ለስእለቴ አብቃኝ
እግዚአብሔር በድንቅ አሠራሩ ካሰኝ፣ በማትመሽ ቀኑ ደረሰልኝ ለማለት አብቃኝ። እኔም እንደ ሰዉ ተራው ይድረሰኝ ። ለስእለቴ አብቃኝ! አምላክህ የት ነው? ያሉኝ የስጦታህን ተአምር በእኔ ይመልከቱ ፣ አምላኬ ትቶኛል ያለው ልቤ "እግዚአብሔር ለካ ለዘላለም አይጥልም" ብሎ ይዘምርልህ። የበዪ ተመልካች እንዳልሆን፣ እንዴት ሆነ ያንተ ጉዳይ? የሚሉኝ ቍስሌን እንዳይቀሰቅሱብኝ፣ አልነጋም ወይ? የሚለኝ ልጄ ብርሃን እንዲያይልኝ እባክህ ለስእለቴ አብቃኝ። ለትዳሬ ሁሉን አለመንገሬ፣ የችግሩን ጥልቀት ቢያውቁ ይሰበራሉ ብዬ ነው ፣ ለትከሻቸው አስቤ ዝም ስል ድብቅ ይሉኛል። እንዲበሉ ብዬ በልቻለሁ ስል ሌላ ቤት ይዟል ብለው ይጠረጥሩኛል። የልብ አውቃ አንተ ብቻ ነህ።
ለስእለቴ አብቃኝና እኔም ለአምላኬና ለሰው የገባሁትን ቃል ለመፈጸም አብቃኝ። ከራሴ ጋር ያለኝ ክርክር ማብቂያ ሲያጣ፣ ትግሉም ገላጋይ የለሽ ሲሆን፣ ጥርስ እየሳቀ ልብ ሲያር አቤቱ ለስእለትህ አብቃኝ። የምትሠራበት ቀን፣ ለእኔ የምትፈርድበት ሰዓት ቢርቅብኝ ሰው ነኝና ተረዳኝ። ሥጋ ነከስኩ ብዬ ቀንድ ስነክስ ጥርሴን እሰብራለሁ። ዓሣ ለመንኩ ብዬ እባብ አዘንባለሁ። ዳቦ ጠየቅሁ ብዬ ድንጋይ እይዛለሁ። አቤቱ ፍለጋ ያደከመኝን እባክህ ለስእለትህ አብቃኝ።
ቀኑ መሸ ብዬ ተስፋ እንዳልቆርጥ በገባዖን ለኢያሱ ፀሐይ ማቆምህን ልቤ ይወቅ። ለመሻገር ባሕሩ ጥልቅ ነው ብዬ ስፈራ ቀይ ባሕርን የከፈለ ያንተ ሥራ ከእኔ ጋር ይሁን። ደርሰው የማያኩት የቋንጃ እከክ ሲሆንብኝ፣ ነገሩ ሁሉ ድፍን ቅል ሆኖ ሲያስጨንቀኝ ፣ የሰው ልብ የመንፈቅ መንገድ ያህል ቢጓዙ አልታወቅ ሲል ፣ የተዘጋው ከተማ ሲያውከኝ ኢያሪኮን ያፈራረሰው ያ ክንድ ዛሬም አለሁ ይበለኝ።
ላታመልጠኝ አታሯሩጠኝ እያለ ሲያሳድደኝ ጠላቴ፣ ላልመለስ ወደ ኋላ ጉዞዬ ይሁን ካንተ ጋራ። አቤቱ ለስእለትህ አብቃኝ አዲስ ነገር መናፈቅ ደከመኝ፣ ተስፋ የሚሰጡኝ እየሸነገሉኝ ሆኖ ተሰማኝ። ሁሉን ተለማማጭ ሆኜ የምታኖረኝን እንዳልረሳ፣ የሰው ፊት በራ ጠቆረ ብዬ ከፍ ዝቅ እንዳልል አቤቱ ለስእለቴ አብቃኝ። ለልመና ከመጣሁበት ደጅህ ለምስጋና መልሰኝ።
ይህ የመጨረሻዬ ነው ብዬ ብዙ ለምኜሃለሁ ፣ ሰጥተህ የማትሰለች መሆንህን ረስቻለሁ። ካንተ እጅ ሲቀበሉት አያሳቅቅም። በልኬ ሳይሆን በልክህ ትሰፍርልኛለህ። ከእኔ እንጂ ካንተ አይጎድልም። ማጣት ጨዋ ቢያደርገኝ፣ ማግኘት ያባልገኛል። ጌታዬ ሆይ ያለ እጅህ በረከት እንዴት እኖራለሁ? ካንተ ደጅ በቀር የማንኳኳው ሌላ በር የለም። ናፍቄአለሁ ለስእለትህ አብቃኝ።
እኔንም ወገኔንም ከነሽክማችን እንዳንሻገር ፣ ወልድ ሆይ መስቀል በመሸከምህ የነጻነት ዓመት ስጠን። የሞቱት በኃጢአታቸው ፣ የቆምሁት በጽድቄ አይደለም። ዕድሜዬን ለበጎ ሥራ እንዳውለው አንተ እርዳኝ። ከዘመኑ በፊት እኔ ልለወጥ። ለስእለቴ አብቃኝ ስከተለው የሸሸኝ ዕድል ፈልጎኝ ይምጣ። በሚራራው ልብህ አሜን!
#ዲያቆን #አሸናፊ #መኰንን
ጳጕሜን 3 ቀን 2017 ዓ.ም.

❤70👏6🥰4😢4
የሚያውቁኝን አሰንብታቸው
በማላውቃቸውና በማያውቀኝ መካከል መኖር ከባድ ነው ። ብዙ ኖሮ ባይተዋር መሆን የሚገርም ነው። ሊያውቅህ የማይፈልግ ሁልጊዜ እንደተዋወቀህ ይኖራል። እባክህ ጌታ የሚያውቁኝን አሰንብታቸው። የኋላ ወዳጅ የፊቱን አያውቅም፣ ቢቀርብም በፍርሃት እንጂ በፍቅር አይሆንም። እነዚያን ስወለድ ያዩኝን፣ ማርያም ማርያም ብለው የተማጸኑልኝን እባክህ አሰንብታቸው። አባት እናቴ ባይኖሩ ምትክ እንዳደርጋቸው እነዚያን የጠዋት ወዳጆቼን ክርስቶስ ሆይ እባክህ በሞቴ አቆያቸው። ሰፈሩ ጭር እንዳይል፣ መንደሩ ሞገስ እንዳያጥረው እነዚያን ደጋግ እባክህ አቆያቸው።
ስድህ መሬት ላይ ተቀምጠው ያገዙኝን፣ እንድራመድ እጆቿን የያዙትን፣ የእናቴ ጡት ሲነጥፍ አጥብተው ያሳደጉኝን እነዚያን ሩኅሩሆች እባክህ ዘመን ጨምርላቸው። "ልጄን አትምታብኝ" ብለው ከአባቴ ጋር የታገሉትን፣ "እርሱን የነኩ እንደሆነ እቀየመዎታለሁ" ብለው እናቴን ያስፈራሩትን እነዚያን በቀሚሳቸው የተደበቅሁባቸውን እናቶች እባክህ አቆይልኝ። የዛሬውን ጉድ እንዲያረክሱልኝ፣ የጠብ ያለ የሚለውን ዘመን እንዲያስረሱኝ እነዚያን ቡሩካን እባክህ አትንካብኝ።
ሊሸጡት ካስቀመጡት ጥቢኛ ላይ "ብላ" ብለው የሰጡኝን፣ ከልጃቸው እኩል አንጥፈው ያስተኙኝን፣ አዝለው ያሳደጉኝን፣ ወላጆቿ እስኪመጡ ለሳምንት ለወር የያዙኝን እነዚያን የአደራ ልኮች እባክህ አሰንብትልኝ። ከድሀ የተወለደ ቶሎ አያገኝም፣ ድሀ ምን ትሠራለህ? እንጂ ምን ትበላለህ? የሚለው የለም። እጄ እስኪሞላ ሞት እንዳይነጥቅብኝ እነዚያን ባለ ውለታዎቼን እባክህ አቆይልኝ። ለሰው ሁሉ "ልጄ ነው የሚመስለኝ" ብለው የሚያወሩትን ፣ ሲያዩኝ እንባ እንባ የሚላቸውን እነዚያን የኢትዮጵያ ወላጆች እባክህ አሰንብታቸው። ከሌላቸው ላይ የሰጡኝን፣ የሩቅ ዘመድ ሳይደርስ የደረሱልኝን፣ የማይወደደውን ማንነቴን የወደዱትን፣ "እስቲ ና ቆሻሻህን ልጥረግልህ" ያሉትን እነዚያን አይፀየፌ እባክህ አቆይልኝ። የአንዱ ቀን መንገድ ዓመት እየፈጀብኝ፣ ለሌላው የቀለለ ለእኔ ከባድ እየሆነብኝ እንዳላረፍድና እንዳላጣቸው እባክህ ጌታዬ አሰንብታቸው። ምን ቢያገኙ አብሮ ከተቸገረ ጋር ካልበሉት አይጣፍጥም። እንጀራዬን ከመራራ ቅጠል ጋር እንዳልበላው እባክህ አምላኬ እነዚያን የረሀቤን መድኃኒት አሰንብታቸው ።
ዛሬ ሲመሸ ከቤት ይወጣል። "አልመሸም ወይ ? ወደ ቤትህ ግባ" የሚሉኝን የምሽቱን አውሬ ቀድመው ያዩልኝን እባክህ አሰንብትልኝ። ዛሬ ልጅ ቢያጠፋም የሚቆጣው፣ ቢስት የሚመልሰው የለም። ልጅ ሁሉ የእኔ ነው ብለሁ ያምኑ የነበሩትን እነዚያን ሆደ ሰፊዎች እባክህ አሰንብትልኝ። ልፈልጋቸው ስሄድ ሁሉም የሉም። በራቸውን ሳንኳኳ ቤቱ ተሽጧል ይሉኛል። አንድ ወላጅ ያቆየውን ቤት አሥር ልጅ መጠበቅ እንዴት ያቅተዋል? ገንዘብን እንጂ ክብርን የማያውቁ ልጆችን እነዚያ ደጋግ እንዴት ወለዱ? የአገሬ ወላጅ በጣር አሳድጎ ለማረፍ ለምን አልታደለም? የልጁን ሬሳ በአደባባይ ወድቆ እንዳላየ ትራፊ ልጁ ሲዳር ለምን አልቆየም?
እባክህን ጌታዬ የሚያውቁኝን አሰንብታቸው። አነሰ በዛ ብዬ እንዳልዘገይባቸው፣ ዕድሉ አምልጦኝ ቁጭቱ እንዳይጎዳኝ እኔንም አፍጥነኝ። ዓይን ነው ዘመዱ ለመተያየት አፍጥነኝ። ምን ይዤ ሲሉ ነው ተቆራርጠው የሚቀሩት እባክህ ዓይኔን ግለጥልኝ። በሙሉ ዓይን አላየውም የሚሉትን፣ ልጄን ሰስቼ እንዳልበላው ብለው እንትፍ የሚሉትን፣ ንጉሥ እንደመጣ የሚሯሯጡልኝን ፣ እነዚያን የወላጅ ምትኮች እባክህ አሰንብትልኝ። የቤት ልጅ አልነበርኩም፣ ሁሉ ጠባቂዬ ነበርና የሀገር ልጅ ነበርሁ፡፡ ሁሉ ቤት አድራለሁ፣ ሁሉ ቤት እበላለሁ ፣ አባት እናቶቼ ሺህዎች ነበሩ። እንዲህ አድርገው አገር ያቆዩትን እነዚያን ደጎች አሰንብታቸው።
አንተ ስትወለድ እንዲህ ተፈጸመ እያሉ የሚያወሩትን የሚያውቁኝን አሰንብታቸው። ማነው ሳይሉ ለወደቀው ሰው ደረታቸውን መትተው እንጀራ የሚሰጡትን፣ ዘሩ ምንድነው ? ሳይሉ ላዩት ሬሳ የሚያለቅሱትን እነዚያን አዋቂዎች ፣ እግዚአብሔርን የሚፈሩትን አሰንብታቸው። ስታመም የሚደነግጡ ፣ ስሞት የሚያለቅሱ እነርሱ ናቸውና ዋጋዬን የሚያውቁትን እነዚያን ጽንፍ የለሽ እባክህ አቆያቸው። ማለፋቸውን እፈራዋለሁ። በአፍሪካ ምድር ከወጣት ሞት በላይ የአዋቂ፣ የትልቅ ሰው ፣ የአረጋዊ ፣ የወላጅ ሞት ያስጨንቃል። ትልቅ ቤተ መጻሕፍት ይቃጠላል። እነርሱ ያለቁ ቀን ኑሮ ቁስ እንጂ ጣዕሙን ያጣል። ልጅም ታሽጎ ያድጋል። ጓደኝነት በገንዘብ ይለወጣል። ለሞተ የሚያለቅስ ይጠፋል። ሰው ቁጥር ሆኖ ስንት ሰው ሞተ? ይባላል።
አንተ የምወድህ ጌታዬ የሚያውቁኝን አሰንብታቸው!
ዲያቆን አሸናፊ መኰንን
ጳ ጒሜን 4 ቀን 2017 ዓ.ም.

❤53👍4🥰3😢1
Forwarded from Nolawi ኖላዊ
በዲያቆን አሸናፊ መኰንን የተጻፉትን ና በገበያ ላይ ያሉትን እነዚህን መጻሕፍት በሙሉ ለሚገዙ አዲስ አበባ ላይ ላሉ ወዳጆች ያሉበት ድረስ እናደርሳለን!
1- የእግዚአብሔር ትዕግሥት 400
2- የኑሮ መድኅን 200
3- ተንሥኡ ለጸሎት 60
4- ረጅሙ ፈትል 170
5- የጊዜው ቃል 200
6- ቅዱስ ጋብቻ 200
7- እንደ እኔ ከተሰማችሁ 150
8- የሕይወት መክብብ 150
9- አካላዊ ቃል 250
10- ቃና ዘገሊላ 250
11- ኒቆዲሞስ 170
12- ሳምራዊቷ ሴት 250
13-መጻጉዕ 250
14- የወዳጅ ድምፅ 180
15- ኅብስተ ሕይወት 250
16- የሕይወት ውኃ 250
17- ኦሪት ዘፍጥረት ትርጓሜ 300
18- ምዕራፈ ቅዱሳን 200
19- የደስታ ቋጠሮ 130
20- የዕለቱ መና 200
21- የበረሃ ጥላ 200
22- ወዳጄ ሆይ 200
23- የአገልግሎት ቱንቢ 250
24- ጴጥሮስ ወጳውሎስ 250
25- ሰንፔር 170
26- መንፈሳዊ በረከት 500
27- ጥበበኛው ድሀ 2ዐዐ
አጠቃላይ ድምር 5,980 ብር
በሚከተሉት የባንክ ሂሳብ በመላክ በ0911 699907 ላይ በቴሌግራም ደረሰኙን ይላኩ ፈጥኖ ይደርሰዎታል
የሕይወት ዘመን ስንቅ ያለባቸው ድንቅ መጻሕፍት!!!
አሸናፊ መኰንን ወርቁ
Ashenafi Mekonnen worku
የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ
1000165078482
አቢሲንያ ባንክ
23202573
ወጋገን ባንክ
0870286030101
አዋሽ ባንክ
Awash Bank
01320034656200

❤18
አልጨርሰውም
ክፉና አስጨናቂ ዘመን ነበር፣ ከላይ ስክበው ከሥር ይናዳል ፣ በሮች ሁሉ ክፍት ሆነው እኔ ስደርስ ይዘጋል ... ጌታዬ ሆይ ይህን ንግግር አልጨርሰውም ፤ አንተ ለእኔ መልካም ነህ ፣ ጎደለ ለማለትም ዘመን መጨመር አለበት ። ደግሞም የሰው ጠባይ የማይጨበጥ ሆነ፣ ቁምነገር የሌለው ትውልድ እንደ ምርት ተትረፈረፈ ... ጌታዬ ሆይ ይህን ቃል አልጨርሰውም፤ በህልውናህ መታጣት፣ በጠባይህ ወረት የሌለብህ አንተ ከእኔ ጋር ነህ። ደግሞም ሁልጊዜ በጌታ ደስ ይበላችሁ እንጂ ሁልጊዜ በሰው ደስ ይበላችሁ አልተባለም። ከዚህ ኑሮ የሞተ ይሻላል፣ የሚለቀሰው ለእኛ ነው ...ጌታ ሆይ ይህን ንግግር አልጨርሰውም ፣ የሙታንም የሕያዋንም ጌታ አንተ ነህ ፤ የገነት መዓዛም አንተ ነህ ፣ ገነት ያላንተ ሲኦል ናት :: መኖር ያንተ ፈቃድ እንጂ የእኔ ፈቃድ አይደለም፣ እኔን በምድር በማስቀመጥህ አልተሳሳትህም ፣ አኑረህ አሠራኝ እንጂ ውሰደኝ አይባልም። ሞት ባይለምኑትም አይቀርምና ለሚበልጠው ጸጋ እንትጋ። ተቆርቋሪ ወገን ፣ ደራሽ ዘመድ የለኝም፣ እንደ ምልምል ዛፍ ብቻዬን ቆሜአለሁ... ጌታ ሆይ ይህን ንግግር አልጨርሰውም። ዘመድ ቢበጅ አቤልና አምኖን በገዛ ወንድሞቻቸው በቃየንና በአቤሴሎም እጅ አይሞቱም ነበር። አንተን የሰቀሉህ የገዛ ወገኖችህ ፣ የእናትህ ዘመዶች ናቸው። ዘመድ አንተ ብቻ ነህ! ዘመድ እኔ ብቻዬን ላቁስለው ብሎ ሌላ ሲነካ የሚጣላ ነው።
ብልጥ መሆን ጥሩ ነው፣ ብዙ ትርፍ ያስገኛል፤ ብዋሽ ምናለበት ይህቺን ታህል ሳልበድል እውላለሁ ወይ? ያለ መሰላል መውጣት አይቻልም፣ እገሌን መጠቀሚያ ባደርገውስ ... ጌታ ሆይ ይህን ንግግር አልጨርሰውም፣ ከአፌ ወጥቶ ሳያልቅ ቀፈፈኝ ፤ ጤና በብልጠት ፣ ሕይወት በገንዘብ አይገኝም ፤ ባለጠጋ ዘመዱ ይመካበታል፣ እርሱ ግን እየተደበቀ ይኖራል ። የበረከት ምንጭ አንተ ነህ ፣ ለራሴ ከቆረስኩት አንተ ያስብህልኝ በለጠ።
ዕድሌ ጥሩ አይደለም፣ ሙሉ ዕጣ ቢሆን ለእኔ አይወጣልኝም፤ ግንባሬ ክፉ ነው፣ አይሳካልኝም ፤ የሞተ ውሻ ለእኔ ሲሆን ይነሣል ፣ ሰው አይወጣልኝም፣ አገሩ ለእኔ አይሆንም ... ጌታ ሆይ ራሴን በቃሌ አላስረውም፣ ይህን ንግግር አልጨርሰውም። የዳዊት ዕድል ፈንታ አንተ አይደለህም ወይ? ከእረኝነት ወደ ንጉሥነት የሚያወጣ ያንተ ዕድል ፈንታ ከሁሉ ይበልጣል። ገመድ ባማረ ስፍራ ትወድቅልኛለች፣ ዕጣዬንም አንተ ታወጣለህ ።
አጥሬ ተደፍሯል፣ ጠላት ያሻውን ያደርግብኛል፣ ከፍታዬ ዝቅ ብሏል የናቅሁት ይረግጠኛል ...ጌታ ሆይ ይህን ንግግር አልጨርሰውም ፤ ከጠላት ውጊያ በላይ የእኔ መኖር ይገርማል። በተኩላዎች መካከል እንደ በግ ማሰማራት ክንድህ ይችላል። እስከ ዛሬ ያለሁት በድንቅ ምሕረትህ ፣ በማይዘናጋ ጥበቃህ ነው። ያለ ልብስ ባለ ሞገስ፣ ያለ አጥር ባለ ግርማ ታደርጋለህና ተመስገን :: ደግሞም የሚመጣው ዓመት ምን ይመስል ይሆን? ያው ነው ፣ ቀኑም ቀን ነው ፣ አገሬም አትለወጥም... ጌታ ሆይ ይህን ግግግር አልጨረሰውም:: መኖር ሹመት ነው፣ ንጉሥ እየሞተ ድሀ ይኖራልና። ከአንተ አዲስነት የተነሣ ዛሬ አዲስ ነው። በሥራ ላይ ነህና ዓመቱ ድንቅ ፣ ነገ የተሻለ ነው። ነገ የተሻለ ባልበላ ስለ ሕይወት የተሻለ እውቀት ይኖረኛል።
ጌታ ሆይ ጨርሶ መብላት እንጂ ጨርሶ መናገር መልካም አይደለም። ቃሌን ይቅር በለው፣ በቃልህ መንገዴን አቅናው። በምድራዊና በሰማያዊ በረከትህ የምባረክበት ዓመት ይሁን። ካንተ ጋር ተራራ ቢሆን ሸለቆ ጉዞው መልካም ነው ። አሜን !
ቡሩክ ዓመት ይሁንላችሁ !
ዲያቆን አሸናፊ መኰንን
መስከረም 1 ቀን 2018 ዓ.ም.

❤76🥰8👏6
እንዴት ልዘን?
የመደሰትና የማዘን፣ የመሳቅና የማልቀስ ተፈጥሮ ሰጥተኸኝ እንዴት ልዘን? ጌታዬ ቸግሮኛል። ሁሉም ነገር የእንቧይ ካብ ሲሆን፣ ላይነጋ የመሸ ሲመስል ከዚህ በላይ ምን ልሁን ? ላልቅስ እንጂ ስል ፊቴ ትመጣለህ። ያጎረሰኝ እጅህ አሁንም ሊደግመኝ አፌ አጠገብ ነው። ኧረ ገለል በልልኝ ልዘን ፍቀድልኝ። እንደ ኑኃሚን ብዙ ሆኖ ወጥቶ ብቻ መመለስ ፣ ልጅን ቀብሮ ነጭ መልበስ እንዴት ይቻላል? እንዳዝን የሚጠብቀኝ ብዙ ወገን አለ፣ ለእውነትም ለይሉኝታም እባክህ እንዳለቅስ ፈቀድልኝ። እንባዬ ተሰንቅሮ፣ ልቤ ላይ ተተክሎ ወግቶ እንዳይገድለኝ እባክህ እንዳዝን ፍቀድልኝ።
ልቅሶዬን ፍቅርህ፣ ግፌን ውለታህ እየካሰብኝ እንዴት ልዘን እባክህ ገለል በልልኝ። ሃና ልቤ ልጅ ጎደለ ብሎ ሲያለቅስ ሕልቃና ማንነቴ ከአሥር ልጅ ጌታ ይበልጣል ይለኛል።
በአራቱ መዓዘን የተወጠርኩ ሲመስለኝ ፣ የወደድኩትን አጥቼ የጠላሁት ሲናፍቀኝ ላዝን ምንጣፍ አስተካክላለሁ ፣ ውለታህ ድቅን ሲልብኝ "ከጌታዬ ምን ጎደለ?" ብዬ እተወዋለሁኝ። መስቀሌ ውበት የለውም፣ ያንተ መስቀል ግን ውብ ያደርጋል። ደግሞም ሲያዩት ያምራል ፣ ዕርቃንህን ሆነህ መስቀል ላይ ታምራለህ። ለውበቴ የመጣውን ለሞቴ ነው ብዬ ትርጉም ሰጥቼ ለማዘን ጊዜ እመድባለሁ፣ ጠላቴም ሆድ እያስባሰኝ፣ እየቆነጠጠ ያስለቅሰኛል። ይህ ፅንስ አይረባም ይወገድ ተብሎ የተወለደ ዛሬ ላይ ደርሶ እንዴት ያዝናል? ባለሙያ ሞት አውጆብኝ በሕይወት ካለሁኝ ምንም ለማዘን መብቴ ቢሆንም አንተን እያየሁ እንዴት ልዘን? ሰው ነኝና አመነታለሁ፣ ግን ያላንተ አይሆንልኝም ብዬ መንገዴን እቀጥላለሁ ። ሰው ነኝና አልቅሼ ይውጣልኝ ብዬ መሐረብ አሰናድቼ በሬን እዘጋለሁ ። ከጎደለብኝ የሞላው ብዙ መሆኑን አይቼ አፍሬ በሬን እከፍታለሁ።
ብዙ መፈተን፣ በመከራ ሰፌድ ላይ እንደ ስንዴ መበጠር ከባድ ነው። አንዱ መከራ ለሌላኛው አቀብሎኝ ይሄዳል እንጂ ይበቃዋል ብሎኝ አይሄድም። በከበዱኝ ቀኖች፣ አንተን ባላውቅ ኖሮ ምነው በሞትኩ በምልበት ሰዓት እንኳ እኔ አለሁ አትበለኝ ፣ እንዳዝን ገለል በልልኝ። ልቅሶ ግዝረት፣ እንባ ጥምቀት ሆኖ ይገላግለኝ፣ እንዳዝን ፍቀድልኝ። የጸናው መሬት እኔ ስረግጠው ይናዳል፣ የመጣው ነገር ከምችለው በላይ ሆኗል ብዬ ላዝን ስዘጋጅ፣ ሆዴ ሲላወስ፣ እንባ ጋኑን ሰብሮ ሊወጣ ሲል የተቸነከረ እጅህን ታሳየኛለህ። ስላቆሰሉህ እልፎች ሳይሆን ስለ ቆሰልኩልህ አንዱ ስለ እኔ አስብ ትለኛለህ። ያለኝ አቅም እርሱ ነው ፣ ጨርሼ እንዳዝን፣ የኖርኩበትን ኑሮ እንድሰርዝ ፍቀድልኝ። በአሳብ የሚረዳኝ፣ በጉልበት የሚቆምልኝ የለም ። ከፈተናው የተነሣ የበደሌ ከፍታ ምን ያህል ቢሆንብህ ነው ? እላለሁ። መልስ ያጣሁ ሆኖ ተሰምቶኝ ላዝን ስዘጋጅ እንባዬን ነፋስ እንደሚበትነው ደመና ትወስድብኛለህ ፣ እንዳዝን ፍቀድልኝ።
ሞትን በምለምንበት፣ ይበቃኛል ጥራኝ በምልበት ሰዓት ኤልያስ ልቤን በሰረገላህ ትነጥቀዋለህ። ለሁሉም ነገር ጣዕም ሳጣ ፣ ለመመረር ሰዓቱ ነው ስል፣ ባወቅሁት መጠን አለመኖሬ ትዝ እያለኝ ምሬቴን እመልሳለሁ። የገነትና የሲኦል ጥያቄ ስላለብኝ ፣ ይቅርታ ጠይቆ ለማረፍም ሳይሆን ይቅርታ ልትጠየቅ የሚገባህ ክቡር መሆንህን አስብና መልሼ ይቅር በለኝ እልሃለሁ። እኮ እባክህ ዛሬ ልክ ልሁንና እንዳዝን ፍቀድልኝ። ከእኔ እንጂ ካንተ አልጎደለምና ፣ ከሰው እንጂ ካንተ ያጣሁት የለምና ልቆጣህ መጥቼ ተገሥጬ እመለሳለሁ።
የት ነህ ብባል እዚህ ጋ ነኝ በማልልበት በጨለማው መንገድ ላይ ስሆን ፣ ዕድሌ ምንድነው ? ብዬ ለማልቀስ፣ የሰውን ጥያቄ ለመሸሽ እጥራለሁ። ካንተ ጋር እየተሟገትሁ መኖር ይበቃኛል ብዬ ራሴን በኀዘን ለመቅጣት እነሣለሁ። ያነጋልኝ ቸርነትህን ሳስብ፣ በአልጋ ያሉትን በሽተኞች ሳስታውስ ማረኝና ልግባ አገሬ እላለሁ። የተቀበልኩት እውነትና የምኖረው ሕይወት ሲለያይብኝ፣ ራሴን ያለ ክርስቶስ ሳየው አስፈሪ ሥዕል ሲመጣብኝ ማዘን እፈልጋለሁ። መልሰህ በር ዘግተህ ትመክረኛለህ ። በጽኑ እጅህ ከጎርፉ ውስጥ ታወጣኛለህ።
ብቻውን የሚወድቅ ነገር የለምና ለትዳሬ መፍረስ፣ ለባልንጀርነቴ መበላሸት የእኔም እጅ አለበት። ጌታ ሆይ ትዳር ነበረኝ፣ ልጅ ነበረኝ ማለት ያቆስላል፣ አሁን እንኳ ተወኝ ልዘንበት? የሣር ተማሪ ሆኜ "ሀ" ያልኩበትን ዘመን አላውቀውም፣ ሁሉንም ነገር የምማረው በሐሳር ነው። እንዲህ ብዬ ላዝን እፈልግና ከእጅህ የበላሁት ያንቀኛል፣ የበረሃው ጓዴ መሆንህ ድቅን ይልብኛል። ባዝንም ባለቅስም አለማመስገን ይቆረቁረኛል።
እንዴት ልዘን? ያበላኝ እጅህ ይታየኛል !
ዲያቆን አሸናፊ መኰንን
መስከም 2 ቀን 2018 ዓ.ም.

❤48🥰4😢4👍2
ዛሬ ዓርብ መስከረም 2 ቀን 2018 ዓ.ም. ከምሽቱ 2:00 ሰዓት ላይ ትምህርታችን ይጀምራል ::
የትምህርታችን ርእስ " መጽሐፍ ቅዱስን እንወቅ"
ክፍል 4
ስያሜው ፣ ሥልጣኑና ስህተት አልባነቱ ይገልጣል።
ማስታወሻ ብትይዙ ይመከራል።
ሌሎች ወገኖቻችንንም ጋብዙ
https://www.tg-me.com/Nolawii
የትምህርታችን ርእስ " መጽሐፍ ቅዱስን እንወቅ"
ክፍል 4
ስያሜው ፣ ሥልጣኑና ስህተት አልባነቱ ይገልጣል።
ማስታወሻ ብትይዙ ይመከራል።
ሌሎች ወገኖቻችንንም ጋብዙ
https://www.tg-me.com/Nolawii
Telegram
Nolawi ኖላዊ
ይህ ቻናል ኦርቶዶክሳዊ መንፈሳዊ ትምህርቶች የሚተላለፉበት ነው። እግዚአብሔር አገልግሎቱን ያስፋ!
አገልግሎቱንም ያግዙ!
0911699907 ዲያቆን አሸናፊ መኰንን
አገልግሎቱንም ያግዙ!
0911699907 ዲያቆን አሸናፊ መኰንን
❤25👍3👏1
አይደክምህም ወይ?
ሁልጊዜ በሥራ ላይ ነህ ፣ የማትሠራበት ቀን፣ የማትሠራለት ፍጥረት የለም። ሰውና እንስሳው አንተን ይጠባበቃል። ለሁሉ አንዱ ትደርሳለህ። ሁሉን በአንዱ ክንድህ ትጋርደዋለህ ። ይህን ሁሉ ስትከውን አይደክምህም ወይ? ዘላለም እንቅልፍ የለብህም፣ ከፀሐይ ይልቅ በሁሉ አገር ሰልጥነሃል፤ በመንግሥተ ሰማያትም ራስህ ታበራለህ። የፀሐይ ፀሐይ አንተ ነህ። የማትጠልቅ ጀምበር፣ እንደ ተወደድህ የምትቀር አንተ ብቻ ነህ። ሰው ሁለት ቃል ያናግራል፤ የፊት ምስጋና ለኋላ ሐሜትም ያስቸግራል። ሁለት ቃል የማታናግር የሰዎች ሰው አንተ ነህ።
ሁሉን ስትወድ አይደክምህም ወይ? ሰዎች ክፉ የሚሉት ዘንዶም ምግቡን ካንተ ያገኛል። ከመልካምነትህ የወጣ ነውና ተፈጥሮ ቅዱስ ነው። ምርጫው ካረከሰው በቀር የሰው ትንሽ የለውም። ድሀ ባለጠጋን እኩል መውደድ ትችላለህ፣ ሁሉም በፊትህ ነዳይና ለማኝ ነውና። በራሱ ይኑር ብለህ ፍጥረትን ያለቀቅኸው በራሱ መኖር ስለማይችል እንጂ አንተ ጨቋኝ ስለ ሆንህ አይደለም። ፍጥረት ያላንተ አንካሳና አቅመ ቢስ ነው። ሁሉን በቃልህ የደገፍከው አንተ ነህ።
ስንቱን አደፋፍረህ ከቤት ታወጣዋለህ፣ ስንቱን አባብለህ ታስተኛዋለህ። ለበሽተኛው አልጋ ታነጥፋለህ። ያንተ ስፍራ ፣ የተወሰንህበት ክልል የት ነው? ከብሶተኛው ጋር ተበድለሃል፣ ከዳኛው ጋር ፍትሕ ትሰጣለህ። የት ነው አገርህ? ያንተ ያልሆነ ሕዝብስ የትኛው ነው? አንተ የማታስፈልገው በራሱ የቆመ ኩሩ ማነው? አንድ ቀን ውኃ ካላገኘ የሚበላሽ ፍጡርስ እንዴት በአንተ ላይ የድፍረት ቃል መናገር ይችላል?
አንድ ሆነህ ሁሉን ታጠግባለህ። ሁሉ የእኔ ሲልህ ለሁሉ ትበቃለህ። እባክህን ዕረፍ አይደክምህም ወይ? አንድ ሰው መሸከም አቅቶን ደክመናል፣ ይህን ሁሉ ፍጥረተ ዓለም ለሆዱ እንጀራን፣ ለኃጢአቱ ይቅርታን፣ ለመንፈሱ እርካታን ትሰጠዋለህ። ለእኔም እዘኑልኝ ደክሞኛል አትልም። እያንዳንዱ የዝናብ ጠብታ ባንተ ይታወቃል፣ ለበረሃውም ታዝንለታለህ። በረዶ ላይ ለሚኖረው ፀጉር ታለብሰዋለህ፣ የበረሃውን እንስሳ መላጣ ታደርገዋለህ። ማንን የት ቦታ መላክ እንዳለብህ ታውቃለህ። አክባሪዎች እንጂ አማካሪዎች የሉህም። ያልከውም ይሆንልሃል፤ ጅምርህ ይፈጸማል። ይህን ስፍራ ሳትለቅ የምድር ጥግ ትገኛለህ። ጠፈርን ለመንካት መንጠራራት የለብህም፣ ሰንበትን ለሰው የሰጠህ ሰንበት የለብህም። አይደክምህም ወይ?
እኛ ለአንድ ሰው ምግብ ለመሥራት ይደክመናል። አንተ ግን ለሁሉ ታበስላለህ። እጅግ የተዋብህ ብትሆንም ኃጢአት ያጎሳቆለንን እኛን ትወደናለህ። ብዙ ወደኸን ትንሽ ብንወድህም አትጠላንም። የነገሥታት ምክር ላይ ተገኝተህ ታዳምጣለህ፣ ከተመራማሪዎች ጋ በቤተ ሙከራ ትገኛለህ ። ጠባቂዎችን ትጠብቃቸዋለህ። ቤተ ሠሪ አንተ ነህ ፣ ቤቱንም ሰውየውንም የሠራኸው አንተ ነህ። ያንተ ሥራ ግሩም ነው። ቤትን ያለ ምሰሶ ታቆማለህ፣ ምድርን ያለ መሠረት ታጸናለህ። ባንተው ሀብት ነዳጅና ወርቅ፣ እህልና መድኃኒት በውድ ይሸጣል። ሁሉ ነዳይ ሳለ ባለጠጋና ድሀ አገራት ይባባላል። ሁሉን ሳትታዘብ ታኖረዋለህ። የሰውን ድካሙን አንተ ታውቀዋለህ። እኛ የሰው የቁንጅናው፣ የጉልበቱ፣ የሥልጣኑ ወዳጅ ነን። አንተ ግን ራሱን ሰውዬውን ትወደዋለህ። ወርቅ አይደልልህ ፣ ጎበዝ አያሸንፍህም። የተጣላህን ታባብለዋለህ፣ ምንም ላታገኝ ላድንህ ብለህ ትለምናለህ። አፍቃሪ ነህ ግን ተለማማጭ አይደለህም። መሐሪ ነህ፣ ዓመፀኞችን ግን ትቀጣለህ። ትመለሳለህ፣ ከሄድህ ግን አትጸጸትም። ታኖራለህ ግን ምክንያት አትሻም። ትሰጣለህ፣ ግን አትቆጥረውም።
ክረምትና በጋውን ስታፈራርቅ አይደክምህም ወይ! ተኝተን ትጠብቀናለህ። እንቢ ብለን ስንርቅህ ብዙ ዘመን ደጅ ደጁን ታያለህ። በገዛ በረከትህ ስንክድህ አሁንም ታፈቅረናለህ። ጠባያችን እንዴት አላደከመህም?!
አይደክምህም ወይ? !
ዲያቆን አሸናፊ መኰንን
መስከረም 3 ቀን 2018 ዓ.ም

❤48👍4🥰3👏2
እግዚአብሔር ቢፈቅድ ብንኖር ዛሬ
እሑድ መስከረም 4 ቀን 2018 ዓ.ም. ከ ጠዋቱ 4:00 ሰዓት ላይ ትምህርታችን ይጀምራል ::
የትምህርታችን ርእስ "ክርስቶስ ለምን ሰው ሆነ?" ክፍል 6 ይቀጥላል
ክርስቶስ ሰው የሆነበትን ከ40 በላይ ምክንያቶች ይተነትናል።

❤22👍1