Telegram Web Link
Live stream finished (1 hour)
Audio
ብሉይ ኪዳን 1

ዲያቆን አሸናፊ መኰንን

ያዳምጡ ያትርፉ
22👏8👍1
ጀምበር ሳይጠልቅ

ጊዜ በዘላለማዊነት ሲለወጥ፣ እግዚአብሔር ወደ እኛ ሕይወት ሲመጣ ሥራችንን ፈጽመን ያገኘን ይሆን? በዕድሜ የገፉ አንድ ሽማግሌ ታላቅ ሥራ ጀምረው አገኘኋቸው ። እኚህ አባት ዘጠና ዓመት አልፏቸዋል። "እኔ እንኳ ከሰማይ ጥሪ መጥቶልኛል፣ በዚያ ሊሾመኝ ና እያለኝ ነው፤ ለቀሪዎቹ ላስተካክል ብዬ ነው" አሉኝ። በዕድሜ የገፉ ረጅም ቀጠሮ አይዙም ፣ አስቸኳይ ጥሪ ሊመጣ ይችላል ብለው በየዕለቱ ሥራቸውን ይፈጽማሉ። ጀምበር ሲያዘቀዝቅ ያልሠራነው ተግባር ፊታችን ላይ ድቅን ብሎ እንዳያስተክዘን ቶሎ ቶሎ ሥራችንን መፈጸም አለብን። ዕድሜአችን ቀኑን ይመስላል፣ ቀኑ ይመሻል የእኛም ዘመን ያበቃል። ቆመን ውለን ማታ እንተኛለን ፣ ኖረን አንድ ቀን እንሞታለን።

ሥራችንን በመፈጸማችን እግዚአብሔርን እናከብረዋለን። አንድ ልጅ ትልቅ ደረጃ ሲደርስ ዘመድ አዝማድ ወላጆቹን እንኳን ደስ አላችሁ፣ የእናንተ የልፋት ውጤት ነው ብሎ ያመሰግናቸዋል ፣ ደግሞም ያከብራቸዋል። እግዚአብሔርም በጸጋ የወለደን ፣ በፍቅር ያሳደገን አባታችን ነውና በእኛ ሥራ ምስጋናና ክብርን ይቀበላል። በሕይወታችን ደስታን የምናገኘው እግዚአብሔር በእኛ ምርጫና ተግባር በተመሰገነውና በከበረው መጠን ነው። እግዚአብሔርን በእኛ ምድር እናከብረዋለን ፤ በእርሱ ዓለም በሰማይ ያከብረናል።

ሥራውን ያልፈጸመ ሰው በሕሊናው ዕረፍት፣ በመንፈሱ ሐሴት የለውም። ሥራውን የፈጸመ ለመሞትም ዝግጁ ነው። ጀምበሩ ሲያዘቀዝቅ፣ ቀኑ ሲፈጸም ከቍጭት የሚድን ተግባሩን የፈጸመ ሰው ብቻ ነው።  መሥራት እየፈለግን ያልሠራናቸው ብዙ ተግባራት አሉ። ቆይ እያልን የገፋናቸው ሥራዎች ፊት ለፊታችን ድቅን እያሉ ያውኩናል። የእኛ ቀን ዛሬ ነውና ልንጀምራቸው ይገባል። ጀምረን ባይሳካ እንኳ አለመሳካት ያናድዳል እንጂ አያጸጽትም። ስላለፈው ትላንት መቆጨት ጥቅም የለውም። ዛሬ በእጃችን ላይ ያለች መክሊት ናት። የዛሬው መነሣት ትላንትን የሚክስ ፍሬ ሊኖረው ይችላል።

ጀምበር ሳያዘቀዝቅ ቀኑ ሳይፈጸም ፣ የሕሊና ወቀሳ ሳይጀምር፣ ሁሉም ነገር ከሄደ በኋላ መሰማራት ሳይመጣ ፍቅራችንን ለወዳጆች እንግለጥ። ባለ ውለታዎቻችንን ሳናመሰግን ሞት እንዳይወስዳቸው ንቁ እንሁን። ስልክ እንኳ ለመደወል እያሰብን እጃችንን የያዘን ምንድነው? ከማያረኩን ጋር ጊዜን እየፈጸምን እነዚያን የልብ ሰዎች ባሰብን ቁጥር መቆጨት ውስጥ መግባት ሊያበቃ ይገባዋል።

የበደልናቸውን ይቅርታ ሳንጠይቅ ሞት እንዳይመጣብን ፣ የበደል ቋጥኝ ተሸክመን ወደ ሰማይ እንዳንሄድ ዛሬ ልናውቅበት ይገባል። የበደልናቸው የሞቱ ቀን መቃብራቸው ላይ ዋይ ዋይ ከማለት፣ ይቅር በሉኝ እያሉ ከንቱ ጩኸት ከመጮህ ዛሬ ይህች ጀምበር ሳትጠልቅ ሰላም ማውረድ ይገባል።

ከሁሉ በላይ እንደ ዓይን ብሌን የሚጠነቀቅልንን፣ አበሳችንን የሸፈነልንን፣ ብቻውን የረዳንን ጌታ ሳናገለግል፤ ለወንጌሉ ሥራ ሳንቆም ዘመናችን እንዳይፈጸም ዛሬ መነሣት ይገባል። በበደላችን ሁሉ ይቅር እንዲለን በንስሐ ወደፊቱ መቅረብ ያስፈልገናል።

መኖር ደስ የሚለው የመሥራት፣ የመካስ ፣ ይቅርታ የመጠየቅ፣ የማመስገን ዕድል ስለሆነ ነው።

ዲያቆን አሸናፊ መኰንን
መስከረም 24 ቀን 2018 ዓ.ም.
51👏3👍1
እግዚአብሔር ቢፈቅድ ብንኖር ነገ

እሑድ መስከረም 25 ቀን 2018 ዓ.ም. ከ ጠዋቱ 4:00 ሰዓት  ላይ ትምህርታችን ይጀምራል ::

የትምህርታችን ርእስ "ክርስቶስ ለምን ሰው ሆነ?" ክፍል 9 ይቀጥላል


ክርስቶስ ሰው የሆነበትን ከ40 በላይ ምክንያቶች ይተነትናል።

ማስታወሻ ብትይዙ ይመከራል።

ሌሎች ወገኖቻችንንም ጋብዙ

https://www.tg-me.com/Nolawii
23👏2👍1
Live stream started
Live stream finished (2 minutes)
Live stream started
Live stream finished (1 hour)
Audio
ክርስቶስ ለምን ሰው ሆነ 9

የመጨረሻው ክፍል

ዲያቆን አሸናፊ መኰንን

አዳምጡና ሃይማኖታችሁን እወቁ
18👏1
ልንሳሳት እንችላለን?

እናንተ የአገሬ ሰዎች ልንሳሳት እንችላለን ብላችሁ አስቡ። በዘላለማዊ ትክክለኛነት ውስጥ የሚኖሩ ብዙ ሰዎች አሉ። ስለ አስተሳሰባቸው፣ ስለ ንግግራቸው ፣ ስለ ተግባራቸው ምንም ነቀፋ መቀበል የማይሹ ብዙ ናቸው። የሚገርመው እነዚያ ሰዎች እኛ መሆናችን ነው። በአገራችን ከሊቅ እስከ ደቂቅ ማሰብም መናገርም የማንፈልገው ነገር ቢኖር ተሳስቻለው የሚለውን ቃል ነው። ተሳስቻለሁ፣ ተሳስተናል ከማለት ሚሊየኖች ቢያልቁ እንመርጣለን። መሳሳትን ማወቅና ይቅርታ መጠየቅ የመኖር ዋጋ ነው። የሌለንን ፍጹምነት ለማሳየት እንሞክራለን። ተሳስተሃል፣ ተሳስተሻል የሚለንን ሰው እንደ እርግጠኛ ጠላታችን እናየዋለን። መንገድ ስተን "በዚህ በኩል ነበረ፣ ተሳስታችኋል" ቢሉን ደስ ብሎን እንመለሳለን፣ መሳሳታችንን የነገሩንን ሰዎች እናመሰግናለን፣ ከራቅንም በኋላ ስለ ቅንነታቸው እናስባለን፣ ላገኘነውም ሰው ተሳስቼ መለሱኝ እንላለን። ከአውራ ጎዳናው ይልቅ የሕይወት መንገድ ትልቅ ነው። በአውራ ጎዳናው ብንጠፋ ለሰዓታት ነው። በሕይወት መንገድ ግን ለሃምሳና ሰባ ዓመታት ልንጠፋ እንችላለን። አንዳንድ ሰው መጥፋቱንም ሳያውቅ፣ መጥፋቱንም ሳይቀበል ወደ መቃብር ይወርዳል። ከሕይወት መንገድ ስንስት የምንከፍለው ዘላለማችንን ነው።

ተሳስታችኋል ላሉን ምስጋና ማቅረብ፣ ቅንነታቸውን ማድነቅ፣ ስለ እነርሱም መመስከር ይገባናል። ደመወዝ መክፈል ያለብን ከሚያሞካሹን ይልቅ መሳሳታችንን ለሚነግሩን ነው። መታመማችንን ለሚነግሩን ባለሙያዎች እንከፍላለን ፣ ስለ እውነተኛው ሕመማችን ስለ ተሳሳተው ምርጫችን የሚነግሩንን ግን እንጠላቸዋለን። ጉድለትን ነቅሰው የሚነግሩ ተቋማት በውጭው ዓለም አሉ። ለእነርሱ በሚሊየን ዶላር ይከፈላል። የተሳሳተውን ምርጫ፣ በተሳሳተ ምርጫ የሚኬድበትን የተሳሳተ መንገድ ነቅሰው የሚነግሩን ባለ ውለታዎቻችን ናቸው። ምክርን ሊፈጽሙ የሚችሉ ምክር አጥተዋል፣ ብዙ ምክር አግኝተው ጆሮ ዳባ ልበስ ብለው የተቀመጡ ደግም ብዙ ናቸው። የሰዎችን ምክር አልቀበልም በማለት እንደ ጀብድ የሚያወሩ አሉ። መልካም ምክር ለሚፈጽማት ሕይወትን ውብ ታደርጋለች። ጠላቶችም ቢሆኑ ስለ እኛ የሚናገሩትን መጥፎ ነገር እውነተኛ ከሆነ መለወጥ መልካም ነው፣ አንዳንዴ ወዳጅ የማይነግረንን ጉድለት የሚነግሩን ጠላቶች የተባሉት ናቸው።

የአገሬ ሰዎች ልንሳሳት እንችላለን ብላችሁ አስቡ። መማርም ማወቅ የማይፈልግ ሰው ትክክልና በቂ የሆነ ነገር አለኝ ብሎ የሚያስብ ሰው ነው። ሺህ ዓመት የመኖር ዕድል ብናገኝ የማንፈጽመው እውቀት በዚህ ዓለም ላይ አለ። በነጻ መማር ፣ በነጻ እውቀትን ከመምህራን መቀበል ከቸገረን በጣም የምናሳዝን ነን። እውቀት የመሰለ ነገር የያዘ ሰው ትክክለኛውን ትምህርት ለመቀበል ልቡ ዝግ ነው። ሌላው ወገንም የእርሱ ቡድን አባላት ካልነገሩት ምንም የማይቀበል ነው። የአገራችን ሰዎች ያልሠሩትን መኪና ተማምነን ከነዳን የእኛ ወገን የማንላቸውም ትክክለኛ ነገር ከነገሩን መቀበል ይገባናል። በዚህ ዘመን ላይ አትስሙ፣ አትዩ ተብሎ ማስጠንቀቂያ አይሰጥም። ሁሉን ፈትኖ መልካሙን መምረጥ የሰው ልጅ የከፍታ ልክ ነው።  የመጽሐፍም ሕግ ነው።

የተጣሉ ሰዎችን ማስታረቅ የማይቻልበት ዘመን ላይ ደርሰናል። ትልቁ ችግር ልንሳሳት እንችላለን ብለው አለመቀበላቸው ነው። ሰው ለራሱ እንኳ የማይረዳው ሌሎች ግን የሚያዩት ስህተት አለበት። አዎ ተሳስቼ ይሆናል ማለት ጠብን ያበርዳል። ሁሉንም ማኅበራዊ ችግር ሊፈታ የሚችል ፍርድ ቤት በዓለም ላይ የለም፣ ፍርድ ቤት ገደብና ቅጣትን እንጂ ፍቅርን ሊሰጥ አይችልም። የሚያስታርቁ ሰዎችን ለማክበር ተሳስቼ ይሆናል ብሎ መቀበል ግድ ይላል።

እኛን ብቻ ስሙን፣ ከእኛ ውጭ የማንንም ጽሑፍ አታንብቡ የሚሉ ደፋሮች ፣ አደንቁረው የሚገዙ ምናልባት የሚገኙት በእኛ አገር ነው። አእምሮ ሥራ ፈትቶ የሚውለው በማያነብና በማይማር ማኅበረሰብ ዘንድ ነው። መጠየቅ፣ ይህ ለምን ሊሆን ቻለ ? ብሎ መመርመር ኃጢአት አይደለም። የምናደርገውን ፣ የምናምነውን የማወቅ መብት አለን። እግዚአብሔር በብርሃን የሚመራ አምላክ ነው። አጨልሞ የሚነዳ ሰይጣን ብቻ ነው። ራሳችንን ለማየት ዘወትር ማንበብ አለብን፣ ፊታችንን ለማየት መስተዋት ከገዛን ውስጣችንን ለማየት መጽሐፍ መግዛት አለብን።  ወደ ሚበልጡን ሄደን ምከሩን ማለት አለብን ። ይህ ትልቅ ጥበብ ነው ። ስለ ራሳችን ያለንን የተጋነነ ዕይታ ማስቀመጥ ይገባል። በዓለም ላይ የማይሰጥና የማይቀበል ማንም የለም።

ትንሽ ቆም በማለት ስህተታችንን ልናይ እንችላለን። መሳሳታችንን ማወቅ መጨረሻችን ነው ማለት አይደለም፣ እንደውም መኖር ጀመርን ማለት ነው። መሳሳታቸውን ላመኑ ሰዎች ክብር መስጠት ፣ ይቅርታ ማድረግ አገርን ይለውጣል። ሰዎች የተሻለ ነገርን የሚሰጡን ሁለተኛ ዕድል ሲያገኙ ነው። የያዝነውን እውቀት ፣ ባሕል ፣ ልማድ ትክክለኛ ነው ወይ ? ብለን መገምገም አለብን። ርእዮተ ዓለማችን፣ ፖሊሲያችን ፣ ትግበራችን የእውነት መሠረት አላቸው ወይ ? ማለት አለብን። የተጣላናቸውን፣ የገፋናቸውን ሰዎች በትክክለኛ ምክንያት ያደረግነው ነው ወይ ? ማለት አለብን። በትክክለኛ አእምሮ ሆነን የትዳር አጋራችን ያን ያህል መጥፎ ናቸው  ወይ? ብለን እንደገና መጠየቅ አለብን። በጨዋታው የበላይ ለመሆን የለጠፍንባቸው ያልሆኑት ነገር አለ። ጊዜው ሲያልፍ፣ ትዳር ሲፈርስ ጸጸት ይጀምረናል። አንዳንድ ሰዎችን የጠላናቸው አውቀናቸው፣ ሰምተናቸው አይደለም፣ የክፉዎች የገደል ማሚቱ ሆነን ነው። እንዴት የራሳችን እንኳ ጠብ የሌለን ሰዎች እንሆናለን? ገንዘብን ሳይሆን ጠብን ተበድሮ የሚጣላ ምስኪን ወገን መሆን አይበቃንም ወይ? እንደውም በልምዳችን እንዳየነው በጣም ጥሩ ሰዎች የተጠሉና ክፉ ሥዕል የተለጠፈባቸው ሰዎች ናቸው። ጀማውና አደባባዩ የከንቱዎች ሆኖ ትውልድ ይማቅቃል። የአረንቋ ጉዞ ገጥሞን የሚረገጠው መሬት ናፍቆናል። አገር በተአምር አይለወጥም፣ የተለወጠ ሕዝብ አገርን ይለውጣል። ለመለወጥ ተሳስቼ ይሆናል ብሎ መቀበል ግድ ይላል።

ዲያቆን አሸናፊ መኰንን
መስከረም 26 ቀን 2018 ዓ.ም.
67👍5🥰3👏1
ዛሬ ዓርብ መስከረም 30 ቀን 2018 ዓ.ም. ከምሽቱ 2:00 ሰዓት  ላይ ትምህርታችን ይጀምራል ::

የትምህርታችን ርእስ " ብሉይ ኪዳን"

ክፍል 2

የሚል ነው

ማስታወሻ ብትይዙ ይመከራል።

ሌሎች ወገኖቻችንንም ጋብዙ

https://www.tg-me.com/Nolawii
21👏4
Live stream started
Live stream finished (1 hour)
Audio
ብሉይ ኪዳን 2

ዲያቆን አሸናፊ መኰንን

አዳምጡት አትርፉበት
29👍1🥰1👏1
እግዚአብሔር ቢፈቅድ ብንኖር ነገ

እሑድ ጥቅምት 2 ቀን 2018 ዓ.ም. ከ ጠዋቱ 3፡30 ሰዓት  ላይ ትምህርታችን ይጀምራል ::

የትምህርታችን ርእስ " የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ስደት


ልደቱና ስደቱ ይተነተናል

ማስታወሻ ብትይዙ ይመከራል።

ሌሎች ወገኖቻችንንም ጋብዙ

https://www.tg-me.com/Nolawii
11👍4
ልብ አድርጉ 3፡30 ሰዓት
31👍2👏2
Live stream started
Live stream finished (2 minutes)
Live stream started
Live stream finished (55 minutes)
2025/10/27 16:12:36
Back to Top
HTML Embed Code: