Telegram Web Link
በሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር አገራዊ የምርምር ስትራቴጂ እና የትኩረት መስክ ልየታ ሰነድ ማዘጋጀት ተጀመረ
==========================

የምርምር ስትራቴጂ እና የትኩረት መስክ ልየታ ሰነዱ ዝግጅት የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ፣የከፍተኛ ትምህርት፣ የቴክኒክና ሙያ እና የምርምር ተቋማት እንዲሁም ሚኒስቴር መ/ቤቶችና ሌሎች የሚመለከታቸውን ባለድርሻ አካላት በማሳተፍ ወደ ስራ ተገብቷል፡

ሰነዱ ከአገሪቱ የፍኖተ ብልጽግና እቅድ የሚነሳና ለአገሪቱ የኢኮኖሚ እድገት ቁልፍ ድርሻ አላቸው ተብለው ከተለዩ ግብርና፣ ማይንኒግ፣ ቱሪዝም፣ ማኑፋክቸሪንግ እና ከአይሲቲ በተጨማሪ ጤና፣ ሰላም ልማትና ዲፕሎማሲ እንዲሁም ትምህርት ላይ እንደ አገር የምርምር ስራው የሚመራበትን ስልት በመንደፍ እውቀትና ሃብትን በማቀናጀት የምርምር ስራዎች ድግግሞሽ ለምርምር የሚመደብን በጀት ያለብክነት በውጤታማነት ለመጠቀም ያስችላል ተብሏል።

የሰነድ ዝግጅቱ የምርምር ውጤቶች ለተጠቃሚው ህብረተሰብ ተደራሽ እንዲሆኑ በማድረግ የተጠቃሚውን ህብረተሰብ ህይወት እንዲቀየር ከማድረግ ባሻገር ለፖሊሲ ግብዓት የሚሆኑ ምክረ ሀሳቦችን ለመንግስት በማቅረብ ለአገር ኢኮኖሚ እድገት አስተዋጽኦ ማድረግ ታሳቢ ያደረገ ነው ተብሏል፡፡

በፕሮግራሙ ላይ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ዴኤታ ፕ/ር አፈወርቅ ካሱን ጨምሮ ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እና ከፌደራል ቴክኒክና ሙያ ትምህርትና ጤና ኤጀንሲ የመጡ የምርምርና ማህበረሰብ አገልግሎት ምክትል ፕሬዝደንቶች፣ የምርምር ዳይሬክተሮች ተመራማሪዎች ፣ መምህራን ከተለያዩ ሚኒስቴር መ/ቤቶች የመጡ የስራ ኃላፊዎች ተሳታፈዋል።

ሰነዱ ተዘጋጅቶ ሲጠናቀቅ በሚመለከታቸዉ ባለድርሻ አካላትና ምሁራን ተተችቶ በተያዘዉ በጀት ዓመት ወደ ስራ የሚገባ መሆኑን ከሳይንስ ዘርፍ ያገኘነው መረጃ ያመላክታል ።
የግል ከፍተኛ ትምህር ተቋማት የመረጃ አያያዝና ልዉዉጥ ስርአት መሻሻል አለበት ተባለ

==========================

ነሃሴ (21/2013ዓ.ም) የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት በ2014 የትምህርት ዘመን እቅድና የመረጃ አያያዝ ሰርአት ላይ ከግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ባለቤቶችና ባለሃብቶች ጋር በአዲስ አበባ ዉይይት አካሄደዋል፡፡

በዉይይቱ ላይ ተገኝተዉ መልእክት ያስተላለፉት የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ሙሉ ነጋ እንደገለጹት ባለፈዉ አመታት መንግስት ለከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ልዩ ትኩረት በመስጠት የትምህርት ተደራሽነት፣ ጥራትና አግባበነት ለማረጋገጥ ከፍተኛ ስራ ሲሰራ ቆይቷል፡፡ በዚህም በአሁኑ ስአት 278 የግል የከፍተኛ ትምህርት ያሉ ሲሆን ቁጥራቸዉ እያደገ መጥቷል፡፡

በዋናነት የዚህ ዉይይት ዋና አለማ የሰለጠነ የሰዉ ሃይል እጥረትን በመፍታት ሃገራችን ካለችበት ድህነት ማዉጣት ነዉ ያሉት ሚኒስትሩ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር የተለያዩ ፖሊሲዎችን፣ ስትራቴጅችን እና ሪፎርሞችን በመስራት ሲደግፍ ቆይቷል ብለዋል፡፡

የትምህርት ጥራት ወሳኝ በመሆኑ ተጠናክሮ መስራት ያስፈልጋል ያሉት ዶ/ር ሙሉ የምናፈራቸዉ ምሩቃን በገበያ ተፈላጊ፣ የኢኮኖሚዉ አጋዥ ሊሆኑ ይገባል ብለዋል።

የመረጃ ጥራት ችግር፣ የመረጃ ልዉዉጥ እና የትምህርት ማስረጃ አሰጣጥ ችግሮች በግል ከፍተኛ ትምህርት ክፍተቶች መኖራቸዉን ገልጸዉ ይህ 2014ዓ.ም ተቀራርበንና ተግባብተን በመስራት ማስተካከል አለብን ያሉ ሲሆን ጥሩ የሰሩትን ማበረታታት እና ክፍተት የፈጠሩትን ማስተካከል ይገባል ብለዋል፡፡

የትምህርት አላማ ማስተማር፡ ምርምር ማድረግ እና የማህበረሰብ አገልግሎት መስጠት በመሆኑ የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት እንደ ኮቪድ ሁሉ በአረንጓዴ አሻራ፣ በበጎ ፈቃድ በተለይም ደካሞችንን በመርዳት፣ ለመከላከያ ሃይላችን በመለገስ እና በቻልነው በገንዘብና በቁሳቁስ በመደገፍ ለሃገራዊ አጀንዳዎች ምላሽ መስጠት ይገባል ብለዋል፡፡

የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር የከፍተኛ ትምህርት አካዳሚክ ጉዳዮች ጀ/ዳይሬክተር ዶ/ር ኤባ ሚጂና በበኩላቸው በሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ አስተባባሪነት የተሰሩ የክረምት በጎ ፈቃድ ስራ ገለፃ ያደረጉ ሲሆን አክለውም ሃገር የጋራ ናት፣ የህዝብ ናት በመሆኑ በተደራጀ መንገድ መርዳት አለብን ብለዋል፡፡
በአሁኑ ስአት ያለውን ችግር ለመቅረፍ የተፈናቀሉትን በምግብ ፣ በቁሳቁስ መደገፍ ፡ በአረንጓዴ አሻራ የተጀመረውን ስራ አጠናክሮ መቀጠል እና በየአካባቢያችሁ ያሉ አቅመ ደካሞችን ማገዝና መደገፍ ይገባል ብለዋል፡፡

በመድረኩም የግል ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መረጃ አስተዳደር ስርአት በከፍተኛ ትምህርት አግባብነትና ጥራት ኢጀንሲ እንዲሁም የከፍተኛ ትምህርት መረጃ አያያዝ፣መረጃዉን ተደራሽ ማድረግ ለብሄራዊ ፖሊሲና ስትራቴጅ ዝግጅት ወሳኝነትና አስገዳጃነት ሰነዶች በከፍተኛ ትምህርት ስትራጂ ማእከል ቀርቦ ውይይት ተደርጓል፡፡
የትምህርት ጥራት ለማረጋገጥ የከፍተኛ ትምህርት የብቃት ምዘና (Accreditation) ሊያደርጉ ይገባል ተባለ
*************************************************************************************
ነሐሴ (24/2013ዓ.ም) የኢትዮጲያ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የብቃት ምዘና አክሪዲቴሽን ስትራቴጅ ዝግጅት ጉባኤ በሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር እና ከአዳማ ሳይንስና ዩኒቨርስቲ አዘጋጅነት እየተካሄደ ይገኛል፡፡
የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ዶ/ር ሳሙኤል ኡርቃቶ የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ባለፉት ሦስት አመታት የትምህርት ጥራት ለማምጣት በሳይንስ፣ በከፍተኛ ትምህርትና በቴክኒክና ሙያ ስልጠና ልማት ማነቆዎችን በመለየት የሪፎርም ስራዎች ለመሰራት ተሞክሯል ብለዋል፡፡
ከህግ ማእቀፎች አንጻርም ከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ያሰሩናል ያሏቸዉን ፖሊሲና ስትራቴጂዎችን በማዘጋጀት ወደ ስራ መግባቱን ገልጸዉ በተመሳሳይም ተቋማቱን ከአካባቢያቸዉ ጸጋና በተልዕኮ መሰረት ተለይተዉ ወደ ሰራ እንዲገቡ ተደርጓል ብለዋል፡፡
የትምህርት ጥራትን ለማምጣት ቀጣይ የኢትዮጲያ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት የሙያ ብቃት (አክሪዲቴሽን) ስርአት የተማሪዎችና መምህራን የሙያ ብቃትና የሚሰጡ ፕሮግራሞችና መሰረተ ልማቶች ምዘና መስፈርት ወጥቶላቸዉ በገለልተኛ ተቋማት የሚለኩ ይሆናል ነዉ ያሉት ሚኒስትሩ፡፡
አላማዉም በአለም አቀፍ ደረጃ ተወዳዳሪ የሆኑ መምህራንና ተማሪዎችን ለማፍራት፣ ተቋማቱ በገበያ ተፈላጊ የሆኑ ፕሮግራሞችና ተማሪዎች መርጠዉ የሚማሩበት ተቋም ለማድረግ ነዉ፡፡ ስለዚህ የከፍተኛ ትምህርት ተቋማት መሪዎች ሰዉ ሃይል ልማት በተመለከተ በትኩረት ልትሰሩ ይገባል ሲሉ ዶ/ር ሳሙኤል ገልጸዋል፡፡
የኢትዮጲያ ብሄራዊ አክሪዲቴሽን ጽ/ቤት ዋና ዳይሬክተር አቶ አርአያ ፍስሃ በበኩላቸዉ የትምህርት ጥራትን ለማስጠበቅ ከዚህ ቀደም የነበረዉን አሰራር በመተዉ ተቋማቱ መለኪያ መስፈርት ወጥቶላቸዉ በገለልተኛ ተቋማት የሚታዩበት ስርአት መመቻቸቱ ተወዳዳሪ፣ በገበያ ተፈላጊ እና ያሉን ጉድለቶችን በቶሎ እያስተካከሉ የሚሄዱበት እድል ይፈጥራል፡፡ ይህም በቀጣይም እንደሚተገበር አምናለሁ ብለዋል፡፡
የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስቴር ዴኤታ ዶ/ር ሙሉ ነጋ በበኩላቸዉ የከፍተኛ ትምህርት ስርአት ከ80 አመት በላይ ቢያስቆጣርም በርካታ ያልተሻገራቸዉ ችግሮች አሉ እሱም የትምህርተ ጥራትና አግባበነት ነዉ ብለዋል፡፡ የትምህርት ጥራት አስፈላጊነት፣ እስካሁን ለምን አልተፈጸመም እና ምንድነዉ መፍትሄዉ በሚሉ ጉዳዮች ላይ ሰፊ ማብራሪያ ሰጥተዋል፡፡
ከምክክር መድረኩ ጎን ለጎን ለአገር መከላከያ ሰራዊት የደም ልገሳ ፕሮግራም የተካሄደ ሲሆን የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትር ዶ/ር ሳሙኤል ኡርቃቶ፣ ሚኒስቴር ዴኤታ ዶ/ር ሙሉ ነጋን ጨምሮ የሚኒስቴር መስሪያ ቤቱ ሰራተኞች እና ከተሳታፊዎች መካከል በጎ ፈቃደኞች ደም ለግሰዋል።
በጉባኤው የሳይንስና ከፍተኛ ትምህርት ሚኒስትርና ሚኒስትር ዴኤታዎችን ጨምሮ የዩኒቨርሲቲዎች፣ የቴክኒክና ሙያ ተቋማት ሃላፊዎች እና የሚመለከታቸው ባለድርሻዎች ተገኝተዉ በትምህርት ጥራትና ምዘና ፖሊሲና ስትራቴጂ ዙሪያ የተወያዩ ሲሆን ፕሮግራሙ በነገዉ እለት ቀሪ ጉዳዮችን ዳሶ የሚጠናቀቅ ይሆናል፡፡
2025/07/14 21:53:24
Back to Top
HTML Embed Code: