Telegram Web Link
ሕልም ... ያለው
ሕልምም ያየው
ከተባለ ባለ ሕልማም
ከጥሪው ነው እንጅ
ከግብሩ አይሟላም !
ሕልም ታይቶት የመራ
በሕልም እንደመራ
ከተባለ መሪ ...
ችግር ይታየናል ከዚህ የቃል ጥሪ!
ስለዚህ ይወጠን ...
ስለዚህ ይታሰስ...
ከዚህኛው መዝገብ እስከዚያኛው ድረስ
ፈልጉ.. . ፈልጉ ...
ይፈለግ እንጅ ቃል ?
ቀለም ቆጥሯል ብለን አዋቂ ነው ያልነው
ለጠንቋይ ይሆናል።

(ሚካኤል.አ)
የቤት አህያና የሜዳ አህያ
ሲኖሩ ሲኖሩ ...
መንገድ ሲያሳልጡ
እቃ ከጀርባቸው ሸክፈው ሲያኖሩ፤
ሰለቸና ወጣ የሜዳ አህያ
አህያ ግን ቀረ ከቤት ከገበያ።
እንዲህ በአንዳንድ ቀን
ሲበዛበት አደን ...
ሳሩ እሳት ገብቶት ሲኖር በሰቀቀን
ባልወጣሁ ምናለ?
ብሎ እንባ ይዘራል የሜዳ አህያ
አያውቅም እንዳለ ...
ስሙን የሚያወሳ መንገድ መሻገሪያ።
የሚል አለ ተረት ...
የአንዱ መለየት ነው
የሌላው ነፃነት ፤
ስንት እግር ተራምዷል
በእንባ ቀን ወ'ቶለት።

(ሚካኤል.አ)
በማይፀፅት ትናንት ፡ በማይናፍቅ ነገ
መካከል ላይ ፍቅርሽ ፡ ስለተሰነገ፣
አልማትር ወደፊት ፡ አልዞር ወደኋላ
«አ...ሁን!» ነኝ ... «አ...ሁኝ!» ነሽ ፡ ከእንግዲህ በኋላ።
Red 8
መልከ ቀና አድርገኝ
ህይወቴ ቢቀለኝ.. .
አውለኝ በክብር
ቀባኝ ሞገስ ቅባት
ቀኖቼ ላይ ልንገስ
በሌሎች ፍርሀት።
ስጠኝ የመሪ ድምፅ
አጥር የሚሻገር...
መንገዴ እንዲሳለጥ
እንዲሆን ገር በገር ።
አልያ አልገፋትም...
ይህችን ስንኩል ዕድሜ
ለአይን አስቀይሜ፥
ቀልዬ ያለ ሞገስ...
ሰው ሰሚ ሲያጣ ነው
ከሞት ደጅ የሚደርስ !!

(ሚካኤል.አ)
ጭንቅላታችሁ እንደ ማግኔት ነው

➡️ በረከትን ስታስቡ በረከት ይመጣል።

➡️ ችግሮችን ካሰባችሁ ችግሮችን ትስባላችሁ።

➡️ ሁልጊዜም ጥሩ ነገሮች በውስጣችሁ አሳድጉ።

➡️ በአስተሳሰባችሁ በጎና ውጤታማነትን አስቡ፡፡

➡️ በሂደት ወዳሰብነውና ወደተመኘነው ነገር እንሄዳለን።

➡️ ጨለምተኝነትን ካሳደግን ጨለምተኛ እንሆናለን...

➡️ ተስፋንና ውጤታማነትን በውስጣችን ካለማመድን ስኬታማ እንሆናለን፡፡
ከአዲስ አድማስ ገፅ
ጊዜ እንዳለኝ እያሰብኩ ነበር — እንደምኖር።

በመጻሕፍት መደርደሪያዬ እኔን መጠበቅ ያደከማቸው ያልተነበቡ መጻሕፍት ተገጥግጠዋል።

አንድ ቀን እንደማነባቸው ተስፋ ሳደርግ ምጽዓት ደረሰ —ሀገሬ። በሲዖል ውስጥ መጽሐፍ ማንበብ አይቻልም። አንደኛ ሀገሩ የእሳት ነው። በእሳት ሀገር ወረቀት ቀለም ይዞ አይቆይም። ይነዳል፥ አመድ ይሆናል። ብዙ ጩኸት አለ —ሰቆቃ። እና አይመችም። ዙሪያው ገደል ነው። ልብ ዝቅ ያደርጋል።

ቀን በቀን መጻሕፍቴን እየተሰናበትኩ ነበር። ምን ትርጉም አለው? ሳልፈልግ አእምሮዬ እንደተረበሸ ከተማ ሐሳብ ይጎሎጉላል። በሥነ ሥርዓት ላጠነጥን እሞክራለሁ —መሥመር ላስይዝ። ግን አልችልም ይሳከርብኛል። አንጎሌ፥ ሰውነቴ ይሰንፋል።

የምናደርገው ነገር ትርጉም መስጠት ያቆመበት በሚመስልበት ጊዜ ላይ ነን። እዚህ ሀገር ልጅ እንወልዳለን። የምናወርሰው ሀገር ግን ሲዖል ነው። ምሽቶች ባሎቻቸው ድንገት በወጡበት ይቀራሉ። ይታፈናሉ፥ ይታገታሉ። ልጆች ያልጠገቡትን፥ በውል ያለዩትን አባቶቻቸውን ባልጠበቁት ቅጽበት ይሰናበታሉ። ለሀገራቸው ውለታ የዋሉ ዋርካ ሰዎች በልጅ እግሮች ይገደላሉ። ደም ይፈሳል —በየመንገዱ፥ በየጫካው። አድባራት አንድ ባንድ ይፈርሳሉ። ማንም ምንም ማምጣት የሚችል አይመስልም። ድንገት ኢምንትነት እንዲሰማህ ትሆናለህ።

ሞት እየጠራህ ትማራለህ? ሞት እያነፈነፈህ ታከማቻለህ? በደጅህ ሞት እያደባ ታገባለህ? ሀገር እየተቃጠለ ትሰርጋለህ? ቆንጆ ቆንጆ ልጆች የጥይት እራት እንዲሆኑ ትወልዳለህ? መሣሪያ የታጠቀ ወንበዴ ቤትህን እየሠረሠረ ታንቀላፋለህ? ዳሩ ብትነቃስ ምን ታደርጋለህ? የዓለም ምጽዓት አንተ ጋር እስከሚደርስ ብትተኛ አይከፋም፥ ብትማር፥ ብትቆጥብ፥ ብታገባ፥ ብትወልድ።

ሀገሩ የባለጌ ነው። ማን ጌታ እንደሆነ አይታወቅም። በመንገድ ስታልፍ ረግጦህ የገላመጥከው ሰው ዘመደ ብዙ ነው። የጦር መሣሪያ አለው። ባታውቀውም የጎበዝ አለቃ ነው። ትንሽ መንግሥት ነው። ሕይወትህን ከአፈር ይደባልቀዋል። ያየህ እስከማይገኝ ድረስ ድራሽህ ይጠፋል። ወዝህ ያስቀናው ሰው ዳር ሊያስይዝህ ይችላል።

ሀገርህ ከየት እስከየት እንደሆነ አታውቅም። እግርህ ከቤት ወጣ እንዳለ የጠላት ሀገር ነህ። በካርታ ባይከለልም የተበጀ ድምበር አለ። ድንገት ትጨመደዳለህ፥ እጅ ትሰጣለህ። ብትማረክም ትገደላለህ። ከቀን ውሎህ ተርፈህ፥ በሰላም ወጥተህ ከገባህ እድለኛ ነህ። ከሄድክበት ስትመለስ ቤትህን በገነባህበት ስፍራ ላታገኘው ትችላለህ። ማንንም መርዳት አትችልም። ግፍና መከራ ተንከባሎ በሁሉም ቤት ይደርሳል። እስከዚያው ግን ተራው ያንተ ከሆነ ያንተ ነው። ትከሻህን ማስፋት፥ መቻል፥ መቀበል ይጠበቅብሃል። እውነት አይመስልም አይደል? ትላንት በእቅፍህ የነበረ ሰው እንደወጣ ሲቀር? ደብዛው ሲጠፋ?? ግን ይህ የብቻህ እውነት ነው። ይህ የብቻህ ሕመም ነው —ጽና።

እ. . .

ሎሬት ጸጋዬ ገብረ መድኅን በሌላ አውድ የጻፈው አንድ ግጥም አለ። ያለ ዐውዱ እዚህ ጋር እንድጠቀመው ይፈቀድልኝ፦

“...ተገልለህ ርቀህ
እውነት ይተዉኛል ብለህ
እንዴት ተስፋ ታደርጋለህ?! . . . .
ተስፋ አድርገህስ ምን ልትሆን ፡ ወይስ ተስፋው ምን ሊሆንህ ?
እንቅልፍ እንጂ እሚያስወስድህ።”
Esubalew Nigussie
ብቸኝነት (በድሉ ዋቅጅራ)

እልፍኝህ እንዳʽብርሀም ቤት፣
አደባባይህ እንደጥምቀት፤
የሰው አሸን ቢወረው፣ ጠጠር መጣያ ቢገድም፤
ለመሀላህ ካስማ ʽሚሆን፣ ሲያነቅፍህ የምʽጠራው ስም፤
ከልቦናህ ሲነጥፍ፣ አንደበትህን ሲያንቀው፤
ብቻህን ነህ፣ ያኔ እወቀው፡፡

-----------
አልሰጋም ይሄን ዱር
አልርድም ለጥሻው ..
ለፅልመት ጭለማው
ለመናፍስት ውጊያው
ሰው መሆኔን ብቻ
እኔ የምፈራው !!
፤፤፤
(ሚካኤል. አ)
ይገርማል!
ከፀሀይዋ ጋር ውል አላችሁ ልበል ?
መምጣትሽን ስታውቅ ፥ ፈክታ ምን አስወጣት ?
ምድርስ ያለወትሮው ፥ እንዲህ ምን አስጌጣት ?
ምንድነው ውላችሁ ከአፀዱ ከነፋስ ?
እንዴት ተሰደሩ እንዲህ በለሆሳስ?
ምንድነው ውላችሁ ከመቅደስ ዝማሬ ?
ምንድነው ሽርክናሽ ከሕይወት ኑባሬ ?
ለምን ሀሴት ዋጠኝ አንቺ ስትመጪ ?
ትናንት እንዳልከፋኝ ከዳሴ ስትወጪ
እንዲያ እንዳልፎከርኩኝ አላይሽም ብዬ
እንዴት ደስ ይለኛል ካለሁ በጤናዬ ?
ወይንስ ወፍፎኛል ....?!
እንደ እብድ አርጎኛል ....
ነገ ለማነባው ደፌን ዘጋግቼ
እቀበልሻለሁ እጆቼን ዘርግቼ ።
-----
የሆንሽ መ'ዳኒታም
እኔም ግን አልረባም!

(ሚካኤል.አ)
አያቴና ፍካሬ እየሱስ
፨ሚኪ ደራሲው፨
ጎዳናው እንደ ወትሮው ሁሉ ግርግሩ ጦፏል። ከክፍለ ሃገር እኔን ጥየቃ የመጣው አያቴ በውዲቷ ሸገር ላይ ተንጣለው የተጎመሩትን ህንጣዎች በ አግራሞት ይማትራል።
'ወቸ ጉድ የኢትዮጲያ ህዝብ ሁላ ለካ አጤ ሃይለ ስላሴን ሆኑአል ' አለኝ በመዳፉ አፉን በአግራሞት ይዞ።
'እንዴት?' አልኩት ትክ ብዬ እያየሁት
'አታይም እንዴ ይህን ሁሉ ክምር ህንጣ ፡ እውነት ግን ይህን የሚገነቡት ለየግላቸው ነው ወይንስ አንድ አውራጃ ህዝብ ተደራጅቶ ነው?'
'እረ ምን በወጣቸው ይደራጃሉ እዚህ ሃገር ሰው የሚደራጀው ወይ ከተመረቀ ወይ ደግሞ ዘይትና ስኳር በመስሪያ ቤት በኩል ገዝተው ሲከፋፈሉ ነው።'
'እሮአ! እና አንድ ሰው ነዋ የ ባቢሎንን ግንብ እየገነባ ያለው?'
'አዎ' አልኩት መመለስ ሰልችቶኝ። እርጅናና ልጅነትን ከሚያመሳስላቸው ነገሮች ውስጥ የሁለቱም ወገኖች ጥያቄ ማብዛት ይመስለኛል።
'ወቸ ጉድ! ስምንተኛው ሺ ባህታዊ ደግሞ ተከተማ ምን ይሰራል?' አለኝ
በአይኔ ባህታዊ ብማትርም እንኳን ባህታዊና አንድ ደና ፓስተርም ያለ አልመስልህ አለኝ፡
ፍካሬ እየሱስ አታነብም እንዴ ልጄ ቃሉ እኮ ቁጭ ብሎ ተጽፎልሃል ፡
ታየኝ እኮ በዚህ ዘመን በ ፍልስምናና በ ሳይንስ የተደናቆረ ህዝብ ፍካሬ እየሱስ ቁጭ ብሎ ሲያነብ፡ አንዳንዴማ የህጻናት ተረት እያነበብክ ያለህ ሁሉ ሊመስልህ ይችላል። በዛን ዘመን የጫካ ጥንቸሎች ከከተማ ይዘልቃሉ ጥንቸሎች ሲል እንስሳቶችን ማለቱ አይደለም መናኒዎችን ማለቱ ነው እንጂ ይለኛል አያቴ በኑሮ ግብ ግብ የደነቆረ ጆሮየ የ አምላክን ቃል ይሰማ መስሎት ምስኪን አያቴ።
'ይቅርታ አርግልኝና ምንም ባህታዊ እየታየኝ አይደለም?!' አልኩት ፈርጠም ብዬ
በሌባ ጣቱ አንድ ሰው ላይ አመላከተኝ፡ ሳቄን መቆጣጠር አልቻልኩም፡ ሰውየው ጋንጃውን ጦዞ
ጸጉሩን አጎድሮ ዋን love የሚል የሱስ ባህታዊ ራስታ ነው።
እኔ እና ፈጣሪ
.
.
ምሬት በከበበኝ...ከአፍላ ቀኔ በአንዱ
ፀሐይ አሽቆልቁላ ፤ ጨልሞኝ መንገዱ
....
አስር ምጣድ ጥጄ ፤ ምኞቴን ሳቦካ
ከሁሉም ስጣደፍ ፤ አንዱም ሳይሳካ
ፈጣሪን እያማሁ ...ቤት እያዘገመኩኝ
የዕለቴን ልሸምት ፤ከሱቅ ደጃፍ ቆምኩኝ
...
ከሱቁ የደረሱ... ቀድመው ከእኔ ኮቴ
አንድ አባትና ልጅ ፤ ቆመዋል ከፊቴ
ልጅየው ያለቅሳል ፤ አባት ግራ ገብቶት
ያየውን አምጣ ነው ..የልጅየው ጸሎት
...
አባት ሳይሰለቸው ፤ ያለውን ይገዛል
ልጅ እያለቀሰ ፤ አዲስ ጣፋጭ ያዛል
ብስኩት.. ቸኮላቱን..ለስላሳ መጠጡን
ጣፋጩን ታቅፎ ክንዱ እንደሞላ
አባት ተናገረው "ያለህ ይበቃሃል የእጅህን ብላ"
...
ልጅ እሪው ቀለጠ
በእጁ የያዘውን መሬት እየጣለ
አባት ይዞት ሄደ አቅፎ እያባበለ
ዞሬ ተመለከትኩ ድምጻቸው ቢርቅም
ከመሬት ላይ ወድቋል
ልጅ ትቶት የሄደው የጣፋጭ ጥርቅም
...
ወድቀው ከነበሩት ጣፋጮች መካከል
አየውት ምኞቴን ካፈር ሲንከባለል
...
ፊቴ ድቅን አለ
ስጥር የዋልኩበት...የባከነ ቀኔ
አዬዬ ልጅነቴ
ሁሉንም ፈልጌ ከአንዱ አለመሆኔ
...
እኔም እንደዛ ልጅ
ይኸው በየዕለቱ ከህይወት ሱቅ ቆሜ
ፈጣሪ ያደለኝን
ስበትን 'ውላለሁ ፤ ምኞት ተሸክሜ
...
ወድቀው ከነበሩት ጣፋጮች መካከል
አየውት ምኞቴን ካፈር ሲንከባለል
...
"እህህህህ" ባለሱቁ ቀሰቀሰኝ
"ምን ልስጥህ?"
አንድ እንጀራ ስጠኝ።
Dawit Nigussu
በመምጣቷ ስስቅ ከንፈሬን ገልጬ
የቀድሞው ሀዘኔን በሀሴት ለውጬ
ይኸው ደላው አሉኝ ...
እነ ባዳ ጆሮ ...ቆመው ከደጃፌ
ማን በነገራቸው እንዳለሁ ወፍፌ !
#መሳቅ ድሎት ከሆን ...
በዚህ በከተማ
ጥርሱን የገለጠ
በምቾት ከ ታማ ...
አላበድናትማ !!

(ሚካኤል.አ)
ኢየሱስ አኩርፎ!

#ሚካኤል አስጨናቂ

።።።።።።።።።።።።።።።

ዮሀንስ ጌታውን

እርቃኑን አጋልጦ ፥ በሸራ ላይ ሳለው

ከነመለመሉ...

ከነ ምናምኑ ፥ እንዲሁ አስቀረው

ኢየሱስ አኩርፎ ፥ ከንፈሮቹን ጣለ

ከአይሁድ ለጥቆ...

ልጄ ዳግም እኔን ፥ ሰቅሎኛል እያለ

አኮረፈ እየሱስ...ከንፈሮቹን ጣለ።

ሠዓሊውም ታድያ...

አይኖቹን አንስቶ ፥ ከአርያም ቃኘው

ጌታዬን.. አምላኬን...

አስኮረፍሁት ብሎ ፥ ሀዘን ቀጠቀጠው።

አፍታም ሳይፈጅበት.. .

ብሩሹን አነሳ ፥ ቀለም በጠበጠ

የጌታውን እርቃን...

ፎጣ አገልድሞ ፥ ስዕሉን አስጌጠ።

በርግጥ ለተመልካች!

በርግጥ ለዳሩ ሰው!

የቀድሞው ስዕሉ ...

የርቃኑ ገፅታ ~ እውነትነት አለው

ደግሞም ለልብ ልጁ

አባቱን አብዝቶ ~ ወዶ ለሚያፈቅረው

አንዳንድ እውነት አለ!

ሀቅታ ቢሆንም ፥ ክብሩን የሚያፈርሰው።

ኢየሱስ ፈገገ!

ኢየሱስ ደስ አለው!

ዮሀንስ ሀፍረቱን ፥ ሸፍኖ ቢስለው።

(ለካስ ያባትነት...

ለካስ የእናትነት...

ክብርን የሚሸርፍ ፥ ቢኖረውም ስ'ተት

ለፍቅር ሲሉ ግን ...

እውነትን ማለፍ ነው ፥ ትክክሉ እውነት።)
#ከጥበብ በላይ !!
(ሚካኤል አስጨናቂ)
።።።።።።።።።።።።።።።
አጃኢብ ያረቢ!
አጃኢብ ያ ጎፍታ !
መገን ያንቺ ውበት
መገን ያንቺ ዝና...
የገላሽ ፍምነት ፥ የቁንጅናሽ ፋና
ደግሞ ተለኮሰ!
ጠዳል ብርሀንሽ ፥ ባገር ተዳረሰ።
ይኸው መጣን ደግሞ!
ጠበብት ተሰብስበን
ብዕር ተሸክመን...
ቀለማት በጥብጠን..
አንደኛው ሊፅፍሽ
ሌላኛው ሊስልሽ
ውበት ቃኙ ብለን ፥ ልናውጅ ለ'ዓለሙ
ነጋሪት ልንጎስም ፥ ስላንቺ ላልሰሙ።
እንችል ይመስል.. .
በብራና ጥራዝ ፥ በቅርፆች ማህደር
ስላንቺ መናገር!
እንችል ይመስል.. .
በሸራ ላይ ስዕል ፥ በሙዚቃ ቃና
መንገር ያንቺን ዝና!
እንዲያው ለሙከራ
እንዲያው ስለደንቡ
እንያዝ ብለን ወጉን
የገጣሚ ልኩን...
ስንኝ ልንቋጥር ፥ ሆሄያት ልንመታ
እንገልፅሽ ይመስል ፥ በቃላት ጋጋታ
እንዲያው ለሙከራ
እንይ ብለን ወጉን
የአዝማሪ ልኩን...
"ቀይ የወደደና ፥ እባብ የነደፈው"
እያልን በዜማ ፥ ውበትሽን ልንገልፀው
እንዲያው ለሙከራ
እንዲያው ስለደንቡ
እንያዝ ብለን ወጉን
የሰዓሊ ልኩን...
በውድር ሸራ ላይ ፥ ስለናታል ልንል
ገፅታሽ በቀለም ፥ ይገለፅ ይመስል
ይኸው መጣን ጠበብት!
ይኸው መጣን ሊቃን !
ሞልቶልን ባንገልፅሽ...
ሞከሯት ለመባል ፥ የፈጠረሽ ያብቃን ።
አሜን 🙏
ብሶት የወለደው ረዘምዛሜ!!😃
(ሚካኤል አስጨናቂ)
ሁሌ ታዋራኛለች...እኔም ለምጃታለሁ...አንድ ቀን ግን እንደልማዷ በኢንቦክስ መጥታ "አድናቂህ ነኝ" አለችኝ..."አድ" ን ተሳስተሽ ጨምረሻት ይሆን? ብዬ መለስኩላት..ከትከት ብላ ሳቀች...ሳቋ በድምፅ ሳይሆን" kkkkk 😂😂" ብለው በሳቅ እንባ በሚረጩ የደላቸው ቀበጥ ስቲከሮች የታጀበ ነበር።
በእውነቱ ከሆነ መሰረት በዛ ምሽት አረቄዬን ፉት እያልኩኝ በምፅፍበት ስሜታዊ ሰዓት ላይ "ከአደንቅሀለሁ መወድስ አለፍ ብላ 'የኔ ጀግና ፥ ነገ ባገኝህ ደስ ይለኛል' " ልትለኝ አይገባም ነበር ።
እንኳንስ ነካክተውን አይደለም እንዲሁም ቀላል ኮርማዎች ፥ ቀላል የፍየል ቆርጴሳዎች እንዳልሆንን መቼም ሀገር ምድሩ ያውቀዋል ...የስሜቴ መጠን አስራ አንድ በመቶ መናሩን እንዳስተዋልሁ " በጣም ደስ ይለኛል" አልኳት
"ምን ብጋብዝህ ይመችሀል ታዲያ ?" ብላ ጨዋታዋን ቀጠለች...ትንሽ እንደ መሽኮርመምም እንደ መግደርደርም እየቃጣኝ "ነጣ ያለ ማክያቶ " ስል መለስኩላት
" የኔ ጀግና ካንተ ጋር ብቻ እነገናኝ እንጂ ውስኪም ልናወርድ እንችላለን " ብላ ስትፅፍልኝ ገና እየጠጣሁ ያለሁትን የ ብር ከቼ አረቄ ደብሮኝ ገላመጥሁት።
።።።።
ነጋና ጠባ ደግሞ ብለዋል እነዛ ሁለት ወንድማማች የዳና ልጆች.. ቢኒ ዳናና...የሆነ ስም ዳና 😃
እኔ ጋር ደግሞ ነጋና መሸ ...ገና ከምሽቱ አስራ ሁለት ሰዓት ሲሆን መሲ ቴክስት አደረገችልኝ...ብሉዝ ካፌ ከምሽቱ 1:00 ላይ እንድንገናኝና ከላይ ቀይ መልክ ያለው ሹራብ እንደምታደርግ ጠቆመችኝ።
አላቅማማሁም.. pis ብዬ አቶ peace ን አሳጥሬ የስልክ መልዕክት ሰደድሁላት።
።።።።
Some crazy moments...
ካፌ መቀመጥ ይነስረኛል..ብዙም አይደላኝም...ወንድ ልጅ የሚያምርበት የጃንቦ ብርጭቆ ደርድሮ ጠረጴዛው ላይ እንደ ቼዝ ድንጋዮች ሲያንጋጋቸው እንጂ ሊፒስቲክና ቻፕስቲክ ተለቅልቃ ሚጢጢ የሻይ ብርጭቆ እንደምትመጥ ቀበጥ እንስት ፉት እያለ ሲሞላፈጥ ማየት አይደለም የሚል በንጉስ ኢዛና ዘመነ መንግስት በስፋት የሚራገብ የጥንታዊ ሀሳብ ባለቤት ነኝ።
ወንድ ልጅ ሆይ ጠጣ! ጠጣ !ጠጣ! ... ግን ፋራ ሆነህ አትስከር 😉
።።።።
በካፌው መስኮት አሻግሬ ሀላፊ አግዳሚውንም ብመለከት መሲን ከሚርመሰመሰው ህዝብ መሀል ልለያት አልቻልሁም...አይኔን ከግራ ወደ ቀኝ ከሰሜን ወደ ደቡብ እያወናጨፍኩኝ ስቅበዘበዝ በመሀል ለሰማይ ለምድር የሚከብድ ጠንካራ መዳፍ ትከሻዬን መታ መታ ሲያደርገኝ.. .ያላሰብሁት አጋዚ ከወዴት መጣብኝ? ብዬ ቆሎዬ ተገፎ ስዞር ቀይ ሹራብ ያደረገ ወደል ጎረምሳ "መሰረት ማለት እኔ ነኝ ሚኩ!" ብሎ የሁመራን መሬት የሚያህል ሰፊውን መዳፉን እንድጨብጠው ሰደደልኝ።
የሴት ስም ወይ የወንድ ስም ይሁን ለመለየት የሚያዳግት ስም ያላችሁ ወንዶችን በሙሉ ጠላኋችሁ!!...ዑራኤልን! 😕
#እምነት!

(ሚካኤል አስጨናቂ)

።።።።

ከእልፍ የቀለም ቀንድ ፥ መጥሀፍ አዋቂ

አንደበተ ርቱዕ ፥ ቃላትን አርቃቂ 

ወጎች ተነጥላ.. .

ሽሙጥ ቧልታቸው ጫንቃዋ ላይ አዝላ 

መሬት የወደቀች ...

በእንባዋ ተማፅኖ ፥ ይቅር በለኝ ብላ

የእየሱስን እግር በጠጉሯ ያበሰች 

አንዲት እንስት አለች!

።።።።

ወዲያ ማዶ ግድም.. .

መጎተት አዝሎት ፥ ሰንፎ የማይለግም

አንድ አባት ይጮሀል ፥ ድምፁን አሰምቶ 

ልጄን ማራት ይላል ፥ መሲሁን ተጣርቶ

።።።። 

ደግሞ ሌላ እናት.. .

የመንጋው ሁካታ ፥ ግርግር የረታት

ደዌዋን ልታሽር ፥ በአማኑኤል ሸማ

እጇን ዘርግታለች ፥ ከጠርዝ ዳር ቆማ 

።።።።።።።

ኢየሱስ ዞር አለ !

በዛች በቀድሞ ሴት ፥ ሀፍረት ተሸብበው 

ሀጥያተኛ ሳለች ፥ ዝም ያላት ለምን ነው?

ብለው ለመጠየቅ እያጉረመረሙ

በእምነቷ መዳኗን ተናግሯቸው ሰሙ።

።።።።።።።።።።

ደግሞም ወዲያ ግድም

ልጅህ ስለሞተች መምህሩን አታድክም 

ብለው የሚመክሩ አዋቂዎች ቆመው 

ሙት ልጁ ተነስታ ጉንጮቹን ብትስመው 

እነርሱ አፈሩ ፥ ከእምነት ተናንሰው ።

።።።

ያቺም አንዲት እናት.. .

መጮህ ባትችልም ፥ ማረኝ ማረኝ ብላ 

ፊቱ ባትቆምም ፥ በግፊያ ተሽላ 

ሸማውን ስትነካ ፥ ምህረቱን ዘርግቶ

ደዌዋን ሽሮታል ፥ ስር እምነቷን አይቶ ።

።።።።

ኢየሱስ ዞር አለ !

ከስቅለቱ በፊት ፥ ከስሩ የማይርቅ 

ህጉን እያፀና ፥ ምግባሩን የሚያርቅ

የእግሩ ስር ተማሪ ቶማስ ተጠራጥሯል

መዳፉን ሊዳስስ እጆቹን ዘርግቷል

ዳሰሰ መዳፉን!

እሳት አነፈረው የዘረጋው እጁን...

ቶማስ ማረኝ አለ ፥ ዳግም ምህረት ሽቶ

ጌታችን አነፃው ፥ ይቅርታውን ሰጥቶ 

ደግሞም ለማስረጃ ፥ አንድ ሀቅታ ሊተው

ገፄን ያልዳሰሱኝ ፥ እኔን ተጠራጥረው

በቃሌ የሚያድሩ ፥ መፈተንን ትተው

ሳያዩ የሚያምኑ ፥ ብፁአኖች ናቸው

ብሎ ተናገረው !
#ቅዱስ መስዋዕት!!
(ሚካኤል አስጨናቂ)
።።
ጀንበር አዘቅዝቃ ፥ ቀኑ ሲጨላልም
መንደርተኛው ሁሉ !
በአልጋ ልብሱ ማህፀን...
የቀን መቅበዝበዙን ፥ ዳግም በ'ልሙ ሲያልም
"እኔና ኮርኒሴ
ኮርኒሴና እኔ"
ከታችና ከላይ ፥ እንደተፋጠጥን
ሀሳብ ስንለካ ፥ ሀሳብ ስንወጥን
እንቆይ.. ....እንቆይና
ያዘቀዘቀችው ጀንበር ስትቃና
.
ሁሉም ሰው ሲወለድ
ከአልጋ ልብሱ ማህፀን
እኔም እከንፋለሁ.. .
ስጦታዬን ይዤ አንቺን ለመማጠን።
።።።
እቴ ይገርምሻል!
ይገርማል.. ..ዓለሜ
.
ገና በማለዳው ፥ ከበርሽ ላይ ስደርስ
ያንቀላፋ ፊቱ በቅጡ ሳይታበስ
ውሀ የመሰለች ....
ብልጭልጭ መኪና ከደጅሽ የሚያፈስ
ወጣት ባለፀጋ!
.
መጋዘኑን ሳይከፍት ፥ ልብሽን ሊከፍት
አበባ ወርቅ አልማዝ...
ዕንቁ ተሸክሞ ፥ ሸቀጥ የሚያንጋጋ
ተስፈኛ ነጋዴ!
.
ለላንቲካ ግብር ፥ ምላሱን አሹሎ
ባዶ እጁን የመጣ የሰፈር መደዴ
.
አፈር ተጠይፎ ፥
በርምጃዎች መሀል እግሩን የሚያነሳ
ዝነኛና ዘናጭ ቅብጥብጥ ጎረምሳ
.
እነ ሹገር ዳዲ ፥ እነ ሹገር ባባ
ወደ አንቺ ሲመጡ..
ለአባትነት ይሁን ለባልነት ይሁን ግራ 'ሚያጋባ
ብዙ.. ..ብዙ.....ብዙ ፥ ዘመናይ አዛውንት!
.
እርሷን ተዋትና ፥ ብትቆርቡ ይሻላል
ብለው 'ሚገስፁ ፥ የደብር ቀሳውስት
ቤትሽን ከበውታል።
።።።።
ይህን ጊዜ ታዲያ!
ሁሉም አሸልበው ፥ ምሽት ሲያንቀላፉ
በሴሰኛ ቅዠት.. .
ቀሚስሽን ለመግለብ ፥ ከአንቺ ጋር ሲላፉ
"እኔና ኮርኒሴ
ኮርኒሴና እኔ"
ከታችና ከላይ እንደተፋጠጥን
ሀሳብ ስንለካ ሀሳብ ስንወጥን
ቆየን.....ቆየንና..
ያዘቀዘቀችው ጀንበር ስትቃና
.
ውሀ ከመሰለች ብልጭልጭ መኪና
ከአልባስ ከክብር ፥ ከንዋይ ከዝና
ከሁሉ የሚልቅ!
ከህሊና ፈልቆ በተፈጥሮ ረ'ቆ
አዳሙን የሚያስንቅ!
"ልቤን ይዤ መጣሁ" ፥ ከልብሽ እንዳርቅ።
.
ተቀበይኝ ልቤን!!
እኔ ምልህ?
አገኘሀት?
:
ያቺን ምጥን
የሰው ምታ'ት!
.
ምናለችህ - ስታወጉ ?
ምን ብላለች ~ ስትጫወት ?
ያምና ውድህ ~ ያይንህ ውበት !
.
ትዝ ይላታል ስላለፈው ?
በዛ ቀሚስ ~ ስስ ነፍስህን ስትንጠው?


ትዝ ይላታል ~ ያንተ ሳቅህ ?
ታወሳት ወይ ~ ያ ደረትህ ?
የክንድህ ላይ ~ ንቅሳትህ
ስሟን ያተምክበት
..............ጥቁር ምልክትህ
ትዝ አላት ወይ?
ጥርስ ገላጭ ~ ለዛ ቀልድህ?

ምን ትላለች
ስለ ትናንት —-
ከንፈርህ ዳሳ - ተኩሳህ እንደ እሳት
ልብህን አድብናት…
ቀልብህን አጉናት ...
ስትነጥልህ ፦ ከሰው መንጋ
ለሌላው ጨልመህ ለርሷ ስትነጋ፤

ታወሳት ፦ ትዝ አላት?
.
ተበድረህ ለልደቷ
የአንገት ሀብል ስትገዛላት?
ለብርቋ ቀን ስትደርስላት
.
ውዴ ብላ
ተንጎማላ
ውዱ ብላ
ተገማሽራ
ስትሸጎጥ ስርህ
ተሞልታ ~ በኩራት
ከእናቷ ለጥቆ
በፍቅር ወልደሀት..
ሞገስ ሆነህ
ቅባት ሆነህ
እንደ ጣይቱ አንግሰሀት
ጓዶቿ ፊት ጌጥ ሆነሀት

እንደው ምናለችህ ?
ስታገኛት ፣ ስትቀርባት
ያቺ ምጥን
የሰው ምታ’ት?
.
ምን ብላለች ስትጫወት?
ያምና ውድህ ያይንህ ውበት !

.
ብዬ ብጠይቀው
እየተናነቀው...
.
"ሳቄ አይደል ጠረኔ
ምኑም የላት ከኔ
ይልቅ ስጠይቃት
የታወሳት የገረማት...
ከቀን መርጦ የመጣላት
የኔ ችጋር ~ የኔ ማጣት
ለዓይኗ እንኳ ጠገነንኳት ።"

ብሎ መለሰልኝ...

(ሚካኤል አ)
2024/06/09 23:10:05
Back to Top
HTML Embed Code: