያት ስላለኝ ነው ቅኔ እምቀኝልሽ
አሁንም ይብዛልኝ ፍቅርሽ ፪×
ከዚህ በላይ እንዳመሰግንሽ
አዝ

አውቃለሁ ከደጅሽ ምን እንዳገኘሁኝ
አስታውሰዋለሁ ሸክሜን እንደጣልኩኝ
የለመንኩሽ ሁሉ መቼ ከንቱ ቀረ
ሰይጣን ተመለሰ እያቀረቀረ
ጠላት ቢከፋውም ለአንቺ በመቆሜ
 አደገድጋለው ደግሜ ደግሜ ፪×
አዝ

ልቤ አርፏል በአንቺ በእናቴ አማላጄ
እንቅፋት እሾሁ አይበቅልም በደጄ
በሚጣፍጥ ዜማ በኤፍሬም ውዳሴ
ሳሸበሽብልሽ ትረካለች ነፍሴ
ጠላት ቢከፋውም ለአንቺ በመቆሜ
 አደገድጋለው ደግሜ ደግሜ ፪×
አዝ

ውለታ ያለበት የማይከፈል
ሲመሽም ሲነጋ ያመሰግናል
ማርያም ማርያም ይላል ምድርና ሰማዩ
በልጅሽ መከራ ሞቶለት ገዳዩ
ጠላት ቢከፋውም ለአንቺ በመቆሜ
አደገድጋለው ደግሜ ደግሜ ፪×
አዝ



ዘማሪት ምርትነሽ ጥላሁን
https://www.tg-me.com/MMezmur
https://www.tg-me.com/MMezmur
https://www.tg-me.com/MMezmur
18🥰3👍2👏2
አዳዲስ እንዲሁም ቆየት ያሉ ድንቅ ኦርቶዶክሳዊ ዝማሬዎችን የምታገኙበትን አዲስ ቻናል ከፍተናል፡፡
Join በማድረግ ቤተሰብ ይሁኑ!
👇👇👇👇👇👇
https://www.tg-me.com/MMezmur
https://www.tg-me.com/MMezmur
https://www.tg-me.com/MMezmur
4🥰3
#ቅድስት_እናት
@Mgetem

ይቺ ቅድስት እናት _ ቃልን ወሰነችው
በከብቶቹ ግርግም_ ወልዳ ታቀፈችው
በመጠቅለያም_ጠቀለለችው።

ለደቱንም ዘር_ አልቀደመውም
የዳዊት ሥር ነው_መድኃኒአለም
በመወለዱም ድንግልናዋን_አልለወጠውም
የተዘጋች ደጃፍ_እናታችን ማርያም።

ቃል ከአብ _ ያለ ድካም ወጣ
የአዳም ልደቱ_ ደረሰለት ዕጣ
ከድንግልም ያለ _ሕማም ተወለደ
በእውነተኛው ብርሃን_ከሳሽ ተሰደደ።

ምጥ ሳያገኛት_ተሰማ እልልታ
ሰበአ ሰገል መጡ_ሊሰግዱ ለጌታ
እረኞች _ ዘመሩ ተሞልተው ደስታ።

ለአምላክነቱ አመጡለት _ዕጣን
ለንጉሥነቱ _ አቀረቡ ወርቁን
መድኃኒት ነውና _ ገለጡት ትንቢቱን
እነሆ አየነው_ ምስዋዕት ከርቤውን።

ግርማ ያለሽ_ድንግል የአሮን በትር
እናደንቅሻለን _ የሁላችን ክብር
ገናንነትሽን _ልንዘረዝር
በያሬድ ውብ ዜማ_ በዳዊት መዝሙር
ቆመናል ከደጅሽ_ ልንደረድር።

እንደ መልአኩ ገብርኤል_ ከላይ እንደመጣው
ልናመሰግንሽ _ ማርያም ግድ ነው
የባሕሪያችን መዳን_ካንቺ ተገኘልን
በማሕጸንሽ ፍሬ_ሞት ተቀበረልን።

እንደ ሠርግ _ቤት ጉድፍ የሌለብሽ
መንፈስ ቅዱስ _ ያደረብሽ
የልዑል ኃይልም ማርያም ጸለለበሽ ።

ዘለአለም ነዋሪ_የነገስታት ንጉስ
ከኃጢአት ያዳነን_ ይመስገን ኢየሱስ
የልባችን ሰላም_ፍቅርህ በኛ ይንገስ።

ከአብ የተወለደ _ከአለም በፊት የነበረ
አንዱ ቃል እራሱን ( ባሕሪዩን) ሰወረ
እንደምን ይረቃል_የሰማዩ ምስጢር
የሱ ያደረገን_ ይመስገን እግዚአብሔር።

የኪዳን ጽላት_ያለብሽ
የተሰወረ መና_የተሸከምሽ
የወርቅ መሶብ_ የምንልሽ
ደብተራ ድንኳን _አንቺ ነሽ
የጥበብን ወንጌል_ በክንድሽ የታቀፍሽ
አሳስቢ ድንግል ሆይ_ ለመሃሪው ልጅሽ
እናምናለንና _ ሁሉ እንደሚቻልሽ

https://www.tg-me.com/Mgetem
https://www.tg-me.com/Mgetem
https://www.tg-me.com/Mgetem
39👍7
# መስክር
https://www.tg-me.com/Mgetem

ልጨክን እልና....
ላልጨክን  ተዋለው :
የእውነት ለመኖር....
የውሸት ኖራለው:

ክርስቲያን ነኝ  ብልም 
ግብሬ ግን ሌላ ነው :
ላልጨክን መጨከን
ለኔ  አይነት አዳ ነው ::
  
       ወይ እውነት ወይ ሐሰት :
       ወይ ድፍረት ወይ ሃፍረት :
       መመስከር ግድ ነው
        አኔ በማምንበት::

https://www.tg-me.com/Mgetem
https://www.tg-me.com/Mgetem
https://www.tg-me.com/Mgetem
58😢20👍4🥰4
ማርያም እስካለ
@Mgetem

የበግ ለምድ ለበሶ ፤ አስመሳዩ ተኩላ
ከእናታችን ነጥቆ ፤ እኛንም ሊበላ
መስሎ ተቆርቋሪ ፤ የእውነት ጠበቃ
ፀሀይን ጋረደች ፤ ይለናል ጨረቃ ።
ደካማ ነው ብሎ ፤ ሺ ጊዜ ቢወድቅም
ማርያም እስካለ ፤ ሰይጣን ሰው አይንቅም።
የጥላቻ መርዙን ፤ በወንጌል አስታኮ
የኛንም ምስጋና ፤ ይለዋል አምልኮ ።
ደግነቷ እንጂ ፤ የጌታዬ እናቱ
ከክፉ ጠማማ ፤ ከእንደኛ አይነቱ
አለም ካሰመጠን ፤ በኃጢያት ማእበል
ባልተገባት ነበር ፤ ምስጋና መቀበል።

https://www.tg-me.com/Mgetem
https://www.tg-me.com/Mgetem
https://www.tg-me.com/Mgetem
✍️ አቤል ታደለ

ለአስተያየት : @abeltadele
100🥰11👍8👏4
እንደምን አይገርም
@Mgetem

አምላክን መጽነሷን ፤ እመብርሃን አውቃ
ዘመዷን ኤልሳቤጥ ፤ ሄዳ መጠየቋ
እንደምን አይገርም ።
ከሴቶች መካከል ፤ ከፃድቃኑም ጎራ
አንቺ ብርክት ነሽ ፤ ተብላ ሳትኮራ
ወደ ተራራማው ፤ የይሁዳ ከተማ
ፈጥና መነሳቷ ፤ ጥቂት ሳታቅማማ
እንደምን አይገርም ።
ታላቅ የምስራች ፤ ሆኖ የእሷ ጉዳይ
ከታናሹ ደስታ ፤ ልትሆን ተካፋይ
አማናዊ ፀሀይ ፤ በማህፀኗ ይዛ
የኮከቡን እናት ፤ ልትጎበኝ መጓዟ
እንደምን አይገርም ።
የንጉሦች ንጉስ ፤ ፈጣሪን ጸንሳ
ትእቢት ሳይኖርባት ፤ ዘመድ ማስታወሷ
ክብሯን ሳትነፃፅር ፤ ከኤልሳቤጥ ጋራ
አጃቢ ሳትሻ ፤ መንገድ መጀመሯ
እንደምን አይገርም።

https://www.tg-me.com/Mgetem
https://www.tg-me.com/Mgetem
https://www.tg-me.com/Mgetem
አቤል ታደለ
ለአስተያየት :
@abeltadele
ንሸጣ፦የብርሃን እናት (ዲያቆን ሄኖክ ሃይሌ)
78🥰11👍6👏5😢1
10🥰2👏2
እርሱ ሚካኤል ነው
@Mgetem

ወደ ፅድቅ መንገድ ፤ እኛን እየመራ
እግዜር እንዳይቆርጠን ፤ ፍሬ ሳናፈራ
እርሱ ሚካኤል ነው ፤ የመላእክት አለቃ
ባማላጅነቱ ፤ የሆነን ጠበቃ።
ለባሕራን የሞቱን ፤ ደብዳቤ የቀየረ
ሰይጣን ዳቢሎስን ፤ በሲኦል ያሰረ
እስራኤልን ከግብፅ ፤ መርቶ ያሻገረ
እርሱ ሚካኤል ነው ፤ ሀያል የከበረ ።
የሰናክሬም ጦሮች ፤ ቢሆኑ ብዙሃን
ሳይዋጋ የፈጃቸው ፤ በሰይፉ ብርሃን
አዛኝና የውሃ ፤ ከጥፋት ታዳጊ
እርሱ ሚካኤል ነው ፤ የእኛ አሳዳጊ ።

አቤል ታደለ

https://www.tg-me.com/Mgetem
https://www.tg-me.com/Mgetem
https://www.tg-me.com/Mgetem

ለአስተያየት : @abeltadele
130🥰13👍5👏4
2025/07/09 12:15:17
Back to Top
HTML Embed Code: