እንዴት ልዘን?
የመደሰትና የማዘን፣ የመሳቅና የማልቀስ ተፈጥሮ ሰጥተኸኝ እንዴት ልዘን? ጌታዬ ቸግሮኛል። ሁሉም ነገር የእንቧይ ካብ ሲሆን፣ ላይነጋ የመሸ ሲመስል ከዚህ በላይ ምን ልሁን ? ላልቅስ እንጂ ስል ፊቴ ትመጣለህ። ያጎረሰኝ እጅህ አሁንም ሊደግመኝ አፌ አጠገብ ነው። ኧረ ገለል በልልኝ ልዘን ፍቀድልኝ። እንደ ኑኃሚን ብዙ ሆኖ ወጥቶ ብቻ መመለስ ፣ ልጅን ቀብሮ ነጭ መልበስ እንዴት ይቻላል? እንዳዝን የሚጠብቀኝ ብዙ ወገን አለ፣ ለእውነትም ለይሉኝታም እባክህ እንዳለቅስ ፈቀድልኝ። እንባዬ ተሰንቅሮ፣ ልቤ ላይ ተተክሎ ወግቶ እንዳይገድለኝ እባክህ እንዳዝን ፍቀድልኝ።
ልቅሶዬን ፍቅርህ፣ ግፌን ውለታህ እየካሰብኝ እንዴት ልዘን እባክህ ገለል በልልኝ። ሃና ልቤ ልጅ ጎደለ ብሎ ሲያለቅስ ሕልቃና ማንነቴ ከአሥር ልጅ ጌታ ይበልጣል ይለኛል።
በአራቱ መዓዘን የተወጠርኩ ሲመስለኝ ፣ የወደድኩትን አጥቼ የጠላሁት ሲናፍቀኝ ላዝን ምንጣፍ አስተካክላለሁ ፣ ውለታህ ድቅን ሲልብኝ "ከጌታዬ ምን ጎደለ?" ብዬ እተወዋለሁኝ። መስቀሌ ውበት የለውም፣ ያንተ መስቀል ግን ውብ ያደርጋል። ደግሞም ሲያዩት ያምራል ፣ ዕርቃንህን ሆነህ መስቀል ላይ ታምራለህ። ለውበቴ የመጣውን ለሞቴ ነው ብዬ ትርጉም ሰጥቼ ለማዘን ጊዜ እመድባለሁ፣ ጠላቴም ሆድ እያስባሰኝ፣ እየቆነጠጠ ያስለቅሰኛል። ይህ ፅንስ አይረባም ይወገድ ተብሎ የተወለደ ዛሬ ላይ ደርሶ እንዴት ያዝናል? ባለሙያ ሞት አውጆብኝ በሕይወት ካለሁኝ ምንም ለማዘን መብቴ ቢሆንም አንተን እያየሁ እንዴት ልዘን? ሰው ነኝና አመነታለሁ፣ ግን ያላንተ አይሆንልኝም ብዬ መንገዴን እቀጥላለሁ ። ሰው ነኝና አልቅሼ ይውጣልኝ ብዬ መሐረብ አሰናድቼ በሬን እዘጋለሁ ። ከጎደለብኝ የሞላው ብዙ መሆኑን አይቼ አፍሬ በሬን እከፍታለሁ።
ብዙ መፈተን፣ በመከራ ሰፌድ ላይ እንደ ስንዴ መበጠር ከባድ ነው። አንዱ መከራ ለሌላኛው አቀብሎኝ ይሄዳል እንጂ ይበቃዋል ብሎኝ አይሄድም። በከበዱኝ ቀኖች፣ አንተን ባላውቅ ኖሮ ምነው በሞትኩ በምልበት ሰዓት እንኳ እኔ አለሁ አትበለኝ ፣ እንዳዝን ገለል በልልኝ። ልቅሶ ግዝረት፣ እንባ ጥምቀት ሆኖ ይገላግለኝ፣ እንዳዝን ፍቀድልኝ። የጸናው መሬት እኔ ስረግጠው ይናዳል፣ የመጣው ነገር ከምችለው በላይ ሆኗል ብዬ ላዝን ስዘጋጅ፣ ሆዴ ሲላወስ፣ እንባ ጋኑን ሰብሮ ሊወጣ ሲል የተቸነከረ እጅህን ታሳየኛለህ። ስላቆሰሉህ እልፎች ሳይሆን ስለ ቆሰልኩልህ አንዱ ስለ እኔ አስብ ትለኛለህ። ያለኝ አቅም እርሱ ነው ፣ ጨርሼ እንዳዝን፣ የኖርኩበትን ኑሮ እንድሰርዝ ፍቀድልኝ። በአሳብ የሚረዳኝ፣ በጉልበት የሚቆምልኝ የለም ። ከፈተናው የተነሣ የበደሌ ከፍታ ምን ያህል ቢሆንብህ ነው ? እላለሁ። መልስ ያጣሁ ሆኖ ተሰምቶኝ ላዝን ስዘጋጅ እንባዬን ነፋስ እንደሚበትነው ደመና ትወስድብኛለህ ፣ እንዳዝን ፍቀድልኝ።
ሞትን በምለምንበት፣ ይበቃኛል ጥራኝ በምልበት ሰዓት ኤልያስ ልቤን በሰረገላህ ትነጥቀዋለህ። ለሁሉም ነገር ጣዕም ሳጣ ፣ ለመመረር ሰዓቱ ነው ስል፣ ባወቅሁት መጠን አለመኖሬ ትዝ እያለኝ ምሬቴን እመልሳለሁ። የገነትና የሲኦል ጥያቄ ስላለብኝ ፣ ይቅርታ ጠይቆ ለማረፍም ሳይሆን ይቅርታ ልትጠየቅ የሚገባህ ክቡር መሆንህን አስብና መልሼ ይቅር በለኝ እልሃለሁ። እኮ እባክህ ዛሬ ልክ ልሁንና እንዳዝን ፍቀድልኝ። ከእኔ እንጂ ካንተ አልጎደለምና ፣ ከሰው እንጂ ካንተ ያጣሁት የለምና ልቆጣህ መጥቼ ተገሥጬ እመለሳለሁ።
የት ነህ ብባል እዚህ ጋ ነኝ በማልልበት በጨለማው መንገድ ላይ ስሆን ፣ ዕድሌ ምንድነው ? ብዬ ለማልቀስ፣ የሰውን ጥያቄ ለመሸሽ እጥራለሁ። ካንተ ጋር እየተሟገትሁ መኖር ይበቃኛል ብዬ ራሴን በኀዘን ለመቅጣት እነሣለሁ። ያነጋልኝ ቸርነትህን ሳስብ፣ በአልጋ ያሉትን በሽተኞች ሳስታውስ ማረኝና ልግባ አገሬ እላለሁ። የተቀበልኩት እውነትና የምኖረው ሕይወት ሲለያይብኝ፣ ራሴን ያለ ክርስቶስ ሳየው አስፈሪ ሥዕል ሲመጣብኝ ማዘን እፈልጋለሁ። መልሰህ በር ዘግተህ ትመክረኛለህ ። በጽኑ እጅህ ከጎርፉ ውስጥ ታወጣኛለህ።
ብቻውን የሚወድቅ ነገር የለምና ለትዳሬ መፍረስ፣ ለባልንጀርነቴ መበላሸት የእኔም እጅ አለበት። ጌታ ሆይ ትዳር ነበረኝ፣ ልጅ ነበረኝ ማለት ያቆስላል፣ አሁን እንኳ ተወኝ ልዘንበት? የሣር ተማሪ ሆኜ "ሀ" ያልኩበትን ዘመን አላውቀውም፣ ሁሉንም ነገር የምማረው በሐሳር ነው። እንዲህ ብዬ ላዝን እፈልግና ከእጅህ የበላሁት ያንቀኛል፣ የበረሃው ጓዴ መሆንህ ድቅን ይልብኛል። ባዝንም ባለቅስም አለማመስገን ይቆረቁረኛል።
እንዴት ልዘን? ያበላኝ እጅህ ይታየኛል !
ዲያቆን አሸናፊ መኰንን
መስከም 2 ቀን 2018 ዓ.ም.

❤48🥰4😢4👍2
ዛሬ ዓርብ መስከረም 2 ቀን 2018 ዓ.ም. ከምሽቱ 2:00 ሰዓት ላይ ትምህርታችን ይጀምራል ::
የትምህርታችን ርእስ " መጽሐፍ ቅዱስን እንወቅ"
ክፍል 4
ስያሜው ፣ ሥልጣኑና ስህተት አልባነቱ ይገልጣል።
ማስታወሻ ብትይዙ ይመከራል።
ሌሎች ወገኖቻችንንም ጋብዙ
https://www.tg-me.com/Nolawii
የትምህርታችን ርእስ " መጽሐፍ ቅዱስን እንወቅ"
ክፍል 4
ስያሜው ፣ ሥልጣኑና ስህተት አልባነቱ ይገልጣል።
ማስታወሻ ብትይዙ ይመከራል።
ሌሎች ወገኖቻችንንም ጋብዙ
https://www.tg-me.com/Nolawii
Telegram
Nolawi ኖላዊ
ይህ ቻናል ኦርቶዶክሳዊ መንፈሳዊ ትምህርቶች የሚተላለፉበት ነው። እግዚአብሔር አገልግሎቱን ያስፋ!
አገልግሎቱንም ያግዙ!
0911699907 ዲያቆን አሸናፊ መኰንን
አገልግሎቱንም ያግዙ!
0911699907 ዲያቆን አሸናፊ መኰንን
❤25👍3👏1
አይደክምህም ወይ?
ሁልጊዜ በሥራ ላይ ነህ ፣ የማትሠራበት ቀን፣ የማትሠራለት ፍጥረት የለም። ሰውና እንስሳው አንተን ይጠባበቃል። ለሁሉ አንዱ ትደርሳለህ። ሁሉን በአንዱ ክንድህ ትጋርደዋለህ ። ይህን ሁሉ ስትከውን አይደክምህም ወይ? ዘላለም እንቅልፍ የለብህም፣ ከፀሐይ ይልቅ በሁሉ አገር ሰልጥነሃል፤ በመንግሥተ ሰማያትም ራስህ ታበራለህ። የፀሐይ ፀሐይ አንተ ነህ። የማትጠልቅ ጀምበር፣ እንደ ተወደድህ የምትቀር አንተ ብቻ ነህ። ሰው ሁለት ቃል ያናግራል፤ የፊት ምስጋና ለኋላ ሐሜትም ያስቸግራል። ሁለት ቃል የማታናግር የሰዎች ሰው አንተ ነህ።
ሁሉን ስትወድ አይደክምህም ወይ? ሰዎች ክፉ የሚሉት ዘንዶም ምግቡን ካንተ ያገኛል። ከመልካምነትህ የወጣ ነውና ተፈጥሮ ቅዱስ ነው። ምርጫው ካረከሰው በቀር የሰው ትንሽ የለውም። ድሀ ባለጠጋን እኩል መውደድ ትችላለህ፣ ሁሉም በፊትህ ነዳይና ለማኝ ነውና። በራሱ ይኑር ብለህ ፍጥረትን ያለቀቅኸው በራሱ መኖር ስለማይችል እንጂ አንተ ጨቋኝ ስለ ሆንህ አይደለም። ፍጥረት ያላንተ አንካሳና አቅመ ቢስ ነው። ሁሉን በቃልህ የደገፍከው አንተ ነህ።
ስንቱን አደፋፍረህ ከቤት ታወጣዋለህ፣ ስንቱን አባብለህ ታስተኛዋለህ። ለበሽተኛው አልጋ ታነጥፋለህ። ያንተ ስፍራ ፣ የተወሰንህበት ክልል የት ነው? ከብሶተኛው ጋር ተበድለሃል፣ ከዳኛው ጋር ፍትሕ ትሰጣለህ። የት ነው አገርህ? ያንተ ያልሆነ ሕዝብስ የትኛው ነው? አንተ የማታስፈልገው በራሱ የቆመ ኩሩ ማነው? አንድ ቀን ውኃ ካላገኘ የሚበላሽ ፍጡርስ እንዴት በአንተ ላይ የድፍረት ቃል መናገር ይችላል?
አንድ ሆነህ ሁሉን ታጠግባለህ። ሁሉ የእኔ ሲልህ ለሁሉ ትበቃለህ። እባክህን ዕረፍ አይደክምህም ወይ? አንድ ሰው መሸከም አቅቶን ደክመናል፣ ይህን ሁሉ ፍጥረተ ዓለም ለሆዱ እንጀራን፣ ለኃጢአቱ ይቅርታን፣ ለመንፈሱ እርካታን ትሰጠዋለህ። ለእኔም እዘኑልኝ ደክሞኛል አትልም። እያንዳንዱ የዝናብ ጠብታ ባንተ ይታወቃል፣ ለበረሃውም ታዝንለታለህ። በረዶ ላይ ለሚኖረው ፀጉር ታለብሰዋለህ፣ የበረሃውን እንስሳ መላጣ ታደርገዋለህ። ማንን የት ቦታ መላክ እንዳለብህ ታውቃለህ። አክባሪዎች እንጂ አማካሪዎች የሉህም። ያልከውም ይሆንልሃል፤ ጅምርህ ይፈጸማል። ይህን ስፍራ ሳትለቅ የምድር ጥግ ትገኛለህ። ጠፈርን ለመንካት መንጠራራት የለብህም፣ ሰንበትን ለሰው የሰጠህ ሰንበት የለብህም። አይደክምህም ወይ?
እኛ ለአንድ ሰው ምግብ ለመሥራት ይደክመናል። አንተ ግን ለሁሉ ታበስላለህ። እጅግ የተዋብህ ብትሆንም ኃጢአት ያጎሳቆለንን እኛን ትወደናለህ። ብዙ ወደኸን ትንሽ ብንወድህም አትጠላንም። የነገሥታት ምክር ላይ ተገኝተህ ታዳምጣለህ፣ ከተመራማሪዎች ጋ በቤተ ሙከራ ትገኛለህ ። ጠባቂዎችን ትጠብቃቸዋለህ። ቤተ ሠሪ አንተ ነህ ፣ ቤቱንም ሰውየውንም የሠራኸው አንተ ነህ። ያንተ ሥራ ግሩም ነው። ቤትን ያለ ምሰሶ ታቆማለህ፣ ምድርን ያለ መሠረት ታጸናለህ። ባንተው ሀብት ነዳጅና ወርቅ፣ እህልና መድኃኒት በውድ ይሸጣል። ሁሉ ነዳይ ሳለ ባለጠጋና ድሀ አገራት ይባባላል። ሁሉን ሳትታዘብ ታኖረዋለህ። የሰውን ድካሙን አንተ ታውቀዋለህ። እኛ የሰው የቁንጅናው፣ የጉልበቱ፣ የሥልጣኑ ወዳጅ ነን። አንተ ግን ራሱን ሰውዬውን ትወደዋለህ። ወርቅ አይደልልህ ፣ ጎበዝ አያሸንፍህም። የተጣላህን ታባብለዋለህ፣ ምንም ላታገኝ ላድንህ ብለህ ትለምናለህ። አፍቃሪ ነህ ግን ተለማማጭ አይደለህም። መሐሪ ነህ፣ ዓመፀኞችን ግን ትቀጣለህ። ትመለሳለህ፣ ከሄድህ ግን አትጸጸትም። ታኖራለህ ግን ምክንያት አትሻም። ትሰጣለህ፣ ግን አትቆጥረውም።
ክረምትና በጋውን ስታፈራርቅ አይደክምህም ወይ! ተኝተን ትጠብቀናለህ። እንቢ ብለን ስንርቅህ ብዙ ዘመን ደጅ ደጁን ታያለህ። በገዛ በረከትህ ስንክድህ አሁንም ታፈቅረናለህ። ጠባያችን እንዴት አላደከመህም?!
አይደክምህም ወይ? !
ዲያቆን አሸናፊ መኰንን
መስከረም 3 ቀን 2018 ዓ.ም

❤48👍4🥰3👏2
እግዚአብሔር ቢፈቅድ ብንኖር ዛሬ
እሑድ መስከረም 4 ቀን 2018 ዓ.ም. ከ ጠዋቱ 4:00 ሰዓት ላይ ትምህርታችን ይጀምራል ::
የትምህርታችን ርእስ "ክርስቶስ ለምን ሰው ሆነ?" ክፍል 6 ይቀጥላል
ክርስቶስ ሰው የሆነበትን ከ40 በላይ ምክንያቶች ይተነትናል።
ማስታወሻ ብትይዙ ይመከራል።
ሌሎች ወገኖቻችንንም ጋብዙ
https://www.tg-me.com/Nolawii
እሑድ መስከረም 4 ቀን 2018 ዓ.ም. ከ ጠዋቱ 4:00 ሰዓት ላይ ትምህርታችን ይጀምራል ::
የትምህርታችን ርእስ "ክርስቶስ ለምን ሰው ሆነ?" ክፍል 6 ይቀጥላል
ክርስቶስ ሰው የሆነበትን ከ40 በላይ ምክንያቶች ይተነትናል።
ማስታወሻ ብትይዙ ይመከራል።
ሌሎች ወገኖቻችንንም ጋብዙ
https://www.tg-me.com/Nolawii
Telegram
Nolawi ኖላዊ
ይህ ቻናል ኦርቶዶክሳዊ መንፈሳዊ ትምህርቶች የሚተላለፉበት ነው። እግዚአብሔር አገልግሎቱን ያስፋ!
አገልግሎቱንም ያግዙ!
0911699907 ዲያቆን አሸናፊ መኰንን
አገልግሎቱንም ያግዙ!
0911699907 ዲያቆን አሸናፊ መኰንን
❤22👍1
ድብቅነት
"በሽታውን የደበቀ መድኃኒት አይገኝለትም" ይባላል። ብዙ ሰዎች ችግራቸውን ደብቀው መጨረሻ ላይ ሊረዱ በማይችሉበት ሁኔታ ላይ ሆነው ይገኛሉ። ራሳቸውን እንደ ገደሉ ያህል ይቆጠራል፣ አብሯቸው ያለውም ሰው መርዳት ባለ መቻሉ ያዝናል። የማኅበራዊነትና የቤተሰብ ጥቅሙ መመካከር መቻሉ ነው። መመካከር ከሌለው ከተማው በረሃ ነው። የሰው ቅርጽ ማየት ሳይሆን የሰውነትን በጎነት መለዋወጥ የመኖር ትርጉም ነው።
ለመንፈሳዊ አገልጋይ ያለበትን ውድቀት የደበቀ ምእመን ለሰይጣን ምርኮኛ መሆኑ የታወቀ ነው። ከሰይጣን ታላላቅ ፈተናዎች አንዱ ድብቅነት ነው። ልጆች ድብቅ በሆኑ ቁጥር ውሎአቸውንና ስሜታቸውን በሰወሩ መጠን እየተጎዱ ይመጣሉ። ብዙ ልጆች በቤት ውስጥ ቢኖሩም ወላጆቻቸውም አያውቋቸውም። የዚህ ችግር ልጆችን በሁሉ ነገር መቆጣት ፣ ማቅረብ አለመቻል ነው። ምንም ዓይነት ሁኔታ ውስጥ ቢሆኑ እንደምንቀበላቸው ካወቁ፣ የልባችንን ስፋት ካስተዋሉ ሊነግሩን ይችላሉ። ለልጆች ወላጅ ብቻ ሳይሆን ጓደኛም መሆን መልካም ነው። ሁሉን ለማወቅ ጥረት ካደረግን ልጆች ድብቅ ይሆናሉ። ማንም ለመርማሪ ፖሊስ ግልጽ መሆን አይፈልግምና ።
መፍትሔ የሚገኝበት ቦታ ላይ ድብቅ መሆን አደጋው ከፍ ያለ ነው። ለወላጆች፣ ለጓደኛ፣ ለሐኪም ፣ ለሥነ ልቡና አማካሪ ፣ በአበ ነፍስ፣ ለአገልጋይ ግልጽ መሆን በጣም ጠቃሚ ነው።
ድብቅነት ብለን ያነሣነው ካለማወቅና በእውቀት ድብቅ የሆኑ ሰዎችን ለማረም ነው። ድብቅነት ሽሽግነት ፣ ሽማቂነት፣ ስውርነት ፣ ለሰዎች ቅኔ መሆን፣ በልብና በአካል ከወዳጆች መሸሸ፣ ምንነቱ የማይታወቅ ሰው መሆን ፣ ግራ በማጋባት መደሰት ነው። ድብቅነት በተለያዩ ምክንያቶች ይመጣል። አሳብን መግለጽ በማይቻልበት ቤተሰብ በማደግ ሊመጣ ይችላል። የጨዋነት መለኪያ ዝምታ አይደለም። በአንዳንድ ቤተሰብ ልጆች እንዳይናገሩ በገደብ ያድጋሉ። ግልጽ በመሆናቸው ምክንያት ቁጣና ጉዳት የደረሰባቸው ሰዎች ድብቅ ይሆናሉ። ሌሎች ደግሞ በጉራ ኑሮ ተሸፋፍነው ስለሚኖሩ ሰዎች ከቀረቡአቸው ባዶነቱ ገሀድ እንዳይወጣ ድብቅ ይሆናሉ።
ያልሆነውን እንደሆንን አድርጎ ማቅረብ የሆነውን እንድንደብቅ ያደርጋል። በዚህ ዓለም ላይ ጥቅሙም ጉዳቱም የባለቤቱ የሆነበት ምርጫ ብዙ ነው። ባለጠጋ፣ አዋቂ፣ ጌጠኛ ብንሆን ለራሳች ን ነው። ይህ ሁሉ ባይኖረንም የመኖር መብት አለን። የድብብቆሽ ኑሮ እንዳንኖር የሆነውን መቀበል ያስፈልጋል። ራሳችንን ስንቀበል ሰዎች ይቀበሉናል። በሽታችንን፣ መልካችንን፣ ኑሮአችንን መቀበል ስልጣኔ ነው። መቀበል ለዓለም ችግር ትልቅ መፍትሔ ነው:: ችግሮች ሰባ ፐርሰንት የሚቀንሱት በመቀበል ነው። ትክክለኛ ማንነታችን ሁልጊዜ ሊገኝ ይችላልና አናፍርም፣ ስለዚህ የሆነውን ይዞ መቅረብ ይገባናል። ያን ጊዜ ከሰዎች ፍቅርና ክብር እናገኛለን። ድብቅነት ሰዎች ራሳቸውን አስረው የሚያሰቃዩበት የዓለማችን ትልቁ እስር ቤት ነው። ድብቅ በሆንሁ መጠን ክብር አገኛለሁ ብሎ ማሰብ ሥቃይ ውስጥ ይከታል።
ድብቅነት የአእምሮ ፈተና፣ የሰይጣን ውጊያ ሊሆን ይችላል። ሁሉ ሰው ስለ እነርሱ ጥናት እያደረገ የሚመስላቸው፣ ሰዎች ይከታተሉኛል ብለው በማሰብ በብዙ አጥር ውስጥ ራሳቸውን የሚከቱ ሰዎች አሉ። የዚህ ችግር ለከፍተኛ ጭንቀት እየዳረጋቸው ይመጣል። ነገሮችን በቀላሉ ከማየት እያከበዱት ይመጣሉ። እያንዳንዱን የሰላምታ ልውውጥ እየፈሩት ይመጣሉ። እፈልጋለሁ አልፈልግም ብለው ቁርጡን ከመናገር ዙሪያ ገባውን የሚዞሩ ይሆናሉ። ማንኛውም ሰው ሊያጠቃኝ ይቻላል ብለው ስለሚያስቡ የቅርብ ሰዎቻቸውንም አያምኑም። በሚፈለጉበት ሰዓት ከመገኘት በአሳቻ ሰዓት ራሳቸው ሌሎችን መፈለግ ይመርጣሉ። የማላውቀውን ስልክ አላነሣም ፣ ብዙ ሰዓት ሰዎችን ማግኘት አልፈልግም ፣ ጨዋታ ይረብሸኛል ወደ ማለት ይሄዳሉ:: ስላሉበት ሁኔታ ማንም ሰው አለማወቁ የድል ስሜት እየመሰላቸው ይመጣል።
የድብቅነት ችግሩ ጉልበት ይጨርሳል። ጦርነት በሌለበት እየፈጠረ ይዋጋል። ነገሮችን አጋኖ ይመለከታል፣ ስልክ ለመደወል ላስብበት ይላል። ችግር ላለመስማት ሽሽት ውስጥ ይገባል። የማይታወቅ ፍርሃት ይንጠዋል። የቀን ሰላም፣ የሌሊት እንቅልፍ ይከዳዋል።
ለሁሉ ሰው መገለጽ ተገቢ አይደለም። በቦታው ግልጽ አለመሆን በሽታ ነው። ድብቅነት ከሰዎች ጋር ያለንን ኅብረት ያፈርሳል። አንዳንድ ሰዎች ከስለላ ስልጠና የተነሣ ድብቅ ይሆናሉ፣ ሌሎች ደግሞ ተንኮለኛ በመሆን ድብቅ ይሆናሉ። ስለ እኔ ማንም አያውቅም የሚል ጨዋታ መጫወት ድል ይመስላቸዋል። የእነዚህ ድብቆች የኋላ ዕድሜ በጣም ከባድ ይሆናል። ትዳራቸውም ፣ ወዳጅነታቸውም ላይጸና ይችላል። ድብቅነት ከሴቶች ይልቅ በወንዶች ላይ ይዘወተራል። ግልጽ መሆን ሕይወትን ቀላል ያደርጋል። ሰዎች ከእኛ ጋር መሆን የሚፈልጉት ቀለል ያለ ሕይወት መምራት ስንችል ነው።
ድብቅነት እንደ ክፉ ሰው እንድንታይ ያደርጋል። ሰዎች እየፈሩን ይሸሹናል። የሰዎችን እርዳታ በፈለግን ሰዓት እንኳ እንዳናገኝ ያደርገናል። ድብቅነት ለሞት ይደርጋል፣ አሰቃይቶ በመግደልም የታወቀ ነው። ሐኪም ቤት ስንሄድ የመጀመሪያው ምርመራ "ተንፍስ" የሚል ነው። መተንፈስ የተቃጠለውን አየር ያወጣል፣ ያለንበትን ሁኔታ ይገልጣል፣ መፍትሔ ያመጣል።
ትልቅ መንፈሳዊ ውድቀት የሚመጣው በድብቅነት ነው:: ካህኑ ሲናዝዝ፦ "መንፈስ ቅዱስ ያወቀውን፣ ሰይጣን የሸመቀውን ኃጢአታቸን ይቅር ይበለን" ይላል። ሽምቅነት የሰይጣን ጠባይ ነው:: ሽምቅነት ችግሩ አለ፣ መፍትሔ እንዳያገኝ መደበቅ ነው ።
ከድብቅነት እንውጣ! በየጊዜው መተንፈስን እንለማመድ ፣ ከቅርብ ሰዎቻችን ጋር እንመካከር፣ አብሮ የመኖር ዋጋው ደስታና ችግርን በጋራ መካፈል ነው::
ዲያቆን አሸናፊ መኰንን
መስከረም 7 ቀን 2018 ዓ.ም.

❤76👏3
ዝምተኛነት
ዝምተኛነት ተፈጥሮ ሊሆን አይችልም። ጨለማ የተፈጠረ ሳይሆን የብርሃን አለመኖር ነው ይባላል። መብራት ማብሪያና ማጥፊያ አለው። ውኃም መክፈቻና መዝጊያ አለው። ሰው የመናገሪያና የዝምታ ጊዜ አለው፡፡ ዝም ብሎ መቅረት ዱዳነት ፣ ሲናገሩ መኖር ለፋፍነት ነው። ዝም ፣ ድርግም ማለት ዱዳነት ፣ ሁልጊዜ ተናጋሪ መሆን እብደት ነው። ሙቅና ቀዝቃዛ ውኃ ተመጣጥኖ ሲወርድ ምቾት ይሰጣል። ዝምታና ንግግርም መመጣጠን አለባቸው። የምናመጣጥነውም ለራሳችንና ለሰዎች ጤንነት በማሰብ ነው።
የተመጠነ የሚባለው ከበርበሬውም ሳያቃጥል፣ ከሽሮውም አልጫ ሳይሆን ነው:: ሁልጊዜ መናገርም ያቃጥላል፣ አንደበት እሳት ነው፣ የፈተና መግቢያም ነው። ሰው ለፈተና የሚዳረገው በመናገርም ነው። በዚህ በኩል ጎበዝ ነኝ ሲል፣ ሲፈርድ፣ ራሱን ከመጠን በላይ ሲገልጥ ለፈተና ሊዳረግ ይችላል። ሁልጊዜ ዝም ማለትም ተገቢ አይደለም። ግዑዝ የትራፊክ ምልክት እንኳ ይናገራል። ሐውልትም ዘመንና ታሪክን ያወሳል። ሰው ከእነዚህ አንሶ ዝም ቢል ይወቀሳል። ዋናው የምንናገርበትና ዝም የምንልበት ሁኔታ በዓላማ ሊሆን ይገባዋል።
ዝም የሚሉ ሰዎች ሲበዛ ሰዎችን ያስጨንቃሉ፣ እንደ ድብቅ ይታያሉ። ንግግር ገና በጠዋቱ የጀመርነው በልምምድ ነው:: ዝምታ በልምምድ የተገኘውን ቋንቋ ማጥፋት ነው። ዝም የሚሉ ሰዎች ከምናውቃቸው የተለየ ጠባይ አላቸው። ጥያቄ መፍጠርና ጥያቄ መሆን ደስ ይላቸዋል። በዝምታቸው ሰዎች ሲተራመሱ ማየት በጣም ይወዳሉ። ዝምታ በቀልም ሊሆን ይችላል። ደስታቸውን መግለጥ ስለማይፈልጉ ስሜታቸውን ሰው እንዳያውቅባቸው ይፈልጋሉ። አጠገባቸው ያሉትን ተናጋሪ ሰዎች በዝምታ መቅጣት ይፈልጋሉ። ተናጋሪ ራሱ ነዶ እስኪጠፋ ድረስ ያዩታል። ውስጣቸው ጠንካራ ሲሆን ሁሉም ነገር ከልክ አያልፍም የሚል አሰተሳሰብ አላቸው።
ዝም የሚሉ ሰዎች ከሌሎች በተሻለ ስለ ዓለም ግንዛቤ አላቸው። ማወቃቸውን ግን ሰዎች እንዲያውቁባቸው አይፈልጉም። ከራሳቸው ጋር በጣም ልዩ ፍቅር አላቸው። ወደ ውስጣቸው በጣም ስለሚያወሩ ከሰዎች ጋር ማውራትን አይፈልጉም። ራሳቸውን አውርተው አይጠግቡትም። አጠገባቸው ስላሉት ሰዎች ቸልተኝነት ሊሰማቸው ይችላል። በጣም የሚወዱት ነገር ጫጫታ ነው። ብዙ ዝምተኞች ኳስ ፣ ዘፈን፣ መዝሙር፣ በዓላት፣ ሰርግ ፣ ድምፁ ከፍ ያለ ነገር ይወዳሉ። ቀኑን በሙሉ የሚለፈልፉ የሬዲዮ አፍቃሪዎች ናቸው። መናገርን ባይፈልጉም የሚዝናኑት ግን ጩኸት በመስማት ነው።
ዝምተኞች ራሳቸውን ገለል ማድረግ ሲወዱ ሁልጊዜ መፈለግ እንዳለባቸው ያስባሉ። በውስጣቸው የማይገለጽ ደስታ ሲኖራቸው ያንን ለሌሎች ማጋራት አይችሉም። ሥራ መሥራት ያስደስታቸዋል :: ሥራቸውን ግን መግለጽ ስለማይችሉ አይታወቅላቸውም። ወንዶች ከሆኑ ብዙ ሴቶችን የማስከተል አቅም አላቸው። ዝምተኛ ሴቶችም በዙሪያቸው ለፍላፊ ወንዶች አሉ። ዝም የሚለው ግን ዝም ያለ አይደለም። ተናጋሪዎችን ቀጥሯል፣ አሊያም በጽሑፍ ተደብቆ ይናገራል። ሥዕል ይሥላል::
የዝምታው ምንጭ ለመናገር የሚያበረታታ ቤተሰብ አለማግኘት ሊሆን ይችላል። በቂ እውቀት አለማዳበር ዝም ያሰኛል። ፍርሃትም የዝምታ ምንጭ ነው። ዝምታን እንደ ቅድስናና ጨዋነት ማሰብም ዝም ያሰኛል። በመከራና በአደጋ መደንገጥ ወደ ዝምታ ዓለም ይወስዳል። ብናገር ሰው ላስቀይም እችላለሁ በማለት ዝም ሊባል ይችላል። ከመጠን በላይ ሰዎችን ማክበርና መፍራትም ዝምታን ይወልዳል።
ዝም የሚሉ ሰዎች ብዙ ዕድሎች ያመልጧቸዋል። ክብርን ያገኙ ቢመስላቸውም በተቃራኒው ግን ምንም እንደማያውቁና ስሜት አልባ እንደሆኑ ይገመታሉ። ተገቢ ንግግር አለማድረጋቸው ከቅን ፍርድ እንዲርቁ ያደርጋቸዋል። የአንደበትን አገልግሎት አልተረዱምና ሌሎችን መስበክ ያቅታቸዋል። ችግርን መናገር እንደ ሽንፈት ስለሚቆጥሩት በቀላሉ ጉዳይ ትልቅ ዋጋ ይከፍላሉ። ራሴ እወጣዋለሁ የሚል ኩራት ቢኖራቸውም መረዳዳት ግን አስፈላጊ መሆኑን ይረሳሉ።
ለመናገር ጊዜውን፣ ቦታውን ፣ ሁኔታውን መርምሩ ! እንዲሁም ለዝምታ ጊዜውን፣ ቦታውንና ሁኔታውን ተመልከቱ !
ዲያቆን አሸናፊ መኰንን
መስከረም 9 ቀን 2018 ዓ.ም.

❤73👍5👏2
ዛሬ ዓርብ መስከረም 9 ቀን 2018 ዓ.ም. ከምሽቱ 2:00 ሰዓት ላይ ትምህርታችን ይጀምራል ::

❤9