Telegram Web Link
አንድ ቀን

ፈገግ ብለን አልሀምዱሊላህ
ይህ ከለመንኩህ በላይ ነዉ ያረብ።

ምንልበትን ቀን አላህ ቅርብ ያድርግልን
👍46🙏7
አንዳንድ ጊዜ አላህ የሚሰጠን
ምንዳ የነፍስ መረጋጋት ነው። ጡምኣኒና።
👍177
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
አንዳ አንዴ ሰውን ለቲኒሽ ጊዜ ከጉዳዪ ጋር ብቻውን ተውት > ከዛም ጉዳዩ ከተረጋጋ በኋላ >ከልብ የመነጨ በሆነ ንግግር አናግሩት
👍11
ከጨለመብን በኋላ ጸሐይ መውጣቷን እስካላቆመች ድረስ፤ ተስፋ የሚቆርጥ ሰው ተስፋ ካስቆረጠው ነገር በኋላ ወደፊት ያለው ነገር ደስታ መሆኑን ይወቅ።

مادامتِ الشمسُ تأتي بعدَ ظُلْمَتِنَا
         فليعلمِ اليأسُ أنَّ القادمَ الفرحُ
👌12👍5
በፅኑ ከምትፈልጉት ነግር ጋር ••••
በጊዜ አሏህ ያገናኛችሁ!!🤲
👍265🔥2
በጌታቹ ደጅ ላይ ለማኝ ሁኑ
ስትቆሙ ልባችሁን እንጂ
ቃላቶችን አታዘጋጁ!!

አሏህ ሁላችንም የልባችን ያሳካልን 🤲🥀
👏15🙏65👍4👌1
የህይወት ትልቁ ትምህርትን የምትማረው በህመም ነው።
15👍10
«من ترك شيئًا لله عَوَّضه الله خيرًا منه»
أبو عبد الله بن خيرو
አዲስ ሙሀደራ ➀


ለአላህ ብሎ የሆነን መጥፎ ነገርን የተወ አላህ ጥሩ የተሻለ ነገርን ይተካዋል

«من ترك شيئًا لله عَوَّضه الله خيرًا منه»

🎙አቡ አብዲላህ «ኢብኑ ኸይሩ»
   
=
https://www.tg-me.com/Sadik_Ibnu_Heyru
«من ترك شيئًا لله عَوَّضه الله خيرًا منه»
أبو عبد الله بن خيرو
አዲስ ሙሀደራ ➁


ለአላህ ብሎ የሆነን መጥፎ ነገርን የተወ አላህ ጥሩ የተሻለ ነገርን ይተካዋል

«من ترك شيئًا لله عَوَّضه الله خيرًا منه»

🎙አቡ አብዲላህ «ኢብኑ ኸይሩ»
   
=
https://www.tg-me.com/Sadik_Ibnu_Heyru
👍8
"ሰላም ያለው በ አልሃምዱሊላህ ውስጥ ነው "

ኢብኑ ሙነወር
👍166
«በሁሉም ነገር ላይ ሶብር (ትእግስት) ይኑርህ።»

ረሱል (ሶለላሁ አለይሂ ወሰለም)
👍238
አብሽር ወዳጄ  ...!

ችግር አንዱ የስኬት አካል ነዉ ።
ካለህበት ይበልጥ ከፍ  ስትል እና ወደ ስኬት ስትቃረብ  ችግርህ በጣም  እየጠነከረ እየገዘፈ ይመጣል ያኔ  ተስፋ  ከመቁረጥ  ይልቅ ችግሮቼን   የማስወግድበት የምቀርፍበት አቅምና  ትእግስት ስጠኝ ብለህ  ጀሊሉን ለምነዉ  አብሽር  ያልፋል ።

=አብሽሩ
👍18
መልካም ብትናገር ታተርፋለህ
ዝም ካልክ ደግሞ ትተርፋለህ_
እንደመጣልህ ካወራህ ትጠፋለህ
12👍5
ሰባት ሰማያትን መፍጠር የቻለው ጌታ ያንቺን ልብ መጠገን ያቅተዋል ብለሽ ታስቢያለሽ?!?!
👏19👍97🔥1
~የትኛውም ዳዒ፣ ታዋቂ፣ አዋቂ(?) የምትሉት ሰው ለሚወዳቸው ሰዎችና እጅግ ለቀረባቸው ሰዎች ካልሆነ በቀር የማይገልጣቸው ቀሽም ባህሪዎች ይኖሩታል። በአደባባይ በቃላቱ፣ በንግግሩ፣ በፅሁፉ መልካም መልካሙን የሚያስታውስ ሁሉ የግላችሁ ብታደርጉት ልባችሁን ደስተኛ የሚያደርገው አይምሰላችሁ። ሰው የሚመስለውን ብቻ ሳይሆን የማይመስለውንም ይመስላል።
ግዴለሽም መልካም ብለሽ ካሰብሸው ሰው ላይ የሚገጥሙሽን ቀሽም ባህሪዎች ለመረዳት ሞክሪ። ግዴለህም ከጠበቅካት ውጪ  የማትገምተው ባህሪ ይኖራታልና ስትገልጠው አትሸበር፣ ሰው ነች። ልብ በሉ ሰው በወደደው በኩል ለመሰበር  እጅጉን ቅርብ ነው። ሰው በሚወደው በኩል እራሱን የሚጠብቅበት ድንበር ልል ነው። ሰው በሚወደው በኩል ጥንካሬው ሊከዳው እጅጉን ቅርብ ነው።
=AbuSufiyan_Albenan
👍8
ሸይኽ ፈውዛን - አላህ ከክፉ ይጠብቃቸውና - ዒልም ፈላጊ ተማሪዎችን ሲመክሩ እንዲህ ይላሉ፦

እውቀትን ከመፈለግ አትሰልች።
አያያዝህ ትንሽ ቢሆን እንኳ እውቀትን ፈልግ።
መልካም ስራ ከመስራት ጋር ሲሆን ትንሹም በረካ አለበት።
እውቀት ፍለጋ ላይ መቀጠል ያለጥርጥር ኸይር ነው።
እውቀት ፍለጋ ዒባዳ ነው።
እውቀት ፍለጋ ግዴታ ካልሆኑ ዒባዳዎች የበለጠ ነው።"

[አልኢጃባቱል ሙሃማህ፡ 84]
=

IbnuMunewor
👍2
የኛ ዉድ ነቢይ ጨረቃን የሚያስንቅ ውበት የታደሉ ነበሩ ❤️🤌
    ᷂اللهمُ ᷂صل ᷂وسلِم ᷂على ᷂نبيّنا ᷂مُحمدﷺ.
ኸሚስ 💚
28👍3
ነገሮች የፈለገውን ያክል ተስፋ አስቆራጭ ቢመስሉም መቼም ቢሆን ከአላህ እዝነት ተስፋ መቁረጥ አይገባም

ከጠማማዎችም በስተቀር ከጌታው እዝነት ተስፋን የሚቆርጥ ማነው አለ
አላህ በዛቱ ከዐርሽ በላይ ቢሆንም የባሮቹን ሁኔታ በማወቅ የራሱን ወዳጆች በመርዳት ከማንም ከምንም በላይ ቅርብ ነው
7👍2
ምርጥ ተውበት !

የ ታላቁ አሊም ማሊክ ኢብን ዲናር የተውበት ታሪክ 🍃

 ማሊክ ኢብን ዲናር ህይወታቸውን በስካር በመጠጥ ነበር የጀመሩት፣ከዛም በአንድ ግዜ አግብተው ልጅ መውለድ ተመኙ አናም አገቡም አላህ 1ሴት ልጅ ሰጣቸው ስሟንም ፋጢማ አሏት። የዛኔ ልባቸው ወደ ኢማን እየተቃረበ መጣ ውጪ ይጠጡ የነበረውን ቤት መጠጣት ጀመሩ። ፋጢማንም ጭናቸው ላይ አድርገው ነበር የሚጠጡት፣አንድ ቀን ፋጢማ በ2 አመቷ እያለ መጠጡን ገፍታ ደፋችባቸው የዛኔ ይህ አላህ በፋጢማ ተው እያለኝ ነው ብለው አሰቡ፣ ከአመት በኃላም ፋጢማ 3አመት ሞላት ከዛም ፋጢማ ሞተች። ከዛም ድጋሚ እንደበፊቱ መጠጣት መስከር ጀመሩ፣ ታዲያ አንድ ቀን ሸይጧን ወሰወሰኝ አሉ ዛሬ ሰክረኸው የማታውቀውን ስካር ነው የምትሰከረው አለኝ እሺ ብየ መጠጥ መጠጣት ጀመርኩ በጣም ሰከሬ ወደኩ አሉ ። ከዚያም በህልሜ ቂያማ የቆመ መሰለኝ ፀሀይቱ ጠቁራለች፣ ሰወ ሁሉ አላህ ፊት ተሰብስቧል፣ባህሩ ይነዳል የሰው ሁላ ስም ሲጠራ ቆየና ማሊክ ኢብኑ ዲናር ና ለሂሳብ ትፈለጋለህ ተባልኩ ከዛም ትልቅ ዘንዶ ማሳደድ ጀመረኝ እሱን  ለመሸሽ ሰሮጥ አንድ ሽማግሌ አገኙሁ አግዘኝም አልኩት እኔ አቅሜ ደካማ ነው አለኝ ሰሮጥ የእሳት ጫፍ ላይ ደረስኩ፣ ዘንዶውን ፈርቼማ አሳት አልገባም ብየ ተመልሼ ሮጥኩ ድጋሚም ሽማግሌውን አገኙሁት አግዘኝም አልኩት አቅሜ ደካማ ነው እስቲ የምትድን ከሆነ ወደዛ ተራራ ሩጥ አለኝ። ከዚህም እየሮጥኩ እያለ  ከተራራው ላይ ህፃኖች ፋጢማ አባትሽን ዘንዶ ሊበላው ነው ሲሉ ሰማሁ ። ለካ በ 3 አመቷ የሞተች ልጅ አለችኝ ብየ ወደ ፋጢማ ሮጥኩ ፋጢማም ዘንዶውን ገፍታ ጣለችው። እኔም ልጄ ሆይ እስቲ ያ ዘንዶ ምንድነው የሚያባረኝ አልኳት እሷም ያ መጥፎ ስራህ ነው አለችኝ እሺ ያ ሽማግሌውስ ያ ጥሩ ስራህ ነው አለችኝ ጥሩ ስራህ ደካማ ሰለሆነ ከመጥፎ ስራህ ሊያስጥልህ አልቻለም አለችኝ። ከዛም 1የቁርአን አያ ቀራችልኝ።

"እነዛ ምእመናን ልባቸው ለአላህ ግሳፄ የሚፈራበት ግዜ አልደረሰምን?" የሚለውን አነበበችልኝ ። ልክ አኔም ከእንቅልፌ አዎ ግዜው ደርሷል አያልኩ እያለቀስኩ ተነሳሁ ሻወር ወሰድኩ ሱብሂ ወደ መስጂድም ሄድኩ። መስጂድም ኢማሙ ይህንኑ አያ እየቀሩት ነበር አልቅሼ ተመለስኩ ይሉናል ታላቁ ኢማም።

እኝህ ሰው ህዝቡን የሚያስተምሩ ታላቅ ኢማም ሆኑ። ሁሌም መስጂድ አንተ አላህን ያመፅክ ባሪያ ሆይ ወደ ጌታህ ተመለስ ይሉ ነበር።

ጌታችን ሆይ ምህረትህን ለግስን 🤲

‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌‌┄┅┅┄┅✶🌹✶┅┄┅┅┄
= FKR_ESKE_JENET
10👍10👏1
2025/07/13 16:51:14
Back to Top
HTML Embed Code: