Telegram Web Link
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርና የሱጆ (Suzhou) ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ
በውሃና በጤና ዘርፍ ላይ በጋራ የምርምር ላብራቶሪ ለመገንባት ተስማሙ፡፡
====================
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴርና የባዮ እና ኢመርጂንግ ቴክኖሎጂ ኢንስቲትዩት ከቻይናው ሱጆ (Suzhou) ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርስቲ ጋር በመተባበር በውሃና በጤና ዘርፍ ላይ በጋራ የምርምር ላብራቶሪ ለመገንባት በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ መክረዋል፡፡

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ባይሳ በዳዳ ኢትዮጵያን በሳይንስ፣ ቴክኖሎጂና ኢኖቬሽን ዘርፍ እየሰራች ያለችውን ዘርፈ ብዙ ስራዎችና እያስመዘገበች ያለው ውጤት ዙሪያ ገለፃ አድርገዋል።

ኢትዮጵያ ከቻይና መንግስት ጋር በትብብር የምትሰራቸው ፕሮጀክቶች ተጠናክረው ሊቀጥሉ ይገባል ያሉት ሚኒስትር ዴኤታው በውሃና በጤና ዘርፍ ላይ በጋራ የሚገነባውን የምርምር ላብራቶሪ ግንባታ ፕሮጀክት ቀደም ብሎ የተፈረመውን የስምምነት ሰነድ ወደ ትግበራ ለመግባት በትኩረት እየተሰራ መሆኑን ገልፀዋል፡፡

ዩኒቨርሲቲው በአጭርና በረጅም ጊዜ ከ 230 በላይ ኢትዮጵውያን ላይ በሳይንስና ቴክኖሎጂ ዘርፍ ላደረገው የሰው ኃይል ልማት ምስጋና በማቅረብ በቀጣይ በምርምር መሰረት ልማትና በቴክኖሎጂ ሽግግር የነበረው ትብብር ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጠይቀዋል።
የሱጆ (Suzhou) ዩኒቨርስቲ ምክትል ፕሬዝዳንት ፕሮፌሰር ሊ ዮን (Li Yong) በበኩላቸው የተጀመሩ ስራዎችን በማጠናከር በምርምር መሰረተ ልማት፣ በጋራ የምርምር ውጥኖች፣ በአካዳሚክ፣ በሰው ሃይል ልማት ላይ በትብብር ለመስራት ዩኒቨርሲቲው ዝግጁ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ስምምነት ላይ የተደረሰውና ወደ ትግበራ የተገባው በውሃና በጤና ዘርፍ የምርምር ላብራቶሪ ግንባታ በተቀመጠለት ጊዜ ተጠናቆ ለአገልግሎት እንዲውል እንደሚደረግ በምክክሩ ላይ በአፅንዖት ተገልጿል፡፡
👏3🔥2
ውጤታማ የንብረት አያያዝና አጠቃቀም አሰራር ሥርዓትን ለመፍጠር የዘርፉ የሰው ሀይል አቅም ማጎልበት ሚናው የላቀ ነው።
==================
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ውጤታማ የንብረት አያያዝና አጠቃቀም አሰራር ሥርዓትን ለማጎልበት በዘርፉ ላይ ለተሰማሩ ባለሙያዎች አቅም የማጎልበት መድረክ አካሂዷል።

በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የኦዲት ስራ አስፈፃሚ አቶ አሻግሬ አለሙ የሀገር ሀብት የሆኑትን ንብረቶች በዘመናዊ የአሰራር ስርዓት በጥንቃቄ የመያዝ፣ የመጠቀም፣ የመቆጣጠር እና አገልግሎቱም ሲያበቃ በተገቢው መንግድ እንዲወገድ ከዘርፉ ባለሙያ እንደሚጠበቅ ግንዛቤ አስጨብጠዋል።

ሁሉም ዘመናዊ የአሰራር ስርዓት ባለቤት ሊሆን ይገባል ያሉት ስራ አስፈፃሚው በተቋሙ ውስጥ የዘመነ የንብረት አያያዝና አጠቃቀም አሰራር ሥርዓትን ለመፍጠር የዘርፉ የሰው ሀይል አቅም ማጎልበት ሚናው የላቀ መሆኑን አንስተዋል።

የሚጠቀሙበትን ንብረቶች በተገቢው መንገድ መጠቀም እንዳለባቸው እንዲሁም በአመታዊ የንብረት አስተዳደር ዕቅድ መሰረት ሊተገበር ይገባል ብለዋል።

በተሻሻለው የፌደራል መንግስት የንብረት አስተዳደር መመሪያ ላይ ገለፃ በማድረግ የአሰራር ስርዓቱን ተከትሎ መተግበር እንደሚገባም አሳስበዋል፡፡

የተቋማችን ንብረት የመጠበቅ በአግባቡ የመጠቀም ኃላፊነት የሁላችንም ነው ያሉት ስራ አስፈፃሚው ንብረትን በአግባቡ መጠቀም መቻል የዘመናዊ አሰራር ስርዓት አካል መሆኑን ጠቁመዋል።

የመድረኩ ተሳታፊዎች በንብረት አያያዝና አጠቃቀም ላይ የተሻለ አቅም ለመፍጠር የተካሄደው መድረክ ለስራቸው አጋዥ እንደሆነና በቀጣይም እንዲህ ያሉ አቅም ማጎልበቻዎች ተጠናክረው እንዲቀጥሉ ጠይቀዋል።
1
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዶ/ር በለጠ ሞላ በሚኒስትሮች ምክር ቤት የመቶ ቀን ግምገማ ወቅት በኮይሻ ውይይት ላይ ያቀረቡት ምልከታ፡፡
ኢትዮጵያ ሰፊ ሀብትና እምቅ አቅም ያላት ሀገር መሆኗን ይበልጥ ልረዳ ችያለሁ። ዶ/ር በለጠ ሞላ፡፡
===================
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶ/ር በለጠ ሞላ በሚኒስትር ምክር ቤት ምልከታ በኮይሻ ውይይት ላይ ምልከታቸውን አቅርበዋል፡፡
በሚኒስትር ምክር ቤት ምልከታ በኮይሻ ውይይት ላይ የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዶ/ር በለጠ ሞላ በመንግስት ውስጥ የመስራት እድል ካገኘሁ በኋላ ኢትዮጵያን የበለጠ እንዳውቃት እረድቶኛል ብለዋል፡፡

ያለንን አቅም አይቶ ወደ ተግባር የመቀየርን ጉጉትና ስራ ላይ ተመስርቶ ሀብቶቻችንን ወደ ተጨባጭ ውጤት በማምጣት በኢትዮጵያ ውስጥ የቱሪዝም አቅምን እጅግ ከፍ የሚያደርጉ ማዕከላት መገንባት እንደተቻለ ገልፀዋል፡፡

የኮይሻ ሀይድሮ ፓወር ፕሮጀክት በአፍሪካ ውስጥ ትልቀ ከሚባሉት አንዱ ነው ያሉት ሚኒስትሩ ለሀገራችን ትልቅ የሀይል ምንጭ የሆነ ስራ መሰራቱን በንግግራቸው ውስጥ አንስተዋል፡፡

በተግዳሮቶች ውስጥ ሆነን እድገታችን ከፍ እያለ ለኢትዮጵ የሚመጥኑ ፕሮጀክቶች እየተጀመሩና እየተመረቁ እንደሚገኙ አንስተዋል፡፡

በሂደት ውስጥ ሆነን ራሳችንን እያስተማርንና እያለማመድን ክፍተቶችን እየሞላን የተሻለ ስራ እየሰራን እንድሄድ የሚያስችሉ እድሎችን አንፈጥራለን ብለዋል፡፡

በመጨረሻም በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩ አመራርነት ለተመሩ ስራዎችን ከፍ ያላ ዋጋ መስጠታቸውን ገልፀዋል፡፡
6👏2🔥1
2025/10/27 18:13:44
Back to Top
HTML Embed Code: