Telegram Web Link
የማኅበረ ቅዱሳን ሰብሳቢ ሊቀ ትጉኅን ቀሲስ ዶ/ር ሙሉጌታ ሥዩም እና የማኅበሩ ዋና ጸሐፊ መ/ር ዋሲሁን በላይ በትናንትናው ዕለት ሚያዚያ 24 ቀን 2016 ዓ.ም በመንግሥት የጸጥታ አካላት ከመኖሪያ ቤታቸው ተወስደው ሜክሲኮ በሚገኘው የፌደራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ቢሮ እንደሚገኙ አሳውቀን ነበር።

በዛሬው ዕለት ሚያዚያ 25 ቀን 2016 ዓ.ም ወደ ቤታቸው መመለሳቸውን እየገለጽን፣ ይህነ ላደረገ ሁሌም ለማይተወን ቸር አምላካችን ምስጋና እናቀርባለን።

በዚህ አጋጣሚ በሂደቱ በቀና መንፈስ ለተባበሩን የተለያዩ አካላት እንዲሁም አጣዳፊ ምላሽ ለሰጡን የመንግሥት የጸጥታ አካላት እናመሰግናለን።

በተጨማሪም በትዕግሥት ስትከታተሉና በጸሎት ስታስቡ ለነበራችሁ አባቶች፣ ምእመናን እና የማኅበረ ቅዱሳን አባላት እያመሰገንን፣ በዓሉ የሰላምና የበረከት እንዲሆንላችሁ እንመኛለን።

ማኅበረ ቅዱሳን!

@ortodoxtewahedo
የጌታችንና የመድኃኒታችን የኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ስቅለት (የድኅነት ቀን) በመንበረ ፓትርያርክ ቅድስተ ቅዱሳን ማርያም ገዳም ቅዱስ ፓትርያርኩ እና አበው ሊቃነ ጳጳሳት በተገኙበት ተከናወነ ።

@ortodoxtewahedo
📖ቅዳሜ ቀዳም ስዑር ትባላለች ፦

ይህች እለት ከድሮ በተለየ መልኩ የጌታችንን መከራ በማሰብ በጾም ታስባ ስለምትውል የተሻረች ቅዳሜ ይባላል።
ለምለም ቅዳሜ ይባላል፡-
ካህናቱ ለምእመናን ለምለም ቀጤማ የሚያድሉበት ዕለት በመሆኑም ለምለም ቅዳሜ ይባላል። ምዕመናንም ይህንን ለምለም ቀጤማ እስከ ትንሣኤ ለሊት በራሳቸው ላይ ያስሩታል።u

📖ቅዱስ ቅዳሜ ይባላል፡-

ቅዱስ የሆነው እግዚአብሔር በጥንተ ተፈጥሮ ፍጥረታትን አከናውኖ ያረፈበት ቀን ሲሆን በዘመነ ሐዲስ ደግሞ የማዳን ስራውን ሁሉ ፈጽሞ በሥጋው በመቃብር ሲያርፍ በነፍሱ ወደ ሲኦል ወርዶ ሲኦልን በርብሮ ባዶዋን ሲያስቀራት በዚያ የነበሩትን ነፍሳት የዘላለም ዕረፍትን ያወረሰበት ዕለት ስለሆነ ቅዱስ ቅዳሜ ይባላል።

   < ወስብሐት ለእግዚአብሔር >

👉 @ortodoxtewahedo
  አሣሪው እና ፈቺው ግን ማን ነው ?

  ✍️  በተመሳሳይ ሰዓት ልዩ ትዕዛዝ የተሰጣቸው ቁጥራቸው በዛ ያለ  የፌደራል ፓሊሶች እና የመንግሥት ደኅንነቶች  ከፊሎቹ ሙሉ ትጥቅ የታጠቁ ቀሪዎቹ በሲቪል ልብስ ሽጉጥ የታጠቁ ከሌሊቱ 11ሰዓት  በር ያንኳኳሉ በተለይ በመርጌታ ብርሃኑ ተክለያሬድ  ቤት ቁጥራቸው ወደ ሃያ የሚደሱ የታጠቁ እና ሲቪል የለበሱ ቤቱን እንደ ጉንዳን ወረው በሩን ሲደበድቡ ጎረቤት ግልብጥ ብሎ ሲወጣ ግቡ የምንይዘው ሰው አለ ፣ ቤቱ ለጥብቅ ፍተሻ ይፈለጋል በማለት ጎረቤቱ ሁኔታውን እንደ ፊልም በሩን ዘግቶ አጮልቆ እንዲያይ አደረጉት

✍️ በሩ ተከፈተ ያለፍርድ ቤት ትዕዛዝ  ዘው ብለው ገቡ የመጀመሪያ ስልክ ጠየቁ ከዛም ያገኙትን ሁለት ላፕቶፕ እሱን ወሰዱ ከዛማ ክፍል ለክፍል  አልጋ እየገለበጡ አንድ ሳይቀር ተፈተሸ እርግጥ በመሪጌታ ብርሃኑ ቤት የመጡት የፓሊሶቹ ኃላፊውም ሆነ ፓሊሶቹ ሥርዓት ያላቸው ሲሆኑ ከበላይ ትዕዛዝ የተሰጣቸውን ለፈጸም ሥራቸው በአግባቡ እየተወጡ ያሉ ቢሆኑም  በአንጻሩ የመረጃ ምንጮቻችን እንዳደረሱን የማኅበረ ቅዱሳን ሰብሳቢ ሊቀ ትጉሃን ቀሲስ ዶ/ር ሙሉጌታ ሥዩም እና የማኅበሩ ዋና ጸሐፊ መ/ር ዋሲሁን  ቤት ፍተሻ ላይ ፍራሽ ሁሉ እየተቀደደ እንደተፈተሻ መረጃውን አድርሰውናል ። ግን በሁሉም ቤት ፍትሻ  የተገኘ የለም።

✍️  የሚገርመው ግን ፍራሽ ቀደው ቤታቸው ሲበረበር የነበሩት የማኅበሩ ኃላፊዎች ከታሰሩ በኃላ በማግስቱ  በአሳሪው እና በፈቺው ትዕዛዝ ሰጪነት በመርማሪው ፓሊስ  ተጠርተው  ጥያቄ ከቀረበላቸው በኃላ በትላትናው  ዕለት መፈታታቸው ተሰምቷል

  ✍️ ይሁን እንጂ በተመሳሳይ ሰዓት  ቤታቸው ተፈትሾ ከታሰሩት መካከል መሪጌታ ብርሃኑ ተክለያሬድ እስካሁን ያናገረውም ይሁን ለምን እንደታሰረ የነገረው መርማሪ ፓሊስ የለም ፍትሕ ያለው ግን የት ነው ? አሣሪው እና ፈቺው ድርጊቱን በአንድ ላይ እንዲፈጸም ያደረገው  ለምንድን ነው ? ሌሎቹ ሲፈቱ  መሪጌታ ብርሃኑን ለምን መፈታት አልፈለገም ?  አቶ ዳንኤል ሆይ ስማ  ዛሬ ኅሊና ከሌላቸው ሆዳቸውን ካስቀደሙ የቤተክህነቱ ምንደኞች  ጋር አብረህ የምትሰራው ክፉ ሤራ ታሪኩ ተቀይሮ የሀማ ዕጣ ፋንታ እንደሚገጥምህ አይቀሬ ነው

✍️ መሪጌታ ብርሃኑ ተክለያሬድ ቋራጥ የዓለማ ሰው ነው ። ሀገሩን የሚወድ እንቁ የተዋሕዶ ፍሬ ነው ። ዓላማውን እና መንገዱን ለማደናቀፍ በተሰራ ክፉ ሤራ እጅግ የሚወዳትን ልጁን እና ሚስቱን ጄሪን እና ቤተሰቡን ጥሎ ትንሣኤን በእስር ቤት እንዲያሳልፍ አድርገውታል   ፥ እውነተኛ ፍትሕ ካለ ነገ ይፈታል ብለን ተስፋ በማድረግ ባለህበት ክፉ አይንካህ እንኳ ለብርሃነ ትንሣኤው አደረሰህ እንላለን 🙏

@ortodoxtewahedo
በግ እና ፍየል የምታርዱ ቆዳውን ለሀመረ ብርሃን ስጡና ብራና ይሰራበት!

@ortodoxtewahedo
Forwarded from ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ (💠 ✞ SAMI ✞ BREAVHEART💠)
#ቀዳሚት ሥዑር

ዕለተ ቅዳሜ እግዚአብሔር አምላካችን የሚታዩትንና የማይታዩትን ፣ በእግር የሚሔዱትን ፣ በክንፍ የሚበሩትን እና በባሕር የሚዋኙትን እንስሳትን፣ በመጨረሻም ሰውን በአርአያውና በአምሳሉ ፈጥሮ ያረፈባት ዕለት ነች፡፡

የመጀመሪያዋ ቅዳሜ ለእግዚአብሔር የዕረፍት ዕለት ናት፡፡ እግዚአብሔርን ፍጥረታትን ፈጥሮ ከፈጸመ በኋላ ስላረፈባት ‹ሰንበት ዐባይ› (ታላቋ ሰንበት) ትባላለች፡፡ ይህቺን ዕለት እስራኤላውያን እንዲያከብሯት ታዟል፡፡ ዕለተ ቀዳሚት (ሰንበት ዐባይ) በዘመነ ሐዲስም የተለየ የደኅነት ሥራ ተከናውኖባታል፡፡

እግዚአብሔር ጥንት ሥነ ፈጥረትን በመፍጠር ዕረፍት እንዳደረገባት ዅሉ፣ የፍጥረት ርእስ የኾነውን አዳምን ለማዳን ሕማምና ሞት የተቀበለው አምላካችን ክርስቶስ በመቃብር አርፎባታል
(ማቴ. ፳፯፥፷፩)፡፡

ቀዳሚት ሰንበት ጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በከርሠ መቃብር አርፎ የዋለባት ዕለት በመኾኗ ‹ቀዳሚት ሥዑር› ትሰኛለች፡፡

‹ሥዑር› የተባለችበት ምክንያትም በዓመት አንድ ቀን ስለምትጾም (የጾም ቀን በመኾኗ) ነው፡፡ የጌታችን እናት ቅድስት ድንግል ማርያም፣ ወዳጆቹ ቅዱሳን ሐዋርያት ጌታችን ተላልፎ ከተሰጠበት ዕለት ጀምሮ ብርሃነ ትንሣኤውን እስኪያዩ ድረስ እኽል ውኃ በአፋቸው አልዞረም፡፡

ይመኩበትና ተስፋ ያደረጉት የነበረ አምላካቸው በመቃብር ስላረፈ ዕለቷን ሞቱን በማሰብና ትንሣኤውን በመናፈቅ በጾም አክብረዋታል፡፡

እመቤታችንና ቅዱሳን ሐዋርያት በማዘን፣ በመጾምና በመጸለይ ዕለቷን እንዳከበሯት ዅሉ የተዋሕዶ ልጆችም የተቻላቸው ከዓርብ ጀምረው በማክፈል (በመጾም) እኽል ውኃ ሳይቀምሱ ለሁለት ቀናት ያድራሉ፡፡ ያልተቻላቸው ደግሞ ዓርብ ማታ በልተው ቅዳሜን በመጾም ትንሣኤን ያከብራሉ፡፡

በዚህ ዕለት ከሰኞ ከሆሣዕና ማግሥት ጀምረው እስከ ስቅለተ ዓርብ ድረስ በስግደት እና በጾም ያሳለፉ ምእመናን በዕለተ ቅዳሜ በቅጽረ ቤተ ክርስቲያን ይሰበሰባሉ፡፡ የጠዋቱ ጸሎት ሲፈጸምም ካህናቱ ‹‹ገብረ ሰላመ በመስቀሉ፤ በመስቀሉ ሰላምን መሠረተ›› እያሉ በቤተ ክርስቲያን ለተሰበሰቡ ምእመናን የምሥራች ቄጠማ ያድላሉ፡፡

ቄጠማው የምሥራች ምልክት ነው፡፡ ቄጠማው የምሥራች ምልክት ተደርጐ የተወሰደው በኖኅ ዘመን ከተፈጸመው ታሪክ ጋር በማቆራኘት ነው፡፡ ቅዱስ መጽሐፍ እንደሚነግረን በጻድቁ ኖኅ ዘመን የነበሩ ሕዝቦች ከሕገ እግዚአብሔር ውጪ ኾነው እጅግ የሚያሳዝን ኃጢአት በሠሩ ጊዜ በንፍር ውኃ ተጥለቅልቀዋል፡፡

በወቅቱ ጻድቁ ኖኅ ወደ መርከብ ይዞአቸው ከገባው እንስሳት መካከል የውኃውን መጉደል ለመረዳት ርግብን በመርከብ መስኮት አሾልኮ ይለቃታል፤ እርሷም ቄጠማ በአፍዋ ይዛ ትመልሳለች፡፡ ኖኅም በዚህ ቄጠማ የውኃውን መድረቅ ተረድቶ ተደስቷል (ዘፍ. ፱፥፩-፳፱)፡፡

ቄጠማ ለጥፋት ውኃ መድረቅ የምሥራች መንገሪያ እንደ ኾነ ዅሉ፣ አሁንም ‹‹በክርስቶስ ሞት ሞተ ነፍስ ከሰው ልጆች ተወገደ፤›› ስትል ቅድስት ቤተ ክርስቲያን ለልጆቿ ቄጠማ ታድላለች፡፡ ምእመናንም የምሥራች ተምሳሌት የኾነውን ቄጠማ በግንባራቸው ያስሩታል፡፡ የክርስቶስ ተከታዮች ዅሉ ከጨለማ ወደ ብርሃን፤ ከዋዕየ ሲኦል (የሲኦል ቃጠሎ) ወደ ጥንተ ማኅደራቸው ገነት መመለሳቸውን በዚህ አኳኋን እየገለጡ በዓለ ትንሣኤን በቅድስት ቤተ ክርስቲያን ያከብራሉ።

የእናንተ አስተያየት ያበረታናልና አስተያየታችሁን በ ☞

@BREAVHEARTT

#ወስብሐት ለእግዚአብሔር
#ወለወላዲቱ ድንግል
#ወለመስቀሉ ክቡር

http://www.tg-me.com/ortodoxtewahedo
Forwarded from ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ (💠 ✞ SAMI ✞ BREAVHEART💠)
#በስመአብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!!!

#በሀገርም ውስጥ ሆነ ከሀገርም ውጭ ለምትኖሩ ለመላው የክርስትና እምነት ተከታዮች በሙሉ *እንኳን ለብርሃነ ትንሣኤ በሰላም በጤና፤ በህይወትና በፍቅር አደረሳችሁ አደረሰን አሜን።


*በመስቀሉ ደም ሰላምን አደረገ በሰማያትም ላሉት እርቅን ሰላምን አደረገላቸው*
*( ቆላ፡ 1 ÷ 19 )*

*ለኃጢአት ሞትን ለፅድቅ እንድንኖር፡ እርሱ ራሱ በሥጋዉ ኃጢያታችንን በእንጨት ላይ ተሸከመ፣ በመገረፉ ቁስል ተፈወሳችሁ፣ እንደ በጎች ትቅበዘበዙ ነበረና፣ አሁን ግን ወደ ነፍሳችሁ እረኛና ጠባቂ ተመልሳችሃል*
(2ኛ ጴጥ 2÷24)

🌹 *እ* 🌹
🌹 *ን*🌹
🌹 *ኳ*🌹
🌹 *ን*🌹
🌹 *ለ*🌹
🌹 *ብ*🌹
🌹 *ረ*🌹
🌹 *ሃ*🌹
🌹 *ት*🌹
🌹 *ን*🌹
🌹 *ሣ*🌹
🌹 *ኤ*🌹
🌹 *ዉ*🌹
🌹 *ዋዘማ*🌹
🌹 *በ*🌹
*ሠ*
🌹 *ላ*🌹
🌹 *ም*🌹
🌹 *አ*🌹
🌹 *ደ*🌹
🌹 *ረ*🌹
🌹 *ሳ*🌹
🌹 *ች*🌹
🌹 *ሁ*🌹
🌹 *አ*🌹
🌹 *ደ* 🌹
🌹 *ረ*🌹
🌹 *ሰ*🌹
🌹 *ን*🌹
🌹 *በ*🌹
*ዓ*
🌹 *ሉ*🌹
🌹 *የ*🌹
🌹 *ሠ*🌹
🌹 *ላ*🌹
🌹 *ም*🌹
*የ*
🌹 *ደ*🌹
🌹 *ስ*🌹
🌹 *ታ*🌹
🌹 *የ*🌹
🌹 *መ*🌹
🌹 *ተ*🌹
🌹 *ሳ*🌹
*ሰ*
🌹 *ብ*🌹
🌹 *ና*🌹
🌹 *የ* 🌹
🌹 *በ*🌹
🌹 *ረ*🌹
🌹 *ከ*🌹
🌹 *ት*🌹
🌹 *በ*🌹
*ዓ*
🌹 *ል*🌹
🌹 *ይ*🌹
🌹 *ሁ*🌹
🌹 *ን*🌹
🌹 *ላ*🌹
🌹 *ች*🌹
*ሁ*
🌹 *ይ*🌹
🌹 *ሁ*🌹
🌹 *ን*🌹
🌹 *ል*🌹
🌹 *ን*🌹
🌹 *አ*🌹
🌹 *ሜ*🌹
🌹 *ን* 🌹
🌹፡፡🌹

*የመሰቀሉ ቃልለምጠፉት ሞኝነት ፣ ለእኛ ለምድን ግን የእግዚአብሔር ኃይል ነው ።
(1ኛ ቆሮ 1÷18)_*

*ከጌታችን ከኢየሱስ ክርስቶስ መስቀል በቀር ሌላ ትምክህት ከእኔ ይራቅ፡ ( ገላ ፮ ÷14 )*

❤️ወስብሐት ለእግዚአብሔር❤️
❤️ወለወላዲቱ ድንግል❤️
❤️ወለመስቀሉ ክቡር🕊

http://www.tg-me.com/ortodoxtewahedo
Forwarded from ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ (💠 ✞ SAMI ✞ BREAVHEART💠)
"አሁን ግን ክርስቶስ ላንቀላፉት በኩራት ሆኖ ከሙታን ተነስቷል "

1ቆሮ 15÷20

#እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ የትንሣኤ በዓል በሠላምና ጤና አደረሳችሁ አደረሰን!

ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን
በዓቢይ ኃይል ወሥልጣን
አሠሮ ለሰይጣን
አግዐዞ ለአዳም
ሰላም
እምይእዜሰ
ኮነ
ፍሥሐ ወሰላም
"እግዚአብሔር ከእንቅልፍ እንደሚነቃ ተነሣ"

መዝ 77÷65

#መልካም የትንሣኤ በዓል ይሁንላችሁ ።

http://www.tg-me.com/ortodoxtewahedo
Forwarded from ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ (💠 ✞ SAMI ✞ BREAVHEART💠)
የኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ /OrtdooxTewahido/ አባላት በሙሉ::

እንኳን ለጌታችን ለመድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ በዓለ ትንሣኤ አደረሰን አደረሳችሁ!!!



💐💐💐👉
ክርስቶስ ተንሥአ እሙታን
በዐቢይ ኃይል ወሥልጣን
አሠሮ ለሰይጣን
ዓግአዞ ለአዳም
ሰላም እም
ይእዜሰ
ኮነ
ፍስሐ ወሰላም!!!!!💐💐💐

http://www.tg-me.com/ortodoxtewahedo
Forwarded from ኦርቶዶክስ ተዋህዶን እንወቅ (💠 ✞ SAMI ✞ BREAVHEART💠)
#እዩና እመኑ ሰዎች

እዩና እመኑ ሰዎች
ድንጋዮ ተፈቃቀወላል
ኢየሱስ በእኩለ ሌሊት
በኃይሉ ሞትን ድል ነስቷል(2)

እልልታ ለዚህ ይገባል
ግርግርታ ለዚህ ይገባል
የሞት ሀይል ተዋርዷል ዛሬ
ሲኦልም ተመሰቃቅሏል(2)

መላእክቱ ነጭ ለብሰው
ምስራቹን አበሰሩ
ተነስቷል ኢየሱስ ብለው
ለዓለም እንዲናገሩ(2)

እዩና እመኑ ሰዎች
ድንጋዮ ተፈነቃቅሏል
እየሱስ በእኩለለሊት
በሃይሉ ሞትን ድል ነስቷል(2)

እልልታ ለዚህ ይገባል
ግርግርታ ለዚህ ይገባል
የሞት ሀይል ተዋርዷል ዛሬ
ሲኦልም ተመሰነቃቅሏል(2)

#ለመቀላቀል #ከታች #ሠማያዊውን #ይጫኑ
👇👇 👇👇
http://t.meortodoxtewahedo
ብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ማትያስ ቀዳማዊ ፓትርያርክ ርዕሰ ሊቃነ ጳጳሳት ዘኢትዮጵያ ሊቀጳጳስ ዘአኲስም ወዕጨጌ ዘመንበረ ተክለሃይማኖት የ2016 ዓ.ም በበዓለ ትንሣኤን በማስመልከት ያስተላለፉት ቃለ በረከት።

በስመ አብ ወወልድ ወመንፈስ ቅዱስ አሐዱ አምላክ አሜን!
በሀገራችን በኢትዮጵያ በገጠርና በከተማ የምትኖሩ፤
ከሀገር ውጭ በተለያዩ አህጉር የምትገኙ፤

የሀገራችንን ዳር ድንበር ለመጠበቅና ለማስከበር በየጠረፉ የቆማችሁ፤
በሕመም ምክንያት በየፀበሉና በየሆስፒታሉ ያላችሁ፤
እንዲሁም የሕግ ታራሚዎች ሆናችሁ በየማረሚያ ቤቱ የምትገኙ ኢትዮጵያውያንና ኢትዮጵያውያት ሁሉ፡-
የትንሣኤ ሙታን በኲር በመሆን ቀድሞ የተነሣው አምላካችን ኢየሱስ ክርስቶስ እንኳን ለሁለት ሺሕ ዐሥራ ስድስት ዓመተ ምሕረት በዓለ ትንሣኤ በሰላም አደረሰን አደረሳችሁ!
“ወይእዜኒ ክርስቶስ ቀደመ ተንሥኦ እምኲሎሙ ሰብእ ሙታን አሁን ግን ክርስቶስ ላንቀላፉት ሁሉ በኲር ሆኖ ከሙታን ተነሥቶአል” (1 ቆሮ 15;20)

በዛሬው ዕለት በከፍተኛ ሃይማኖታዊ ሥነ ሥርዓት የሚከበረው የጌታችን ትንሣኤ ለሰው ልጅ ያለው መንፈሳዊ ትርጉም እጅግ የላቀ ነው፤ እግዚአብሔር ፍጥረታትን በሙሉ በተለይም የሰው ልጅን ሲፈጥር በፍጹም ፍቅር ነው፡፡
ለዚህም የሰው በአርአያ እግዚአብሔር መፈጠር በቂ ማስረጃ ነው፤ ሰው በበደሉ ምክንያት ለሞት ቢዳረግም የእግዚአብሔር ፍጹም ፍቅር ጨርሶ አልተለየውም፤ እግዚአብሔር አንድ ቀን ሞትን ከሰው ጫንቃ አሽቀንጥሮ እንደሚጥል በየጊዜው ይገልጽ ነበረ፤ ያም በራሱ ልዩ ጥበብ እንደሚከናወን አረጋግጦ ለሰው ልጅ ተስፋውን አሳውቆ ነበር፤ ያም ልዩ ጥበብ መድኃኒታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ነው፡፡
የእግዚአብሔር ዕውቀትና ጥበብ ድንበር የለውምና ከፍጥረተ ዓለም በፊት ሳይቀር የሰው ድኅነት በኢየሱስ ክርስቶስ ደም እንደሚፈጸም በእግዚአብሔር ዘንድ የተቈረጠ ነገር ነበረ፤ ጊዜው ሲደርስም በህላዌና በክዋኔ ከእርሱ ጋር አንድ የሆነ እግዚአብሐር ወልድ የሰውን ሰውነት ተዋሕዶ ሰውን የማዳን ስራውን አንድ ብሎ ጀመረ፡፡
ሰዎች በኃጢአትና በዲያብሎስ በደዌና በሞት ላይ ሥልጣን ያለው አዳኝ እሱ እንደሆነ ያውቁ ዘንድ የማዳን ስራውን በመዋዕለ ሥጋዌው በስፋት አከናወነ፡፡
ልዩ ልዩ ደዌና በሽታ የሚያሠቃያቸውን ፈወሰ፤ ኃጢአተኞችን በይቅርታ ተቀበለ፤ ኃጢአታቸውንም ደመሰሰ፤ አጋንንትንም በትእዛዝ አስወጣ፤ ወደ ጥልቁም አሰመጣቸው፤ ዲያብሎስንም ድል ነሥቶ አባረረ፤ ሙታንንም አነሣ፤ በባሕር ላይ በእግሩ ተራመደ፤ ነፋሳትን ገሠጸ፤ በአምስት እንጀራ ከአምስት ሺሕ ሕዝብ በላይ መገበ፤ ውሀውንም ወደ ጠጅ ለወጠ፡፡
ሰውን ሁሉ በፍቅርና በይቅርታ ይቀበልና ያገለግል ነበር እንጂ በአንዱ ስንኳ የመጨከንና የማግለል መንፈስ አላሳየም፤ ይህ ሁሉ ፍጹም የሆነውን የእግዚአብሔር ፍቅር ማሳያ ነበረ፡፡
በፍጥረት ሁሉ ላይ መለኮታዊ ሥልጣን እንዳለውም ማረጋገጫ ነበረ፤ መልእክቱም ዓለም መዳኛዋና አዳኝዋ እሱ መሆኑን አውቃ በአእምሮ እንድትከተለውና የድኅነቱ ተቋዳሽ እንድትሆን ማስቻል ነው፡፡
የተወደዳችሁ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን ምእመናንና ምእመናት!

በእግዚአብሔር አሠራር ኃጢአት ያለ ቤዛነት አይሰረይም፤ በመሆኑም ሰው በእግዚአብሔር ፊት ፍጹም ኃጢአተኛ ሆኖ ስለተገኘ ቤዛ ሆኖ የሚያድነው ያስፈልገው ነበር፤ ቤዛ መሆን የሚችለው አካል ደግሞ ራሱ ፍጹም ንጹህ መሆን ነበረበት፡፡

ከዚህም አንጻር በእግዚአብሔር ፊት ለሱ የሚመጥን ንጹህ ኣካል ከፍጡራን ወገን አልተገኘምና እሱ ራሱ ሰው ሆኖ የሰው ቤዛ ለመሆን በሥጋ ተገለጠ፤ በዚህም መሠረት የሰው ቤዛ ሆኖ በመስቀል ላይ በመሰቀል ንጹህ ደሙን አፈሰሰ፤ በዚህ ደም ምክንያት የሰው ኃጢአት በሥርየት ተዘጋ፤ ለዚህም ነው ቅዱስ መጽሐፍ “ያለ ደም ሥርየት ወይም ይቅርታ የለም” ብሎ የሚነግረን፡፡
ከዚህ ደም መፍሰስ በኋላ ወደ ሲኦል ወርዶ በዚያ የነበሩ የኃጢአት ግዞተኞችን በሙሉ ፈትቶ ወደ ቀደመ ስፍራቸው ወደ ገነት መለሰ፤ ከስቅለተ ክርስቶስ ጀምሮ እስከ መጨረሻ ያለው የሰው ኃጢአት በሙሉ በክርስቶስ ደም ይደመሰሳል፡፡

ሆኖም ይህ ሥርየት የሚገኘው በእምነት መሆኑን ቅዱስ መጽሐፍ አበክሮ ይነግረናል፣ በክርስቶስ አምኖ በደሙ የነጻ ሁሉ ክርስቶስ በተነሣው ዓይነት ትንሣኤ ይነሣል፡፡
የተወደዳችሁ የመንፈስ ቅዱስ ልጆቻችን ምእመናንና ምእመናት!
የጌታችንን ትንሣኤ ስናከብር የኛንም ትንሣኤ በማሰብ ሊሆን ይገባል፤ ትልቁ ነገርም የኛን ትንሣኤ ማሰቡ ላይ ነው፤ ምክንያቱም የክርስቶስ ትንሣኤ ለኛ ተብሎ የተደረገ በመሆኑ ነው፡፡

የሱ ትንሣኤ ለኛ ትንሣኤ በኲር ነው፤ ማሳያና ማረጋገጫም ነው፤ እግዚአብሔር በየዕለቱ የሚፈልገው የኛን ትንሣኤ ማየት ነው፤ የኛ ትንሣኤ በአንድ ቀን በቅፅበት የሚሆን አይደለም፤ ትንሣኤያችን አምነን ስንጠመቅ ተጀምሮ ከመቃብር ስንነሣ የሚጠናቀቅ ነው፡፡
እግዚአብሔር ዛሬም እያንዳንዱ ሰው በትንሣኤ ሕይወት እንዲመላለስ ይጠራል፤ ምክንያቱም የኋለኛው ትንሣኤ የሚገኘው በፊተኛው ትንሣኤ እንደሆነ እግዚአብሔር በመጽሓፉ ነግሮናልና ነው፤ በፊተኛው ትንሣኤ ዕድል ያለው ብፁዕ ነው፤ በሱ ላይ ሞት ሥልጣን የለውምና ነው፤ ለሰው ልጆች ተጠብቆልን ያለው ተስፋ ይህ ነው፡፡

ተስፋውን እውን ማድረግ የሚቻለውም በኛ ሃይማኖታዊና ተግባራዊ ተሳትፎ እንደዚሁም በኢየሱስ ክርስቶስ ቤዛዊ ደም ነው፤ የነገውን ትንሣኤ ተሳታፊ ለመሆን ዛሬ መነሣት ግድ ይላል፤ ይህም የሚቻል እንጂ የማይቻል አይደለም፡፡

በእምነት ትንሣኤ፣ በአምልኮተ እግዚአብሔር ትንሣኤ፣ ለእግዚአብሔር በመታዘዝ ትንሣኤ፣ በፍቅር ትንሣኤ፣ በሰላም ትንሣኤ፣ በይቅርታ ትንሣኤ፣ በመከባበር ትንሣኤ፣ በአንድነት ትንሣኤ፣ በመተሳሰብ ትንሣኤ ወዘተ በመሳሰሉ ሃይማኖታዊና ግብረ ገባዊነት ጸንተን መኖር ከቻልን የፊተኛው ትንሣኤ ማለት እሱ ነው፡፡ ዛሬ እግዚአብሔር እያንዳንዳችን ይህንን ትንሣኤ እውን አድርገን ስንኖርና ስንመላለስ ማየት ይፈልጋል፡፡
በአንጻሩም ክሕደትን፣ ከሕገ ተፈጥሮ ያፈነገጠ ጸያፍ ተግባርን፣ ጥላቻን፣ ጦርነትን፣ መለያየትን፣ ራስን ብቻ መውደድን፣ መጨካከንን፣ ግብረ ኃጢአትን፣ ፈሪሐ እግዚአብሔር ገንዘብ አለማድረግን፣ ፈጣሪን አለማመንን የተጸየፈ ምእመንን ማየት ይፈልጋል፡፡
ምክንያቱም ሁሉም ኃጣውእ አፅራረ ትንሣኤ ናቸውና ነው፤ ኃጣውእ በምድርም በሰማይም የሰው ጠላቶች ናቸው፤ በምድር ለሥጋዊና መንፈሳዊ በሽታ ይዳርጉናል፡፡

በተለይም በእግዚአብሔር ፊት እጅግ አስጸያፊ የሆነው የነውረ ኃጢአት ርኲሰትና በጋብቻ ያልታሰረ ሩካቤ ሥጋ ትውልድን እንደ ቅጠል እያረገፈው እንደሆነ፣ ምንም ዓይነት ፈውስ ላልተገኘለት የኤች አይ ቪ ኤድስ በሽታ ዋነኛ መተላፊያም ይህ ነውረ ኃጢአት እንደሆነ ተደጋግሞ ተነግሮአል፡፡
ይሁንና አሁንም ጥንቃቄ በጎደለው ድርጊት ስሕተቱ በመቀጠሉ በጦርነት ከሚያልቀው ሕዝብ ባልተናነሰ በዚህ ገዳይ በሽታ ብዙ ወገን እያለቀ ነውና እባካችሁ ሕዝበ እግዚአብሔር አንድ ለአንድ በመተሣሰርና በተቀደሰ የጋብቻ ሕይወት በመወሰን ትንሣኤያችንን እናብስር፡፡
2024/05/29 09:32:55
Back to Top
HTML Embed Code: