Telegram Web Link
በተለያዩ ሀገራት የሳይንስ ማህበረሰቦች መካከል ውህደትንና ትብብርን ለመፍጠር መድረኮች ወሳኝ ናቸው ያሉት ዋና ዳይሬክተሩ የዓለም አቀፍ የሳይንስ ድርጅቶች ጥምረት(ANSO) እና የአፍሪካ የሳይንስ እና ፈጠራ ማዕከል በሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን መስክ በሚያደርጋቸው ትብብር በዓለም አቀፍ  ደረጃ ተወዳዳሪ መሆን የሚቻልበትን እድል መፈጠር እንዳለበት ገልፀዋል።

በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የሀገራዊ ምርምርና ልማት መሪ ስራ አስፈፃሚ ዶ/ር ሀብታሙ አበራ አፍሪካን በሳይንስ፣ ቴክኖሎጂ እና ኢኖቬሽን ለማጎልበት የአፍሪካ የሳይንስ እና ፈጠራ ማዕከል ትብብር  ወሳኝ መሆኑን አስገንዝበዋል፡፡

በአፍሪካ እና በቻይና ተቋማት መካከል ያለውን አጋርነት አፍሪካ ለዘላቂ ልማት እና ለአለም አቀፍ ተወዳዳሪነት የምታደርገውን አስተዋፅኦ ያፋጥናል ያሉት መሪ ስራ አስፈፃሚው ኢትዮጵያ ሀገራዊ የምርምር እና የፈጠራ ስርአቶችን ከአለም አቀፍ እና ክልላዊ የልማት ማዕቀፎች ጋር ለማጣጣም ቁርጠኛ መሆኗን ተናግረዋል።

በጉባኤው ላይ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር፣ የአምቦ ዩኒቨርሲቲ፣ የባዮ እና ኢመርጂንግ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት፣ የዚምባቡዌ የኢንጂነሪኒግ ድርጅት፣ የኬንያ አፍሪካ አካዳሚ፣  የናይጄሪያ የምርምር ተቋም፣ የአለም አቀፍ የሳይንስ ድርጅቶች አሊያንስ (ANSO)፣ የቻይና ሳይንስ አካዳሚ፣ እና ሌሎች ከአጋር ተቋማት የተውጣጡ ተወካዮችን ተሳትፈውበታል።
5
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶ/ር በለጠ ሞላ የስማርት ዛምቢያ ኢኒሼቲቭ ብሔራዊ አስተባባሪ ሚስተር ፐርሲ ቺኒያማ የተመራውን ልዑካን ቡድን በጽ/ቤታቸው ተቀብለው  መከሩ
====================
ምክክሩ በኢትዮጵያ ዲጅታል ትራንስፎርሜሽን አፈጻጸም ላይ ልምድ ለመቅሰም  ያለመ ነው።

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶ/ር በለጠ ሞላ ለልኡካኑ በዲጅታል ኢትዮጵያ በተገኙ ውጤቶች እና በስትራቴጂው  አመራር ላይ ገለፃ በማድረግ ኢትዮጵያ  ወደ 2030 የሚወስዳትን ስትራቴጂ እየነደፈች መሆኑም አብራርተዋል።

አክለውም የአፍሪካ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽንን እውን ለማድረግ በአፍሪካ ሀገሮች መካከል ትብብር ሊኖር እንደሚገባም አጽኖት ሠጥተው ተናግረዋል።

የስማርት ዛምቢያ ኢኒሼቲቭ ብሔራዊ አስተባባሪ ሚስተር ፐርሲ ቺኒያማ (Mr. Percy Chinyama, National Coordinator, Smart Zambia Initiative) ኢትዮጵያ የዲጂታል ትራንስፎርሜሽን ለማሳካት ያደረገችውን ጉዞ አድንቀዋል፡፡

በአፍሪካ ውስጥ ውጤታማ ነገሮች ስናይ ልምድን  ከሌላ ቦታ ከመቅሰሙ ይልቅ ከዚሁ መቅሰሙ አንድ አይነት አውድ ውስጥ ስላለን ጠቀሜታው የጎላ እንደሚሆን ገልፀዋል፡፡

ልኡካኑም በተደረገለት ገለጻ አመስግኖ ከኢትዮጵያ ጋር በተለይ በዲጅታል መታወቂያ እና በአህጉራዊ ዲጅታል ጉዳዮች ላይ በትብብሩ እንደሚሰሩ  አስታውቀዋል ።
4
በአለም ባንክ የተደረገው የኢትዮጵያ ቴሌኮም ገበያ ዳሰሳ ጥናት የባለድርሻ አካላት ውይይት ተደረገ፡፡
=====================
በዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ጉዞ የኢትዮጵያ ቴሌኮም ገበያ በዓለም ባንክ ዳሰሳ ጥናት ላይ(Ethiopia Telecom Market Assessment፡ the WORLD Bank Group) ያተኮረ አውደ ጥናት አካሄደ።
 
በአውደ ጥናቱ መክፈቻ ላይ የተገኙት የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ሙሉቀን ቀሬ በዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ስትራቴጂ ትግበራ ወቅት በመንግስት የብቻ ቁጥጥር ውስጥ የነበረው የቴሌኮም ዘርፍ ሊበራላይዝ ከመደረጉ ጋር ተያይዞ ስትራቴጂውን አፈጻጸም ያገዙ አመርቂ ስኬቶች መገኘታቸውን በመግለጽ በተለይ እድሜ ጠገብ የሆነው ኢቲዮ ቴሌኮም ባደረጋቸው ወሳኝ ሪፎርሞች፣ እንደ ቴሌ ብር ያሉ አዳዲስ የፈጠራ አማራጮችን ለገበያው በማስተዋወቁ፣ በወሰዳቸው የአገልግሎት ማሻሻያ ርምጃዎች እና የብሮድባንድ ኔትዎርክ ማስፋፊያ ሥራዎች ተጠቃሽ ስኬትን በማስመዝገብ ለውድድር ሜዳው መሰረት ጥሏል ያሉ ሲሆን በሌላ በኩል የተወሰደውን የፖሊሲ ርምጃ ተከትሎ የቴሌኮም ገበያውን የተቀላቀለው ሳፋሪኮም ኢትዮጵያም ውድድር የገፋው ፈጠራ እንዲያብብ እና ጤናማ ዉድድር እንዲኖር በማስቻል የቴሌኮም ዘርፉን አጠናክሯል ብለዋል።
2
አክለውም ሀገራችን የዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ማብቂያ እና በቀጣዪ ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂ መጀመሪያ ምዕራፍ ላይ የምትገኝ መሆኑን አስታውሰው በመጀመሪያው ስትራቴጂ ትግበራ ያገኘናቸውን እንደ ብሮድባንድ መስፋፋት፣ የአካታች የዲጂታል ፋይናንስ አጠቃቀም ማደግ፣ የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ስርዓት ተዘርግቶ አገልግሎት መጀመር እና የፈጠራ ስነምህዳር መጠናከር ያሉ ስኬቶችን ቆጥረን በመያዝ ለቀጣዩ የ2030 ስትራቴጂ ትግበራ መዘጋጀት እንዳለብን ገልፀዋል።

አክለውም አጋር አካላትም እንደቀደመው ሁሉ ድጋፋቸውን እንዲቀጥሉ እና ዲጅታል ኢትዮጵያን እውን በማድረግ ሂደት ውስጥ ጥረታችንን በመደገፍ ከጎናችን እንዲቆሙ ጥሪ አቅርበዋል።

ክቡር ሚንስትር ዴኤታው አውደ ጥናቱን አስመልክቶ ተሳታፊዎች የጥናቱን ዋና ዋና ግኝቶች እንዲፈትሹ እና መሬት ላይ ካለው እውነታ ጋር እንዲያገናዝቡ፣ የተወሰዱ ወሳኝ የፖሊሲ እርምጃዎች ላይ ሀሳብ እንዲያጋሩ እና ጉዳዪ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር ግልጽ ውይይት እንዲያደርጉ መልዕክት ያስተላለፉ ሲሆን የዳሰሳ ጥናቱ ሳይንሳዊ መርሆዎችን እና ሂደቶችን የተከተለ መሆኑን ማረጋገጥ ለሚቀርቡ የፖሊሲ ምክረ ሀሳቦች ወሳኝ መሆኑን ጠቅሰዋል።

በአወደ ጥናቱ ላይ የተገኙት የዓለም ባንክ ሪጅናል ዲጂታል ኢኮኖሚ  ዳይሬክተር ሚስተር ሚሼል ሮጊይ በበኩላቸው የኢትዮጵያ ቴሌኮም ገበያ በዕድገት ጎዳና ላይ መሆኑን ባንኩ ባደረገው ዳሰሳዊ ጥናት ማረጋገጡን ገልጸዋል፡፡
 
አውደ ጥናቱን ያዘጋጁት የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር፣ የዓለም ባንክ ሪጅናል ቢሮና የኢትዮጵያ ቴሌኮም በመተባበር ነው።
 
በአውደ ጥናቱ ተጨማሪ ግብዓት እንደሚቀርቡበትና መካተት ያለባቸው ሀሳቦች ተካተው ለፖሊሲ አውጪዎች እንደሚቀርብ ይጠበቃል።
3
2025/10/25 19:07:36
Back to Top
HTML Embed Code: