Telegram Web Link
"ሐዋርያቲሁ ከበበ እግረ አርዳኢሁ ሐፀበ ኮኖሙ አበ ወእመ ወመሀሮሙ ጥበበ
👉ትርጉም
ሐዋርያቱን ሾመ የደቀ መዛሙርቱ እግር አጠበ አባትና እናት ሆናቸው ጥበብንም አስተማራቸው"
📚ሊቁ ቅዱስ ያሬድ

እንኳን ለጸሎት ሐሙስ ወይም ለአዲስ ኪዳን ሐሙስ በሠላም በጤና አደረሳችሁ፤ አደረሰን
@Mgetem
@Mgetem
"ይህች ቤተክርስቲያን
ክርስቶስን ከቶ አታውቀውም" በሉ
ግድ የለም ለቃሉ !
ግን ድምጽ ቀንሱ !
የጌታን መከራ ሕማሙን አስባ
ስግድት ላይ ናትና ልጆቿን ሰብስባ
ግድ የለም አንቋሿት
ግን አትረብሿት !!

ዲ/ን ሔኖክ ኃይሌ
_____________
ፎቶ_ አሰላ ደ/መ/መ/ዓ/ካቴድራል
@Mgetem
@Mgetem
👍1
#አቤቱ_ይቅር_በለኝ 😢
@Mgetem

የዕንባ ጅረት ባይታይ በጉኝጭ በደረት ባይኖር ማቅ መልበስ ማንባት ቢሳን በአንደበት

ከል መነስነስ ቢቀር ቅይጥ ቢሆን ህሊና
መድረስ ባንችል ከዚያ ጥግ ሕይወት አዙሪት ሆና
ቅርብ ማደራችን እንደሁ አይቀር ከዚህ
ዕጣ ፈንታችን ነውና

እንደ ኖኅ ዘመን እንደጠፉ በማይ ንፍር
ተለካክፈን በሥጋዊ ጥምር ፍቅር

ቀልጠን እንዳንቀር እንደ ሰዶም ድኝ ገሞራ
ፋታ በሚያሳጣን ስጋዊ ምንዘራ

እስከ መቼ ይሆን እኔስ በውስጤ ማልቀሴ
ጥርኝ አልባ ሕይወት ማጣቴ ለነፍሴ

ስንት ዘመን ሙሉ ከኔው እየዋሉ ጥልና ክርክር
የናኙ በውሰጤ ፍቅር አልባ ምስጢር
ተጣብቀው ’ሚኖሩ ከጉያዬ ሥር

ከኔው ጋር ሲከርሙ ነፍሴን እያደሙ
ቁስለቱ ቢሰማኝ ውስጤን ቢያሳምሙ

ካቅሜ በላይ ስበላ
ያገኘሁ መስሎኝ መጋቢ አባ መላ

ሆዴን ሳጠረቃ ሥጋዬን ሳደልብ
ሆድ አምላኩ ሆኜ ሳብል ስስገበገብ

ነፍሴን ጥግ ጥዬ ከታዛው ባሻገር
ሕይወት ይጥም መስሎኝ እንዲያው ስውተረተር

ያ’ለም ሕይወት ሳንካው መዘዙ
መጨነቅ መተከዙ

ከውስጤ ገብቶ እኔነቴን ቢያምስ
ከነፍሴ ጥጋት መንጭቶ የውስጤ ረቂቁ መንፈስ

አነቃኝ አናጥቦ ከጠሊቁ እንቅልፍ
ሊመልሰኝ በንስሐ ከውድቀት አፋፍ

አነባ ውስጤ የንስሐ እንባ
ቢያቀል ሸክሜን ንዶ ለላይኛው አምባ

ምን ገዶኝ ማንባቱ ቢመነጭ ከልቤ
የጌታዬን ማዕድ እንዳልቀር ተርቤ
በንስሐ ጠበል ኃጢአቴን አጥቤ
መኖርን እሻለሁ ትሩፋት ደርቤ
♻️♻️♻️♻️♻️♻️♻️♻️♻️♻️♻️♻️
@Mgetem
@Mgetem
@Mgetem
👍3
#ክርስቶስ ተነሳ
@Mgetem

ድውይ በፈወሰ ሙታንን ባነሳ
ይሰቀል ተባለ ውለታው ተረሳ።
ክርስቶስ ይሰቀል በርባንን ልቀቀው
ብሎ ተናገረ ሀጢያት የናፈቀው።
የይሁዳ ክህደት ዓይኑን ያፈጠጠ
ለሰላሳ ብር ሲል አምላኩን የሸጠ።
ቸሩ መድሐኒዓለም ብዙ ተገረፈ
መከራው ቢጠናም በትዕግስት አለፈ።
እየተጋገዙ ጨርሶ እስኪቀር አጥንቱ
የአዳም ዘርን ሁሉ ከሲኦል ለማውጣት
ፈጣሪ በፍጡር ተቀበለ ቅጣት።
ተሰቀለ ብላ ስታዝን እናቱ
ገድለነዋል ብለው አህዛብ ሲዘብቱ
አዳኙን ቢገድሉት ያለ አንዳች አበሳ
ሞትን ድል አድርጎ ክርስቶስ ተነሳ።
__________________________
እንኳን ለብርሃነ ትንሣኤው በሰላም አደረሳችሁ
__________________________
@Mgetem
@Mgetem
@Mgetem
👍4
Forwarded from Daregot Media
​የዳረጎት ዘተዋሕዶ ዲጂታል መፅሔት

መልካም ራት።
#ማህሌት
@Mgetem

ፈልቀሽ የተገኘሽ ከአፈ መላእክት፣
ያሬድ የተማረሽ ከላይ ከሰማያት፣
እንከን የሌለብሽ አዲሷ ምስጋና።
ምስጢርሽ ሲገለጥ በአስደናቂ ዜማ፣
ከሰማይ መንጭተሽ በምድር ሲሰማ፣
በቃናሽ መሰጠሽ ልቡናን በመክፈት፣
ማርከሽ ትወስጃለሽ ነፍስን ወደ ገነት።
የፍቅር መግለጫ የሕይወታችን አርማ፣
ጣእምሽ ልዩ ነው ሲገለጥ በዜማ።
የአድባራቱ ሁሉ ቋንቋና ድምጻቸው፣
የካህናት ቅኔ ሰምና ወርቃቸው፣
ለህዝብ ኢትዮጵያ የነፍስ ምግባቸው፣
ማኅሌት እኮነሽ ጸጋና ሃብታቸው።

____________________________
@Mgetem
@Mgetem
@Menfesawi_getem_bot
#ስም_ብቻ_ምን_ሊጠቅመኝ
@Mgetem

መጠሪያ ብቻ ከሆነኝ -- እኔ ክርስቲያን መባሌ
በግብሬ ካላሳየሁት -- ካልተዋሐደ ከአካሌ
በጨለማ መቅረዝ ሆናኝ-- እግሬን ከእንቅፋት ካላዳነ
ጌታዬ በኔ ካልከበረ -- ስሙ በኔ ካልገነነ
ሻማ ሆኜ ካላበራሁ -- ጨለማ ለዋጠው ወገኔ
ስሙ ብቻ ምን ሊጠቅመኝ -- ምን ሊሠራልኝ ነው ለኔ?
በአርባ ቀኔ ስጠመቅ -- ክርስቲያን ተብዬ ልጠራ
በእምነት ዳብሬ እንዳድግ -- መልካም ፍሬን እንዳፈራ
ሥነምግባር መጠመቄን-- እንዲያሳየኝ አጉልቶ
ክርስትናዬን እንዲናገር -- በደረስኩበት ሁሉ ገበቶ
የተቀበልኩት ልጅነት -- በእኔነቴ ዙርያ አብርቶ
ለዚህ ነበረ ምክንያቱ -- የጥምቀት ክርስቲያን መሆኔ
በጸበሉ ነጽቼ -- ልጁ የተባልኩ እኔ
በአነጋገር በሥራዬ -- ክርስትናዬን ካላሳየሁ
ጌታዬ በሰጠኝ መክሊት -- አትርፌበት ካልተገኘሁ
እንደተዘናጋሁ ካለቀ -- ከተጨረሰ ዘመኔ
ክርስቲያን መባሌ ምን ሊረባኝ -- ምን ሊጠቅመኝ ነው ለእኔ?


ከሳህሉ ወንድሙ

___________________________
@Mgetem
@Mgetem
@Menfesawi_getem_bot
👍2
#አዎ_እመቤቴ_ነሽ
@Mgetem

ምን ነው ዛሬ ሊቁ ቅዱስ ያሬድን በሆንኩ፣
ኤፍሬምንም በተካሁ ሕርያቆስን በመሰልኩ፣
ገብርኤልን በሆንኩኝ ሰላም ለኪን በዘመርኩ።
ንዒ ንዒ ባልኩሽ ቁሜ አባ ጊዮርጊስን ተክቼ፣
ሰቆቃሽንም በጻፍኩ ጽጌ ድንግልን ሰምቼ።
አንድም በራዕይ ሆኖ ወይንም ሌሊት በህልሜ፣
ከፊትሽ ላይ ሰግጄ እመቤቴ ባልኩሽ ቁሜ።

አዎ አመቤቴ ነሽ.........!!!!

አባ ጊዮርጊስን አልሁን የያሬድም ይቅርብኝ፣
አባ ጽጌ ድንግልን አልሆን ኤፍሬምንም አታሳይኝ፣
ሕርያቆስን ሁኜ ባልቀኝም ቅዳሴ፣
#አመቤቴ ልበልሽ በምችለው በራሴ።

አዎ እመቤቴ ነሽ.........!!!

ንግስት አለሽ ዳዊት ቀድሞ፣
ሙሽራ አለሽ ልጁ ቆሞ፣
የተነበየልሽ ነቢዩ በትንቢት እንቅልፍ አልሞ፣
የታደሰብሽ ስምዖን የበኩር ልጂሽን ስሞ።
ድንግልም እናትም ሆነሽ የረቀቀብሽ ምስጢሩ፣
ሰማይ መሬትን ሆነሽ የልዑል አምላክ ሀገሩ፣
አሁን ምንድን ነው ነውሩ ስለ ቅድስናሽ መንገሩ።
ስለ ማርያም ማውራቱ ስለ ጽዮን ማስተማሩ?

አዎ እመቤቴ ነሽ..........!!!

ድምጽሽን የሠማሁት ከእናቴ ማህጸን ስወጣ፣
ሀኪም ቤት ሳይኖር ቀድሞ አምቡላስም ሳይመጣ፣
እኔ ለመውለድ በምጥ ስትጨናነቅ እናቴ፣
ጎረቤቶቹ ቁመው እያሉ ነበር " #እመቤቴ "!
የሰማሁትን ቀድሜ እኔም እላለሁ እንደናቴ
ይህን ታላቅ ስም እንቁዕ የሚባለውን " #እመቤቴ !"

አዎ እመቤቴ ነሽ..........!!!

አቅሙ ኑሮኝ ባልደርስም አዲስ ቅኔና ዜማ፣
ባልሰማቼውም ምስጋናሽን መላእክቱንም ከራማ፣
የደረሱትን አባቶቼ የሚገባውን ከአንጄቴ፣
" #ሰአሊ_ለነ "ልበልሽ ፍቀጂልኝ እመቤቴ!!!

#ሰዓሊ_ለነ_ቅድስት ይልሻል ተማሪ፣
አንቺ አደለሽም ወይ የአይነስውር መሪ!

@Mgetem
@Mgetem
👍2
#የቀበሮ_ፀሎት
(ታገል ሰይፉ)
@Mgetem
------
እባክህ አምላኬ- ብትሬን ቀባና
እኔም ልወዝወዘው-የሙሴን ጎዳና
ያላንዳች ፍርሃት-ያለምንም ችግር
ባህሩን ከፍዬ- ህዝቤን እንዳሻግር፡፡
*
አቤት የኔ ጌታ ይህም አያረካም
በቃልህ ታምኜ -ከሆንኩልህ መልካም
ለእኔም ፍቀድልኝ-ያብራምን ምልክት
ከምድር አሸዋ-ዘሬ እንዲበረክት፡፡
*
አቤቱ ምን ልሁን-ይህም አልጠቀመኝ
እስቲ እንደ ዮናስ-ህዝብ ፊት አቁመኝ
*
ትንቢቴን ሰምቶልኝ-ሀገር ይተራመስ
ሰው እህል ይጡም-ከብቱም ሳር አይቅመስ፡፡
ይህም አያረካም-ይልቅ እንደዳዊት
አንተን በሚፈራ-ብዙ ሺህ ሠራዊት
ዙፋኔ ተከቦ-በደስታ እንዳመልክህ
የዚህን ሰው ኮከብ -አውጣልኝ እባክህ
*
አደራህን ታዲያ- ጭንቅ አትወድም ነፍሴ
ልመናዬን ሰምተህ-ካደረግከኝ ሙሴ
መከራውን ማረኝ-ያርባ ዓመት ስደቱን
በሲና በረሃ-መራብ መጠማቱን፡፡
*
ነቢዩ ዮናስን -አርገህም ስትፈጥረኝ
የባህሩን ፍዳ- ያሳውን ሆድ ማረኝ፡፡
*
አብረሃምን ሆኜም-በደስታ ሳመልክህ
ልጅህን እረደው-አትበለኝ እባክህ፡፡
***
የዲዊትም ኮከብ-በኔ ላይ ሲወጣ
እባክህ አምላኬ -ጎልያድ አይምጣ፡፡
@Mgetem
@Mgetem
@Menfesawi_getem_bot
👍51
Forwarded from ስንክሳር (Bereket Gudisa)
'''' ኑ ! ቆርቆሮ እንግዛላቸው !”
••••••••••••••••••••••••••••••••
-------- መጪው ክረምት ነው !!!
በጉምዝ አካባቢ የተሰሩ አብያተ ክርስቲያናትን ዝናብ ሳይገባ ቆርቆሮ የማድረግ ዘመቻ ኑ የተዋህዶ ልጆች እንድረስላቸው ።
#10_ለቆርቆሮ
በሞተር እየተመላለሰ ጉምዞችን የሚያስተምረው ወንድማችን ዲ/ን ቶማስ ከቤታቸው ካሉበት ድረስ በመሄድ የአካባቢው ኗሪዎችን ሰብስቦ ያስተምራቸዋል ዝናብ ሳይመጣ
በቅርቡ ቆርቆሮ እናድርግላቸው የተዋህዶ ልጆች እየተማፀኑ ነውና የተዋህዶ ልጆች በሙሉ እንደ ከዚህ ቀደሙ ሁሉ ልንረባረብና አለንላችሁ ልንላቸው ይገባል ። ገንዘብ ያለህ በገንዘብህ፣ ጉልበት ያለህ በጉልበትህ፣ ይህችን ምስኪን ቤተክርስትያን እንርዳት የተዋህዶን መቅደስ በቆርቆሮ እናሰራት ።
የሚዘረጉ እጆች ካሉ ገና ብዙ የሚሠሩ አሉ። ሐዋርያው አለ። ገንዘብ ግን ይጎድላል።

ይህንን ቤተ ክርስቲያን በተሻለ መልኩ ለመሥራትም ሆነ ሌሎች አገልግሎቶችን
ለማጠናከር እገዛችን ይፈለጋል። እናም አለን እንበላቸው።
በዲያቆን ቶማስ ጎሹ መሪነት ከ66,000 በላይ አዲስ ክርስቲያኖችን አጥምቀዋል።
አሁንም የአዳዲስ ተጠማቂያን እና አዳዲስ ቤተ ክርስቲያን የመስራት ስራ ተጠናክሮ ቀጥሏል ስለሆነም በአካባቢው ላይ ያሉትን ማኅበረሰብ ክረምት ከመግባቱ በፊት ከታች
በምስሉ ላይ የተጀመረውን የቤተ ክርስቲያን ስራ ቆርቆሮ እንድናለብስላቸው ሲሉ ጠይቀዋል።
@senkesar
Forwarded from ስንክሳር (Bereket Gudisa)
Forwarded from ስንክሳር (Bereket Gudisa)
Forwarded from ስንክሳር (Bereket Gudisa) via @like
10 ብር ብቻ.....ለቆርቆሮ! ይስማማሉ!
1
" አዕሩግ አመ በከዩ ብካየ
ረከቡ ወለተ ዘታሥተሰሪ ጌጋየ
ለወንጌላውያን ኩልነ ዘኮነተነ ምጉያየ
ኢያቄም ወሀና ወለዱ ሰማየ
ሰማዮሙኒ አሥረቀት ፀሐየ
ምስራቀ ምስራቃት ሙፃዕ ፀሐይ
እግዝእትየ ዘመና ሙዳይ
ተወልደት ዮም ዳግሚት ሰማይ "
አረጋውያኑ ― በእጅጉ ቢያለቅሱ፣
በደል በምታርቅ ― በሴት ልጅ ተካሱ፤
ለወንጌልም ልጆች ― መሸሻቸው ካለም ፣
ሰማይን ወለዱ ― ሃናና ኢያቄም ፣
ሰማይዋም (ሰማዯም) ፀሐይን ― አውጥታለች ለዓለም፤
የምሥራቃት ምሥራቅ ― መውጫዋ ለፀሐይ ፣
የፍጥረት እመቤት ― የመናዋ ሙዳይ ፣
ዛሬ ተወለደች ― ዳግማዊቷ ሰማይ ።
👍21
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
👍3
#እድሜ_ለንስሃ
@Mgetem

ያማረ ያጌጠ አዲስ ቤት ሰርቼ
እስክመለስ ድረስ አደራ ሰጥቼ
ሰፈሩን መንደሩን ቀየውንም ትቼ
ብዙ ዓመታትን ኖሬ ከዛ ሀገር ወጥቼ
አሁን ተመልሼ ስጎበኘው ቤቴን
አይኔን ማመን አቅቶኝ በእጄ ይዤ አፌን
እንዲጠብቅልኝ አደራ ይልኩት ሰው
እሳት ሲያነድበት ሲያጨስበት ኖሮ
ጣሪያውም ጠልሽቶ ግርግዳውም ጦቅሮ
ተረጋግጦ ሳየው ውስጡ ተሰባብሮ
እራሴን ታዘብኩት አዝኜ ከውስጤ
ድሮም!በሰው ተማምኜ ትቼው መቀመጤ
እንግዲ ፍረዱኝ!እስክመለስ ድረስ
ያደፈውን ዘመን በጊዜው እስካድስ
ጣርያ ግርግዳውን ወለሉን አፅደቶ
ያፈራርሰውን ካልጠበቀኝ ሰርቶ
እፋረደዋለው ህግ በፊት አቁሜ
ግን እስከዛው ድረስ
ሰጥቼዋለሁኝ ጥቂት ቀሪ እድሜ።
__________________________
@Mgetem
@Mgetem
@Menfesawi_getem_bot
👍3
ተናፋቂው ግንቦት 11 እየደረሰ ነው!

መቼም “ግንቦት 11 ደግሞ ምን አለ?” ብለው እንደማይጠይቁ እምነታችን ነው!

ባሕረ ጥበባት ቅዱስ ያሬድ - ብርሃናችን እና ጌጣችን ሊቁ ቅዱስ ያሬድ የተሠወረበት ዕለት እኮ ነው፡፡

አምላካችንን - ምክንያተ ድኂን እመቤታችንን - ቅዱሳን መላዕክትን - የምንወዳቸውን ቅዱሳንን - የምንጠለልባት ቤተክርስቲያንን የምናመሰግነው እኮ እርሱ ባቀበለን ዜማ ነው፡፡ መቅረት አይቻልም!

ደግሞ ዕለቱ እሑድ ቀን ነው፡፡ ከአኹኑ ቀጠሮዎን ከወዳጆችዎ ጋር በደብረ ይባቤ ቅዱስ ያሬድ ያድርጉ!

በቡድን እና በኅብረት ከዋዜማው ጀምሮ በማኅሌቱ ለመሳተፍ ለሚመጡ ልዩ አቀባበል እናደርጋለን፡፡

ሊቁ አባታችን ዓለም ዛሬ ላይ የሚያደንቃቸውን ዓለማውያን ሞዛርት እና ቬትሆቨን በ1250 ዓመታት ይቀድማቸዋል፡፡ ዓለም በነዚኽ ሰዎች ቤተመጻሕፍት - አደባባይ - መንገድ እና ትምህርት ቤት ሰይማ እስካሁን እንደታላቅ ቅርስ ስትዘክር አለች፡፡

ቅዱስ ያሬድ ግን ሰማያዊውን የመላእክት እንጀራ አሻግሮልን ልናመሰግነው አልቻልንም፡፡ በአዲስ አበባ እንኳን በስሙ መታሰቢያ ያለው ቤተክርስቲያን አንድ ብቻ ነው፡፡

መላዋ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተክርስቲያን በቅዱስ ያሬድ ማኅሌት አምላኳን የምታመሰግን ናት፡፡ ጌጧ ለኾነው ለቅዱስ ያሬድ ግን በዓመታዊ መታሰቢያው ዕለት እንኳን አስባው ማኅሌት አትቆምለትም፡፡

በሌላው ዓለም ቢኾን ስንት ነገር በስሙ ተከናውኖ እና ተሰይሞ ነበር፡፡ አይ ቅዱስ ያሬድ! የአንተን ፈለግ ተከትለን ሰማያዊውን ሥራ መሥራት ቀርቶ አምላክ የመረጠህን አንተን እንኳን በወጉ ማክበር አልቻልንም፡፡

ቅዱስ ኤፍሬምን ከሶርያ - አባ ሕርያቆስን ከብህንሳ አምጥታ ምስጋናዬ በቅዱስ ያሬድ ዜማ ይኹንልኝ ያለችኽ እመ አምላክ በእኛ “የበሉበትን ወጭት ሰባሪነት” እንዴት ታዝንብን ይኾን!?

ለኢትዮጵያ እኮ ነፍሷ ነህ ቅዱስ ያሬድ - ጣዕሟ እኮ ነህ - አላወቀችኽም እንጂ!
____________________
አድራሻ፡ ጎተራ ከአጎና ሲኒማ ወደ መስቀል ፍላወር በሚወስደው መንገድ
#Share #share
#ይህን_እናውቃለን
@Mgetem

ዳግም ለመወለድ እንደማትመጣ
ደግሞም እናምናለን!
ስለ ኖኅ ኪዳንህ ምድርን በእሳት እንደማትቀጣ
በቃ እንጨፍራለን!
እንሰየጥናለን!ለመጨረሻ ፍርድ ዳግም እስክትመጣ።
አሁን በዚህ ሰዓት!?
ልምጣ ብትል በየት!?
መልካም ሥራን ሳይሆን ክፋትን አጥብቀን
የምህረት መንገድህን ዘግተናል አርቀን
በትዕቢት አንደበት!
ንስሐ አያሻንም ጻድቃን ነን ብለናል
አሁን በግብራችን ሰይጣንን መስለናል።
ዳግም ብትመጣም
ባስቀመጥኸን ምድር ከቶ አታገኘንም
መናፍስት ሆነናል ሥጋ እንኳን የለንም
አንተ ፍቅር ስቦህ የለበስኽው ሥጋ
በምን እንደሁ እንጃ ተወስዷል ከእኛ ጋ
አሁን በተለምዶ ሥጋ የምንለው
አጥንት የሸፈነ <የኃጢአት ክምር> ነው።
∅∅∅∅∅∅∅∅∅∅∅∅∅∅
@Mgetem
@Mgetem
@Menfesawi_getem_bot
👍2
#ከሳሽ_ዕድፉን_ሳያይ
@Mgetem
 
ስታመነዝር አገኘናት፣
ብለው አካልበዋት፣
ከጌታ ፊት እያቻኮሉ፣
ከእግሩ ሥር አምጥተዋት ጣሉ፡፡

ምን ትላለህ ? ስለዚች ሴት፣
ይዘናታል በማመንዘር ኃጢአት፣
ሙሴ እንደው በሕጉ፣
ብሎናል ወግራችሁ ግደሉ፣
አንተስ ምን ትላለህ ?
ይሰማ እስኪ ፍርድህ … ?

ይላሉ ከሳሾች ….
ወንዱን አስመልጠው ፣ ሴቷን አሳዳጆች፤
እውነት አንሻፋፊ ፣ ግማሽ ምስክሮች፤

ኢየሱስ መለሰ ….
ጐንበስ ብሎ ከምድር ፣ አንዳች እየጻፈ፤
ከʻናንተ መካከል ፣ ነውሯ ያላገኘው፤
ድንጋይን ከሯሷ ፣ አሁኑ ይጫነው፤
ብሎ ሳያበቃ ፣ ቀና ሲል ካለበት፤
ከʻርሷ በቀር የለም ፣ ከተከሳሿ ሴት ፤
ለካስ ሁሉም ጥሎ ፣ ከዚያ ሥፍራ የጠፋው፤
ከʻርሷ ጋር ተጋድሞ ፣ ዕድፉን ባያየው ነው፡፡

ያመነች ግን እርሷ ፣ ተከናወነላት ፤

መንገዷን ቀየረች ፣ ከሞት ወደ ሕይወት፡፡ 🙏
__________________________
@Mgetem
@Mgetem
@Menfesawi_getem_bot
👍31
2025/07/09 20:43:16
Back to Top
HTML Embed Code: