ነቢዮ ዮሱፍ ከሁለት ወጣቶች ጋር እስር ቤት ገቡ።
ግና ሁለቱም ቀድመዋቸው ወጡ።
ሲወጡ የሱን ነገር ለአለቃቸው እንዲነግሩለት አደራ አላቸው።
እነርሱ ግን ረሱት።
ሓጃዉን ከነርሱ ይልቅ ለአምላካቸው መናገር የነበረባቸው ዩሱፍም ለዓመታት በእስር ቤት ቆዩ።
ቀድመዋቸው ከወጡት አንደኛው አገልጋይ ሆነ።
ሁለተኛው በስቅላት ተገደለ።
ዘግይተው የወጡት ዩሱፍ ግን ከግብጽ ሚኒስቴሮች አንዱ ሆኑ።
እናሳ
እናማ
ያንተ/ያንች ፋይል አልተረሳም።
ጌታህም ረሺ አይደለም።
ጉዳይህ የዘገየው ለምክንያት ሊሆን ይችላል።
በደንብ አብስሎ ሊሰጥህ ይሆናል።
እስቲ አትቸኩል ንጉሥ ትሆን ይሆናል።
ሚኒስቴር ትሆን ይሆናል።
ይቅናህ አቦ ..
ሰባሐል ኸይር !
https://www.tg-me.com/MuhammedSeidAbx

፨ ዱንያ የቱን ያህል ብትወስድባቸዉም ሀብታም የሆኑ ሰዎች አሉ።
፨ ዱንያ የቱን ያህል ብትሠጣቸዉም ድሃ የሆኑ ሰዎች አሉ።
፨ ሀብታም ሆነው ለመኖር ሲሉ የድህነት ኑሮ የሚኖሩ ብዙ አሉ - ይቆጥባሉ አይበሉም አይጠጡም።
፨ መብቃቃት ግዙፍ የማያልቅ ሀብት ነው።
፨ ሀብታምነት የልብ ክብረት ነው፤ የገንዘብ መብዛት አይደለም ።
፨ ድህነትን አትፍሩ። ሞት እንደሚፈልጋችሁ ሁሉ ሲሳያችሁ እንደሚፈልጋችሁ እወቁ። ተብሏልና ።
"አንዳንድ ሰዎች በጣም ድሀ ከመሆናቸው የተነሳ ብር እንጂ ምንም የላቸውም"
https://www.tg-me.com/MuhammedSeidAbx
፨ ዱንያ የቱን ያህል ብትሠጣቸዉም ድሃ የሆኑ ሰዎች አሉ።
፨ ሀብታም ሆነው ለመኖር ሲሉ የድህነት ኑሮ የሚኖሩ ብዙ አሉ - ይቆጥባሉ አይበሉም አይጠጡም።
፨ መብቃቃት ግዙፍ የማያልቅ ሀብት ነው።
፨ ሀብታምነት የልብ ክብረት ነው፤ የገንዘብ መብዛት አይደለም ።
፨ ድህነትን አትፍሩ። ሞት እንደሚፈልጋችሁ ሁሉ ሲሳያችሁ እንደሚፈልጋችሁ እወቁ። ተብሏልና ።
"አንዳንድ ሰዎች በጣም ድሀ ከመሆናቸው የተነሳ ብር እንጂ ምንም የላቸውም"
https://www.tg-me.com/MuhammedSeidAbx
ሰበር
**
ዓለም ሰላም አድራለች ብለን አይናችንን እያሻሸን ከእንቅልፋችን ስንነቃ ለረጅም ጊዜ በስጋት ሲጠበቅ ከነበረው የጦርነት መጀመር ጋር ተነሳን።
ጦርነቱ የዓለምን አቅጣጫና የኃይል አሰላለፍ ከሚወስኑት መካከል አንዱ ነው ተብሎ ይጠበቃል ።
እነሆ ሌሊቱን ከሰዓታት በፊት ኢራን ላይ ላለመጠቃት ቀድሞ የማጥቃት መጠነ ሰፊ ጥቃቴን ጀምሬያለሁ ብላለች ኢስራኢል፡፡
ለዘመቻው “እንደ አንበሳ የሆነ ሕዝብ” የሚል መጠርያ ሰጥቼዋለሁ ያለችው ኢስራኢል፤ ጥቃቱ በዋናነት በተለያዩ የኢራን ከተሞች ውስጥ በሚገኙ የኒውክሌር ማብለያና ማምረቻ ተቋም፣ የረጅም ርቀት የባሊስቲክ ሚሳይል መገኛዎችና ሌሎች ወታደራዊ ተቋማት ላይ፣ እንዲሁም የኢራን የኒውከለር ሳይንቲስቶች ላይ ያነጣጠረ ነው ብላለች፡፡
ጥቃቱን ተከትሎ በኢራን ከተሞች ሌሊቱን ከባባድ ፍንዳታዎች ተሰምተዋል ተብሏል፡፡
አዝራኢል ኢራን የመልሶ ማጥቃት እርምጃ ልትወስድ እንደምትችል እንገምታለን ያለች ሲሆን ለዚህም ለመልሱ ዝግጁ ነን ብሏል የአጥቂዋ ጠቅላይ ሚኒስቴር፡፡
ትናንት የዓለማቀፉ የኒውክለር ፈታሽ ቡድን ኢራን ለሥራችን ሙሉ ተባባሪ ልትሆን አልቻለችም ሲል መግለፁ ይታወሳል፡፡
ኢራን ኒውክለርን የማበለጽገው ለሰላማዊ የኃይል ምንጭ ለመጠቀም ነው ስትል ኢስራኢል፣ አሜሪካና የአካባቢው የዐረብ አገራት ይህን አባባሏን አይቀበሉም፣ የአካባቢውና የዓለም ስጋት ናት ይሏታል፡፡
በጥቃቱ የአብዮታዊ ጦሩ ዋና አዛዥ ሑሴን ሱላሚን ጨምሮ የኢራን ዋና ዋና የጦር አዛዦችና ሳይንቲስቶች መገደላቸው እየተነገረ ሲሆን መረጃው ሙሉ በሙሉ አልተጣራም፡፡
ጥቃቱ የተፈፀመው በርካታ የጦር ጄቶችን በመጠቀም ነው።
አሜሪካ በጥቃቱ እጄ የለበትም ግን እደግፈዋለሁ ያለች ስትሆን ከትናንት ጀምሮ ዜጎቿን ከአካባቢው እያራቀች ነበር፡፡ በአካባቢው የሚገኙ የጦር ሰፈሮቿም በተጠንቀቅ ላይ ናቸው፡፡
የኢራን መልስ በሚቀጥሉት ሰዓታት የሚጠበቅ ይሆናል፡፡
ከዚያም ዓለም እንደተፈራው ትበጠበጥ ይሆን ወይስ ሌላ የምናየው ነው እንግዲህ።

ካንተ የሚፈልጉትን ነገር ባጡ ወይም ባገኙ ጊዜ እንዴት እንደሚቀየሩ እይልኝ ብቻ። ያውም በሚገርም ፍጥነት
https://www.tg-me.com/MuhammedSeidAbx
https://www.tg-me.com/MuhammedSeidAbx
Forwarded from Nejashi Printing Press
ዛሬ በተከፈተውና እስከ ነገ በሚቆየው የአዲስአበባ መስተዳድር ባዘጋጀው ከተማ አቀፍ የኪነጥበብ ፌስታቫል ላይ ተሳትፈናል። መጥተው ይጎብኙን።
https://www.tg-me.com/NejashiPP
https://www.tg-me.com/NejashiPP
ይህ ነው የሆነው ጓዶች፡፡
****
ፍልስጤማውያንን ስንደግፍ ሐማስን የደገፍን ይመስለዋል ከፊሉ ሰው፡፡ እንደዚያ አይደለም ጓዶች፡፡ እኛ ከተበዳዮች ጎን ነው የሆንነው፡፡
የፈለስጢን ምድር ጥንት ጀምሮ የከንዓኖች ነው፡፡ ከነዓን ደግሞ ከዐረብ አያቶች መካከል አንዱ ነው፡፡ ኢስራኢል የምትባል አገር የዛሬ 80 ዓመት እንኳን አልነበረችም፡፡ በ1ኛው የዓለም ጦርነት ጊዜ በዋናነት በጀርመኑ ሂትለርና በአውሮፓ በዚህም በዚያም የተዋከቡት አይሁዳውያን የማስፈርያ ቦታ ተፈለገላቸውና በነብሪታኒያ ሸፍጥ አገረ ፍልስጤም ውስጥ እንዲሠፍሩ ተደረገ፡፡ ጥንትም ጀምሮ በመሠሪነታቸው የሚታወቁት አይሁዳውያን በምዕራባውያን የጦር እገዛ በሂደት እየተስፋፉ ነባሩን የአገሬውን ሕዝብ አፈናቀሉት፡፡ ሂትለር ወዶ አይምሠላችሁ ከነርሱ የሰውነት ሞራ ሳሙና ሠርቷል የሚባለው፡፡ በዚህ መልኩ ኢስራኢል በፍልስጤም ውስጥ እግሯን ተከተለች፡፡
እናም እንዲህ እያለ እያለ 1967 ደረሰ፡፡ የዓለም ህግ የማይገዛትና ከድሮም ጀምሮ ቀድሞ በመምታት የምትታወቀው ኢስራኢል እነ ግብፅን የጦር አውሮፕላኖች ቀድማ በመምታት ሲና ድረስ ዘልቃ ሰፊ ግዛት ተቆጣጠረች፡፡ ኋላ ላይ ግን ከሲና መውጣት እንደ መስፈርት ተደረገና ከግብጽ ጋር የሰላም ስምምነት ተፈራረመች፡፡ ከጆርዳን ጋርም እንዲሁ፡፡ አሁን በምዕራብ በኩል ግብፅ፤ ጆርዳን ደግሞ በምሥራቁ አቅጣጫ የአዝራኢል ዘብ ናቸው፡፡ የጆርዳኑ ደግሞ ይባስ .. በሰሞኑ ቁርቅስ ብዙዎችን አስገርማለች፡፡ ከአዝራኢል ወደ ኢራን የሚሄዱትን የጦር ጀቶች አትነካም፤ ከኢራን ወደ አዝራኢል የሚመጡትን ድሮችና ሚሳይሎች ግን በአየር ክልሌ ቢያልፉ እመታለሁ እያለች ያዙኝ ልቀቁኝ ትላለች፡፡
እና ከ1967 በኋላ በፍልስጤም ትልቁ የመከራ በር ተከፈተ፡፡ 11 ሚሊዮን ከሚገመተው የፈለስጢን ሕዝብ ግማሽ ያህሉ 5 ሚሊዮን የሚሆኑት ወደተለያዩ የጎረቤትና ሌሎች አገራት ተሰደዱ፡፡ በብዙ ሺዎች ተገደሉ፡፡ ሚሊዮኖችም እዚያው ውስጥ ከቀያቸው ተፈናቅለው ገዛና ዌስት ባንክ ላይ ሰፈሩ፡፡
ኢስራኢል በ1948 በምድረ ፍልስጤም ውስጥ ከተመሠረተች በኋላ የፍልስጤም ሕልውና ተሸረሸረ፡፡ እሷ ወደ ቀኝ ገዢነት ስታድግ ለፍልስጤም የራስገዝ አስተዳደር ሠጠቻት፡፡ አባወራ ሆና ባለቤቶቹን ገዛች፡፡ በነኚህ አስተዳደሮች ጭምር ለከተሞችና ለሰፋፊ የሰፈራ ጣቢያዎች ምሥረታ ብላ ፈለስጢንን ምድር ቆራርሳ ጨረሠች፡፡ በወታደራዊ ቴክኖሎጂ ፈርጥማ የተቃወሟትንና ቀና ብሎ ያያትን ሁሉ አሸ ፡ባሪ በማለት ፈጀች። አሁንም ከ10ሺ በላይ እስረኞች በእስር ቤቶቿ አሉ።
ፍልስጤም የተባረከ ምድር ነው፡፡ የሦስቱ ሰማያዊ ሃይምኖቶች የአይሁድ፣ የክርስትና፣ እና የእስልምና ቅዱስ ሥፍራዎች የሚገኙበት ነው፡፡ የመጀመርያው ቂብላ በመባል የሚታወቀው የአል-አቅሷ መስጂድ መገኛው አል-ቁድስ /ኢየሩሳሌም ነው፡፡ ነቢዩ ሶ.ዐ.ወ. ከጂብሪል ጋር ሆነው ወደ ሰማይ ጉዞ ያደረጉት ከዚሁ መስጂድ ነበር፡፡ ቤተልሄም የኢየሱስ ክርስቶስ ዒሳ ዐለይሂ ሰላም የትውልድ ሥፍራ ናት፡፡ በአል-ቅሷ መስጂድ እና ዙርያው በርካታ የአይሁዳውያን ቅርሶችና ቤተመቅደሶች ይገኛሉ፡፡
በ1994 ኢስራኢልና ፍልስጤም በኖርዌይ ኦስሎ የሰላም ስምምነት አድርገው ነበር፡፡ ስምምነቱ ሳይፈፀም ተደራዳሪው ጠቅላይ ሚኒስሯ ይስሐቅ ራቢን በመገደሉ እክል ገጠመው፡፡
በ2005 የታጣቂዎች ዱላ የበዛባት ኢስራኢል የገዛ የሰፈራ ጣቢያዎቿን ነቃቅላ ጦሯንም ይዛ ወጣች፡፡ በ2007 ሐማስ የገዛን ሥልጣን ሲቆጣጠር ገዛ በየብስም በባህርም ከበባ ውስጥ ገባች፡፡ ያለ ኢስራኢል ፈቃድ የሚገባ የሚወጣ አንድም ነገር የለም፡፡ አፈናውና ሰቆቃው የበዛባቸው ሐማሶች በየጊዜው ትናንሽ ሮኬታቸውን መወራወራቸው አልቀረም፡፡ የኢስራኢልም አፀፋ በየጊዜው የከፋ ነበር፡፡
እንዲህ እያለ ይኸው ኦክቶበር 7/2023 ደረሰ፡፡ ሐማስ የድንበር አጥሮችን አፍርሶ ኢስራኤልን ጎዳት፡፡ ብዙ ገደለ፣ በመቶዎች የሚቆጠሩትን አገተ፡፡ ኢስራኢልም ታጋቾቼን በኃይል አስለቅቃለሁ፣ ሐማስንም እንበረከካለሁ ብላ ከባድ የጥቃት ማዕበል ከጀመረች ሁለት ዓመት ሊሆናት ነው፡፡ ገዛ ፈረሠች፣ መሠረተ ልማቶቿ ወደሙ። ከ55 ሺ የሚልቁት ተገደሉ፣ ከመቶ ሺ በላይ የሚሆኑት ቆሰሉ፡፡ ጦርነቱ እንደቀጠለ ነው፡፡
የኢስራኢል ሀሳብ ሐማስ ታጋቾቼን ይልቀቅ፣ ትጥቁንም ይፍታ፣ አመራሮቹም ገዛን ለቀው ይውጡ፣ ይህ ከሆነ ብቻ ጦርነቱን አቁሜ ገዛን ለቅቄ እወጣለሁ የሚል ነው፡፡ ሐማስ ደግሞ ትጥቅ አልፈታም ይላል፡፡ ግና ኢስራኢል ጦርነቱን አቁማ ገዛን ለቃ ከወጣች ታጋቾቹን እለቃለሁ ይላል፡፡ በዚህ እልህ መሀል ነው ጦርነቱ እየቀጠለ ያለው፡፡ ተጎጂውም በአብዛኛው ሰላማዊ ሰው ነው፡፡ ጦርነቱ ከቀጠለና ኢስራኢልም ሙሉ በሙሉ ገዛን ከተቆጣጠረች ታጋቾቹ በሕይወት ይለቀቃሉ የሚል ተስፋ የለም።
የፍልስጤም ኢስራኢል ግጭትን ለማስቆም በርካታ ምክረ ሀሳቦች የቀረቡ ቢሆንም ሁሉም በኢስራኢል ውድቅ ተደርጓል፡፡ ዐረቦች በፖሊስ ብቻ የምትተዳደር መከላከያ አልባ አገረ ፍልስጤም ትመስረት ፤ ላንችም ዕውቅና እንስጥሽ፣ ዲፕሎማሲ ግንኙነታችንም ይጠናከር ብለው ኢስራኢልን ቢማፀኑም ምላሿ በጎ አልሆነም፡፡ ለተበዳይ ፍልስጤም የሚያደሉ ኢስራኢልን የሚኮንኑ በርካታ ውሳኔዎች በተመድ እና በፀጥታው ምክር ቤት ቢተላለፉም በአሜሪካ ተቃውሞ ተፈፃሚ አልሆኑም፡፡
የፍልስጤም ሕዝብ ዐረብ ነው፡፡ ሙስሊምም ክርስቲያንም አለው፡፡ እኛ ሃይማኖታቸው እና ለቅዱስ ሥፍራዎች ብቻ ሳይሆን ተበዳይ ስለሆኑም ጭምር ነው ልባችን የሚያዝንላቸው፡፡ ይህ ለፍልስጤም መንግሥትና አገር መመሥረት ድጋፍ የሚሠጡ ከ150 በላይ የሚሆኑ አገራትም አቋም ነው፡፡ ለዚህም ነው የኢስራኢል ደጋፊ የበደል ደጋፊ ነው የምንለው፡፡ የሆነው ይህ ነው ጓዶች፡፡
ለተጨማሪ ታሪክና መረጃዎች ይህን የስለሺ ቱጂ መጽሐፍ ያንብቡ ።
ነጃሺ ማተሚያ ቤት ያገኙታል።

እውነት ግን ምን ነክቶን ነው?
አንድ ሙስሊም ያልሆነ የብሪታንያ አክቲቪስት በሰሞኑ ጉዞ ወደ ረፈሕ ገዛ ድንበር እንዳያልፉ የከለከሏቸውን የግብፅ ፖሊሶች አሳልፉን፣ በረሀብ ከሚሞቱ ወንድሞቻችሁ ጎን ሁኑ፣ ሰብዓዊነት ይሰማችሁ እያለ እያለቀሰ ሲማፀን።
ሙስሊሞች ምን ነክቷችሁ ነው የንፁህ ቀልብ ባለቤት ነበራችሁ ይላል።
የደረቀን ቀልብ ምን ያለሰልሰዋል ብለሁ ..
አላህ እዝነትን ልብህ ውስጥ ሊያስቀምጥ የግድ ሙስሊም መሆን አይጠበቅብህም።
የሰውየውን የክንድ ንቅሳት እዩልኝ።☝️

ተስፋን ሲያልሙ "ሶባሕ" የሚል ሥም ይሠጧቸዋል ዐረቦች ለልጆቻቸው።
ማለዳ፣ ንጋት እንደማለት ነው።
ሁሉ ነገር ከማለዳ ጋር ይወለዳል። ተስፋ፣ ዕድል፣ በረከት፣ ሲሳይ፣ ስኬት፣ ዕድሜ ...በጠዋት ተነስተን የምናልማቸው፣ የምንጠብቃቸው ናቸው።
የትናንቱን ዉድቀት ለትምህርት ካልሆነ ዝጋበት።
የትናንቱን ህመም ለልምድ ካልሆነ አታንሳው እርሳው።
ዛሬ ሌላ ታሪክ ጀምር።
ስትጀምርም ቢስሚላህ ተወከልቱ ዐለሏህ በል።
ሰባሐል ኸይር
ማለዳችሁ ትባረክ!
https://www.tg-me.com/MuhammedSeidAbx
ማለዳ፣ ንጋት እንደማለት ነው።
ሁሉ ነገር ከማለዳ ጋር ይወለዳል። ተስፋ፣ ዕድል፣ በረከት፣ ሲሳይ፣ ስኬት፣ ዕድሜ ...በጠዋት ተነስተን የምናልማቸው፣ የምንጠብቃቸው ናቸው።
የትናንቱን ዉድቀት ለትምህርት ካልሆነ ዝጋበት።
የትናንቱን ህመም ለልምድ ካልሆነ አታንሳው እርሳው።
ዛሬ ሌላ ታሪክ ጀምር።
ስትጀምርም ቢስሚላህ ተወከልቱ ዐለሏህ በል።
ሰባሐል ኸይር
ማለዳችሁ ትባረክ!
https://www.tg-me.com/MuhammedSeidAbx
በዚህች ምድር ላይ የሰው ልጅ ለራሱ ሊያደርግ ከሚችላቸው ነገሮ መካከል ላለመውደቅ መታገል፣ ከወደቀም ከማንም ሳይጠብቅ ራሱን ማንሳት፣ ከተበታተነም ራሱሱ ሰብስቦ እንደገና መጠንከር፣ ተስፋ ከቆረጠም ራሱን ማገዝና ማበረታታት፣ ሀሳብ የገባዉና የጨለመበት እንደሆነም የራሱ መብራት በገዛ እጁ አበጅቶ ራሱን ችሎ መንቀሳቀስ ናቸው።
ከሰው መጠበቅን ያህል ስንፍና የለም።
ራስን መሸከምን የመሰለ ጉብዝና የለም።
ሶባሐል ኸይር
https://www.tg-me.com/MuhammedSeidAbx
ከሰው መጠበቅን ያህል ስንፍና የለም።
ራስን መሸከምን የመሰለ ጉብዝና የለም።
ሶባሐል ኸይር
https://www.tg-me.com/MuhammedSeidAbx
፨ መንገድ የምታቋርጥን ጉንዳን አትርገጥ፣
፨ ጥሬ የምትለቅምን ወፍ አታስደንግጥ፣
፨ ዉሃ የሚጠጣ ዉሻ አታስበርግግ፣
፨ ርቦት የሚግጥን አህያ/ፈረስ አታስደንብር፣
፨ ተመቻችታ የተኛች ድመት አትቀስቅስ፣
፨ የሸረሪት መኖርያን አታፍርስ፡፡
ይላል ኢስላም፡፡
ሱብሓነከ ረቢ!
እየኖርነው ነው ግን?
https://www.tg-me.com/MuhammedSeidAbx
፨ ጥሬ የምትለቅምን ወፍ አታስደንግጥ፣
፨ ዉሃ የሚጠጣ ዉሻ አታስበርግግ፣
፨ ርቦት የሚግጥን አህያ/ፈረስ አታስደንብር፣
፨ ተመቻችታ የተኛች ድመት አትቀስቅስ፣
፨ የሸረሪት መኖርያን አታፍርስ፡፡
ይላል ኢስላም፡፡
ሱብሓነከ ረቢ!
እየኖርነው ነው ግን?
https://www.tg-me.com/MuhammedSeidAbx
Telegram
ABX
ወደ ቤታችሁ እንኳን መጣችሁ!!
Forwarded from Nejashi Printing Press
ድንቅ አባባሎች
** ‹‹የኢስላም ዋነኛ መርህ የአላህ አንድነት ነው። ʻከአላህ በስተቀር ሌላ አምላክ የለምʼ የሚለው የኢስላምን ጠቅላላ አስተምህሮትና ተግባራት በዋነኝነት አጠቃሎ የያዘ ነገር ነው።›› (ፕሮፌሰር ራማክሪሽና ራኦ /የነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) ማንነት በህንዱ አንደበት ገ/55)
** ‹‹ነጻ የሆነውን የአውሮፓን ሕዝብ ወደ ሃይማኖታችን ለመጥራት ከፈለግን በመጀመሪያ እኛ ሙስሊሞች አለመሆናችንን ልናሳምናቸው ይገባል። ምክንያቱም እነርሱ እኛን በቁርኣን ውስጥ የሚመለከቱት በዚህ መልኩ ነው። ከቁርኣን ጀርባ ድህነት የተስፋፋባቸው፣ የተዋረዱና ሕይወትን የተዉ ሰዎችን ይመለከታሉ። ይህ ቁርኣን ጠቃሚና አስተማሪ ቢሆን ኖሮ፥ ተከታዮቹ እንደምንመለከታቸው አይሆኑም ነበር ይላሉ።›› (ጀማሉዲን አል-አፍጋኒ /አልወሕዩ አልሙሐመዲይ ገ/10)
** ‹‹ጆርጅ በርናርድ ሾው፦ በሚቀጥሉት መቶ ዓመታት ውስጥ ሃይማኖት ወደ እንግሊዝ ብሎም ወደ አውሮፓ መግባት ከቻለ፥ ያ ሃይማኖት ኢስላም ነው ብሏል።›› (ፕሮፌሰር ራማክሪሽና ራኦ /የነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) ማንነት በህንዱ አንደበት ገ/ 22)
** ‹ከዚህች ዓለም ጸጋዎች -ኢስላም፣ ከተግባሮች -አላህን መታዘዝ እና ከመካሪዎች-ሞት ይበቃሃል።›› (ዐሊይ ኢብን አቡ ጣሊብ /የነቢዩ (ሰ.ዐ.ወ) የአጎት ልጅ)
** ‹‹ልብን ከፍጡራን ባርነት ነጻ የሚያደርገው ለአላህ ባሪያ መሆን ብቻ ነው።›› (ዶክተር ዩሱፍ አልቀረዷዊ)
‹‹ወንድሜ ሆይ! ዓለም ምንም ሳትለወጥ ከማንም ጋር እንዳለች አትቆይም። ልቦናህን ሁለንተናዊውን ዓለም ከፈጠረው አምላክ ጋር አቆራኝ።›› (የሰዓድ ጥበቦች)
ዓይነታው ነቢይ ከተሠኘው መጽሐፍ
አዘጋጅ ፡ ኡስታዝ ሙሐመድ ዑመር
ነጃሺ የዕውቀት ማዕድ

ሰውን አታስጠብቁ
****
አንድ ንጉሥ እጅግ ብርዳም በሆነ ምሽት ላይ ወደ ቤተመንግሥቱ ሲገባ ስስ ልብስ ለብሶ ብርድ ላይ ቆሞ የሚለምን አንድ ለማኝ ሽማግሌ አገኘ፡፡
“ምነው አይበርድህም እንዴ!” አለው፡፡
“ይበርደኛል፣ ነገርግን ብርድ የሚከላከል ልብስ የለኝም፡፡” አለው፡፡
ንጉሡም “በል ወፈር ያለ ልብስ በሠራተኛ እልክልሃለሁ” ብሎት ወደ ዉስጥ ገባ፡፡
ሰዉዬዉም በጣም ተደሠተና መጠባበቅ ጀመር፡፡ ንጉሡ ግን እዉስጥ ከገባ በኋላ የገባዉን ቃል ረሳ፡፡
ሲነጋ ሽማግሌው በር ላይ ሞቶ ተገኘ፡፡ በብርድ እየተንቀጠቀጠ የፃፈ የሚመስለው ወረቀት አጠገቡ ነበር፡፡ እንዲህ ይላል፡-
“ንጉሥ ሆይ ብቻዬን ብሆን በቁርጠኝነት ብርዱን እጋፈጠው ነበር፡፡ ነገርግን ልብስ አልክልሃለሁ ብለህ የሠጠኸኝ የተስፋ ቃል ሀሳቤን በተነው፣ ጉልበቴንና ፅናቴን አፍረከረከዉና ገደለኝ፡፡”
አንዳንድ ጊዜ ለሰው የምትገቡት ቃል እናንተ ከምታስቡት በላይ ሊሆን ይችላልና ሰዉን በተስፋና በማስጠበቅ አትግደሉ፡፡
መሳአል ኸይር!