Telegram Web Link
የከተራ ዕለት አመሻሹን የቀሩ ምስሎች ናቸው።

ጌታችን መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዮሐንስ እጅ ሊጠመቅ ወደ ዮርዳኖስ ወረደ። ይኽን ለማመልከት ካህናቱ ታቦታቱን አክብረው ወደ ባሕረ ጥምቀት ይወርዳሉ።

የምስሎቹ ብዛት በዕለቱ ቀን ቁጥር የኾነ ነው።

ጥር ፲ ፡ ፳፻፲፬ ዓ.ም
አዲስአበባ,ኢትዮጵያ
ሚኪያስ ልየው/Mikiyas Liyew
ጥምቀተ ባህሩ ላይ ከአዕምሮዬ አልጠፋብህ ያለኝ የህፃናቱ ስሜት ነው።

ብቻልኩት ይኸው ተመልከቱት።

@Mykeyonthestreet
የዚህን አይነት መታደል አገኝ ከኾነ ብዬ ነው በየመንገዱ ላይ የምማስነው ...
 
ከገጠሪቷ የኢትዮጵያ ቦታዎች ለተለያየ ጉዳያቸው ወደ መሐል ከተማ የሚመጡ ሰዎች ስነ-ባህርይ ግርም፣ድንቅ ነው የሚለኝ።

እኚኽ ሰው አቶ ሞገስ ይባላሉ። መንገደኛ ናቸው። ''በአትኩሮት ስመለከትዎ እንደው ሁሉ ነገሮ ደስ ነው ያለኝ'' ብዬ በድፍረት ሄጄ ብነግራቸው ፥ አቤት ያሳዩኝ ፈገግታ...! እውነት ለመናገር እንደተመለከትኩት አይነት ፈገግታ የከተማ መንገድ ላይ በቅርብ ያገኘሁበትን አላስታውስም።

የከተማ ሰው እንዳልኾኑ እና ከተማ ከሚገኝ ደጀ ሰላም የቂርቆስ በዓለ ንግስ ለማክበር ከክፍለ ሀገር እንደመጡ ፤ ያረፉትም ዘመድ ጋር እንደኾነ በወፍ በረር ነገሩኝ።
እኔ የጠየኳቸው አንድ ጥያቄ ነበረ! የከተማ ሰው ነዎት ወይ? ከላይ የፃፍኩትን ነው የመለሱልኝ። አስቡት! ያለ የዛን ቀን አይተውኝም አያውቁም።

ኧረ ወገን እኛ እንዴት ነው የኖርነው!? 🤔

ምን እንደገባኝ ልፃፍማ ፥ በመንገድ ላይም ኾነ በማንኛውም ቦታ የቦታው ሁናቴ ምቹ ከኾነ ፥ ያለ የዛን ቀን አይተነው ከማናውቀው ሰው ጋር መግባባት ፣ ማውራት ፣ ኀሣብ እና ፈገግታ መለዋወጥ በብዛት ሁለቱንም ፤ ካልኾነ ግን ወይ እኛ ራሳችንን ወይ ደግሞ ያወራነውን ሰው እንዴት ''ደስ'' አስብሎ እንደሚያስገኝ ብታውቁ።

 እኔ እድለኛ ኾኜ በቅርብ ከመንገዴ የተረዳኹት ይኽን ነው።

I wonder around the streets hoping that i would be lucky enough to encounter an occasion of such kind

I always get astounded and astonished by the etiquette of people residing in the rural area who come to undertake tasks of different kind

This man’s name is Mr. Moges. This man is a traveler.

I summoned my courage and initiated the conversation. “The more I consider you, the more your disposition pleases me.” I began. In response, He produced such a smile as I had never seen on the city roads in recent memory. A lively conversation ensued after our introduction. He informed me that he wasn’t a city-dweller and had come to the city to partake in the ceremony commemorating the martyr Kirkos at “Deje Selam” (or “The Threshold of Peace” in its literal English translation). At the time, he told me that he was staying with his relatives.

I had made just a single remark followed by a simple question “Are you from around here?”. Consider it. We made acquaintances that day and, on the selfsame day, he had divulged the above information regarding himself. How are we, the city-dwellers, living? Can we converse with people we don’t know prior, let alone, understanding each-other and exchanging personal details? How about exchanging a laugh or a simple smile? If not though, it is worth considering how our engagement would please ourselves and those who we communicate with.

I reckon myself lucky to have learnt this on my recent journey.

ሚኪያስ ልየው/Mikiyas Liyew
አዲስ አበባ,ኢትዮጵያ
ጥር ፲፯/፳፻፲፬ ዓ.ም

#Ethiopia #Addisabeba #Totravlers #ወደመንገደኞች #Selfproject
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
| ንሸጣ (Inspiration) Se.፩/Ep.፪ •ጥር ፲፰|፳፻፲፬•|

•የንሸጣው ማብራሪያ ከ ሙሉ የመንገደኛው ውጥን ጽሁፍ ተቀንጭቦ የተወሰደ
በእንግሊዝኛ እና በአማርኛ•

I wonder around the streets hoping that i would be lucky enough to encounter an occasion of such kind

I always get astounded and astonished by the etiquette of people residing in the rural area who come to undertake tasks of different kind

This man’s name is Mr. Moges. This man is a traveler.
———-
የዚህን አይነት መታደል አገኝ ከኾነ ብዬ ነው በየመንገዱ ላይ የምማስነው ...
 
ከገጠሪቷ የኢትዮጵያ ቦታዎች ለተለያየ ጉዳያቸው ወደ መሐል ከተማ የሚመጡ ሰዎች ስነ-ባህርይ ግርም፣ድንቅ ነው የሚለኝ።

እኚኽ ሰው አቶ ሞገስ ይባላሉ። መንገደኛ ናቸው።


•የድምፅ ግብዓት: ርዕስ "Ethiopian lullaby" ያሰናዱት እነ @Samsklair @Popsmohamed @danselsick ናቸው። ድምፁን ያገኘሁት ከ @Spotify መተግበሪያ ነው።

•የተቀረው ተንቀሳቃሽ ምስል በመንገዴ ሁሉ የኾነ ነው።

ሚኪያስ ልየው/Mikiyas Liyew
አዲስ አበባ,ኢትዮጵያ
ኅዳር ፳፻፲፬ዓ.ም

#Ethiopia #Addisabeba #Totravlers #Inspiration #ንሸጣ
#ወደመንገደኞች
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ከላይ የተለጠፈው ተንቀሳቃሽ ምስል MB መጠን በዛ አለሳ ያላችኹኝ እንደኾነ የጥራቱ ነገር ዝቅ ቢልም ይኽን ተመልከቱት

@Mykeyonthestreet
•Adama,Nazreth 09 Kebele Morning Light.•

•This is random project•፩

፲ ፡ ፮ ፡ ፳፻፲፬ ዓ.ም

#Ethiopia #Adama #Nazret #09Kebele #Naturallightproject #Naturallight #mykeyonthestreet #Adamarandomseries

@Mykeyonthestreet
2024/05/17 20:52:58
Back to Top
HTML Embed Code: