በአለም ባንክ የተደረገው የኢትዮጵያ ቴሌኮም ገበያ ዳሰሳ ጥናት የባለድርሻ አካላት ውይይት ተደረገ፡፡
=====================
በዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ጉዞ የኢትዮጵያ ቴሌኮም ገበያ በዓለም ባንክ ዳሰሳ ጥናት ላይ(Ethiopia Telecom Market Assessment፡ the WORLD Bank Group) ያተኮረ አውደ ጥናት አካሄደ።
በአውደ ጥናቱ መክፈቻ ላይ የተገኙት የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ክቡር አቶ ሙሉቀን ቀሬ በዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ስትራቴጂ ትግበራ ወቅት በመንግስት የብቻ ቁጥጥር ውስጥ የነበረው የቴሌኮም ዘርፍ ሊበራላይዝ ከመደረጉ ጋር ተያይዞ ስትራቴጂውን አፈጻጸም ያገዙ አመርቂ ስኬቶች መገኘታቸውን በመግለጽ በተለይ እድሜ ጠገብ የሆነው ኢቲዮ ቴሌኮም ባደረጋቸው ወሳኝ ሪፎርሞች፣ እንደ ቴሌ ብር ያሉ አዳዲስ የፈጠራ አማራጮችን ለገበያው በማስተዋወቁ፣ በወሰዳቸው የአገልግሎት ማሻሻያ ርምጃዎች እና የብሮድባንድ ኔትዎርክ ማስፋፊያ ሥራዎች ተጠቃሽ ስኬትን በማስመዝገብ ለውድድር ሜዳው መሰረት ጥሏል ያሉ ሲሆን በሌላ በኩል የተወሰደውን የፖሊሲ ርምጃ ተከትሎ የቴሌኮም ገበያውን የተቀላቀለው ሳፋሪኮም ኢትዮጵያም ውድድር የገፋው ፈጠራ እንዲያብብ እና ጤናማ ዉድድር እንዲኖር በማስቻል የቴሌኮም ዘርፉን አጠናክሯል ብለዋል።

❤2
አክለውም ሀገራችን የዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ማብቂያ እና በቀጣዪ ዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂ መጀመሪያ ምዕራፍ ላይ የምትገኝ መሆኑን አስታውሰው በመጀመሪያው ስትራቴጂ ትግበራ ያገኘናቸውን እንደ ብሮድባንድ መስፋፋት፣ የአካታች የዲጂታል ፋይናንስ አጠቃቀም ማደግ፣ የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ስርዓት ተዘርግቶ አገልግሎት መጀመር እና የፈጠራ ስነምህዳር መጠናከር ያሉ ስኬቶችን ቆጥረን በመያዝ ለቀጣዩ የ2030 ስትራቴጂ ትግበራ መዘጋጀት እንዳለብን ገልፀዋል።
አክለውም አጋር አካላትም እንደቀደመው ሁሉ ድጋፋቸውን እንዲቀጥሉ እና ዲጅታል ኢትዮጵያን እውን በማድረግ ሂደት ውስጥ ጥረታችንን በመደገፍ ከጎናችን እንዲቆሙ ጥሪ አቅርበዋል።
ክቡር ሚንስትር ዴኤታው አውደ ጥናቱን አስመልክቶ ተሳታፊዎች የጥናቱን ዋና ዋና ግኝቶች እንዲፈትሹ እና መሬት ላይ ካለው እውነታ ጋር እንዲያገናዝቡ፣ የተወሰዱ ወሳኝ የፖሊሲ እርምጃዎች ላይ ሀሳብ እንዲያጋሩ እና ጉዳዪ ከሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት ጋር ግልጽ ውይይት እንዲያደርጉ መልዕክት ያስተላለፉ ሲሆን የዳሰሳ ጥናቱ ሳይንሳዊ መርሆዎችን እና ሂደቶችን የተከተለ መሆኑን ማረጋገጥ ለሚቀርቡ የፖሊሲ ምክረ ሀሳቦች ወሳኝ መሆኑን ጠቅሰዋል።
በአወደ ጥናቱ ላይ የተገኙት የዓለም ባንክ ሪጅናል ዲጂታል ኢኮኖሚ ዳይሬክተር ሚስተር ሚሼል ሮጊይ በበኩላቸው የኢትዮጵያ ቴሌኮም ገበያ በዕድገት ጎዳና ላይ መሆኑን ባንኩ ባደረገው ዳሰሳዊ ጥናት ማረጋገጡን ገልጸዋል፡፡
አውደ ጥናቱን ያዘጋጁት የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር፣ የዓለም ባንክ ሪጅናል ቢሮና የኢትዮጵያ ቴሌኮም በመተባበር ነው።
በአውደ ጥናቱ ተጨማሪ ግብዓት እንደሚቀርቡበትና መካተት ያለባቸው ሀሳቦች ተካተው ለፖሊሲ አውጪዎች እንደሚቀርብ ይጠበቃል።

❤3
የዲጂታል ኢኮኖሚ አመላካቾች ወደ ከፍተኛ ማደጋቸውን የኢፌዲሪ ፕሬዝዳንት ታዬ አጽቀሥላሴ ገለፁ።
====================
6ኛው የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት እና የፌዴሬሽን ም/ቤት 5ኛ ዓመት የሥራ ዘመን መክፈቻ ሥነ ሥርዓት ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) በተገኙበት ተካሂዷል፡፡
ምክር ቤቶቹ ዓመታዊ ሥራቸውን እንደጀመሩ ያበሰሩት ፕሬዚዳንት ታዬ አጽቀ ሥላሴ የዲጂታል ኢትዮጵያ ልማት እውን መሆን የቴክኖሎጂ ሽግግር ጉዳይ ብቻ ሳይሆን የሀገራችን የፖለቲካ ተራክቦት ኢኮኖሚያችንና ማህበራዊ ህይወታችንን ይቀይራል ብለዋል፡፡
ዲጂታል ኢትዮጵያ 2025 ስትራቴጂ አመርቂ ውጤቶችን መመዝገባቸውን ጠቅሰው በቀጣይም የዲጂታል ኢትዮጵያ 2030 ስትራቴጂ ወደ ላቀ ደረጃ ለማሸጋገር እንደሚሰራ ገልፀዋል፡፡
ዲጂታል ቴክኖሎጂን በማስፋት የመረጃ ልውውጥን በማቀላጠፍና አገልግሎቶችን ተደራሽ በማድረግ የኢኮኖሚ መዋቅራዊ ሽግግርን በአጭር ጊዜ እውን ማድረግ እንደሚቻል መንግስት በፅኑ እንደሚያምን አንስተዋል፡፡
በ2018 በጀት ዓመት ዜጎች የዲጂታል መታወቂያ ተጠቃሚ እንዲሆኑ በማስቻል አገልግሎቶች በዲጂታል ማዕቀፍ እንዲሰጡና እንዲሳለጡ ይደረጋል ብለዋል፡፡
የዲጂታል ዘርፍ ለሌሎች ዘርፎች አስቻይ ሁኔታ የሚፈጥር እንዲሆን እንደሚደረግ ተናግረዋል፡፡

በኢትዮጵያ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ የአስተዳደር ማዕቀፍ በመንግስት ተቋማት የፖሊሲ ጣልቃገብነት አስፈላጊነት ዙሪያ በተደረገ ጥናት ላይ የባለድርሻ አካላት ዎርክሾፕ ተካሄደ፡፡
=======================
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ከኢትዮጵያ የፖሊሲ ጥናቶችኢንስቲትዩት ጋር በመተባበር “የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ የአስተዳደር ማዕቀፍ በኢትዮጵያ የመንግስት ተቋማት የፖሊሲ ጣልቃገብነት አስፈላጊነት" በሚል ርዕስ ሲያካሂድ በቆየው ሰፊ ጥናትና ግኝቶች ላይ የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት የማረጋገጫ ዎርክሾፕ ተካሂዷል፡፡
በዎርክሾፑ መክፈቻ ላይ የተገኙት የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ሙሉቀን ቀሬ ባለፉት የለውጥ ዓመታት መንግስት ትኩረት ካደረገባቸው የልማት ዘርፎች አንዱ ቴክኖሎጂ ልማት ዘርፍ መሆኑን እና የቀጣይ ሀገራዊ ጉዟችንም የቴክኖሎጂ ልማት ላይ በምንፈጥረው ሀገራዊ አቅም ላይ የተመሰረተ እንደሚሆን አስገንዝበዋል፡፡
ልክ ከኛ በፊት እንደቀደሙት የበለጸጉ ሀገራት ኢኮኖሚያቸውን፣ ዕውቀታቸውን እና ቴክኖሎጂን በመጠቀም የሕዝባቸውን ችግር መፍቻ እንዲሆን እንዳደረጉት ሁሉ ሀገራችን ኢትዮጵያም በቴክኖሎጂ ገፊነት ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ የልማት ስኬቶችን ለማስመዝገብ በቆራጥነት እየሰራችበት ትገኛለች ብለዋል፡፡

የቴክኖሎጂ ለውጥና ዕድገት በትክክል በሕግ ማዕቀፍ እንዲመራ ካልተደረገ ከጥቅሙ ጉዳቱ ሊያመዝን ይችላል ያሉት ሚኒስትር ዴኤታው የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ የአስተዳደር ማዕቀፍ ሰነድ ላይ የምናደርገው ውይይት ያለንበትን ጊዜና የዓለም አቀፍ አሁናዊ ሁኔታዎችን ባገናዘበ መልኩ በተለይ በዓለማችን የሰው ሠራሽ አስተውሎት አጠቃላይ የቴኮኖሎጂ ሥርዓተ ምህዳሩን እየለወጠው ከመሆኑ እውነታ ጋር ተያይዞ የቴክኖሎጂ አስተዳደር ማዕቀፍ ስንቀርጽ አሁን ያለንበትን ነባራዊ ሁኔታ በዋጀ መልኩ መሆን እንዳለበት እና በውጤቱም ሀገራዊ የቴክኖሎጂ ሉዓላዊነትን በሚያረጋግጥ መልኩ መሆን እንዳለበት አሳስበዋል፡፡
አክለውም የሀገራችንን የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ኢንቨስትመንትን በማበረታት የዲጂታል ኢኮኖሚ ልማት እመርታን ከማምጣት ባሻገር ሀገራዊ የዲጂታል፣ ዳታ፣ቴክኖሎጂ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ እንዲህ ያሉ የቴክኖሎጂ አስተዳደር ማዕቀፎች አስፈላጊ እና ጠቃሚ መሆናቸውን አንስተዋል።
በማጠቃለልም የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ የአስተዳደር ማዕቀፍ ሲተገበር ጥቅም እንዳለው ሁሉ “በትክክል ካልተተገበረ ጉዳቶቹ ምን ይሆናሉ?” የሚለውን ጥያቄ የሚመልስ ውይይት በማድረግ፣ ልምድን በመቀመር ቀድሞ ተዘጋጅቶ መፍትሄ ለመስጠት የሚያስችል ሥርዓታዊ ፍጥነትን የሚያረጋግጥ የአስተዳደር ፍሬምዎርክና ምክረ ሀሳብ ከተመራማሪዎች እንደሚጠበቅ እንዲሁም ውይይቱ በዚሁ መልክ እንዲቃኝ አሳስበዋል።
በኢትዮጵያ የፖሊሲ ጥናቶች ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ክቡር አቶ ተፈሪ ጥያሮ በበኩላቸው ኢንስቲትዩታቸው በጥናቱ ሲሳተፍ እየዘመነ ከመጣው ዓለም ጋር ተያይዞ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ አስፈላጊነት እየጨመረ በመምጣቱ በመንግስት ተቋማት የአገልግሎት አሰጣጥ ላይ በማተኮር ምላሽ ሰጪ ጥናቶችን በማካሄድ እያቀረበ እንደሚገኝ አስገንዝበዋል፡፡