Telegram Web Link
የቁርአን_መርሀ_ግብር.pdf
2.1 MB
በረመዳን ቁርዓንን ለማኽተም የሚረዱ ፕሮግራሞች።


SHARE አርጉት
ረመዷን የተባረከ ወር 🌙መጣላችሁ
ረሱል ሶለሏሁ ዓለይሂ ወሰለም
❪ إِنَّ اللَّهَ وَمَلائِكَتَهُ يُصَلُّونَ عَلَى النَّبِيِّ يَا أَيُّهَا الَّذِينَ آمَنُوا صَلُّوا عَلَيْهِ وَسَلِّمُوا تَسْلِيمًا ❫

" اَللَّهُمَّ صَلِّ علىٰ نَبِيِّنَا مُحَمَّدٍ وَعَلىٰ آلِهِ وَصَحْبِهِ وَسَلِّمْ "
አልሐምዱ ሊላህ! ሸዕባን አጠናቀናል። ቅዳሜ ረመዷን 1 ነው። ምሽቱን ተራዊሕ እንጀምራለን።
Please open Telegram to view this post
VIEW IN TELEGRAM
ماجد الحازمي
{ شَهْرُ رَمَضَانَ الَّذِي أُنْزِلَ فِيهِ الْقُرْآنُ هُدًى لِلنَّاسِ وَبَيِّنَاتٍ مِنَ الْهُدَى وَالْفُرْقَانِ فَمَنْ شَهِدَ مِنْكُمُ الشَّهْرَ فَلْيَصُمْهُ وَمَنْ كَانَ مَرِيضًا أَوْ عَلَى سَفَرٍ فَعِدَّةٌ مِنْ أَيَّامٍ أُخَرَ يُرِيدُ اللَّهُ بِكُمُ الْيُسْرَ وَلَا يُرِيدُ بِكُمُ الْعُسْرَ وَلِتُكْمِلُوا الْعِدَّةَ وَلِتُكَبِّرُوا اللَّهَ عَلَى مَا هَدَاكُمْ وَلَعَلَّكُمْ تَشْكُرُونَ }

=
🔖የማይሰግድ ሰው የሚፃመው ፃም ተቀባይነት የለውም። የውመል ቂያማ ሊጠቅመው አይችልም። መጀመርያ ስገድ ከዛ ፁም ይባላል።
በፆም ወቅት ጁኑብ መሆን
~
1- መብላት መጠጣት በሚፈቀድበት የሌሊቱ ክፍል ላይ ሐላል ግንኙነት የተፈቀደ መሆኑ ግልፅ ነው። አላህ እንዲህ ይላል:-
{ أُحِلَّ لَكُمۡ لَیۡلَةَ ٱلصِّیَامِ ٱلرَّفَثُ إِلَىٰ نِسَاۤئكُمۡۚ }
"በፆም ሌሊት ወደ ሴቶቻችሁ መድረስ ለናንተ ተፈቀደላችሁ።" [አልበቀረህ: 187]

2- በሌሊቱ ክፍል ጁኑብ ሆኖ ሳለ ሳይታጠብ የፈጅር ወቅት ቢገባ ፆሙ ላይ ችግር የለውም። እናታችን ዓኢሻህ - ረዲየላሁ ዐንሃ - እንዲህ ትላለች፦
كَانَ رسول الله صلى الله عليه وسلم يُدْرِكُهُ الفَجْرُ وَهُوَ جُنُبٌ مِنْ أَهْلِهِ، ثُمَّ يَغْتَسِلُ وَيَصُومُ.
"የአላህ መልእክተኛ ﷺ ከባለቤታቸው ጀናብተኛ ሆነው የፈጅር ወቅት ይደርስባቸው ነበር። ከዚያ ታጥበው ፆማቸውን ይቀጥላሉ።" [አልቡኻሪይ እና ሙስሊም]

3- በቀኑ ክፍለ ጊዜ ተኝቶ ኢሕቲላም በመሆኑ ጀናባ የገጠመው ሰው ፆሙ ላይ ተፅእኖ የለውም። ምክንያቱም እንቅልፍ ላይ ያለ ሰው እስከሚነቃ ድረስ ተጠያቂነት የለበትምና። በኢስላም ማንም ቢሆን ከአቅሙ ውጭ በሆነ በማይችለው ነገር አይጠየቅም። አላህ እንዲህ ይላል፦
{لَا يُكَلِّفُ اللَّهُ نَفْسًا إِلَّا وُسْعَهَا}
"አላህ ነፍስን የችሎታዋን እንጂ አያስገድዳትም።" [አልበቀራህ: 286]
ነብዩም ﷺ መፆም ያሰበ ሆኖ ሳለ ጀናባ ሆኖ እንደሚነጋበት ለነገራቸው ሰው እሳቸውንም እንደሚገጥማቸውና ፆሙ ላይ ችግር እንደሌለበት ነግረውታል። [ሙስሊም ዘግበውታል።]

4- በቀኑ ክፍለ ጊዜ ከቀጥታ ግንኙነት ውጭ ባለ መንገድ ራሱን በማርካት (ኢስቲምናእ በማድረግ) ጁኑብ የሆነ ሰው አብዛኞቹ ዑለማእ ዘንድ ፆሙ ተበላሽቷል። ፆሙ እንደማይበላሽ የገለፁ ቢኖሩም ራስን ከውዝግብ ማራቅ የተወደደ ነው።

5- በቀኑ ክፍለ ጊዜ ቀጥታ ግንኙነት የፈፀመ ሰው ፆሙ ይበላሻል። ከዚያም ባሻገር ለጥፋቱ ጥብቅ ማካካሻ ይጠበቅበታል።
በህይወታችን #ትልቁ ድክመት ተስፋ መቁረጥ ነው። ህይወት ሁሌም የትግል መድረክ ናት!  ተስፋ ያልቆረጠ የትግሉን መድረክ ያሸንፋል ።
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
በዚህ ስዓት ሙተዘዊጆች ከሚስቶቻቸው ጋር በሳቅ በጨዋታ በደስታ እየቧረቁ  ያፈጥራሉ ላጣዎች ደግሞ ብቻቸውን አፍጠዋል አለያም በየ ሻይ ቤቱ ባክነዋል አይ ልዩነት!

አላህ ይስጣችሁ ምን ይባላል ሌላ¡
የምትፈልጊው የምትመኝውን ነገር ሁሉ ይሳካልሻል!

➷ሊዘገይ ይችላል እንጅ በርግጠኝነት ህልምሽ እውን ይሆናል፣ አሏህ ልብሽን ይጠግነዋል፣ በተሻለ ሁኔታ እና ግዜ ያስደስትሻል።

➷በዚህ መልኩ ይሆናል ብለሽ ባልገመትሽው መንገድ ያሳካልሻል፣
ካንች የሚፈልገው በእምነት ወደህልምሽ  በትዕግስት መጓዝ ነው።
አህባቢ እያስተዋላቹ ነው ግን...? እንደቀልድ 4 የረመዷንን ቀናቶች አሳለፍን..? ምን ያክል ሰርተንበታል ምን ያክል ተጠቅመንበታል ወይ ከረመዳንም በፊት የነበረው አህዋላችን እንዳለው ነው...ከምግብ ብቻ ተቆጥበን..? ..

እ ?? እንዴት ነን ???
በዱዓህ ምክንያት አላህ ነገሮችን እንዴት እንደሚገለባብጥ በቅርቡ ታያለህ። በርትተህ ዱዓ አድርግ።

=
🛑👉ቁርአን የት ደረስክ? ስንቴ አኸተምክ? ይህ የብዙዎቻችን ጥያቄ ነው። አንዴ ወይም ሁለቴ አኸተምኩ አልያም እዚያ ቦታ ደረስኩ እያልን ለሰዎች የምናሳውቅበት አጋጣሚ ብዙ ነው። ኢህላሳችን ሙሉ ይሆን ዘንድ ስራችንን እንደብቅ። ነፍስያ አስቸጋሪ ናት። መደነቅ መወደስ ጀግና መባል ትፈልጋለች። ያ ስሜት ኢህላሳችን እንዳያበላሸው መጠንቀቅ ያስፈልጋል። ኢብራሂም አነኸእይ እየቀራ ሰው ከገባ እስኪወጣ ይዘጋው ነበር። ሰውን ለማበረታታት አስፈላጊ ሆኖ ካልተገኘ በስተቀር ስራችንን ለሰው አናውራ። ለማበረታታት ከሆነም ሌላ ብዙ መንገድ ስላለ ስራህ መናገሩ የግድ አይደለም። ወንጀላችን ከምንደብቀው በላይ መልካም ስራችን እንደብቅ።

      
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
በጣም መንገብገብ፣ በጣም ክፍት መሆን፣ በጣም ራስን መስጠት ብዙ ጊዜ በጣም ያዋርዳል። ሁለተኛ ሰው ወይም አማራጭ የሚታይበት ሰው ያስደርጋል። ሁሉንም ነገር ሰጥቶ አንድ ነገር እንዲሰጡት የሚለምን አይነት ሰው ያስደርጋል። ሰዎች ያልተዘጋጁበትና ያላሰቡት ዓይነት ቦታ ስትመጣላቸው ይኮራሉ። በእጅ ያለወርቅ እንደመዳብ የሚሉትን ዓይነት እንዲሆኑ እናደርጋቸዋለን… በራሳችን እጅ። አንዳንዴ "አይመቸኝም" ያስፈልጋል። አንዳንዴ "ፈልገው ይደውሉ" ብሎ መተውም ያስፈልጋል። … ሲመስለኝ።
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ለሴቶች
~
1. የወር አበባ ከመጣ በኋላ ፆምን መቀጠል ትርጉም የለውም፡፡ አንዳንድ ሴቶች ፆም ይዘው ቀኑን ካጋመሱ በኋላ የወር አበባ ሲመጣባቸው ደክሜበታለሁ ብለው ይቀጥላሉ፡፡ ይሄ አጉል ልፋት ነው፡፡ የወር አበባ ላይ ያለች ሴት በኢጅማዕ ፆም አይፈቀድላትም፡፡ ይልቁንም በዚያው ቁጥር ልክ ቀዷእ ታወጣለች፡፡ ፈላጎቷ ከሆነ ወሩን ሳታቋርጥ ለመፆም እንድትችል የወር አበባ የሚያስቆም መድሃኒት መውሰድ ትችላለች። ጉዳት የማያደርስባት ከሆነ ነው ታዲያ።

2. አንዳንድ ሴቶች የወር አበባ ስሜት ስለተሰማቸው ብቻ ደም ሳያዩ ፆማቸውን ማፍረሳቸው ስህተት ነው። የወር አበባ በታወቀ ጊዜ የሚመጣ የታወቀ የደም አይነት ነው፡፡ ኢብኑ ጁረይጅ ረሒመሁላህ፡ “በወር አበባዋ ቀናት ከደሙ ቀደም ብሎ የምታየው ዳለቻ ወይም ውሃ ፈሳሽ የወር አበባ ነውን?” ብየ ዐጣእን ጠየቅኳቸው ይላሉ፡፡ እሳቸውም፡ “በጭራሽ! ደሙን እስከምታይ ድረስ ሶላት እንዳትተው፡፡ ከሶላት ሊያግዳት የሚያስብ ሸይ ~ጣን እንዳይሆን እፈራለሁ” አሉ። [ሙሶነፍ ዐብዲረዛቅ፡ 1160]

3. አንዳንድ የወለዱ ሴቶች ደም ከቆመላቸው በኋላ አርባ ቀን አልሞላንም ብለው አይሰግዱም፡፡ ይሄ ስህተት ነው፡፡ ኢማሙ ቲርሚዚይ ረሒመሁላህ እንዲህ ይላሉ፡- “የነብዩ ﷺ ሶሐቦች፣ ታቢዕዮችና ከነሱም በኋላ ያሉ ምሁራን የወሊድ ደም ላይ ያሉ ሴቶች ለአርባ ቀናት እንደማይሰግዱ ተስማምተዋል፡፡ ከዚህ በፊት የጠራች ካልሆነች በስተቀር። በዚህን ጊዜ (ከአርባ በፊት ከጠራች) ታጥባ ትሰግዳለች፡፡” [ጃሚዑ ቲርሚዚይ፡ 1/258]

ስለዚህ ከአርባ ቀን በፊት ከጠራች ሶላት መስገድ ይኖርባታል። ፆሙን በተመለከተ እሷ ላይ ወይም ልጇ ላይ ጉዳይ ከሌለውና ካልከበዳት ብቻ ትፆማለች።

4. ሌላው ሴቶች ትኩረት ሊሰጡት የሚገባው ነገር የወር አበባ እና የወሊድ ደም ላይ ሲሆኑ “ፆም አልያዝንም” ብለው ወሩን ከመልካም ስራ ሊዘናኑ አይገባም። የተከለከሉት ፆምና ሶላት ነው፡፡ ስለዚህ ቁርኣን ማዳመጥ፣ ዒልም መማር፣ ዚያራ፣ ሶደቃ፣ ልጆቻቸውን እንዲፆሙ፣ እንዲሰግዱ፣ ቁርኣን እንዲቀሩ ማበረታታት፣ ቤተሰብና ዘመድ ጋር መጠያየቅ፣ ባጠቃላይ ሌሎች ኸይር ስራዎችን በመስራት በረመዳን በተለየ የሚገኘውን ምንዳ ለማግኘት ሊጥሩ ይገባል፡፡ ለቤተሰባቸው የሚያዘጋጁት የሰሑር እና የፊጥራ መስተንግዶ ራሱ ትልቅ ዒባዳ ነው።

5. በረመዳን ወር ቀን ላይ ከወር አበባ የጠራች ሴት ቀሪውን የቀኑን ክፍል ከሚያስፈጥር ነገር የመቆጠብ ግዴታ የለበትም። መብላት መጠጣት ትችላለች።

IbnuMunewor
2025/07/04 15:47:24
Back to Top
HTML Embed Code: