Telegram Web Link
Oromoo Protests
Photo
ው ተከሳሾች ድርጊት በዝርዝር ሲገልጹ በተጠቀሱት የህግ ድንጋጌዎች ወንጀል ብሎ የወንጀል ተግባሩን የሚያቋቁሙ የተለዩ ድርጊቶች/specific elements) በክሶቹ ውስጥ የተገለጹበት ዝርዝር ሁኔታ ሲታይ፤
"…ተከሳሾች የመንግስት ሕጋዊ የስልጣን ዘመን መስከረም 30/2013 ስለሚያበቃ መንግስት ሆኖ መቀጠል አይችልም፤ በነፍጠኛ ሥርዓት መተዳደር አይገባም፤ የነፍጠኛ ሥርዓት በፊትም አሁንም እየጨረሰን ነው፤ የፀጥታ ሃይሎች ሕብረተሰቡን ማሰቃየት የለባቸውም፤ ብልፅግና የኦሮሞ ልጆችን እያሳደደ እየገደለ ነው፤ የኦሮሞ ሕዝብ የአገር ባለቤትነት መረጋገጥ አለበት፤ የሚኒሊክ ሀውልት መፍረስ አለበት፤ የአሁኑን መንግስት ታግለን ማስወገድ አለብን በማለት የተለያዩ የመገናኛ ብዙሀን እና የማህበራዊ ትስስር ድህረገፆችን በመጠቀም ህብረተሰቡ ወደ አመጽ እንዲገባ በመቀስቀስ ወይም በማነሳሳት ባነሳሱት የእርስ በርስ ግጭት በአዲስ አበባ እና በኦሮሚያ የተለያዩ ዞኖችና ከተሞች በሰዉ ህይወትና አካል እና በመንግስት እና በግል ንብረት ላይ ጉዳት እንዲደርስ አድርጓል…" የሚል ነዉ፡፡
ሆኖም ግን አብዛኞቹ ተከሳሾች እንደ ፖለቲካ አመራርነታቸው ለነፍጠኛ ስርዓት አንገዛም፤ ነፍጠኛ ነው የኦሮሞን ህዝብ ሲጨርስ የነበረዉ ማለት ፕሮግራሞቻቸውንና ሃሳባቸዉን ለህዝብ በማቅረብ ህዝብ እንዲመርጣቸው (ሃሳባቸውን መራጩ ህዝብ እንዲገዛቸዉ) ከመቀስቀስ ዉጪ ምንም ዓይነት የወንጀል ድርጊት ተብሎ በህጉ የተጠቀሰውን ድንጋጌ መተላለፋቸውን አያሳይም፡፡ ድርጊቱ ወንጀል ነው ተብሎ በአንቀጽ 240 ስር የተደነገገዉን ሊያቋቁም አይችልም፡፡ ንግግራቸውም በማን እና በማን መካከል የእርስ በርስ ጦርነት እንዳስነሳና የእርስ በርስ ጦርነት መነሳቱንም በክሳቸዉ አላሳዩም፡፡ የእርስ በርስ ጦርነት ትርጉም ምን እንደሆነ አልተገለጸም፡፡ ትርጉሙን ወይም የቃሉን ፍቺ የሚበይነው፤ ከግጭቶችና ሌሎች ጦርነቶች መለያው ምንድነው የሚሉትን ክሱ አያስረዳም፡፡ የትኛዉ ብሄር በየትኛው ብሄር፣ የትኛው የፖለቲካ ፓርቲ በየትኛው ፖለቲካ ፓርቲ እንዲሁም የትኛው ሃይማኖት በየትኛው ሃይማኖት ላይ የእርስ በርስ ጦርነት እንዳስነሳና የእርስ በርስ ጦርነቱም በምክንያትና ውጤት ቁርኝት የትኛዉ ተከሳሽ ምን በመናገሩ የእርስ በርስ ጦርነት እንደተቀሰቀሰ የሚያሳይ የወንጀል ድርጊቱ በዝርዝር ባለመገለጹ ተከሳሾች ራሳቸውን ለመከላከል የሚቸገሩና ምንም ዓይነት የወንጀል ድርጊት ስለመፈጸሙ በክሱ ያልተገለጸ በመሆኑ ክሱ ውድቅ ሊሆን ይገባዋል፡፡ ተከሳሾች ከላይ የተገለጹትን ንግግሮች ካደረጉ በኋላ ከአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ ግዲያ በፊት ብዙ የአሮሞ ብሔር ተወላጆች በኦሮሚያ ክልል በመንግስት ታጣቂዎች መገደላቸው ሀሰት ስለመሆኑ የተገለጸ ነገር ካለመኖሩም በላይ የተከሳሾች ንግግር ህዝብን የሚያነሳሳ ከሆነ በዚያን ጊዜ ለምን ህዝቡ ሆ ብሎ ለአመጽ አልተነሳም፤ መንግስትስ ለምን በዚያን ጊዜ በተከሳሾቹ ላይ ክስ አልመሰረተም የሚለው ሲታይ የተከሳሾቹ ንግግር የወንጀል ዲርጊት አለመሆኑንና የፓርቲ አመራር የሆኑት ተከሳሾች በምርጫ እንዳይሳተፉ ሆን ተብሎ የቀረበባቸዉ ክስ መሆኑን መረዳት አያዳግትም፡፡ ተከሳሾች የተናገሩት፤የጻፉት ሁሉ ባይኖር ኖሮ ከአርቲስት ሃጫሉ ግድያ በኋላ አሁን የተፈጠረው የህዝብ ቁጣ እንደማይደርስ እንዴት እንደታወቀ አልተገለጸም፡፡
በክሱ የተጠቀሰውን የተወሰኑ ተከሳሾች ፈጸሙት ስለተባለው ድርጊትና ስለተፈጸመው ጉዳይ በተመለከተ ለምሣሌ፤ ከመስከረም 2012 ዓ.ም ጀምሮ ለተባለው ድርጊት አንድ አመት አስቀድመው ለጻፉትና ለተናገሩት ከአንድ ዓመት በኋላ በንግግራቸው ምክንያት የእርስ በርስ ጦርነት ተነሳ የተባለው የምክንያት እና የውጤት ምንም ዓይነት ቁርኝት የለውም፡፡
የኢ-ሜይል ወይም የፌስቡክ ግንኙነት ተከሳሾች እንዲደረግ የሚፈልጉት ወንጀል እንዲያደርጉ ጉትጎታ የተደረገበት፤ተስፋ የተገባለት፤ የገንዘብ ስጦታ የተሰጠው፤ በማስፈራራት ወይም ሌላ ተመሳሳይ ዘዴ ወንጀል እንዲፈፅም ያግባባ ሰው ስለመኖሩ የተገለጸ ነገር የለም፡፡ በመሆኑም ተከሳሾች የፈፀሙት የማነሳሳት ተግባር የለም፡፡ በክሱ ዝርዝር ውስጥ እንደተገለፀዉ ተቀስቃሹ ሕዝብ ስለሆነ የማነሳሳት ወንጀል በማሳመን፤ በማግባባት እና በመጎትጎት የሚፈጸም በመሆኑ ሌሎች ተለይተዉ የታወቁ ወንጀል አድራጊዎች በሌሉበት ሁኔታ ማነሳሳት አለ ለማለት ፈፅሞ አይቻልም፡፡ ለመሆኑ ተከሳሾች አንድም ብሄር/ህዝብ በአማራ ብሔር ላይ ጫና እንዲፈጥር ስለመናገራቸው ወይም መጻፋቸው በክሱ ውስጥ ሳይገለጽ ነፍጠኛ የሚለው ቃል ከአማራ ህዝብ እና ከኦርቶዶክስ ሀይማኖት ተከታዮች ጋር እንዴት እንደተገናኘም ግልጽ ካለመሆኑም በላይ የወንጀል ድርጊት አይደለም፡፡
በተከሳሾች ላይ የቀረበው ክስ የወንጀል ዝርዝር የአለም አቀፍ የሰብአዊ መብቶች ድንጋጌዎች በሚያስቀምጡት መስፈርቶች መሠረት ተከሳሾች ህብረተሰቡን ለሁከትና ለብጥብጥ የማነሳሳት ተግባር ስለመፈፀማቸዉ የሚያሳዩ አይደሉም፡፡ በአለም አቀፍ የሲቪልና የፖለቲካ መብቶች ቃልኪዳን አንቀጽ 19(2) መሠረት ማንም ሰው ያለማንም ጣልቃ ገብነት ሃሳቡን የመግለፅ መብት አለው፡፡ ይህም በዚሁ ድንጋጌ አንቀጽ 19(3) ሥር እንደተጠቀሰው የሌላ ሰው መብት ፤ የአገር ሰላምና ደህንነት የሚነካ ካልሆነ ወሰን ሳይደረግበት በቃልም ሆነ በፅሑፍ ወይም በህትመት፤ ወይም በሥነ ጥበብ መልክ ወይም በመረጠዉ በማንኛውም የማሰራጫ ዘዴ ማንኛውንም ሃሳብና መረጃ የመሰብሰብ፤ የመቀበልና የማሰራጨት መብት አለዉ፡፡
ሃሳብን በነፃነት የመግለፅ መብት በኢ.ፌ.ዴ.ሪ ሕገ መንግስት አንቀጽ 29 እና በሲቪልና የፖለቲካ መብቶች ቃልኪዳን አንቀጽ 19 (1-2) ሥር ተደንግጓል፡፡ ይህ መብት በአስተሳሰባዊ ይዘቱና ሊያስከትል በሚችለዉ አስተሳሰባዊ ውጤት ሊገታ እንደማይገባ በሕገ መንግስቱ አንቀጽ 29(6) ሥር ተደንግጓል፡፡ በአለም አቀፍ የሲቪልና የፖለቲካ መብቶች ቃልኪዳን አንቀጽ 20(2) መሠረት ለሁከትና ለብጥብጥ የሚያነሳሳ ከሆነ ግን የተከለከለ ነዉ፡፡ በመሆኑም አንቀጽ 19 በዲሞክራሲያዊ ማህበረሰብ ውስጥ ሊታገሱ የሚገቡ እና ሊታገሱ የማይገቡ እና በአንቀጽ 20 ክልከላ ውስጥ የሚወድቁ ሃሳብ በነፃነት ከመግለፅ መብት ያለፉ ናቸዉ ሊባሉ የሚገቡትን ፍ/ቤቶችና ሌሎች አካላት ሊከተሉ የሚገባቸውን እስታንደርድ አስቀምጧል፡፡ ይህም የተባበሩት መንግስታት የሰብአዊ መብት ኮሚቴ (HR Committee) ዓለም አቀፍ የሲቪልና የፖለቲካ መብቶች ቃልኪዳን አንቀጽ 20(2) ዓለም አቀፍ እስታንደርድ አንጻር ሊተረጎም እና ሥራ ላይ መዋል የሚገባበትን የመፍትሔ ሃሳብ (Recommendation for interpreting Article 20(2) of the ICCPR) በተራ ቁ. 8 ሥር ለሁከትና ለብጥብጥ የማነሳሳት ተግባር አለ ለማለት የሚቻልባቸውን መስፈርቶች (standards of Incitement for violence) አስቀምጧል፡፡ ኢትዮጵያ ዓለም አቀፍ የሲቪልና የፖለቲካ መብቶች ቃልኪዳን ተቀብላ አፅድቃለች፡ በመሆኑም በሕገ መንግስቱ አንቀፅ 9(4) መሠረት የሀገሪቱ ሕግ አካል ነው፡፡ ተከሳሾቹ ተናግረዋል ወይም ፅፈዋል፤ ለተለያዩ ሚዲያዎች ሰጥተዋል የተባሉት ቃለ ምልልሶችና ንግግሮች በአጭሩ ከላይ የተገለፁት ናቸው።
ለሁከትና ለብጥብጥ የማነሳሳት ተግባር አለ ለማለት የሰብአዊ መብት ኮሚቴዉ የመጀመሪያው መስፈርት ሁከትና ብጥብጥ የማነሳሳት ፍላጎት ወይም ሃሳብ (Intent to incite violence) መኖር ነው፡፡ እንደ ኮሚቴው ተናጋሪው ወይም ፀሃፊው የተጠቀመዉ ቋንቋ
Oromoo Protests
Photo
ግልፅና ቀጥተኛ የሁከት ጥሪ ሲሆን ሁከትና ብጥብጥ ከማነሳሳት ሌላ ሃሳብ የሌለዉ መሆኑን ያሳያል፡፡ ሌላው የተናጋሪው ወይም ፀሃፊው ዓላማ (Objectives pursued) ነዉ፡፡ እንዲናገር ወይም እንዲፅፍ ያስገደደዉ ነገር ነው፡፡ የተናጋሪው ወይም ፀሃፊው ሃሳብ በጥቅሉ (as a whole) ሲመረመር ዋና አላማው ሁከትና ብጥብጥ ማስፋፋት ከሆነ (propagation of violence) የማነሳሳት ሃሳብ እንዳለዉ ይቆጠራል፡፡ ተናጋሪው ወይም ፀሐፊው ሌላ የተለየ አላማ አለው ከተባለ ማነሳሳት አይሆንም፡፡ አጠቃላይ የሕዝብን ጥቅም በሚመለከት ሕብረተሰቡን ለማሳወቅ የሚሰራጨዉ ዜና፤ የታሪክ ጥናት እና ለሕዝብ ጥቅም ሲባል ተጠያቅነትን ለማስፈን የመንግስት መጥፎ ሥራዎችን ለማጋለጥ ከሆነ ማነሳሳት አይሆንም፡፡ እንደ ኮሚቴው የመፍትሔ ሃሳብ የግንኙነቱ እርክን (ደረጃ) ድግግሞሽ (scale and repetition) መታየት አለበት፡፡ ለረጅም ጊዜና ብዙ ጊዜ ከሆነ (repeated over time or on several occasions) የማነሳሳት ሃሳብን ያመለክታል፡፡ በክሱ ውስጥ ሰኔ 23 ቀን 2012 ዓ.ም በአርቲስት ሃጫሉ ሁንዴሳ ላይ ግድያ እንደሚፈጸም ተከሳሾች አስቀድመው ስለማወቃቸው የተገለጸ ነገር የለም፡፡ በዚህ ቀንም አንዱ ብሔር በሌላው ላይ ወይም አንዱ ሃይማኖት በኦርቶዶክስ ሀይማኖት ተከታዮች ላይ ወይም በመግስት ላይ የእርስ በርስ ጦርነት እንዲነሳ ስለማድረጋቸው በግልጽ አልተገለጸም፡፡ የሚኒሊክ ሃውልት ተብሎ እንኳን ቢሆን ይህንን ሀውልት ማፍረስንና በአማራ ህዝብ ላይ ወይም በኦርቶዶክስ ሀይማኖት ተከታዮች ላይ ወይም በመንግስት ላይ እንደት ጦርነት መቀስቀስ እንደሚሆን በግልጽ በክሱ ወስጥ አልሰፈረም፡፡ በሌሎች አገሮች ለምሳሌ በእንግሊዝ አገር፤ በአሜሪካ እና ሌሎች አገሮች በመንግስት ቸልተኝነት ወይም ጸጥታ ሀይሎች በፈጸሙት በደሎች ህዝቡ ቁጣውን አሰምቶ የዲሞኪራሲ እና የእኩልነት ተምሳሌት ያልሆኑ ሃውልቶች ሲፈርሱ የእርስ በርስ ጦርነት ነው ተብሎ ክስ አልቀረበም፡፡ የሚኒልክ ሀውልትም የዴሞኪራሲና እና የእኩልነት ተምሳሌት እንዳልሆነ ከፍተኛ የመንግስት አመራሮች በአደባባይ እየተናገሩ ተከሳሾች ሀውልቱ ይፍረስ ብለው ቢሆን እንኳን እንዴት ወንጀል እንደሚሆን ግልጽ አይደለም፡፡
የሁሉም የክሶች ይዘት ስናይ ተከሳሾች በግልፅ እና በቀጥታ ለሁከትና ለብጥብጥ ያደረጉት ጥሪ የለም፡፡ ተከሳሾች ተናግረዋል የተባሉትን ነገሮች በጥቅሉ ስናይ ከመስከረም 30 በኋላ በስልጣን ላይ ያለው መንግስት ሕጋዊ ስልጣን አይኖረውም የሚለው የሕገ መንግስቱ ቃል ነው። ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከማንም ቀድመው በግልፅ የተናገሩት ነው። ሕጋዊ ስልጣን ቢኖረው ኖሮ ወደ ሕገ መንግስት ትርጉም ባልተገባ ነበር። የሽግግር ጥያቄውም ቢሆን የ40 ዓመት ዕድሜ ያለው ጉዳይ ነው። በመሆኑም ሃሳቦቹ የሕዝብን መብት ለማስከበር ጥያቄ የመጠየቅ አላማ ያላቸዉ ናቸው እንጂ ሁከትና ብጥብጥ ለመቀስቀስ የተደረጉ መሆናቸውን አያመለክቱም፡፡ የመንግስትን ፖሊሲዎችንና እስትራቴጂዎችን የመቃወም፤ የመተቸት ሕገ መንግስታዊ እና ዲሞክራሲያዊ መብት እንጂ በምንም መልኩ ለወንጀል ተግባር ሕዝብን ማነሳሳት ተግባር አይሆንም፡፡ የኢትዮጵያ መንግስት የሕዝቡን ተቃውሞ በአግባቡ ማስተናገድ አልቻለም፤ እንዲሁም አገሪቱን በአግባቡ መያዝ አልቻለም በማለት መንግስትን መተቸት ወይም አስተያየት መስጠት ትክክለኛና በማንኛውም ዲሞኪራሲ ሽግግር ውስጥ ያለ እና ሊኖር የሚገባ ነዉ፡፡ የተናገሩትም ሆነ የጻፉት ነገር እንኳን ውሸት ስለመሆኑ የተጠቀሰ ነገር በለሌበት ሁኔታ እና የህዝቡ ቁጣ ገና በ22/10/2012 ዓ/ም ከክሱም ሆነ ከተከሳሾች ጋር በማይገናኝ ምክንያት በተቀሰቀሰበት ሁኔታ የተከሳሾች ጥያቄዎች በምንም መስፈርት የብሄራዊ ደህንነትና የግዛት ሉዓላዊነትን አደጋ ላይ የሚጥሉ አይደሉም፡፡ በማንኛውም መስፈርት ምንም አይነት የሃይል ተግባር የሚያበረታታም ስለመሆኑ ማሳያ ምልክት አልተገለጸም፡፡ ተከሳሾች አደረጉ የተባለው ንግግር እና ጻፉት የተባለው ጽሁፍ ለሕዝብ ጥቅም ሲባል ተጠያቅነትን ለማስፈን የመንግስት የመልካም አስተዳደር ችግሮችን ለማጋለጥ ያደረጉትን ጥረት የሚያሳዩ ካልሆነ በስተቀር ሁከትና ብጥብጥ የማነሳሳት ፍላጎት ወይም ሃሳብ (Intent to incite violence) እንዳላቸዉ የሚያስረዱ አይደሉም፡፡
ተከሰሾች መንግስት ከሕብረተሰቡና ከፖለቲካ ቡድኖች ጋር እንዲያወያይ ያቀረቡት ጥያቄና አቤቱታ ወንጀል ሳይሆን እንደ መብት በሕገ መንግስቱ ቁ. 30 ሥር ተደንግጎ የሚገኝ ነዉ፡፡ በዚህ መሠረት ማንም ኢትዮጵያዊ ሰላማዊ ሰልፍ የማድረግ እና አቤቱታ የማቅረብ መብት አለው፡፡ ተከሳሾች የሕዝብ አካል በመሆናቸዉ ከሕዝቡ ጋር በመሆን በሰላማዊና በሕጋዊ መንገድ ሕ/መንግስታዊ መብታቸውን በመጠቀም ተመሳሳይ ጥያቄ ከማቅረብ የሚያግዳቸዉ ነገር በለሌበት ሁኔታ ህጋዊና ፖለቲካዊ መብትን እንደ አዲስ ወንጀል መፍጠር ከልሆነ በስተቀር ማናቸውንም ጥያቄዎች ከሕዝቡ ጋር በመሆን መጠየቅ ሕብረተሰቡን ለየትኛዉም ወንጀል የሚያነሳሱ አይደሉም፡፡
ሌላዉ የሰብአዊ መብት ኮሚቴ መስፈርት የሃሳቡን ይዘት የሚመለከት ነው፡፡ ይህ በተጨባጭ የተባለ ወይም የተደረገ ነገርን ይመለከታል፡፡ ይህ የተባለዉ ነገር ግልፅ በሆነ እና በማያሻማ መልኩ ሁከትና ብጥብጥ እንዲፈጽሙ ለተደራሲያን የቀጥታ ጥሪ ከሆነ ማነሳሳት ነው፡፡ የተገለፀዉ ሃሳብ ቀጥታና አነሳሽ ወይም ቀስቃሽ፣ ወደ ሕገ ወጥ ድርጊት የመገፋፋት ሃይል ያለው ከሆነም ተመሳሳይ ውጤት አለዉ፡፡ ኮሚቴው ሃሳቡ የተገለፀበት ፎርምም መታየት እንዳለበት ይገልፃል፡፡ በመሆኑም እውነተኛ የሕዝብ ጥቅም ለማስከበር የሚሰነዘሩ ሂሶች በተለይም በምርጫ፤ በምርጫ ዘመቻ፤ በፖለቲካ ፓርቲዎች ክርክር ጊዜ የሚሰጡ ሃሳቦችን የሚመለከቱ ንግግሮች፤ ፅሐፎች ማነሳሳት አይሆኑም፡፡ ትምህርት ነክ ጥናቶችን የሚመለከቱ ሃሳቦች አክራሪ የሆነ አመለካከት (extreme views) ቢኖራቸውም ለሕዝብ ጥቅም ሲባል ጥበቃ ሊደረግላቸዉ ስለሚገባ ማነሳሳት ሊሆኑ አይገባም፡፡ የፍሬ ነገር መግለጫዎችና ድምዳሜዎች (Statements of facts and value judgments) መግለፅ ማነሳሳት አይሆንም፡፡ ድምዳሜዎች ግን እውነትነታቸውን በፍሬ ነገር ማስረጃ ማስረዳት የማይቻል ከሆነ ማነሳሳት ሊሆኑ እንደሚችሉ ኮሚቴዎቹ ይገልፃሉ፡፡
ጠ/ዐ/ሕግ ያቀረበው ክስ ውስጥ ተከሳሾች ተደዋውለዋል፤ ተፃፅፈዋል እና በተለያዩ ሚዲያዎች ሰጥቷል በተባሉት አስተያየቶች ውስጥ አንድም በቀጥታ እና በማያሻማ መልኩ ለሁከትና ብጥብጥ ጥሪ የማያደርግ ወይም የማያበረታታ፣ የማይቀሰቅስ እና ሰላምን የሚሰብክ እንጂ ህበረተሰቡ ሕገወጥ ድርጊቶችን እንዲያደርግ የሚገፋፋ ቃል፣ ሐረግ ወይም አረፍተነገር የለም፡፡ ከተከሳሾቹ አንዳንዶቹ በሕገ መንግስቱና አግባብነት ባለው ሕግ የተቋቋመ ኦፌኮ የሚባል የፖለቲካ ድርጅት አመራር እንደመሆናቸዉ ለሚታገሉለት ማህበረሰብ ይበጃል ብለዉ ያመኑትን ማንኛውንም ጥያቄዎች ሕገ መንግስቱን መሠረት በማድረግ ግንባር ቀደም ሆነዉ መጠየቃቸዉ ማነሳሳት አይሆንም፡፡ በመሆኑም ተከሳሾች ተናግረዋል፣ ወይም ፅፈዋል የተባሉት ሃሳቦች ይዘት የወንጀል ሀላፊነት የማያስከትሉ፤ ሕገ ወጥነታቸው በሕግ ያልተደነገገና ሕገ መንግስታዊ ጥበቃ የተደረገለት መብት በመሆኑ የተከበረው ፍ/ቤት ውድቅ እንዲያደርግልን እንጠይቃለን፡፡
ከላይ እንደተገለፀው የተ.መ.ድ የሰብአዊ መብት ኮሚቴ ለአንቀፅ 20(2) በሰጠው ትርጉም መሠረት በምርጫና በ
Oromoo Protests
Photo
ምርጫ ዘመቻ ጊዜ የሚሰጡ ሃሳቦችን የሚመለከቱ ንግግሮች፤ ፅሐፎች ማነሳሳት ስለማይሆኑ ተቀባይነት የላቸውም፡፡ በወቅቱ የተከሰቱትን ነገሮች፤ የደረሱትን የሕይወትም ሆነ የንብረት ጉዳቶችን ለተለያዩ አካላት ሪፖርት ማድረግም የፍሬ ነገር መግለጫ በመሆኑ በኮሚቴው ትርጉም መሠረት ማነሳሳት አይሆንም፡፡
ሌላው የሰብአዊ መብት ኮሚቴ ያስቀመጠው መስፈርት የሃሳብ መግለጫው መጠንና ስፋትን (Extent and Magnitude of the expression) የሚመለከት ነው፡፡ እንደ ኮሚቴው አገላለፅ በዚህ ሥር ዳኞች ሶስት ቁልፍ ጉዳዮችን ማጤን አለባቸው፡፡ እነሱም፡- 1ኛው ሃሳቡ ሰፊዉ ሕዝብ ጋር የመድረስ ባህርይ ያለው መሆኑ (public nature of the expression) የሚመለከት ነው፡፡ ንግግሩ ወይም ፅሑፉ ቀጥታ ለሰፊው ሕዝብ መደረጉ ለብዙ ሰዎች ሕዝባዊ ቦታዎች (exposed public space) ላይ ከተደረገ፣ በተወሰነ ቦታ ብቻ የሚዘዋወር (circulated in a restricted environment) ሳይሆን ለህዝቡ ተደራሽ መሆኑ (widely accessible to the general public) ይዘቱ ሃይል ካለው ሕዝቡን ማነሳሳት ይችላል፡፡
እንደኮሚቴው ኢንተርኔት፤ ፌስቡክና ኢ-ሜይል ሕዝባዊ ቦታዎች አይደሉም፡፡ 2ኛው የማሰራጫ አውታር (means of dissemination of the expression) ለሕዝብ በቀላሉ ሊደርስ በሚችሉ ዘዴዎች የተሰራጨ መሆኑን የሚመለከት ነው፡፡ 3ኛው የሃሳቡ መግለጫ ስፋት (The magnitude the expression) የሚመለከት ነው፡፡ ግንኙነቱ በመደበኛና በአጫጭር የጊዜ ልዩነቶች መደረጉ፣ ድግግሞሽ ወይም ብዛቱ፣ ሽፋን የመሳሰሉት ከግምት ውስጥ መግባት አለባቸው፡፡ የተከሳሾች የስልክ ግንኙነቶች እዚያዉ በፓርቲያቸዉ አባላት መካካል የተደረገ የሃሳብ መለዋወጥ በመሆኑ በተወሰነ ቦታ ብቻ ሲዘዋወር የነበረ በመሆኑ ለኦሮሚያ ክልል ሕዝብ ተደራሽ የሚሆንበት መንገድ አልነበረም፡፡ አንዱም ተከሳሽ በስልካቸው ያደረጉትን ለሰፊው ህዝብ ተደራሽ ሊሆን በሚችል መልኩ ማሰረጨቱን በቀረበው ክስ አልተገለጸም፡፡ በመሆኑም ለሕዝቡ ተደራሽ ነው የሚባል እንኳን ቢሆን ይህ ከሆነ ደግሞ በምንም መልኩ ሕዝቡን በመጎትጎት፣ ተስፋ በመስጠት፣ በገንዘብ፣ በስጦታ፤ በማስፈራራት ወይም በማናቸውም ሌላ ዘዴ ለአመፅና ብጥብጥ የማነሳሳት ተግባር ፈፅመዋል ሊባል አይችልም፡፡
ሌላዉ መስፈርት እንዲደረግ የተፈለገዉ ነገር የመሆን ዕድል፤ ቅርበቱን (Likelihood of the advocated action occurring, and its imminence) የሚመለከት ነው፡፡ የሃሳቡ መገለፅ እና የተደራሲያን ድርጊት መካከል የምክንያትና የውጤት ግንኙነት መኖር አለበት፡፡ ይህን ለማወቅ ተደራሲያኑ በእውነት ለሁከትና ለብጥብጥ የተደረገ ጥሪ መሆኑን መረዳታቸውን ወይም ሊረዱ የሚችሉ መሆኑን፣ መልዕክቱ ተቀባይነት የማግኘት ዕድል እና ኢላማ የተደረጉ ተጎጂዎች ስለመኖራቸው መረጋገጥ አለበት፡፡ መስፈርቱ አንድ ተራ ምክንያታዊ የሆነ ሰው የተገለፀው ነገር እሱን ለሁከትና ብጥብጥ የሚያነሳሰውና በቅርብ ጉዳት የሚደርስ መሆኑን የተረዳ ከሆነ ነው፡፡ ተከሳሾች ተናገሩ ወይም ፅፈዋል የተባሉት ሃሳቦች የወንጀል ሀላፊነት የማያስከትሉ፣ ሕገወጥነታቸው በሕግ ያልተደነገገና ሕገ- መንግስታዊ ጥበቃ የተደረገላቸው መብቶች ናቸው፡፡ በመሆኑም ተከሳሾች እንደደረግ የሚፈሉጉት የወንጀል ድርጊት የለም፡፡ ተከሳሾች ከወራት እና ከዓመት በፊት የተናገሩትን እራሳቸው የማያስታውሱት ከመሆኑም በላይ ከሃጫሉ ግዲያ ማግስት ስንቅ ሆኖ ለአመጽ ሊቀሰቅስ እንዴት እንደቻለ አልተገለጸም፡፡
በአጠቃላይ በተከሳሾች ላይ የቀረበው ክስ ይዘት በተለይም ለተለያዩ ሚዲያዎች የሰጡት ቃለ ምልልስ፣ ንግግር እና ፅሁፎች ሃሳብን በነፃነት ከመግለፅ መብት ውስጥ የሚጠቃለሉ እና የመብቱን ገደብ ያላለፉ ናቸው፡፡ አንድ ንግግር ሃሳብን በነፃነት ከመግለፅ መብት ዉጪ ሆኖ እንደ ማነሳሳት የሚቆጠረው ከላይ የተጠቀሱትን መስፈርቶች ሲያሟላ ብቻ ነዉ፡፡ ከላይ እንደተጠቀሰው የተከሳሾቹ ንግግሮችና ፅሑፎች የተጠቀሟቸዉ ቃላቶች በግልፅ የሚያነሳሱ ወይም ማነሳሳትን የሚያበረታቱ አይደሉም፡፡ በመሆኑም ተከሳሾች በግልፅ በሕግ ያላቸውን ገደብ ሳያልፉ መብታቸውን ተጠቀሙ እንጂ ያነሳሱት የወንጀል ድርጊትም የለም፡፡ በመሆኑም ተከሳሾች ለተለያዩ ሚዲያዎች የሰጡት ቃለ ምልልስ፣ ንግግር እና በፅሑፍ የተለዋወጧቸው መልዕክቶች ተከሳሾች ሃሳባቸውን በነፃነት የመግለፅ መብታቸውን ገደቡን ሳያልፉ በአግባቡ መጠቀማቸውን የሚያሳዩ እንጂ ለሁከትና ለብጥብጥ ሕዝቡን የማነሳሳት ድርጊት መፈፀማቸውን የሚያሳዩ አይደሉም፡፡
ከላይ እንደተገለፀው በክሱ ውስጥ የተገለፀው የወንጀል ዝርዝር የሚያሳየው ተከሳሾች ሕዝብን ለአመፅ አነሳስተዋል የሚል ሲሆን በአንጻሩ አመጽ ግን ጠንከር ያለ ተቃውሞ እንጂ ወንጀል አይደለም፡፡ አመጽ የሚለው የአማርኛ ቃል አሉታዊ እንድምታ ያለው ይመስላል፡፡ ተዋቂው የሕግ መዝገበ ቃላት ብላክስ ሎው ‘protest‘ ከሚለው የእንግሊዘኛ ቅጂ ጋር ይመሳሰላል፡፡ ትርጉሙም በሕግ ውስጥ እንደ መብት አንድን ነገር የመቃወምና አቤቱታ የማቅረብ ሁኔታን የሚመለከት ነው፡፡ የተለያዩ ጥያቄዎችን ይዞ ለመንግስት አቤቱታ ማቅረብ ወንጀል ሳይሆን እንደ መብት በኢ.ፌ.ዲ.ሪ ሕ/መንግስት ቁ. 30 ሥር ተደንግጎ የሚገኝ ነው፡፡ በሕገ መንግስቱ አንቀጽ 43(2) ዜጎች እነሱን የሚመለከቱ ፖሊሲዎችና እስትራቴጂዎች ላይ የመሳተፍ እና የመጠየቅ መብት በግልጽ ተደንግጎ ይገኛል፡፡ ተከሳሾች 1ኛ የሕዝብ አካል በመሆናቸው ከሕዝቡ ጋር በመሆን በሰላማዊና በሕጋዊ መንገድ ሕ/መንግስታዊ መብታቸውን በመጠቀም ተመሳሳይ ጥያቄ ከማቅረብ የሚያግዳቸው ነገር የለም፡፡ ማናቸውንም ጥያቄዎች ከሕዝቡ ጋር በመሆን መጠየቅ የየትኛውንም ሕግ ድንጋጌ የሚጥስ አይደለም፡፡ የ1996 የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የወ/ሕ/ቁ. 2 መሠረት ሕገ ወጥነቱ በሕግ ያልተደነገገ ድርጊት ወይም ግድፈት እንደ ወንጀል ተቆጥሮ ክስ ሊቀርብበት አይችልም፡፡ በመሆኑም ተከሳሾች ፈጽመዋል የተባሉት ድርጊቶች የወንጀል ሀላፊነት የማያስከትሉ፣ ሕገ ወጥነታቸው በሕግ ያልተደነገገና ሕገ መንግስታዊ ጥበቃ የተደረገለት መብት በመሆኑ ክስ ሊቀረብባቸው ስለማይገባ የተከበረዉ ፍ/ቤት በተከሳሾች ላይ የቀረበው ክስ የተከሳሾችን ሰብአዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶችን የሚጻረር ነው በማለት ሰርዞ ተከሳሾችን በነጻ እንዲያሰነብተን እንጠይቃለን፡፡
በ2ኛ ክስ ስር ከ16-24 ተራ ቁጥር ባሉት ተከሳሾች ላይ የቀረበው ክስ የወ/ህ አንቀጽ 240 ስር የተነደገጉትን የማያሟላ፣ የጸና ፈቃድ ሳይኖራቸዉ የጦር መሳሪያ መያዝ ይሁን፣ በሰው ህይወት ላይ ሞትን ማስከተል ይሁን ክሱ በወ/ህጉ ከተጠቀሰው አንቀጽ ጋር ግልጽ ሆኖ በጣም በተቀራረበ ሁኔታ ያልተገለጸና ግልጽነት የጎደለው ነው፡፡ ክሱ የወ/ህ አንቀጽ 240 ከመጥቀስ ውጪ ተከሳሾች ፈጸሙ የተባለው ድርጊት ወንጀል ከሚያደርገው የህግ ድንጋጌ ጋር ምንም ዓይነት ግንኙነት የሌለው በመሆኑ ክሱ ዉድቅ እንዲደረግልን እንጠይቃልን።
Oromoo Protests
Photo
👆👆👆👆👆👆👆👆👆👆
ከመጀመሪያው ጀምራችሁ አንብቡት። በጣም ረጅም ፅሁፍ ነው ነገር ግን በትዕግሥት አንብባችሁ ጨርሱት።

እነ ጀዋር መንግስትን የተቃወመበት 30 ገፅ pdf እለጥፍላቸዋለሁ።👇👇👇
አቶ ጥላሁን ያሚ
#Urgent

እነ ጀዋር መሃመድ የምግብ አድማ ላይ እንዳሉ ይታወቃል። ይሄው ምግብ ከቀመሱ ዛሬ ዘጠነኛ ቀናቸውን ይዘዋል። በጣም ደክሟል ፣ ከቃሊቲ እስር ቤት የሚመጡ ዜናዎች ያስፈራሉ።

the government refuses to answer their question. They let them to die.

#share #share
አሳዛኝ ነው! ትንሽ እንኳን አርቆ የሚያስብ፣ መጭውን ግዜ የሚተነብይ አንድ ፖለቲከኛ የለንም፤ ከጀዋር መሐመድ በስተቀር።

ጀዋር በመታሰሩ አንድም ያተረፈ አካል የለም። መንግስት ተጎድቷል። አገር ተጎድታለች። ከፍተኛ የሃሳብ ድርቅ አጋጥሟል።

መንግስት ይህን ሰው ቢፈታ አብዝቶ ያተርፋል። ስለዚህ እሱን ፍቱትና በጠረጴዛ ዙሪያ አውሩ። ተመካከሩ። ተደራደሩ።
ከታማኝ ምንጮች እንዳረጋገጥኩት ሁለት አምቡላንሶች በፍጥነት ወደ ቃሊቲ እስር ቤት ማለትም እን ጀዋር የታሰሩበት እስር ቤት ገብቷል።

#Share
ትናንት ጀዋር ለፍርድ ቤት ከተናገራቸው መካከል አንዱ!


"በዚህ የረሀብ አድማችን ራሳችንን ብንስት እና ህክምና የሚያስፈልገን ቢሆን እንዲያውቅልን የምንፈልገው ይህ መንግስት በሚያቀርብልን ሀኪሞች ላይ እምነት ስለሌለን የግል ሀኪሞቻችን እንዲያዩን እንዲደረግልን ነው።"
This media is not supported in your browser
VIEW IN TELEGRAM
Guutuu Abarraa!
#Hawanawa
#Amazing_Music
😍😍

Here is the link. 👇👇
Watch "Gutu Abera-Hawanawa-New Ethiopian Oromo Music 2021(Official Video)" on YouTube
https://youtu.be/z1qDanoqzzs
2024/05/16 11:33:01
Back to Top
HTML Embed Code: