Telegram Web Link
NArcHome Architecture
The #silhouette of this globally renowned #monument stands as one of the most iconic symbols of urban #AddisAbeba. It exudes strength and epitomizes elegance; reportedly being one of the two globally celebrated works of Maurice Calka in 1955. Installing such…
ሞሪስ ካልካ
ቀራፂ . ነዳፊ . ከታሚ | 1913 - 1991 ዓ.ም

አሁን በአዲስ አበባ ከተማ ከብሔራዊ ቲያትር አጠገብ ያለውንና በዓለም የታወቀዉን ባለ 10 ሜትር ቁመት የአንበሳ (የይሁዳ አንበሳ) ሥነ-ቅርፅ በ1948 ዓ.ም በአፄ ሃይለ-ሥላሴ ትዕዛዝ ከቲያትሩ የሥነ-ኪነ-ሕንፃ ነዳፊዎች ሄነሪ ሾሜና አንቶይን ላጌት ንድፍ ጋር በማናበብ የነደፈና በግሩም መልኩ የቀረፀ ስመ ጥር ፈረንሳዊ (ፖላንዳዊ ተብሎም ይጠቀሳል) የሥነ-ቅርፅና ንድፍ ባለሙያ ነበር።

ሞሪስ ከመኪና ፣ ከሥነ-ሥቅለት ቅርፅ ፣ ከጠረጴዛ ፣ ከወንበር ፣ ከተለያዩ የሠዉና የእንሠሳት ገፅታዎችና ሁለንተናዊ የሥነ-ቅርፅ ስራዎቹ በተጨማሪ ግሩም የመጠንና (Scale) የምጣኔ (Proportion) ዕሳቤዎቹን ጨምሮ ለቅርፅ ከሚጠቀማቸው ቁሶችም አንፃር ልዩና ጥበባዊ የሥነ-ቅርፅ አገላለፅን የተካነ ባለሙያ ነበር።

ከ50 በላይ የሚሆኑ ስራዎቹ በሙሉ በሁለቱ እጅጉን ዓለም አቀፍ ዝናን ያተረፈ ሲሆን በከተማችን ከእነውበቱና ሞገሱ 'እስካሁን' ዓይንን በቀላሉ በሚይዝ ቅርፃዊ ምስሉ (Silhouette) እየታየ የሚገኘው የአንበሳ ሥነ-ቅርፅ ዋነኛው ነው። ሞሪስ ሁሉንም ሊባል በሚችል መልኩ የሥነ-ቅርፅ ሥራዎቹን በፓሪስ ከተማ ሩ ራፌት በሚገኘው የስራ ቦታው (Studio) የተገበረ ሲሆን 15 የተገነቡ የከተማ ቦታና የሥነ-ኪነ ሕንፃ ሥራዎችም ላይ በተባባሪነት ተሳትፏል።

ምስል ምንጭ: የገፁ ክምችትና ህሊና ታፈሰ

#addisabeba #heritage #history #city #urbaninsight #ethiopia #architecture #update

📌 ንድፍ ለሰበዓዊነት
@NArcHomeArchitecture
መሬት መቀጥቀጥ በኢትዮጵያ
በመሐንዲሶች እይታ


መሬት መንቀጥቀጥ ሊያሥከስታችው የሚችልው ችግሮች እና መደረግ ያለባችው ጥንቃቄዎች ከዶ/ር መሰለ ሀይሌ ጋር የተደረገ ቃለ መጠይቅ።

ሙሉ ቃለ ምልልሱን እዚህ ያገኙታል።

#addisabeba #city #urbaninsight #ethiopia #architecture #update #feature

📌 ንድፍ ለሰበዓዊነት
@NArcHomeArchitecture
በኢትዮጵያ ያሉት አብዛኞቹ ህንፃዎች በዲዛይን ወቅት በሚፈጠር ክፍተትና በግንባታ ጥራት ጉድለት የተነሳ ለርዕደ መሬት አደጋ የተጋላጡ እንደሆኑ የአዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ባለሞያዎች ተናግረዋል፡፡

ኢትዮጵያ ከ1976 ዓ.ም ጀምሮ ህንፃዎች ርዕደ መሬትን እንዲቋቋሙ በሚያስችል መልኩ ዲዛይን እንዲደረጉ አስገዳጅ የህንፃ ኮድ ብታዘጋጅም፣ መስፈርቱን ከመከተል አኳያ ክፍተቶች አሉ ብለዋል፡፡

መንግሥት በበኩሉ፣ “በህንፃዎች ግንባታ ወቅት፣ መስፈርቱ እንዲተገበር ጥብቅ ክትትል እየተደረገ ነው፣ ህንፃዎቹም የተወሰነ የርዕደ መሬት መጠንን የመቋቋም አቅም አላቸው” ይላል፡፡

ሙሉ ዘገባውን እዚህ ያገኙታል።

#addisabeba #city #urbaninsight #ethiopia #architecture #update #feature

📌 ንድፍ ለሰበዓዊነት
@NArcHomeArchitecture
The 'earliest #earthquake recorded in #Ethiopia' dates to 1432, the year Zara Yaqob became king.

"There was an earth tremors & a total solar eclipse..." now identified as Eclipse 6286 in Oppolzer's classification.

A 17th-century manuscript 'Compendium of History; Chronicles of #Ethiopia', Or 821 (page 472-2) now in British Library recorded on 30 June; earth tremors were felt near Gonder Dembia, north of Lake Tana.

Via Eyob Derillo, former Curator: Ethiopian Studies, British Library

#update #history #ethiopia

📌 Design for Humanity.
@NArcHomeArchitecture
እንኳን ለጌታችን ለመድሃኒታችን ለኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ-ልደት በጤና አደረሰን። መልካም በዓል።

ምስል: ሕሊና ታፈሰ- ላሊበላ

#ethiopia #event #feature

📌 ንድፍ ለሰበዓዊነት
@NArcHomeArchitecture
በ1960ዎቹ  የንባብ ባህል፣ የከተማ ኑሮ ትዝታዎች እና ሌሎች ዘመነኛ መልኮች ዙሪያ

ከአቶ አንዳርጋቸው አሰግድ ፣
አቶ ታምራት ከበደ እና
ጴጥሮስ ቶጃ (ፕ/ር) 

ጋራ የትውልዶች ውይይት ይደረጋል።

ቅዳሜ፣ ጥር 03
ከሰዓት
9፡00 እስከ 11፡30

በር 8፡30 ይከፈታል

የመመዝገቢያ ሊንክ
📍አድራሻ

#ethiopia #event #feature #history #urbaninsight

📌 ንድፍ ለሰበዓዊነት
@NArcHomeArchitecture
In pursuit of a modern capital, Ethiopian leader razes history

"But for the thousands of people across Addis whose houses and businesses have been destroyed, the campaign to build a 21st-century metropolis here often feels more like a vanity project than like an effort to make life better for its inhabitants."

Read the complete article here.

#architecture #addisabeba #city #urbaninsight #feature #update #heritage #history #article

📌 Design for Humanity.
@NArcHomeArchitecture
Angsila Oyster Scaffolding Pavilion
CHAT Architects


Ang Sila, Thailand
Architects: CHAT Architects
Year: 2023
Photographs: W-Workspace

"The pavilion design draws on and “bastardizes” the widely deployed bamboo scaffolding traditionally used for oyster cultivation. When in use, local fishermen bring small groups of visitors from Angsila to the pavilion, where they can handpick oysters pulled from the ocean below, which are then prepared fresh to eat …a sea-to-table dining experience in a remarkable coastal setting."

You can read more about the project here.

#update #history #ethiopia

📌 Design for Humanity.
@NArcHomeArchitecture
2025/07/05 14:42:20
Back to Top
HTML Embed Code: