Telegram Web Link
♡ ሙስሊም ነኝ እኔ ♡ | I am Muslim
እኛ ሙስሊሞች የማሪያም እና የኢየሱስ ወዳጅ እንጂ ጠላት አይደለንም!!
በል እንደሁም እኛ ሙስሊሞች ከክርስቲያኖች የበለጠ ማሪያምንና ኢየሱስን እንወዳቸዋለን እናከብራቸዋለን።
ለማንም ብለሺ ሳይሆን ለራስሺ ስትይ ጠንካራ ሁኝ
የራስሺን ህይወት መቀየር እምትችይው ከአላህ በታች
ጠንካራ ሁነሺ አንች ነሺ ስበቦች በማድረስ የምትቀይሪው!!

አንች የራሰሰሺን ህይወት ያልቀየርሺውን
ማን ይቀይርልኛል ብለሺ ታስቢያለሺ!?
የሚቀይርልሺ አንድ አሏህ ነው ከአላህ በታች ስበብ
ሁነሺ የምትቀይሪው ራስሺ ነሺና ጠንካራ ሁኝ
ዱኒያ ለደካሞች ቦታ የላትም።
~አንዳንዴ እኮ አንዳንድ ጊዜ ሐጃዎቻችንን፣ ችግሮቻችንን፣ ድካሞቻችንን፣ህመሞቻችንን ... ሌላው ቀርቶ ደስታዎቻችን ጭምር የማንናገርበት ጊዜ አለ።

ወዳጆቻችን ሆይ ደብቀን ወይም ለናንተ ቦታ አጥተን ሳይሆን እናንተኑ ላለማስቸገር ብለን ነው። እንዴት ሳይነግረን፣ እንዴት ሳንሰማ፣ እንዴት ሳይጠራን፣ እንዴት ሳናውቅ ... ብላችሁ ብትወቅሱ በርግጥ እውነት አላችሁ ። በዚያው ግን መልካም ጠርጥሩ።

ዱንያ የብዙዎችን ዐቅል ይዛለች። ብዙዎችን በውክቢያ ዓለም ውስጥ ከታለች። ለሐዘኑም፣ ለሰርጉም፣ ለዐቂቃውም፣ ለምርቃቱም፣ ለማግባቱም፣ ለህመሙም፣ ለችግሩም ... ሰውን ማስቸገር ደግም ጥሩ አይደለም  የሚል ሀሳብ አለን።

በረካ ሁኑልን።
AbuSufiyan_Albenan
አንዲት ሰለምቴ እህታችን ወላጆቿ በዲኗ ላይ እንድትጠነክር እና ዲኗን እንድትማር እንደሚያግዟት ነገረችኝ። ኒቃቧንም እንድትለብስ እንደሚያበረታቷትም እንደዚሁ ነገረችኝ። መታደል ነው። አላህ ሂዳያውን አድሏቸው ደስታዋን ሙሉ ያድርግላት።

ተመልከቱ እንግዲህ! እዚህ ላይ ሙስሊሞች ያልሆኑ ሰዎች ከጎኗ ሲቆሙ እና ኒቃቧን ሲደግፉ በሌላ በኩል ደግሞ ሙስሊሞች ሆነው ሳለ ሴቶቻቸውን በተሟላ መልኩ ልሰተር ባሉ ልክ ብልግና የፈፀሙ ያህል ቁም ስቅል የሚያሳዩ ወላጆች፣ ወንድሞች፣ ባሎች አሉ። ኒቃብ የሶሐቦቹ የነ ዓኢሻህ፣ የነ አስማእ ልብስ ነው። እንዴት ሙስሊም የሆነ ሰው ይህንን አለባበስ ይዋጋል?! እንዲህ አይነቱ የውስጥ ፈተና ውጭ ላይ ከሌሎች አካላት ከሚገጥመው የበለጠ ያማል። አንደኛ የኔ በምንለው አካል መሆኑ የተለየ ህመም አለው። ሁለተኛ እንደ ውጭ ሰው በቀላል አይገላገሉትም። ንዝንዙ አይጣል ነው። ሰላም ይነሳል። ህይወትን ያከብዳል።

"የጣት ቁስልና - የዘመድ ምቀኛ
እየነዘነዘ - ሌቱን አያስተኛ።"

በንዲህ አይነት የጎን ውጋት ሰላም ያጡ ብዙ እህቶች አሉ። እንዲህ አይነት አጉል ባህሪ የተጠናወታችሁ ወገኖች! እባካችሁን ከዐቅል ሁኑ። ያለ አንድ ተጨባጭ ምክንያት ሰዎች ለኢስላማዊ እሴቶች ጥላቻ እንድታረግዙ ሲያደርጓችሁ እጅ አትስጡ። በተለይ ባል ሆኖ ኒቃብን የሚቃወም ማየት አይደንቅም ወይ? ሚስትህን ሽልማት በሚገባት ተግባሯ ስትፈትናት አታፍርም ወይ?! ልክፍት ነው ይሄ!
=

IbnuMunewor
!!
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
ያኔ በዚያ ዘመን ፈፅሞ የሌለ፡
በድን ላይ ጭማሬ አሁን የታከለ፡
በወህይ አልፀደቀ ነቢ አልተናገሩት፡
መረጃ የሌለው ሶሀቦች ያልሰሩት፡
ከጥመት ቡድኖች በቅርቡ የመጣ፡
በዒድ ተሰይሞ ከመስመር የወጣ፡
▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰▰
መረጃ አልባ ተረት ተራ ዝባዝንኬ፡
ትንሽ ዒድ የሚባል የለውም ታሪኬ፡
አሏህ ይጠብቀን አምላክሽ አምላኬ፡

ሙሉ ነው ኢስላሜ ጭማሬ አያሻውም፡
የሰው ልጂ ፈጠራ አያስፈልገውም፡
ከሁለት ዒዶች ውጭ ትንሽ ዒድ የለውም፡
▱▱▱▱▱▱▱▱▱▱▱▱▱
ትንሽ አይደለንም ትንንሽ የለንም፡
ሀያላን ህዝቦች ነን ትላንትም አሁንም፡
ይህን ፍልስፍና ኢስላም አያውቀውም፡
ትንሽ የሚባል ዒድ ሙስሊሙ የለውም፡

የቢዲዐ ኮተት ሀቅን የለቀቀ፡
ከትንሽ ጭንቅላት አሁን የፈለቀ፡
የሸዋል ፆም እንጂ የሸዋል ዒድ የለም፡
እምነት መረጃ እንጂ ስሜትኮ አይደለም፡
ሙሉ ነው ሲል ያኔ ጌታችን በወዒድ፡
አልፀደቀልንም የለንም ትንሽ ዒድ፡
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
እንደሌለን ሁሉ እንዛዝላ መውሊድ፡
ሶሀቦች ያልሰሩት ዑመር ዑስማን ኻሊድ፡
በቁርዐን በሀዲስ የለንም ትንሽ ዒድ፡
እኛ ትልቅ እንጂ ህፃን አይደለንም፡
አዲስ የተገኘ ትንሽ ዒድ የለንም፡
▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬▬
     
▭▭▭▭▭▭▭▭▭▭
አንዳዴ መናገር እየፈለክ ግን የማትናገራቸው ነገሮች አሉ
በዝምታ ውስጥ ብዙ ጥያቄወች እና መልሶች አሉ
በውስጥህ ደብቀህ በአይኖችህ እያነባህ በልብህ እያዘንክ የምትኖረውም ሂወት ይኖራል
ወደ ጌታህ ዞር በል እና ጉዳይህን ለአዛኙ ንገረው ያኔ እረፍት ታገኛለህ➤🌹
ሰሞኑን በሪያድ ከተማ የተከሰተው የመኪና አደጋ

የ Mercedes እና Lexus መኪና ፊት ለ ፊቴ ተጋጭተው ነበር። አምቡላንስ አየሁ። ከዛም የተሰበሰበ ህዝብ። አንድ ወጣት ልጅ እድሜው 26 አካባቢ የሆነን ከመኪናው ሲያወጡት አየሁ፡፡ ሰውነቱ በደም ተሸፍኗል። አካላቱ ተቆራርጧል። እግሩም ጭምር ተቆርጧል። እና እሱም እየጮኸ ነው"፡፡ ይለናል የታሪኩ ዘጋቢ።

ልጁም ወደ ወንድሙ እየተመለከተ ምናልባትም የቅርብ ቤተሰቡ ይሆናል
"መሞት አልፈልግም። በጣም ፈርቻለሁ እሳት ነው 'ምገባው እኮ" ይለዋል። እዛው ተኝቶም እየጮኸ "ሙሀመድ እኔ 'ኮ አልሰግድም ነበር። ምናልባትም አካል ጉዳተኛ እሆን ይሆናል መሞት ግን አልፈልግም። ከዚህ በኋላ እሰግዳለሁ። ወላሂ እሰግዳለሁ ብቻ ግን መሞት አልፈልግም" ይላል።

ሰዎችም ተሰበሰቡ። እኔም ሁሉንም ክስተት እየተመለከትኩ አዛው ቆምኩ። በጣምም ፈርቻለሁ፡፡ በቦታው ላይ የሚታየው በሙሉ እጅግ በጣም ይዘገንናል፣ ያስፈራል። የልጁም መድማት እየጨመረ መጣ። ጩኸቱም ቀጠለ። ሰውነቱም ወደ ሰማያዊ እየጠቆረ ሄደ። ሊያድኑት ግን አልቻሉም።

አብሮት የነበረውም ልጅ እያለቀሰ “እሺ ሸሃዳ በል! ከሊማዉን በል…በል” ይለዋል። ልጁ ግን እየጮኸ ነበር ምላሱም ከሊማውን ልትል አልቻለችም። ሱብሃነላህ በጣም ፈርቶ ነበር። ነገር ግን ነፍሱም ተወሰደች ድምፁም ተሰወረ። ከሁሉም የሚያሳዝነው ግን ሸሃዳን ምላሱ ለማለት እምቢ ማለቷ ነው። ዚያም አልተንቀሳቀሰም ሰውነቱም ደርቆ ቀረ።

ዶክተሮቹም ያላቸውን መሳሪያ ሁሉ አወጡ። ልጁንም ቃሬዛ ላይ አስቀመጡትና ጭንቅላቱን ሸፈኑት። ወደ ወንድሙም በመዞር “አለቀ” - “ወንድምህ የለም። ዱዓ አድርግለት ልናድነው አልቻልንም። ምክንያቱም ከጭንቅላቱ እና ከሰውነቱ ብዙ ደም ፈሷል” አሉት። ዘጋቢውም ይለናል " በሕይወቴ ለመጀመሪያ ጊዜ ሰው ከፊት ለፊቴ እያየሁት ግን ሸሀዳን ለማለት ሳይችል ሞተ። እህት ወንድሞቼ ሞት ድንገት ነው የሚመጣው። ሰላታችሁን ግን ጠብቁ። በፍፁም ከነገ ጀምሮ እሰግዳለሁ አትበሉ፡፡ ዛሬውኑ መስገድ ጀምሩ። የመጨረሻ ቀናችን መቼ እንደሆነ ማንም አያውቅም። እኔም ከዚህ ክስተት በኋላ መተኛት አልቻልኩም። እንደ ህፃን ሳለቅስ ነበር። ልጁን ባላውቀውም ቃላቶቹን ግን በደንብ አስታዉስ ነበር...”። እሰግዳለሁ፣ወላሂ ከዚህ በኋላ እሰግዳለሁ፣መሞት ግን አልፈልግም...ባለቀ ሰዓት ከንቱ ልፍለፋ ብቻ።”
➧. #የሚያሸልም_ጥያቄ!  ከነብዩ ሙሀመድ (ሰ.ዓ.ወ)  ሞት ቡኋላ  የተቀበረው ነብይ ማነው!?
ውዷ እህቴ!!

ስትራመጅ ከፊትሽ የሚያደናቅፉ ነገሮች አይጠፉም ግን ሊጥሉሽ ብቻ ሳይሆን ሊያነቁሽ ነው  ለምትሄጅባቼው ነገሮች ትኩረት እድሰጭ ነው በህይወትም ላይም  ወደፊት አንድ እርምጃ ስትሄጅ ብዙ እንቅፋቶች የሚገጥሙሽ ስለሰራሽ እና ስለጠነከርሽ  ስለቀደምሻቸው ይሆናል እና እንቅፋቱን እደብርታት ተጠቅመሽ ወደፊት ቀጥይ እንጅ እትቁሚ ።

 
ትልቅነት የሚለካው በምታሳካው ነገር ሳይሆን
በምታልፍቸው ከባባድ መሳናክሎች ነው !
2025/07/04 15:24:39
Back to Top
HTML Embed Code: