ቀናት ባለፉ ቁጥር በጣም እየተረዳሁ የመጣሁት ነገር ቢኖር፦
በዚህች ምድር ላይ የተረጋጋና የተሻለ ሕይወት እንደሚገባን ነው፡፡
ምቀኝነት የሌለበት፣
ክፋት የሌለበት፣
ሰዉን በክፉ መጠርጠር የሌለበት፣
ቅናትና የዐይን ቅላት የሌለበት፣
መጉዳትም ሆነ መጎዳት የሌለበት፣
መልካምና የተሻለ ሕይወት ይገባናል።
ምን አስበህ ነው ና አስረዳ፣ አብራራ የሌለበት፣
ምን ለማለት ፈልገህ ነው የሌለበት፣
ማሸማቀቅ፣ መረበሽና ማስደንገጥ የሌለበት፣
ጥላቻና ስጋት የሌለበት፣
መጯጯህ መናቆር የለሌበት፣
በየት ወጣህ በየት ገባህ መነዛነዝ የሌለበት፣ ...
ሕይወትና ኑሮ ይገባናል ።
አዎ ዕድሜያችን እያለቀች ነው። በቀሪው የሕይወት ዘመናችን ለኛ ጥሩ ሕይወት ይገባናል፡፡
ሶባሐል ኸይር!
https://www.tg-me.com/MuhammedSeidAbx

እስቲ ለትዳር የምትሆን ጥሩ ልጅ ፈልግ ይላል ያንንም ይሄንንም።
ላንተማ እንዴት ይጠፋል ብለው መርቅነው አብረውት ይፈልጋሉ።
ይቀጥሩታል፣ ያሳዩታል ያያል። ውሳኔ ላይ ወፍ የለም።
ሲያፈላልግ ከአሥር ዓመት በላይ ሆኖታል ብለችሁስ!! ።
እንደ ዕቃ ገዥ መዞር ነው ሥራው።
ያያል ይጠይቃል።
ለመተው ግን ሰበብ አያጣም ።
እንዲያ ነው በቃ ሕይወቱ።
አንዳንዱ መጀንጀን እንጂ ማግባት አይሆንለትም ።
በፕሮሰሱ ኢንተርታይን የሚያደርግ ይመስለኛል ።
አንዳንዴ እንደውም እሺ መባሉን ካየ ደንግጦ ይፈረጥጣል።
ከሰውም የዚህ ዓይነት ሱስ ያለበት ሰው አለ።
ለመግዛት ብሎ ገበያ የሚወጣ አንዳንድ ሰው አጋጥሟችሁ አያውቅም?!።
ሲዞር፣ ሲጠይቅ ውሎ ባዶ እጁን ቤቱ ይመለሳል ።
ነጋዴዎች ፊቱን ለምደውታል።
ሲመጣ ይሄ እንኳን አይገዛም ዝምብሎ ነው የሚጠይቀው ብለው ፊት ይነሱታል ።
እናስ
እናማ
ያንተም ዕጣፈንታ እንደዚያ እንዳይሆን ያሰጋል ።
ከመጠየቅ ብዛት ተለምደህ ይሄ ዝምብሎ በጭባጫ ነገር ነው አያገባም እንዳትባል ፍራ።
በጭባጫ አትሁን ወስን።
ቲ ኢዛ
አልጫ።

Forwarded from Nejashi Printing Press
ሐጅ እና ታሪካዊ ሂደቱ
፨፨፨፨፨፨
ሐጅ (የአላህን ቤት መጎብኘትና ተያያዥ የአምልኮ ተግባራትን መፈፀም) ከነቢዩ ኢብራሂም (ዐ.ሰ.) ጀምሮ የነበረ ወደ አላህ መቃረቢያ የአምልኮ ተግባር ነው።
የአላህ ቤት የምለው በዋናነት ከዕባን ነው፡፡ አላህ ከዕባን በምድር ላይ ለሰዎች መመለሻና የሰላም ቦታ እንዲሆን አደረገው- (የአል-በቀረህ ምዕራፍ ቁጥር 125 )፡፡
ከዕባን ማየትም ሆነ የተቀደሰውን ምድር መጎብኘት እርካታን ይሰጣል። ሐሴትን ያጎናጽፋል።
ነቢዩ ኢብራሂምና ልጃቸው ነቢዩ ኢስማዒል (ዐ.ሰ./የአላህ ሰላም ይስፈንባቸው)፣ ይህንን ቤት ወደዚያ ለሚመላለሱ ሑጃጆች ንጹሕ አድርገው ያዘጋጁ ዘንድ አላህ (ሱ.ወ.) አዘዛቸው። ትእዛዙን የተቀበሉት ሁለቱ ነቢያት በበካ (መካ) ሸለቆ ቀደም ሲል በአላህ መላእክት ተገንብቶ የነበረውን የአላህን ቤት (ከዕባን) መሠረቱን ከፍ እያደረጉ አላህ ይህን መልካም ሥራቸውን እንዲቀበላቸው ዱዓእ አደረጉ። የሰዎች ቀልብም ከዚህ ቤት ጋር የተሳሰረ ይሆን ዘንድም አላህን ተማፀኑ።
ቀጥሎም ሰዎች ይጎበኙት ዘንድ ጥሪ እንዲያደርጉ አላህ አዘዛቸው። ነቢዩ ኢብራሂም (ዐ.ሰ.) ለሐጅ ጥሪ አደረጉ። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ የያኔ ጥሪ ደርሷቸው አቤት ያሉ ነፍሶች ሁሉ አላህ አድሏቸው ወደ መካ ያቀናሉ። ለጥሪው ምላሽ የመሰጠቱ ሂደት እስከ ዕለተ ቂያማ የሚቋረጥ አይደለም። የምእመናን ቀልብ ከመካ ጋር የመተሳሰር ሚስጢሩም ይኸው ይመስላል፡፡ የነቢያት አባት በመባል የሚታወቁት የነቢዩ ኢብራሂም ዱዓ፡፡
ሐጅ የጥንት አምልኮ ነው። ሌሎች ነቢያትም ፈጽመውታል። በአንድ ወቅት የአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ.) ሐጅ ለመሄድ ብለው በመካ አቅጣጫ በሚገኘው በመካና መዲና መካከል ባለ ሸለቆ ውስጥ ሲያልፉ፣ “አቡበክር ሆይ! በዚህ ሸለቆ ሁድና ሳሊሕ የአላህን ቤት ለመጎብኘት ብለው አልፈዋል” ማለታቸው ተወስቷል።
በሌላ ዘገባ ደግሞ አላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ.)፣ “ይህንን ቤት ሰባ ነቢያት ጎብኝተውታል” ብለዋል።
ከዕባን ምድር ላይ የተኖረ የመጀመሪያው የአላህ ቤት ነው። አላህ (ሱ.ወ.) እንዲህ ይላል፡-
«ለሰዎች (መጸለያ) መጀመሪያ የተኖረው ቤት ብሩክና ሲኾን፥ ያ በበካህ (በመካ) ያለው ነው።» (ኣለ ዒምራን፡ 96)
‹በካ› ማለት ለቅሶ ማለት ሲሆን፣ እንዲህ የተባለችው በሷ ውስጥ ለቅሶ ስለሚበዛ ነው ተብሏል።
የመካን ምድር ረግጦና ከተከበረው ከተማ ገብቶ እንባን ለማፍሰስ አለመታደል በርግጥም ዕድለ-ቢስነት ነው!!
የአላህን ቤት ልቅና ከሚያመለክቱ የቁርኣን አንቀጾች መካከል አላህ (ሱ.ወ.) እንዲህ ማለቱ ይጠቀሳል።
ﭽ ﯝ ﯞ ﯟ ﯠ ﯡ ﯢ ﭼ البقرة: ١٢٥
«ቤቱንም ለሰዎች መመለሻና ጸጥተኛ ባደረግን ጊዜ (አስታውስ)።» (አል-በቀረህ፡ 125)
‹መሣበተን› ማለት መመለሻ ማለት ሲሆን፣ በጎበኙት ቁጥር መልሶ ጎብኙኝ የሚል መንፈስ ያለው ነው -ከዕባ። ከዕባን ለመጀመሪያ ጊዜ የሚጎበኝ ሰው ለሷ የሚኖረው ናፍቆትና ጉጉት በእጅጉ ከፍ ያለ ነው።
የአላህ ቤት ምንድነው?
በቀጣይ የምናየው ይሆናል፡…
https://www.tg-me.com/NejashiPP

ሆ ሆ የዘንድሮ ለማኝ ደግሞ እንዴት እንዴት ያረገዋል በረቢ።
ኪሳችን ገብቶ ብራችንን ማለቴ ሳንቲማችንን ሊያወጣ ምን ቀረው።
ባይሆን መጽሐፌ ግዙኝ እኔን።
ሰላም አውለኝ ጌታዬ።
ሶባሐል ኸይር
https://www.tg-me.com/MuhammedSeidAbx
ኪሳችን ገብቶ ብራችንን ማለቴ ሳንቲማችንን ሊያወጣ ምን ቀረው።
ባይሆን መጽሐፌ ግዙኝ እኔን።
ሰላም አውለኝ ጌታዬ።
ሶባሐል ኸይር
https://www.tg-me.com/MuhammedSeidAbx
Forwarded from Nejashi Printing Press
በሐጅ ወቅት በብዛት የምንሰማቸው ቃላቶችና ትርጓሜያቸው
****
1- ኢሕራም፡
ሐጅ ወይም ዑምራ ያሰበ ሰው ለሐጅ/ዑምራ ሥራ የሚለበሰውን ልብስ ከለበሰ በኋላ ኢሕራም ያደርጋል፡፡ ይህም (ለሐጅ/ዑምራ) በቀልቡ መነየት ማለት ነው። ‹ኢሕራም› ቃሉ መክከልከል ማለት ሲሆን፣ አንድ ሐጅ አድራጊ ኢሕራም ከማድረጉ በፊት ይፈቀዱለት የነበሩ ነገሮች የተከለከሉበት መሆኑን ለማሳየት ነው።
2- ተልቢያ ፡
አንድ ሐጅ አድራጊ ለአላህ የሐጅ ጥሪ ምላሽ ለመስጠት ቦታው ድረስ መገኘቱን የሚገልጽበት ቃል ነው፡፡ ቃሉም “ለበይከል-ላሁምመ ለበይክ፣ ለበይከ ላ ሸሪከ ለከ ለበይክ፣ ኢንነል ሐምደ ወን-ኒዕመተ ለከ ወል ሙልክ ላ ሸሪከ ለክ” የሚል ሲሆን ትርጉሙም “አቤቱ አላህ ሆይ! አቤቱ (ጥሪህን ተቀብዬ እዚህ ተገኝቻለሁ)፣ አጋር የለህም፤ አቤቱ ምስጋና የሚገባው ለአንተ ነው፤ ፀጋ ሁሉ የአንተ ነው፤ ንግሥናም የአንተ ነው። አጋር የለህም” ማለት ነው።
3- ከዕባ ፡ በሳዑዲ ዐረቢያ መካ ከተማ የሚገኝ በአራት ማእዘን ቅርጽ የተሠራ የተቀደሰ ቤት ነው። ይህ ቤት “በምድር ላይ የመጀመሪያው የአላህ ቤት” በመባል ይታወቃል። “የአላህ ቤት” የተባለበት ምክንያት አላህ (ሱ.ወ.) የኔ ቤት ብሎ ወደራሱ ስላስጠጋው ነው። ምድር ላይ ያሉ መስጂዶች ጭምር የአላህ ቤት የሚባሉ ስለመሆኑ ግልጽ ነው።
4- መስጂደል ሐራም፡ በዋናነት ከዕባው ዙሪያ የሚገኝ መስጂድ ሲሆን፣ ከዕባን ይዞ አጠቃላዩ “መስጂደል ሐራም” ወይም “ሐረም” በመባል ይታወቃል። ትርጉሙም የተከበረ የተቀደሰ ቦታ እንደማለት ነው። ሐረም ጦርነት እንዳይካሄድ በመከልከል አላህ ለቦታው ክብር ሰጥቷል። እንዲሁም መስጂደል ሐራም በምድር ላይ የመጀመሪያው መስጂድ ነው።
5- ጦዋፍ ፡ ጦዋፍ ማለት ከዕባን መዞር ማለት ነው። ዙሩም ሰባት ሲሆን ከዕባ ወደ ግራ ተትቶ ከሐጀር አል-አስወድ ጀምሮ ነው የሚዞረው፡፡ አንድ ሐጅ አድራጊ ሦስት ጊዜ ጠዋፍ ሊያደርግ ይችላል፡፡ የመጀመርያው መካ ከገባ በኋላ የሚደረግ ሲሆን የመግቢያ ጦዋፍ ይሠኛል፡፡ ሌሎች ሁለት ጦዋፎች የመመለሻ ጠዋፍ (ጦዋፈል ኢፋዷ) የዒድ ቀን ወደ መካ በመመለስ የሚደረግ ሲሆን ሦስተኛ መካን ሲለቁ የሚደረገው የመሠናበቻ ጠዋፎች ናቸው ።
6- ሐጀረል አስወድ ፡ ጥቁሩ ድንጋይ ማለት ነው። ይህ ድንጋይ የተቀመጠው ነቢዩ ኢብራሂም (ዐ.ሰ.) ከዕባን በሚገነቡበት ጊዜ ነበር። ሐጀር አል-አስወድ ከጀነት እንደመጣ እና መጀመርያ ነጭ እንደነበርና ኃጠአት የሠሩ የሰው ልጅ እጆች እንዳጠቆሩት ተዘግቧል፡፡ ሑጃጆች በከዕባ ዙርያ ጦዋፍ ሲያደርጉ ሐጀር አል-አስወድን መሳም ነቢያዊ ፈለግ ነው፡፡ ከዚህ ባለፈ ሐጀር አል-አስወድ በራሱ ጥቅምም ሆነ ጉዳት አለው ተብሎ የሚደረግ ነገር የለም።

Telegram
Nejashi Printing Press
ይህ የነጃሺ ማተሚያ ቤት ኦፊሻል የቴሌግራም ቻናል ነው። የተለያዩ ጠቃሚ መልዕክቶችን፣ አዳዲስ የህትመት ውጤቶቻችንና አገልግሎቶቻችንን ተከታተሉን፣ ለሌላውም ሼር አድርጉ።
Forwarded from Nejashi Printing Press
የነጃሺን መፃሕፍት በዳሽን ሱፐር አፕ ይዘዙ፣ ይግዙ።
**
“ዳሸን ሱፐር አፕ ተጨማሪ ገበያ ይዞ የሚመጣ ነው”
°አብደላ ሰኢድ - የነጃሺ ማተሚያ ቤት ምክትል ስራ አስኪያጅ
ከ30 ዓመታት በላይ ኢስላማዊ መጻሕፍትን በማሳተምና በማሰራጨት የሚታወቀው ነጃሺ ማተሚያ ቤት ዳሸን ሱፐር አፕን ተቀላቀለ፡፡
ዳሸን ሱፐር አፕ እየሰጠ በሚገኘው የኢ-ኮሜርስ አገልግሎት ምርትና አገልግሎታቸውን የሚያቀርቡ በርካታ ተቋማት ዳሸን ሱፐር አፕ ውስጥ መገበያየት ጀምረዋል፡፡
ነጃሺ ማተሚያ ቤትም አሁን ላይ የተለያዩ ይዘት ያላቸውን መጻሕፍት ለተደራሲያን በዳሸን ሱፐር አፕ በኩል ይዞ ቀርቧል፡፡
የማተሚያ ቤቱ ምክትል ስራ አስኪያጅ አቶ አብደላ ሰኢድ ዳሸን ሱፐር አፕ የኢ-ኮሜርስ አገልግሎትን ይዞ መምጣቱ ተጨማሪ የገበያ ዕድል ይፈጥርልናል ብለዋል፡፡ ይህ ዕድል ነጃሺ ማተሚያ ቤት የረጅም ጊዜ ደንበኞቹን በበለጠ ተደራሽ እንዲሆን እንደሚያግዘው ገልጸዋል፡፡
ማተሚያ ቤቱ የቅዱስ ቁርአን የአማርኛና ሌሎች ቋንቋዎች ትርጉም፣ የሐዲስ፣ የታሪክ፣ የፊቂህ፣ የሕጻናት መጻሕፍትና ሌሎችም በእስልምና ዙሪያ የተጻፉ የሕትመት ውጤቶችን ለአንባቢያን እያቀረበ ይገኛል፡፡
አንባቢያን ባሉበት ሆነው በዳሸን ሱፐር አፕ ከነጃሺ ማተሚያ ቤት የሚፈልጉትን መጻሕፍት ማዘዝ እንደሚችሉ የሚያስረዱት አቶ አብደላ የማድረሻ አገልግሎት ማግኘት እንደሚችሉም ጠቁመዋል፡፡
ከአዲስ አበባ ውጭ ያሉ አንባቢያን ዳሸን ሱፐር አፕን ተጠቅመው ከማተሚያ ቤቱ መጻሕፍትን ማዘዝ የሚችሉ ሲሆን ማተሚያ ቤቱ በፖስታ ወይም በፈጣን አገልግሎት(ኢኤምኤስ) በኩል እንደሚልክም አመላክተዋል፡፡

ዋና ዋና የሐጅ ሥራዎች በቅደም ተከተል
1- ኢሕራም
2- የመግቢያ ጦዋፍ
3- በሶፋና መርዋ መካከል መሮጥ
4- ሚና ማደር
5- ዐረፋ መቆም
6- ሙዝደሊፋ ማደር
7- ጠጠር ውርወራ
8- መስዋዕት ማረድ
9- ፀጉር መላጨት ወይም ማሳጠር
10- የመመለሻ ጦዋፍ
11- የሦስቱ ጉድጓዶች ጠጠር ውርወራ
12- የመሠናበቻ ጦዋፍ
https://www.tg-me.com/NejashiPP
1- ኢሕራም
2- የመግቢያ ጦዋፍ
3- በሶፋና መርዋ መካከል መሮጥ
4- ሚና ማደር
5- ዐረፋ መቆም
6- ሙዝደሊፋ ማደር
7- ጠጠር ውርወራ
8- መስዋዕት ማረድ
9- ፀጉር መላጨት ወይም ማሳጠር
10- የመመለሻ ጦዋፍ
11- የሦስቱ ጉድጓዶች ጠጠር ውርወራ
12- የመሠናበቻ ጦዋፍ
https://www.tg-me.com/NejashiPP
Forwarded from Nejashi Printing Press
ከቢስሚከ ነሕያ መጽሐፍ
መውጫ ይሆኑናል ብለን ያሰብናቸው በሮች ሁሉ የተዘጉብን እንደሆነ ወደ _ ‹አል-ወኪል› እንሂድ፡፡ መንጠልጠያ ገመዶች ሲቆረጡ የሰው ልጅ ተስፋም አብሮ ይቆረጣልና ዘወትር በአላህ (ሱ.ወ) ላይ ከመንጠልጠል አንራቅ፡፡
አንዳንድ ጊዜ አላህ (ሱ.ወ) በሆነ መንገድ ውስጥ ያስገባናል፡፡ በዚያ መንገድ ላይ የቻልነውን ሁሉ ካደረግን በኋላ ‹አል-ወኪል› መሆኑን እንረዳ ዘንድ በሩን ይዘጋብናል፡፡ ነብዩ (ሰ.ዐ.ወ) ለደዕዋ ስራ ብለው በእግራቸው ወደ ጣኢፍ አቀኑና በድንጋይ ተደብድበው ተመለሱ፡፡ የሄዱበትን ጉዳይ አላሳኩም፡፡ ሲመለሱ ከዒራቅ የሆነ ዐዳስ የሚባል ሰው አገኛቸውና አመነባቸው፡፡ ከሱ ከተለዩ በኋላ ደግሞ ጅኖች አመኑባቸው፡፡ ቀጥሎም የሆነው የኢስራእ እና ሚዕራጅ ጉዞ ነው:: ኋላም ብዙ ሳይቆዩ አንሷሮች (የመዲና ሰዎች) እስልምናን ተቀበሉ፡፡
የአላህ መልእክተኛ (ሰ.ዐ.ወ) ጣኢፍ እንድትሰልምላቸው ነበር ያሰቡት አላህ (ሱ.ወ) ግን መዲናን መረጠ፡፡ እሳቸው የጣኢፍን ሰዎች ለመቅረብ ሞከሩ፤ አላህ (ሱ.ወ) ግን የዒራቁን ሰው ላከላቸው፡፡ ሰዎችን ለማስለም አስበው ነበር የተንቀሳቀሱት አላህ የፈቀደላቸው ግን ጅኖች ሆኑ፡፡ የምድር ላይ ሰዎችን ተቀባይነት ነበር ያለሙት፤ አላህ በአክብሮ የሰማይ ቤት እንግዳ አደረጋቸው፡፡ ስለሆነም አላህ (ሱ.ወ) የሚያስብልንን አናውቅም፡፡ በሱ በመመካት የቻልነውን ሁሉ መጣር ይኖርብናል፡፡ ድል የሚመጣው ከአላህ (ሱ.ወ) መሆኑ ልናውቅ ይገባል፡፡
ዶ/ር ዐምር ኻሊድ ጽፎት
Muhammed Seid Abx እንደተረጎመው

ነገን መፆም እንዳትረሱ።
ሌሎች እንዲፆሙም አስታውሱ።
ነገን ዱዓ ማድረግ እንዳትረሱ።
በውድ አጀንዳችሁ ዙርያ ዱዓ አድርጉ።
https://www.tg-me.com/MuhammedSeidAbx
ሌሎች እንዲፆሙም አስታውሱ።
ነገን ዱዓ ማድረግ እንዳትረሱ።
በውድ አጀንዳችሁ ዙርያ ዱዓ አድርጉ።
https://www.tg-me.com/MuhammedSeidAbx
አላህ ሆይ
ምህረትህ
ቸርነትህ
በረከትህ
እዝነትህ
ለሁላችንም ይድረስ።
ያ ረብ 🤲
አስታውሱ ወዳጆች ፡
ምርጡ ዱዓ የዐረፋ ቀን ዱዓ ነው።
በዱዓችሁ
https://www.tg-me.com/MuhammedSeidAbx
ምህረትህ
ቸርነትህ
በረከትህ
እዝነትህ
ለሁላችንም ይድረስ።
ያ ረብ 🤲
አስታውሱ ወዳጆች ፡
ምርጡ ዱዓ የዐረፋ ቀን ዱዓ ነው።
በዱዓችሁ
https://www.tg-me.com/MuhammedSeidAbx
41 ኪሜ ርዝመትና ከ6-12 ኪሜ ስፋት ያለው የጋዛ የባህር ሰርጥ ከ2007 ጀምሮ በኢስራኤል ኃይሎች ዝግ ነው፡፡ 17 ዓመቱ፡፡ በዚህም የተነሳ የፈለስጢኗ ጋዛ በባህር፣ በየብስም ሆነ በዐየር ከዓለም መገናኛ የላትም፡፡ ለዚህም ነው ገዛ የምድር ላይ ትልቁ ክፍት እስር ቤት የሚባለው። ይህን ከበባ ለመስበር በነኚህ ዓመታት ከ30 ጊዜ በላይ ሙከራዎች ተደርገዋል፡፡ አንዱም ግን ውጤት አልመጣም፡፡
ትልቁ ሙከራ በቱርኳ “መርመራ” በተባለችው መርከብ የተደረገው ሲሆን 581 በጎ ፈቃደኞች ይዛ ነበር። መርከቧ ገና ወደ ጋዛ ድንበር ሳትደርሰ የአዝራኢል ኃይሎች ጥቃት በመፈፀም ከበጎ ፈቃደኞች የተወሰኑትን በመግደልና ከፊሎቹን በማሰር መርከቧን ከነያዘችው የእርዳታ ጭነት በመውሰድ የዓለም መነጋገርያ የሆነው ነበር፡፡
ሰሞኑን ደግሞ ማድሊን የተሠኘችው ጀልባ ከኢጣሊያ ወደብ 12 የሰብዓዊ መብት ተሟጋች በጎ ፈቃደኞችን ይዛ ከቀናት በፊት ተንቀሳቅሳለች፡፡ ጀልባዋ ሰብዓነት አንግባ ትልቅ ዓላማ፣ የተወሰነ ምግብ እና መድኃኒቶችን ነው የያዘችው፡፡ አዝራኢል ተጓዦቹ ወደዚያ እንዳይጠጉ በተደጋጋሚ ብታስጠነቅቅም ተጓዞቹ በዓላማቸው በመግፋት የሚደርስብንን አደጋ ሁሉ ለመቀበል ዝግጁ ነን ብለዋል፡፡ በዚህ ቻሌንጅ የተሳተፉት ሰዎች የተለያየ አገር ዜግነት ያላቸው ሲሆን 5 የፈረንሳይ፣ 1 የጀርመን፣ 1 የብራዚል፣ 1 የስዊድን፣ 1 የሆላንድ፣ 1 የስፔን፣ 1 የቱርክ፣ 1 የግብጽ አሉበት፡፡ ጀልባዋ አሁን ላይ ወደ ገዛ እየተቃረበች ሲሆን ምሽቱን አሊያም ጠዋት ላይ ከገዛ የውሃ ክልል ትደርሳለች ተብሎ ይጠበቃል፡፡
ጀልባዋ የተሰየመችበት “ማድሊን” የሚለው ሥም በገዛ ባህር በዓሳ ማጥመድ ሥራ ላይ የተሠማራችና በ2023 በወራሪዎቹ ጥቃት ሁሉ ንብረቷን ያጣች ጎበዝ ሴት ነች፡፡
ማድሊን በተለይ ዝምታውን ላበዛው ለሙስሊሙ ዓለም ትልቅ ደወል ነበረች፡፡ ግና ይነቃሉ ተብሎ አይታሰብም፡፡