Telegram Web Link
ናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ 🤷‍♂
Photo
#ክፍል_14
#ሶስት_የአዕምሮ_ደረጃዎች
/ንቃተ ህሊና ፣ ውስጠ ህሊና ፣ ንቁ ያልሆነ ህሊና/
www.tg-me.com/psychoet
(ናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ እና በአቤል ታደሰ )

ታዋቂው የስነ-ልቦና ባለሙያ የሆነው ሲግመንድ ፍሮይድ: ባህሪ እና ስብዕና የሚመነጨው በሦስት የተለያዩ የግንዛቤ ደረጃዎች መካከል በሚፈጠር የስነ-ልቦና ኃይሎች(Psychic Forces) ልዩ መስተጋብር ነው ብሎ ያምናል ፡፡
ፍሮይድ እያንዳንዱ የአእምሮ ክፍሎች በባህሪ ላይ ተጽዕኖ በማሳደር ወሳኝ ሚና እንደሚጫወቱ ያምናል ፡፡

የፍሮይድ ፅንሰ-ሀሳቦችን ለመረዳት በመጀመሪያ እያንዳንዱ የባህርይ ክፍል እንዴት እንደሚሠራ እና ለሰው ልጅ ባህሪ እድገት አስተዋፅኦ የሚያደርጉበትን መንገድ ማወቅ አስፈላጊ ነው ፡፡

#የፍሩድ ሦስት የአእምሮ ደረጃዎች :-

#1 The Preconscious Mind(ውስጠ ህሊና)
#2 The Conscious Mind (ንቃተ ህሊና)
#3 The Unconscious mind (ንቁ ያልሆነ ህሊና)

#1 The Preconscious (ውስጠ ህሊና)
ወደ አእምሮ ሊመጣ የሚችለውን ማንኛውንም ነገር ያካትታል ፡፡

#2 The Conscious Mind (ንቃተ ህሊና) በማንኛውም ጊዜ የምናውቃቸውን ሁሉንም ሀሳቦች ፣ ትውስታዎች ፣ ስሜቶች እና ምኞቶች ይይዛል። ይህ በአዕምሯችን ማሰብ እና ማውራት የምንችልበት የአዕምሯችን ሂደት ገጽታ ነው ፡፡ ሁልጊዜ የእኛ የንቃተ ህሊና አካል ያልሆነ ነገር ግን በቀላሉ ሊገኝ እና ወደ ግንዛቤ ሊመጣ የሚችል ማህደረ ትውስታችንን ያካትታል።

#3 The Unconscious Mind (ንቁ ያልሆነ ህሊና) ከስሜታችን ግንዛቤ ውጭ የሆኑ የስሜት ፣ የሀሳብ ፣ የምኞት እና ትውስታዎች ማጠራቀሚያ ነው ፡፡ እንደ ህመም ፣ ጭንቀት ወይም ግጭት ያሉ ተቀባይነት የሌላቸውን ወይም ደስ የማይሉ ይዘት ያላቸውን ትውስታዎችን ይይዛል።

The Unconscious Mind (ንቁ ያልሆነ ህሊና) የተደበቁ ትውስታዎችን የተደቆሱ ስሜቶችን ፣ ልምዶችን ፣ ሀሳቦችን ፣ ምኞቶችን እና ግብረመልሶችን ያካትት ይችላል ፡፡

እንደ ፍሮይድ ገለፃ ፣ ምንም እንኳን እነዚህን ውስጣዊ ተጽዕኖዎች የማናስተውል ቢሆንም በባህሪያችን እና በማንነታችን ላይ ተጽዕኖ ማድረጉን ይቀጥላል።


_____በሌላ ጊዜ ደግሞ እነዚህ ሦስት የአዕምሮ ደረጃዎች እንዴት ባህሪያችንን እንደሚገነቡ እንመለከታለን ፡፡ ለምሳሌ "የአፍ ወለምታ በቅቤ አይታሽም" የሚል ትልቅ አባባል ኢትዮጵያኖች አለን እና ይሄ "የአፍ ወለምታ" ከየትኛው ክፍል ይመነጫል ፣ ለምንና እንዴት ይመነጫል የሚለውን ጨምሬ አሳያችኅለሁ ፡፡ ሰው አምልጦኝ ተሳደብኩ ፣ ንዴቴን መቆጣጠር አልቻልኩም ፣ ሰይጣኔን አታምጣው ፣ ደሜን አታፍላው የሚልበትን ምክንያት ከነዚህ ሦስት የአዕምሮ ደረጃዎች መስተጋብር አንፃር እናያለን ፡፡

www.tg-me.com/psychoet
www.tg-me.com/wikihabesha
_________❖
Source: verywellmind.com (web)

ይህ ፅሁፍ ለብዙ ሰው እንዲደርስ ሁላችንሞ ባለንበት የFacebook/Telegram ግሩፕ ውስጥ #ሼር እናርገው 💛

ስለ ሳይኮሎጂ የበለጠ ለማወቅ ፔጁን ይከታተሉ ለወዳጆችዎ ያጋሩ

ዕውቀት ከአሉታዊ የአስተሳሰብ እስር ቤት ነፃ ያወጣል !
የሳምንት ሰው ይበለን!
እወዳችኅለሁ !
ናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ
__________❖
ኦሲዲ (OCD) ያለበት ሰው አእምሮ ውስጥ

በሩን ቆልፌዋለሁ ወይስ አልቆለፍኩትም? ስቶቩን አጥፍቼዋለሁ ወይስ አላጠፋሁትም? የሚል ሀሳብ መጥቶባችሁ ሄዳችሁ ቼክ አድርጋችሁ የምታውቁ ከሆነ የኦሲዲ (OCD) ምልክት በትንሹም ቢሆን አጋጥሟችሁ ያውቃል።

ኦሲዲ በአጭሩ ሲገለፅ ጥርጣሬ የሚፈጥር የሚነዘንዝ ሀሳብና ያንን ሀሳብ ተከትሎ የሚመጣውን ጭንቀት ለማርገብ የሚደረግ ተደጋጋሚ ድርጊት ነው። አንዳንድ ኦሲዲ ያለባቸው ሰዎች "የሚለውን ካላደረግኩ የሚያጨናንቅ ጉልቤ አእምሮ ውስጥ ያለ ይመስለኛል።" ይላሉ።

አንድ ኦሲዲ ያለባት ሴት አእምሮ ውስጥ፦

ወንበር ስትነካ እጇ የቆሸሸ ይመስላትና አእምሮዋ "ታጠቢ፣ ታጠቢ" እያለ ይነዘንዛታል። ንዝንዙ (ይህን ቃል ስፅፍ በወፍ ቋንቋ እያወራሁ መስሎኝ ነበር😂) ሲበዛባት ለመታጠብ ትነሳለች። አእምሮዋ "የውሀ መክፈቻውም ቆሻሻ እኮ ነው።" ይላታል። መጀመሪያ መክፈቻውን ለአምስት ደቂቃ ታጥባለች።

አእምሮዋ ይቀጥልና "ሳሙናውም እኮ ቆሻሻ ነው።" ይላታል። ሳሙናውን ለአምስት ደቂቃ ሙልጭ አድርጋ ታጥባለች። ከዛ መታጠብ ትጀምራለች። አእምሮዋ "እዛ ጋር ይቀራል፣ እዚ ጋር ይቀራል።" እያለ መታጠብ ያለባትን ቦታ ይጠቁማታል። እሷም ትታዘዛለች። ታጥባ ልትጨርስ ስትል "የውሀ ፍንጣቂ ነክቶሻል፤ ታጠቢ" ይላታል። እንደገና ትታጠባለች...

ቤተሰቦቿና የስራ ባልደረቦቿ "እሷ መታጠቢያ ቤት ከገባች አትወጣም።" ይሏታል።

በታክሲ ስትሄድ አጠገቧ የሚቀመጠው ሰው ባይነካት ደስ ይላታል። የታክሲ ረዳቱ መልስ ሲሰጣት የእጁን ንፅህና ትመለከታለች። ከመቼ ወርዳ እስከምትታጠብ ይጨንቃታል። የበር እጀታ ባትነካ ትመርጣለች... ጭንቀቱን አስቡት። የሚጠፋውን ጊዜ አስቡት። ማህበራዊ ህይወት ላይ የሚያሳድረውን ተፅእኖ አስቡት።

ኦሲዲ የሚታከም የአእምሮ ህመም ነው።
©ሀኪም
#ሀሙስ 13

መጥረቢያህን ሳለው!!

በአንድ ከተማ ውስጥ የሚኖር እንጨት ፈላጭ ነበር፡፡ ሆኖም ቋሚ የሆነ ስራ ስለሌው ገቢው እየዋዠቀበት ለመኖር እጅግ በጣም አስቸጋሪ ሁኔታ ፈጠረበት ስለሆነም ወደ አንድ የጣውላ መሰንጠቂያ ድርጅት በመሄድ ባለቤቱን ስራ እንዲቀጥረው ጠየቀው ኃላፊውም የስራ ፈላጊውን የሰውነት ፈርጣማነት እና የስራ ተነሳሽነቱን በማድነቅ ከሚሰራበት ደን ውስጥ የተወሰነ ቦታ በመከለል ዛፎችን የመቁረጥ ስራ ሰጠው፡፡  በመጀመሪው ቀን 18 ዛፎችን ቆረጠ፤ በዚህ የተደሰተው አለቃም እጅግ በጣም ጥሩ ስራ እንደሰራና እንደሱ ዓይነት  ዛፍ ቆራጭ አይቶ እንደማያውቅ እንዲሁም  በዚሁ እንዲቀጥልበት አበረታታው፡፡ በአለቃው የማበረታቻ ቃላት የተነሳሳው ዛፍ ቆራጭም በሁለተኛው ቀን በበለጠ ተነሳሽነት ወደ ስራው መጣ ሆኖም ግን የቆረጠው ዛፍ 15 ነበር፤ በሶስተኛው ቀን ደግሞ 10 ዛፎችን ቆረጠ፡፡ ቀናት አልፈው ቀናት በተተኩ ቁጥር የሚቆርጠው የዛፍ ቁጥር እያነሰ እያነሰ እንደውም ከሁሉም ዛፍ ቆራጮች ዝቅተኛ የሆነ የዛፍ ቁጥር የሚቆርጠው እሱ ሆኖ አረፈው፡፡ አለቃውም ይህን የማያሻሽል ከሆነ ከስራው እንደሚያባርረው ነገረው በዚህ የተደናገጠው ዛፍ ቆራጭም የዕረፍት ሰዓቱን ጭምር በመሰዋት ቢሰራም ጠብ የሚል ነገር ጠፋ፤ ጥንካሬዬን አጥቻለው ሲልም ደመደመ፡፡  በመጨረሻም አለቃው መጥቶ ከስራው እንደተባረረ ነገረው፤ በሁኔታው ግራ የተጋባው ዛፍ ቆራጭም የተቻለውን ሁሉ ቢጥርም ምን የሚፈይደው ነገር ማጣቱን ምን እየተፈጠረ እንዳለ ግራ እንደገባው ነገረው፡፡ ሁኔታው የገባው አለቃም መቼ ነው ለመጨረሻ ጊዜ መጥረቢያህን የሳልከው ብሎ ሲጠይቀው ዛፍ ቆራጩም መጥረቢያዬን ለመሳል ጊዜ አልነበረኝም አለው፡፡ ስለዚህ የችግሩ ምንጭ የነበረው የሰውየው ጥንካሬ ማጣትና የስራ ተነሳሽነት ሳይሆን የመጥረቢያው አለመሳል ነበር፡፡

ከላይ ካነበብነው አጭር ታሪክ ውስጥ ራሳችንን አስገብተን ካየነው ለስራ ከመነሳታችን በፊት ወይም በስራ ላይ እያለን እረፍት ማድረግና አዕምሮን እንዲሁም አካልን ማሳረፍ ለሚቀጥለው ስራ አብዝቶ እንደሚያዘጋጀን ነው፡፡ ይህ የማይሆን እንደሆነ እና ሁልጊዜ ስራችንን ብቻ አትኩረን የምንሰራ ከሆነ ውጤታማነታችን እየቀነሰ ወይም እዛው ባለበት ይቀጥላል ስለዚህ ውድ የ ዘሳይኮሎጂስት ቤተሰቦች ሁላችንም መቼም አንድ ዓይነት ነገርን ዐዕምሮን የማሳረፊያ መንገድ አንጠቀምም ሆኖም ግን በራሳችን መንገድ የሚያዝናንን ነገር እየመረጥን አዕምሮና አካላችንን ለሚቀጥለው ውጤታማ ስራችን ማዘጋጀት ይኖርብናል፡፡ እስኪ እነዚህን ጥቂት አዕምሮን እና አካልን የማሳረፊያ መንገዶችን  አብረን እንዝለቃቸው ፡-

#ከቤተሰብ ጋር ጊዜን ማሳለፍ

ስንቶቻችን ነን ጠዋት ወተን ማታ የምንገባው ? ከልጆቻችንን ጋር በቂ ጊዜ የምናሳልፈው? ከትዳር አጋራችን ጋር ወጣ ብለን እራት የምንገባበዘው? ቤቱ ይቁጠረው ፡፡ እንደውም እንዳንዶቻችን ወደ ቤት የምንገባው በስራ ከመወጠራችን የተነሳ እራት በልቶ ለመተኛት ነው፡፡ ግን ይሄ እየቆየ ውጤታማነታችንን እየሸረሸረ እንዲሁም ከቤተሰባችን እያራቀን ስለሚሄድ ትኩረት መስጠት ወሳኝ ነው፡፡በህይወታችን ከገንዘብ በተጨማሪም ሌሎች ወሳኝ ነገሮች እንዳሉ መገንዘብ ይኖርብናል፡፡

#የተለያዩ መጽሕፍትን ማንበብ

ማንበብ አዳዲስ ሀሳቦችን ለማፍለቅ እንደ ግብዓት ሆኖ ያገለግላል፤ እንዲሁም አዕምሮን ለማሰረፍ ዓይነተኛ ሚና ይጫወታል፡፡ ታዲያ መጽኃፍት ስንል ልብ ማለት የሚገባን ከስራችን ጋር የተገናኙ መጽሀፍትን ማንበብ እሰየው የሚያስብል ቢሆንም ቅሉ ግን ታሪካዊ፣ ኃማኖታዊ ፣ ፖለቲካዊ ………ወዘተ እንደምርጫችን ማካተትም ይኖርብናል፡፡

#ሙዚቃ፣ ስዕል ፣ ፊልም ቲያትር…. ላይ ጊዜን ማሳለፍ

በህይወታችን ላይ ጥብብን እንደ አንድ የማስከኛ እና የማደሻ መንገድ በመጠቀም የደከመን አዕምሮ እና አካልን እንደገና በማነቃቃት እና ለሚቀጥለው ስራ ማዘጋጀት  ይመከራል፡፡

#ኃይማኖታዊ ህይወት ማዘውተር

የዕረፍት ጊዜን ከማሳለፊያ መንገዶች አንዱ የኃይማኖት ተቋማትን በማዘውተር ከፈጣሪ ጋር ግንኙነትን ማጠናከር እና የተለያዩ ኃይማኖታዊ ክዋኔዎች ላይ መሳተፍ ይበረታታል፡፡

#የአካል ብቃት እንቅስቃሴዎች ማዘውተር

በቀን ቢያንስ ለ30 ደቂቃ የአካል ብቃት እንቅሰቃሴዎች ላይ መሳተፍ እና በቀዝቃዛ ውኃ ሰውነትን መታጠብ ህይወታችን ላይ ዓይነተኛ ሚና ይጫወታል፡፡ ጥናቶች እንደሚያመለክቱት ከሆነ አካላዊ እንቅስቃሴ የሚያደርጉ ሰራተኞች ከማያደርጉት የበለጠ በስራቸው ውጤታማና ቀልጣፋ ሆነው ተተገኝተዋል፡፡

#ከጓደኞቸ ጋር ሰብሰብ ብሎ መሳቅ መጫወት

መቼም በጉጉት ከሚጠበቁትት የእረፍት ማሳለፊያ ነገሮች መካከል ከአብሮ አደግ ጓደኞች፣ ከቢሮ የስራ ባልደረቦች እንዲሁም ከልባዊ ወዳጆች ….ወዘተ ጋር ተሰብስቦ ስለ ተለያዩ ነገሮች እያወሩ መሳቅ እና መጫወት አንዱ ነው፡፡ ይህ ክዋኔም አዕምሮን በማደስ አካልን ያነቃቃል፡፡

#ቀናችንን በፕሮግራም መምራት

በቀን ውስጥ የምንሰራቸውን ስራዎች በቅደም ተከተላቸው መሠረት እና የሚወስዱበትን ጊዜ ጨምረን ፕሮግራም እናውጣ ከስራችን መኃልም የእረፍት ጊዜን ማካተት እንዳንረሳ፡፡

#አጭር የዕንቅልፍ ሠዓት ይኑረን

በቀን ውስጥ ሲበዛ ለ20ደቂቃ እንቅልፍ ማሸለብ ውጤጣማ እና ቀልጣፋ እንደሚያደርግ ብዙ ጥናቶች አመላክተዋል፡፡ ሆኖም ግን ይህን የእንቅልፍ ሰዓት ማራዘም በራሱ ጉዳት እንዳለው ልብ ይለዋል፡፡

ውድ ቤተሰቦች ልብ እንድትሉልኝ የምፈልገውና በግሌ የተሳሳተ አባባል እና አመለካከት የሚመስለኝ አንድ አቢይ ጉዳይ  አለ፤ ይህም ብዙዎቻችን እረፍትን  ጊዜ ማሳለፊያ  ብቻ ነው እንጂ የምንለው እና የምንቆጥረው እንጂ በህይወታችን ላይ ዓይነተኛ ሚናን እንደሚጫወት ድረጊት አይደለም፡፡  ግና ወዳጆጄ ይህን ጉዳይ  በደምብ ማጤን አለብን ይህንም ስል እረፍት በራሱ እንደ አንድ ዓቢይ  ነገር በመያዝ የህይወታችን አንድ አካል ማድረግ እንዳለብን ነው፡፡ ጠንካራ፣ ጎበዝ እና ለውጤት የሚታትር ሰው መሆን እጅግ የሚበረታታ ሰብዕና እና ባህርይ ነው ሆኖም ግን ይህ ነገር ገደቡን አልፎ ስራ ብቻ ላይ ከሆነ ትኩረታችን አዕምሮኣችንን እያደነዝንና አካላችን እያደከምን መሆኑን ከግምት ውስጥ በማስገባት ለዕረፈትም ጊዜ በመስጠጥ ልክ እንደመጥረቢያው እኛም ሁልጊዜ አዕምሮአችንን መሳል ይኖርብናል፡፡ ጽሁፌን በአብርሃም ሊንከን አባባል ልቋጨው ዛፍ ቁረጥ ብለህ 6 ሰዓታትን ብትሰጠኝ 4ቱን የምጠቀምበት መጥረቢያዬን በመሳል ነው፡፡

ሰላማችሁ ይብዛ…. መልካም ሳምንት

#Share
©(ቁምላቸው ደርሶ ©ዘ-ሳይኮሎጂስት)
@Psychoet
ጥንቃቄ አድርጉ! አደራ እንዳትበሉ!!

ከዲጂታል ቴክኖሎጂው መስፋፋት ጋር ተያይዞ በዚያኑ ያክል የዲጂታ ማጭበርበሮች ይከናወናሉ። በርካታ ሰዎች በዚህ የዲጂታል ማጭበርበር ብዙ ገንዘብ ተበልተዋል። ለትምህርት ይሆናችሁ ዘንድ የዛሬውን ገጠመኜን ላጫውታችሁ።

ዛሬ አንድ የሆቴል ቡኪንግ ስራ ኦንላይን ጋብዘውኝ ነበር። ከመጀመሪያው የማጭበርበር ስራ እንደሆነ ስላወኩኝ ስራ ፈላጊ መስየ ያዘዙኝን እያደረኩ ተከተልኳቸው። ስራው መጠነኛ እንደ ዌብሳይት አይነት ፕላትፎርም ተዘጋጅቶለታል። በበልተር ሆቴል ስም የሚሰራ ነው። ታስክ አንድ ሁለት ሶስት እና አራት ተብሎ ተመድቦለታል። የመጀመሪያውን ስራ ለመጀመር የ300 ብር ክፍያ ይጠይቃሉ። ይህንን ከፍሎ ስራዎቹን ክሊክ ክሊክ አድርጎ ለጨረሰ ወዲያው 600 ብር ወደ አካውንቱ ገቢ ይደረግለታል።

እኔም ይህንን ተስማምቼ ፍቃደኝነቴን ካረጋገጥኩላቸው በኋላ ለመጀመሪያ ዙር 300 ብር እንድከፍልና ወደ ስራ እንደገባ ጠየቁኝ። የ300 ብር የገቢ ደረሰኝ ሿሿ ላኩላቸው። 😁 አመኑኝ። የሆነች ጠቅ ጠቅ የምትደረግ ነገር ሰጡኝና 605 ብር እንደሸቀልኩ አሳወቁኝ። 600 ብር ወጪ አዘዝኩና ወደ አካውንቴ ገቢ አደረጉልኝ። 🥰

ከዚያ ከ አንድ እስከ አራት ስራዎች ላኩልኝ። አራተኛውን ስራ መረጥኩ። ያንን ስራ ለመስራት እስከ 5ሺ ብር ገቢ እንዳደርግ ጠየቁኝ። እዚህ ጋር እኔም ሁለተኛ ዲጂታል ማጭበርበር ልፈፅምባቸው ስል ሆቴሉ ገንዘቡ ወደ አካውንቱ እስኪገባ እና እስኪያሳውቀን መጠበቅ አለብን። ስለዚህ እየጠበቅን ነው አሉ። "ግዴለም የንግድ ባንክ ሲስተም ይሆናል" ምናምን ብል ያው 'ሌባ እናት ልጇን አታምንም' ይባል የለ?
"አይሆንም" አሉኝ። በዚህ ምክንያት ግንኙነታችን 6መቶ በር ተቀብየ እዚህ ላይ ቆመ።

ስራውን የሚሰሩት በርካታ ሰዎች ሆነው ነው። አንዱ ለአንደኛው አንደኛው ደግሞ ለሌላው አቀባብለው ነው ገንዘብ ማስገባቱ ላይ ያደረሱኝ። የቴሌግራም መጠቀሚያ ስማቸው ደግሞ ፈረንጅኛ ስም ነው። አሁን እኔ ጋር የ3 አጭበርባሪዎች የንግድ ባንክ አካውንት አለ። አንደኛው ሰውየ የቴሌግራም አካውንቱን ወዲያው አጠፋው። በዚህ ማጭበርበር ብዙ ሰዎች ብራቸውን ተበልተዋል። በቀን እስከ 5ሺ እና 10ሺ ብር ገቢ ታገኛላችሁ ብለው ያማልሏችኋል።

በእርግጥ ብዙዎች የሚበሉት ቁጭ ብሎ ገንዘብ ለማግኘት ካላቸው ጉጉት ነው። የሆነ ነገር ክሊክ አድርገን ገንዘብ የምናገኝ ቢሆን ኖሮ እንደ እኛ ኢንተርኔት ላይ አፍጥጦ የሚውል ሰው አልነበረም። ስለዚህ በቀን እስከዚህ ሺ ብር ገቢ ታገኛላችሁ ምናምን የሚሏችሁን ሰዎች አትመኑ። ተጠንቀቁ። ከፍሏችሁ ስራ ሊያሰራችሁ የሚፈልግ ሰው በፍፁም ከእናንተ ገንዘብ የሚፈልግበት ምክንያት የለም።

ሼር አድርጉትና ሌሎች ይማሩበት።
በአዲስ መኮንን
አንዳንድ ነገሮች ስለድብርት ፣ ራስን ስለማጥፋት

የሆነ ቀን ማታ ከክላስ እየተመለስኩ ሰፈር ልደርስ አካባቢ የቀለጠ ድንገተኛ ጩኸት ሰማሁ እና ጩኸቱ ወደተሰማበት ጊቢ ሮጬ ሔድኩ። አንድ በአስራዎቹ እድሜ የሚገኝ ልጅ ራሱን አጥፍቶ ተገኘ። ያሳዝናል አይደል? ከዚህ በላይ የምር ያሳዘነኝ የሰዉ response ነው!

በቤተሰቡ የድንጋጤ ጩኸት የተሰበሰቡ የመንደሩ ሰዎች አጠገቤ እንደቆሙ "ምን ሆንኩ ብሎ ነው አሁን?"፣ "የበርበሬ ወጪ የለበት የጨው፥ ቅብጠት ካልሆነ በቀር"፣ "ጨካኝ ነው ለቤተሰቦቹ እንዴት አያስብም?"... ሲሉ መስማት ይበልጥ ይሳዝናል።

አዕምሮ ነክ ችግሮች ትልቁ ጉዳታቸው እንደሌሎቹ በሽታዎች አለመሆናቸው፣ ማለቴ አካላዊ አለመሆናቸው ይመስለኛል። ብዙዎቹ ምልክቶች ከባህሪ ጋር ስለሚምታቱ፣ "እሱ/እሷ ልማዱ/ዷ ነው" እየተባለ ከመታለፍ ባለፈ የሚረዳ እና የሚረ'ዳ ሰው ማግኘት ይከብዳል። ወለም ያለህ እንደሆነ ግን "ልሽህ፣ ልደግፍህ" ባዩ ብዙ ነው።

ከልብ ስብራት ይልቅ የእግር ወለምታ more sense ይሰጠናል፤ ምክንያቱም ወለምታ physical evidence ሊቀርብለት ይችላል... ማለቴ አላምን ባይ እንኳን ካለ x-ray ተነስተህ ታሳየዋለህ። ግን የልብ ስብራትና የአዕምሮ መታወክ ታማሚው ሸፋፍኖ ሊደብቀው ከመቻሉም በላይ ቢናገሩት ራሱ አጉል የስም ተቀጥያ ያሰጣል በሚል ፍራቻ ዝምታን ያስመርጣል። "Am I being dramatic? Am I just seeking attention?" በሚሉ ጥያቄዎች ምክንያት አዕምሮን ዝም ለማሰኘት መጣር እና "normal" ለመሆን መሞከር የተለመደ ነው።

የድህነታችን ሰፊ እጅ እዚህም ጋር ሳይዳብሰን የቀረ አይመስለኝም። እንኳን በፊደል መቁጠሩ ያልገፉት ወላጆቻችን ቀርቶ ተምረናል የሚሉ እኩዮቻችን ብናስረዳቸው ብዙ የማይገቧቸው ነገሮች አሉ። ምክንያቱም እንኳን የአዕምሮ ደህንነት፣ በቀን ሦስቴ መብላት ራሱ እንደቅንጦት (luxury) የሚቆጠርባት ሀገር ውስጥ ነዋ የምንኖረው! ሌላውን ትተን "depression አይደለም ብሮ ... ርቦህ ነው ብላበት ይተውሀል" የሚሉ ፖስቶችን ስንት ጊዜ አየን?

በቀላሉ መፈወስ የሚችሉ ህመሞች ለከፋ የአእምሮ ህመም ወይም ለሞት ሲዳርጉ ከንፈር መምጠጥ ምንም አንደማይፈይድ ማህበረባችን ገና የገባው አይመስልም። እና አዎ Mental health is not a luxurious thing, it's a necessity!!

ፈረንጅ እግዜር ይስጠው እኛ የማናውቃቸውን ብዙ በሽታዎች በቅጥ ከማወቅና ከመሰነድ አልፎ መድሃኒቶቹንም ቀምሞ አዘጋጅቶልናል። ግን እኛ መታከም ለምን እንደምንፈራ አይገባኝም!

ጠበሉም ፀሎቱም ጋር መሄዱ ጥሩነቱ እንዳለ ሆኖ ሀኪም ጋር መሄድ ከኃጢአት እኩል የመቆጠሩ ነገር ያስገርማል። በጥቂት ፕሮፌሽናል እገዛ የሚስተካከሉ ችግሮች በዳተኝነት ምክንያት ሲብሱ ሲባባሱ ማየት ያሳዝናል። Anxiety disorders, personality disorders, depression and bipolar disorders, ADHD (attention deficit hyperactivity disorder)... የሚባሉትን አዕምሮ ነክ ሕመሞች ስማቸውን እንኳን በቅጥ የምናውቅ ስንቶቻችን ነን?

ብቻ We should normalize seeing professionals, getting treatment and taking medications!

እና ከሁሉም በላይ ስለራሳችን ስንል ራሳችንን ማበርታት ያለብን ይመስለኛል። You should be your own priority! I should be my own priority! በኛ መጎዳት ውስጥ የሚጎዱ ብዙ ሰዎች ቢኖሩም፣ መጀመሪያ የጉዳቱ ሰለባዎች እኛው ነን! "የእኔን ደህንነት የሚነካ የማንም expectation ቢሆን ገደል መግባት ይችላል!" ማለት መልመድ ያለብን ይመስለኛል። በቃ ለራሳችን መቆም አለብን!

ተስፋ እንዳለ ለራሳችን ማሳየት አለብን፣ አንዲትም እርምጃ ቢሆን ወደፊት ፈቀቅ ለማለት መታገል አለብን። የእኛን ያህል ማንም እኛን ሊረዳን አይችልም! I should stand for myself! You should stand for yourself!!

ግን ደግሞ ቢመርረንም ልንውጠው የሚገባን ሀቅ ያለ ይመስለኛል። ሁሉም ሰው ለየራሱ ሕይወት ተጠያቂ ነው! ምንም ብንፍጨረጨር ልንቀይረው የማንችለው ሀቅ ፣ ልናድናቸው የማንችላቸው ሰዎች አሉ አንዳንዴ። ስለዚህ ስላለፍነው እና ስላለፉት ራሳችንን እየወቀስን መኖር የለብንም። Everyone is responsible for his own actions!

የሚበጀን ስለወደፊቱ መጨነቅ ነው። በዙሪያችን ላሉ ሰዎች ግድ ይሰጠናል ወይ? ጓደኞቻችንን እንሰማቸዋለን ወይ? ሲደብራቸው "አለሁ፣ አይዞኝ" እንላቸዋለን ወይ? ሊደረግልን የምንፈልገውን ለሰዎች እናደርጋለን ወይ?

እኛ እግዜር አይደለንም፣ ለሁሉም ሰው መፍትሔ የለንም። ሁሉንም ሰው አድምጠን አንችለውም፤ ግን ቢያንስ ሁላችንም በዙሪያችን ላሉ ጥቂት ሰዎች concerned እንሁን።

Idk why I'm ranting all this nonsense. ምናልባት የሆነ ሰው ከጠቀመ ብዬ ነው!

እና If you're struggling, you should know this...You ain't alone! ብቻችሁን አይደላችሁም! ብዙ ታጋይ አለ! ምንም እንኳን "ሁሌም ከጎናችሁ እሆናለሁ" ምናምን ብዬ ቃል የምገባበት አቅም ባይኖረኝም። ግን I will try at least! Genuinely እርዳታ የምትፈልጉ ከሆነ ብዙ ሊረዷችሁ የሚፈልጉ ሰዎች እዚህ አሉ - Reach them out! ከሁሉ በላይ ራሳችሁን እርዱ! Stand for yourself!

እርሶ ወይም ወዳጅ ዘመድዎ በራስ ማጥፋት ሀሳቦች እየተጨነቁ ከሆነ እባክዎን በአቅራቢያዎ ወደሚገኝ ጤና ጣቢያ ወይም የስነ-ልቦና ማዕከል በመሄድ የባለሙያ ድጋፍ እና ሪፈራል ያግኙ።

ለአእምሮ ህክምና ተጨማሪ መረጃ: https://bit.ly/3KTRnDr

በYonathan Getachew (Software Engineer)
#ክፍል_15
#ሰዎች_እንዴት_ይወዱናል?
በሰዎች መካከል ያለ መሳሳብ / Interpersonal Attraction /
(ናሁሰናይ ፀዳሉ እና )
www.tg-me.com/psychoet

ሰዎችን እንዴት እንወዳቸዋለን?
የማህበረሰብ ሳይኮሎጂስቶች ለምን ሰዎችን እንወዳለን ለምንስ እንወደዳለን ብለው ያወጡትን በጥናት የተደገፉ ነጥቦች እንይ እስኪ፡፡እዚህ ጋር ግን ማፍቀር እና መውደድ የተለያዩ እንደሆኑና መውደድ የማፍቀር መነሺያው እንደሆነ ልብ ማለት ይገባናል፡፡

ሌላን ሰው ለመውደድ ምክኒያት የሚሆኑን ጉዳዬች እነዚህ ናቸው ፡፡

1. Physical attractiveness (ሳቢ ተክለ-ሰውነት) ነው፡፡ ብዙዎቻችን ቆንጆ የሆነ ነገር ሁሉ መልካም እና ጥሩ ይመስለናል (beautiful=good) ፤ ስለዚህ ሌሎች ተጨማሪ ምክንያቶች እንኳን እኩል ቢሆኑ መልከ መልካምና ያማረ ተክለ-ሰውነት ያላቸው ከሌላቸው ሰዎች ይበልጥ ተወዳጅነት ያገኛሉ (እዚህ ጋር ግን ውበት እንደ ተመልካቹ እና እንደ ሀገሩ ባህል ስለሚለያይ መለኪያችንም ይለያያል) ይሄ ነጥብ ግን ቀስ በቀስ አብረው ብዙ በሚቆዩ ሰዎች መካከል እየጠፋ ይሄዳል፡፡

2. Proximity (አካላዊ ቅርበት)
በአቅራቢያችን ከሚኖሩ ሰዎች ጋር መልካም የሆነ የጓደኝነት ስሜት እንፈጥራለን፡፡ ብዙ ጥናቶችም እንደሚያመላክቱትም በተመሳሳይ የመኖሪያ ስፍራ ከሚኖር ሰው ጋር የምንፈጥረው ወዳጃዊ ግንኙነት ወደ መውደድ እና መወደድ ይወስደናል ብለው ነው፡፡ (you became friendliest with those who lived geographically closest to you).

3. Mere exposure (አዘውትሮ የሚደረግ ግንኙነት
ወይም መስተጋብር )

ሲሆን በዚህም ከሰዎች ጋር የሚኖረን ተደጋጋሚ የሆነ ግንኙነት መልካም የሆኑ ስሜቶችን በመፍጠር ወደ መውደድ ይወስደናል፡፡ ይሄ ግን ሁልጊዜ የሚሰራ አይደለም ምክንያቱም ለመጀመሪያ ጊዜ የሚያጋጥመን መጥፎ የሆነ ግንኙነት በተደጋጋመ ቁጥር ለዛ ሰው የምናዳብረው መውደድ ሳይሆን ጥሩ ያልሆነ መጥፎ ስሜት ነው፡፡

4. Similarity (ተመሳሳይነት)

ከእኛ ጋር ተመሳሳይነታቸው የሚበዛ ሰዎችን እንወዳለን ሆኖም ግን በዚህ ነጥብ ላይ የሚነሱ ሁለት ዓይነት ተቃራኒ ሀሳቦች አሉ የመጀመሪያው Birds of the same feather fly together በግርድፉ አማርኛ የሰው ልጅ እሱን የሚመስለውን ይፈልጋል ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ opposite forces attract each other ሁለት ተቃራኒዎች ይፈላለጋሉ የሚሉ ናቸው፡፡የማህበረሰብ ሳይኮሎጂስቶች በዚህ ላይ ጥናት በማድረግ የትኛው ሀሳብ የተሻለ ትክክል ነው ወደሚል መደምደሚያ ደርሰዋል፡፡ በዚህም ሰዎች ከራሳቸው ጋር ተመሳሳይ ስነ ባህርይ፣ ስነ ልቡና፣ እሴቶችና የመሳሰሉት ያሏቸውን ሰዎች ይወዳሉ፡፡ ለዚህ ደግሞ መነሻው ተመሳሳይ በሆነ ሚዛን እንመዘናለን ተብሎ ስለሚታሰብ እና የሚወዱንን እና የሚመስሉንን እንወዳለን (reciprocity of liking) የሚል አስተሳሰብ ነው፡፡

5. Reciprocal Liking (መልሶ መውደድ)

ብዙ ጊዜ ሰዎች የሚወዷቸውን የሚያደንቋቸውን መልሰው የመውደድ ሁኔታ አለ፡፡ በተጨማሪም ሰዎች እንደወደዱን ስናውቅ እኛሞ የበለጠ እንዲወዱን ራሳችንን ወደሚፈልጉት ሁኔታ የመዉሰድ ዝንባሌ አለ፡፡

6. Complementarity ተሟሟይነት (ጎዶሎአችንን የሚሸፍን)

ብዙ ሰዎች ጉለታቸውን የሚያጎላ ሳይሆን የሚሞላ ሰው ይፈልጋሉ ፡፡

ሰላማችሁ ይብዛ………
www.tg-me.com/psychoet
_________❖

ይህ ፅሁፍ ለብዙ ሰው እንዲደርስ ሁላችንሞ ባለንበት የFacebook/Telegram ግሩፕ ውስጥ #ሼር እናርገው 💛

ስለ ሳይኮሎጂ የበለጠ ለማወቅ ፔጁን ይከታተሉ ለወዳጆችዎ ያጋሩ

ዕውቀት ከአሉታዊ የአስተሳሰብ እስር ቤት ነፃ ያወጣል !
የሳምንት ሰው ይበለን!
እወዳችኅለሁ !
ናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ
__________❖
ክፍል 16
#Emotional_Intelligence & Communication
#የስሜት_ብልሃትና_ተግባቦት
(በናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ)


የስሜት ብልህነት ማለት ስሜታችንን የማወቅ ፣ የመረዳት የመምራት ችሎታ ነው ፡፡ ጥሩ የስሜት ብልሀት ያላቸው ሰዎች የተመሰገኑ ፣ በማንኛውም ሁኔታ የተረጋጉ ፣ የሩጫ ህይወት የማይመሩ ፣ የበለጠ ደስተኛና ራሳቸውንም ሆነ አካባቢያቸውን የሚመሩ ናቸው ፡፡

በህይወታቸው በጣም ደስተኛና ስኬታማ ከሆኑ ሰዎች አንዱ መገለጫቸው ያለቸው የስሜት ብልሃት ( Emotional Intelligence ) ነው ፡፡ ብዙ ጊዜ ሰዎች ከሚሰሩበት መስሪያ ቤት ሙያውና ችሎታው እያላቸው በባህሪ ምክንያት ይሰናበታሉ ፡፡ ከዚህም በተጨማሪ ጥሩ ሀሳብ እያላቸው ባላቸው ባህሪ ምክኒያት ሰሚ ያጡ ፣ ተቀባይነት ያጡ ሰዎች ይኖራሉ ፡፡

#ለዛሬ እነዚህ የተግባቦትና የስሜት ብልሀት አለመኖር በሕይወታችን የሚያመጡትን ችግር እንመልከት ፡፡

እኔ አንዱን ድግሪዬን በማኔጅመንት ስሰራ የመመረቂያ ጽሑፌ (Competency development in business areas ) የሚል ነበር ፡፡ በዚህ ጥናት ያገኘሁት አንዱ ግኝት ሰዎች ለቢዝነሳቸው መውደቅ አንዱ ምክንያት ያላቸው አነስተኛ #የተግባቦትና #የስሜት_ብልሀት ነው ፡፡ በእርግጥ ተግባቦትም ሆነ የስሜት ብልህነት ሳይንሳዊ የሆኑ መንገዶችን በመጠቀም ማሳደግ ይቻላል ፡፡

#የስሜት_ብልሃትና_ጥሩ_ተግባቦት_የሌላቸው_ሰዎች_መገለጫዎች

★የራሳቸውን ስሜት አይቆጣጠሩም ( በቀላሉ ይናደዳሉ ፣ ይበሳጫሉ ፣ ከልክ ያለፈ ቁጣ ይታይባቸዋል )

★ከሰው ጋር ተግባቢ አይደሉም ፣ ፍርሀት ጭንቀት ይታይባቸዋል ፣ ስለ ራሳቸው አሉታዊ አመለካከት የላቸውም

★በትንሽ ነገር አብዝተው ያዝናሉ

★በአካባቢያቸው ያሉ ሰዎችን ባህሪ እና ስሜት ስለማይረዱ ፣ ብዙ ጊዜ ከሰዎች ጋር በሀሳብ ፣ በወሬ የመጋጨት ሁኔታ ይታይባቸዋል

★ሰው ስለነሱ ስላለው አስተሳሰብ አብዝተው ይጨነቃሉ ፣ ይረበሻሉ ፡፡

★ሃሳባቸውን በድፍረት አይገልፁም ፣ እየተጎዱ ከጉዳቱ መውጣት እየቻሉ ዝምታን ይመርጣሉ ፣

★ለውሳኔዎች ከተገቢው በላይ ይቸኩላሉ፣ በወሰኑት ነገር ለመጸጸት ደግሞ የመጀመሪያ ናቸው

ከላይ የዘረዘርኳቸው መገለጫዎች( የስሜት ብልሃትና ጥሩ ተግባቦት ክህሎት አለመኖር) የሚያመጣቸው ጉዳቶችና የባህሪ መገለጫዎች ናቸው ። በእርግጥ እነዚህ ሁሉ መገለጫዎች ሳይኮሎጂካል ህክምና አላቸው ፡፡

ስለዚህ ከላይ የጠቀስኳቸውን ችግሮች በራሳችሁ ላይ የምታዩ ሰዎች ተስፋ አትቁረጡ ፡፡ በጥቂት ጊዜ ጥሩ የሆነ ተደጋጋሚ ሳይኮሎጂካል ልምምዶችን በማረግ መዉጣት ይቻላል ፡፡
___

፠፠__፠፠

ይህ ፅሁፍ ለብዙ ሰው እንዲደርስ ሁላችንሞ ባለንበት የ Telegram / Facebookግሩፕ ውስጥ #ሼር እናርገው 💛

በቴሌግራም በዚህ ታገኙኛላችሁ 🚙 www.tg-me.com/Psychoet 👍


ዕውቀት ከአሉታዊ የአስተሳሰብ እስር ቤት ነፃ ያወጣል !
ቸር ሰንብቱ!
፠፠__፠፠
ሳምንት ሰው ይበለን!
#ሀሙስ 14

አድናቆት

ስለእራሱ ጥሩ ነገር እየተነገረው ያደገ ልጅ ማድነቅን ይማራል
አግባብነት ያለው ማበረታቻ እያገኘ ያደግ ልጅ በእራስ መተማመንን ይማራል
መቻቻል በሰፈነበት ሁኔታ ያደገ ልጅ ትዕግስተኝነትን ይማራል
ልጅ ከአድሎ ነጻ በሆነ ሁኔታ በአግባቡ ካደገ ፍትህን ይማራል
ልጅ ዋስትናና ደህንነት በተሞላበት ኑሮ ካደገ ሰውን ማመንን ይማራል
ልጅን በማንነቱ ተቀብለን በማቅረብ ካሳደግነው ምሉዕ ፍቅር ከአለም ይማራል
ጥላቻ በተሞላበት አካባቢ ያደገ ልጅ ጠባጫሪነትን ይማራል
ልጅ በሃፍረት ካደገ የጥፋተኝነት መንፈስን ይማራል

…. እንዳለው ዶርቲ ሎው

በየትኛውም ስፍራ የሚኖር የሰው ልጅ ህጻንም ይሁን አዋቂ አድናቆትንና ሙገሳን ይወዳል እንዲሁም ይፈልጋል፡፡ መደነቅ በሰዎች ዘንድ ትኩረት ማግኘታቸንን ስለሚያመላክት ተደናቂው ክብርና የመንፈስ ከፍታ ይሰማዋል፡፡ “አንበሳ ፣ ጎበዝ ፣ ጀግና ፣ በጣም ድንቅ ስራ ነው የሰራኸው…..ወዘተ” ሰዎች አድናቆትን ለመግለጽ የሚጠቀሙባቸው ቃላት ናቸው፡፡

አድናቆት ተስፍ ለቆረጡና ምንም ማድረግ አንችልም ብለው ለተቀመጡት እንደ ጉዞ ስንቅ በማገልገል እንደገና ተስፋቸውን አለምልመው ወደ ተሻለ ደረጃ እንዲደርሱ ይራዳቸዋል ይላሉ ፡፡

ወጣት ልጆችን እንዴት እናድንቃቸው?

ትልቁ ትኩረትና ጥያቄ ልጆችን ማድነቅ ያስፈልጋል የሚለው ሳይሆን እንዴት እናድንቃቸው የሚለው ነው፡፡ ብዙ የምርምር ስራዎች እንደሚያመለክቱት የልጆችን የስራ ሂደት ማድነቅ ልጆች ጠንክረው እንዲሰሩ ፤ እንዲማሩ ፤ እንዲመራመሩና ስለ ችሎታቸው አወንታዊ አመለካከት እንዲኖራቸው ይረዳል፡፡ በተጨማሪም በግልጽነትና በእውነተኝነት ላይ የተመሰረት አድናቆት የልጆችን በእራስ መነሳሳት ያሳድጋል፡፡ ወጣት ልጆችን ለማድነቅና ለማበረታታት ከዚህ የሚከተሉት ነጥቦች ወሳኝነት አላቸው፡-

ስለ ልጆችች ስራና ጥረት መግለጽ፡- ፍርደ ገምድልነት የሌለው ውሳኔ በመስጠት የስራዎቻቸውን ጥረት ማድነቅ

ለአወንታዊው ስራና ጥረት ትኩረት መስጠት

ተግዳሮት ለሌለውና ብዙ ጥረት ለማይጠይቅ ስራ አድናቆትን መቆጠብ

አድናቆቱና ስራው ተመጣጣኝ መሆን አለበት

አግባብነት ያለውን ድርጊት በመምረጥ አድናቆትን መስጠት

በጊዜ ሂደት አድናቆትን መቀነስ ምክንያቱም ልጆች በአድናቆት ላይ ጥገኛ በመሆን ለመደነቅ ብቻ ሲሉ አንድን ነገር እንዲከውኑ ስለሚገድባቸው፡፡

አድናቆት ተፈጥራዊ ሂደትን ተከትሎ መቅረብ አለበት ከበጎና ከመልካም ድርጊት በኋላ የሚከተል፡፡

በአጠቃላይ የአድናቆት ዋንኛው ግብ ልጆች በእራሳቸው ተነሳሽነት አንድን ድርጊት እንዲከውኑና ተግዳሮቶችን በመቋቋም ጥገኝነትን አስወግደው ወደ ሚፈልጉት የዕድገት ምዕራፍና ውጤት እንዲሸጋገሩ ማስቻል ነው፡፡ እናንተስ በአድናቆት ወይስ በትችት ነው ያደጋችሁ እስቲ ያስከተለባችሁን አወንታዊና አሉታዊ ተጽእኖዎችን አካፍሉን!? ሻሎም

በአንቶኒዩ ሙላቱ ©Zepsychology
#ለተጨማሪ የሳይኮሎጂ ነክ ትንታኔና መረጃ ይህን ገጽ #ሼር #ላይክ ያድርጉ 
@psychoet
ክፍል 17

የአእምሮ ጤንነትን የሚጠብቁና የሚያሳድጉ 5 ተግባራት
(በናሁሰናይ ፀዳሉ)

የአእምሮ ጤንነት ለሰው ልጅ ወሳኝ የሆነ የሕይወት ማገር ነው፡፡  ሰው እንደ ሰው ፣  ህዝብ እንደህዝብ ፣ ሀገርም እንደሀገር እንዲቀጥልና እንዲያድግ ዋናውን ሚና የሚጫወተው የአዕምሮ ጤንነት ነው ፡፡ በአለማችን ሆነ በአገራችን  ብዙ ሰዎች ለአዕምሮ (ሥነልቦናዊ) ቀውስ እየተጋለጡ ይገኛሉ  በዚህም ብዙዎች ቀናቸውን በድብርት ፣ በፍርሀት ፣ ተስፊ በመቁረጥ ፣ ስለ ነገ አሉታዊ ነገሮችን በማሰብ ያሳልፉሉ ብሎም ብዙ ሰዎች ራሳቸውን አጥፍተዋል ፣ ከስራተቸው ለቀዋል ፣ ማህበራዊ ህይወታቸውን አቁመዋል ... ብዙ ብዙ ፡፡

ከሥነልቦና ቀውሶች ለመውጣት ወይንም የአእምሮ ጤንነታችንን ጠብቀን ለመቆየት የሚያስችሉን 5 ተግባራትን እንመለከታለን፡፡

1. አካላዊ ጤንነትንና ንቃትን ማዳበር

አካላዊ ጤንነትና ንቃት ማለት ሁለንተናችን የተመጣጠነ እድገት ሲኖረውና ሰውነታችንን ከተለያዩ በሽታዎች ሲጠበቅ ማለት ነው፡፡ አካላዊ ጤንነት ሁልጊዜ ከአዕምሮ ጤንነት ጋር ይያያዛል ፡፡ በዚህ ንቃት ውስጥ የሚዳብር በራስ መተማመን ፣ ማቀድና መፈፀም እንዲሁም ችግሮችን በስልት መፍታት በሰውነታችን ውስጥ የኬሚካሎች ለውጥ እንዲኖር ያደርጋል ይህም ለኬሚካል ለውጥ በባህሪያችንና በስሜታችን ላይ አወንታዊ ለውጥን ያመጣል፡፡

📌ማድረግ ያለብን ነገሮች

ባለንበት ቦታ የአካል ብቃት እንቅስቃሴ ማድረግ፣ የተለያዩ የሚያስደስቱንን ስራዎች በቤታችን ሁነን መስራት ፣ ጥሩ መጸሐፍትን ማንበብ ፊልሞችን መመልከት ፣በትንሹ እቅድ ማቀድና መተግበርን መለማመድ፡፡

2. አዳዲስ ክህሎቶችን መማር

ብዙ ጥናቶች እንደሚያሳዩት አዳዲስ ክህሎቶችን መማር ለአዕምሮ ጤንነትና እድገት ወሳኝ እንደሆነ ነው ፡፡ አዳዲስ ክህሎቶችን መማር በራስ መተማመናችንን ያሳድጋል ፣ የሕይወትን አላማ የቀለጠ እንድንረዳ ያግዛል በተጨማሪም ከሌሎች ሰዎች ጋር የትውውቅና የስራ እድል ይፈጥራል፡፡

📌ማድረግ ያለብን ነገሮች
አዳዲስ ክህሎቶችን ለመማር ዩኒቨርስቲ / ኮሌጅ መግባት ፣ ብዙ ገንዘብ ማፍሰስ አይጠይቅም ባሉበት ሆኖ በቅርብ በሚቀኙ ቁሳቁሶች በመጠቀም መማር ይቻላል ፡፡

በዚህ ጊዜ እቤቱ ያለ ሰው የተለያዩ ምግብ አሰራሮችን በየቀኑ መማር ፣ ዩቲዩብ ላይ የተለያዩ ቲቶሪያሎች በማውረድ በነፃ ክህሎቶችን መግኘት ፤ በነፃ ትምህርት የሚሰጡ Online ትምህርቶችን መከታተል በተጨማሪም አዳዲስ ልማዶችን መሞከር ለምሳሌ መጻፍ ፣ መሳል ፣ጥልፍ መስራት አዳዲስ የእስፖርት አይነቶችን መለማመድና እቤት ውስጥ የተበላሸ ነገሮችን መጠገንና ማስተካከል ይቻላል፡፡

በመስሪያ ቤት ያለ ሰው አዳዲስ ሀላፊነቶች
ስራችን ላይ ጨምሮ ቢወጣ ( እዚህ ላይ ግን አብዛኞቻችን ስለምንሰንፍ አሁን ያለኝን ሃላፊነት ራሱ በስነስርአቱ አልተወጣንም ብለን እናስባለን ) ግን አዲስ ሀላፊነት መቀበል የበለጣ የሚከብድ ነገር አይደለም እንዲያውም ቋሚ ሃላፊነቱን የበለጠ እንድንወጣ ይረዳናል፡፡

3. ለሌሎች ማካፈል

ከሚቀበል ይልቅ የሚሰጥ ደስተኛ ነው ፡፡ ሁሉም ሰው ወይ ለሀይማኖቱ አልያም ለሕሊናው ሲል መለገስ / ማካፈል ይወዳል ፡፡ ይህም የሆነው ሰዎች ከሰጠን / ለሌሎች ካካፈልን በኀላ በውስጣቸን የሚፈጠረው የኬሚካል ለውጥ ምክንያት በጣም ደስተኛ ስለምንሆን ነው ፡፡ መስጠት አወንታዊ አመለካከትን ይፈጥርልናል ፣ ከፈጣሪ ጥሩ መልስ እንድንጠብቅ ያደርጋል ፣ ለራሳችን ያለንን አመለካከት ያሳድግልናል አላማችንን የበለጠ ለመፈፀም ያተጋናል ፡፡

📌ማድረግ ያለብን ነገሮች

*ሰዎች ላደረጉልን ነገሮች ምስጋናን መለገስ
*በቅርብ ያሉ ሰዎችን ስለውሎአቸው መጠየቅ
*ጊዜያችንን ለሚፈልጉ ሰዎች መገኘት
*ካለን ገንዘብ ፣ ችሎታ ለሌሎች ለተቸገሩ ወገኖች መስጠት
*በመጨረሻም ዋናው መስጠት የምንችለው በጎ ፍቃድ አገልግሎቶች ላይ መሰማራት


4. ከሰዎች ጋር ያለውን ግንኙነት አጥብቆ መያዝ

ጥሩ ወዳጅነት / ዝምድና አይምሮን ከሚያድሱ ነገሮች ቀዳሚው ነው ፡፡ ከሰዎች ጋር ጥሩ ግንኙነት መፍጠር ለራሳችን ያለንን አመለካከት ከማሳደጉ በተጨማሪ አስደሳች ጊዜያቶችን እንድናሳልፍ ዕድል ይሰጠናል ፡፡ ከሰዎችም የድጋ ስሜት እንድንቀበልና እንድንሰጥ ይረዳናል ፡፡

📌ማድረግ ያለብን ነገሮች

*ከቤተሰቦቻችን ጋር ጊዜ ሰተን የጫዎታ ፣ የመወያያ የመመገቢያ ጊዜ ማሳለፍ ፡፡
*ድጋፍ የሚፈልጉ ጓረቤት ዘመዶችን ጊዜ ሰተን መጠየቅ ፣ ሰዎችን በሆስፒታልና በእስር ቤት መጎብኘት፡፡
*ካገኘናቸው ጊዜያት ያስቆጠሩ ወዳጆቻችንን ጋር መደወል።
*በዝንባሌያችን መሰረት በአካባቢያችንም ሆነ በሀገር አቀፍ ደረጃ ያሉ የተለያዩ ሕብረቶች ውስጥ መሳተፍ፡፡

5. ከነገና ከትናንት ይልቅ በአሁን ባለው ነገር ላይ ትኩረት መስጠት

ከምንም በላይ አሁን ላሉበት ነገር ትኩረት መስጠት የአዕምሮ ጤንነታችን እንዲጠበቅ ያደርጋል ፡፡ ብዙ ሰው አሁን ባገኘው ነገር እንደመደሰትና ፈጣሪን እንደማመስገን ትናንት ስለደረሰበት በደል እያሰበ ያዝናል ፣ ትናንት ስለሰራው ስህተት እየተፀፀተ ይኖራል ። ከዚህም ሲቀጥል ስላልኖረበት ነገ መኖሩን ሳያውቅ ከልክ በላይ "ምን እሆን ?"ብሎ እየተጨነቀ ዛሬውን ያበላሻል ፡፡

ሁልጊዜ አሁን ላይ ትኩረት መስጠት ሕይወትን የበለጠ እንድንረዳና እንድንወድ ያረገናል፡፡

#ማድረግ ያለብን ነገሮች

ትናንት በሕይወታችን የሆኑ መጥፎ ነገሮች መርሳት ባንችልም እነዛ ነገሮች ግን ዛሬ ላይ መተው ሕይወታችንን እንዲረብሹ አለመፍቀድ፡፡

ምንጭ : Mental wellbeing & my personal reflection
መልካም ቀን ይሁንላችሁ!

ጽሑፉ ለናንተ ከጠቀማችሁ ሎችም እንዲጠቀሙበት #Share በማድረግ አካፍሉ! ማካፈል ከዚህ ይጀምራል፡፡
www.tg-me.com/psychoet
#ሀሙስ 15

ለለውጥ መነሳሳት

በአንድም ይሁን በሌላ ምክንያት ዕለት ተዕለት በሚኖራችሁ ህይወት ውስጥ ሁሉም ነገር አስጠልቷችሁ ፤ ምንም ለማድረግ ወኔና ፍላጎቱ ጠፍቷችሁ መነሳሳት ከእናንት ርቆ ያውቃል? እንግዲያውስ ህይወትን በኃይልና በመነሳሳት መንፈስ እንደገና ለመጀመር እነኚህን ነጥቦች ይተግብሯቸው፡፡

1. የህይወትን ዓላማ ማወቅ፡- እያንዳንዳችን ወደዚህች ምድር የመጣነው ያለ ዓላማና ምንክንያት ስላልሆነ ለእኛ በህይወት መኖር ለራስና ለሌሎች የሚያበረክተው ጥቅም ስላለው በህይወት የመኖራችንን ዓላማ ጠንቅቀን ማወቅ ያስፈልጋል፡፡

2. ጊዜን በአግባቡ መጠቀም፡- ለሰው ልጅ በነፃ ከተሰጠው የተፈጥሮ ሃብት ውስጥ ጊዜ ነው፡፡ ማድረግ የምንፈልገውንና መሆን የምንመኘውን በጊዜ ቀመር ማስቀመጥ ወደ ምንፈልገው የዕድገት ደረጃ ይመራናል፡፡ ጊዜ ሰይፍ ነው ይቆርጣል ያቆስላል ፤ ጊዜ መድኃኒት ነው ከውድቀት ያነሳል፡፡ “ጊዜን ስሩበት እንጂ አይስራባችሁ!”

3. ተስፋ፡- ዛሬ በእጃችን መዳፍ ውስጥ ናት የስኬትንና የውድቀትን ካርድ ልንመዛባት እንችላለን፡፡ ዛሬ ባይሳካ ነገ ደግሞ ሌላ ቀን ነው ፤ ህይወት ሎተሪ ናትና ደጋግመን መሞከር ያስፈልጋል፡፡ የተሻለ ነገን ለማሰብ ተስፋ ትልቅ ስንቅ ነው፡፡

4. ውድቀትን አለመፍራት፡- ብዙዮች ጠንክረው ላመስራታቸውና ህይወትን በተሻለ መልኩ ላለመኖራቸው ትልቁ ምንክንያት ውድቀትን መፍራት ነው፡፡ ነገር ግን ሰዎች ወድቀው በተነሱ ቁጥር ጠንካራ መንፈስን እንደሚላበሱ ጥርጥር የለውም፡፡ ገና ለገና ባይሳካልኝና ብወድቅ እሳ ብሎ ከመጨነቅ ተፋልሞ ወድቆ መነሳት ይሻላል፡፡

5. በዕቅድ መመራት፡- ህይወት ዝብርቅር እንድትል ከሚያደርጉ ነገሮች ውስጥ አንዱ በዕቅድ አለመመራት ነው፡፡ በዕቅድ መመራታችን በህይወታችን ውስጥ ያሳካናቸውንና ያላሳካናቸውን ነገሮች እንድናውቅ ስለሚረዳን ምን ማድረግ እንዳለብን አቅጣጫ ያሳየናል፡፡

6. አወንታዊ አስተሳሰብ፡- በአሉታዊ አስተሳሰብ ጫና ውስጥ ያሉ ሰዎች የመስራትና የመነሳሳት ስሜታቸው ቀዝቃዛ ነው፡፡ ከብርሃን ይልቅ ጨለማው ቀድሞ ስለሚታያቸው ስልቹዎች ናቸው፡፡ መልካም ማሰብ ወደ መልካም ይመራል ድርጊት ከተጨመረበት፡፡

7. ፍላጎትን መቀነስ፡- መስራትና መሆን የምንፈልጋቸው ነገሮች በበዙ ቁጥር አንድ ነገር ላይ አእምሮአችንንና ጊዜአችንን አሳርፈን መስራት ስለማንችል በምኞት ብዛት ራዕይአችን፤ ጊዜአችንና ጉልበታቸን በከንቱ ይባክናል፡፡

 8. ትዕግስት፡- የአንድን ነገር ውጤትና ለውጥ በቅጽበታዊ ጊዜ ውስጥ መፈለግ መነሳሳትን ይገድባል፡፡ በትዕግስት የሚጠባበቁና የሚጥሩ ከሆነ ቢዘገይ እንጂ መድረስ ያለባችሁ ቦታ ከመድረስ የሚያግዳችሁ የለም፡፡

9. ዛሬውኑ መጀመር፡- ስራዎቻችንንና ዕቅዶቻችንን ለማሳካት ከነገ ከመጀመር ይልቅ ከአሁኗ ደቂቃ መጀመር ትልቅ ጥቅም አለው፡፡ የነገን ለነገ በመተው የዛሬን በትንሽ በትንሹ መጀመር ወደ ትልቁ ደረጃ ይመራናል፡፡

 10. ስራችንን በደስታ መጀመር፡- ውስጣዊ ስሜቶቻችንን ለስኬቶቻችን ትልቅ አስተዋጽኦ ስለሚኖራቸው የምንሰራውን ስራ መውደድ ይጠበቅብናል፡፡ የማንወደው ስራ ቢሆን እንኳን የምንወደውን ስራ እስክናገኝ የአሁኑን ስራችንን መውደድ አለብን፡፡

#Share #Like
www.tg-me.com/psychoet

(በአንቶኒዮ ሙላቱ)
©Zepsychology
ክፍል 18

በአዲስ መልክ ስራ ጀምረናል

ብዙውን ጊዜ ይህን ማስታወቂያ የምንመለከተው በምግብ ቤቶች ላይ ነው፡፡ ገበያቸው ሲቀዘቅዝ፤ ደንበኞቻቸው ከጊዜ ወደ ጊዜ ሲመናመኑና መክሰር ወደሚባለው ደረጃ ላይ ሊደርሱ ሲሉ ለተወሰነ ቀናት ወይም ሳምንታት አገልግሎት መስጠት ያቋርጡና ቤቱን በማደስ አንዳንድ ጭማሪ ነገሮችን በማካተት የቀድሞና አዳዲስ ደንበኞችን ለመሰባብ ሲሉ በአዲስ መልክ ስራ መጀመራቸውን ባነር ወይም የሚታይ ማስታወቂያ ለጥፎ በማብሰር ስራቸውን ይጀምራሉ፡፡

ይህ የሚያመለክተው በህይወት ጉዞ ሁሌ ወደፊት ብቻ ሳይሆን አንዳንዴም ያሳለፍነውን ደስታ፤ መከራና ውጣ ውረድ ዞር ብሎ መመልከት ለዛሬ ማንነት አስተዋጽኦ እንዳለው ለማጠየቅ ነው፡፡

ትናንት ሞክረናቸው ያልሰመሩልን የህይወት ውጥኖችን ተስፋ ባለመቁረጥ በአዲስ ሞራልና ወኔ እንደገና እንሞክረው፡፡ በህይወታችን ውስጥ በአዲስ መልክ መጀመር ያለብን ነገሮች ምንድን ናቸው?

ትዳራችን እንዴት ነው?

አንቺ ትብሽ እኔ እብስ ተብሎ የተጀመረ ነገር ሁሉ በጊዜ እርጅና ይፈዛል አልፎ ትርፎም ቀለሙ ይወይባል፡፡ ትናንትና የነበረው ፍቅር፤ መረዳዳት፤ መከባበር፤ መደማመጥና ትዕግስት በጊዜ ሂደት ጠፍቶ ሊሆን ይችላል፡፡ በተጣማሪዎቹ መካከል አንደኛው ወይም ሁለቱም የመጠቃት ስሜት እየተሰማቸው ሊሆን ይችላል፡፡ እስቲ የቀደመውን ጊዜ ፍቅርና መልካምነት በማሰብ የዛሬ መጠቃትንና የመገፋት ስሜትን ለአንድ አፍታ በመተው ትዳራችሁን/ፍቅራችሁን እንደ ገና በአዲስ ምዕራፍ ለመጀመር ሞክሩት፡፡ በትዝታ ብቻ የቀረው ፍቅራችሁና የትዳራችሁ መልካምነት ወደ ቀደሞ ክብሩ ይመለሳል፡፡ ግድ የላችሁም ከቻላችሁ ሁለታችሁም ይህ የማይቻል ከሆነ አንዳችሁ በመጀመሪያ ኃላፊነት በመውሰድ ትዳራችሁን/ፍቅራችሁን እንደገና ስሩት፤ በውጤቱ ትደነቃላችሁ፡፡

ማኅበራዊ ህይወታችሁ?

ማኅበራዊ ህይወት መልካም እንደሆነ ሁሉ አንዳንዴ ባልተፈለገና ባልተጠበቀ አቅጣጫ ያመራና ከወዳችነት መንፈስ ወደ ጠላትነት የመሸጋገር ዕድሉ ከፍተኛ ነው፡፡ አንዱ በዳይ ሌላኛው ደግሞ ተበዳይ ሆኖ በአንጀት መቆሳሰል የግንኙነት ሰንሰለቱ ተበጣጥሶ ይሆናል፡፡ የተራራቃችሁትና የተቆራረጣችሁት ሰው ምንም እንኳን ቢያጠፋና ቢበድል በህይወታችሁ አስፈላጊ ነው ብላችሁ የምታምኑት ዓይነት ሰው ከሆነ እስቲ አንድ ዕድል ስጡትና ማኅበራዊ ህይወታችሁን በማደስ እንደገና ሞክሩት፡፡

ስራችሁስ?

በግልም ይሁን ተቀጥራችሁ በምትሰሩት ስራ ውጤታማና ተሸላሚ ለመሆን ብዙ ርቀት ተጉዛችሁ ፤ ለፍታችሁ፤ ወዛችሁን አሟጣችሁ በስተመጨረሻም የልፋታችሁ ውጤት ሲታይ ትርፍና ኪሳራው እንደማይታወቅ ነጋዴ ዓይነት ሆኖባችሁ ይሆናል፡፡ ዛሬ ላይ ቆም በሉና ሌሎቹ ሲሳካላቸው እኔ ያልተሳካልኝ ምክንያት ምንድን ነው ብላችሁ በመጠየቅ በአዲስ መንፈስና ወኔ ጀምሩት፡፡ እስቲ በትናንትናው ጅምርና ልምድ ሳይሆን በሌላ አተያይ ችግራችሁ ምን እንደነበር ለመፈልፈል ጥረት አድርጉ፡፡ ከዚያ በአዲስ መልክ ስራችሁን ጀምሩ በእርግጠኝነት ይሳካላችዋል፡፡

አመለካከታችሁ?

ለዘመናት ሰው ለምን ይጠላኛል ብላችሁ እራሳችሁን በሃዘን፤ በትካዜ እንዲሁም እራስን ከማኅበራዊ ህይወት እስከ ማግለል ደርሳችሁ በብቸኝነት ስሜት እየተገረፋችሁ ሊሆን ይችላል፡፡ ግድ የለም ሰው ለምን ይጠላኛል ሳይሆን የሚጠላብኝ ነገር ምንድን ነው ብላችሁ እራሳችሁን ፈትሹ፡፡ አንዳንዴም ሌላው ሰው ምንም ሳይለን እኛው እራሳችን በምንፈጥረው ምክንያት የለሽ አስተሳሰብ ሌሎች እንደሚጠሉን ልናስብ እንችላለን፡፡ አእምሮአችሁን በአወንታዊ አስተሳብ በመገንባት ስለእራሳችሁ ጥሩ ምልከታ ይኑራችሁ፡፡ ከዚያ ሁኔታዎችን እንደ አመጣጣቸው በአዲስ መልክ ለመመለስ ሞክሩ ፤ ደስታንም ታገኛላችሁ፡፡

ተስፋ መቁረጥ ይታይባችዋል?

ሁሉም ነገር በእናንተ ተቃራኒ የሚሄድ ከሆነ እናንተ እራሳችሁ የተሳሳታችሁት ነገር ሊኖር ስለሚችል ቆም ብላችሁ እራሳችሁን መርምሩ፡፡ ትናንት ብትወድቁና ባይሳካላችሁ ዛሬ ደግሞ ሌላ ቀን ነው እንደገና ሞክሩት፡፡ ከአይሳካልኝም፤ ይሳካልኛል፤ ከአልችልም እችላለሁ፤ ሁሉም ነገር ጨለማ ነው ብሎ ከማሰብ ከጨለማው በኋላ ጽልመቱ በብርሃን ጸዳል ይገፈፋል ብሎ ማሰብና አዲስ ተስፋ መሰነቅ፡፡ ህይወት ሎተሪ ናት ደጋግመህ ሞክራት ይባል የለ፤ ተስፋ ባለመቁረጥ ጉዞአችሁን አንድ በማለት እንደገና ጀምሩት፡፡

ሱሰኝነት?

አዲስ ዓመትና አዲስ ቀን በመጣ ቁጥር ከሱስ ለመገላገል ለእራስችሁ ቃል በመግባትና ምሎ በመገዘት ጥራችሁ ጥራችሁ ወደ ምትጠሉት ወጥመድ ትብታብ ውስጥ ወድቃችሁ ይሆናል፡፡ ትናንትና ሱስን ለመተው በመጀመሪያ አእምሮአችሁን ሳታሳምኑ ቀጥታ ድርጊቱን በመተው ጀምራችሁ ይሆናል፡፡ ዛሬ ግን መጀመሪያ እንደምትችሉ  አእምሮችሁን አሳምኑ ከዚያ ድርጊቱን በአንዴ ሳይሆን ቀስ በቀስ ለመተው በአዲስ አስተሳሰብና መንገድ ጀምሩት፡፡ በእርግጠኝነት መድረስ ወደ የምትፈልጉበት ቦታ ላይ እንዳትደርሱ እንቅፋት ሆኖ የሚይዛችሁ ነገር የለም፡፡ ከእናንተ የሚጠበቀው ቁርጠኛ መሆን ብቻ ነው፡፡

በአጠቃላይ በህይወት መንገድ ሁሌ ወደ ፊት ብቻ መሄድ ሳይሆን አንዳንድ ጊዜ ከተነሱበት የህይወት አቅጣጫ እራስን ዞር ብሎ በመመልከት እንደገና እንደ አዲስ የሚጀመሩ ምዕራፎች አሉ፡፡ ስለዚህ በህይወቴ ይህንና ያንን አጥቻለው ብላችሁ የምታምኑትንና እንደገና ለማግኘት የምትመኙት ነገር ካለ ያለማቅማማት ህይወትን በአዲስ መልክ ጀምሯት ይሳካላችዋል፡፡

(በአንቶኒዮ ሙላቱ)
©Zepsychology
@psychoet
የይቅርታ ደብዳቤ... 🙏
እንደሚታወቀው ሜሎሪና ቁጥር ሦስት መጽሐፌን ለኹለተኛ ጊዜ አራዝሜው ለገና በዓል አካባቢ አወጣዋለሁ ማለቴ ይታወሳል። ነገር ግን ከአቅሜ በላይ በኾኑ ግላዊና ሀገራዊ ጉዳዮች ምክኒያት ባልኩት ሰዓት ልጨርስና ለተከበራችሁ አንባቢያን ላደርስ አልቻልኩም። ስለዚህ ጠብቃችሁ ላላገኛችሁኝ በሙሉ ታላቅ ይቅርታ እጠይቃለሁ።

በተለይም በስልክ በመደወልና በቴክስት አስታውሳችሁ ለጠየቃችሁኝ በሙሉ በድጋሜ ይቅርታ እጠይቃለሁ። እንደፈጣሪ ፈቃድ ግን ሁሉ ሰላም ከኾነ በዚህ ክረምት ሀምሌ ወር ላይ ወደ እናንተ ይደርሳል።በተረፈ፥ ሜሎሪና መጽሐፍን አንብባችሁ አሁንም አስተያየታችሁን ለምትልኩ ወዳጆች ምስጋናዬን አቀርባለሁ።
ክፍል 19

ሃዘንን መቋቋም የሚያስችሉ ዘዴዎች

በህወታችን ውስጥ ትልቅ ቦታ የምንሰጣቸው እና መልካም አቀጣጫን በመጠቆም ትልቅ አስተዋጽኦ ያበረከቱልን ሰዎች አሉ ይኖራሉም፡፡ የቤተሰብ አባል ፤ የልብ ጓደኛ ወይም አርአያ የሆኑን በልባችን አግዝፈን የምናያቸው ምግባራቸው ያስከበራቸው ሰዎችን ለምሳሌ ያህል መጥቀስ ይቻላል፡፡ በመወለድ ወደ ህይወት መምጣት እንዳለ ሁሉ የማይቀረው ህልፈተ ህይወት አለና በሞት ሲለዩን የሚሰማንን የቅስም መሰበር፤ የቁጭት፤ የጥፋተኝነት ፤ የጸጸት፤ የንዴት፤ የናፍቆት አልፎ ተርፎም የመንኮታኮትና የውድቀት ስሜት በግርድፉ ለማጠቃለል ያህል የሃዘን ስሜት ብለን እንጠራዋለን፡፡ የሰው ልጅ እንደ ጸባዩ ይህንን የሃዘን ስሜት የሚያመጡበት ገጠመኞችና ሁኔታዎች የተለያዩ ሲሆኑ የስሜቱም ጥልቀት እና ቆይታ ጊዜ የዚያኑ ያህል ይለያያል፡፡ በዚህ ጽሑፍ የሃዘን ስሜትን መቋቋም የምንችልባቸውን ጥቂት ዘዴዎችን እንመለከታለን፡፡

1. የሃዘን ስሜትን አለመካድ

የገባንበትን የሃዘን ስሜት መወጣት እንዳንችል ወደኋላ ወጥረው ከሚያሰቃዩን ስሜቶች ውስጥ አንዱ የሃዘን ስሜትን መካድ ነው፡፡ የገባንበትን መጥፎ ስሜት መካድ ከስሜቶቹ ጋር ያለንን ቆይታ ያረዝመው ይሆናል እንጂ እንድንላቀቃቸው አያግደንም፡፡ ስለዚህም ምንም እንኳን ከማንም እና ከምንም በላይ እናፈቅራቸው ነበረ ቢሆንም ላናገኛቸውና ላይመለሱ እንደተለዩን አምነን ባንወደውም የሚደርስብን ሃዘን መቀበል ከስሜቱ መላቀቅ እንድንችል ይረዳናል፡፡

2. ጠንካራ ነኝ እቋቋመዋለው ብሎ እራስን አለማታለል

አብዛኛውን ጊዜ አሉታዊ የሆኑ ስሜቶችን በመቋቋም ለማለፍ “ዋጥ” አድርገን ለማለፍ ስንጣጣር የባሰ እራሳችን ላይ ከሚደርስብን የመንፈስ ስብራት አልፎ የእንቅልፍ ማጣት፤ የምግብ ፍላጎት መዛባት፤ የድብታ ችግር፤ እንዲሁም ሌሎችንም ሊያመጣብን ይችላል፡፡ ስለዚህም ተመራጭ የሚሆነው የሚሰማንን ስሜት ለመቋቋምና ለመከላከል ከመሞከር ይልቅ ስሜቱን እንደ አመጣጡ መቀበል ስላጣነው የህይወት አጋር ስንል እራሳችንን ካለንበት የስሜት ዝቅታ ማንሳት እንድንችል ለእራሳችን ዕድል ልንሰጠው ይገባል፡፡

3. የሃዘን ስሜትን ገልጾ ማውጣት ስለስሜቱ ከሌሎች ጋር መነጋገር

ብዙዎች የወዳጃቸውን የማጣት ስሜት አውጥተው ከመናገር ይልቅ በውስጥ አምቆ መብሰልሰልን እንደ አማራጭ አድርገው ይይዛሉ፡፡ ይህ ግን ስሜቱን ያለረዳት ብቻችንን በጫንቃችን ተሸክመን ለመጓዝ እንደ መሞከር ነውና የመድከምና የመሰላቸት ስሜት ይፈጥርብናል፡፡ የሆዴን በሆዴ ለሃዘን ስሜት አይሰራምና ለትዳር አጋራችን፤ ለቤተሰባችን፤ ለልብ ጓደኞቻችን ወይም ደግሞ ለስነ-ልቦና ባለሞያዎች የተሰማንን ስሜት በመናገር፤ በመጻፍ፤ ስዕል በመሳል ወይም በማንኛውም ችሎታችን በሚፈቅደው መንገድ መተንፈስ የሃዘንን ስሜት ይቀንሳልና ስሜታችንን ገልጾ ማጋራት ጥሩ አማራጭ ነው፡፡

4. ታጋሽ መሆን

የሃዘን ስሜቱ ከባድነት የተነሳ ብዙውን ጊዜ በሞት የተለየንን ግለሰብ የሚያስታውሱንን ነገሮች ለማራቅ እንሞክራለን፡፡ ስሜቱን ያራቅነው እየመሰለን ይጠቀሙበት የነበሩ ንብረቶችን ማራቅ፤ መኖርያ ቤታችንን መቀየር፤ የስራ ቦታችንን መቀየር፤ እንደው በአጠቃላይ እንደ ፎቶ ያሉ ትዝታ የሚቀሰቅሱ ንብረቶችን ለማስወገድ አለመቸኮል ጥሩ አማራጭ ነው፡፡ የሃዘን ስሜቱም ካለፈ በኋላ የእነዚህ ንብረቶች መኖር ያጣናቸውን ግለሰቦች በመልካምነት እንድናስባቸውና እንዳንረሳቸው፤ ለእኛ የነበራቸውን ፍቅር እና አክብሮት እንድናስታውስ ይረዱናል፡፡

5. የጤናችንን ጉዳይ ቸል አለማለት

ሰዎች በሃዘን ጊዜ እራሳቸውን ይጥላሉ፡፡ ለእራሳቸው ያላቸው ክብር፤ እንክብካቤ ከመቀነስም ባለፈ እራሳቸውን በረሃብ ይቀጣሉ፡፡ የምናደርጋቸው ማናቸውም ድርጊቶች ያጣነውን ግለሰብ አይመልሱምና የጤናችንን ጉዳይ ቸል ልንለው አይገባም፡፡ የምናስበውን ያህል የምግብ ፍላጎት ባይኖረን እንኳን ምግብ መመገብ ይገባናል፡፡ ያጣናቸው ሰዎች በህይወት ቢቆዩ እንዲህ እንድንጎሳቆል እንደማይፈልጉ ለእራሳችን ደጋግመን ልንነግረው ይገባል፡፡

6. የሃዘን ስሜትም ያልፋል

በሃዘን ስሜት ውስጥ ስንሆን አብዛኛዎቻችን ስሜቱ የማይላቀቅና ሽሮ የማያልፍ አድርገን እንስለዋለን፤ ይመስለናልም፡፡ የፈጀውን ያህል ቢፈጅ የሃዘን ስሜት ከጊዜ ወደ ጊዜ ግን እየቀነሰ የሚመጣ ነው፡፡ መዘንጋት የሌለብን መኖር ማለት አሉታዊ ስሜቶችን ሳይሰሙን ተንደላቀን የምንፈላሰስበት ሳይሆን ተጋፍጠንና ተቋቁመን የምናልፍበት ነው፡፡ በህይወታችን ውስጥ የሚያጋጥሙን ማናቸውም ነገሮች የሚያልፉ መሆናቸውንና ህይወት የሚቀጥል መሆኑን ልናስተው ይገባል፡፡

በአጠቃላይ ጊዜ የማይሽረው ነገር የለምና ለማንነታችን ሃቀኛ በመሆን ካጋጠመን የተጠበቀ ይሁን ድንገተኛም የሃዘን ስሜት በመቋቋም ማንነታችንን ልንመልስ ይገባል፡፡

©(በዘመነ ቴዎድሮስ zepsychologist)
@Psychoet
#ሀሙስ 16

ስር ነቀል ለውጥ

“ሰዉዬዉ ጭልፋዉን ዉሻ ትለክፍበታለች አሉ ፡፡ ያን ጭልፋ በካህን አስባረከዉ ፡፡ በነጋታዉም ድስቱን ስትለክፍበት ድስቱንም ወስዶ አስባረከዉ ፡፡ እሷ መጠጫዉንም መብያዉንም ሁሉ ስትለክፍ እሱ እየነጠቀ ወደ ካህኑ በማመላለስ ማስባረኩን ያዘ ፡፡ በስተመጨረሻም ካህኑ የሰዉዬዉ ነገር ቢታክታቸዉ ለብቻዉ ጠርተዉት ‘ዉሻዋን ራሷን አምጣትና ልባርክልህ ‘ አሉት ይባላል። ” ይሄን ጽሑፍ የዛሬ አመት ገደማ ነበር ያነበብኩት፡፡ ጽሑፉ ስለ ሰው ልጅ የአስተሳሰብ ለውጥ አጉልቶ ያሳያል ፡፡
ሕይወት ላይ ምንም ነገር ከምንጩ ካልተቀየረ ውጤቱን በየጊዜው መቀያየር የሚያመጣው ትልቅ ለውጥ የለም፡፡ ለዚህ ይመስለኛል ሁልጊዜ በየሚዲያው “ስር ነቀል ለውጥ ” ሲባል የምንሰማው፡፡ ማንኛውም ያለንበትን ሁኔታ ለመቀየር ስናስብ ሁልጊዜ ከላይ ከላይ ሳይሆን በደንብ ከውስጥ ለመቀየር መነሳት ይገባናል ፡፡ የሰው ልጅ ማንኛውም ለውጥ የሚጀምረው ደግሞ ከራሱ አስተሳሰብ ፣ ከራሱ ተግባር ነው ፡፡ ሙሉ ሀሳብና ተግባር ያልያዘ ለውጥ ጊዜያዊ ብቻ ነው፡፡
ብዙ ጥናቶች እንደሚያመለክቱትም አብዛኛው ሰው ደስተኛ ሕይወት የማይኖረው ፥ “ለመኖር በሚያስበው ሕይወትና አሁን እየኖረ ባለው ሕይወት” መካከል ሰፊ ልዩነት ስላለ ነው ፡፡ ይህ ልዩነት ደግሞ የሚሞላው ሀሳብና ተግባርን አካቶ በያዘ “ስር ነቀል” ጠንካራ የለውጥ ሂደት ነው ፡፡
መልካም ቀን ይሁንላችሁ!
ናሁሰናይ ፀዳሉ
ክፍል 20

#አራቱ የሰው ባህሪ አይነቶች
www.tg-me.com/psychoet
(በናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ)

በዛሬው ርዕስ ለሰው ልጆች ተግባቦትና የቀን ተቀን መስተጋብር ወሳኝ ስለሆነው አመል ( Temperament) እንመለከታለን፡፡ እንደሚታወቀው ማንኛውም ባህሪ መነሻ ምክኒያት አለው ፡፡ ምክንያቶቹ ደግሞ #ተፈጥሮአዊ ወይም #አካባቢያዊ ሊሆኑ ይችላሉ ፡፡

1. ተፈጥሮአዊ ተፅዕኖ :- ተፈጥሮአዊ ተፅዕኖ ስንል በዘር ከወላጆቻችን የምንወርሰው ሲሆን

ለምሳሌ ፦ አንድ ልጅ እናቱ ወይም አባቱ ያላቸውን ባህሪ ሲወርስ

2. አካባቢያዊ :- ከቤተሰብ ጋር ባለ ግንኙነት ፣ በጓደኛ ተፅዕኖ ፣ በትምህርት ቤት ቆይታና በምንኖርበት ባህል የምንወርሳቸውን ባህሪያቶች ያጠቃልላል

ለምሳሌ ፦ አንድ ሰው በጣም ተሳዳቢ ቢሆን ( ያን ስድብ የወረሰው በአካባቢው ከሚኖሩ ሰዎች አልያም ከሰዎች በተለያዩ መንገድ ከተመለከታውና ከሰማው ሊሆን ይችላል )


የስነልቦና ተመራማሪዎች የሰውን ተፈጥሮአዊ አመል (Temperament ባህሪ) በአራት በመክፈል ያስቀምጡታል

1 .📌ሳንጊዊን (Sanguine)
ሳቂታና ተጫዎች ...
#ተግባቢና ምክኒያታዊ ናቸው

2.📌ኮለሪክ (Choleric)
ተነጫናጭ/ አዛኝና አኩሪፊ ...
#ተግባቢና ስሜታዊ ናቸው

3 .📌ሜላንኮሊክ (Melancholic)
አይናፋር ...
#ጭምቶችና ስሜታዊ ናቸው

4. 📌ፊላግማቲክ (Phlegmatic)
ግትር...
#ጭምተኛና ምክኒያታዊ ናቸው

እነዚህ አራት የሰው አመሎች የየራሳቸው መገቸጫ አላቸው

📌ሳንጊዊን  
❇️አየር   ⭕️ማሕበራዊ ሰዎች

ሳንጊዊን አመል ያላቸው ዋናው መገለጫቸው አብዝቶ ተጫዎችና ወሬኛነት ፣ ነገሮችን ለመስራት ፈጣንነት ፣ ማሕበራዊነት ይገኙበታል ፡፡ ሳንጊዊኖች በጣም ተግባቢና የሕብረት ነገር የሚወዱ ናቸው፡፡ ይህ አመል ያላቸው ሰዎች ሁልጊዜም ለራሳቸው ሳይሆኑና ምንም ሳይሰሩ ኑሮአቸውን የግል ሳይሆኖ የጋራ ያረጋሉ፡፡

📌ኮለሪክ
❇️ እሳት ⭕️አስተዳዳሪዎች
ኮለሪኮች በጣም ተግባቢ ሲሆኑ የሚገለፁበት ባህሪ በውሳኔ ሰጭነታቸው ፣ በግብ ተኮርነታቸው ፣ በምኞታቸው ፣ በኢጥገኛነታቸው ነው፡፡ በተጨማሪም ኮለሪኮች ቁጡዎች ቂም የሚይዙ ለስሜት ቅርቦች ናቸው፡፡

📌ሜላንኮሊክ
❇️መሬት  ⭕️ሰዎችን ከሕይወታቸው  አግላይ

ሜላንኮሊክ ሰዎች አስተዋያዮችና ዝርዝር ጉዳይ ላይ ትኩረት ሰጪዎች ደግሞም ጥልቅ አሳቢዎችና ጭምቶች ናቸው ፡፡ ከዛ በተጨማሪ ራሳቸውን ብዙ ሰዉ ካለበት ቦታ ማግለል / ማሸሽ የሚመርጡ ናቸው ፡፡ እነዚህ አይነት ሰዎች ሁሌም ፍፁም ለመሆን የሚሞክሩና የሚፈልጉ ናቸው፡፡ይህ ባህሪ ሰዎችን ራሳቸውን ችለው እንዲቆሙ የሚገፋፋ ፣ ቁጥብ እንዲሆኑ የሚያረግ ነው ፡፡

📌ፊላግማቲክ 
❇️ውሀ   ⭕️ሰዎችን ከወደሕይወታቸው አቅራቢ

ፊላግማቲክ ሰዎች ረጋ፣ ፈታ ያሉና ከሁሉ ጋር እንደውሀ የሚራመዱ ናቸው ፡፡  ለሌሎች በጣም የሚያዝኑ ግን የራሳቸውን ስሜት በማፈን የማይገልፁ ናቸው ፡፡  እነዚህ ሰዎች  የተለያዩ ሀሳቦችን እና ችግሮችን ወደአንድ በማምጣት ለመፍታት የሚሞክሩ ናቸው ፡፡


አንዳንድ ሰዎች ከነዚህ ባህሪያት ሁለቱን ወይንም ከዛ በላይ ሊያሳዩ ይችላሉ ፡፡ በቅርብም የተጠኑ ጥናቶች ከ4ቱ አመሎች ላይ አንድ ጨምረው 5 አድርሰውታል ፡፡ አምስተኛው ደግሞ የሁሉም ቅልቅል ያለበት ከሁሉም መሀል የሆነ ሲሆን (SUPINE )ብለው ጠርተውታል፡፡

የናንተ ባህሪ ከየትኛው ይመደባል ? በ #Comment አሳውቁኝ ?

በዩቲዩብ የምንለቃቸውን ትምህርቶች ለማግኘት ቻናላችንን Subscribe አድርጉ

https://youtube.com/@Psychoet?feature=shared
_____
ይህ ፅሁፍ ለብዙ ሰው እንዲደርስ ሁላችንሞ ባለንበት የFacebook ግሩፕ ውስጥ #ሼር እናርገው 💛

ዕውቀት ከአሉታዊ የአስተሳሰብ እስር ቤት ነፃ ያወጣል !

የሳምንት ሰው ይበለን!
__❖

ለ ሳይኮሎጂ የበለጠ ለማወቅ ፔጁን ይከታተሉ ለወዳጆችዎ ያጋሩ

ናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ
#ሀሙስ 17

እያንዳንዱ ትልቅ ነገር ትናንሽ መነሻዎች አሉት

ተፈጥሮ በኡደት (Process) የተመላች ናት፡፡ ዘመናትን በጊዜ ቀመር አስልታ ከአንዱ ምዕራፍ ወደ ሌላኛው ታሻግራለች፡፡ የኡደት ስሌትዋ ከትልቅ ወደ ትንሽ ሳይሆን ከትናንሽ ወደ ትላልቅ የሚያመራ ነው፡፡

የሰው ልጅ የዕድገት ለውጥ ዓላማ በተፈጥሮ የወረሰውን እምቅ ኃይል ከከፍተኛ ደረጃ ላይ ማድረስ ነው፡፡ ኤልሳቤጥ ሃርሎክ የተባለች የሳይኮሎጂ ምሁር እንደገለጸችው ሰዎች በአእምሮ ፤ በአካል ከሌሎች የተሻሉ ሆነው ለመገኘት የሚያደርጉት ጥረት ወደ ዕድገት ለውጥ ግብ ለመድረስ የሚደርጉት ጥረት ስለሆነ እነዚህን ጥረቶቻቸውን እውን ለማድረግ ይችሉ ዘንድ ዕድሉ ሊሰጣቸው ይገባል፡፡

እዚህ ላይ ትልቁ ጉዳይ ሰዎች እራሳቸውን ለማሻሻል እምቅ አቅምና ችሎታ ካላቸው ከወዴት ነው የሚጀሚሩት የሚለው ነው፡፡ ብዙዎቻችን በስራችንና በህይወታችን የምንፈልገውንና የምንሻውን ያህል ውጤታማ መሆን ያልቻልነው ዕቅዶቻችንንና ስኬቶቻችንን ከታች ከትንንሽ ነገሮች ስለማንጀምራቸው ነው፡፡ ቀድሞ የሚታየን ትልቁ ስዕል እንጂ ወደ ትልቁ የስኬት ጎዳና ለመድረስ ከትንሽ ነገር መጀመር እንዳለብን አንገነዘብም፡፡ ከዚህ በታች ከትንንሽ ነገር ተነስተን ወደ ትልቁ ስኬት ለመጓዝ የሚረዱንን ነጥቦች እንመለከታለን፡፡

1.ትምህርት

የተሻለ የትምህርት ደረጃ ያለቻው ሰዎች ስራዎቻቸውን የሚያከናውኑት ዕውቀትንና ዕቅድን መሰረት አድርገው ነው፡፡ በስራዎቻቸው ላይ ወሳኝ ጉዳዮችን በደንብ ስለሚያውቁ ከሌላው ሰው በተሻለ ሃሳብና መረጃ ይኖራቸዋል፡፡ ስለዚህ ዕውቀቶቻቸውን በመመንዘርና ማኅበራሰባቸውን በማገልገል የተሻለና የተሳካ ህይወት (ገቢንም ጨምሮ) መኖር ይችላሉ፡፡ ዕውቀት በጨመረ ቁጥር የሰው አስተሳሰብ አድማሱ ስለሚሰፋ ምን ሰርቶ ምን ማግኘትና የት እንደሚደርስ አቅጣጫን ይጠቁማል፡፡ ትምህርት ስንል በአንድ የትምህርት መስክ የምናገኛውን የሰርተፍኬት ብዛት ብቻ ሳይሆን በህይወት ልምድና ተሞክሮ ያገኘነውን ዕውቀት ትርጉም ባለው ስራ ላይ ማዋልና በትንሽ በትንሹ በመደበኛም ይሁን ኢ-መደበኛ ትምህርት ታግዘን ህይወትን ለማሸነፍ የምንሄድበትን የህይወት ጉዞን ሁሉ ያጠቃልላል፡፡

2. ክህሎት

በአንድ ነገር ላይ የሚኖረን ክህሎት የምናስመዘግበውን ውጤት ብዛትና ጥራት ይወስናል፡፡ የምንሰራውን ስራ በደንብ ካወቅነው በስራችን ቅልጥፍና ወደ ሚቀጥለው ምዕራፍ በብቃት መሸጋገር እንችላለን፡፡ ከማናውቀው ነገር አንድ ብለን ከመጀመር የምናውቀውን ነገር አሻሽሎ በመስራትና ክህሎትን በማዳበር የተሻለ ለውጥ ማምጣት ይቻላል፡፡
3. ግንኑነትን ማስፋት
በምንሰራው ስራ ላይ ብዙ ሰዎችን ለማወቅ ከጣርን ግንኙነታችንን በማጠናከር አማራጮችን ማስፋት እንችላለን፡፡ ስለዚህ የግንኙነት አድማስን ለማስፋት ዘውትር ማኅበራዊ ገመዶቻችንን በረጅሙ መዘርጋት አለብን፡፡

4. ጥሩ የስራ ልምድ

ጥሩ የስራ ልምድ በአጭር ጊዜ ውስጥ ብዙ ስራዎችን እንድንሰራ ይረዳናል፡፡ ይህን ለማድረግ ስራዎቻችንን በዕቅድ መስራት አለብን፡፡ ጥሩ የስራ ልምድ አንድን ነገር ከማከናወናችን በፊት አስቀድመን እንድናስብበት ስለሚያስችለን ከስራው በኋላ የሚከሰቱትን ማንኛውንም አወንታዊና አሉታዊ ውጤቶችን አስቀድሞ መገመት ስለሚያስችል ኪሳራን ለመቀነስ ይረዳል፡፡

6. አወንታዊ አመለካከት

የምንሰራው ስራ እኛነታችንን ስለሚገልጸው በስራችን ላይ አወንታዊ አመለካከት ፤ በእራስ መተማመን ፡ ከስራ ባልደረቦቻችን ጋር ጥሩ መስተጋብር ካለን ሁሌም መልካም ነገር እንድናስብ ስለሚረዳን ወደ ምንፈልግበት ደረጃ እንድንደርስ አወንታዊ አመለካከት የበኩሉን አስተዋጽኦ ያበረክታል፡፡

7. ስለራሳችን ጥሩ ስዕል ይኑረን

ስለራሳችን ጥሩ ስዕል ወይም ምልከታ መያዝ የምንፈልገውንና ደስተኛ ህይወት እንዲኖረን ይረዳናል፡፡ ሰዎች በውጫዊ ገጽታችን ሊገምቱንና ሊፈርጁን ይችሉ ይሆናል፡፡ ነገር ግን ውጫዊ ምልከታ የእኛንም ሆነ የሌላውን ስለማይገልጽ ስለእራሳችንም ሆነ ስለሌሎች ሰዎች ጥሩና የተቃና አመለካከት ሊኖረን ይገባል፡፡

8. ፈጠራ

ፈጠራ አንድን ነገር ዘውትር በተሻለ ፍጥነት፤ ቅልጥፍና ፤ በቀላል አኳሃን እንድንተገብረው ይረዳናል፡፡ ፈጠራ አዲስ ነገር ፈጥሮ ወይም ሰርቶ ማሳየት ብቻ ሳይሆን ነገሮችን ከዚህ ቀደም ከምናያቸው ዕይታና ግንዛቤ በአዲስ መልኩና በሌላ አቅጣጫ ማየትንም የሚያካትት ነው፡፡

9. ማንነት

እራስን መግራትና ግልጽነት ብዙ የስኬት በሮችን እንድንከፍት ይረዳናል፡፡ መተማመን የግንኙነት ሁሉ መሰረት ነው፡፡ ሰዎች የሚያውቁን በድርጊታችንና በቃላችን የምንታመን ከሆነ ነገሮችን በፍጥነት በቀላልና በታማኝነት በእኛ በኩል እንደሚያገኙ ያምናሉ፡፡ ይህም ብርታትና በራስ መተማመንን ስለሚፈጥርልን ወደምንፈልገው ደረጃ ለመድረስ ትልቅ እገዛ ያደርግልናል፡፡
ዕቅድህ 15ኪሎ ክብደት መቀነስ ከሆነ በቀላሉ እንቅስቃሴ ማድረግና አመጋገብህን በማስተካከል ከትንሹ መጀመር ትችላለህ፡፡ ከዚያ ወደ ምትፈልገው ደረጃ ስትደርስ እያንዳንዱ ትልቅ ነገር ትናንሽ መነሻዎች እንዳሉት ትገነዘባለህ፡፡ ሻሎም

©አንቶኒዮ ሙላቱ

@psychoet
ክፍል 21

#የብቸኝነት ስሜትን ማሸነፊያ መንገዶች
www.tg-me.com/psychoet
(በናሁሰናይ ፀዳሉ አበራ)

ሰው በተሰበሰበበት ቦታ ሁናችሁ ብቸኝነት ተሰምቷችሁ ያውቃል ? በዚህ ወረርሽኝ ምክንያት እቤት በመክረማችሁ የብቸኝነት ስሜት እያጠቃችሁ ነው? እንግዲያውስ ይሄን ስሜተት የማሸነፊያ የሥነልቦና መፍትሔዎችንና ምክሮችን ይዤላችሁ መጥቻለሁ ፡፡
__
አዕምሮአችን የተፈ
ጠረው የተለያዩ አይነት ስሜቶችን እንዲረዳና እንዲያስተናግድ ነው ፡፡ እነዚህ ስሜቶች አወንታዊና አሉታዊ ሲሆኑ ለኛ ማንነትና አኗኗር ወሳኝነት አላቸው ፡፡ በውስጣችን የሚፈጠሩት አወንታዊ ስሜቶች የሚገነቡንን ያህል አሉታዊ ስሜቶች ደግሞ ከውስጥ እያፈረሱን ከውጭ ደግሞ በድካም ፣ በድብርት ፣ በጭንቀት ፣ ስለ ነገ ባለ ፍርሀት ያስሩናል ፡፡

በአዕምሮአችን ከሚፈጡሩ አሉታዊ ስሜቶች አንዱ ደግሞ የብቸኝነት ስሜት ነው ፡፡ የብቸኝነት ስሜት እድሜና ፆታ ፣ ሀብትና ስልጣን ሳይለይ ከልጅነት እስከ ሽምግልና ፣ ከደሀ እስከ ሀብታም  የሚያጠቃ አሉታዊ ስሜት ነው ፡፡

አዕምሮአችን " ማንም አይወደኝም ፣ እኔ ተሸናፊ ነኝ ፣ ሁሉም ሰው ጥሩ አይደለም ፣ ይሄ ወረርሽኝ እኔና ቤተሰቤን እንዳይጎዳ"  የሚሉ የተለያዩ ምክንያቶችን ሲያቀርብ በውስጣችን የብቸኝነት ስሜት እንዲያድግ ያሆናል ፡፡ በተጨማሪም ከዚህ ቀደም የደረሱብንን የስነልቦና ፣ የስሜት ፣ የአካል ... ጥቃቶች ፣ ትችቶች መላልሶ ሲያሰላስል እንዲሁም በሌሎች የመገለል ነገር ሲኖር ወደዚህ ብቸኝነት ስሜት ልንመጣ ይችላል ፡፡

ከዚህ በታች የብቸኝነት ስሜትን ተረድተን እንዴት በጤነኛ መንገድ ማሸነፍ እንደምንችል 3 ሀሳቦችን እናያለን

1.ብቸኝነት ስሜት እንጂ እውነታ እንዳልሆነ መረዳት

ብቸኝነት ስሜት ሲሰማን በሕይወታችን  አንድ የተፈጠረ ነገር ይሄን ስሜት እንዳስነሳው መረዳት አለብን ፡፡ የብቸኝነት ስሜት የሚመጣው 'በመገለል ወይም ለብቻ በመሆን ' ብቻ አይደለም ስለዚህ ብቸኝነት ሲሰማን ቁጭ ብለን ጊዜ በመውሰድ ይህን ስሜት ያመጣብንን ምክኒያት ለማወቅ መሞከርና መንስኤውን ለማስወገድ ካልተቻለም ለመቀነስ እቅድ ማውጣት ተገቢ ነው ፡፡

2.በየቀኑ ትርጉም ያለው ስራ በመስራት ማሳለፍ

በዚህ ወረርሽኝ ወቅት ባለንበት ቦታ ( በቤትም ሆንን በውጭ ) እያንዳንዱን ቀን ትርጉም ያለው ስራ ሰርተንበት እንለፍ ፡፡ በዚህ ጊዜ ቀኑን ሙሉ ፊልም መመልከት ፣ ማሕበራዊ ሚዲያ ከአንዱ ወደአንዱ እየተሸጋገሩ ማየት ወደባሰ ድብርት ፣ ጭንቀትና ብቸኝነት ስሜት ስለሚመራ በየቀኑ አንድ አዲስ ነገር ለመስራት መሞከር ከብቸኝነት ስሜት ለመውጣት ይረዳል ፡፡ ይህም ብቻ ሳይሆን ማታ ስንተኛ ዛሬ ከነጋ ምን ሰራሁ ብለን ራሳችንን በመጠየቅ ነገ ደግሞ ምን መስራት እንዳለብን ማቀድ መልካም ነው ፡፡


3. በጣም የምንወዳቸው ሰዎች ማግኘት ፣ የምንወዳቸውን ነገሮች መስራት

ይሄን ማድረግ በውስጣችን መልካም ሀሳብና ኢነርጂ እንዲፈጠር ያደርጋል ፡፡ ይሄም የተሻለ የስራ ተነሳሽነት ይፈጥርልናል ፡፡ ከሚወዱት ነገር ጋር ጊዜ ማሳለፍ በውስጣችን አወንታዊ ሀሳብ እንዲፈልቅ ፣ አሉታዊዉ ደግሞ እንዲቀንስ ይረዳል ፡፡ በተጨማሪም በዙሪያችን ለብቸኝነት መንስኤ ከሆኑ ሁኔታዎችና ሰዎች መሸሽ ተገቢ ነው፡፡

እነዚህ ከላይ የተጠቀሱት ጥቂጥ መፍትሔዎች ናቸው ፡፡ የብቸኝነት ስሜት ሲሰማን ሊረዱን የሚችሉ ሌላ ብዙ መንገዶችን ከመጸሐፎች ፣ ከድህረ ገፆች፣ ከሰዎች ልናገኝ እንችላለን።


       ❇️❇️❇️❇️❇️❇️❇️❇️❇️❇️❇️❇️
                  
_____
ይህ ፅሁፍ ለብዙ ሰው እንዲደርስ ሁላችንሞ ባለንበት የግሩፕ ውስጥ #ሼር እናርገው 💛

ዕውቀት ከአሉታዊ የአስተሳሰብ እስር ቤት ነፃ ያወጣል !

                  የሳምንት ሰው ይበለን!
__❖

ሁሰናይ ፀዳሉ አበራ
ሀሙስ 18
ሰዎች ስለእኛ በሚያስቡት ነገር ላይ መጨነቅን ለማቆም ቀላል ዘዴዎች
Telegram www.tg-me.com/psychoet

‘’የማይባል ነገር ተናገርሁ እንዴ? እንዴት እንደዚህ አደርጋለሁ? ሰዎች እኮ መሃይም :ገገማ:የሚያናድድ ሰው ነው/ነች ይሉኝ ይሆናል’’ እያልን ራሳችንን የምናስጨንቅ ስንቶቻችን ነን! ሌሎች ሰዎች ስለእኛ በሚያስቡት ነገር ላይ በመጨነቅ አእምሯችንን በጨለማ ቦታ እንዲንከራተትና ራሳችንን በመጠራጠር የስጋት ስሜት እንዲሰፍንብንና እንዳንረጋጋ እያደረግን መሆኑን ልናውቅ ይገባል:: ለነገሩ ሁላችንም ሰዎች ስለእኛ ያላቸው ሃሳብ/አስተያየት ምን ይሆን ብለን መጨነቅ እንደሌለብን እናውቃለን ወደ ተግባር ለመቀየር ግን ስንቸገር እንታያለን:: ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ዘዴዎች ብንጠቀምባቸው ይረዱናል!

1. የሰዎችን አዕምሮ ማንበብ እንደማንችል መረዳት፡- እስኪ ሰዎች ስለእኛ የሚያስቡትን በእርግጠኛነት ማወቅ እንችላለን? ብዙ ጊዜ ነገራትን ሳናጣራ ይሆናል በማለት ብቻ ማወቅ እንደምንችል ነው የምናስበው ይህ አስተሳሰባችን ደግሞ ለህይወታችን ፀር ወደሆኑ ድምዳሜዎች/ዉሳኔዎች ይመራናል::ስለዚህ እነዛ ሰዎች ሃሳባቸውን የሚገልጹበትን ዕድል አግኝተው ሃሳባቸውን እስካልገለጹልን ድረስ ስለምን እንደሚያስቡ ማወቅ በፍጹም አንችልም፡፡

2. በቋሚነት ለሚጠቅመን ነገር መስራት:- ከሌሎች ሰዎች የሚሰነዘሩ የኩነኔ አስተያየቶች በእርግጥም እኛን ይጎዱናል ነገር ግን ከእነዚህ ሰዎች የሚመጣውን አሉታዊ ምላሽ በመፍራት የምናጣቸው/የምናሳልፋቸው መልካም ዕድሎች ጥለውብን ከሚያልፉት የአእምሮ ጠባሳ አይበልጥም፡፡ እነዚህ የኩነኔ/አሉታዊ አስተያየቶች የሚያደርሱብን ጉዳት ቅጽበታዊ ሲሆን ባጣናቸው/ባመለጡን መልካም ዕድሎች ምክንያት የሚደርስብን ጸጸትና ቁጭት ግን ከጊዜ ወደ ጊዜ ስር እየሰደደና እያደገ ነው የሚሄደው፡፡ ስለዚህ በቋሚነት የሚጠቅመንን ነገር ለማግኘት ጊዜያዊ የሆኑ ተቀባይነት ማጣትን ለመቀበል ፈቃደኞች እንሁን::

3. ራስን ከመኮነን/በራስ ላይ ከመፍረድ መቆጠብ:- እስኪ ሰዎች ምን ይሉን ይሆን ብለን የምንጨነቅበትን ሃሳብ ለሰከንድ ቆም ብለን እናስበው! በእርግጠኝነት እኛ ለራሳችን የምናስበውን ነገር ላይ ነው ሌሎችም እንደዚ ያስባሉ ብለን የምንሰጋ፡፡ ስለዚህ በራሳችን ላይ መፍረድን አቁመን(ራስን ከመኮነን ተቆጥበን) እኛነታችንን ከተቀብለነው ወይም ለራሳችን ጥሩ ግምት ከሰጠን ሌሎቹ ስለእኛ ለሚሰጡት/ለሚያስቡት ሃሳብ ፍርሃትና ስጋት አይኖረንም ማለት ነው፡፡

4. ሌሎች ሰዎችን መኮነንን/በሌሎች ላይ መፍረድን ማቆም፡- ሰዎችን እየገመገምን፡እየኮነንና እየፈረድንባቸው የምንኖር ከሆነ እነሱም በተመሳሳይ ሁኔታ እንደሚፈርዱብን ነው የምናስበው፤ ስለዚህ በእነሱ ላይ ከመፍረድ ይልቅ ህይወታችንን ለማሻሻልና ለማደራጀት እንደሚያግዙን ቆጥረን ብናደንቃቸውና ብናበረታታቸው የበለጠ ተጠቃሚዎች መሆን እንችላለን፡፡

5. ስለእኛ አለመሆኑን መረዳት፡- ሰዎች በራሳቸው እይታ ከደረሰባቸው ክስተት፡ ቁስል፡ ፍራቻና እንከን የተነሳ ለነገሮች የተለያዩ አሉታዊ ምላሾችን ይሰጣሉ ነገር ግን የእነሱ ምላሽ ከእኛ ጋር የሚገናኝ እንዳልሆነ ልብ ልንል ይገባናል፡፡ ለምሳሌ የሆነ ቢዝነስ ለመጀመር ብንወስንና አንድ ሰው ”እመነኝ ይህንን ስራ ከጀመርህ በሚቀጥሉት ወራት አሊያም ዓመታት ምንም ዓይነት የእረፍት ጊዜ አይኖርህም” ቢል ሰውዬው የተናገረው ቢዝነስ መጀመር ላይ ያለውን ሃሳብ/አመለካከት እንጂ እኛን በተመለከተ እንዳልሆነ ለይተን መረዳት ይጠበቅብናል::

6. በሚያስደስተን ነገር ላይ ትኩረት ማድረግ:- ይህን ባደርግ ሰዎች ይፈርዱብኛል በማለት የሚያስደስቱንን ተግባራት ከማድረግ የምንገደብ ከሆነ(የማኅበረሰቡን እሴቶች በጠበቀ መልኩ) ጊዜያችንን ምንም ዓይነት ጥቅም በሌለው ጭንቀት እያባከንነው መሆኑን እናስተውል፡፡ ስለዚህ በህይወታችን ከፍተኛ ለውጥ ማምጣት የሚችለውን ብርቅ የሆነውን አቅምና ኃይላችንን በመሸርሸር ፈንታ እኛን በሚያስደስቱን ነገራት ላይ ትኩረት ልናደርግ ይገባል፡፡

7. የሚያውኩንን ነገሮች መለየት፡– ሌሎች ሰዎች አሉታዊ በሆነ መልኩ ይገመግሙናል/ይፈርዱብናል ብለን የምንጨነቀው ምናችንን በተመለከተ ነው? በስራችን ሁኔታ: ከሌሎች ጋር ባለን ግንኙነት: ምናልባትም በክህሎታችንና ነገሮችን በመመርመር ባለን አቅም ሊሆን ይችላል:: ስለዚህ በውስጣችን መረጋጋት እንዳይኖር የሚቀሰቅሱ ነገሮችን መለየትና ማሻሻል ከቻልን ማሻሻል አሊያም እንዳሉ መቀበል ያስፈልጋል:: ምክንያቱም ከሁኔታዎች ጋር ሰላም መፍጠር ከቻልን የሰዎች አጸፋዊ ምላሽ አያስጨንቀንም ማለት ነው::

8. ራሳችንን መቀበል:– ፍጹም አለመሆናችንን፡ እንከንና ድክመቶች እንዳሉን መቀበል ነገር ግን አቻ የሌለን(ልዩ) በዓለም ላይ እኛን የሚመስል ሰብዕናና ተሰጥኦ የታደለ ሰው እንደሌለና ወደፊትም እንደማይኖር ልናስተውል ይገባል፡፡

9. አጸፋዊ ምላሾችን መጠበቅ/ተስፋ ማድረግ፡- በሰዎች ዘንድ የሚፈጠረውን አጸፋዊ መልስ በመፍራት ፈንታ ያ ምላሽ ሊፈጠር እንደሚችል አስቀድመን ተስፋ ማድረግ አለብን(የሰዎችን ስሜት ለመቀስቀስ መፍራት የለብንም) ምክንያቱም በሰዎች ዘንድ አሉታዊም ይሁን አዎንታዊ ምላሽ መፍጠር ካልቻልን ምናልባትም ራሳችንን የመሆን ድፍረቱን ልናጣ እንችላለንና፡፡

10. እየኮነኑን/እየፈረዱብን ነው ብለን ካሰብናቸው ሰዎች ጋር ማውራት፡- እንዲያው ሁኔታዎች ተመቻችተውልን ስለእኛ መጥፎነት ያስባሉ/እየፈረዱብን ነው ብለን ከምናስባቸው ሰዎቸ ጋር ተቀራርበን ብናወራ እስከምንገረም ድረስ ምንም ባለጠበቅነው ሁኔታ አዕምሯቸው በብዙ ጭንቀቶች እንደተሞላ ልናውቅ እንችላለን፡፡ ማን ያውቃል ልክ እኛ እንደምንጨነቀው እነሱም ሌሎች ሰዎች ስለእነሱ ምን ሊያስቡ/ሊሉ በሚችሉት ሃሳብ እየተጨነቁ ሊሆን ይችላል እኮ፡፡ ስለዚህ ራሳችንን ግልጽ በማድረግ ከእነዚህ ሰዎች ጋር ተቀራርበን ሃሳብ ማንሸራሸር ያስፈልጋል::

በአጠቃላይ ከላይ የተዘረዘሩትን ሃሳቦች ወደ ተግባረ ከቀየርናቸው እኛም መቀየር እንችላለን!

(በአለበል አዲስ)
©Zepsychologist
Telegram www.tg-me.com/psychoet
2024/06/01 14:55:47
Back to Top
HTML Embed Code: