በኢትዮጵያ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ የአስተዳደር ማዕቀፍ በመንግስት ተቋማት የፖሊሲ ጣልቃገብነት አስፈላጊነት ዙሪያ በተደረገ ጥናት ላይ የባለድርሻ አካላት ዎርክሾፕ ተካሄደ፡፡
=======================
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ከኢትዮጵያ የፖሊሲ ጥናቶችኢንስቲትዩት ጋር በመተባበር “የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ የአስተዳደር ማዕቀፍ በኢትዮጵያ የመንግስት ተቋማት የፖሊሲ ጣልቃገብነት አስፈላጊነት" በሚል ርዕስ ሲያካሂድ በቆየው ሰፊ ጥናትና  ግኝቶች ላይ የሚመለከታቸው ባለድርሻ አካላት የማረጋገጫ ዎርክሾፕ ተካሂዷል፡፡

በዎርክሾፑ መክፈቻ ላይ የተገኙት የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ሙሉቀን ቀሬ ባለፉት የለውጥ ዓመታት መንግስት ትኩረት ካደረገባቸው የልማት ዘርፎች አንዱ ቴክኖሎጂ ልማት ዘርፍ መሆኑን እና የቀጣይ ሀገራዊ ጉዟችንም የቴክኖሎጂ ልማት ላይ በምንፈጥረው ሀገራዊ አቅም ላይ የተመሰረተ እንደሚሆን አስገንዝበዋል፡፡

ልክ ከኛ በፊት እንደቀደሙት የበለጸጉ ሀገራት ኢኮኖሚያቸውን፣ ዕውቀታቸውን እና ቴክኖሎጂን በመጠቀም የሕዝባቸውን ችግር መፍቻ እንዲሆን እንዳደረጉት ሁሉ ሀገራችን ኢትዮጵያም በቴክኖሎጂ ገፊነት ኢኮኖሚያዊ እና ማህበራዊ የልማት ስኬቶችን ለማስመዝገብ በቆራጥነት እየሰራችበት ትገኛለች ብለዋል፡፡
2
የቴክኖሎጂ ለውጥና ዕድገት በትክክል በሕግ ማዕቀፍ እንዲመራ ካልተደረገ ከጥቅሙ ጉዳቱ ሊያመዝን ይችላል ያሉት ሚኒስትር ዴኤታው የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ የአስተዳደር ማዕቀፍ ሰነድ ላይ የምናደርገው ውይይት ያለንበትን ጊዜና የዓለም አቀፍ አሁናዊ ሁኔታዎችን ባገናዘበ መልኩ በተለይ በዓለማችን የሰው ሠራሽ አስተውሎት አጠቃላይ የቴኮኖሎጂ ሥርዓተ ምህዳሩን እየለወጠው ከመሆኑ እውነታ ጋር ተያይዞ የቴክኖሎጂ አስተዳደር ማዕቀፍ ስንቀርጽ አሁን ያለንበትን ነባራዊ ሁኔታ በዋጀ መልኩ መሆን እንዳለበት እና በውጤቱም ሀገራዊ የቴክኖሎጂ ሉዓላዊነትን በሚያረጋግጥ መልኩ መሆን እንዳለበት አሳስበዋል፡፡

አክለውም የሀገራችንን የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ኢንቨስትመንትን በማበረታት የዲጂታል ኢኮኖሚ ልማት እመርታን ከማምጣት ባሻገር ሀገራዊ የዲጂታል፣ ዳታ፣ቴክኖሎጂ ሉዓላዊነትን ለማረጋገጥ እንዲህ ያሉ የቴክኖሎጂ አስተዳደር ማዕቀፎች አስፈላጊ እና ጠቃሚ መሆናቸውን አንስተዋል።

በማጠቃለልም የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ የአስተዳደር ማዕቀፍ ሲተገበር ጥቅም እንዳለው ሁሉ “በትክክል ካልተተገበረ ጉዳቶቹ ምን ይሆናሉ?” የሚለውን ጥያቄ የሚመልስ ውይይት በማድረግ፣ ልምድን በመቀመር ቀድሞ ተዘጋጅቶ መፍትሄ ለመስጠት የሚያስችል ሥርዓታዊ ፍጥነትን የሚያረጋግጥ የአስተዳደር ፍሬምዎርክና ምክረ ሀሳብ ከተመራማሪዎች እንደሚጠበቅ እንዲሁም ውይይቱ በዚሁ መልክ እንዲቃኝ አሳስበዋል።

በኢትዮጵያ የፖሊሲ ጥናቶች ኢንስቲትዩት ምክትል ዋና ዳይሬክተር ክቡር አቶ ተፈሪ ጥያሮ  በበኩላቸው ኢንስቲትዩታቸው በጥናቱ ሲሳተፍ እየዘመነ ከመጣው ዓለም ጋር ተያይዞ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ አስፈላጊነት እየጨመረ በመምጣቱ በመንግስት ተቋማት የአገልግሎት አሰጣጥ ላይ በማተኮር ምላሽ ሰጪ ጥናቶችን በማካሄድ እያቀረበ እንደሚገኝ አስገንዝበዋል፡፡
2
በዚህም የአይቲ ግንኙነት፣ ንግድ እና ትምህርት በዓለም አቀፍ ደረጃ ቢቀያይርም፣ በኢትዮጵያ የአስተዳደር መዋቅር ውስጥ ያለው ውህደት ትልቅ ፈተናዎች እየገጠሙት መሆኑን ጠቁመው፤  ወጥ የሆነ የአይቲ አስተዳደር ማዕቀፍ አለመኖሩ የተበታተኑ ውጥኖች፣ የጥረቶች ድግግሞሽ፣ የተጠያቂነት ውስንነት እና የአይቲ ኢንቨስትመንቶች ጥቅም ላይ እንዳይውሉ እንዳደረገው በጥናቱ ግኝቶች ተመላክቷል ብለዋል።
18ኛው የብሔራዊ የሰንደቅ ዓላማ ቀን በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ተከብሮ ውሏል።
==============
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራሮችና ሰራተኞች በተገኙበት 18ኛው የብሔራዊ የሰንደቅ ዓላማ ቀን ‘’ሰንደቅ ዓላማችን ለኢትዮጵያ ታላቅ የከፍታ ዘመን ብሥራት፣ ለብሔራዊ አንድነታችን፣ ለሉዓላዊነታችንና ለኢትዮጵያ ሕዳሴ! ‘’ በሚል መሪ ቃል ተከብሯል።
7👍2
የታደሰ ጂኦስትራቴጂያዊ ቁመና በሁሉም ኢትዮጵያውያን የጋራ ትጋት ሊገነባ እንደሚገባ ተገለፀ፡፡
======================
የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ከፍተኛ አመራሮችና ሰራተኞች "የታደሰ ጂኦስትራቴጂያዊ ቁመና፣ በሁሉም ኢትዮጵያውያን የጋራ ትጋት!!! " በሚል መሪ ቃል የጋራ የምክክር መድረክ አካሄደዋል፡፡

ሰነዱን በማቅረብ መድረኩን የመሩት የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ባይሳ በዳዳ ኢትዮጵያ በአፍሪካ ቀንድ ያላትን ጂኦስትራቴጂካዊ ጠቀሜታ በማጉላት፣ ዓለም አቀፍ ዲፕሎማሲያዊ ግንኙነቷን በማጠናከር፣ ሉአላዊነቷ እና ብሔራዊ ጥቅሟ በማስከበር እና ተፅዕኖ ፈጣሪነቷን በማጎልበት የሀገራዊ ኢኮኖሚ እድገትን ማረጋገጥ እንደሚቻል አስገንዝበዋል፡፡

የኢትዮጵያን የግዛት አንድነት እና የውስጥ ችግሮቻችንን ደረጃ በደረጃ በሰለጠነ መንገድ እየፈታን ሰላማችንን ማስጠበቅ ከቻልን ሀገራችን ወደ ብልፅግና ማማ ለማሸጋገር የሚያዳግተን ምንም ዓይነት ፈተናና እንቅፋት አይኖርም ብለዋል፡፡

የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅምን ማስከበር የአንድ ወገን ኃላፊነት ብቻም ሳይሆን የሁላችንም ኃላፊነት ነው ያሉት ሚኒስትር ዴኤታው በኢትዮጵያ ብሔራዊ ጥቅምና የታደሰ ዓለም አቀፋዊ ስትራቴጂካዊ ቁመናን ከማረጋገጥ አኳያ ከወንድም ጎረቤት ሀገራት ህዝቦች ጋር በአብሮ የማደግ መርህ በጋራ እንደምትሰራም አንስተዋል፡፡

በየዘርፉ የተቋማት ውጤታማና የማይናወጥ የተቋማት ግንባታ ሥራ የምንሠራበት፣ የልማት ትልሞቻችን ከማሳካት ጎን ለጎን እንደ አባቶቻችን በአርበኝነት ስሜት የኢትዮጵያን አንድነትና ብሔራዊ ጥቅም በማስከበር በሀገራችንን እየተመዘገቡ ያሉ ሁለንተናዊ እድገቶችን ለማስቀጠል ሁሉም በተሰማራንበት ሥራ ላይ ውጤታማ ሊሆን እንደሚገባ ተናግረዋል፡፡
ከኢትዮጵያ ጀርባ ላይ ያልወረደው የሁለንተናዊ እድገት መሰናክልና እንቅፋት የሆነው የባዕድ ጣልቃ ገብነት አባዜን ለማስወገድ ሁሉም የድርሻውን ለመወጣት ዝግጁ መሆናቸውን ተሳታፊዎች ጠቁመዋል፡፡

በመድረኩ የብሔራዊ ጥቅም ምንነት እና ጂኦስትራቴጂክ ቁመና፣ የኢኮኖሚ ብልፅግና፣ ፖለቲካዊ አቅምና ተፅዕኖ ፈጣሪነት፣ ሉዓላዊነት፣ የግዛት አንድነትን፣ የባህር በር ጉዳይ፣ ሰላምና ጸጥታን ማረጋገጥ፣ ከፖለቲካ ሀይሎች ጋር ሰላማዊ አማራጭ መከተል፣ የባህል ነፃነት፣ የህዝቦች ማህበራዊ ልማትና ዋስትና የሚሉ ሀሳቦች ተዳሰዋል።
2025/10/18 00:39:14
Back to Top
HTML Embed Code: