Telegram Web Link
Forwarded from Tofik Bahiru
በዐስሩ ቀናት ምን እንስራ?
================
የሰው ልጅ በነፍስ እና በሩሕ ወይም በስጋ እና በመንፈስ መሀል የሚዋልል ፍጡር ነው። አንዴ መንፈሱ በሌላ ጊዜ ስጋው እየተሸናነፉ ይኖራል። እንደ መላኢካ የመንፈስ ህይወት ብቻ እንዲኖር፣ በአላህ ዒባዳ ላይ በቋሚነት ያለማቋረጥ እንዲሰነብት አልተደረገም። መንፈሳዊነቱ ሁሌም ቋሚ አይደለም። በእርግጥ ሁሌም ወደ ከፍተኛው የመንፈሳዊነት ልዕልና የሚያድጉ ነቢያትን የመሰሉ ሰዎች በሰው ዘር ውስጥ ቢኖሩም አብዝሃኛው ግን ከፍታና ዝቅታ ያለበት የመንፈስ ህይወት የሰው ልጅ መደበኛ ጠባይ መሆኑን ያሳብቃል። ሰው አንዴ ከመላኢካ በላይ በሌላ "አዕላ ዒሊዪን" ላይ በኬላ ጊዜ ከሰይጣናት ጋር "አስፈለ ሳፊሊን" የሚኖር ህዝብ ነው!
:
ነገርግን የአላህ ችሮታ ሆኖ ይህ ድክመታችንን ይሸፍንልን ዘንድ፣ ሰነፎች ወደ ታታሪዎቹ የአላህ ወልዮች ከፍታ ያስጠጋን ዘንድ ልዩ የአምልኮ ጊዜያት ተሰጥተውናል። በስንፍና ወራታችን ያሳለፍነውን እንድናካክስ ድጋፍ ተደርጎልናል።
ደጋጎች በእነዚህ ጊዜያት መልካም ስራን በማብዛት ከጌታቸው ለሚወርደው እዝነት ራሳቸውን ያቀርባሉ። ጌታቸው ዘንድ ቅርብ በሚያደርጓቸው ስራዎች ላይ ይሻማሉ። ምርጥ የአላህ ባርያ ሆኖ ለመታየት ይሽቀዳደማሉ። በጥቂት ጊዜያት ትእግስት ትልልቅ ደረጃዎችን ይጎናፀፋሉ። እነዚህ የታደሉ ሰዎች ናቸው!
:
አንዳንዶች ደግሞ እነዚህን ልዩ ጊዜያትም እንደሌላው ተራ ጊዜያት በዋል ፈዘዝ ያሳልፋሉ። የአላህ እዝነት ከምን ጊዜውም በላይ በሚቀርባቸው ቀን እንኳን እነርሱ ከአላህ ይሸሻሉ። ማትረፍ እየቻሉ ይከስራሉ። መዳን እየቻሉ ይጠፋሉ። ከፍ ማለት እየቻሉ ይወድቃሉ። አላህ ይጠብቀን!
:
የዐሽሩ ዚል‐ሒጅ‐ጃ (ዐስሩ የዙል‐ሒጃ ቀናት) ትሩፋት ከእነዚህ የአላህ ስጦታዎች አንዱ ነው። ከዱንያ ቀናት ሁሉ ምርጦች፣ መልካም ስራ ከምንም ጊዜ በላይ ታላቅ ምንዳ የሚያስገኝባቸው እና አላህ የማለባቸው ታላቅ ቀናት ናቸው።
ይህን የአላህ ስጦታ ለማግኘት መጓጓት፣ የተሰጠንን ታላቅ እድል ለመቋደስ መኳተን፣ ዓቅም በፈቀደው ሁሉ ታግለን ለአኺራችን ለመሰነቅ እና ለአላህ ያለንን ፍቅር ለማሳየት መንጎዳጎድ የኛ ፋንታ ነው!
አቀባበሉን ማሳመር፣ አጠቃቀሙን ማወቅ እና በታላቅ ወኔ ማሳለፍ የኛ ሚና ነው!
አላህ ተውፊቅ ይስጠን!
:
⚀ ነገርግን በእነዚህ ቀናት ውስጥ ምን እናድርግ?
❶ ተውበት: ‐
በማንኛውም ጊዜ‐ ለኔ ቢጤ ኃጢኣተኛ ብቻ ሳይሆን ለማንኛውም የአላህ ባሪያ ምርጡ ተግባር ተውበት ነው። በተለይ እንዲህ ዓይነት ጊዜያትን በተውበት ስሜት ማሳለፍ ወሳኝ ነው። እውነተኛ ተውበት፣ በሙሉ ወኔ ወደ አላህ መመለስ፣ ርቀነው ወደሄድነው የጌታችን እቅፍ መጠጋት የመጀመሪያም የመጨረሻም ስራችን መሆን አለበት።
በዱንያም ሆነ በአኺራ የሰው ልጅ መድህን እና ስኬት ያለው በዚህ ውስጥ ነው። ያፈረስነውን መገንባት፣ ያቆሸሽነውን ማፅዳት፣ ያበላሸነውን ማደስ… ተውበት ነው።
ማን አለ ከእኛ መሀል ያላመፀ? ማናችን አለ ያላጠፋ? ማን አለ ንፁህ? ማን አለ ግፍ ያልሰራ?
ማንም!
ማጥፋቱን እንደተካንበት ሁሉ ያሳለፍነውን ደግሞ እንድንክስ ዘንድ የተሰጠን እድል ነው፤ ተውበት።
አላህ እንዲህ ብሏል: ‐
[وَتُوبُوٓا۟ إِلَى ٱللَّهِ جَمِيعًا أَيُّهَ ٱلْمُؤْمِنُونَ لَعَلَّكُمْ تُفْلِحُونَ]
«ምእመናኖች ሆይ! ትድኑ ዘንድ ሁላችሁም ወደ አላህ (በመመለስ) ተጸጸቱ፡፡»
:
❷ ጊዜውን ለመጠቀም መጓጓት: ‐
እነዚህን ጊዜያት ለመጠቀም እና በመልካም ስራዎች ለማሸብረቅ መጓጓት አለብን። አላህ በሚፈልገው መልኩ በአግባቡ ጊዜውን ለመጠቀም መወሰን አለብን። አንድን ነገር ከልቡ ወስኖ የነየተን ሰው አላህ ያግዘዋል።
[وَٱلَّذِينَ جَٰهَدُوا۟ فِينَا لَنَهْدِيَنَّهُمْ سُبُلَنَا وَإِنَّ ٱللَّهَ لَمَعَ ٱلْمُحْسِنِينَ]
«እነዚያም በእኛ መንገድ የታገሉ መንገዳችንን በእርግጥ እንመራቸዋለን፡፡ አላህም በእርግጥ ከበጎ ሠሪዎች ጋር ነው፡፡»
:
❸ ከኃጢኣት መራቅ: ‐
በእነዚህ ወቅቶች የሚሰራ መልካም ስራ ከሌላው ጊዜ በበለጠ ወደ አላህ እንደሚያቃርቡ ሁሉ በእነዚህ ጊዜያት የሚፈፀሙ ኃጢኣቶችም ከሌላው ጊዜ በበለጠ ከአላህ የሚያርቁ መሆናቸው መታወቅ አለበት። ምናልባት ከምንም ጊዜ በበለጠ ከአላህ እዝነት ሊያባርሩን ይችላሉ።
አንዳንዴ በአንድ ኃጢኣት ምክንያት ከአላህ የምንርቅበትን መጠን መገመት ልንቸገር እንችላለን።
«ጀነት ከአንዳችሁ የነጠላ ጫማ ዘለበት በላይ የቀረበች ናት። እሳትም እንደዚያው።» ብለዋል ተወዳጃችን [ﷺ]
ስለዚህ ኃጢኣትህ እንዲማር፣ ከእሳት ነፃ እንድትደረግ፣ የአላህ ቅርብ ባሪያ መሆን ከሻህ በማንኛውም ጊዜ ከኃጢኣት ራቅ። በተለይም በእንዲህ ባሉ ወቅቶች የተለየየ ጥንቃቄ አድርግ!
:
የሚያገኘውን ነገር ትልቅነት ያወቀ የሚከፍለው ዋጋ ያንስበታል!
ጥቂት መታገስ ለመገመት የሚያዳግት ፍሬ ያፈራል!
ከሞት በኋላ ሁሉም ነገር ይገለጣል!
:
http://www.tg-me.com/fiqshafiyamh
Forwarded from Tofik Bahiru
ዓረፋ‐ትልቁ የአላህ ቀን
==============
ነገ ጠዋት ፀሀይ ስትፈነጥቅ አላህ የፈቀደላቸውና በምርጫው ከሌሎች የለያቸው ጥቂት ሑጃጅ የአላህ ባሮች ወደ ዐረፋ ሜዳ ያመራሉ። ዋነኛውን የሐጅ ስነስርዐት አካል "ዉቁፍን" ሊፈፅሙ።…
በእርግጥ የተርዊያ ቀን የሚሰኘውን የዛሬውን ቀን ሚና ውስጥ በዒባዳና በዚክር አሳልፈዋል።
:
የዐረፋ ቀን ታላቁ የአላህ ቀን ነው። ኃጢኣት ይሰረዝበታል። በእለቱ ዱዓ ተቀባይነት ያገኛል። ከምንም ጊዜ በበለጠ የአላህ እዝነት ለባሮቹ ቅርብ ይሆናል።
:
የዐረፋ ቀን ዲን የተሟላበት ቀን ነው። በሙስሊሞች ላይ የአላህ ፀጋ የተፈፀመበት እለት ነው።
የተውበት ቀን ነው። ምህረት የሚታደልበት ቀን ነው። ለአላህ የሚዋደቁበት የዱዓ ቀን ነው። የለቅሶና የተስፋ ቀን ነው። በርካታ ትሩፋቶቹ በሐዲስ ላይ ተጠቅሰዋል። በእለቱ መፈፀም ያለባቸው ተግባራት ተጠቁመዋል: ‐
:
⚀ የአመቱ ምርጥ ቀን
ጃቢር [ረዐ] እንደዘገቡት ነቢዩ [ﷺ] እንዲህ ብለዋል: ‐ «ከቀናት ሁሉ በላጩ የዐረፋ ቀን ነው።» ኢብኑ ሒባን ዘግበውታል።
በሌላ ሐዲስ የአላህ መልክተኛ [ﷺ] እንዲህ ብለዋል: ‐ «ከዐረፋ ቀን በላይ አላህ ዘንድ በላጭ የሆነ ቀን የለም። አላህ [በእዝነቱ] ወደ ቅርቡ ሰማይ ወርዳል። በሰማይ ፍጡራን ላይም በምድር ሰዎች [ልቅና] ይፎክራል።»
:
⚁ መላኢካ የሚሰበሰብበት ቀን:
የዐረፋ ቀንን ክብር ለማወቅ አላህ የማለበት ቀን መሆኑ ብቻ ይበቃል። አላህ እንዲህ ይላል: ‐
[وَشَاهِدٍ وَمَشْهُودٍ]
«በተጣጅና በሚጣዱበትም፤ (እምላለሁ)፡፡»
ከአቡሁረይራ [ረዐ] እንደተዘገበው: ‐ ነቢዩ [ﷺ] እንዲህ ብለዋል: ‐ «[ሱረቱል ቡሩጅ ላይ] 'ወልየውሚል‐መውዑድ/በተቀጠረው ቀን' የተባለው የቂያማን ቀን ነው። አልየውሙል‐መሽሁድ/የሚጣዱበት ቀን ደግሞ የዐረፋ ቀን ነው። አልየውሙሽ‐ሻሂድ/የሚጣደው ቀን ደግሞ ጁሙዐ ቀን ነው።» ቲርሚዚ ዘግበውታል።
ሱረቱል‐ፈጅር ላይም በድጋሚ አላህ የማለበት ቀን ነው። አላህ እንዲህ ይላል: ‐
[وَٱلشَّفْعِ وَٱلْوَتر]
«በጥንዱም በነጠላውም።»
በዚህ አንቀፅ አል‐ወትር/ነጠላ የተባለው የዐረፋ ቀን ነው።
ዐብዱላህ ኢብኑ ዐባስ [ረዐ] እንዲህ ብለዋል: ‐ «ጥንድ የተባለው [ዙልሒጃ 10 ወይም] የአድሓ ቀንን ነው። ነጠላ የተባለው የዐረፋ ቀን [ዙልሒጃ 9] ነው።»
:
⚂ ዲን የተሟላበት ቀን:
ቡኻሪና ሙስሊም ዑመር ኢብኑል ኸጣብን [ረዐ] ዋቢ በማድረግ እንደዘገቡት «አንድ አይሁድ ዑመርን እንዲህ አላቸው: «የሙእሚኖች አሚር ሆይ! በመፅሀፋችሁ ውስጥ ያለች አንዲት አንቀፅ አለች። በእኛ በአይሁዶች ላይ ወርዳ ቢሆን የወረደችበትን ቀን ዒድ አድርገን እንይዘው ነበር።» አለ። ዑመርም «የቷ አንቀፅ?» አሉ። ተከታይዋን አንቀፅ ጠቀሰላቸው: ‐
[اليوم أَكْمَلْتُ لَكُمْ دِينَكُمْ وَأَتْمَمْتُ عَلَيْكُمْ نِعْمَتِى وَرَضِيتُ لَكُمُ ٱلْإِسْلَٰمَ دِينًا]
«ዛሬ ሃይማኖታችሁን ለናንተ ሞላሁላችሁ፡፡ ጸጋዬንም በናንተ ላይ ፈጸምኩ፡፡ ለእናንተም ኢስላምን ከሃይማኖት በኩል ወደድኩ፡፡»
ዑመርም [ረዐ] እንዲህ አሉ: ‐ «ይህ የወረደበትን ቀን እና በነቢዩ [ﷺ] ላይ የወረደበትን ስፍራም አውቀነዋል። በጁሙዐ ቀን የዐረፋ ሜዳ ላይ ቆመው ሳለ የወረደ ነው።»
:
ዲን በዚያን ቀን ተሟላ የተባለው ሙስሊሞች ከዚያ በፊት ሐጅ አድርገው ስለማያውቁ ነው። ሐጅ ሲያደርጉ ዲኑ ያኔ ተሟላ። ምክንያቱም ሐጅ የኢስላም አንዱ መዐዘን ነው። በዚያን ዓመት ከሺርክ የፀዳው በኢብራሂም መንገድ ላይ የተመሰረተው የሐጅ ስነስርዐት ከነሙሉ ክብሩ ዳግም ተግባራዊ ተደርጓል። ዲኑም ሙሉ ማእዘናቱ ተሟልቷል።
:
⚃ ምርጡ ዱዓ:
የአላህ መልክተኛ [ﷺ] እንዲህ ብለዋል:‐
«ምርጥ ዱዓ የዐረፋ ቀን ዱዓ ነው። እኔና ሌሎች ነቢያት ከተናገርነው ሁሉ ምርጡ ንግግር "ላኢላሀ ኢልለላህ ወሕደሁ ላ ሸሪከ ለሁ ለሁል ሙልክ ወለሁል ሐምድ ወሁወ ዐላ ኩልሊ ሸይኢን ቀዲር" የሚለው ቃል ነው።»
ቲርሚዚ ዘግበውታል።
በዐረፋ ቀን የአላህን እዝነት እና ምህረት ለማግኘት ዚክርና ዱዓ ማብዛት ያስፈልጋል። በተለይም «ላኢላሀ ኢልለላህ» የእለቱ ምርጥ ዚክር ነው።
:
⚄ ጾም:
የአላህ መልክተኛ [ﷺ] እንዲህ ብለዋል: ‐ «የዐረፋ ቀን ጾም ያለፈውን እና የሚመጣውን ዓመት ኃጢኣት ያስምራል ብዬ አምናለሁ።» ሙስሊም ዘግበውታል
:
⚅ የዒድ ቀን ነው:
የዐረፋ ቀን የዒድ ቀን ነው። ሙስሊሞች ከሚኮሩባቸው የበዓል ቀናቶቻቸው መሀል ይመደባል። የአላህ መልክተኛ [ﷺ] እንዲህ ብለዋል: ‐
«የዐረፋ ቀን፣ የአድሐ ቀን እና የተሽሪቅ ቀናት ለሙስሊሞች የዒድ ቀናችን ናቸው። የመብልና የመጠጥ ቀናት ናቸው።» ቲርሚዚ እና አቡ ዳዉድ ዘግበውታል።
:
⚆ የምህረት እና ከእሳት ነፃ የሚደረግበት:
የአላህ መልክተኛ [ﷺ] እንዲህ ብለዋል:‐ «አላህ ሰዎችን ከእሳት ነፃ የሚያደርግበት ከዐረፋ ቀን የበለጠ ቀን የለም። አላህ [በእዝነቱ] ወደ ምድር ይቀርባል። በመላኢካዎች ላይም ይፎክራል። 'እነዚህ ባሮቼ ከእኔ ውጪ ሌላን አይፈልጉም!' ይላል።» ሙስሊም ዘግበውታል።
:
በዚህ እለት ከእሳት ነፃ መሆንና የአላህን ምህረት ማግኘት የሚሻ ሰው በአላህ እዝነት ለመታየት የሚያበቁትን ተግባራት ይፈፅም። ከሁሉም የመጀመሪያው ስራ ደግሞ ከኃጢኣት ነፍሱን መጠበቅ ነው።
ሌሎች ተግባራት ተከታዮቹ ናቸው:
① ጾም
ከሐጀኛ በስተቀር ሌላው ሰው ይጾማል። የዚህ ቀን ጾም የሁለት ዓመታት ኃጢኣት ያስምራል።ተክ
② ተክቢራ
ተክቢራ የእለቱ ዓርማ ነው። በተለይም ከሱብሒ ሶላት ጀምሮ ከማንኛውም ሶላት በኋላ ተክቢራ ይደረጋል።
③ ማንኛውም ዚክርና ዱዓእ
ቁርኣን መቅራት፣ ሶለዋት ማድረግ፣ ተክቢራ፣ ተስቢሕ፣ ተህሊል፣ ኢስቲግፋር ማድረግ። አንዳንዴ ለብቻ ቆይቶም በጀመዐ ዱዓና ዚክር ማድረግ የእለቱ ድምቀት ነው።
እለቱ ጥቂት ተሰርቶ ብዙ የሚገኝበት በመሆኑ እንጠቀምበት! ቤተሰቦቻችንን እናንቃ! የምናውቀውን ሁሉ እናነሳሳ!
አላህ ተውፊቅ ይስጠን!
https://www.tg-me.com/fiqshafiyamh
Forwarded from Bright (Japi 😎😜)
❤️❤️❤️ 3 ነገሮች ❤️❤️

.........አላህ 3 ነገሮች ይጠላብናል........
1ኛ........አሉባልታን
2ኛ.........በሆነ ባልሆነ ጥያቄ ማብዛትን
3ኛ.........ማባከንን

...........አላህ (ሱ.ወ)3 ዓይነት ሰዎችን ይረዳል........

1ኛ.........በአላህ መንገድ የሚታገልን
2ኛ.........እዳውን ለመክፈል የሚጣጣርን
3ኛ..........ከዝሙት መታቀብን አስቦበት ኒካህ ለማድረግ የሚንቀሳቀስን

.............ዱዐ ላደረገ ሠው 3 የምላሽ ዓይነቶች..........
1ኛ.......ወዲያው መልስ ሊያገኝ ይችላል
2ኛ.......ለአኺራ ተላልፎለት ይሆናል
3ኛ.......ሊደርስበት የተቃረበን ያላሰበውን መጥፎ ነገር ሊያስወግድለት
ይችላል

😍😍😍😍😍😍😍😍😍😍

وَإِذَا سَأَلَكَ عِبَادِى عَنِّى فَإِنِّى قَرِيبٌ ۖ أُجِيبُ دَعْوَةَ ٱلدَّاعِ إِذَا دَعَانِ ۖ فَلْيَسْتَجِيبُوا۟ لِى وَلْيُؤْمِنُوا۟ بِى لَعَلَّهُمْ يَرْشُدُونَ
ባሮቼም ከእኔ በጠየቁህ ጊዜ (እንዲህ በላቸው)፡- እኔ ቅርብ ነኝ፡፡ የለማኝን ጸሎት በለመነኝ ጊዜ እቀበለዋለሁ፡፡ ስለዚህ ለኔ ይታዘዙ፤ በኔም ይመኑ፤ እነሱ ሊመሩ ይከጀላልና፡፡

@Brighhhttt
Forwarded from Bright (Japi 😎😜)
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
የለይል ሰላት አፍቃሪወች በጀነት አብሽሩ
😭😭😭😭😭😭😭😭😭

@Brighhhttt
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
9ኛ ዙር 1 GB ጥቅል ሚያሸልም ጥያቄና መልስ 😍😍😍😍😍 😍😍
እሁድ 2:30 ላይ 10 ኢስላሚክ ጥያቄና መልስ በቻናላችን ሲለቀቅ እስከ ማታ 4:00 ሰአት ድረስ መሞከር ይቻላል እና አሸናፊው ወይንም 10ኑም ጥያቄ የመለሰ 1ኛ የወጣው 🙈 1GB ይሸለማል ❤️❤️❤️❤️❤️
እስከ 3 ደረጃ እንገልፃለን ስትሞክሩ ሙሉ ስማችሁን ከነአድራሻችሁ ግለፁ ሙሉውን የመለሱ ካሉ በደቂቃ እንለያለን
በየሳምንቱ አለን ኢንሻአላህ😍😍😍😍😍😍 መልካም እድል መልሶቹ ሚመለሱት @abushreqett ነው
❤️❤️❤️መልካም እድል 👍👍👍👍
Forwarded from Bright (Japi 😎😜)
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
ጣፋጭ ታሪክ❤️ ሰኢድ ኢብኑ ሙሰየብ
ልጁን የዳረለት ደሃ 😍😍😍😍

https://www.tg-me.com/Brighhhttt
Forwarded from Bright (Japi 😎😜)
ውድ የቻናላችን ተከታታዮች 😘😍😍
👇👇👇👇👇👇👇👇👇👇
1ኛ ዙር 1 GB ጥቅል ሚያሸልም ጥያቄና መልስ 😍😍😍😍😍 😍😍
እሁድ 2:30 ላይ 10 ኢስላሚክ ጥያቄና መልስ በቻናላችን ይኖረናል 👍 እስከ ማታ 4:00 ሰአት ድረስ መሞከር ይቻላል እና አሸናፊው ወይንም 10ኑም ጥያቄ የመለሰ 1ኛ የወጣው 🙈 1GB ይሸለማል ❤️❤️❤️❤️❤️
እስከ 3 ደረጃ እንገልፃለን ስትሞክሩ ሙሉ ስማችሁን ከነአድራሻችሁ ግለፁ ሙሉውን የመለሱ ካሉ በደቂቃ እንለያለን
በየሳምንቱ አለን ኢንሻአላህ😍😍😍😍😍😍 መልካም እድል መልሶቹ ሚመለሱት @abushreqett ነው
❤️❤️❤️ 👍👍👍👍

https://www.tg-me.com/Brighhhttt
Forwarded from Bright (Japi 😎😜)
🙏🙏🙏🙏👇👇👇👇👇👇

❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️

9ኛ ዙር😊 የጃፒ ወዳጆች 1 GB ዳታ ስጦታ ያለው እና ቤተሰባዊ ጥያቄና መልስ ከአጠቃላይ ነው የወጣው 🎁🎁 🙈🙈


1⃣ኛ ኢትዮጲያ ላይ ATM ( ኤቲኤም) ካርድ አገልግሎት ለመጀመሪያ ጊዜ የጀመረው ባንክ ማን ይባላል 💵💰 ?

2⃣ኛ የደውላ አባሲያ ኢስላማዊ ግዛት መናገሻ ዋና ከተማ ማነው? 🏛

3⃣ኛ እንደሰው ህልም ማየት ሚችለው እንስሳ ምንድነው? ? 😑

4⃣ኛ ጀነት ምትናፍቃቸው 3ቱ ሶሀቦች እነማን ናቸው 😭

5⃣ኛ 5ኛው ኸሊፋ በመባል ሚታወቀው ማነው? ?👱‍♂

6⃣ኛ ንብ ስንት አይኖች አሏት? ??🐝

7⃣ኛ የሰው ልጅ የአጥንት ብዛት ስንት ነው? ? 🧑‍🦱

8⃣ኛ ከአራቱ ኸሊፋወች ሸሂድ ሁኖ ያልሞተው የትኛው ነው? ? 💔

9⃣ኛ ከአራቱ መዝሀቦች ከቀዳሚው ተከታዩ ወይም ሁለተኛ የነበረው የትኛው ነው ( abu hanifa ahmed shafie malik)

1⃣0⃣ኛ ረሱል ሰአወ ማንን ነው እኔና ------- (ይህ ሰው) ጀነት ላይ እንደዚ ነን ብለው ሁለት ጣታቸውን ገጥመው ያሳዩት ?


🅱Ones

የሞናሊዛ ስእል የት ሀገር ሚገኘው ሙዝየም ውስጥ ነው ያለው? ?? 🖼

መልካም እድል 🎁🎁

መልሶቻችሁን 👇👇👇 በዚ ላኩ
@abushreqett

😍😍😍😍😍😍😍😍😍😍😍👨‍🦰👨‍🦰👨‍🦰
@Brighhhttt
Forwarded from Bright (Japi 😎😜)
ሸገሮች 😭😭😭 በጂማወች ተበልጠናል መቱ እና ቤቴል ብቻ ነው ተሳትፎ ያለው 🤷‍♂🤷‍♂😊😊😊😊😊😏😏😏
Forwarded from Bright (Japi 😎😜)
ድሬወች አሪፍ ተሳትፎ ወላሂ ሊመሩ ነው መሰለኝ ❤️❤️ ከኡመር ቢን ኸጣብ መስጊድ ነን ይሉናል ባረከላሁ ፊኩም 😍😍😍😍😍😍
Forwarded from Bright (Japi 😎😜)
ሰበታወች ከኛ አያልፍም የመወዳ ልጆች ነን 💪💪 😍😍😍😍😍❤️❤️❤️❤️
Forwarded from Bright (Japi 😎😜)
አሸናፊውን ነገ እናሳውቃለን 3 ሰአት ላይ መልሶቹን ግን ከ 10 ደቂቃ በኋላ እንለቃለን 🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏🙏
@Brighhhttt
Forwarded from Bright (Japi 😎😜)
❤️❤️❤️❤️❤️

አሸናፊውን ነገ 3 ሰአት እናሳውቃለን ሙሉ የመለሱት ብዙ ናቸው በጥንቃቄ አይተን በቦነሱ ለይተን በደቂቃው ለይተን ጊዜ ይጠይቃልና ነገ ብለናል 😍😍😍

መልሶቻቸው ግን በጭንቀት እንዳታድሩ ይነገራችሁ እና ለነገው ውጤት ከመልሶቻችሁ ጋር አወዳድሩ 🙏🙏

👇👇👇👇👇👇😍😍😍😍😏

1ኛ ዳሽን ባንክ 🙏

2ኛ ኢራቅ ( ባግዳድ )🇮🇶

3ኛ ፈረስ 🐺

4ኛ ሰልማን ቢን ፋሪስ
አማር ቢን ያሲር
አሊይ ቢን አቢ ጣሊብ 😭

5ኛ ኡመር ቢን አብዲልአዚዝ ( ሙአዊያ ያላችሁ አጠጋግቼ አርሜዋለሁ)🌕

6ኛ አምስት 🐝

7ኛ 206 👍

8ኛ አቡ በከር ሲዲቅ😍

9ኛ ኢማሙ ማሊክ 👨‍🦳

10ኛ የቲምን ተንከባካቢ ( ካፊሉልየቲምን) 🏌

Bones France 🇫🇷🇫🇷
@Brighhhttt
Forwarded from Bright (Japi 😎😜)
🌐10 የሪዝቅ መክፈቻ ቁልፎች

1- ኢስቲግፋር እና ተዉባ፣💡
2- እውነተኛ የሆነ የአላህ ፍራቻ፣😭
3- መስፈርቱን ያሟላ ዱዓእና የተመረጡ አዝካሮችን ማብዛት፣ 😍
4- ነቢዩን መውደድ እና በርሣቸው ላይ ሰለዋት ማውረድ፣ 💚
5- ዘካን ማውጣት ሰደቃ መስጠት፣📿
6- ለደካሞችና ችግረኞች መልካም መዋል፣👴
7- እዉነተኛ መመካትን በአላህ ሱ.ወ. መመካት፣
8- ለእናት አባት በጎ መዋል፣😘
9- ለአላህ ሱ.ወ. ምስጋናና ዉዳሴ ማድረስ፣🙏
10- ኒካህ ማድረግ🙄👀

😍❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️❤️
@Brighhhttt
"LOVE vs LIVE":
አሁን ይሄንን ወደምታነቢው እህት ወይም ወንድም ልመለስ ፤ የአላህን ንፁ አየር ያለ አንዳች ክልከላና ክፍያ ይሄን ያህል ስትተነፍሺ ኖረሻል ወይም ስትተነፍስ ኖረሃል ። አሁን ከግዜሽ ወይም ከግዜህ ላይ 2 ሰከንድ በመውሰድ
" አላህ ሆይ ስለነፃ ስጦታህ አላሀምዱሊላ" በማለት ለ20 ጓዳኞችህ / ሽ forward አርጉላቸዉ share 🙏🙏🙏

ሰይጣን :🤣🤣🤣🤣🤣🤣🤣
አላህም : ምንድነው የሚያስቅህ?
ሰይጣን : ይሄ ባሪያህ የኔ ነው አላልክም
አላህም ፡ የትኛው?
ሰይጣን : ይሄ የሚያነበው!
አላህም : አዎ ባሪያዬ ነው
ሰይጣን : ያንተ ባሪያህ ለ 10 ሰው እንኳን አይልክም
አላህም ፡እይ የኔ ባሪያ አሁን ለ 20 ሰው ይልካል
ሰይጣን : እሺ የኔ ግን ሳይልክ ይተወዋል
እስኪ ለስይጣን #እምቢ! በማለት በመላክ አሳዩት

#እስቲ_አላህን_እናስደስተው
#ሽር_share_በማደረግ

አንድ ቀን #ረሱል (ሰ.ዐ.ወ)
ለዐሊይ (ረዐ) እንዲህ አሉት::
አንተ ዐሊይ ሆይ ከመተኛትህ በፊት አምስት ነገሮችን ተግብር፡፡
1,ስትተኛ አራት ሺ ዲናር ሶደቃ ስጥ
2,ቁርዐን አኽትም
3,ለጀነት ዋጋዋን ክፈል
4,ሁለት ሰዎችን አስታርቅ
5,ከዚያም አንድ ጊዜ ሐጅ አድርገህ ተኛ፤
ዐሊይም(ረዐ)እንዲህ በማለት ጠየቁ፦ያ ረሱለላህ ይሄን በአንድ ለሊት እንዴት ማረግ ይቻላል?ብሎ ጠየቃቸው
❄️ረሱልም❄️(ሰ.ዐ.ወ) የሚከተለውን ተናገሩ፡
1,አራት ጊዜ ሱረቱል #ፋቲሀን የቀራ 4000 ዲናር ሰደቃ ከሰጠው ጋር እኩል ነው።
2,ሶስት ጊዜ ሱረቱል #ኢኽላስን(ቁል ሁ ወላሁ አሀድ) የቀራ አንድ ጊዜ እንዳኸተመ ይቆጠርለታል።
3,ሶስት ጊዜ ላ ሀውላ ወላ ቁወተ ኢላ ቢላሂል ዐሊዩል ዐዚም ያለ የጀነት ዋጋዋን ከፍላል።
4,አስር ጊዜ #እስቲግፋር ያረገ ሁለት ሰዎችን እንደ ማስታረቅ ነው።
5,አራት ጊዜ #ሸሀዳ ያደረገ አንድ ጊዜ ሀጅ እንዳደረገ ነው:;;

አስብ ይሄ መልእክት አንተ ጋር ብቻ እንዲቆይ አትፍቀድ ለሌሎችም አጋራ ባንተ ምክንያት ሌላ ሰው አንብቦ ቢጠቀም አንተም የሱ ምንዳ ተካፋይ ነህና።

አላህ ባነበብነው ባስተላለፍነው ተጠቃሚ ያድርገን
🗯🗯🗯🗯🗯🗯🗯
https://www.tg-me.com/ONLYFORTRUTHERSJ
#ለሰው_ልጅ_ትልቁ_ደስታ_መልካም_ትዳር_ነው
✿✿<>✿✿<>✿✿<>✿✿<>✿✿<>✿
💐💐💐💐💐💐
#ሴት_ሆይ_ለትዳርሽ_ብቁ_ነሽን?!"
➊.ባለቤትሽ ወደ ቤት በገባ ጊዜ በእጅሽ ያለውን ነገር ትተሽ እሱን ለመቀበል ካልሄድሽ፣ ከፊቱ ላይ የተመለከትሺውን የድካም ስሜት ካላስረሳሽ
{ አንቺ ለትዳርሽ ብቁ አይደለሽም}
:
➋.ባለቤትሽ አንቺ በእጅሽ ሰርተሽ የማታባይው ከሆነ ከምግብ ቤቶች ከተመገበ ፣ ልብሶቹን የማታዘጋጂለት ከሆነና ወደ ማጠቢያ ቤት ከወሰደ
{አንቺ ለትዳርሽ ብቁ አይደለሽም}
:
➌.ባለቤትሽ በተቆጣ ጊዜ በአስር ቃላት የምትመልሺለት ከሆነ፣ድምፅሺን ከፍ አድርገሽ ካወራሽው{አንቺ ለትዳርሽ ብቁ አይደለሽም}
:
➍.ከባለቤትሽ አጠገበ በተቀመጥሽ ጊዜ ጠረንሽ ጥሩ ካልሆነ፣የልብስሽን ንፅህና ካልጠበቅሽ፣እሱን የሚማርኩ ካልሆኑ {አንቺ ለትዳርሽ ብቁ አይደለሽም}
:
➎.ከሱጋ በተጣላሽ ወቅት ወደ እናትሽ ቤት፣ወደ እህትሽ፣ ወደ ጓደኛሽ ቤት የምትሄጂ ከሆነ
{አንቺ ለትዳርሽ ብቁ አይደለሽም}
:
➏.ከባለቤትሽ ቤተሰቦች ጋር ስትሆኚ የሱን ቤተሰቦች መልካምን በማድረግ የማትንከባከቢ ከሆንሽ {አንቺ ለትዳርሽ ብቁ አይደለሽም}
:
➐.በፀሎት ጊዜ እሱን የማትቀሰቅሺ ከሆንሽ፣ ፈጣሪን በመታዘዝ ላይ የማተበረታቺው ከሆነ፣ ክልክል ነገራቶችን እንዲተው የማታደርጊ እና ወደ ተውበት የማትገፋፊው ከሆንሽ
{አንቺ ለትዳርሽ ብቁ አይደለሽም}
:
➑.ባልሽ የሚወዳቸውን እና የሚጠላቸውን ነገሮች ለይተሽ ካላወቅሽ {አንቺ ለትዳርሽ ብቁ አይደለሽም}
:
❖❖~❖❖~❖❖< >❖❖~❖❖~❖❖
:💐💐💐💐💐💐
#ወንድ ሆይ ለትዳርህ በቁ ነህን?
:
➊.ሚስትህ ምቾት እና እንክብካቤ ስለምትፈልግ
ካልተንከባከብካት እና ያለህን ነገር በሙሉ ሳትሰስት ካላጋራሃት አንተ ለትዳርህ ብቁ አይደለህም።
:
➋.ሚስትህ ፍቅርህን እንድትገልጽላት ትሻለች። ባገኘከው አጋጣሚ ከንፈሯን እየሳምክ ፍቅርህን የማትገልፅላት ከሆነ አንተ ለትዳርህ ብቁ አይደለህም።
:
➌.ሚስትህ ግትር ባል ትጠላለች። ደካማ ባልን ደግሞ ትንቃለች አንተ ጥንካሬ በሚያስፈልግበት ቦታ ጠንካራ ሌላ ጊዜ ደግሞ ገር መሆንን ካልቻልክ አንተ ለትዳርህ ብቁ አይደለህም።
:
➍.ሚስትህ መልካም ንግግር፣ ወንዳ ወንድ ገጽታ፣ በስፖርት የተገነባ ሰውንት፣ ንጹህ ልብሶችና ጥሩ መአዛ ይማርካታል እነዚህን ማድረግ ካልቻልክ አንተ ለትዳርህ ብቁ አይደለህም።
:
➎.ለሚስትህ ቤቷ ቤተ መንግስት ነው። ይህን ቤተመንግሥቷን ካስደፈርክባት አንተ ለትዳርህ ብቁ አይደለህም።
:
➏.ሚስትህ እጅግ በጣም ብትወድህም ቤተሰቦቿን ማጣት አትፈልግም። ቤተሰቦቿን ብትንከባከብ ከነበረው ፍቅር ላይ ሌላ ፍቅር ትጨምራለህ ይህ ካልታየህ አንተ ለትዳርህ ብቁ አይደለህም።
:
➐.ሚስትህ አንዳንዴ የዋልክላትን ውለታ ልትዘነጋ ትችላለች። (ስትናደድ) ያደረክላትን ነገርም ልትክድ ትችል ይሆናል። ይህን ባህሪዎቿን ባትወድላት ሌሎች የሚወደዱ ብዙ ባህሪዎች እንዳሏት ከዘነጋህ አንተ ለትዳርህ ብቁ አይደለህም።
:
➑.ሚስትህ አካላዊ ድካም፣ ተፈጥሯዊ ወይንም ወራዊ ህመም እና ስነልቦናዊ ጫና እየተፈራረቁ ስለሚያጠቋት ልትነጫነጭ ትችላለች። ይህን ዘንግተህ እሷን ከመንከባከብ ፈንታ አንተም
እንደሷ ከተነጫነጭክ አንተ ለትዳርህ ብቁ አይደለህም።
:
➒.ባገኘሁ አጋጣሚ ሚስትህን እቀፍ፣ ሳም፣ ፀጉሯን ወገቧን እሽ ሚስትህ ላንተ ሁሌም ቆንጆ እንደሆንች አስመስክር። ሚስትህ እንደ አንተ አልጋ ላይ የፍቅር ጨዋታ ያምራታል በግልፅ ፍላጎቷን በሚገባ አርካት ይህ ካልታየህ አንተ ለትዳርህ ብቁ አይደለህም።
➓.ሚስትህ እንደ አቅሟ ተውባ እና አጊጣ መታየትን ትፈልጋለች።
የመጀመሪያ የውበቷ አድናቂ ቧልዋ መሆኑን አትዘንጋ ስለዚህ ሁሌም ውበቷን አድንቅላት።
ሚስትህ ተውባ እና አጊጣ ማየት ካልፈለክ አንተ ለትዳርህ ብቁ አይደለህም።
➊➊.ደስታን፣ ሀዘንን፣ ችግርን እና ቅሬታን ለሚስትህ በግዜ ንገራት። ደስታውን አመስግኑ። ሀዘኑን ተፅናኑ፣ ችግርን እና ቅሬታን ብቻችሁን በውይይት ፍቱ። ሚስትህን በፍፁም አታኩርፍ እንዚህን መምራት ካቃተህ አንተ ለትዳርህ ብቁ አይደለህም።
:
➊➋.ሚስትህ ስትናገር እስከመጨረሻው በጥሞና ካላደመጥካት ችግሯን ካልፈታህላት አንተ ለትዳርህ ብቁ አይደለህም።
➊➌.ከፈጣሪ ቀጥሎ ከምንም እና ከማንም በላይ መጀመሪያ አንተ፣ ሚስትህ፣ እና ልጆችህን ብቻ አስቀድም። ቤተሰብ፣ ጓደኛ፣ ጎረቤት እና ሌላው ከእናንተ ቀጥሎ ናቸው። ይህን ማስተዋል
ከተሳነህ አንተ ለትዳርህ ብቁ አይደለህም።
❖❖~❖❖~❖❖< >❖❖~❖❖~❖❖
# ወዳጆቼ፥
እንግዲህ አሏህ የራሳችሁ በሆነ ሰው ባርኮ የስጣችሁ፡፡
በተረፈ ፈጣሪ ላገባነውም ላላገባነውም ማስተዋል ይስጠን እላለሁ
❖❖~❖❖~❖❖< >❖❖~❖❖~❖❖
☞በትዳር ዓለም ውስጥ ላላችሁም መልካም ትዳር ፡፡

ለወደፊት ትዳር ለምትመሠርቱ ሁሉ ትዳራችሁ የሏህ አንዱ ኒእማ ነዉ እና ፡፡
ፍቅር የበዛበት ያድርግላችሁ!
አሚን
ዚክር፣ የዘነጋነው ሃብት
~~~~~~
መቼም ሰው ነንና ፈራሽ እንደሆንን እናውቃለን። እንደ ሙስሊም ከሞት በኋላ ህይወት እንዳለ እናምናለን። ስለሆነም የአኺራችን ጉዳይ ያስጨንቀናል። ለዚህም ሲባል በጌታችን ህግ ለመኖር፣ ትእዛዛቱን ለመፈፀም ክልከላውን ለመራቅ፣ ስለ ድክመታችን ተውበት ለማድረግ እንሞክራለን። ሆኖም ግን አንድ በቀላል ጥረት ብዙ ትርፍ የምንሸምትበትን ነገር ስንዘነጋ እንስተዋላለን።
አዎ ስራሽን እየሰራሽ፣ መኪናህን እየሾፈርክ፣ ወረፋ እየጠበቃችሁ፣ በመኪና እየተጓዝክ፣ ሰው እየጠበቅሽ፣ በእግራችን እየተንቀሳቀስን፣… ዚክር ቢደረግ በየእለቱ ስንትና ስንት አጅር በሰበሰብን ነበር። ዚክር ከምናስበው እጅግ የላቀ ፋይዳ አለው። ነብዩ ሶለ፞ላ፞ሁ ዐለይሂ ወሰለ፞ም እንዲህ ብለዋል:–
"أَلَا أُنَبِّئُكُمْ بِخَيْرِ أَعْمَالِكُمْ، وَأَزْكَاهَا عِنْدَ مَلِيكِكُمْ، وَأَرْفَعِهَا فِي دَرَجَاتِكُمْ، وَخَيْرٌ لَكُمْ مِنْ إِنْفَاقِ الذَّهَبِ وَالْوَرِقِ، وَخَيْرٌ لَكُمْ مِنْ أَنْ تَلْقَوْا عَدُوَّكُمْ، فَتَضْرِبُوا أَعْنَاقَهُمْ، وَيَضْرِبُوا أَعْنَاقَكُمْ ".
قَالُوا : بَلَى.
قَالَ : " ذِكْرُ اللَّهِ تَعَالَى".
* "ከ(መልካም) ስራዎቻችሁ በላጭ፣
* ከንጉሳችሁ ዘንድ የጠራ፣
* ደረጃዎቻችሁን ከፍ የሚያደርግ፣
* ወርቅና ብር ከመለገስ የሚሻላችሁ፣
* ጠላቶቻችሁን አግኝታችሁ አንገቶቻቸውን ከምትመቱና አንገቶቻችሁን ከሚመቱ (ከጂሃድ) የሚበልጥባችሁን አልነግራችሁምን?"

√ (ሶሐቦች):– "እንዴታ! (ይንገሩን) የአላህ መልእክተኛ ሆይ" አሉ።
* "አሸናፊና የላቀውን አላህ ማውሳት" አሉ።
[ቲርሚዚ ዘግበውታል: 3377]

ትልልቅ ምንዳ ያላቸው አጫጭር ዚክሮች
~~~~~~~~~~~~~~~~~
① ነብዩ ሶለ፞ላ፞ሁ ዐለይሂ ወሰለ፞ም እንዲህ ብለዋል:–
(مَن قال: سبحان الله وبحمده، في يوم مائة مرة، حُطَّت خطاياه وإن كانت مثل زبد البحر)؛
"በቀን ውስጥ መቶ ጊዜ ‘ሱብሓነላ፞ሂ ወቢሐምዲሂ’ ያለ ሰው ወንጀሎቹ እንደ ባህር አረፋ ቢሆኑ እንኳን ይረግፉለታል።" [ቡኻሪ]

② እናታችን ጁወይሪያህ ቢንቲል ሓሪሥ ረዲየላ፞ሁ ዐንሃ ባስተላለፈችው በአንድ ወቅት ነብዩ ሶለ፞ላ፞ሁ ዐለይሂ ወሰለ፞ም ሱብሕን ከሰገዱ በኋላ ማለዳ ላይ ከሷ ዘንድ ወጡ። እሷ መስገጃዋ ላይ ተቀምጣ ዚክር ላይ ነች። እዚያው እንደተቀመጠች ረፋድ ላይ ተመለሱ።
"ካንቺ ከተለየሁ ጊዜ አንስቶ እስካሁን በተለየሁብሽ ሁኔታ ላይ ከመሆን አልተወገድሽም?" አሏት።
"አዎ" አለች።
በዚህን ጊዜ እንዲህ አሉ:–
" لَقَدْ قُلْتُ بَعْدَكِ أَرْبَعَ كَلِمَاتٍ ثَلَاثَ مَرَّاتٍ، لَوْ وُزِنَتْ بِمَا قُلْتِ مُنْذُ الْيَوْمِ لَوَزَنَتْهُنَّ : سُبْحَانَ اللَّهِ وَبِحَمْدِهِ عَدَدَ خَلْقِهِ، وَرِضَا نَفْسِهِ، وَزِنَةَ عَرْشِهِ، وَمِدَادَ كَلِمَاتِهِ ".
"በእርግጥም ካንቺ በኋላ አራት ንግግሮችን ሶስት ጊዜ ተናግሬያለሁ። ከንጋት ጀምሮ አንቺ ካልሺው ጋር ቢመዘኑ (እኔ ያልኳቸው) ይመዝናሉ።
* ሱብሓነላ፞ሂ ወቢ ሐምዲሁ ዐደደ ኸልቂሁ፣
* ወሪዷ ነፍሲሂ፣
* ወዚነተ ዐርሺሂ፣
* ወሚዳደ ከሊማቲሂ።" [ሙስሊም የዘገቡት]

③ ነብዩ ሶለ፞ላ፞ሁ ዐለይሂ ወሰለ፞ም እንዲህ ብለዋል:–
(كلمتان خفيفَتان على اللسان، ثقيلَتان في الميزان، حبيبَتان إلى الرحمن: سُبحان الله وبحمده، سبحان الله العظيم)؛
"ምላስ ላይ የቀለሉ፣ ሚዛን ላይ የከበዱ እና አረ፞ሕማን ዘንድ የተወደዱ ሁለት ንግግሮች አሉ። ‘ሱብሓነላ፞ሂ ወቢሐምዲሂ፣ ሱብሓነላ፞ሂል ዐዚም።" [ቡኻሪና ሙስሊም]

④ ነብዩ ሶለ፞ላ፞ሁ ዐለይሂ ወሰለ፞ም ከጀነት ድልብ ሃብቶች ውስጥ እንደሆነ የገለፁት የዚክር አይነት
(لا حول ولا قوة إلا بالله)؛
"ላ ሐውለ ወላ ቁወ፞ተ ኢላ፞ ቢላ፞ህ" [ኢብኑ ሒባ፞ን]

⑤ ነብዩ ሶለ፞ላ፞ሁ ዐለይሂ ወሰለ፞ም እንዲህ ብለዋል:–
(مَن قال: لا إله إلا الله وحده لا شريك له، له الملك وله الحمد وهو على كل شيء قدير - عشر مرات - كان كمَن أعتق أربعة أنفُسٍ مِن ولد إسماعيل)

"አስር ጊዜ ’ላ ኢላሀ ኢለ፞ላ፞ህ ወሕደሁ ላ ሸሪከ ለህ። ለሁል ሙልኩ ወለሁል ሐምዱ። ወሁወ ዐላ ኩሊ፞ ሸይኢን ቀዲር’ ያለ ሰው ከኢስማዒል ልጆች አራት ነፍሶችን ነፃ እንዳወጣ ነው።" [ሙስሊም]

⑥ ነብዩ ሶለ፞ላ፞ሁ ዐለይሂ ወሰለ፞ም እንዲህ ብለዋል:–
(سيِّد الاستغفار أن تقول: (اللهمَّ أنت ربي، لا إله إلا أنت، خلقتَني وأنا عبدُك، وأنا على عهدك ووعدك ما استطعتُ، أعوذ بك من شرِّ ما صنعتُ، أبوء لك بنعمتك عليَّ، وأبوء لك بذنبي، فاغفر لي، فإنه لا يغفر الذنوب إلا أنت، قال: ومَن قالها من النهار موقنًا بها، فمات من يومه قبل أن يُمسي فهو مِن أهل الجنَّة، ومَن قالها من الليل وهو مُوقن بها، فماتَ قبْل أن يُصبح، فهو مِن أهل الجنَّة)؛
"የኢስቲግፋር ሁሉ አለቃ ‘አላ፞ሁመ፞ አንተ ረቢ፞ ላ ኢላሀ ኢላ፞ አንተ። ኸለቅተኒ። ወአነ ዐብዱከ። ወአነ ዐላ ዐህዲከ ወወዕዲከ መ’ስተጦዕቱ። አዑዙ ቢከ ሚን ሸሪ፞ ማ ሶነዕቱ። አቡኡ ለከ ቢኒዕመቲከ ዐለየ፞። ወአቡኡ ለከ ቢዘንቢ። ፈግፊር ሊ። ፈኢነ፞ሁ ላ የግፊሩ ዙ፞ኑበ ኢላ፞ አንተ’ የሚለው ነው።
በሷ አረጋግጦ በቀኑ ካላት በኋላ ሳያመሽ በእለቱ የሞተ ሰው እርሱ ከጀነት ሰዎች ነው። በሷ አረጋግጦ በሌሊት ካላት በኋላ ሳያነጋ የሞተ ሰው እርሱ ከጀነት ሰዎች ነው።" [ቡኻሪ]

እነዚህ ምሳሌዎች ብቻ ናቸው። ሌሎችም ብዙ አሉ። ከነዚህ በተጓዳኝ ከውዱእ በኋላ፣ ከአዛን በኋላ፣ መስጂድ ስትገባ፣ ከመስጂድ ስትወጣ፣ ከሶላት በኋላ፣ ከምግብ በኋላ፣ ስትተኛ፣ ስትነሳ፣ ወዘተ ያሉትን ብትል ቆጥረህ የማትዘልቀው አጅር አለህ።
በጥቅሉ ጊዜህን መድበህ ዚክርን የህይወትህ አካል አድርገው። ለዚህ ከተቸገርክ እየሰራህ፣ እየተጓዝክ ብዙ መፈፀም ትችላለህ። ዚክር ትኩረት እንጂ የረባ ጥረት አይጠይቅህም። መልእክተኛው ሶለ፞ላ፞ሁ ዐለይሂ ወሰለ፞ም እንዳሉት "ምላስህ አላህን በማውሳት ከመርጠብ አይወገድ።"
2025/10/01 08:03:36
Back to Top
HTML Embed Code: