#ዜና

የIONNA የኤሌክትሪክ መኪኖች ቻርጀሮቹን ኢንስታቴሽን በታቀደበት ጊዜ አይጀመርም።



በቅርቡ የተመሰረተ የኤሌክትሪክ መኪኖች ቻርጂንግ ካምፓኒ IONNA በዚህ Summer አቅዶት እንደነበረው ቻርጀሮቹን መትከል አይጀምርም።

IONNA በBMW ፣ Hond ፣ Hyundai ፣ Kia ፣ Mercedes እና Stellantis አጋርነት ፈጥረው የመሰረቱት እና በያዝነው አመት መጀመሪያ ላይ ይፋ ያረጉት ካምፓኒ ነው።
አላማው 30,000 የቻርጂን ስቴሽኖችን ሰሜን አሜሪካ ላይ መገንባት ነው። ከቀም ብሎ እንዳሳወቀው የካምፓኒው የመጀመሪያዎቹ ፈጣን ቻርጀሮች በዚህ Summer መገጠም እንደሚጀምሩ ቢሆንም WardsAuto ይዞት የወጣው መረጃ ላይ ህብረቱ ውስጥ ያሉ ሁለት የመኪና አምራቾች በተባለው ጊዜ ቻርቸሮቹ መገጠም እንደማይጀምሩ ገልፀዋል።
በዛ ምትክ በአመቱ ማገባደጃ ላይ የሚጀመር ይመስላል።

IONNA የቻርጀሮቹን ኢንስታሌሽን ለማዘግየቱ ምክንያት ከሆኑት ምክንያቶች ውስጥ አንዱ ቻርጀሮቹን በCCS እና በቴስላው NACS ኮኔክተሮች ማቅረብ ስለፈለገ ነው።

#IONNA #EV_Charging_Station
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ዜና

Archer የተባለው VTOL(vertical take-off and landing aircraft) ኮሪያ ላይ ትልቅ ሽያጭ አገኘ።


የአሜሪካው የVOTL ካምፓኒ Archer Aviation ደቡብ ኮሪያ ላይ 50 እንደ ሄሊኮፕተር በቆሙበት ወደ መብረር የሚችሉ እና በዛው መልክ ማረፍ የሚችሉ Aircraftቶችን ለመሸጥ ስምምነት ፈረመ።

aircrafቶቹን ለመግዛት ስምምነቱን የፈረመው KakaoMobility የባለ የመጓጓዣ ካምፓኒ ሲሆን በ250 ሚሊየን የአሜሪካ ዶላር ነው ስምምነቱን ያደረጉት።

ካምፓኒው ደቡብ ኮሪያ ላይ የeVTOL ትራንፖርት አገልግሎትን መስጠት የሚጀምር ሲሆን ከ2026 ጀምሮ ለ30 ሚሊየን ለሚሆኑ ተጠቃሚዎቹ ይሄን የአየር ጉዞ ማቅረብ የሚጀምር ይሆናል።

የኮሪያ መንግስትም የከተማ ላይ የአየር ጉዞዎችን ወደ ንግድነት ከ2030 በፊት ለመጀምር ያቀደ ሲሆን አገልግሎቱ በዋና ከተማዋ Seoul ይጀመራል ተብሎ ይጠበቃል።

በነገራችን ላይ Archer በተባለው የVTOL ካምፓኒ ላይ Stellantis ፣ American Airlines እና Boeing ኢንቨስት አድርገውበታል።

#Archer #VTOL-Aircraft
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ዜና

Jeep የመጀመሪያ ኤሌክትሪክ መኪናውን ለአሜሪካ ገበያ አቀረበ።


የ2024 Jeep Wagoneer S የብራንዱ የመጀመሪያ ኤሌክትሪክ መኪና ሲሆን በመጀመሪያም የቀረበው በአሜሪካ እና በካናዳ ገበያ ላይ ነው።

ይህ መኪና Four wheel drive ሲሆን 600 የፈረስ ጉልበት እና 836 Nm torque ይኖረዋል። በዚህም አቅርቦቱ ከ0 ወደ 100 ኪሎሜትር በሰአት በ3.4 ሴኮንድ መድረስ እንደሚችል እና በ አንድ ቻርጅ እስከ 482 ኪሎሜትር እንደሚሄድ ተነግሯል።

Jeep ብራንድ የራሱ የሆነ ያለመንሸራተት ቴክኖሎጂ ያስገባበት ሲሆን በ Auto, sport, Eco, Snow እና sand በማንኛውም አየር ሁኔታ እና መንገድ ላይ መነዳት እንደሚችል አሳውቋል።

በስታንዳርድ ቨርዥኑ ካሉት ፊቸሮች መካከል 20 inch ጎማ 45 inch ስክሪን እና Panoramic sunroof ወጣ ብለው የሚታዩት ገፅታዎቹ ናቸው።

የዚህ መኪና ዋጋ ከ 72,000 የአሜሪካን ዶላር የሚጀምር ሲሆን በ2024 የመጀመሪያ ግማሽ አመት ላይ የJeep መሸጫዎች ውስጥ ይገኛል።

#Jeep #Wagoneer_S
@OnlyAboutCarsEthiopia
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
#Ad

Yango pro ላይ በቀን በትንሹ ለ 5 ሰአታት በመስመር ላይ በመሆን እና የሚመጣውን ጥሪዎች ተቀብሎ በማጠናቀቅ በትንሹ በየሳምንቱ የተረጋገጠ 10,000 ብር ማግኘት እንደሚችሉ ያውቃሉ?

አሽከርካሪዎች አፑን ለመጫን ከስር ያለውን ሊንክ ይጫኑ
bit.ly/4bEE8m8

ተጨማሪ መረጃ ለማግኘት የቴሌግራም ገፃቸው
https://www.tg-me.com/YangoETH

እንዲሁም የፌስቡክ ገፃቸው
https://www.facebook.com/groups/1171500204006823

#Yango_pro #Earnings #Driving
ነገ ግንቦት 25, 2016 የ ራሊ የመኪና ውድድር ይካሄዳል

ቦታው - ገላን ኮንዶሚኒየም ፊት ለፊት ነው የሚሆነው ::

መታሰቢያነቱ ከዚህ በፊት ተወዳዳሪ ለነበረው ጆርጅ ፓውሎ ነው ::

ነገ እዛው እንገናኝ

#CarRace #Ethiopia
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ዜና

DS የሽያጭ ሰልፉ ላይ ጥይት የማይበሳው መኪና አስገባ።


DS በሚባል የሚታወቀው የፈረንሳይ አምራች DS 7 Elysee ያሳየውን ተቀባይነት በመደገፍ እና DS 7 E-Tense 4x4 300ን መሰረት በማድረግ  DS 7 Vauban የተባለ Armored plug-in ሀይብሪድ መኪና ለገበያው አቅርቧል።

ይህ መኪና የሚመረተው ፈረንሳይ ውስጥ ሲሆን ከDS 7 E-Tense 4x4 300 ወደ DS 7 Vauban የሚለወጠው Herimoncourt የምትባል ከማምረቻው 100 ኪሎሜትር ርቀት ውስጥ የምትገኝ ከተማ ውስጥ ነው።

ክብደቱ በጣም እንዳይጨምር በማድረግ እና የተገጠመለት Armor (ጥይት እንዳይበሳው) ለይቶ እንዳይታይ የተደረገ በመሆኑ ከተመሰረተበት DS 7 E-Tense 4x4 300 መኪና ለመለየት ይከብዳል ።

#DS #7_Vauban
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ዜና

Renault group እና Geely “HORSE powertrain limited” የተባለ የቴክኖሎጂ ኩባንያ መፍጠራቸውን አሳውቀዋል


July 11, 2023 በተፈረመው ስምምነት መሰረት HORSE powertrain limited May 31, 2024 በRenault group እና Geely ግማሽ ግማሽ ባለቤትነት ተፈጠረ።

አዲሱ ኩባንያ ገበያ ላይ የhybrid እና የነዳጅ መኪና እቃ እና አገልግሎት እንደሚሰጥ ተናግሯል።

Matias Giannini CEO ሲሆኑ የBoard ዳይሬክተር ደግሞ Daniel Li በመሆን ተሹመዋል።

ይህ ኩባንያ 15ቢልዮን ዩሮ ገቢ እንደሚኖረው እና 5ሚልዮን የሀይል አስተላላፊ ክፍል ለገበያ እንደሚያቀርብ ተገምቷል። 

ኩባንያው ከመጀመሪያው ቀን ጀምሮ ከሚያቀርበው የHybrid system፣ የነዳጅ ሞተር፣ የTransmission system እና የባትሪ መፍትሄዎችን ያጠናቀቀ ፖርትፎሊዮ ይኖረዋል።

#Geely #Renault_group #horsepower_powertrain_limited
#ዜና

የFord ምርት የሆነው የኤሌክትሪኩ F-150 lightning መኪና Demonstrator በPikes peak ላይ እንደሚወዳደር ተገለፀ።


መኪናውን የሚነዳው የPikes peak ሪከርድ የያዘው Romain Dumas ሲሆን ውድድሩ የሚካሄደው June 23, 2024 እንደሚሆን ተነግሯል።

ይህ መኪና በF-150 Lightning ላይ የተመሰረተ ሲሆን ከSTARD ጋር በመተባበር የተሰራ ሲሆን እስከ 1400 የፈረስጉልበት ይኖረዋል።

በተጨማሪም የመኪናው Aerodynamics 241 ኪሎሜትር በሰአት በሚሄድበት ጊዜ 2721 ኪሎግራም ጭነት በሚያክል ሀይል መኪናውን በመጫን የተሻለ Grip እንዲኖረው ያደርጋል።

ከውድድሩ በተጨማሪ መኪናው በሚያሳየው ጥራት እና ድክመት ላይ ተመስርቶ ለገበያው የሚቀርበው መኪና ላይ ማሻሻያ እደሚደረግ ተነግሯል።

#Ford #F-150_lightning
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ዜና

Hyundai Ioniq 5 N የተባለው ኤሌክትሪክ መኪናውን ለ Pikes peak ውድድር አቀረበ።


በውድድሩ ላይ ለገበያ የቀረበውን Ionic 5 N እና  በጣም ሞዲፋይ የተደረገውን Time Attack Spec Ionic 5 N ይዛ ቀርቧል።

ይህ መኪና ከተደረገለት Aerodynamic ቦዲ በተጨማሪ ከኖርማሉ Ionic 5 N በ37 የፈረስጉልነት በመብለጥ አጠቃላይ ጉልበቱን ወደ 685 የፈረስጉልበት ሊጨምረው ችሏል።   

በተጨማሪም በዝሁ መኪና ወደ Nurburgring በመመለስ የTCR ክፍል ውድድሩን ለ4ተኛ ጊዜ ለማሸነፍ አቅደዋል።

#Hyundai #Ioniq5
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ዜና

Ford በ2 አመት ውስጥ ሹፌሮች መንገዱን ሳያዩ መንዳት እንደሚችሉ ተናገረ።


የFord CEO Jim Farley ሹፌሮች እጃቸውን ከመሪ ላይ አንስተው አይናቸውንም መንገድ ላይ ሳያደርጉ መንዳት የሚቻል መሆኑን ተናገሩ።

አላማው መኪናን ተንቀሳቃሽ ቢሮ ለማድረግ ሲሆን የዋጋ መቀነስ ጉዳይ ሆኖ እንጂ ይህ ቴክኖሎጂ አሁንም ያለ ነው ሲሉ ተናግረዋል።

መኪኖቹ እንደዚህ ሆነው እስከ 130 ኪሎሜትር በሰአት መነዳት የሚችሉ ቢሆንም በዚህ ፍጥነት ለመንዳት የአየር እና የመንገዱ ሁኔታ በጣም ጥሩ መሆን አለበት።

Ford በአሁኑ ጊዜ የሚጠቀመውን Blue Cruise system በወር 75 የአሜሪካን ዶላር በመክፈል ወይም በ 3 አመት 2100 የአሜሪካን ዶላር በመክፈል መጠቀም ሲቻል ለአዲሱ ሲስተም እንደጨመሩ እና እንዳልጨመሩ አልተናገሩም ።

ይህ ሲስተም ወደ ገበያው እስከ 2026 እንደሚቀርብ ተገምቷል ።

#Ford #Autonomous
@OnlyAboutCarsEthiopia
ከ TOYOTA BZ4X የተሻለ ኤሌክትሪክ መኪና ነው?

2024 Nissan Ariya

ይሄ የመጀመሪያው የኒሳን ኤሌክትሪክ SUV መኪና ሲሆን በጣም እንዳሻሻሉት የምታውቁት ከውጪ እንዳያችሁት ነው :: ዲዛይኑ ከ Concept ጋር በጣም ተመሳሳይ ነው :: ለዛም ነው የጃፓን የወደፊት መኪና የሚል ስያሜን የሰጡት :: ታድያ ውስጡ እና ምን የተለየ ፊቸር አለው? ከ Toyota BZ4X ጋር እያወዳደርን እናያለን :: ምን የተሻለ ነገር አለው? የሚሉትን ነገሮች በዛሬው የዩትዩብ ቪድዮ እናያለን :: ተመልሻለሁ ማየት የምትፈልጉትን መኪና በኮሜንት ላይ አሳውቁኝ
የቪድዮውን ሊንክ ከስር ታገኛላችሁ
👇🏽👇🏽👇🏽👇🏽

https://youtu.be/H60jr1P0pmE

መኪኖቹን ማየት እና መግዛት ከፈለጋችሁ
Afrolink Motors ሾው ሩማቸው ጎራ በማለት መመልከት ትችላላችሁ :: ስለ መኪኖች ማወቅ አለባችሁ የምንላቸውን ቪዲዮዎች እኛው ራሳችን ስለምንለቅ የቴሌግራም ቻናላቸውን ፎሎ ማድረግ እዳትረሱ ::
👇🏽👇🏽👇🏽👇🏽

@afrolinkmotors

መኪና መሸጥ እና ማከራየት የምትፈልጉ ሁሌመኪና ላይ 300 ብር ብቻ በመክፈል ማስተዋወቅ እና መሸጥ/ማከራየት ትችላላችሁ ::
👇🏽👇🏽👇🏽👇🏽

@hulemekina

ድንቅ ምሽት ተመኘን
#Nissan #Electric
#Afrolinkmotors #Hulemekina
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ዜና

Toyota ለሙከራ ካዋላቸው 7 የመንግስት ስታንዳርድ የማያሟሉ ሞዴሎቹን መለሰ።


Toyota ከሚለቃቸው ሞዴሎች ውስጥ ለደህንነት የሚያሰጉ የሆኑትን 3ቱን እንደሚመለስ ገለፀ። 

እነዚህ መኪኖች የደህንነት ፍተሻ የጎደላቸው በመሆኑ ከገበያው ላይ እነዲወጡ መደረጋቸው ተነገረ።

Mazda፣ Honda ፣ Yamaha እና Suzuki እንደዚው አይነት ክስ ቀርቦባቸው እንደነበር እና የደህንነት ፈተኖቻቸውን አጭበርብረው እነደነበር የጃፓን መንገድ ትራንስፖርት ሚኒስተር አሳውቋል።

#toyota #mazda #Suzuki
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ዜና

Ford አዲሱ Explorer ሙሉ በሙሉ ኤሌክትሪክ እነደሚሆን ገለፀ።


Ford በአውሮፓ የኤሌክትሪክ መኪና ብቻ ፋብሪካው ማስመረቁ ተናገረ። ይህ ፍብሪካ 2 ቢልዮን ዶላር ያወጣ ሲሆን የመጀመሪያ መኪና የሚሆነውም አዲሱ ኤሌክትሪክ Explorer እመደሚሆን ተነግሯል።

በዚሁ አመት አዲስ የ ኤሌክትሪክ መኪና እንደሚያወጡም ተናግረዎል። አዲሱ Explore እስከ 600 ኪሎሜትር በ አንድ ቻርጅ መሄድ የሚችል ሲሆን የጀርመን እና የአሜሪካን ጥራት ያማከለ ነው።

አዲሱ ፋብሪካ ለFord ወደ ከብክለት ነፃ ወደሆኑ መኪኖችን ማምረት የሚሸጋገርበት እነደሆነ እና በሚቀጥሉት አመታት ውስጥ የተለያዩ መኪኖችን እነደሚያመርት ተናግሯል።

#Fordexproler #FordEV
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ዜና

BYD የመጀመሪያ ማከፋፈያውን በካሪቢያን ውስጥ ከፈተ።


BYD ገበያውን በማስፋት ትሪኒዳድ እና ቶቤጎ ዋና ከተማ የሆነችው ፖርት ኦፍ ስፔን ውስጥ ማከፋፈያውን ከፈተ።

በአመቱ ምርቃቱ ላይ BYD Atto 3, Seal, Dolphin እና E6 የተባሉ ሞዴሎች አሳይቷል።
በተጨማሪም አዲሱ BYD Shark የተባለውን ሀይብሪድ ፒካፕ መኪናቸውን አሳይተዋል።

BYD ከATL አውቶሞቲቭ ግሩፕ ጋር በመተባበር  
ማከፋፈያዎቹን በጀማይካ፣ ባርቤዶስ እና በኬማን ደሴቶች ውስጥ እስከ አመቱ መጨረሻ እደሚከፍት ተናገረ። 

ከዚህ በተጨማሪ በብራዚል ውስጥ አንደኛ ኤሌክትሪክ አከፋፋይ መሆኑ እና በርካታ እንደ ቺሌ፣ባሊቪያ እና ኮሎምቢያ የመሳሰሉት የደቡብ አሜሪካ ሀገራት ውስጥ BYD በስፋት እየተሸጠ መሆኑን ጥናቶች አመላክተዎል።

#BYD #BYDShark #Caribbean
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ዜና

Volvo አዲስ ኤሌክትሪክ SUV ማምረት መጀመሩን ተናገረ።


Volvo EX90 የተባለ አዲስ ገበያውን የሚፎካከር ኤሌክትሪክ SUV ምርት ጀመረ። ይህ መኪና ምርት የጀመረው South Carolina ሲሆን የመጀመሪያ ደንበኞቹ በዚህ አመት መጨረሻ ላይ መኪናቸውን እነደሚረከቡ ተገምቷል።

የVolvo ዋና ስራ አስኪያጅ Jim Rowan ይህ መኪና ፖርትፎልዮአችንን ከማስፋት በተጨማሪ ለኩባንያችን የለውጥ አርማ ነው ሲሉ ተናግለዋል። 

አዲሱ EX90 የተለያዩ የሴንሰር አይነቶች ሲኖሩት በርካታ የደህንነት ሲስተሞች የተገጠመለት ሲሆን በአንድ ቻርጅ እስከ 600 ኪሎሜትር መሄድ የሚችል ነው።

#Volvo #EX90 #EV
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ዜና

Volkswagen 4 አዲስ የ ID.7 ሞዴሎች አቀረበ።


Volkswagen የID.7 GTX፣ ID.7 GTX Tourer፣ ID.7 PRO S እና ID.7 Tourer Pro S ሽያጭ እንደአማራጭ በመጨመር የሞዴሎች ጥራት እያሻሻለ ነው።

ሁሉም አዳዲስ ሞዴሎች ከተለመደው 77kWh ባትሪ ወደ 86kWh አሳድጟቸዋል :: ID.7 GTX Tourer ፍጥነት መጨመር ላይ ያተኮረ ሲሆን ከ0-100 ኪሎሜትር በሰአት በ 5.4 ሴኮንድ ይደርሳል።  

ID.7 Pro S ደግሞ ርቀት መጨመር ላይ ያተኮረ በመሆኑ በአንድ ቻርጅ እስከ 709 ኪሎሜትር መሄድ ይችላል።

እነዚህ ሞዴሎች ለገበያው የቀረቡት በትላንትናው እለት ወይም June 6, 2024 ላይ ሲሆን ከ 58,985 ዩሮ ተነስቶ እስከ 63,955 ዩሮ በጀርመን ገበያ ላይ ሽያጭ ጀምሯል።

#volkswagen #ID7 #EV
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ዜና

BMW አዲሱን 1 Series ለገበያ ለማቅረብ ዝግጅቱን አጠናቀቀ።


ቻንሲ በማሻሻል የBMW መኪናቸውን ከገበያው ላይ በጣም ተፎካካሪ ከሚባሉት ውስጥ አድርገዋል።

አዲሱ BMW 1 Series ነዳጅ ቆጣቢ ሞተር እና 48 volt ማይልድ ሀይብሪድ የሚጠቀም እና ሪሳይክል የተደረገ ማቴሪያል የሚጠቀም ነው።

በተጨማሪም የBMW አዲሱን የiDrive ሲስተም እና Quick-select ፊቸሮች ሲኖሩት የሚጠቀመውም BMW Operating System 9 ነው። 

ይህ መኪና ለብራንዱ የ20 የስኬት አመታት አዲስ ምእራፍ እንደሚሆን እና በLeipzig ፋብሪካም አዳዲስ ሞዴሎችን BMW እንደሚያስተዋውቅ ተናግሯል።

መኪናው በዚህ አመት መጨረሻ ወደ October አካባቢ በዋነኛው የጀርመን ገበያ ላይ ይቀርባል።

#BMW #BMW1Series  #BMWGroup
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ዜና

Toyota የCrown ሞዴሉን በCrown Signia አስፋፋው።


አዲሱ Crown በXLE እና በLimited Grade ሀያብሪድ ሆኖ በ All wheel-drive አማራጭ የቀረበ ነው።

በሊትር 16.15 ኪሎሜትር መሄድ ሲችል 240 የፈረስ ጉልበትም ይኖረዋል። በተጨማሪም 21 ኢነች ጎማ እና 2 ሜትር የሚሆን የካርጎ ቦታ ይኖረዋል።

ለፀጥታ ሲባል ውስጡ የተገጠመለት ሲስተም ሲኖረው ሌዘር መቀመጫና የወንበር ማሞቂያ ስታንዳርድ ሆኖ ይቀረባል።

12.5 ኢንች የስፒከር እና የመልቲሚድያ ሲስተም የተገጠመለት እና የToyotaን ሴፍቲ ሴንስ 3.0 ከPanoramic Sunroof ጋር በማሟላት ቀረቧል።

#Toyota #ToyotaCrown #Hybrid
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ዜና

ZF LifeTech አዲስ የኤር ባግ ሲስተም ፈጠረ።


ZF ተብሎ የሚታወቀው ኩባንያ ስሙን ወደ ZF LifeTech ቀይሮ አዲስ የኤረ ባግ ሲስተም ለመኪና አምራቾች ማቅረብ ጀመረ።

ZF LifeTech በተለምዶ በመሪ መሀል ላይ የነበረውን የኤር ባግ ደህንነት ሲስተም መሪው ላይ በማድረግ የፈጠረውን ሲስተም አቀረበ።

የህ የሲስተም ለውጥ ለአምራቾች ደህንነትን ሳይቀንሱ የተሻለ የዲዛይን ነፃነት እነዲኖራቸው የተደረገ ነው።

በዝህ ሲስተም የመሪው መሀል እንደ ሬድዮ፣ መስኮቶችን እና AC የመሳሰሉትን ነገሮች መቆጣጠሪያ ቦታ መደረግ የሚቻል መሆኑን ZF LifeTech ተናግሯል። 

#ZF #ZFLifeTech #Airbag
@OnlyAboutCarsEthiopia
#ዜና

SAIC-GM እራሱን በራሱ የሚነዳ መኪና መፈተኛ ፕላትፎረም ለቀቀ።


RoboTest በሚባል የተሰየመው አዲሱ የመፈተኛ ፕላትፎርም ጥራትን ከጉድለት በጥንቃቄ እና በፍጥነት ለይቶ መሻሻልና መቀየር ያበትን በቀላሉ አቅርቦ ያሳያል።

የህ ፕላትፎርም በጥንቃቄ በመስራቱ እራስን በራስ ለሚነዱ መኪኖች አካባቢን ለመረዳት የሚያስፈልጋቸውን ራዳር፣ ካሜራ፣ ሴንሰር እና የመሳሰሉትን ሲስተሞች ያሟላ ነው።

ፕላትፎረሙ ለመንገድ ላይ ደህንነት ካለው ጥቅም በተጨማሪ ለሪሰርች እና ማሻሻል የሚወስደውን ጊዜ በጣም ይቀንሳል።

ከዚያም በተረፈ በSAIC-GM 100% ሞዴሎች ላይ እነደሚሰራ ተነግሯል።

#SAIC #GM #autonomousdriving
@OnlyAboutCarsEthiopia
2024/06/09 11:45:25
Back to Top
HTML Embed Code: