Telegram Web Link
ሰላም የA4P ቤተሰቦች

📚 መንፈሳዊ መፅሀፍትን ለማግኘት ትክክለኛውን ቦታ እንጠቁማችሁ

👉 @amharicspritualbooks 👈
👉 @amharicspritualbooks 👈

📌 ቻናሉን በመቀላቀል በየጊዜው የሚለቋቸውን መንፈሳዊ መፅሀፍት በማንበብ መንፈሳዊ ህይወትዎንና ዕውቀትዎን ያሳድጉ
Forwarded from Purity Tube
#ወቅታዊና_ጠቃሚ_ምክር ወደ ዩኒቨርስቲ ለምትገቡ ተማሪዎች

👉ዩኒቨርስቲ ማለት የለውጥ ቱቦ (a vessel of change ) ነው፡፡

💢በብረት ማቅለጫ በአንደኛው ጫፍ ውስጥ የገባ ማንኛውም አይነት ቅርፅ የነበረው ብረት በሌላኛው ጫፍ ሲወጣ ቀድሞ የነበረውን ቅርፅ ለቆ ፈሳሽ ሆኖ እንደሚወጣ ሁሉ ዛሬ ዩኒቨርስቲ ገብታችሁ ከጥቂት ዓመታት በኋላ ተመርቃችሁ ስትወጡ ዛሬ ላይ ያላችሁን ማንነት ይዛችሁ እንደማትወጡ እወቁ

👉ለውጥ ስንል ሁለት አይነት ለውጦች ናቸው
󾠮 አዎንታዊ Positive
󾠯 አሉታዊ Negative

ሁለቱም ለውጦች እንዲከሰቱ ከኋላ የሆነ አምጪ ሃይል (Driving Force) አላቸው፡፡

💢አሉታዊው ለውጥ ከሚያመጡ ሃይላት በዋናነት የሚጠቀሱት
1)የአቻ ግፊት (peer pressure) እና
2)'ነፃነት' (freedom) ወይም ከቤተሰብ ተፅእኖ ውጪ መሆን ናቸው፡፡

💢አዎንታዊውን ለውጥ የሚያመጣው በዋናነት መንፈሳዊ ህብረት ነው፡፡
ይህም በፌሎሺፕ መሳተፍና
በsmall teams ውስጥ መሳተፍ ናቸው፡፡

(መዝሙረ ዳዊት ምዕራፍ 133)
----------
1፤ ወንድሞች በኅብረት ቢቀመጡ፥ እነሆ፥ መልካም ነው፥ እነሆም፥ ያማረ ነው።

2፤ ከራስ እስከ ጢም እንደሚፈስስ፥ እስከ አሮን ጢም፥ በልብሱ መደረቢያ እንደሚወርድ ሽቱ ነው።

3፤ በጽዮን ተራሮች እንደሚወርድ እንደ አርሞንዔም ጠል ነው፤ በዚያ እግዚአብሔር በረከቱን ሕይወትንም እስከ ዘላለም አዝዞአልና።

💯ዛሬ ላይ በሱስና በተለያዩ የህይወት ዝቅጠት ውስጥ ያሉ የዩኒቨርስቲ ተማሪዎችን የኋላ ታሪክ ብታጠኑ አብዛኞቹ ጊቢ ከመግባታቸው በፊት "ጨዋማ ከእሱ ወዲያ የለም" የተባለላቸው ናቸው፡፡

💯ለውጥ የማይቀር ነው፡፡
💯አለመለወጥ ምርጫችሁ አይደለም፡፡ 💯የለውጡ አይነት ግን የእናንተ ምርጫ ነው፡፡

#ትክክለኛውን_ምረጡ👍

@Appeal4Purity
@Appeal4Purity
የቻናልዎን Members በማብዛት አገልግሎትዎን ለብዙዎች ተደራሽ ማድረግ ይፈልጋሉ

እነሆ christian promotion መጣልዎ

የምስራች ለክርስቲያን ቻናሎች Group promo ለመጀመር ዝግጅታችንን አጠናቀን የእርሶን እሽታ ብቻ እየጠበቀን ነው እና ጥሩ ቦታ ለመያዝ ቶሎ ቶሎ ይመዝገቡ

የGp ሰዓት የአገልግሎት ሰዓታችሁን በማያሻማ ሁኔታ በሳምንት 2 ጊዜ መሆኑና የቻናልዎን አባላት የማያሰለች መሆኑ የእኛን Gp ለየት ያደረገዋል ስለዚህ ያሉት ውስን ቦታዎች ሳያልቁ አሁኑኑ ይመዝገቡ

📛 መስፈርታችን fake promotion የማይሰራ እና ሌላ Gp ውስጥ የሌለ

📌 Gp ፕሮግራሙን የሚያካሄደው በ4 አይነት መንገድ ሲሆን እርሱም

1. ከ300-5k members
2. ከ6k-9k
3. ከ10k-19k
4. ከ20k-40k

ለመመዝገብ ከ 10k በላይ ➠ @Agapeloved
ከ10k በታች ➠ @chrispromo
💯 ፍቅር ከጋብቻ ውጪ ወሲብ በመፈፀም አይገለፅም‼️

እውነተኛ ፍቅር የሚገለፀው እስከ ትዳር ድረስ የወሲብን ስሜት አሸንፎ በመቆየት ውስጥ ነው

👉 መጋባታችን ስለማይቀር ብሎ ወደ አልጋ መሮጥ ያቺ ሴት የአልባስጥሮስ ሽቶውን በጌታ እግር ስር ባፈሰሰች ጊዜ ይሁዳ ይህ ሽቶ ቢሸጥ ኖሮ ለብዙ ድሆች በሆነ ነበር ብሎ ካለው የክፉ ሃሳብ #ሽፋን በምንም አይለይም ፡፡

📛 ምንም አይነት ሰበብ ፈጥረን ከጋብቻ በፊት የሚደረግን ወሲብ ከሃጥያት መደርደሪያ ልናወርደው አንችልም 📛

💢💢 @Appeal4purity 💢💢
💢💢 @Appeal4purity 💢💢
#ወሲባዊ_ንፅህና

👉 ሰዎች ስለ ወሲባዊ ንፅህና ምንነት ባሰቡ ጊዜ የሆኑ ለመፈፀም የሚከብዱ ደንብና መመሪያዎች ወደ አእምሮአቸው ይመጣሉ ፡፡

ብዙ ሰዎች ማስተዋል የማይችሉት ነገር ወሲባዊ ንፅህና ማለት እንዲህና እንዲያ ማድረግ አትችሉም የሚል ትዕዛዝ ማለት ሳይሆን ለማድረግ የምንመርጠው ምርጫ መሆኑን ነው ፡፡

📌 ወሲባዊ ንፅህና ማለት የሆነ የምንደርስበት ግባችን አይደለም ፡፡ ይልቁንም በየቀኑ ለመሄድ የምንመርጠው ጎዳና ነው ፡፡

👉 ወሲባዊ ንፅህና ለነዚህ ለሁለቱ ማለትም ለድርጊታችንና ለአመለካከታችን ተግባራዊ የሚደረግ ነው ፡፡

👉 ወሲባዊ ንፅህና ከትዳር ውጪ ካለ ከማንኛውም አይነት ወሲባዊ ድርጊት ለመሸሽ የምናደርገው ምርጫ ነው ፡፡

👉 አእምሮአችንና ልባችንን ከክፉ መሻት ሃሳብና አመለካከት ለመጠበቅ የምናደርገው እርምጃ ነው ፡፡

👉 ከአጭር ጊዜ ደስታ የምንልቅ መሆናችንንና ለህይወታችን የታቀደልን መልካም ነገር ከፊታችን እንዳለ ማመን ነው ፡፡

#General

💢💢 @Appeal4purity 💢💢
💢💢 @Appeal4purity 💢💢
📛 ስለ ዘፈን ጠለቅ ያለ ማብራሪያ
👉ከዶ/ር ተስፋዬ ሮቤሌ

በቅርብ ቀን በ @Appeal4purity ይጠብቁ
📌 እስከዛ ለወዳጆችዎ #ሼር በማድረግ ይጋብዙ

💢💢 @Appeal4purity 💢💢
💢💢 @Appeal4purity 💢💢
በዶክተር ተስፋዬ ሮቤሌ ስለ ዘፈን የተዘጋጀውን ቀደም ያለ( ሁለት ዓመት ያለፈው ) ፅሁፍ ከጉዳዩ አሳሳቢነት አንፃር አሁን ልናቀርብላችሁ ግድ ብሎናል ፡፡

የመጀመሪያው ክፍል እንደሚከተለው ይቀርባል ፡፡

💢💢 @Appeal4purity 💢💢
💢💢 @Appeal4purity 💢💢
“እየመረጥን እንዝፈን! እየመረጥንም እንሞዝቅ!”
የወር ተረኛው ርእሰ ጒዳይ
ከዶ/ር ተስፋዬ ሮበሌ
ወርኀ ሰኔ 2016 ዓ.ም
(እንደ ጐርጐሮሳውያኑ የዘመን ቀመር)

ክፍል አንድ

“ቤት ያጣው ቤተኛ”
የዚህ ጽሑፍ ፅንሰትና ልደት፣ “የወር ተረኛው” ርእሰ ጒዳይ ነው፡፡ ባልንጀራዬ ዮናስ ጐርፌ፣ “ቤት ያጣው ቤተኛ—ሙዚቃ፣ ሙዚቀኛነትና ኢትዮጵያዊቷ ቤተ ክርስቲያን” በሚል ርእስ ያሳተመው መጽሐፍ እንዲሁም መጽሐፉን ተከትሎ የወጡ በርካታ አጸፋዎችና መወድሶች፣ የዚህ ጽሑፍ መነሻ ናቸው፤ መድረሻ ግን አይደሉም 1፡፡ አጸፋዎቹንና መወድሶቹን በተመለከተ ጠቅለል ካለ አስተያየት ያለፈ (ያውም ኢርቱዕ በሆነ መንገድ) ዝርዝር ሐተታ አላቀርብም—ፋይዳ ያለው ስለማይመስለኝ 1፡፡ ጌታ ይችን ምስኪን ጽሑፍ ባርኮ ዳርቻዋን ቢያሰፋ ግን፣ ምንኛ ደስተኛ እሆን ነበር፡፡ ይህች መጣጥፍ፣ “ምስኪን” ያልኋት፣ “በጠባብ ደረት በአጭር ቊመት” በመወሰኗ ብቻ ሳይሆን 2፣ በችኰላ የተጻፈች እንዲሁም ከብዙ አንጻር ጽንፈኛ መጣጥፍ ስለመሰለችኝ ነው—በነሂትለር መንደር እማሆይ ትሪሳ ይወደሱ፣ ይንገሡ የምትል የቅስቀሳ ጽሑፍ ቢጤ፡፡ ከብዙ አንጻር ሳየው የዘመኑ መንፈስ ቋሚው የክርስትና ትምህርት በሚቀዝፍበት እቅጣጫ እየቀዘፈ እንዳልሆነ ከገባኝ ሰነባብቷል፡፡ “ሚስቴን ለመፍታት ፈልጊያለሁ፣ እስቲ ጥሩ ጥቅስ ፈልግልኝ” ወይም “ሊቃውንት የማይወዛገቡበት ርእሰ ጒዳይ ስለሌለ፣ እኔ የምደግፈውን አስተሳሰብ አቅጣጫ የሚከተል ምሁር ስሙንና መጽሐፉን ብትጠቁመኝ” ከሚለው ጀምሮ፣ የዘፈን ዜማ የሚያሰርገው 3፣ “ሜልኮል ትናቀኝ” (2ሳሙ. 6÷21) በሚባለው “ሽብሸባ” በዐውደ ምሕረቱ ላይ የዘፈን ውዝዋዜ፣ ዳንኪራና ዳንስ እስከ ሚያሾልከው ድርስ፣ የዘመኑ መንፈስ “አትዝፈኑ!” ለሚለው ተግሣጽ ብዙ የተመቸ አይደለም—ዞሮ ዞሮ በተለያየ መልክ በደንብ እየተጨፈረ በደንብ እየተረገጠ ነው 4፡፡
እግዚአብሔር የሚሠራውን ግን ማን ያውቃል? ምናልባት ይህ አሁን የተነሣው ውይይት ቤተ ክርስቲያንም ሆነች ቤተ እምነቶች 5፣ የዝምታና የእኔ-የምንተዕዳዬን “ፖሊሲአቸውን” በመለወጥ፣ በጒዳዩ ላይ የአቋም መግለጫ እንዲያወጡ ምክንያት ሊሆን ይችላል፡፡ ከመጥፎ ነገር ውስጥ መልካም ነገር እንዲሁም እጅ በምታኽል ደመና አገር ማጥገብ የሚችለው ልዑል አምላክ እስካለ ድረስ፣ “ድንቄም” የሚለው ምፀት የእኔን መጣጥፍ ሊያኳስስ፣ ሊመጣ የሚችለውንም ለውጥ ሊያሳንስ አይችልም፡፡ ስለዚህም እሞግታለሁ፡፡
ወንድም ዮናስ ጐርፌ የረጅም ጊዜ ወዳጄ ነው (“ረጅም” የሚለው ቅጽል አንጻራዊ መሆኑ የሚጠፋችሁ አይመስለኝም)፡፡ እስከማውቀው ድረስ ወንድም ዮናስ፣ በሙያውም ሆነ በሥነ ምግባሩ ተወዳጅ ሰው ነው፡፡ ግልጽነቱ፣ ለጋስነቱ እንዲሁም ለሰዎች ያለው በቀላሉ የማይነጥፍ ፍቅር በአብዛኞቻችን ዘንድ እንዲከበር አድርገውታል (መቼም ሁሉ ይወደኛል ማለት ሞኝነት፣ ሁሉ ይጠላኛል ማለትም ወፈፌነት መሆኑን እናውቃለን ለዚህም ነው፣ “በአብዛኞቻችን” የሚለውን ቊጥብ ቅጽል የመረጥሁት)፡፡ ምናልባትም ብዙ ልንጠቀምበት ሲገባ፣ በተለያየ ምክንያት (ከአቀራረብ እስከ አስተዳደር፣ ከነገረ መለኮት እስከ ባህል) እንዲሁም ምክንያታዊ በሆነና ባልሆነ ሰበብ፣ የሚገባውን ያህል ያልተጠቀምንበት እርሱም የሚገባውን ያህል ያላገለገለን ሰው ይመስለኛል፡፡ በአንድ ታሪካዊ አጋጣሚ አሠልጥኖ ያቀረባቸው የቡድን መዘምራን፣ ብዙዎቻችንን አስደምመው አስደንቀው አልፈዋል፡፡ እኔ በግሌ እንደነዚያ የተዋጣለት የመዘምራን ቡድን፣ ያን ዐይነት ጡዑመ ዝማሬ፣ እንደ ጅረት የሚፈስ ማኅሌተ እግዚአብሔር ሰምቼ የማውቅ አይመስለኝም፡፡ ያውም ያለአንዳች የሙዚቃ መሣሪያ እንዲያው በአካፔላ (a cappella) ስልት የቀረበ መሆኑ፣ ነገሩን ትንግርት አድርጐት ዐልፏል፡፡ ያን የመዘምራን ቡድን ያላየ ሰው፣ እንዳጋነንሁ ሊጠረጥር ይችላል—ግን አንዳችም ግነት ወይም እብለት የለበትም፡፡ ንባቡ ያመረ፣ ምስጢሩ የጠለቀ፣ ጣዕመ ዝማሬው የረቀቀ መዝሙር ሰምተናል፡፡ ያን የመዘምራን ቡድን እጹብ ድንቅ ዜማ ያየ፣ በወንድም ዮናስ ጐርፌ ውስጥ እጅግ ትልቅ ስጦታና ክህሎት እንደ ታጨቀ የሚያስተውል ይመስለኛል፡፡ ግን ምን ይደረግ፣ የላመ የጣመ ለመብላት የታደልን አይመስልም፡፡ ተቀባብለን መሥራት አልሆንላችሁ፣ ተረዳድቶ መኖር አላምርባችሁ ብሎን ይኸው እንዳለን አለን፡፡ ጆሮ የሚበጥስ የሙዚቃ ጩኸት፣ የገመረረ ድምፅ፣ ለቅዱሳት መጻሕፍት ባዕድ የሆነ ግጥም፣ ለአማርኛ ቋንቋ ባይተዋር የሆነ የሰዋስው አሰካክ፣ ግጥምና ትርጒሙ ለአፍታ ተራክቦ በማያደርጉበት መዝሙር፣ እንዲያው በአጭሩ ሥርና ጫፉ በውል በማይታወቅ የዝማሬ ማዕበል ውስጥ ነው ያለነው፡፡ ቅኔ ዘርፎ፣ ግሥ ገሥሦ፣ ወረብ በማዘጋጀት ማኅሌት መቆም ሲበዛ እልም ነው፡፡
የመሞገት መብት አለኝ!
እኔ፣ ሐሳብን በማንኛውም መልኩ መግለጽ የሰብአዊ መብት አንዱ ክፍል መሆኑን አምናለሁ፡፡ ወንድም ዮናስ የመናገር መብቱን ተጠቅሞ፣ መጽሐፍ በመጻፍ ሐሳቡን እንዳንሸራሸረ ሁሉ፣ እኔም መጣጥፍ በማዘጋጀት ከእርሱ የምለይበትን ሙግት አቀርባለሁ፡፡ ስለዚህ ይህን ከአምላክ የተቸርሁትን መብት እውን ማድረጌ፣ ቢሆን ሊያስመሰግነኝ እንጂ፣ በጭራሽ ሊያስነቅፈኝ አይገባም፡፡ አድበህ ጨምተህ ለምን አትቀመጥም የሚለኝ ካለ ተሳስቶአል፡፡ ከዚህ ባለፈ በሥልጡን ውይይት አገር እንደሚደረጅ፣ ጨለማ እንደሚበራ፣ ነገረ መለኮት እንደሚጐመራ አምናለሁ፡፡ ይህ እውነት ከሆነ፣ ከባልንጀራዬ ጋር እንካ ሰላንታ እንደ ገጠምሁ ሊታሰብ አይገባም፡፡ የጽሑፉም ይዘት ከእንካ ሰላንታ መራቁ፣ ሰላም ወዳድና ጭቅጭቅ ጥዩፍ ለመሆኔ አንዱ አብነት ይመስለኛል፡፡ እንደ ወትሮው ሁሉ፣ ዐቅም በፈቀደ መጠን ሥነ ምግባርን ተከትዬ ሐሳቤን እሰነዝራለሁ፤ ሒሴን አደራጃለሁ፡፡ “ሰው ሆኖ አይስት፣ እንጨት ሆኖ አይጤስ” የለምና ከዚህ የሥነ ምግባር መስፈርት ጐድዬ ብገኝ፣ በአደባባይ ይቅርታ ለመጠየቅ ሙሉ ፈቃደኛ ነኝ፡፡ በምንም ዐይነት መልኩ፣ ከሐሳብ ጋር መጣላት ከግለሰቦች ጋር መጣለት አይደለም፤ ከሐሳብ ጋር መፋጨት ከግለሰቦች ጋር መቧቀስ አይደለም፡፡

እንዲያውም ሐሳቦች ሲቧቀሱ፣ ያሞጠሞጡ ሐሰቦች እየተወቀሩ ቱንቢ ይገባሉ፣ ገለባ የሆኑ ሐሰቦች ይበናሉ፣ ስሑት ሙግቶች ይተናሉ፡፡ ስለዚህ “መርጠን እንዝፈን” የሚለው የወንድም ዮናስ ጐርፌ ነባርና ቋሚ ሙግት፣ ትክክል አይደለም የሚል አቋም አለኝ፡፡ በዚህም ጽሑፍ፣ በምን ምክንያት ወደዚህ ድምዳሜ እንደ ደረስሁ ለመተንተን ሙከራ አደርጋለሁ፡፡ በአጭሩ ከወንድም ዮናስ ጐርፌ በተቃራኒው አንጻር የቆምሁ፣ ክርስቲያን ወንድም ነኝ፡፡

ዶ/ር ተስፋዬ ሮቤሌ

💢💢 @Appeal4purity 💢💢
💢💢 @Appeal4purity 💢💢
ክፍል ሁለት

“ሰጥቶ መቀበል"

ዳር ድንበር ሲጣስ መኻል አገር ወደ ዳርድንበርነት ይቀየራል፡፡ ባላንጣችን ሰይጣንም ሆነ ዓለም ብልኅ ተደራዳሪዎች ናቸው፡፡ “ሰጥቶ መቀበል” የሚባለውን የድርድር ቴክኒክ፣ ከፖለቲከኞቻችን ይልቅ ጠንቅቀው ያውቁታል፡፡ እንዲያው እመር ብለው፣ በአንዴ የመኻሉ አገር ይገባኛል የሚል የገልቱ ጥያቄ አያቀርቡም፤ ደረጃውን በጠበቀ ድርድር ግን፣ መኻል አገር መናገሻ ከተማቸው እንደሚሆን ልቦናቸው ያውቀዋል፡፡ በአሜሪካንና በአውሮፓ አብያተ ክርስቲያናት ሕይወት የታየው፣ ይኸው የድርድር ስልት ነው፡፡ በአንድ ወቅት የአልኮል መጠጥ መጠጣትና ሲጃራ ማጤስ፣ የቅድስና ጠር እንደ ሆኑ በብርቱ ይሰበክ ነበር፡፡ ዛሬ ግን እንኳን በምዕመኑ፣ በመጋብያኑም ዘንድ እንደ ቊም ነገር አይታይም፡፡ በአንድ ወቅት፣ “ሮክ ኤንድ ሮል” የሙዚቃ ሥልት፣ በቤተ ክርስቲያን ውስጥ መቅረብ የለበትም የሚል የጦፈ ክርክር ነበር፡፡ ዛሬ በሮክ ኤንድ ሮል የማይውረገረግ ቤተ ክርስቲያን ማግኘት ሲበዛ አስቸጋሪ ነው 6፡፡ በአንድ ወቅት ክርስቲያን ሰዶማዊ ሊሆን አይገባውም የሚል እሰጥ አገባ ነበር፤ ዛሬ የሰዶማውያኑ የቤተ ክርስቲያን ሙሉ አባልነት ጸድቆ፣ ውይይቱ ጠለቅ መጠቅ ወዳለ ደረጃ ተሸጋግሮል፡፡ ይኸውም ብዙ አብያተ ክርስቲያናት ሰዶማውያንን በሙሉ አባልነት መቀበል ብቻ አጥጋቢ አይሆንም የሚል አቋም ስላላቸው፣ ሙሉ አባልነታቸው እንደ ጸደቀ ሁሉ፣ በቅስናና በሊቃነ ጳጳስነት ከማገልገል መብታቸው ሊጐሉ አይገባም እየተባለ ነው፡፡ ስለዚህ የቅስና መንበራቸውን በመያዝ፣ ሙሉ ክህነታዊ ባርኮት ይስጡን፣ ሥርዐተ ቊርባን ይምሩልን፣ እንዲያው በአጠቃላይ አብነታቸውን ያሳዩን፣ ፋናቸውን ያስከትሉን እየተባለ ነው፡፡ ሙግቱ ደረጃውን ተከትሎ እንዴት እንዳደገ ልብ ይሏል፡፡ “ግማሽ ሕይወት ይመር ግማሽ ሕይወት ዑመር” 7 ማለት ከዚህ ውጪ፣ ሌላ ምን ሊሆን ይችላል?
የዘፈን እንዝፈን፣ የዘፈን አንዝፈን ጥያቄ ከግብረ ሰዶም ክርክር ጋር አንድ ዐይነት ነው እያልሁ አይደለም፡፡ እኔ ሰዶማዊነትን የጠቀስሁት፣ የቤተ ክርስቲያን ሥነ ምግባር እየተጣሰ፣ አስተምህሮዋ እየተማሰ መሆኑን ለማመላከት ያህል ብቻ ነው፡፡ የዚህም ጽሑፍ ቀዳማይ ዐላማዎቹ መኻል አንዱ፣ ይህ የአስተምህሮ ዝግመተ ለውጥ፣ ተገቢ ያለመሆኑን መውቀስና መዝለፍ ነው፡፡ ዘፈን፣ ጭፈራና ዳንኪራ ለኢትዮጵያ የወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት አማኞች ሲበዛ ባዕድ ነው፡፡ ባህል እንደሚለወጥ፣ ቋንቋም እንደሚቀየር ዐውቃለሁ፡፡ በዚህ ረገድ ቋሚ ወይም “ዐፅመ ርስት” የሚባል ነገር እንደ ሌላ እረዳለሁ፡፡ ነገረ መለኮት ግን፣ በዚህ ዐይነቱ የዝግመተ ለውጥ ሂደት ውስጥ ማለፍ አለበት ብዬ በጭራሽ አላምንም 8፡፡ በዝግመተ ለውጥ ሂደት ውስጥ መሆን አለበት ከተባለ ግን፣ በርቱዕ አስተምህሮና በኑፋቄ ትምህርት መኻል ነባራዊ የሆነ ግድግዳ አለ ማለት ያስቸግራል፡፡ የጊዜ ጒዳይ ካልሆነ በቀር፣ የጽድቅ ሰማዕታት ውግዝ አራጥቃ (መናፍቅ) የማይሆኑበት አንዳችም ምክንያት ሊኖር አይችልም፡፡ የጊዜ ጒዳይ ካልሆነ በቀር፣ ክርስትና ከእስልምና ጋር የማይቀላቀልበት፣ ከቡዲሂዝም ጋር ውሕደት የማያደርግበት፣ ከይሁዲ ሃይማኖት ጋር የማይፈጣጠምበት፣ በአጠቃላይ መሥዋዕት እንሆንላቸዋለን የምንላቸው አስተምህሮዎቻችን ለድርድር የማይቀርቡበትም ሆነ፣ የማይለወጡበት አንዳችም ምክንያት አይታየኝም 9፡፡
እውነቱን ለመናገር ዘፈን እንዝፈን ወይስ አንዝፈን የሚለው ጥያቄ፣ የዳር ድንበር ጥያቄ ነው፡፡ የዳርድንበር ጥያቄ የሚሆንበት ቢያንስ ሁለት ዐበይት ምክንያቶች ያሉ ይመስለኛል፡፡ በየትኛውም መስፈርት ርእሰ ጒዳዩ፣ ዐበይት ከሚባሉት ክርስቲያናዊ ትምህርቶች መኻል የሚፈረጅ አይደለም—ከንዑሳን ወይም ከደቂቃን አስተምህሮዎች መኻል እንጂ 10፡፡ ሁለተኛው ደግሞ ርእሰ ጒዳዩ ፍርጥም ያለ አቋም ለመውሰድ አስቸጋሪ የሚያደርጉት ሥነ ምግባራዊ፣ ባህላዊና ነገረ መለኮታዊ ጒዳዮች ጋር መጐዳኘቱ ነው 11፡፡ አንድም ጐበዝ ተነሥቶ፣ “ዝፈኑ” የሚል ጥቅስ ከመጽሐፍ ቅዱስ ሊያሳየን አይችልም፡፡ በአንጻሩ፣ “አትዝፈኑ” የሚሉትን ጥቅሶች አማራጭ ትርጓሜያቸውን በመወሰን፣ ክፍሉ በመደበኛው አካሄድ ዘፈን የሚለውን ቃል የሚወክል አይደለም ማለት ይቻላል (ወንድም ዮናስም ሆነ አንዳንድ “የነገረ መለኮት ድጋፍ ሰጪዎች” ይህንኑ ነው እያደረጉ ያሉት)፡፡ እንግዲያው ሙግታችን ፈርጀ ብዙ ጒዳዮችን ማጣቀሱ፣ ጒዟችንን ውስብስብ ያደርገዋል፡፡ ለዚህ ነው ጒዳዩ የዳርድንበር ጥያቄ ነው ማለት አግባብ የሚሆነው 12፡፡
የእንዝፈንና የእንጨፍር አጀንዳ የቤተ ክርስቲያንን ቅጥር ዐልፎ ከገባ ግን፣ በምንም ሂሳብ ለቤተ ክርስቲያን ክብር ሊሆንላት አይችልም፡፡ ሰዎች በቤተ ክርስቲያን አስተምህሮ ላይ እምነት ሊያድርባቸው አይችልም፡፡ አትዝፈን ሲባል የከረመው ሰው፣ ነገ ዝፈን ከተባለ፣ ዛሬ አትንኩ አትቅመሱ የተባሉ ሥነ ምግባራዊ ጒዳዮች፣ ነገ ላለመለወጣቸው ዋስትናው ምንድን ነው? በምንም ሂሳብ የመሐሙድን ትዝታ ማንጐራጐራችን፣ የቴዲ አፍሮን ጥቊር ሰው መኰምኰማችን ከጥሬነት ወደ ብስልነት አያሻግረንም፡፡ በምንም መልኩ በዚህ መንገድ የውስጥ ፍሥሓና ሐሴት ልንጐናጸፍ አንችልም፡፡ ባለመዝፈኔ ተጐዳሁ፣ ናይት ክለብ (ጭፈራ ቤት) ባለመሄዴ ከደስታ ጐድያለሁ ብሎ የሚቈጭና በዐላፊው ጊዜ የሚብከነከን ክርስቲያን ቢኖር፣ በእውነቱ እጅግ እገረማለሁ 13፡፡ ተገላገለን የሚል እንጂ፡፡ በዚህ ረገድ ለውጥ የሚመጣ ከሆነ (አብያተ ክርስቲያናት ዘፈንን “ግባ” የሚሉት ከሆነ) ለውጡ ከሚያመጣው “በረከት” ይልቅ፣ የሚያስከትለው ጥፋትና መዘዝ ከብዙ አቅጣጫ ሰፊ ነው 14፡፡
የአልኮል መጠጦችን እንጠጣ ወይስ አንጠጣ የሚለውም ክርክር፣ በይዘትም ሆነ በትንታኔው ከዚህ ርእሰ ጒዳይ ጋር በብዙ መልኩ ኲታ ገጠም ነው፡፡ በነገረ መለኮት፣ አንዱ አስተምህሮ ከሌላው ጋር እንደ ሰንሰለት የመያያዝ ጠባይ አለው፡፡ አንዱ ሲፈታ ሌላው ጸንቶ የሚቈምበት ዐቅም ወይም ባሕርይ የለውም፡፡ ምክንያቱም ክርስቲያናዊ አስተምህሮዎች በአንድም ሆነ በሌላ መልክ የመገናኘት፣ የመደጋገፍ፣ የመሰናሰን ባሕርዮት አላቸውና፡፡ ለዚህም ነው መናፍቃን በአንድ አስተምህሮ ሲስቱ፣ ያን አስተምህሮ በሳቱበት ቅጽበት፣ በበርካታ አስተምህሮዎች መንገድ ጥሰው የሚወጡት፡፡ በርግጥ መዝፈን ከጸደቀ፣ የዘፈን መንታ ወንድም የሆነው መጠጥ እነሆ በደጅ ነው 15፡፡ ከዚያም ታናናሽ ወንድሞቹ ማጨስና መቃም፣ “ከልጅ ልጅ ቢለዩ ዓመትም አይቆዩ” በሚለው አካሄድ፣ የይገባኛል ጥያቄ የማቅረብ፣ ሙሉ መብት ይጐናጸፋሉ፡፡ አንዱን ፈቅዶ ሌላውን ወግድ ማለት በፍጹም አይቻልም፡፡ ሁሉን ደግፎ የያዘው መሠረት ከተናደ፣ በምን መሠረት ላይ ቆሞ እነዚህን ተጓዳኝ ጒዳዮች ወግድ ማለት እንደሚቻል አይገባኝም፡፡ በዚህ አንጻር ሲታይ ዛሬ እየተሟገትን ያለነው፣ በዘፈን ርእሰ ጒዳይ ላይ ብቻ አይደለም፤ ከእርሱ ጋር ተጓዳኝ በሆኑ ፈርጀ ብዙ ግብረገባዊ ርእሶች እንጂ 16፡፡

ዶ/ር ተስፋዬ ሮቤሌ

💢💢 @Appeal4purity 💢💢
💢💢 @Appeal4purity 💢💢
Forwarded from YM4TN-Mekelle
ይህ ቪዲዮ በሱሰ፣ በጭንቀት፣ በማስመሰል ፣ እራስን የማጥፋት ሀሳብ፣ ትርጉም የሌለው ህይወት ከመኖር ፣ ከጭንቀት የተነሳ እንቅልፍ በማጣት ለሚሰቃዩ ወጣቶች የመውጫ መንገድን የሚያሳይ ነው።

በነዚህም ነገሮች ለሚሰቃዩ ወጣቶች በመላክ ወንጌልን እንስራ።
⬇️⬇️⬇️⬇️
Forwarded from YM4TN-Mekelle
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ክፍል ሶስት

ዘፈን ወይስ መዝሙር

ቋንቋ የሰዎች ስምምነት ውጤት ነው፡፡ በሬን በሬ ለማለት፣ ግድግዳን ግድግዳ፣ አህያን አህያ ለማለት አንዳችም ሥነ አመክንዮአዊ ምክንያት የለም፡፡ አንድ ቃል በሚወክለው ሐሳብ ወይም በሚያመለክተው ነገር ስንስማማ ተግባቦት ይፈጠራል፡፡ በዚህ አንጻር የአንድን ቃል ትርጒም የመወሰን እንዲሁም አማራጭ ትርጓሜውን የመለጠጥም ሆነ (እንደ ብር ማሰሪያ ላስቲክ) የማሳነስ ሙሉ መብቱ የቋንቋው ተጠቃሚዎች ነው፡፡
የአማርኛ መዝገበ ቃላት፣ ዘፈን እና መዝሙር ለሚሉት ቃላት ያቀረቡላቸው ገለጻ፣ በብዙ መልኩ አንድ ዐይነት ነው፡፡ እንዲያውም በአንዳንድ ዐውደ ምንባቦች ውስጥ፣ ሁለቱንም ቃል ያለአንዳች የትርጒም ለውጥ እያቀያየርን በተወራራሽነት ልንጠቀምባቸው እንችላለን፡፡ በወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት አካባቢ ግን፣ ዘፈን እና መዝሙር እጅግ ደማቅ መስመር ተበጅቶላቸዋል፡፡ ይህም የወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ስያሜ፣ በማኅበረሰቡ ዘንድ ተቀባይነት አግኝቶአል፡፡ መዝሙር የሚለው ቃል በተለያየ መልኩ ከአምልኮተ እግዚአብሔር (ለአምላክ ከሚቀርብ ማኅሌት) ጋር የሚጐዳኝ ሲሆን፣ ዘፈን የሚለው ደግሞ ከዚህ ውጭ ያለው ሁሉ ነው፡፡ እኔ በዚህ ጽሑፍ ዘፈንና መዝሙር የሚሉትን ቃላት የምጠቀመው፣ የወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት መደበኛ በሆነው መንገድ ቃላቱን በሚጠቀሙበት ትርጒማቸው ነው፡፡ ስለዚህ በርእሰ ጒዳዩ ላይ የምናካሄደው ውይይት፣ በቃላት መረጣ ላይ የሚደረግ ውይይት፣ እንዲያው ዝም ብሎ የቃላት ጭቅጭቅ ተደርጐ መወሰድ የለበትም—ቃላቱ በሚወክሉት ፅንሰ ሐሳብ ላይ የሚካሄድ ሙግት እንጂ፡፡
እኔ እስከማውቀው ድረስ፣ በኢትዮጵያ የሚገኙ ሁሉም የወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት፣ ክርስቲያን ዘፈን መዝፈን የለበትም የሚል ጠንካራ አቋም አላቸው፡፡ ብሔራዊ መዝሙሮች ወይም ለአገራቸው ትልቅ ሥራ ሠርተው ያለፉ ጀግኖችን የሚያሞካሹ ዘፈኖችን በተመለከተ ግን፣ ክርስቲያኑ ማኅበረሰብ የተለያየ አቋም ያለው ይመስለኛል 17፡፡ አንዳንድ ክርስቲያኖች ብናደርገው ምንም አይደለም ሲሉ፣ አንዳንዶች ደግሞ ዜማ የተቀላቀለበት ነገር ከአድናቆት ወደ አምልኮ የመንደርደር ጠባይ ስላለው፣ ክርስቲያኖች እንዲህ ዐይነቱን ዘፈን መዝፈን የለባቸውም ባዮች ናቸው፡፡ አንዳንዶች ደግሞ በዚህ መልክ ጀግኖችን ማድነቅ፣ ለሰዎች ኅሊናዊ ብያኔ መተው አለበት ይላሉ (ሮሜ 14÷1-6)፡፡ እኔ እስከሚገባኝ ድረስ፣ በኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ዘንድ ያለው ልዩነት ይህ ብቻ ነው፡፡
ወንድም ዮናስ በዘፈንና በመዝሙር መካከል ያለው ግድግዳ፣ ሙሉ ለሙሉ መፍረስ አለበት የሚል አቋም የለውም፡፡ ለዚህ ምክንያቱ ደግሞ በአውስቦት/በፍትወት የነፈዙ፣ በጦረኝነት የከነፉ፣ በደም የሰከሩ፣ በጥላቻ የተሞሉ፣ በዘረኝነት የጨቀዩ በቀላል አነጋገር ከክርስቲያናዊው ሥነ ምግባር ጋር በእጅጉ የሚጣረሱ በርካታ ዘፈኖች ስላሉ ነው፡፡ በዚህ ምክንያት ክርስቲያኖች፣ “እየመረጡ መዝፈን” ይጠበቅባቸዋል ባይ ነው፡፡ ነገር ግን መጽሐፍ ቅዱስ ሙሉ ለሙሉ ፈቅዷል ብሎ እየሞገተ፣ በአንጻሩ ደግሞ የተወሰኑ ማዕቀቦች መኖር አለባቸው ለምን እንደሚል ለእኔ ግልጽ አይደለም—ማለትም በምን ሒሳብ ነው ማዕቀብ የሚጥልባቸው? ለማለት ፈልጌ ነው 18፡፡ የሆነው ሆኖ፣ በዚህ አንጻር ሲታይ ወንድም ዮናስ በሩ ሙሉ ለሙሉ እንዲዘጋ፣ በአንጻሩ ደግሞ ሙሉ ለሙሉ እንዲከፈት አይፈልግም—እየመረጥን እንድንዘፍን፣ እየመረጥን እንድንሞዝቅ እንጂ 19—በሌላ አነጋገር በሩ ደርበብ ተብሎ እንዲከፈት እንጂ፣ ሙሉ ለሙሉ ወለል ተድርጎ እንዲከፈት አይፈልግም፡፡ የሙዚቃ መሣሪያ ተጫዋቾችም ላይ ያለው አካሄድ፣ “ደርበብ ተብሎ ይከፈት” ከሚለው የተለየ አይደለም 20፡፡ እኔ ደግሞ ክርስቲያኖች እየመረጡ መዝፈን የለባቸውም፣ የሙዚቃ መሣሪያ ተጫዋቾችም እየመረጡ መሞዘቅ የለባቸውም የሚል አቋም አለኝ፡፡ ከዚህ አንጻር ሲታይ እኔ ሙሉ ለሙሉ ይዘጋ ባይ ነኝ 21፡፡ ስለዚህ በእኔና በወንድም ዮናስ መካከል ያለው ልዩነት፣ ሙሉ ለሙሉ ይዘጋ በሚለውና 22 በተወሰነ ደረጃ ደርበብ ተደርጐ ይከፈት በሚሉት መሠረታውያን ነጥቦች ላይ ያለ ልዩነት ነው፡፡ ወንድም ዮናስ ሙሉ ለሙሉ አይዘጋ፣ ሙሉ ለሙሉም አይከፈት የሚለው አማራጭ፣ ወዲህ ወዲያ እንዲያጣቅስ ሰፊ የሙግት መላወሻ ስፍራ የሰጠው ሊመስለው ይችላል፡፡ ነገር ግን ከብዙ አንጻር ደርበብ ብሎ መከፈቱ፣ ሙሉ ለሙሉ ወለል ብሎ ከመከፈት ይልቅ፣ ዝርክርክ መሆኑን ወደ መሞገቱ ልዝለቅ፡፡
አንደኛ፣ መጽሐፍ ቅዱስ ዘፈንን ሙሉ ለሙሉ ስለከለከለ፣ ሙሉ ለሙሉ ልንከፍተው አንችልም (ኋላ እሞግትበታለሁ)፡፡ ሁለተኛ፣ መጽሐፍ ቅዱስ በዚህ ጒዳይ ላይ አንዳችም አስተያየት ባይሰጥ እንኳ፣ አስተያየት ያለመስጠቱ እንዳሻችሁ አድርጉት ወደሚለው ድምዳሜ እንጂ 23፣ አድርጉት የሚለውን ፈቃድ መስጠቱን በጭራሽ አያሳይም፡፡ ሦስተኛ፣ ዘፈን አትዝፈኑ የሚለው አቋም የወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ቋሚ ትውፊት ነው፡፡ ትውፊቱ ደግሞ ከብዙ አንጻር ጠቀመን እንጂ አልጐዳንም—ቢያንስ ከወጪ ቀሪ ጥቅሙ አመዝኖ ተገኝቶአል 24፡፡ አራተኛ፣ በአካሄድ ወይም በአፈጻጸም ደረጃ ሲታይ፣ በተወሰነ ደረጃ ይከፈት የሚለው ሐሳብ፣ ሙሉ ለሙሉ ይከፈት ከሚለው ይልቅ ውስብስብ ችግሮች አሉበት፡፡ ለምሳሌ ዘፈኖችን የምንገመግምበት፣ በሰዎች ሁሉ ዘንድ ተቀባይነት ያለው ወጥ መስፈርት ማዘጋጀት አዳጋች ስለሆነ፡፡ እንዲሁም ቤተ ክርስቲያን ዘፈኖችን ሁሉ አንድ በአንድ ገምግማ፣ በእያንዳንዱ ዘፈን ላይ መግለጫ ልታወጣ አትችልም፡፡
“ስለልተኰነነ መደገፉን ያሳያል”
ወንድም ዮናስ መጽሐፍ ቅዱስ ዘፈንን አልከለከለም፤ ዘፈንን አልኰነነም የሚለውን ሙግት አስታኮ፣ ስላልተኰነነ (ስላልተከለከለ ወይም ስላልተቃወመ) ደግፏል ማለት ነው፤ የሚል ድምዳሜ ላይ ደርሷል፡፡ ይህ ሙግት መሠረታዊ የሆነ የአመክንዮ ችግር አለበት፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ ያለመኰነኑ (ያለመከልከሉ፣ ያለመቃወሙ፣ ያለማውገዙ)፣ አድርጉ የሚል ፈቃድ መስጠቱን በጭራሽ የሚያሳይ አይደለም (ኰንኗል የሚለውን ሙግቴን በቀጣይነት አቀርባለሁ)፡፡ እርሱ “አትዝፈኑ የሚል መከልክል አላኖረም” የሚል ከሆነ፣ በሌላ አንጻር ያለው ሰው ደግሞ፣ “ዝፈኑስ የሚል ፈቃድ መቼ ሰጠ?” የሚል ሙግት ሊያቀርብ ይችላል፡፡ የይሖዋ ምስክሮች፣ “‘ኢየሱስ አምላክ ነኝ’ አላለም፤ ስለዚህ አምላክ አይደለም” የሚል ክርክር ይገጥማሉ፡፡ እኔ ደግሞ፣ “‘አምላክ ነኝ’ ብሎ ያለመናገሩ አምላክ ያለመሆኑን የሚያሳይ ከሆነ፣ ‘አምላክ አይደለሁም’ ስላላለ፣ አምላክ ነው ማለት ነው” የሚል አጸፋ አቀርባለሁ፡፡ የእኔ ሙግት የእነርሱን ሙግት አካሄድ የተከተለ ቢሆንም፣ በሁለቱም ወገን ይህ የጥሩ ሙግት አካሄድ አይደለም፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ የኢየሱስን አምላክነት የሚያስተምረው በራሱ የሙግትና የትንታኔ መንገድ እንጂ፣ እኛ እንዲልልን በፈለግነው መንገድ አይደለምና፡፡ ስለዚህ መጽሐፍ ቅዱስ አልከለከለም ማለት ፈቅዷል ማለት እንዳልሆነ ሊሰመርበት ይገባዋል፡፡

ዶ/ር ተስፋዬ ሮቤሌ

💢💢 @Appeal4purity 💢💢
💢💢 @Appeal4purity 💢💢
ክፍል አራት

ወንድም ዮናስ ዘፈንን ይከለክላሉ በመባል የሚጠቀሱትን የመጽሐፍ ቅዱስ ምንባባት በመጥቀስ፣ አለመከልከላቸውን ከመሞገት ባሻገር፣ መዝፈንን ደግፈዋል ወደሚል ሐሳብ ሙግቱን ቀልብሶታል፤ አጡዞታል፡፡ ይህ ፍጹም ስሕተት ነው፡፡ ለዚህ ነው አልከለከለም የሚለው ክርክር፣ ደግፎአል ከሚለው ክርክር መነጠል የሚኖርበት፡፡ በዚህ ሒሳብ ሲታይ ወንድም ዮናስም ሆነ የእርሱን ሐሳብ የሚጋሩ ወገኖች መጽሐፍ ቅዱስ ዘፈንን ደግፎአል የሚል አንዳችም ሙግት እንዳላቀረቡ እንዲሁም አንዳችም መጽሐፍ ቅዱሳዊ ድጋፍ እንደ ሌላቸው፣ ሕዝበ ክርስቲያኑ በግልጽ ሊያውቅ ይገባዋል 25፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ በእነዚህ ወገኖች እየተጠቀሰልን ያለው፣ “ዘፈንን ኀጢአት አትበሉ” ለማለት እንጂ፣ “መጽሐፍ ቅዱስ ዘፈንን ይደግፋል” ለማለት አይደለም፡፡
“የምሁራን አስተያየት”
ወንድም ዮናስ ጐርፌ በግሪክ ቋንቋ ዕውቀታቸው የተመሠከረላቸውን ሰዎች ስለጠቀስሁ፣ መጽሐፍ ቅዱስ ዘፈንን አለመኰነኑን ተቀበሉ ብሎናል 26፡፡ የመስኩ ምሁራንን አስተያየት ጠይቆ ሙግት ማደራጀት፣ የትክክለኛ ሙግት አካሄድ ነው 27፡፡ ወዳጄ ይህን በማድረጉ አንዳችም ቅሬታ የለኝም፡፡ የመስኩን ምሁራን አስተያየት ዐውቆ ሙግትን ማዋቀር በተመለከተ ግን፣ ልናውቃቸው የሚገቡ ቢያንስ ሦስት መሠረታውያን ነጥቦች ያሉ ይመስለኛል (ከርእሳችን ጋር በተጐዳኘ)፡፡ አንደኛ፣ በርእሰ ጒዳዩ ላይ የመስኩ ምሁራን አንድ ዐይነት አቋም አላቸው ወይስ የላቸውም የሚለው ጒዳይ በትክክል መመለስ ይኖርበታል፡፡ ለምሳሌ ሥነ ፍጻሜን አስመልክቶ የነገረ መለኮት ምሁራን አንድ ዐይነት አቋም የላቸውም፡፡ አንድ ሰው በአንዱ ወገን የተሰለፈውን ምሁር በእማኝነት በመጥቀስ ብቻ፣ የመስኩ ምሁራን ሁሉ አንድ ዐይነት አቋም አላቸው፣ ስለዚህ ሙግቴን ተቀበሉ ቢል ሙግቱ ትክክል አይሆንም፡፡ ሁለተኛ፣ ወንድም ዮናስ እነዚህ ምሁራን ሰጥተውኛል የሚለውን አስተያየት እኔ የምመለከተው በአምስት አቅጣጫ ነው:— (1) ምናልባት የሚፈልገውንና ሙግቴን ያጠናክራል የሚለውን መረጃ ብቻ መርጦ ቢሆንስ? (2) የነገሩትን ነገርበትክክል አላስተዋለው ቢሆንስ? (3) የነገሩትን መረጃ በተሟላ መልክ አልነገረን ቢሆንስ? (4) ግለሰቦቹ ተሳስተው አሳስተውት ቢሆንስ? (5) የነገሩትን መረጃ በትክክል አልተነተነው ቢሆንስ? እነዚህን አማራጭ ትንታኔዎች የማቀርብበት፣ አጥጋቢ ምክንያት አለኝ (ከሦስተኛው ነጥብ በኋላ ያለውን ትንታኔ ይመለከቷል)፡፡ ሦስተኛ፣ አስተዳደጋችን በቅዱሳት መጻሕፍት አተረጓጐማችን ላይ አዎንታዊም ሆነ አሉታዊ ተጽእኖ እንዳለው ማወቅ ይኖርብናል፡፡ በዚህ ረገድ አንድ ናሙና ላቅርብ፡፡ ከተለያየ የሕይወት ተሞክሮና ከተለያየ አገር የመጡ ወጣቶች፣ በሉቃስ ወንጌል ምዕራፍ ዐሥራ አምስት ላይ የሚገኘውን ጠፍቶ የተገኘውን ልጅ ታሪክ አንብበው፣ ያነበቡትን ታሪክ በትረካ መልክ እንዲያቀርቡት ተደረገ፡፡ የሚያስደንቀው ነገር ከአፍሪካ የመጡት ወጣቶች በሙሉ፣ ልጁ በመራቡና በመቸገሩ ጒዳይ ላይ ትልቅ ትኵረት ሰጥተው ሲናገሩ፣ ከሰሜን አሜሪካ የመጡት ወጣቶች መኻል ግን አንድም ሰው ልጁ የመራቡን ጒዳይ አልጠቀሰም 28፡፡ ይህ ክሥተት አንድ ትልቅ ቊም ነገር የሚያስጨብጠን ይመስለኛል፡፡ ይኸውም አስተዳደጋችን፣ በቅድመ ግንዛቤያችንና በአተያያችን ላይ አዎንታዊም ሆነ አሉታዊ ተጽእኖ እንዳለው የሚያስተምር ነው፡፡ ወንድም ዮናስ ጥያቄ ያቀረበላቸው ሰዎች አብዛኞቹ ከምዕራቡ አገር የመጡ መሆናቸው፣ አንዳንድ መረጃዎችን እኛ ኢትዮጵያውያን ባየንበት መልክ እንዳያዩ ሊያደርጋቸው ይችላል፡፡ ሁሉም ባይሆኑ እንኳ፣ በምዕራቡ ዓለም ያሉ አብዛኞቹ አብያተ ክርስቲያናት ዘፈንን እንደ ኀጢአት አይመለከቱም 29፡፡ ይህ አመለካከት ደግሞ ቀስ በቀስ ወደ ምዕራብ አብያተ ክርስቲያናት የገባ የለዘብተኝነት ጅኒ ነው፡፡ ስለዚህ መጠየቅ ያለብን ጥያቄ፣ “እናንተ ኢትዮጵያውያን ከምንባቡ አየነው የምትሉት መረጃ በርግጥ በክፍሉ ውስጥ አለ?” የሚለው እንጂ፣ “ምዕራባውያኑ ስላላዩ፣ እናንተም ልታዩ አትችሉም” የሚለው ሊሆን አይገባውም፡፡ ለዚህም ነው የመጽሐፍ ቅዱስ ምሁራን፣ ነገረ መለኮት ዓለም ዐቀፋዊም ሆነ ቀዬአዊ ውበት አለው የሚሉት፡፡ ያየነውን መረጃ ምዕራባውያኑም ሊያዩትና ሊቀበሉት በሚችል መልክ ላብራራ፡፡
“ኮሞስ ዘፈንን አያካትትም”
ነገሩ እንዲህ ነው— የአማርኛ የመጽሐፍ ቅዱስ ትርጒሞች፣ “ዘፈን” ብለው የተረጐሙት፣ ግሪኩ “ኮሞስ” (κῶμος) የሚለውን ቃል ነው 30፡፡ ይህን የግሪክ ቃል፣ የግሪክ መዝገበ ቃላት ሦስት አማራጭ ትርጒሞች አቅርበውለታል (ሮሜ 13÷13፤ ገላትያ 5÷21፤ 1ጴጥሮስ 4÷3)፡፡ አንደኛው፣ ቅጥ ያጣ፣ ኢሥነ ምግባራዊ የሆነ፣ ከአውስቦት/ከወሲብ ጋር የተገናኘ፣ በአልኮል መጠጥ የተደገፈ ጭፈራ 31፡፡
ሁለተኛ፣ በአረማውያን የጣኦት አምልኮ ወቅት የሚካሄድ ጭፈራና ዜማ 33፡፡ ሦስተኛ፣ የመንደር ክብረ በዓል፤ ታላቅ ደስታ፣ ፈንጠዝያ 32፡፡
ወንድም ዮናስ “ኮሞስ” (κῶμος) የሚለው የግሪክ ቃል፣ ሁለት ትርጒሞች እንዳሉት ቢጠቅስም (አንደኛውና ሁለተኛው ትርጒም)፣ የእርሱ ዐላማ ከዳር የሚደርሰው ግን፣ ቃሉ በመጀመሪያው ትርጒሙ ብቻ ጥቅም ላይ ከዋለ ነው፡፡ ነገር ግን አንደኛውና ሦስተኛው ትርጒም ከእርሱ አቋም ጋር በቀጥታ ይቃረናሉ፡፡ በቅድሚያ አንደኛውን ትርጒም እንመልከት፣ “ቅጥ ያጣ፣ ኢሥነ ምግባራዊ የሆነ፣ ከአውስቦት/ከወሲብ ጋር የተገናኘ፣ በአልኮል መጠጥ የተደገፈ ጭፈራ” 34፡፡ “ቅጥ ያጣ” የሚለው ገለጻ፣ “ቅጥ ያው ዘፈን አለ እንዴ?” የሚለውን ትርጒም ይጭራል፡፡ ለእኔ ብዙ ግልጽ ስላልሆነ፣ ለውይይታችንም ብዙ እርባና ያለው ስላልመሰለኝ ብናልፈውስ? “ኢሥነ ምግባራዊ የሆነ” የሚለው ቃል፣ ከክርስትና ሥነ ምግባር ጋር የሚቃረኑ ብዙ ዘፈኖችን ከመስመር የሚያስወጣቸው ይመስለኛል፡፡ ከአውስቦት/ከወሲብ ጋር የተገናኘ የሚለው ሐረግ ደግሞ፣ ሰማንያ በመቶ የሆነውን ኢትዮጵያዊ ዘፈን ዶግ ዐመድ ያደርገዋል (ያራግፈዋል) 35፡፡ የአገራችን አብዛኛው ዘፈን የተቃራኒ ጾታን ፍቅር ታሳቢ ያደረገ መሆኑ የሚያከራክረን አይመስለኝም፡፡ “በአልኮል መጠጥ የተደገፈ” የሚለው ሐረግ ደግሞ፣ ዘፈን በአልኮል መጠጥ መታገዝ እንደሌለበት የሚያሳስብ ነው፡፡ ይህ ደግሞ የምሽት ጭፈራ ቤቶች ይዘጉ የሚል ዐዋጅ ዐይነት ነው፡፡
ሁለተኛው ትርጒም ብዙ የሚያከራክረን ስላልሆነ ወደ ሦስተኛው ትርጒም እንዝለቅ፣ “የመንደር ክብረ በዓል፤ ታላቅ ደስታ፣ ፈንጠዝያ”፡፡ ይህ ለወንድም ዮናስም ሆነ “እየተመረጥ ይዘፈን” ለሚሉ ወዳጆቼ ሁሉ የራስ ምታት ነው 36፡፡ ምክንያቱም ማናቸውንም ዐይነት ፈንጠዝያዎች ወይም ደስታ የማግኛ ጥረቶች ሁሉ ፉርሽ ስለሚያደርጋቸው፡፡ ሙዚቃ ለፊሽታ እንዳይውል ከከለከለ፣ እንግዲያው ምን ቀረልን? ለአምላክ ጥዑመ ዝማሬ ከማቅረብ በስተቀር አንዳችም ምርጫ ያለን አይመስለኝም፡፡


ዶ/ር ተስፋዬ ሮቤሌ

💢💢 @Appeal4purity 💢💢
💢💢 @Appeal4purity 💢💢
እራስዎን በስልጠና በማሳደግ ሁለንተናዊ ስኬትን መቀናጀት ይፈልጋሉ

ፍካት የስነ ልቦና ማዕከል

👉 በመሪነት፥በቢዝነስ፥በስኬታማ የትዳር ህይወትና በሌሎች ጉዳዮች ላይ ሰርተፍኬት የሚያሰጥ ስልጠና አዘጋጅትዋል፥

በወር 24 ብር ብቻ ይከፍላሉ፥ለመመዝገብ 6374 ላይ ok ብለው ይላኩ

📲 6374 ላይ ok ብለው በመላክ ያሰቡበት የሚደርሱበትን የስነ ልቦና ስልጠና ይውሰዱ
ክፍል አምስት

ወንድም ዮናስ በዋነኝነት ሊታይልኝ የሚገባው ሁለተኛው ትርጒም ብቻ ነው የሚል ክርክር አለው (አንደኛው ትርጒም ደግሞ በደምሳሳው)፡፡ ይህን አካሄድ የመረጠው ሌሎቹ ትርጒሞች ጥረቱን ሁሉ መና ስለሚያስቀሩበት ይመስለኛል፡፡ እኔ ደግሞ አንደኛውና ሦስተኛው ትርጒሞች በአንክሮ ይታዩልኝ እያልሁ ነው (ዐላማዬን ቤቱ ስለሚያደርሱልኝ)፡፡ እርሱ “ኮሞስ” (κῶμος) የሚለው ቃል፣ እኛ በመደበኛው አነጋገር ዘፈን ብለን የምንጠራውን ቃል የሚወክል አይደለም ከተባለ፣ እኔ ደግሞ እነዚህኑ መዝገበ ቃላት ጠቅሼ (በተለይ አንደኛውንና ሦስተኛውን ትርጒም)፣ “ነው እንጂ ጐበዝ!” ብል፣ የዳኝነት ፍርዱ እንዴት ሊሰጥ ይችላል?
ወገኖቼ በዚህ ረገድ ያለው የዳኝነት ፍርዱ እንዴት ይሰጥ፣ የሚለው ጒዳይ እጅግ ወሳኝ ጥያቄ ነው፡፡ የአንድን ቃል አማራጭ ትርጒም የሚወስነው ቃሉ የሚገኝበት ዐረፍተ ነገር ወይም ዐውድ እንደ ሆነ ቅቡል ነው፡፡ በዚህ ዐይነቱ ሁኔታ ቃላት አሻሚ ትርጒም ሲኖራቸው፣ በዋነኝነት የምንጠቅሰው ቃሉ የሚገኝበት ዐውድ ወይም ዐረፍተ ነገር የሚያቀርቡትን ማብራሪያ ነው፡፡ ነገር ግን ይህ ቃል የሚገኝባቸው ዐውደ ምንባቦች ሁሉ (ሮሜ 13÷13፤ ገላትያ 5÷21፤ 1ጴጥሮስ 4÷3) 37፣ ቃሉን ይጠቀሙ እንጂ፣ ቃሉ በየትኛው ትርጒሙ ጥቅም ላይ መዋል አለብት የሚለውን ጒዳይ ለመወሰን የሚያስችል ፍንጭ አልሰጡንም (የእኔንም ሆነ የወንድም ዮናስን የአማራጭ ትርጓሜ መረጣ ለማጽደቅ የሚያስችል አቅጣጫ ጠቋሚ ማለቴ ነው) 38፡፡ ግራም ነፈሰ ቀኝ ወንድም ዮናስ የጠቀሳቸውን ክፍሎች እንዲሁም መዝገባ ቃላት ጠቅሼ አትዝፈኑ ወይም ዘፋኝነት ኀጢአት ነው ማለት የሚከለክለኝ አንዳችም ምክንያት ያለ አይመስለኝም፡፡ ምክንያቱም ለቃሉ የቀረቡለት አማራጭ ትርጒሞች እኛ ዘፈን ብለን ከምንጠራው ቃልና ሐሳብ ጋር የሚጓደኙ ናቸውና፡፡ የመልእክቶቹ ቀዳማይ ተደራስያን ወይም የመልእክቶቹ ጸሓፍያን በአካል ተገኝተው፣ “እኔ ማለት የፈለግሁትና ክፍሉንም መተርጐም የሚጠበቅባችሁ በዚህ ትርጒሙ ብቻ ነው” የሚል ማሳሰቢያ ካልሰጡን በስተቀር፡፡ ልብ በሉ እነዚህን ሦስት አማራጭ ትርጒሞች ያገኘነው ስመ ጥር ከሚባሉትና በነገረ መለኮቱ ዓለም ሙሉ ተቀባይነት ካላቸው መዝገበ ቃላት ነው፡፡ እነዚህ መዝገበ ቃላት ደግሞ የሐዲስ ኪዳን ጸሓፍያን ጽሑፋቸውን በሚጽፉበት ወቅት ቃሎቹ የነበሯቸውን ትርጒሞችና የያዙትን አማራጭ ትንተናዎች የሚያገልጹ ናቸው 39፡፡ ስለዚህ ዘፈንን ለመኰነን እነዚህ ጥቅሶች አያስሄዷችሁም የሚባልበት አንዳችም ምክንያት የለም 40፡፡
አንባቢዎቼ እንዲረዱልኝ የምፈልገው አንድ ቊም ነገር አለ፡፡ ይኸውም በእማኝነት የጠቀስኋቸው የግሪክ መዝገበ ቃላት፣ “ኮሞስ” የሚለውን ቃል የፈቱልን፣ “የሐዲስ ኪዳን ጸሓፍት ጽሑፋቸውን በሚያጠናቅሩበት ጊዜ፣ ቃሉ ምን ትርጒም እንዲሸከምላቸው ፈልገው ነው? የመልእክቱ ቀዳማይ ተደራስያንም ቃሉን ሲያነቡ በአእምሮአቸው የሚያቃጭለው ትርጒም ምንድን ነው?” የሚለውን መሠረታዊ ጭብጥ ታሳቢ አድርገው ነው፡፡ እውነቱ ይህ ከሆነ እነዚህ አማራጭ ትርጒሞች በዋዛ ፈዛዛ ሊታዩ አይገባም፡፡ በሐዲስ ኪዳን መጻሕፍት ውስጥ እነዚህ ሦስት ትንተናዎች “ኮሞስ” የሚለውን ቃል በትክክል ባይወክሉ ኖሮ፣ በአማራጭነት በአማራጭ ትንታኔ ውስጥ አይካተቱም ነበር፡፡
ወንድም ዮናስ በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ “ዘፈን” የሚለው ቃል ተቀይሮ ሁለተኛው አማራጭ ትርጒም ብቻ ተብራርቶ ይቀመጥልኝ/ይጻፍልኝ እያለ ነው፡፡ ቊም ነገሩ ግን ቃሉ ሳይሆን ቃሉ የወከለው ሐሳብ ምንድን ነው የሚለው ነው፡፡ “ዘፈን” የሚለው የአማርኛ ስያሜ አያስፈልግም ከተባለ፣ ሁለተኛው ትርጒም ተብራርቶ ይቀመጥ እንደ ተባለው ሁሉ፣ አንደኛውና ሦስተኛው ትርጒም ተብራርቶ ይቀመጥ የማልልበት ምክንያቱ ምንድን ነው? 41 አንደኛውና ሦስተኛው ትርጒም ደግሞ እኛ ዘፈን የምንለውን ቃል ለመወከሉ የሚያጣላን አይመስለኝም፡፡ እንዲያውም አብዛኞቹ የ“ኮሞስ” (κῶμος) አማራጭ ትርጓሜዎች፣ ክርስቲያኖች በጭፈራ ቤት እንዲገኙም ሆነ፣ በጭፈራው ቤት ውስጥ የሙዚቃ መሣሪያ እንዳይጫወቱ አጥብቆ ይከለክላል (ጐበዝ አማራጭ ትርጓሜዎቹ ሁሉ በርጋታ ይታዩልኝ)፡፡ ይከለክላል ስል ፍጹም ይከለክላል ማለቴ እንጂ፣ እየመረጡ ይዝፈኑ እየመረጡ ይሞዝቁ የሚለውን አያሳይም፡፡ በዚህ ሂሳብ ሲታይ፣ ወንድም ዮናስ የመጽሐፍ ቅዱስ ተርጓምያን፣ የነገረ መለኮት ሰዎች፣ አንዲሁም የቤተ ክርስቲያን መምህራን አሳስተውናል የሚለው መሪር ክሱ፣ ፍጹም ፍትሓዊ አይደለም፡፡ እንዲያውም እውነቱ፣ እርሱና ባልንጀሮቹ፣ ክርስቲያኑን ማኅበረሰብ እያሳሳቱ ነው (ይህን የሚያደርጉት ግን ባለማወቅ ይመስለኛል)፡፡ እንግዲያው ወገኖቼ ይህ የሙግት አካሄድ በደንብ ከገባችሁ፣ መጽሐፍ ቅዱስ ዘፈንን ይከለክላል ብላችሁ መስበክም ሆነ ማስተማር ሙሉ መብታችሁ ነው፡፡ ድሮም እያደረጋችሁት ነበር፣ አሁን ደግሞ ከሙሉ ዕውቀት ጋር ቀጥሉበት፡፡ ይህን ማድረጋችሁ ከመጽሐፉም ሆነ ከሊቃውንቱ ጋር መስማማታችሁ የሚያሳይ ነው፡፡ ዘፈን ኀጢአት ነው፡፡ አራት ነጥብ 42፡፡
የኮይኔ ግሪክ መዝገበ ቃላት “ኮሞስ” የሚለውን የግሪክ ቃል፣ “በአረማውያን የጣኦት አምልኮ ወቅት የሚካሄድ ጭፈራና ዜማ” 43 በሚለው ትርጒሙ ብቻ አልተረጐሙትም፡፡ እንዲያ ተርጒመውት ብቻ ቢሆን፣ የወንድም ዮናስ ክርክር ሚዛን የደፋ ነበር፡፡ ነገር ግን፣ “ቅጥ ያጣ፣ ኢሥነ ምግባራዊ የሆነ፣ ከአውስቦት/ከወሲብ ጋር የተገናኘ በአልኮል መጠጥ የተደገፈ ጭፈራ” 44 እንዲሁም “የመንደር ክብረ በዓል፤ ታላቅ ደስታ፣ ፈንጠዝያ” 45 ብለው ነው የተረጐሙት፡፡ እግዚአብሔር ያሳያችሁ፣ እኛ ዘፈን የምንለው ከአውስቦት/ከወሲብ ጋር የተገናኘውን ጭፈራ አይደለም እንዴ? በቡድን ሆኖ ለፌሽታ የሚደረግ ጭፈራ/ዜማ አይደለም እንዴ? (በመሠረቱ ጭፈራዎች ሁሉ ዐላማቸው ከፊሽታ ውጪ ሌላ ምን ሊሆን ይችላል?) ይህ ዐይነቱ ግብር በመጽሐፍ ቅዱስ ከተኰነነ፣ ዘፈን በመጽሐፍ ቅዱስ ተኰንኗል የማንልበት ምክንያቱ ምንድን ነው (ሮሜ 13÷13፤ ገላትያ 5÷21፤ 1ጴጥሮስ 4÷3)?


ዶ/ር ተስፋዬ ሮቤሌ

💢💢 @Appeal4purity 💢💢
💢💢 @Appeal4purity 💢💢
ክፍል ስድስት

“ናይት ክለብ ጥሩም ነው! መጥፎም ነው!”
ወንድም ዮናስ፣ “የምሽት ጭፈራ ቤቶች ጥሩም ናቸው መጥፎም ናቸው” የሚል ሙግት አለው፡፡ ጥሩ የሚያደርገው ተመርጦ መዘፈኑ፣ መጥፎ የሚያደርገውም ተመርጦ ያለመዘፈኑ እንደ ሆነ ማብራሪያ አቅርቧል 46፡፡ በአንጻሩ ክርስቲያን ሙዚቀኞች (ይኸውም ሙዚቃ መሣሪያ የሚጫወቱም ሆነ፣ መረዋ ድምፅ ያላቸው ቮካሊስቶች)፣ ለዳንኪራ የማይመቹ እንዲሁም ከክርስቲያናዊው ሥነ ምግባር ጋር የሚጣጣሙ ወይም የእንደ ቤትሆቨን ያሉ በሙዚቃ ብቻ የተቀነባበሩ የሙዚቃ ስልቶችን በናይት ክለብ መጫወት ይኖርባቸዋል የሚል አስተያየት ሰጥቶአል 47፡፡ ግን ጥያቄዎች አሉኝ:— (1) “በኢትዮጵያ ውስጥ እንዲህ ዐይነት ጭፈራ ቤቶች አሉን?” (ማለትም ተመርጦ የሚዘፈንባቸውና ተመርጦ የማይዘፈንባቸው፤ በሕዝብ ጭፈራ መኻል መራጩ ባለሥልጣንስ ማነው?)፣ (2) “ይህን የሙዚቃ ሥልት፣ መሸታ በሚሸመትባቸው የምሽት ጭፈራ ቤቶች ውስጥ ማካሄድ ለምን አስፈለገ (“ፉት” ለማለት እንዲመች ካልሆነ በስተቀር፡፡ የምሽት ጭፈራ ቤቶቹ ደግሞ ዋና ምናልባትም ብቸኛ ገቢያቸው የአልኮል መጠጦችን መሸጥ አይደለም እንዴ? አልኮል መጠጥ የማይሸጡ ከሆነ፣ ትርፋቸው ምን ሊሆን ይችላል)? (3) በርግጥ ቅምቀማንና ጭፈራን ታሳቢ ካላደረግን፣ ይህ ዐይነቱን የሙዚቃ ምሽት በቤተ ክርስቲያን ቅጥር ግቢ ውስጥ እንዳናካሂደው የሚከለክለን ነገር ምንድን ነው? ማድረግ የምንችል ከሆነ ናይት ክለብ ለምን በአማራጭነት ይቀርባል?” (4) “አንዱን ዘፈን ከሌላው ዘፈን የምንመርጥበት ቋሚና ሁሉን የሚያግባባ መስፈርት ማዘጋጀት ይቻላልን?” ሕዝበ ክርስቲያኑ ሁሉ መስፈርቱን ይቀበል ዘንድ፣ ዘፈን ኀጢአተ ያለመሆኑን ካመነ በኋላ በግምገማ በመስፈርቱ ላይ መወያየትም ሆነ መተማመን ይኖርበታል፡፡ እውነቱ ይህ ከሆነ በርግጥ በዚህ ጒዳይ ሕዝበ ክርስቲያኑን ሁሉ የሚያቅፍ ጉባኤም ሆነ ሱባኤ ማደራጀት ይቻላል? እነዚህ መሠረታዊ ነገሮች በሌሉበት ሁኔታ፣ “እየተመረጠ በሚዘፈንበት ቦታ የሙዚቃ ተጫዋቾቻችንም ሆኑ ድምፀ መረዋዎቹ (ቮካሊስቶቹ) ሄደው ሙዚቃ ይሥሩ” የሚለው ነገር ትክክል ነውን? ድፍረት ካልሆነብኝ በስተቀር ወንድም ዮናስም ሆነ እርሱን የሚደግፉ ወገኖች የሚናገሩትን ነገር ቊጭ ብለው እስከ ጥግ ድረስ የመረመሩት አይመስልም (ዘፈን ከጸደቀልን በኋላ በዝርዝር ጒዳዮቹ ላይ እንወያያልን ለማለት የፈለጉ ይመስላል፡፡ ነገር ግን እንዝፈን አንዝፈን ከሚለው የክርክር ጭብጥ ይልቅ፣ ዝርዝር ጒዳዮቹና አፈጻጸሞቹ ይመልጥ ራስ ምታት እንደ ሆኑ ሊገነዘቡት ይገባል) 48፡፡
“ችግር የለም እየመረጣችሁ ዝፈኑ”
ምናልባት አንዳንድ ወገኖች፣ “ከእኛ ሥነ ምግባር ጋር የሚጣጣሙ፣ በአንጻሩ አንዳችም የአውስቦት መንፈስ የሌለባቸው፣ ዘፈኖችስ እንዴት መታየት አለባቸው?” የሚል ጥያቄ ሊያቀርቡ ይችላሉ፡፡ ይህ የአንድ ሚሊዮን ብር ጥያቄ ነው፡፡ ወንድም ዮናስ ጐርፌም እየመረጥን እንድንዘፍን ሐሳብ አቅርቦልናል፡፡ ይህ አስተያየቱ ከሥነ ምግባራችን ጋርም ሆነ ከነገረ መለኮታችን ጋር የሚጣጣሙ ዘፈኖች መኖራቸውን አጣቅሶ ነው (ለምሳሌ ስለ እናት ፍቅር፣ ስለ አገር ፍቅር፣ ስለ ባልንጀርነት፣ ቀጠሮን ስለማክበር፣ ስለታማኝነት ወዘተረፈ)፡፡ ሥነ ምግባራችንን የሚጋሩ፣ ነገር ግን እንደ አስቴር መጽሐፍ የአምላክ ስም የሌለባቸው በርካታ ጥሩ ዘፈኖች መኖራቸው እሙን ነው፡፡ ነገር ግን እነዚህን ዘፈኖች የማንዘፍንባቸው ቢያንስ ሰባት መሠረታውያን ምክንያቶች ያሉ ይመስለኛል፡፡ አንደኛው፣ ይህ ዐይነቱን ዘፈን መዝፈን የወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ትውፊት አይደለም፡፡ ቈይ! ትውፊት ምንድን ነው? ትውፊት ማለት ከእኛ ውጭ ያለ፣ የጥንት አባቶች ይከተሉት የነበረ ሕግ ማለት ነው? መልሱ በተወሰነ መልኩ አዎ፣ በተወሰነ መልኩ ደግሞ አይደለም የሚል ነው፡፡ ትውፊት እኛ ነን፡፡ አስተዳደጋችን፣ አስተምህሮአችን፣ አተያያችን፣ የደስታ፣ የፍቅር፣ የሐዘን አገላለጽ ዘዬአችን፣ የሙሾ አወራረዳችን በአጠቃላይ የኢትዮጵያ ወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ባህልና ልማድ ነው፡፡ እንዲያው በአጭሩ የአኗኗር ቅኝታችን ነው፡፡ ለዚህ ነው የሥነ ሰብ ምሁራን፣ “ሰው ሁሉ የባህሉ እስረኛ ነው” የሚሉን፡፡ ይህን ጒዳይ ያብራራልኝ ዘንድ፣ አጭር ሐሳብ ወለድ ብጠቀምስ?
እኔና ባለቤቴ የወር አስቤዛ ልንገዛ በሄድንበት ገበያ፣ ለትንሹ ልጃችን የሚሆን መልኩ ያማረ ፖፖ በጥሩ ዋጋ አገኘን፡፡ ከገበያ የተመለስነው ግን በጣም ደክሞን ነበር፡፡ ትላንት ራት የተበላባቸው ሳሕኖች አይታጠቡ እንጂ፣ ከራት የተረፈ እጅ የሚያስቈረጥም የዶሮ ወጥ በሸክላ ድስቱ ውስጥ አለ፡፡ ባለቤቴ ይህን የዶሮ ወጥ ስታሞቅ፣ እኔ “የምንበላበትን ሳሕን እጠብ” የሚል የሥራ ድርሻ ተሰጠኝ፡፡ ነገር ግን ድካሙ በርትቶብኝ ስለነበር በተቀመጥሁበት እንቅልፉ ለሽ አደረገኝ፡፡ ከዛ ጣፋጭ እንቅልፍ የቀሰቀሰኝ፣ “ሳሕኖቹ ታጠቡ?” የሚለው ንግግር ነው፡፡ ዐይኔን ስከፍት ወዲያው አንድ መላ አብሮ ከች አለልኝ፣ “ባልታጠበ ሳሕን ከምንበላ፣ የጆጆን 49 ፖፖ በሳሕንነት ብንጠቀምስ”፡፡ “በስመ አብ በፖፖ፤ ፖፖ ነው ያልኸው? እንዴት ምግብ በፖፖ ይበላል? ስንፍናህ ወደር አይገኝለትም፤ በቃ ተወው ቢያንስ አንድ ሳሕን ለቅለቅ አድርጌ ላንጣ” አለች፡፡ “እንዴ ምን ችግር አለው የእኔ እመቤት፤ በአሁኑ ወቅት ቤታችን ውስጥ ካሉ ሳሕኖች ሁሉ ይህ ፖፖ ንጹሕ እንደ ሆነ እንኳን እኛ ጆጆ ራሱ ጠንቅቆ ያውቀዋል፡፡ ከዛሬ በኋላ መደበኛ ሥራውን ይጀምራል፣ ዛሬ ግን ንጽሕናውን ምክንያት በማድረግ፣ የሳሕን ወግ ብናሳየውስ?” አልኋት፡፡ ባለቤቴ፣ “ኧረ እንዴት አድርገን በፖፖ እንበላለን” ስትል በመኅተሟ ጸናች፡፡ እኔ ደግሞ የፖፖውን ንጽሕና በመጥቀስ፣ ያለማወቋን በመውቀስ እንዲበላበት ቀጭን ትእዛዝ አስተላለፍሁ፡፡ እንዲያውም ይህን ማድረጋችን ዘመናዊ ሰዎች መሆናችንን፣ የተማርን የተመራመርን መሆናችንን ያሳያል ስል ሞገትሁ፡፡ እንደ ወትሮው ሁሉ ባለቤቴ በሙግቴ ስለተረታች፣ ፖፖውን የምግብ ጠረጴዛው ላይ አድርጋው እንጀራውን አነጠፈችበት፡፡ ወጡንም አወጣችበት፡፡ ሁለታችንም እጃችንን ታጥበን ቀረብን፡፡ እኔ፣ የምንበላው በፖፖ ነው የሚለውን ጒዳይ በጭራሽ ማሰብ አልፈለግሁም፤ ፖፖነቱን ካድሁ፡፡ ባለቤቴ ግን፣ “ይህ ነገር የሚሆን አልመሰለኝም፤ እኔ አላደርገውም አሁን የሚታየኝ ዶሮ ወጥ ሳይሆን…አለች”፡፡ እኔም “ካፈርሁ አይመልሰኝ” ሆኖብኝ እንጂ፣ ሽቅብ ሽቅብ እያለኝ ነበር፡፡
ለምንድ ነው በፖፖ ያልበላነው? መልሱ አጭር ነው፤ ፖፖ በእኛ ባህል የምግብ መብያ ሳሕን አይደለም፡፡ ቤት ውስጥ ካሉ ሳሕኖች ይልቅ ንጽሕ አይደለም እንዴ? ምንም ጥያቄ የለውም ንጹሕ ነው፡፡ ነገር ግን ሳሕንን ሳሕን የሚያደርገው ንጽሕናው ብቻ ሳይሆን፣ ባህል ወይም የሕዝቡ አኗኗር ዘዬ ጭምር ነው፡፡ ቊም ነገሩ እዚህ ላይ ነው፡፡ እንኳን ነቢያት አምላክ ራሱ ክንፍ ያላቸውን መላእክት ልኮ ዘፈን “ከኮሞስ” ግላጼ ወጥቶአል ቢል፣ ቢያንስ እኔን ጨምሮ ቀደምት ክርስቲያናች ልንዘፍን አንችልም፡፡ ፖፖው ንጹሕ እንደ ሆነ ሁሉ፣ ጥሩ ዘፈኖች እንዳሉ ቅን ልቦና ያለው ሰው ሁሉ በግልጥ የሚረዳው ጒዳይ ነው፡፡ ነገር ግን ፖፖው ንጹሕ መሆኑ ለሳሕንነት እንዲያገለግል እንዳልረዳው ሁሉ፣ እነዚህ ዘፈኖች ጥሩ መሆናቸው ክርስቲያኑ ማኅበረሰብ እንዲዘፍናቸው ምክንያት ሊሆን አይችልም፡፡

ዶ/ር ተስፋዬ ሮቤሌ

💢💢 @Appeal4purity 💢💢
💢💢 @Appeal4purity 💢💢
የመጨረሻው ክፍል

እንኳን እኛ ክርስቲያኖች፣ ዓለማውያኑም የእኛን መዝፈን፣ የስምንተኛው ሺህ ምጽአት እንጂ፣ የነገረ መለኮት ለውጥ አድርገው ሊመለከቱት አይችሉም፡፡ እንዲህ የሚዋዥቅና የሚንሸራተት ሕይወትስ ይዘን፣ ወጥነት ያለውን ክርስቲያናዊ ሕይወት አብረናቸው መኖር እንዴት እንችላለን? ወንድም ዮናስ በግልጽ ያላስተዋለው ሐቅ ይሄ ይመስለኛል፡፡
ሁለተኛ፣ ልክ ነው እነዚህ መዝሙሮች ጥሩ ይዘት አላቸው፣ ነገር ግን ባለመዝፈናችን ምን ተጐዳን? ምን ጐደለብን? 50 እንዲያውም ጊዜያችን፣ ኢኮኖሚያችን ተጠብቋል (በየጭፈራ ቤት እንዲሁም ለሲዲና ካሴት ግዢ የምናወጣው ገንዘብ በኪሳችን ዐድሯል)፡፡ ሦስተኛ፣ የምናደርጋቸውን ማናቸውም ነገሮች ለእግዚአብሔር ክብር እንድናደርገው ታዘናል (1ቆሮንቶስ 10÷31፤ ሮሜ 12÷1-2) 51፡፡ ምናልባት እግር ኳስ መጫወት፣ መጽሐፍ ማንበብ ወዘተ ለእግዚአብሔር ክብር እንዴት ሊውሉ ይችላሉ? የሚል ካለ መልሱ አጭር ነው፡፡ እግዚአብሔር የሰጠንንና የመንፈስ ቅዱስ ማደሪያ የሆነውን አካላችን ጤነኛ እንዲሆን፣ አእምሮአችንን ንቁ እንዲሆን አምላክ ይፈልጋል፡፡ ስፖርት መጫወትም ሆነ መጻሕፍትን ማንበብ መንፈሳዊ ፋይዳቸው እዚህ ጋ ነው፡፡ አራተኛ፣ እየመረጡ መዝፈን እጅግ ሲበዛ ውስብስብ መሆኑን ወንድም ዮናስ በቅጡ የተረዳው አልመሰለኝም፡፡ መስፈርት ማዋቀሩ አስቸጋሪ የመሆኑን ያህል፣ ጒባኤ ጠረቶ፣ አገር ሰብስቦ፣ “የትኛውን ዘፈን እንዝፈን? የትኛውን ደግሞ አንዝፈን?” የሚለውን ጒዳይ መገምገም፣ ትልቅ አበሳ፣ ትልቅ አሳር ነው፡፡ ቤተ ክርስቲያን እንኳን ዘፈንን፣ መዝሙርን እንኳ በቅጡ ለመገምገም ጊዜ አግኝታ አታውቅም፡፡ ከዚህ ሁሉ ዝርክርክ አካሄድ ሁሉን ዘግቶ መቀመጡ የተሻለ ነው፡፡
አምስተኛ፣ በሩን አንገርብበን (ደርበብ አድርገን) ከከፈትነው፣ “ምን ያህል ይከፈት?” “ምን ያህልስ ይዘጋ?” በሚለው ኅሊናዊ ፍርድ ከምንወዛገብ ሙሉ ለሙሉ መዝጋት፣ ዕዳው ገብስ ነው፡፡ ስለዚህ አማራጩ አንገርብቦ (ደርበብ አርጐ) መክፈት ሳይሆን፣ ሙሉ ለሙሉ መዝጋት ነው፡፡ መቼም ሙሉ ለሙሉ ይከፈት የሚለውን ጒዳይ ወንድም ዮናስ ራሱ አይስማማበትም፡፡ ምክንያቱም በርካታ ኢሥነ ምግባራዊ የሆኑ፣ ከነገረ መለኮታችን ጋር በቀጥታ የሚጻረሩ ትምህርቶች ስላሉ፡፡ ለዘመናት ዘግተን መቀመጣችን አንዳችም ነገር ካልጐዳን፣ ሕዝባችንም ይህን አሜን ብሎ ከተቀበለው፣ እንዲያውም ይህ የሙሉ ለሙሉ ማዕቀብ አካሄድ፣ ኢኮኖሚያችንንና ጊዜያችንን ከታደገልን፣ ጠቃሚውን ነገር ከማይጠቅም ነገር ጋር ሳይሆን ጠቃሚውን ነገር ከሚጐዳ ነገር ጋር እያነጻጸርነው ነው ማለት ነው፡፡
ስድስተኛ፣ የምሽት ጭፈራ ቤቶች ተመርጠው የሚዘፈንባቸው ቦታዎች አይደሉም 52፡፡ ይህ እውነት ከሆነ ወንድም ዮናስ ሙዚቀኞቻችን ናይት ክለብ ሄደው ይጫወቱ የሚለን ለምንድን ነው? በአንድ ወቅት ለወንድም ዮናስ፣ “ክርስቲያን ሙዚቃ ተጫዋች የጭፈራ ቤት ታዳሚዎቹ፣ ዘፈኑን ወደ ወሲብ ቢያንደረድሩት ምን ሊያደርግ ይችላል?” የሚል ጥያቄ ጠይቄው ነበር፡፡ “ይህ ዐይነቱ ሁኔታ ከተፈጠረ ክርስቲያኑ ጊታሩን አስቀምጦ መሄድ አለበት” የሚል ምላሽ ሰጥቶኛል 53፡፡ ምላሹ አላሳመነኝም፤ ምክንያቱም ይህ አካሄድ አስጀምሮ ሳያስጨርሱ መሄድ ነውና፡፡ በተረፈ የጭፈራ ቤቱን ታዳሚዎች በዚህ መልክ ማስቀየም ተገቢ አይደለም፡፡ ስለዚህ ክርስቲያን ቦታው ለእኔ የሚመጥን አይደለም በማለት፣ ከጅምሩም ወደዚያ ስፍራ ዝር ያለማለት፣ ከሄደም ደግሞ ሙሉ ክብሩን ብቻ ሳይሆን የሚያስከትለውንም አበሳ መጠጣት፣ ፍዳውን መብላት ይኖርበታል፡፡ ሰባተኛ፣ ክርስቲያን ዘማርያን ቀጠሮ ስለማክበር፣ ስለወንድማማችነት ፍቅር አስፈላጊነት፣ ስለቤተሰብ ፍቅር፣ ጠንክሮ ስለመሥራት ወዘተ (እንዲዘምሩ ማድረግ የእነዚህ ነገሮች ሁሉ መሠረት አምላካችን እግዚአብሔር እንደ ሆነ በሚያስገነዝብ መልኩ)፡፡ ችግሩ የአማራጭ መዝሙሮችን ማጣት፣ ወደ ቅልውጥና ወስዶን ከሆነ፣ መዝሙሮቹን እኛው ብናዘጋጃቸው መፍትሔ ሊሆን ይችላል ለማለት ነው 54፡፡
ማጠቃለያ
አንድ የንጉሥ ልጅ፣ አንድ ዕውቅ ዘፋኝ ታገባለች፡፡ ንጉሡ ከመንበራቸው ሲገረሠሡ፣ የንጉሡ ቤተ ሰቦች ከያሉበት እየተለቀሙ ዘብጥያ ይወረወራሉ፡፡ ዘፋኙ ግን በለስ እየቀናው፣ ተወዳጅነቱ ከዕለት ዕለት እየጋመ ይመጣል፡፡ በአንጻሩ የልዑላኑ ቤተሰብ መከራና አሳር እየበረታ ይሄዳል፡፡ በዚህ ጊዜ ነው ዘፋኙና ልዕልቲቱ ተገናኝተው የተጋቡት፡፡ ትዳራቸው ግን ብዙም አልዘለቀም፤ ዘፋኙ ልዕልቲቱን በመፍታት ሌላዋን ባለሳምንት ያገባል፡፡ በአንድ አጋጣሚ የአገሪቱ ብሔራዊ ቴሌቪዥን፣ ልዕልቲቱ ከአርቲስቱ ጋር እንዴት እንደ ተገናኙ ጥያቄ አቅርቦላት ነበር፡፡ እርሷም፣ “የተገናኘነው እርሱ ወደ ላይ ሲወጣ፣ እኔ ደግሞ ወደ ታች ስወርድ ነው” አለች ይባለል፡፡ መልእክቱ ወደ ልባችሁ የደረሰ ይመስለኛል፡፡ በምንም ሂሳብ ይህ ርእስ ቤተ ክርስቲያን ወደ ላይ በምትወጣበት የታሪክ ጊዜ ላይ የመጣ ጥያቄ አይደለም፡፡ በቀን ጐዶሎ፣ በድጡ መንገድ እየተንሸራተተች ባለበት የታሪክ ወቅት ያገኛት አበሳ ፍዳ እንጂ፡፡ ይህ የእንዝፈን ጥያቄ ከሃያና ከሠላሳ ዓመት በፊት ቀርቦ ቢሆን ኖሮ፣ ወንድም ዮናስም ሆነ ባልደረቦቹ እግር ከወርች ታስረው አማኑኤል ይወሰዱ ነበር 55፡፡ ዛሬ ግን ይህን እንግዳ ሐሳብ፣ አንዳችም ፋይዳ የሌለውን ትምህርት ለቤተ ክርስቲያን ለማስተዋወቅ የትውልዱ ሥነ ምግባር ፈቅዷል፡፡
ወንድም ዮናስ የመጽሐፉን ርእስ፣ “ቤት ያጣው ቤተኛ” ያለው በምን ሂሳብ ነው? ዘፈን የወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት ቤተኛ የሆነው መቼ ነው? በመጽሐፉ ሽፋን ላይ፣ አንድ ሰው ቤተ ክርስቲያን በር ላይ እንደ ጒድፍ ተጥሎ ይታያል፡፡ በእውነቱ ምን መልእክት ለማስተላለፍ ተፈልጎ እንደ ሆነ በጭራሽ አልገባኝም፡፡ ባይሆን፣ “ቤት ያላገኘው ነገር ግን ቤተኛ ለመሆን የሚዋደቀው ታጋይ” ቢባል ይሰዳል/ያስሄዳል (የገላትያ 5÷21 ትርጒም ቀይሮ)፡፡ ከዚህ መለስ ግን በምንም ሂሳብ መዝፈንም ሆነ ናይት ክለብ ሄዶ ሙዚቃ መጫወት፣ የወንጌላውያን አብያተ ክርስቲያናት አስተምህሮ፣ ትውፊትም ሆነ ሥነ ምግባር አይደለም፡፡ አትዝፈኑ፣ አትጨፍሩ የሚለውን ትምህርት ከቤተ ክርስቲያን በማስወጣት፣ ባይተዋር እናደርገዋለን፤ ቤተ ክርስቲያን በር ላይ እንደ ጒድፍ እንጥለዋለን፤ ይህም መጽሐፍ የዚህ ዘመቻ አንድ አካል ነው የሚል ምፀታዊ ተምኔት ከሆነ ግን ይገባኛል 56፡፡ እኔ በዚህ ጽሑፍ ዘፈን ኀጢአት አይደለም የሚለው ሙግት ትክክል ያለመሆኑን፣ መርጠን እንዝፈን የሚለውም ሐሳብ ከብዙ አንጻር የከሰረ ሐሰብ መሆኑን፣ ከዚህ በተረፈ ደግሞ በቤተ ክርስቲያን ላይ ትልቅ የሥነ ምግባር አደጋ እንደ ተጋረጠ ለማሳየት ሞክሬአለሁ፡፡
በቸር ይግጠመን

ዶ/ር ተስፋዬ ሮቤሌ

💢💢 @Appeal4purity 💢💢
💢💢 @Appeal4purity 💢💢
Purity Tube pinned a video
Forwarded from Sexual purity
😱pornography የሰውን ስብእና ሙሉ ለሙሉ የሚቀይር እና ማንነትን የሚያስክድ ክፉ ልምምድ ነው.👹
🔔ከ Pornography ሱስ ለመላቀቅ የ ምክር እና የ ፀሎት አገልግሎት ለማግኝት መወሰን ብልህነት ነው! ቀኑ ሳይጨልም ራሶን ያስመልጡ!!🏃‍♀️🏃‍♀️🏃‍♀️🏃🏽‍♂️🏃🏽‍♂️🏃🏽‍♂️🏃‍♀️🏃🏽‍♂️🏃🏽‍♂️
ከዚ በታች ምታዩት ሰው Ted Bundy ይባላል፡ በ ቸርች ያደገ እና ጥሩ ወላጆች የነበሩት ሰው ነው። በአንድ ወቅት ብዙ ሰዎችን በመድፈርና  በመግደል የሞት ፍርድ የተፈረደበት ሲሆን ለዚ ለመብቃቱ ዋነኛ ምክንያት የ Pornography ሱስ መሆኑን ተናግሯል።🔥🔥🔥🔥🔥
ሊገደል ደቂቃዎች ሲቀሩ የሰጠውን ቃል ከዚ በታች ያለውን ቪድዮ ተጭነው ይመልከቱ 📺
2025/07/05 19:36:57
Back to Top
HTML Embed Code: