Telegram Web Link
ሰላም የቻናላችን ቤተሰቦች

እንደሚታወቀው በቴሌግራም ቻናላችን ከሁለት ዓመት በላይ " Appeal 4 purity " በሚል ስያሜ ጌታ በረዳን መጠን አስተማሪ መልዕክቶችን ወደናንተ ስናደርስ ቆይተናል ፡፡

Appeal 4 purity የሚለውን ስያሜ ከ Appeal for purity መስራች ከዶ/ር መስከረም ክፈተው ፍቃድ በመውሰድ በተውሶ እስካሁን ስንጠቀምበት ቆይተናል ፡፡

በቻናላችን ገፅም በተደጋጋሚ ይህ የቴሌግራም ቻናል የዶ/ር መስከረም ክፈተው #እንዳልሆነ ስንገልፅ ብንቆይም ብዙ ሰዎች የዶ/ር መስከረም እንደሆነ እንደሚያስቡ በውስጥ መስመራችን ከሚላኩልን መልዕክቶች ለመረዳት ችለናል ፡፡

በመሆኑም ብዙ ጊዜ ወስደን አስበንበት በቅርብ ቀን የቻናላችንን ስያሜ ለመቀየር የወሰንን መሆኑን ውድ ቤተሰቦቻችን እንድታውቁ እንወዳለን ፡፡

እናመሰግናለን

#ከአድሚኖች
Purity Tube pinned «ሰላም የቻናላችን ቤተሰቦች እንደሚታወቀው በቴሌግራም ቻናላችን ከሁለት ዓመት በላይ " Appeal 4 purity " በሚል ስያሜ ጌታ በረዳን መጠን አስተማሪ መልዕክቶችን ወደናንተ ስናደርስ ቆይተናል ፡፡ Appeal 4 purity የሚለውን ስያሜ ከ Appeal for purity መስራች ከዶ/ር መስከረም ክፈተው ፍቃድ በመውሰድ በተውሶ እስካሁን ስንጠቀምበት ቆይተናል ፡፡ በቻናላችን ገፅም በተደጋጋሚ ይህ…»
Media is too big
VIEW IN TELEGRAM
ዝማሬ🎙 “መታደል ነው”
ዘማሪ👥 Amanuel Merdkios
የተለቀቀው📅 Nov 4, 2019
ርዝመት 8:36
Quality🎬 480p
Genres 🎹 Praise & Worship

🙈ድንቅ ዝማሬ ነው ስሙትና ተባረኩበት!😱
ለሌሎችም እንዲደርስ #share♻️
      
     🔻🀄️🀄️ሉን🔻
@christian_mezmur
@christian_mezmur
መጽሐፍ ቅዱስ ከዝሙት ሽሹ ይላል እንጂ ከዝሙት ራቁ አይልም.. አየህ የምትርቀው የሆነ የቆመን ነገር ሲሆን የምትሸሸው ግን የሚከታተልህን ነገር ነው( በጓደኛ, በፊልም, በማህበራዊ ድረገፅ, ከውስጥህ ስሜት.....)፤

👉 ስለዚህ ትላንት አምልጠን አንደሆነ ዛሬ እንዳያገኘን ዕለት ዕለት መንቃት ይሁንልን።
አሜን !!

ናኦል ከጅማ ዩኒቨርስቲ ፌሎሺፕ

💢💢 @Appeal4purity 💢💢
💢💢 @Appeal4purity 💢💢
ሚስት በገዛ ሥጋዋ ላይ ሥልጣን የላትም
እንዲሁም ደግሞ ባል በገዛ ሥጋው ላይ ሥልጣን የለውም

ብዙ ጊዜ 1ኛ ቆሮ 7 ስለ የጋብቻ ትምህርት ላይ ሲጠቀስ ይስተዋላል።
እንደዛ መሆኑ በጣም መልካም ነው። ምክንያቱም ይህን ክፍል በትክክል ባለመረዳታቸው ብዙ ባለትዳሮች ወደ መቃቃር ያመራሉ።

በዚህ ፅሁፍ ግን ከተለመደው የዚህ ክፍል አተያይ ወጣ ብለን ለማየት እንሞክራለን።

"ባል ለሚስቱ የሚገባትን ያድርግላት፥ እንደዚሁም ደግሞ ሚስቲቱ ለባልዋ።
ሚስት በገዛ ሥጋዋ ላይ ሥልጣን የላትም፥ ሥልጣን ለባልዋ ነው እንጂ፤ እንዲሁም ደግሞ ባል በገዛ ሥጋው ላይ ሥልጣን የለውም፥ ሥልጣን ለሚስቱ ነው እንጂ።" 1ኛ ቆሮ 7 ፥ 3-4 (ስጋ ማለት አይን ጆሮ ምናምን ማለት ሳይሆን የወሲብ መፈፀሚያ ክፍልን ነው የሚጠቁመው)


ከዚህ ጥቅስ በዋናነት ልንወስድ የምንችለው ሃሳብ
በትዳር ውስጥ ባል ወይም ሚስት አንዳቸው ወሲብ መፈፀም ቢያሻቸው ሌላኛቸው " አይ ዛሬ አላሰኘኝም ስለዚህ ሌላ ቀን እናድርግ ! " ብሎ የመከልከል ስልጣኑ እንደሌላቸው ይልቁንም ይህ ስልጣን ለነሱ ሳይሆን ለትዳር አጋራቸው የተሰጠ መሆኑን ነው።

ሆኖም ከዚህ ጥቅስ ከዚህ በዘለለ መረዳት የምንችለው ነጥብ አለ።

"ሚስት በገዛ ሥጋዋ ላይ ሥልጣን የላትም፥ ሥልጣን ለባልዋ ነው" ሲል የወሲብ መፈፀሚያ አካላችን ባለቤት አለው ማለት ነው።ባለቤቱም የትዳር አጋር እንጂ እጮኛ ወይም የተቃራኒ ፆታ ጓደኛ ወይም እኛ ራሳችን አይደለንም ።

ስለዚህ ከትዳር በፊት የሚደረግ ወሲብ የወደፊት ባልሽ ላይ መማገጥ ነው።ወይም ራስህን በራስህ ማርካት ወሲባዊ እርካታን ከተፈቀደልህ ኣካል ውጪ ለማግኘት መጣር ነው።


#General
#Single
#maried

💢💢 @Appeal4purity 💢💢
💢💢 @Appeal4purity 💢💢
ጭር ያለ ቦታ እንገናኝ

ብዙ ወጣቶች በወሲባዊ ሃጢያት ለመውደቃቸው እንደ ምክንያት የሚያቀርቡት ከፍቅር ጓደኛቸው ወይም ከተቃራኒ ፆታ ጓደኛቸው ጋር ሰው የሌለበት ፣ ጭር ያለ ፣ ጨለም ያለ ቦታ መገናኘታቸው እንደሆነ ይናገራሉ ፡፡

" ብርሃንም ወደ ዓለም ስለ መጣ ሰዎችም ሥራቸው ክፉ ነበርና ከብርሃን ይልቅ ጨለማን ስለ ወደዱ ፍርዱ ይህ ነው።"
(የዮሐንስ ወንጌል 3:19)

አያችሁ ሰው የማያየውና ጨለማ ቦታ የሚመረጠው ለክፉ ስራ እንጂ ለመልካም አይደለም ፡፡

ጥንዶቹ ሳያስተውሉ አልያም ደግሞ ከሁለቱ አንዳቸው በሌላኛቸው ተታለው ወይም ተገፍተው ሊሆን ይችላል ጭር ወዳለ ቦታ የሚሄዱት ፡፡

ብዙ ጊዜ እንዲህ ባለ ሁኔታ ለወሲባዊ ሃጥያት የሚጋለጡት የዩኒቨርስቲ ተማሪዎች ናቸው ፡፡ ጭር ያለ ቦታ ለመገናኘት እንደ ጥናት ፣ Bible study እና ፀሎት የመሳሰሉ በጣም መልካም ነገሮችን ለሽፋን ይጠቀማሉ ፡፡

በዩኒቨርሲቲ ተማሪነት የእድሜ ክልል ያሉ ወጣቶች እንኳን ጭር ያለ ቦታ ተገናኝተው ይቅርና በሌላ በማይመች ሁኔታ እንኳን ለወሲባዊ ሃጥያት የመጋለጥ እድላቸው እጅግ ሰፊ ነው ፡፡

መፅሐፍ ቅዱስ ደግሞ ሰው እጅግ አፀያፊና ህይወትን ከሚያመሰቃቅል ከዝሙት ሃጥያት ማምለጥ የሚችለው #በመሸሽ ብቻ እንደሆነ ይናገራል ፡፡

ስለዚህ የእጮኝነት ጎዳና ውስጥ ለመግባት ብቁ የሆናችሁ ወጣቶች ከእጮኛችሁ ጋር ጊዜ ማሳለፍ የግድ ነው ነገር ግን ጊዜ ለማሳለፍ ጨለማንና ጭር ያለ ቦታን መምረጥ የለባችሁም ፡፡ እንደ ካፌ እና ሰዎች የሚንቀሳቀሱባቸው መናፈሻዎችን መጠቀም ትችላላችሁ ።

🗝 ምክንያቱም በPrivacy ሰበብ ቅድስናችሁን ማጣት የለባችሁም

#General


💢💢 @Appeal4purity 💢💢
💢💢 @Appeal4purity 💢💢
ከፖርኖግራፊ ሱስ መውጫ መንገድ
ከፖርኖግራፊ ሱስ ለመውጣት የምትፈልጉ ወገኖች ከዚህ ቀጥሎ የቀረቡትን ተግባራዊ ነጥቦች ብትከተሉ መልካም ነው፡፡ወረቀትና እስኪብርቶ ይዛቹ ለተቀመጡት ጥያቄውች በጽሁፍ መልስ እየሰጣቹ እለፉ።

1.እግዚአብሔር እንደሚወዳቹ አስባቹ ንሰሐ ግቡ።
በዚህ ሱስ ውስጥ የገቡ ሰዎች እግዚአብሔር እንደሚጠላቸውና እንደሚጸየፋቸው ያስባሉ።እንዲህ አይነቱ ሃሳብ ሰዎችን የሱሱ ባሪያ አድርጎ ለማኖር ሰይጣን ይጠቀምበታል።እውነታው ግን እንደዚህ አይደለም።በእናንተና በሐጥያታቹ መካከል ልዩነት አለ።እግዚአብሔር ሐጥያትን ይጠላል።ሐጥያተኛን ግን ይወዳል።እናት የልጅዋ ልብስ ቢቆሽሽ ለልጅዋ ያላት ፍቅር እንደማይቀየር እግዚአብሔርም በለእናንተ ያለው ፍቅር አይቀየርም።ከዚህ ህይወት ወጥታቹ ወደ እርሱ ለመምጣት ብትወስኑ እጆቹን ዘርግቶ ይቀበላቹሃል።በቀራንዮ ላይ የፈሰሰው የኢየሱስ ደም ከሐጥያታቹ ሁሉ እንደሚያነጻቹ አምናቹ በእግዚአብሔር ፊት ንሰሐ ግቡ።”የልጁም የኢየሱስ ክርስቶስ ደም ከኃጢአት ሁሉ ያነጻናል”።1ዮሐ 1፡7 የኢየሱስ ክርስቶስ ደም ስለ አለም ሁሉ ስለፈሰሰ በእግዚአብሔር ፊት ይቅር የማይባል ሐጥያት የለም።
2.አምናቹ ጸልዩ
የሰው ልጅ በራሱ ጥረት ከሐጥያት መውጣት አይችልም።የእግዚአብሔር ጸጋ ሲያግዘው ግን የማይቻለውን ችሎ በቅድስና አሸብርቆ መኖር ይቻለዋል።እስከ ዛሬ በግል ጥረታቹ ከዚህ ሱስ መውጣት ስላልቻላቹ ተስፋ ቆርጣቹ ሊሆን ይችላል።ጸጋው ግን ጣልቃ ገብቶ አዲስ ህይወት ሊሰጣቹ ይችላል።ይህ ደግሞ የሚሆነው “እኔ ደካማ ስለሆንኩ የሚረዳኝ ጸጋ ይሰጠኝ”ብሎ በጸሎት እግዚአብሔርን በመለመን ይሆናል።መውጣት እንደሚቻል አለምማመን በራሱ ሰንሰለት ነው።የእግዚአብሔር ጸጋ ታሪክን እንደሚቀይር ከዚህ ህይወት መውጣት እንደሚቻል እመኑ።ምክንያቱም ከሐጥያት አስወጥቶ ቅዱስ የሚያደርግ ሰዎችን ሁሉ የሚያድን የእግዚአብሔር ጸጋ ተገልጦአልና፤ቲቶ 2፡11-13

3.ለምን እንደምታዩ እወቁት
አንዲት እህቴ ከ 4 አመት በፊት የመደፈር አደጋ ደርሶባት ነበር።ለሊት ስትተኛ ያሳለፈችው ሁሉ እየመጣባት ትጨነቅ ነበር።ከዚህ ስቃይ ማምለጫ ያደረገችው ፖርኖግራፊ መመልከት ነበር።እዚህ ጋር የምንመለከተው ነገር ለዚህች እህት ፖርኖግራፊ መመልከት የችግሩ መገለጫ እንጂ ዋናው ችግሩ አልነበረም።ከዚህች እህቴ ጋር ጊዜ ወስደን ስናወራ አሰቃቂ ከሆነ ጉዳት በዋላ ሰዎች የሚኖራቸው የስነ ልቦና መቃወስ /Post Traumatic Stress Disorder/እንዳለባት አረጋገጥኩ።

ፖርኖግራፊ መመልከት ሰዎች በህይወታቸው ያልፈቱት የውስጣዊ ችግር መገለጫ ነው።ጊዜ ወስዳቹ በሕይወታቹ የሚያስጨንቃችሁን ነገር ለማወቅ ሞክሩ።ችግሩን ለመሸፈን/repress/ለማድረግ መሞከር ወደ ባሰ ችግር ይወስዳልና ችግሩን ተጋፍጣቹ መፍትሄ ለመስጠት ሞክሩ።

4.ቀስቃሽ ነገሮችን ለዩ።
ከዚህ በታች ያሉትን ጥያቄዎች ለራሳቹ መልሱ።
በብዛት ፖርኖግራፊ የምታዩት የትኛው ሰአት ላይ ነው?
ለመጨረሻ ጊዜ ፖርኖግራፊ ያያችሁት መቼ?
ፖርኖግራፊ ከመመልከታቹ በፊት ምን አይነት ስሜት/mood/ላይ ነበራቹ?

ቀስቃሽ ነገሮቻቹ ምንድን ናቸው?ስሜትን የሚያነሳሱ የሙዚቃ ክሊፖች ወይንስ ፊልሞች?አንዲት እህቴ ፖርኖግራፊ ይዘት ያላቸውን ነገሮች የምታገኘው ከፌስ ቡክ ላይ ነበር።ከዚህ ህይወት ሙሉ ለሙሉ መውጣቷን እስክታረጋግጥ ድረስ ፌስቡክ መጠቀሟን አቆመች።ከዚህ በፊት የሰበሰባችሁት ፊልምና ማንኛውም ነገር አሁኑኑ አጥፉ።ገፋፊ ነገሮችን ከእናንተ ለማራቅ ወስኑ።ኢንተርኔት መጠቀም ማቆም ካለባቹ አድርጉት።መጠቀም ካለባችሁም ሰዎች በተሰበሰቡበት ቦታ ተቀመጡ።
ወደ ፖርኖግራፊ የሚገፋፋቹ ጭንቀት ከሆነ ከጭንቀት መውጫ ሌሎች መንገዶችን ፍጠሩ።ስሙን ሳልጠቅስ ታሪኩን እንዳጋራ የፈቀደልኝን የአንድ ወንድም ሕይወት ላንሳ
“ከሚስቴ ጋር ባለን ህይወት ደስተኛ አይደለሁም።እቤት መሄዴን ሳስብ ጭንቀት ይወረኛል።መደበሪያዬ ፖርኖግራፊ ሆኖ ለዘመናት ኖርኩኝ።የትዳሬን ችግር መፍታቴ ከፖርኖግራፊ ሱስ አስመለጠኝ”።

የእናንተን ቀስቃሽ ነገርን ጻፉት።

5.ታገሉ
ከዚህ ሱስ መውጣት ሂደት ነው።ለማቆም ከወሰናቹ በኋላ እንኳን ልትቸገሩና እስከ ዛሬ ያያችሁት ፊታቹ ላይ እየመጣ ልትጨነቁ ትችላላቹ።ይሄ ማለት ከዚህ ህይወት አልተላቀቃችሁም ማለት አይደለም።ቡና ለረጅም ጊዜ ጠዋት መጠጣት የለመደ ሰው ሊያዛጋው እንደሚችል ማለት ነው።አዕምሮአችን ወደ ቀደመው ቦታ እስኪመለስ ከማንኛውም ሱስ ስንወጣ የምናልፍበት ጤናማ ሂደት ነው።ዋናው በጦርነቱ ተሸንፎ እጅ አለመስጠት ነው።ጸንታቹ በታገላቹና የሚፍልገውን እስከነሳችሁት ድረስ ሱሱ በእናንተ ላይ ያለውን አቅም ያጣል።ከመገባችሁት ግን ያድግና ይውጣቹሃል።

6.ስሜቶቻችሁን ተቆጣጣሩ
ፖርኖግራፊ ማየት ሶስት ደረጃዎች አሉት።እነሱም ስሜት/Emotion/
ሐሳብ/Thought/-ተግባር/Action/ናቸው።ስሜት የምንለው የመጀመሪያው ደረጃ ጭንቀት፣ መከፋት ወይንም ፖርኖግራፊ የማየት ፍላጎት ሊሆን ይችላል።ከዛ ነው ፖርኖግራፊ የማየት ሐሳብ የሚመጣው።መጨረሻ ላይ ሁሉም ወደ ተግባር ይቀየራል።ስለዚህ ራሳችሁን መቆጣጠር የምትችሉት ገና ስሜት ሲሰማቹ ነው።አንዲት እህቴ እንዲህ አይነት ስሜት ሲሰማኝ ከቤት ወጥቼ መዝሙር እየሰማሁ የእግር ጉዞ ማድረግ እጀምራለሁ ይሄም በጣም ጠቅሞኛል ስትል ልምዷን አጋርታኛለች።አንድ ወንድሜ ደግሞ እንዲህ አይነት ስሜት ሲሰማው ስፖርት እንደሚሰራ አጫውቶኛል።ይህ ስሜት ሲሰማቹ ምን ብታደርጉ ጥሩ ነው?3 ነግሮችን ጻፉና የሚስማማችሁን ነገር አድርጉ።

7.ብቸኝነትን አስወግዱ
ለረጅም ሰአት ብቻችሁን ላለመሆንና ጊዜያችሁን ከቤተሰብና ከወዳጆቻችሁ ጋር ለማሳለፍ ሞክሩ።በተቻለ መጠን ቀናችሁን በተሻለና ትርጉም ሊሰጥ በሚችል ነገር ላይ አውሉት።እንደ ስፖርት መስራት መጽሐፍት ማንበብ ወደ ቤተ ክርስቲያን መሄድ ያሉ አዳዲስ ልምዶችን አዳብሩ።እስኪ ከዛሬ ጀምሮ ልታዳብሩት የምትችሉት 5 ልምምዶችን ጻፉ።

8.በአዕምሯቹ ተለማመዱ
ተግባራችን የሐሳባችን ውጤት ነው።እስኪ አይናችሁን ጨፍኑና ፖርኖግራፊ የማየት ስሜት ሲሰማቹና እምቢ ብላቹ ተቃውማቹ በተቀራኒው መልካም ነገር ስታደርጉ በአዕምሯች ስላቹ ይሄን በተደጋጋሚ ተለማመዱ።

9.ተስፍ አትቁረጡ
ከዚህ ህይወት ለመውጣት በምታደርጉት ጥረት ውስጥ መውደቅና መነሳት ሊያጋጥማቹ ይችላል።ተስፋ ሳትቆርጡ ከስህተታቹ ተምራቹ እንደ አዲስ በብሩህ ተስፋ ነገን አሻግራቹ ተመልክቱ።
10.ግልጽ ሁኑ
ይሄን ጽሁፍ ሳዘጋጅ እስከዛሬ ድረስ በዚህ ሱስ የተጠቁና ያማከርኳቸውን ሰዎች ከዚህ ሱስ እንድትወጡ ያስቻላችሁን ነገር ግለጹልኝ ስል ጠይቄ ነበር።በሁሉም ውስጥ ያገኘሁት 2 ሐሳብ ነው።አንደኛው የእግዚአብሔር እርዳታ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ በችግሩ ላይ በግልጽነት ማውራቴ የሚል ነበር።ብዙ ሰው በጉዳዩ ላይ ማውራት ስለሚያሳፍረው እርዳታም ለማግኘት ይቸገራል።ከዚህ ህይወት ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለመውጣት ከፈለጋቹ ሊረዳቹ ለሚችል ለአንድ ሰው በግልጽ ችግራችሁን መናገር ይኖርባቹሃል።ይሄንን ምክር ሰጥቼው የተቀበለ አንድ ወንድም ችግሩን ለጓደኛው አካፈለው።መጥፎ ስሜት ሲሰማው ይደውልና እባክህን እየተቸገርኩ ስለሆነ ጸልይልኝ ይለዋል።ልታማክሯቸው የምትችሉ ሶስት ሰዎችን ጻፉና አንዱን ምረጡ።
ጽሁፌን በጌታችን ኢየሱስ ቃል ልደምድም።”እናንተ ደካሞች ሸክማችሁ የከበደ ሁሉ፥ ወደ እኔ ኑ፥ እኔም አሳርፋችኋለሁ”።
ከአንድ የsexual purity chanel ተከታታያችን
የተላከ
@sexualpurity
ሰላም የቻናላችን ቤተሰቦች
ቀደም ብለን ባስታወቅናችሁ መሰረት የቻናላችንን ስም ከዛሬ ምሽት 3:00 ጀምሮ ,"Purity Tube " በሚል አዲስ ስያሜ ይቀየራል

መስማማትዎን በ 👍 ያሳውቁን
ለዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች ወቅታዊ መልዕክት
========================
ዩኒቨርሲቲ የሰው ልጅ እውቀት የሚቓደስበት እና ለዚህች አለምም ሆነ ለአገሩ ለውጥ ፈጣሪ የሚሆንበት ቦታ ነው:: የአንዲት አገር እድገት ምንጩ ይኸው ቦታ ነው:: ይህ ቦታ አንድ ሰው በዚህች አለም እንዲኖር ለተፈቀደለት አጭር የህይወት ዘመኑ ለእርሱም ሆነ ለአለማችን የሚሆን ነገር እንዲሰራ ማዘጋጃ ቦታ ነው:: ያደጉት ምእራባውያን እዚህ የደረሱት ዩኒቨርስቲዎቻቸውን በጣም ስላደራጁ ነው:: እኔ ወንድማችሁ በአገር ቤትም ሆነ በአገረ አሜሪካ ወደ ስድስት ዩኒቨርስቲዎች አስተምሪያለሁ:: በአሜሪካን አገር ባስተማርኩባቸው ዪኒቨርስቲዎች ብዙ ኢትዮጵያንና ኤርትራውያን ተማሪዎች ያጋጥሙኛል:: እኔም ሆንኩ እነኝህ ተማሪዎቼ እንዴት ደስ ብሎን እንደምንቀባበል እኔ አውቀዋለሁ:: አንዴም ዘር ተጠያይቀን አናውቅም:: ከፍተኛ ነጥብ በፊዚክስም ሆነ አስትሮኖሚ አምጥተው የምንለያየውም እነኝሁ ናቸው:: እኔ ተማሪ በነበርኩበት ዘመንም ይህ የዛሬው ክፍፍል ነበረ:: ሰዎች የፖለቲካ ፍጆታቸውን ለማስፈፀም የዩኒቨርቲ ጨቅላ እና ደሃውን ወጣት ለመጠቀም አፒታይታቸው ክፍት በነበረበት ወቅት እኛ ብንጣላም ሳንገዳደል ከዩኒቨርስቲ እውቀቶቻችንን ቀስመን ለቀናል:: በኢትዮጵያ ምድር ብቻ ሳይሆን በምእራቡም አለም በሙያዎቻችን አለምን ያገለግልን እንገኛለን:: አንድም ሰው በዮኒቨርስቲ ዘመኖቻችን እንደኛው ደሃ ወንድም እህቶቻችንን ስላልገደልን ዛሬ ላይ የህሊና እስረኞች አይደለንም:: የማናቀው ዶርም ሄደን በሶና ዳቦ ተጠያይቀን ስንሰጣጥና ጃኬቶች በጋራ ስንለብስ ትምህርቶቻችንን አጠናቀናል:: ደሃ ወንድምህን ገድለህ ምን አይነት ኢንጅነር: ሃኪም : አካውንታንት: ፋርማሲስት: ኢኮኖሚስት : መምህር : ሳይንቲስት ---- ልትሆን ነው?
እኔ ወንድማችሁ በምሰራበት ቦታ ስሙን ሰምቼው ከማላውቀው አገር እና ሰምቼው የማላውቀው ቋንቋ የሚናገሩ የስራ ባልደረባዎች አሉኝ:: በካንፓስ ደረጃ የእራሱን ወገን ያልተቀበለ ሰው ከምን አይነት ሰው ጋር ሊሰራ ነው ከጨረሰ በኃላ? እባካችሁ ተከባብራችሁ ሁሉንም እንደማንነቱ ተቀብላችሁ የህይወትን ጏዳና ተደጋግፋችሁ ተጓዙ:: እግዚአብሄር ይባርካችሁ::
ዶ/ር ጥላዬ ታደሰ
ናሳ-ጆንሰን የህዋ ማእከል
ከህዋ ህክምና ማሰራጫ ክፍል::

#ሼር #ሼር

💢💢 @Appeal4purity 💢💢
💢💢 @Appeal4purity 💢💢
Channel name was changed to «Purity Tube»
Channel photo updated
የቃልኪዳኑ መስራች እግዚአብሄር ነው

የጋብቻ ቃልኪዳን በጣም ጠባብ በስስት ሌላውን የምንይዝበት ወይም ባልና ሚስት ከእርስ በርሳቸው በስተቀር ሌላውን ማየት የማይችሉበት የፍቅር አድማ አይደለም ፡፡

ይልቁንም ይህ ፍቅር በተለየ መንገድ ለሌሎች ይተርፋል ፡፡ ፍቅር በሁለት ሰዎች መካከል ብቻ የሚፈስ ወንዝ ሳይሆን ከእነሱ አልፎ የሚፈስ ነው ፡፡ በትዳር ውስጥ ያለ እውነት ይህ ነው ፡፡

💢💢 @PurityTube 💢💢
💢💢 @PurityTube 💢💢
የማገባው ማንን ነው-1.pdf
2.2 MB
የማገባው ማንን ነው?
በዶ/ር የሺጥላ መንግስቱ

@AmharicSpritualBooks
💢💢 @PurityTube 💢💢
💢💢 @PurityTube 💢💢
የማገባው ማንን ነው-2.pdf
2.9 MB
🤦‍♀🤦🏼‍♂ 👇የብዙዎች ጥያቄ👇
📔ርዕስ፦ የማገባው ማንን ነው?
👤ጸሐፊ፦ ዶ/ር የሺጥላ መንግስቱ
📄የገፅ ብዛት 255 💾2.5MB

@AmharicSpritualBooks
💢💢 @PurityTube 💢💢
💢💢 @PurityTube 💢💢
📌📌 ከፀጋ በታች 📌📌

(ወደ ሮሜ ሰዎች ምዕራፍ 6)
----------
13፤ ብልቶቻችሁንም የዓመፃ የጦር ዕቃ አድርጋችሁ ለኃጢአት አታቅርቡ፥ ነገር ግን ከሙታን ተለይታችሁ በሕይወት እንደምትኖሩ ራሳችሁን ለእግዚአብሔር አቅርቡ፥ ብልቶቻችሁንም የጽድቅ የጦር ዕቃ አድርጋችሁ ለእግዚአብሔር አቅርቡ።

14፤ #ኃጢአት_አይገዛችሁምና_ከጸጋ_በታች_እንጂ_ከሕግ_በታች_አይደላችሁምና



👉 በኃጢአት አለመገዛት ወይም ነፃነት የሚገኘው የሆኑ ህጎችን በማድረግና ባለማድረግ ውስጥ ሳይሆን ከፀጋ በታች በመሆን ነው ፡፡

⭕️ ከፖርኖግራፊ ከማስተርቤሽን ሱስ በማመለጥ ነፃ መውጣት የሚቻለው ፤ እነዚህን የኃጢአት ድርጊቶች ከዛሬ ጀምሮ አላደርግም ብሎ በመወሰን ብቻ ሳይሆን ከእግዚአብሄር ፀጋ በታች በመጠለል ነው ፡፡

ታዲያ ይህ ፀጋ ምን ያደርግልናል

📌 " ይህም ጸጋ፥ ኃጢአተኝነትንና ዓለማዊን ምኞት ክደን፥ የተባረከውን ተስፋችንን እርሱም የታላቁን የአምላካችንንና የመድኃኒታችንን የኢየሱስ ክርስቶስን ክብር መገለጥ እየጠበቅን፥ ራሳችንን በመግዛትና በጽድቅ እግዚአብሔርንም በመምሰል በአሁኑ ዘመን እንድንኖር ያስተምረናል፤"
(ወደ ቲቶ 2:12-13)


💢💢 @PurityTube 💢💢
💢💢 @PurityTube 💢💢
በመካከላችሁ mini sex አለ ወይ?

ረዘም ላለ ጊዜ አብረን በፍቅር ቆይተናል ግን ስለ ትዳር ማንሳት አይፈልግም ! ምክንያቱን አላውቅም !

ከላይ ያለው ሁኔታ በ Relationaship ውስጥ ባሉ ብዙ ሴቶች የሚታወቅ ችግር ነው ፡፡

በእንዲህ ባለ ሁኔታ ውስጥ ላሉ ሴቶች ምክንያቱ ሊሆን የሚችለው አጭር ነው 👇👇

በመካከላችሁ mini sex አለ ወይ?
(mini sex ማለት መሳሳም መተሻሸትና የመሳሰሉ የወሲብ ስሜትን ' ለማስታገስ ' ሰዎች የሚጠቀሙባቸው ድርጊቶች ናቸው ፡፡ )

ብዙ ወንዶች የወሲብ ፍላጎታቸውን የሚያሟሉበት ሁኔታ ውስጥ ካሉ ስለ ረዥም ጊዜ አያስቡም ወይም ስለ ትዳር አይጨነቁም፡፡

ምክንያቱም ትዳር ውስጥ ሳይገቡ ወይም ከባድ ሃላፊነት ሳይቀበሉ ስሜታቸውን ማርካት ስለቻሉ ነው ፡፡

ስለዚህ በmini sex ልምምድ ውስጥ ሆነሽ የወንድ ጓደኛዬ ስለ ትዳር ያስባል ብለሽ ማሰብ ሲበዛ የዋህነት ነው ፡፡

#General
#Couple

💢💢 @PurityTube 💢💢
💢💢 @PurityTube 💢💢
Purity Tube pinned «በመካከላችሁ mini sex አለ ወይ? ረዘም ላለ ጊዜ አብረን በፍቅር ቆይተናል ግን ስለ ትዳር ማንሳት አይፈልግም ! ምክንያቱን አላውቅም ! ከላይ ያለው ሁኔታ በ Relationaship ውስጥ ባሉ ብዙ ሴቶች የሚታወቅ ችግር ነው ፡፡ በእንዲህ ባለ ሁኔታ ውስጥ ላሉ ሴቶች ምክንያቱ ሊሆን የሚችለው አጭር ነው 👇👇 በመካከላችሁ mini sex አለ ወይ? (mini sex ማለት መሳሳም መተሻሸትና…»
📌 ፋራ መባል ቅድስናን ከማጣት አይበልጥም

የዚህ ክፉ ዘመን የአራዳነት መለኪያ የሆኑ ነገሮች ሁሉም ለማለት በሚቻል ሁኔታ የሰይጣን አጀንዳን ያዘሉ ነገሮች ናቸው ፡፡

ከወሲባዊ ኃጢያት ጋር በተያያዘ የአራዳነት መስፈርት ከተለጠፈባቸው ድርጊቶች ለማየት እንሞክር

👉 ከአንድ እጮኛ ጋር ለረዥም ጊዜ አብሮ መቆየት ወጣትነትን ማበከን ነው እየቀያየሩ ማየት 'አራድነት' ነው

👉 ከእጮኛ ወይም ከተቃራኒ ፆታ ጓደኛ ጋር አለመሳሳም ወይም አለመተኛት ፋራነት ነው እንደፈለጉ እየሆኑ Enjoy ማድረግ ' አራዳነት ' ነው ፡፡

እና ሌሎችም ብዙ ተመሳሳይ ሃሳቦችን ሰይጣን በዚህ ዘመን ትውልዱን አስታጥቋል ፡፡

መፅሃፍ ቅዱስ ግን እንደዚህ ያለውን የዓለም ሃሳብ እንድንንቀው ያስተምረናል ፡፡

ቅድመ ጋብቻ ወሲብ ኃጢያት ነው ስንል ዓለም ፋራ ትለን ይሆናል ግን አይደንቀንም ምክንያቱም ያ እንደሚሆን መፅሀፍቅዱሳችን ቀድሞ ነግሮናል ፡፡

" ወንድሞች ሆይ፥ ዓለም ቢጠላችሁ አትደነቁ።"
(1ኛ የዮሐንስ መልእክት 3:13)

#ፋራ_ተብለን_በቅድስና_መኖር_ይሻለናል

#General

💢💢 @PurityTube 💢💢
💢💢 @PurityTube 💢💢
2025/07/05 07:03:36
Back to Top
HTML Embed Code: