እግዚአብሔር ቢፈቅድ ብንኖር ነገ
እሑድ ጥቅምት 2 ቀን 2018 ዓ.ም. ከ ጠዋቱ 3፡30 ሰዓት ላይ ትምህርታችን ይጀምራል ::
የትምህርታችን ርእስ " የጌታችን የኢየሱስ ክርስቶስ ስደት
ልደቱና ስደቱ ይተነተናል
ማስታወሻ ብትይዙ ይመከራል።
ሌሎች ወገኖቻችንንም ጋብዙ
https://www.tg-me.com/Nolawii

Telegram
Nolawi ኖላዊ
ይህ ቻናል ኦርቶዶክሳዊ መንፈሳዊ ትምህርቶች የሚተላለፉበት ነው። እግዚአብሔር አገልግሎቱን ያስፋ!
አገልግሎቱንም ያግዙ!
0911699907 ዲያቆን አሸናፊ መኰንን
አገልግሎቱንም ያግዙ!
0911699907 ዲያቆን አሸናፊ መኰንን
❤11👍4
ጌታ ይሰማል
"ጸሎትህ ተሰምቶልሃልና አትፍራ"
(ሉቃ .1፥ 13)
መልአኩ ይህን አስደሳች ብሥራት የተናገረው ለካህኑ ለዘካርያስ ነው። ዘካርያስ ማለት የስሙ ትርጓሜ "እግዚአብሔር ያስታወሳል" ማለት ነው ። በርግጥም እንደ ስሙ ትርጓሜ እግዚአብሔር አስታወሰው። ዘካርያስ በማስተስሪያ በዓል ቀን ለእስራኤልና ስለ ዓለም ጸሎትን ሲያሳርግ ሳለ የእርሱን ምኞት የሚሞላ የምሥራች መጣ። ስለ ሌሎች ሲጸልይ የእርሱ ጉድለት ሞላ ። ዓመቱን በሃያ አራት ሰሞን ተከፋፍለው ካህናት ያገለግሉ ነበር። ስለዚህ በዓመት ሁለት ሳምንት ሰሞነኛ ሆነው በእግዚአብሔር ቤት ያገለግላሉና መንፈሳውያን የሆኑ አገልግሎት ወዳዶች እነዚህን ሁለት ሰሞኖች ከልባቸው ይናፍቁ ነበር ። በዚያ ዘመን ከሃያ ሺህ በላይ ካህናት ነበሩ። በእያንዳንዱ ቀንም አንድ ሺህ የሚያህሉ አገልጋዮች ያገለግሉ ነበር። ለአገልግሎትም በዕጣ ይደለደሉ ነበር። ከሁሉ የበለጠው በማስተስሪያ በዓል መሥዋዕትንና ዕጣንን ለእግዚአብሔር ማሳርግ ትልቅ ዕድል ነበረ። በቤተ መቅደስ ተገኝቶ ዕጣን ማጠን የማይገኝ ዕድል ሲሆን ዘካርያስ ዕጣ ወጥቶለት ነበር። በዚህ ታላቅ ደስታ ላይ በሰንበት ላይ ደብረ ዘይት እንዲሉ የምሥራች መጣለት ።
በአይሁድ ባሕል አለመውለድ ትልቅ ውግዘትን ያስከትል ነበር። ያላገቡ፣ አግብተው ያልወለዱ ሰዎች ትልቅ ነቀፋ ይገጥማቸው ነበር። በዚህ ዘመንም ያሉ ክርስቲያን ፈሪሳውያን ሰው ሲቸገር፣ ሲታመም "ባለማመኑ ነው" ብለው ይደመድማሉ። ዘካርያስና ኤልሳቤጥ ጉድለት ቢኖርባቸውም እግዚአብሔርን በማምለክ፣ ቃል ኪዳናቸውን በመጠበቅ ጸኑ። ጉድለት የሚመስል ነገር ከእግዚአብሔር ካልለየን ትልቅ ሰዎች ነን። ቃል ኪዳንም በተራራና በሸለቆ ተያይዞ ለመሄድ የሚደረግ ነውና ጋብቻ መጽናት አለበት።
መሥዋዕቱ ለኃጢአት የሚቀርብ ዋጋ ነበር። የመሥዋዕቱ ሽታ ጣዕም የለውም። የተቃጠለ ሥጋ ሽታው ይረብሻል። ኃጢአትም አስከፊና ከሕይወት መዓዛ የሚለይ ነው። መጥፎ ሽታ ራሳችንን፣ አካባቢውን እንድንጠላ የሚያደርገን ነው። ኃጢአት የጥላቻ ስሜት ያመጣል። ስሜታዊ ደስታ እውነተኛ ኀዘን ፣ ጊዜያዊ ፈንጠዝያ ዘላቂ ቁስል የሚገኘው በኃጢአት ነው። ዕጣኑ መሥዋዕቱ በጣዕም እንዲያርግ የሚረዳ ነበር። ጸሎት ለእግዚአብሔር የሚቀርብ ጣፋጭ ሽታ ነው። እግዚአብሔርን ደስ ያሰኘዋል። ንስሐችን፣ ምልጃችን፣ ምስጋናችን ፣ መሥዋዕታችን የሚያርገው በጸሎት መሰላል ነው። ጸሎት ሰማያዊ ጌታ በቤታችን እንዲገኝ ፣ ምድራውያን እኛ በሰማይ እንድንገኝ የሚያደርግ ነው። እግዚአብሔርን መጋበዝና በእግዚአብሔር መጋበዝ እንዴት ደስ ያሰኛል!
ዘካርያስ የጸሎት መልሱ ቢዘገይም ይጸልይ ነበረ። አገልጋይና ጸሎተኛ ከሆንን ዕጣ ወጥቶልን፣ ታላቅ ዕድል ገጥሞን ነው ። እግዚአብሔርን ማገልገል ከሺህ ሰው ለአንድ የሚደርስ ነው ። ዲያቆን ከሆንህ ከቤተ ዘመድ ብቸኛው ሰው አንተ ልትሆን ትችላለህ ? ጳጳስ ከሆንህ ካደግህበት ክፍለ አገር ብቸኛው ሰው ፣ ከሚሊየኖች አንዱ ልትሆን ትችላለህ። ማገልገል ዕጣ ነው። የግል ጸሎት ባይመለስም የጌታ መሆን ከመልስ በላይ ነው። ዘካርያስ አይሰጥህም አልተባለም፣ ጠብቅ የተባለ ሰው ነው። ጀምበር ልትጠልቅ የተቃረበች ቢሆንም መልሱ መጣ። ለእግዚአብሔር መሸ አይባልም። ሰውም ለንስሐ ፣ ለጸሎት፣ ለአገልግሎት መሸ አይባልበትም፡ ከእግዚአብሔር ጋር ሠርኩ ማለዳ ነው። በመሸ ጊዜ የንስሐ ድምፅ ወደ አዳም መጣ። አሁን ካረጀሁ ንስሐ መግባት፣ መላ ሲያጡ መመለስ ደስ አይልም እያለ የራቀ ወገን አለ። እስከ መጨረሻዋ ህቅታ ድረስ የንስሐ ዕድል ቢኖርም ቀኑ ግን ዛሬ ነው። መዳን ቀጠሮ የለውም።
መልአኩ ቅዱስ ገብርኤል ይዞት የመጣው የምሥራች ለዘካርያስ ብቻ ሳይሆን ለብዙዎች ደስታ የሚሆን የዮሐንስን መወለድ ነው። በርግጥም ጸሎቱ የጸለየ ቀን ምናልባት የዛሬ ሰባ ዓመት ተሰምቷል ። አፈጻጸሙ ግን ዛሬ ሆኗል። እግዚአብሔርን መጠበቅ አያከስርም፣ ዮሐንስን የመሰለ ልጅ ያሰጣል። እንኳን በሰባ ዓመት በሺህ ዓመት ተጋድሎስ ዮሐንስ ይገኛል ወይ ?
ዮሐንስ የጌታን መንገድ ሊጠርግ የተላከ መልእክተኛ ነው። ዮሐንስ ማለት "እግዚአብሔር ጸጋ ነው" ማለት ነው። ራሱ እግዚአብሔር ጸጋ ነው፣ ቢሳካም ባይሳካም እግዚአብሔር ራሱ ጸጋ ነው። ይህ አለኝ ከማለት እግዚአብሔር አለኝ ማለት ይበልጣል። የሚገርመው ዘካርያስና ኤልሳቤጥ ይህን ልጅ ለማሳደግ ዕድሜአቸው ገፍቷል። እኔ ባልኖር ልጅ ምን ይሆናል? የሚል ፍርሃት ሺህ ጊዜ ይገድለናል። ልጅን የሰጠ ጌታ፣ ልጅን ያሳድጋል። ትውፊቶች እንደሚነግሩን ሄሮድስ ሕፃናትን ሊያስገድል በወጣ ጊዜ ኤልሳቤጥ ዮሐንስን ይዛ ወደ ይሁዳ በረሃ ገባች። ዘካርያስን በመቅደስ ያገኙት ወታደሮች ልጅህን አምጣ ቢሉት አላሳይም በማለቱ ሰማዕት ሆነ። ደሙ በመቅደስ ፈሰሰ ። ኤልሳቤጥም ጥቂት ቆይታ ሞተች፣ ያ ልጅ በበረሃ አደገ። ጌታን የያዘ ምን ይሆናል ይባላል። ነገር ግን የማይሆነው ነገር የለም። እግዚአብሔር ራሱ ዮሐንስን በበረሃ አሳደገው። ልጁን ለቤተ እግዚአብሔር ወለዱ።
ጸሎት ካልተመለሰ ፍርሃት አለ። ጸሎታችን መልሱ ሊዘገይ ይችላል፣ የጸለይን ቀን ግን ተሰምተናል። ለጸሎት መልስ ከሚረዱ ነገሮች አንዱ ትዕግሥት ነው። ዘካርያስ ጻድቅ ቢሆንም ጉድለት ነበረው፣ ኤልሳቤጥ ቅድስት ብትሆንም ነቀፌታ ነበራት ፣ የቡና መጠጫ ፣ የጠላ ማወራረጃ ነበረች ።
ዘካርያስ የጸሎቱን መልስ በቤተ መቅደስ ሰማ፣ የሰማይ ድምፅ በቤተ ክርስቲያን ይሰማልና መገስገሰ ይገባል። "እቤቴም ይሰማኛል" የሚሉ ሰዎች ዘካርያስ ይህን አያውቅም ነበር ወይ? መገስገስ መሥዋዕት ነው፣ መሥዋዕትም ጸሎትን ሥሙር ያደርጋል። ያለ መሥዋዕት ጸሎት አያርግም። እንቅልፍን፣ ስንፍናን መሠዋት ይጠይቃል።
ጸሎት እንዲሰማ መታዘዝ ይገባል ፣ ያልነውን እንዲፈጽምልን ያለውን መፈጸም ግድ ነው። ሁለተኛው በቤቱ መጽናት ግድ ይላል። ዘካርያስ ዮሐንስ ከተወለደ በኋላ የቆየው ሁለት ዓመት ከመንፈቅ ነው። ጸሎታችን ለምን እንደ ዘገየ አናውቅም። ወልድ ሆይ በእውቀትህ አድነኝ ብሎ መጸለይ ብልህነት ነው።
ዲያቆን አሸናፊ መኰንን
ጥቅምት 3 ቀን 2018 ዓ.ም.

❤57🥰7
ፈልጉ ታገኙማላችሁ
ማቴ. 7፥7
በቤታችን ደስታ አልተሰማን ከሆነ የልባችንን የሚፈጽምልን ሰው አጥተን ነው። በሥራችን ቦታ ደስታ ያልተሰማን የልብ አድርስ የሆነ ሠራተኛ ተቸግረን ነው ። በአገራችን ሥራ ነው የሌለው ወይስ ሠራተኛ ? ብለን መመርመር ያስፈልገናል። ያዘዝነው ባለሙያ ትእዛዙ ላይ ተኝቶ የሚያበሳጨን ጊዜ ጥቂት አይደለም። ልጆቻችን በፍላጎታችን መንገድ አልሄድ እያሉ ልባችንን ይሰብሩታል። አካሌ የምንላቸው ብሽሽቅ ውስጥ ገብተው የማንወደውን ያደርጉታል። የልብን መሻት ፈጽሞ የሚያረካ አንድ አለ፦ የልባችን ልብ ፣ የሕይወታችን ሕይወት፣ የመንገዳችን ብርሃን፣ ቀሪ ገንዘባችን፣ ተዘናግተን የሚያይልን ፣ ተኝተን የሚጠብቀን አንድ ስመ መልካም አለ ። እርሱም የፍጥረታት ባለቤት እግዚአብሔር ነው። ለዚህ ነው ነቢዩ፦ "በእግዚአብሔር ደስ ይበልህ፥ የልብህንም መሻት ይሰጥሃል" ያለው (መዝ 36፥ 4 ) ።
የልብን የሚያውቅ የልብ አምላክ ፣ የተሰወረውን ምኞት የሚያነብ የነፍስ ወዳጅ እግዚአብሔር ነው። በዚህ ምድር ላይ የምንኖረው መሻቱን ለመፈጸም ብቻ ሳይሆን የእኛንም መሻት ሊፈጽምልን ነው።
መጽሐፍ፦ "ፈልጉ ታገኙማላችሁ" ይላል። የጠፋብንን ነገር ለመፈለግ ከእንቅልፍ እንነቃለን፣ አልጋውን ገልብጠን እናቆመዋለን፣ ካገኘሁ በኋላ አስተካክለዋለሁ ብለን ቤቱን በአንድ እግሩ እናቆመዋለን፣ ወረቀቶቹን በትነን የዘመናት ሰነድን እናገላብጣለን። ከምንፈልገው ውጭ ሌላ ማግኘት አያስደስተንም፣ ሁሉንም አሁን አታስፈልጉኝም ብለን እንገፋቸዋለን። ልባችን በእልህ፣ እንዴት? በሚል ሙግት፣ የት ሊሄድ ቻለ ? በሚል ቍጣ፣ ማን ገብቶ ነበር? በሚል ጥያቄ የሚፈልገውን ነገር ይበረብራል። ብርሃኑ አነሰብኝ ብሎ ባትሪ ያበራል ፣ ቤተሰቡ አብሮ ይዋትታል። ፈላጊው ቢቆጣም ማንም መልስ አይሰጠውም፣ ቆይ ተረጋጋ ይሉታል። ባገኘው ጊዜ ደስ ይለዋል፣ ልበ ቢስነቱን ይታዘባል፣ ይቅር በለኝ እገሌን ጠረጠርሁ ይላል፣ የተቆጣቸው ቤተሰቦቹ ያራሩታል። ከማግኘት በፊት ብርቱ ፍለጋ ሲኖር ባገኘ ጊዜ ደስታ፣ ንስሐ፣ ከእኔ ጋር ተደሰቱ የሚል ግብዣ ይኖራል።
መፈለግ የሚፈልጉትን ነገር ማወቅን ይጠይቃል። በትክክል የምንፈልገውና የሚያስፈልገን ነገር ምንድነው? እርሱን ካላወቅን ዘመናችን በመባዘን ያልቃል። ያለኝ ይበቃኛል አለማለት፣ ስግብግብነት፣ በመጠን አለመኖር የምንፈልገውን ባለማወቅ የሚመጣ ነው። ይህ ደስታ እያሳጣን፣ እያቅበጠበጠን ፣ ትዳርና ኅብረታችንን እንድናፈርስ ያደርጋል። የሚፈልጉትን ለማግኘት የሚፈልጉትን ማወቅ ተገቢ ነው። ሁለተኛው አስፈላጊ ቢሆኑም ሌሎች ግኝቶችን መተው ይገባል። የምንፈልገውን የማንፈልገው ነገር እንዳያስረሳን መጠንቀቅ ግድ ይላል። ብዙ ሰው መንገድ ላይ የቀረው በዚህ ምክንያት ነው። ለምንኩስና ወጥቶ ሥልጣን ላይ ፣ ለትምህርት ወጥቶ ቁማር ላይ የቀረው በተላላነቱ፣ ያየውን ብቻ ለመከተል አለመፍቀዱ ነው። ሦስተኛው ያለው ብርሃን በቂ ስለማይሆን ተጨማሪ ብርሃን፣ የቃሉን ፓውዛ ማብራት ይገባል። ብሩህ አእምሮ ብቻውን በቂ አይደለም፣ መንፈሳዊ ምሪት ያስፈልጋል። አራተኛ የቅርብ ቤተሰቦችን አፋልጉኝ ብለን መጥራት ፣ ምክር መጠየቅ ይገባል። አተርፍ ባይ አጉዳይ የሆነ፣ ሁሉን እይዛለሁ ብሎ ሁሉን ያጣ ፣ ምክር አያስፈልገኝም ብሎ ገደል የገባ ብዙ ነው።
"ፈልጉ ታገኙማላችሁ" ማለት ተኝታችሁ ተመኙ የተባለ መስሎት ብዙ ሰው ስቷል። መፈለግ መነሣት፣ ማሰስ፣ መድከም፣ ለዚያ ነገር ትኩረት መስጠት፣ ለምን እና እንዴት ብሎ መጠየቅ ፣ አግዙኝ ብሎ መጥራት ያለበት ነው። ለሚፈልግ ሰው ነገሮች ቅርብ ናቸው። ፈልጉ ታገኛላችሁ የሰውን ንብረት መመኘት፣ ወላጅ ሳይሞት ሞቶ በወረስሁ የሚል ጭካኔ አይደለም። መፈለግ የራስን አእምሮና ጉልበት መጠቀም ፣ የሌላውን ልፋት አለመከጀል ነው ። መፈለግ እግዚአብሔርን ይዞ ጉዞ ማድረግ ፣ አምላኬ ሰጪዬ ነው ብሎ ማመን መታመን ነው።
ብዙ ቅዱሳን አባቶች እግዚአብሔርን ለማገልገል ፈለጉ፣ ከወላጅ ቤት ርቀው ለትምህርት መነኑ ። የሚፈልጉት ጋ ለመድረስ ዋጋ መክፈልን አልፈሩም። ልጆቻቸውን አገልጋይ ለማድረግ ፈለጉ፣ ገና በጠዋቱ ወደ ቤተ እግዚአብሔር አመጡ ። ምክረ ሥላሴን ለትውልድ ለማቆየት ፈለጉ ፣ ጀርባቸውን አጉብጠው መጻሕፍትን ጻፉ። ከአራት ሺህ እስከ ስምንት ሺህ መጻሕፍትን በግለሰብ ደረጃ የጻፉ አባቶች አሉ።
የምንፈልገው ምንድነው ? መፈለግ አሁን መነሣት ይፈልጋል። ቀጠሮ የሚያበዛ ሰው የተመኘውን አያገኝም ። መፈለግ እንቅስቃሴ ነው ። ቤቱ ሊተራመስ ይችላል። ፍላጎታችን አንዳንዴ ቤተሰባችንን ሳይቀር ሊያሳጣን ይታገለናል። የተመኙልንና የምንፈልገው ሲጣላ ሙግት ውስጥ እንገባለን። መፈለግ አሁን የማያስፈልጉንን ነገሮች ወደ ጎን እንድናደርግ ያስገድደናል። መፈለግ ቁልፍ ለመስበር፣ በር ለመክፈት ሊያበቃን ይችላል። መፈለግና መከጀል ትልቅ ልዩነት አለው። ዛሬ የሚከጅል ትውልድ ፣ ከመኝታው የማይነሣ ፣ የማይጠቅመውን ነገር ሲያገላብጥ የሚውል ወገን እያፈራን ነው ። "ፈልጉ ታገኙማላችሁ" እንዲህ ያለውን አይመለከትም። ሰባኪ ለመሆን የሚፈልግ ማንበብ፣ የሰባኪዎችን ትምህርት ቀን ከሌሊት መስማት፣ መለማመድ ፣ ሰው ቢያጣ ዛፎችን እንደ ሰው ቆጥሮ ማስተማር ፣ የመምህራን እጅ አስታጣቢ መሆን ይገባዋል። መፈለግ ያለ መሠዋዕትነት አይሆንም።
የሚፈልግ ያገኛል! እንኳን እግዚአብሔር ስንቱ ሊቅ እውቀትን ሊያወርስ የሚፈልግ ሰው እያሰሰ ነው። ባለጠጎች ራእይ ያለው ሰው፣ እውነተኛ ወገን ይፈልጋሉ። እግዚአብሔርም ጸጋውን ለመልቀቅ የሚፈልግ ሰው እያማተረ ነው። በመፈለግ በልጽጉ !
ዲያቆን አሸናፊ መኰንን
ጥቅምት 4 ቀን 2017 ዓ.ም.

❤45🥰4👍3
ሦስቱ መርሖች
ክርስትና ብዙ ነገሮችን ለውጧል። አይሁድ ከአሕዛብ ጋር በአንድ መንገድ መሄድ፣ በአንድ ቤት መመገብ፣ በአንድ መቅደስ ማምለክ አይችሉም ነበር። በሕግ ገደብ ፣ በራሳቸውም ጽዩፍነት ይህን ማድረግ አይችሉም ነበር። ክርስትና ግን ሕዝብና አሕዛብን አንድ ያደረገ፣ ቀራጭና አመንዝራን በንስሐ የተቀበለ፣ የጾታ ልዩነትን ወይም ንቀትን ያስወገደ፣ ዓለም አቀፍ ራእይን ይዞ የወጣ ፣ ግንቡን አፍርሶ ድልድይ የሠራ ነው። ሉቃስ ወንጌላዊ ከአሕዛብ ወገን የሆነ ሰው ነው። ሉቃስ በክርስትና ውስጥ አማኝና አገልጋይ ለመባል የበቃው በሐዲሱ ሥልጣን ነው። ክርስትና የተራራቁትን የሰው ልጆች አቀራረበ።
በክርስትና ሰዎች ለእግዚአብሔር ያላቸው አመለካከትም ተለውጧል። ግሪኮች እግዚአብሔር እጅግ ሩቅ ፣ ስሜት አልባ ፣ ወደ ፍጥረቱ ሊቀርብ የማይችል ኣምላክን ያስቡ ነበር። ይህ አምላክ ሊሰማና ፍጥረቱን ሊረዳ አይችልም። አይሁዳውያን የሕግ ሰዎች ነበሩና የሕጉን ባለቤት እንደ ዳኛ ያዩት ነበር። በእነርሱ ምልከታ ይህ አምላክ ጨካኝ ፣ መቅጣት የሚወድና አስጨንቆ የሚገዛ ነው። በክርስትና ግን እግዚአብሔር አፍቃሪ አባት፣ ነፍሱን ስለ ጠላቶቹ የሚሰጥ ልዩ ወዳጅ መሆኑ ተገለጠ። ሞቱና ትንሣኤውም ተሰበከ ። በሞቱ ፍቅርን፣ በትንሣኤው ኃይሉን ገለጠ። የሚኖርልን በሌለበት ዓለም ላይ የሚሞትልን ተገኘ፣ ሞትም የመጨረሻ ነው ተብሎ የሰው ተስፋ ተገድቦ ነበር ፣ ትንሣኤ የሞትን ግርማ ገፈፈ። በክርስትና ሰዎች ተቀራረቡ፣ ከሁሉ በላይ እግዚአብሔር ኑሮአችንን የሚካፈል ፍቅር መሆኑ ተገለጠ።
ወንጌላዊው ሉቃስ ከአሕዛብ ወገን የሆነ ክርስቲያን ነው። ወንጌሉንም የጻፈው ለአንድ ሮማዊ ባለሥልጣን ወይም ለአሕዛብ ነው። አሕዛብ ሕዝቦች የሚል ፍቺ አለው። የሚገልጠው ግን አረመኔ የሚለው ነው። አይሁድ ከእነርሱ ውጭ ያሉትን አረመኔ፣ ጨካኝ፣ በምድር በሰማይ ስደተኛ ብለው ይጠሯቸው ነበር ። ወንጌላዊው ሉቃስ ሁለት ሙያዎች ነበሩት፦ የመጀመሪያው ሠዓሊ ነበረ፣ በዚህ ሙያውም የድንግል ማርያምን ሥዕል እንደ ሳለ በመላው ዓለም ይታመናል። ሁለተኛ ሙያው ሐኪም ነበረ። የሉቃስ ወንጌል ሥዕላዊ ወንጌል ነው። ሰሌዳው የሰው አእምሮ ቡሩሹ ቃላት ነበሩ። የሥዕሉ ፍጻሜ ክርስቶስ የሁሉ ወዳጅ ነው የሚል ነው። ሐኪም በሽታን የሚመረምር ፣ ሥራን በጥንቃቄ መሥራት ያለበት ነው ። ሉቃስ የክርስቶስን መዋዕለ ሥጋዌ በጥንቃቄ መርምሯል። የታሪኩ አካል የነበሩትን በቀጥታ በአካል አነጋግሯል። ጥሩ የታሪክ ተመራማሪም ነበር። ከሁሉ በላይ መንፈስ ቅዱስ በዘመናት ለሚነሡ ክርስቲያኖች የክርስቶስን መልክ የሚያዩበት የሉቃስ ወንጌልን የመሰለ መስተዋት ትቶልናል። የሉቃስ ወንጌል መልክአ ኢየሱስ ነው።
ሉቃስ ወንጌሉን የጻፈው ለቴዎፍሎስ ነው። አስቀድሞ በክርስቶስ ያመነና የተማረ ነው። እውቀቱ ሙሉ እንዲሆን ወንጌሉን ጻፈለት። ሉቃስ ለአንዲት ነፍስ ግድ የሚለው የክርስቶስ ተከታይ ነበረ። የአንድን ሰው ዋጋ የማያውቅ አገልጋይ መሆን አይችልም። ሺህ ሰው ካልመጣ ስብከት የማይመጣለት አገልጋይ ምስኪን ሰው ነው ። ለአንድ ኒቆዲሞስ በሌሊት፣ ለአንዲት ሳምራዊት በቀትር ስለ ተጋው ጌታ መናገር አይችልም። ባለ ሥልጣኖችን መጥላት የሐቀኝነት ምልክት እየተደረገ ነው። የዘመናችን ዲሞክራሲ ጥላቻን መግለጥ ነው። ባለ ሥልጣኑም ክርስቶስ ያስፈልገዋል ብሎ እንደ ሉቃስ ማመን ይገባል።
ቴዎፍሎስ የሚባል ሰው የለም ብለው የሚያስቡ ሰዎች አሉ። ቴዎፍሎስ ማለት የእግዚአብሔር ወዳጅ ማለት ነውና ለሁሉም አማንያን የተጻፈ ነው ብለው የሚናገሩ አልታጡም። ነገር ግን ሉቃ .1፥1 በመግቢያው ላይ "የከበርህ ቴዎፍሎስ ሆይ" በማለት አንድን ሮማዊ ሹም በማዕረግ ስም ይጠራዋል። ስለ አንድ ግለሰብም ይናገራል:: ክርስትና እኩልነት ያለው የመከባበር ሕይወት ነው። ሁለተኛው "ስለተማርኸው ቃል እርግጡን እንድታውቅ" ይላል፣ ቴዎፍሎስ አስቀድሞ የተማረ ግን ተጨማሪ ማስረጃ የሚያስፈልገው ነው። "በየተራው ልጽፍልህ" በማለት አንድን ግለሰብ አድራሻ ያደርጋል። ቴዎፍሎስ ለሚባል ባለሥልጣንና ግለሰብ ወንጌሉ ተጽፏል። ቴዎፍሎስ ማለት የእግዚአብሔር ወዳጅ ማለት ነውና የመላው አማንያን መጠሪያ ሊሆን ይችላል።
በቤተ ክህነት በጣም የታወቁ ሰባኪ ነበሩ። እኚህ ሰው ጣዕማቸው፣ ስብከታቸው ልዩ ነው። መጨረሻ ላይ መንገድ ዳር ተቀምጠው በሰማንያ ዓመታቸው ሣንቲም የሚጠይቁ ሆነው አልፈዋል። የእኛ ቤት እያለ የሚናገረው የቅን ፍትሕ እንዲሰጥ የተቀመጠው አባት መሆኑ ይገርማል። ሰባኪ ለማኝ ቢሆንም አይደንቀንም፣ መፍረድ የሚችሉት አለቆች "አይ የእኛ ቤት" ብለው ያልፉታል። ታዲያ እኚህ መምህር ወመገሥጽ አባት "እግዚአብሔር የሚወዳችሁ እግዚአብሔርን የምትወዱት ምእመናን" የሚለውን ሰላምታ ሁልጊዜ ሲቃወሙ ይሰማ ነበር። "እግዚአብሔር የሚወዳችሁ ትክክል ነው፣ እግዚአብሔርን የምትወዱት የሚለው ግን ሐሰት ነው" በማለት ይናገሩ ነበር። ብቻ እግዚአብሔር በጸጋው እንደ ወዳጆቹ ቆጥሮናል (ዮሐ.15፥15) ።
ወንጌላዊ ሉቃስ በመግቢያው ላይ ያነሣቸው ነገሮች ለሕይወታችን ጠቃሚ ናቸው።
በየተራ
ነገሮች ቅደም ተከተል ይፈልጋሉ። የዜማ መሣሪያዎች ቅደም ተከተላቸውን ስለሚጠብቁ ጣዕም አላቸው። ቅደም ተከተል የውበትና የጣዕም መገኛ ነው። የሚቀድሙትና የሚከተሉት ሆሳዕና በአርያም ይሉ ነበር (ማቴ 21 ፥ 9) ። አእምሮአችንም ቤታችንም እንዳይዘባረቅ ቅደም ተከተል ማወቅ አለብን። መቅደም ያለበት፣ መከተል የሚገባው ነገር እንደ ግለሰብም እንደ አገርም አላወቅንበትም ። የሚቀድመውን አለማወቅ በብዙ ነፍስ ላይ መፍረድን ያመጣል። ጨካኝ ያደርጋል። የሃይማኖት አለቆች ይህን የሳቱ ይመስላል። ያሉት ጌጥ ላይ እንጂ የሚረግፈው ወገን ላይ አይደለም። በዓለም ያለው ሀብት በቂ ነው ፣ የሚቀድመውን ባለ ማወቅ ግን ይባክናል። በሕይወታችን እየሮጥን ያለ ነው ለሚቀድመው አይመስልም። አንዳንድ ሰው ጤናው እያበራ ምልክት እያሳየ ቢሆንም ገንዘብ በማከማቸት ላይ ነው። ላይነሣ ሊወድቅ ይችላል።
ማዘጋጀት
አንድን የተሰናዳ ነገር ማቅረብ ለማሳመንም ይጠቅማል። ሳንዘጋጅ ትውልድ እንደ ጎርፍ መጥቶብናል ። ዘመን የከዳን ምስኪን አገልጋይ እንመስላለን። ሳንዘጋጅ በፉከራ ብቻ ዘመኑን የእኛ የምንደርገው ይመስለናል። በብዙ መንገድ መዘጋጀት ካልቻልን በፍርድ ስብከት ብቻ ሰውን ማትረፍ አንችልም። ጥፋት ሊመጣ እንደሚችል ከጠፉ አብያተ ክርስቲያናት መማር ይገባል። "አልሞትንም ብለን አንዋሽም" እንደተባለው አልተጎዳንም ማለት አንችልም።
ጥንቃቄ
ጥንቃቄ ለኑሮ ወሳኝ ነው። ጥንቃቄ በእግዚአብሔር በጣም ማመን እንጂ አለማመንን አያሳይም። ለራሳችንና ለሰዎች መጠንቀቅ አለብን። ይልቁንም የእግዚአብሔርን ሥራ በቸልታ የሚሠራ ርጉም ይሁን ተብሏልና በጣም መጠንቀቅ አለብን። ከወንጌላዊው ሉቃስ የወንጌሉን በረከት ያገኘነው እነዚህን ሦስት ነገሮች ቢፈጽም ነው።
ዲያቆን አሸናፊ መኰንን
ጥቅምት 5 ቀን 2018 ዓ.ም

❤42🥰5
እግዚአብሔር ያለመኑትን ይሰጣል
ከአባቱ ጋር የዘመን እኩያ የሆነ፣ እናቱንም የፈጠረ ልጅ ከክርስቶስ በቀር ማንም የለም። እንደ ተፈጥሮ ሥርዓት አብ ወልድን የወለደ አይደለም፣ አብርሃም ይስሐቅን ቢወልድ በዘመን ቀድሞ ፣ በክብር በልጦ ነው፤ አብ ወልድን በመውለዱ በዘመን አይቀድመውም፣ በክብር አይበልጠውም። እናቱንም የፈጠረ ልጅ ከጌታችን በቀር የለም። አብን አህሎና መስሎ ፣ በክብር ተካክሎ ዘላለማዊ ልደት የተወለደው፣ እኛን መስሎ ፣ ቤዛ ሊሆነን ከድንግል ተወለደ። ድንግል ፈጣሪዋን ወለደች። በእናቱ እቅፍ ጡት እየለመነ በዚያው ቅጽበት ዓለምን ይመግብ ነበር ። ታናናሽ ጣቶች ያሉት ያ ሕፃን ዓለምን በመሐል እጁ የያዘ ነው። ሰማያውያን ሊያደርገን ምድራዊ የሆነ፣ ድህነታችንን ተካፍሎ ባለጠጋ ሊያደርገን የመጣ አንዱ ክርስቶስ ነው።
ከእግዚአብሔር ሳንለምን የምንቀበለውና ለምነን የምንቀበለው ነገር አለ። ድንግል ማርያም ያለመነችውን ተቀበለች። የአምላክ እናት ለመሆን ለምና አታውቅም። እርሱ ግን እናቱ ትሆን ዘንድ መረጣት። በዚህም ሁለት ነገርን ማየት እንችላለን፦ የመጀመሪያው እግዚአብሔር የለመነውን ይሰጠናል፣ እንደ ሰውነታችን ብንለምን እንደ አምላክነቱ ይሰማናልና ከለመነው በላይም ይሰጠናል። እግዚአብሔር ከዚህ በላይ ያለመነውን ይሰጠናል። ለምነን ከምንቀበለው ይልቅ ሳንለምን በምርጫው የሚሰጠን እጅግ ትልቅ ነው። ድንግል ማርያም መሢሑን ከሚጠብቁ መካከል ብትሆንም መሢሑን ግን እኔ ልውለድ ብላ ለምና አታውቅም። ሁለተኛው እግዚአብሔር የማይደገም ነገር ይሰጣል። ከእርስዋ በፊትም ከእርስዋ በኋላም አምላክን ለመውለድ የተመረጠች ሴት የለችም፣ አትኖርም። እግዚአብሔር የሰጠን ነገር ሌላ ቦታ የማይገኝ ልዩ ነገር ነው።
በመልኩና በአምሳሉ መፈጠራችን ያለመነው ልዩ በረከት ነው። ከሰማይ ወደ ምድር እንዲወርድ ፣ መልካችንን መልኩ እንዲያደርግ ያስገደደው የራሱ ፍቅርና ፈቃድ ነው። ውሉደ እግዚአብሔር፣ የሰማይ ቤተሰቦች የሆነው ያለመነውን በሚሰጥ በእግዚአብሔር ነው። ሰው ሆነን መፈጠራችን፣ ከእንስሳት ወይም ከእጽዋት አንዱን ሆነን አለመገኘታችን የእግዚአብሔር ምርጫ ነው። እግዚአብሔር የመረጠልን ነገር ለራሳችን አስበን ከምንለምነው የላቀ ነው። ሺህ ጊዜ ለራሳችን ብናስብ እልፍ ጊዜ ብንጸልይ እርሱ የመረጠልንን አያህልም። የምንወለድበትን ዘመንና ቦታ፣ የሚዛመዱንን ቤተሰቦች የመረጠው እርሱ ነው። ከዚህ በፊት ባያውቁንም ስንወለድ በደስታ የሚቀበሉንን ሰዎች ያዘጋጀ እርሱ ነው። የለፉበትን የሚያወርሱን ፣ ያላቸውን የሚሰጡን፣ በይቅርታ የሚቀበሉን ወላጆች የሰጠን፣ ለእኛ አንጀታቸው ስስ የሆነ አባትና እናት ያዘጋጀልን እግዚአብሔር ነው ። እርሱ ያለመኑትን ይሰጣል፣ ሁልጊዜ በሥራው ትክክል የሆነው ፣ በመጥራቱ የማይጸጸተው ጌታ ውድ ነገርን አዘጋጅቶልናል።
ምድራውያን የሚያጩን ለምድራዊ ነገር ነው፣ እግዚአብሔር ግን ለሰማያዊ ነገር ያጨናል። የበረታች ነፍስ የደከመን ሥጋ መሸከም ትችላለች ፣ ነፍስን የሚያበረቱ አገልጋዮች ያስፈልጋሉ። ለአገልጋይነት መመረጥ ትልቅ ዕድል ነው። ቃሉን መስማት ማንም የማይቀማው በጎ ዕድል ነው ከተባለ ቃሉን ማሰማት ደግሞ የበለጠ ዕድል ነው። እግዚአብሔርን ለማገልገል ጥሪና ምርጫ ከሰማይ ሲመጣ ከምድር ደግሞ የባለቤቱ ፈቃድና ትጋት ያስፈልጋል። ጥሪው ማቅረቢያ ሲሆን ምርጫው ጸጋህ ይህ ነው መባል ነው። እግዚአብሔር አስፈቅዶ የሚያድን ፣ በቤቱ የሚሾም አምላክ ነው። ፈቃደኝነት ከሰው ይጠበቃል። ትጋት ጸጋን ያቀጣጥላል፣ ያበዛል። ጸጋ እሳት ነው፣ እሳት ቆስቁሱኝ የሚል ነው። ጸጋ ከሰነፍ ላይ አይበዛም፣ ሊወሰድም ይችላል። ሌሊትና ቀንን፣ ክረምትና በጋን የሚያፈራርቀው አምላክ ሰነፍ ልጆች የሉትም። ሳይዘናጋ ፍጥረቱን የሚጠብቀው ጌታ ቸልተኛ ልጆች የሉትም። እግዚአብሔር ያለመነውን ይሰጣል።
እግዚአብሔር ለሚሰጠን ጸጋ፣ ለሚሾመን መንበር አስቀድሞ ያዘጋጃል። ዮሴፍ በእስር ቤት ለቀጣዩ ሥልጣን እንደ ተዘጋጀ እግዚአብሔር በማይጠበቁ ስፍራዎች ሳይቀር እያዘጋጀን ሊሆን ይችላል። መጪውን ነገር በማሳወቅ ያዘጋጃል፣ በመከራ ውስጥ በማሳለፍም ያዘጋጃል፣ በትምህርት ያዘጋጃል ፣ የመምህራን ደቀ መዝሙር በማድረግም ያዘጋጃል። ያለ ዝግጅት የመጣ ሀብት እብድ ያደርጋል፣ ሞትንም ያፋጥናል። እንዲሁም ባካናና ጠፊ እንዳንሆን እግዚአብሔር ያዘጋጀናል።
ደስታችንን መመሥረት ያለብን ከምድር ሳይሆን ከሰማይ በሆነው ነገር ላይ ነው። ምድራዊ ነገር ሕልም እልም ነው። ታይቶ ጠፊ ፣ አብቦ ረጋፊ ነው። ልደትን ሞት ይከተለዋል፣ ሹመትም በሽረት ይለወጣል። ከደስታው ዘመን የኀዘኑ ዘመን ይበልጣል። የሰው ልጅን የደስታ ጥም ሊያረካ የሚችል የማይለወጠው እግዚአብሔር ብቻ ነው።
ምናልባት በጓደኞቻችን፣ በጎረቤቶቻችን ራሳችንን እየለካን እናዝን ይሆናል። ከእነርሱ ይልቅ የተባረክን እኛ ልንሆን እንችላለን። በረከታችንም ራሱ እግዚአብሔር ነው። በዚህ ደስ ሊለን ይገባል። ደስታን የሚቀማን ከሌሎች ጋር ራስን ማነጻጸር ነው። እኛ ጋ ያለው ማንም ጋ የለም። እግዚአብሔር በተፈጥሮአችን ፣ በመልካችን ልዩ አድርጎ ፈጥሮናል። ሰውነታችንን፣ ጾታችንን መቀበል አለብን። የደስታ መንደርደሪያ የሆነው መቀበል ነው። የሆነውን ያልተቀበለ ሰው በጥያቄ ይኖራል። ዓለም ክፉ ነውና የሆንከው ትክክል አይደለም በማለት እግዚአብሔር የሰጠንን ነገር እንድናርም ይገፋፋናል። ውጤቱ ግን ሕይወትን መጥላት ይሆናል።
ሳንለምን በተቀበልነው፣ ያለ ልፋት በጸጋ በተቸርነው ነገር ከውዳሴ ከንቱ መጠበቅ አለብን። መደንገጥ ያለብን ሲረግሙን ሳይሆን ሲያመሰግኑን ነው። "ሰዎች ሁሉ መልካም ሲናገሩላችሁ ወዮላችሁ ፤ አባቶቻቸው ለሐሰተኞች ነቢያት እንዲሁ ያደርጉላቸው ነበርና " ይላል (ሉቃ. 6፣ 26 )። ሞት ወደ ዓለም የገባው በውዳሴ ከንቱ በርነት ነው። የሆንኩትን የሆንኩት በእግዚአብሔር ነው ፣ ክብር ምስጋና ለእርሱ ይሁን ማለት ተገቢ ነው ። አስደንጋጩ ነገር መመስገን እንጂ መነቀፍ አይደለም። ዓለም አስብቶ አራጅ ነውና ሲያመሰግኑን ጌታ ሆይ እርዳኝ ማለት፣ ምስጋናውንም ለባለቤቱ መመለስ አለብን። ይህች ዓለም ሆሳዕና ብላ አመስግና ይሰቀል ብላ የምትገድል ናትና።
በዚህ ዓለም ላይ የምናገኛቸው ነገሮች ሁሉ ፍርሃትን የሚያመጡና የሚጨምሩ ናቸው። የእግዚአብሔር ስጦታ ብቻ፣ የእርሱ መሆን ብቻ ከፍርሃት ያድናል። የመረጠልን ከመረጡልን ይበልጣል። ያለመነውን የሰጠን የምንለምነውን አይከለክለንም። ምስጋና ወደር ለሌለው ስጦታው ! አሜን ።
ዲያቆን አሸናፊ መኰንን
ጥቅምት 6 ቀን 2018 ዓ.ም .

❤42👍3🥰1
ከምድር የጎደለ
"በእንግዶች ማደሪያ ስፍራ ስላልነበራቸው በግርግም አስተኛችው" (ሉቃ.2፥7)
ጨካኙ ዓለም እስካሁን ለእርጉዞችና ለወላዶች ይራራል። በሰለጠነው ዓለም በሕዝብ መጓጓዣ አውቶብስና ባቡር ውስጥ የእርጉዞች ወንበር አለ። ሕይወትን የተሸከሙ ፣ ትልቅ ስጦታ የሆነውን ልጅ የያዙ ናቸውና ሁሉም የሰው ልጅ እንክብካቤ ያደርግላቸዋል። በግፍ ስለ ተገደሉ ሴቶች ሲነገር እገሌ እርጉዝ ነበረች ተብሎ እንደ ሁለት ሞት ይተረካል። ሁለት ነፍስ ነው የያዘችው በማለት ለእርጉዝ ያማራትን መስጠት፣ ምቹ ቦታ ላይ ማስቀመጥ የአገራችን ባሕል ነው። ድንግል ማርያም ግን ያውም የመውለጃዋ ሰዓት ተቃርቦ ማንም አላዘነላትም። ፊቱን የሚያፈካላት፣ ቤቱን የሚከፍትላት፣ ደጁን የሚያከራያት አላገኘችም።
አማኝ ስንሆን የተለየ እንክብካቤ የምናገኝ ይመስለናል። እግዚአብሔር ግን የጠራን ለምቾት ሳይሆን ለራእይ ነው። ሃይማኖት የመዝናኛ ስፍራ ሳይሆን የመሥዋዕትነት ቦታ ነው። እንደውም ክርስቲያን ስንሆን ለማንኛውም ሰው የሚደረገው ማኅበራዊ ክብርና ጥቅም ሊቀርብን ይችላል። ድንግል ማርያም ድርስ እርጉዝ ሁና ይህን አላገኘችም፣ የመውለጃዋ ወራት ተቃርቦ ዓለም ለእርስዋ ስፍራ አልነበረውም።
በጤና መርጃ ተቋማት ሊወልዱ የተቃረቡ ሲመጡ ሁሉም ባለ ሙያ ወደ እነርሱ ይሮጣል። በየባሕሉ ምጡ ሲፋፋም እሳት አቀጣጥለው ፣ ከበው ማርያም ማርያም ይላሉ። ማርያም ራስዋ ግን ይህን አላገኘችም። የእግዚአብሔር መሆን ላለመነካት ዋስትና አይደለም፣ የመስቀሉ ወዳጅ ሆኖ በዓላማ መጽናት ነው። ብዙዎችን ያጽናና እርሱ ግን አይዞህ ባይ ሊያጣ ይችላል። ያች በምጥ የተያዘች ሴት ማርያምን አስቢ እያሏት ነው። አንድ ቀን መከራችን ለሌሎች የብርታት ድምፅ ይሆናል። አንቺስ ተከበሽ ነው ፣ ማርያም ሁሉ በሩን ዘግቶባት ጎረቤት ሳይደርስላት እንደ ወለደች አስቢ እያሏት ነው። በእውነት ቡሩካኑ በተጨነቁበት ዓለም እኛ ክፉዎቹ ብንጨነቅ ምን ይደንቃል?
በአይሁድ ባሕል አንዲት ሴት ለመውለድ ስትቃረብ የዜማ ሰዎች የዜማ መሣሪያዎችን ይዘው ቤቱን ከበው ይጠባበቃሉ። የመውለድዋ ዜና ወደ ውጭ ሲወጣ የተወለደው ወንድ ከሆነ ዜማው መሰማት ይጀምራል። ታላቅ ደስታም ይሆናል። ያ ቤት ብቻ ሳይሆን መላው እስራኤል ወንድ ልጅ እንደ ተጨመረለት ይቆጠራል። መሢሑ ሲመጣ ዓለምን እንገዛለን የሚል አሳብ ስለ ነበራቸው ያ ወንድ ልጅ እንደ ባለሥልጣን ይታይ ነበር።
ድንግል ማርያም የመውለጃዋ ሰዓት ሲቃረብ ማደሪያ አጣች። ማንም የማይፈልገው የከብቶች በረት አገኘች። በበረቱ ውስጥ ዘመድ አዝማድ ጎረቤት አልነበሩም፣ ከበረቱ ዙሪያ መሣሪያ የያዙ ሙዚቀኞች የሉም። ታላቅ ፀጥታ የሰፈነበት፣ መገፋትና ብቸኝነት ያጠላበት ይመስላል። ዮሴፍ በዚያ የድካም ዘመኑ ምን ማድረግ ይችላል ? ረዳትዎችዋ አረጋዊው ዮሴፍና ወጣትዋ ሰሎሜ ናቸው። እነርሱስ ምን ተሰምቷቸው ይሆን? በለመዱት በናዝሬት ቢሆን ይሻል ነበር ። የሚያውቃቸውና የሚያስጠጋቸው በሌለበት ፣ በብርድ ወራት፣ የመውለጃዋ ወራት ሲቃረብ፣ በሩ ሁሉ ለእነርሱ ዝግ ሲሆን፣ በበረት መውለድን ሲያዩ ምን ያህል ይሰማቸው ይሆን?
ለዓለሙ ጌታ እንዴት በሮች ዝግ ሆኑ? ሁሉ የእርሱ የሆነው እንዴት ሁሉን አጣ? የሰውን ያህል እንኳ አቀባበል እንዴት አላገኝም? ይህ ሁሉ ጥያቄ በዚያ በረት ውስጥ ከሰው ሕሊና አስተጋብቶ ይሆናል። በዚህ ጊዜ የሰማይ መላእክት ሰማይና ምድርን በዝማሬ አናወጡ። እረኞችንም በረት ውስጥ የከብቶቻችሁ ማደሪያ ውስጥ የተፈጸመውን ታላቅ ነገር እዩ ተባሉ። ሳያውቁት በረትን ለጌታ ለቀዋልና ለልደቱ ተጋባዥ ሆኑ። በበረቱ ዙሪያ የዜማ ሰዎች ባይኖሩም የመላእክት ምስጋና ተሰማ።
እጁም ልጁም ያልሰጠውን ማን ሊክሰው ይችላል? ከሰማይ ግን መልስ አለ። አንዳንድ መገፋቶች ልክ የላቸውም። መከራው የሚያስጠጋ ወገን የታጣበት ፣ ደስታው የሚተባበር ወዳጅ የሌለበት ሲሆን ይረብሻል። ወገን ለወገን የሚያደርገውን ክብር ማጣት ያስቆጫል። በጌታችን ልደት ሳያውቁት በረት የፈቀዱት እረኞች ዋጋ ተቀበሉ፣ ብዙ ባለቤቶች ይህን ተግባር ቢፈጽሙ ኖሮ በከበሩ ነበር። ዛሬ ቤተ ልሔም የጌታን የልደት በዓል የሚያከብሩ ጎብኚዎችን በግዙፍ ሆቴሎች ትቀበላለች። ባለቤቱን ግን አልተቀበለችውም። ባለን ትንሽ ነገር ጌታን ስናገለግል ዋጋችን ከፍ ያለ ይሆናል። ምናልባት እነዚያ እረኞች እኛ በረቱን እንለቃለን እናንተ ግቡ ብለው ይሆናል። ማንም ያላየውንና ያልሰማውን ክብር ለማየትና ለመስማት በቁ ።
ስንቱ በጥባጭ ልጅ ሲወለድ የዜማ መሣሪያ ይዘው ይመጡ የነበሩት የሰላም አለቃ ሲወለድ ግን አልነበሩም። ለጌታ ሲሆን ልማዶች ቀሩ፣ እንደ አምላክ ሳይሆን እንደ ፍጡርም የሚቀበለው አልተገኘም። ክርስቶስ በምድር ላይ የተገኘለት ነጻ ቦታ በረትና መስቀል ብቻ ነበር። ከወገን ከዘመድ የምንጠብቀው እልልታ ፣ የደስታ ተካፋይነት ባይኖር የመላእክት ምስጋና በሰማይ ይሰማል። በመመለሳችን በአርያም ዝማሬ ይሆናል (ሉቃ.15:7)። ሰማይ አማኝነትን፣ ተነሣሒነትን ያከብራል። ወገን ሲርቅ እግዚአብሔር ወገን ሆኖ ከእኛ ጋር ቆሟል። ከላይ ተቀብለናልና አጣሁ ብለን መማረር፣ ከለከሉኝ ብሎ ሰው መውቀስ ሊበቃ ይገባዋል። ከሰው ብንቀበል ከእግዚአብሔር አናገኝም ነበርና።
የሚያስጠጋን፣ ለአንድ ቀን መከፋት የምንሄድበት የለንም ይሆን? ምጣችን አይዞህ ባይ ፣ ግፋ ወዳጄ የሚል አጥቶ ይሆን? ይህ ሁሉ በክርስቶስ ሆኗል። የእርሱ መከራ ለእናቱ ተርፏል። መጠላታችንን ጌታ ተቤዥቶታል። ደስታችን የሚያስደስተው ሰው የለም ብለን እናስብ ይሆን? ዕድሎቻችንን መደበቅ እንደ ዋስትና ቆጥረነው ይሆን? ጌታም ሲወለድ የተደሰተ ጎረቤት አልነበረም። ወንድ ልጅ ተወለደ ብሎ ያለ ዘመኑ ከሰባት መቶ ዓመት በፊት የዘመረው ኢሳይያስ ነው። በዘመናችን የተገፋን ፣ ያለ ዘመናችን የተከበርን እንሆናለን። ዓለም ህልውናችንን ካላከበረ መቃብራችንን ማክበሩ አይቀርም። አብሮን የሚደሰት ብናጣ ቅዱሳን መላእክት በምስጋና ሊተባበሩን ቆመዋል። እንደውም ስለ እኛ መዳን አስቀድመው ዜማ ጀምረዋል።
ከምድር የጎደለ ከሰማይ ይሞላል፣ የጎደለው ለበለጠ ክብር ነው። ሙዚቀኞች ሲቀሩ ቅዱሳን ዘማሪዎች ይመጣሉ።
ተመስገን !!
ዲያቆን አሸናፊ መኰንን
ጥቅምት 7 ቀን 2008 ዓ.ም

❤42👏2👍1
ዛሬ ዓርብ ጥቅምት 7 ቀን 2018 ዓ.ም. ከምሽቱ 2:00 ሰዓት ላይ ትምህርታችን ይጀምራል ::
የትምህርታችን ርእስ " ብሉይ ኪዳን"
ክፍል 3
የሚል ነው

❤18👍3