Telegram Web Link
======አበበ + ከበደ 👬 =====
አበበ + አልማዝ 👫

👉በኢትዮጵያውያንም ሆነ በአብዛኛው የዓለማችን ሀገራት በቤተሰብ ውስጥ ስለ ግብረስጋ ግንኙነትና ተያያዥ ጉዳዬች የማይወሩ ፣የማይደፈሩ፣ባለጌ የሚያሰኙና ነውር(Taboo) 🔞ተብለው ተፈርጀዋል፡፡

👉 ይህ ባህል ግን በነዚህ ጉዳዮች ዙሪያ ሰዎች በቂ ዕውቀት ሳይኖራቸው እንዲያድጉ ያደርጋቸዋል፡፡

🔑 ይህን አለማወቃቸውን ደግሞ ሰይጣን ተጠቅሞ አላስፈላጊ ወደ ሆኑ ኢ -ተፈጥሮአዊ ባህሪያት እንዲገቡ ያደርጋቸዋል፡፡

🔴 ስለዚህ ወላጆች ልጆቻቸሁን ቢያንስ ከአራት ዓመታቸው ጀምሮ ስለነዚህ ጉዳዮች ለዕድሜያቸው በሚመጥን አገላለፅ ማስተማር አለባችሁ፡፡

የአራት ዓመት ልጅ እንዴት ተብሎ ይነገረዋል
👇👇
አበበ እና አልማዝ እንጂ አበበ እና ከበደ
የሚባል ሰርግ የለም ተብሎ ይነገረዋል

ጌታ ጥበብና ማስተዋልን
ያብዛልን

💢💢 @PurityTube 💢💢
💢💢 @PurityTube 💢💢
💥💥የባል ትግል " #ይቅርታ "💥💥

ለምን

👉አንዱ ምክንያት የሰሩትን ስህተት ሚስታቸው የምታየውን ያህል አጥርተው አለማየታቸው ነው፡፡

🔹በእርግጥም ጥፋት እንዳጠፉ ሳይገባቸው ይቅርታ መጠየቅ አሳማኝ ሊሆን አይችልም፡፡

👉ሌላው ምክንያት ከማግባታቸው በፊት "ይቅርታ" ማለትን ስላለመዱ ካገቡ በኃላ ይህን ማለት ዳገት ስለሚሆንባቸው ነው፡፡

💯ስለዚህ ያላገቡ ወንዶች ሊለማመዱ ከሚያስፈልጋቸው ሚሊዬን ነገሮች አንዱ "ይቅርታ" ማለትን ነው፡፡
ምንም እንኳን ይቅርታ ለማለት የሚታይና ግልፅ የሆነ ምክንያት ባያገኙም፡፡

ባል ለሚስቱ "ይቅርታ የኔ ውድ" ሲላት የሚስት አእምሮ ይሄን ንግግር ቀጥታ "አፈቅርሻለሁ የኔ ቆንጆ" ብሎ ይተረጉመዋል፡፡😊

🔵እናም የተበሳጨች ሚስት እነዚህን ጣፋጭ የፍቅር ቃላት ከባሏ አንደበት ስትሰማ ትግሏን ታቆማለች ፡ ያኔ ሰላም እና እረፍት ይሆናል፡፡

💯የሚገርም ልውውጥ ፦ ሰላምና እረፍት በአንድ ቀላል ንግግር .....


💢💢 @PurityTube 💢💢
💢💢 @PurityTube 💢💢
👉ማንም የማያውቀው👈

የህይወት ታሪኮች ለምሳሌ
📌የማርቲ ሉተር፡
📌c.s ሊዊስ ፡
📌ኦግስቲን እና የመሳሰሉትን ስናስብ አንድ የጋራ ነገር እንዳላቸው እናስተውላለን ፡፡

🔑 ሁሉም የኃጢአት ውጊያዎች እንደነበራቸው እናም ብዙ ጊዜያትም ተሸንፈዋል፡፡

👉እንደዚሁም ሐዋርያው ጳውሎስ " እኔ ምንኛ ጎስቋላ ሰው ነኝ! ለዚህ ሞት ከተሰጠ ሰውነት ማን ያድነኛል?" (ወደ ሮሜ ሰዎች 7:24) ብልዋል ፡፡

ይህን ጥቅስ ለመረዳት ፡ ጥሩ ሰው ለመሆን "ከዛሬ በኃላ ___አቆማለሁ "
ራስን በማለት ( ዳሹን ሙሉት እናንተ ከምትታገሉበት ነገር ጋር ማለትም ነፃ ለመሆን
ከምትፈልጉት ጋር ለምሳሌ ከመናደድ ፣ porn ከማየት ፣ በሀሰት ከመማል
እና ሌሎችም )

ከዛ ከእነዚህ ነገሮች በራሳችሁ እንደማትችሉ ስታውቁ እንደሌሎች " እኔ ምንኛ ጎስቋላ ሰው ነኝ! ዳግም አልተወድኩም!ወደ አለም ተመልሼ እዛው ብኖር ይሻላል !" ትላላችሁ

ሊዊስ አንደዚህ ይላል "ሰው ጥሩ ለመሆን ሲጥር ማንም የማያውቀውን የራሱን
መጥፎነት ያውቃል "

ኀጢአተኛነታችንን ስናውቅ፡ የክርስቶስን ኢየሱስ መስቀል በትኩረት እንመለከታለን ኢየሱስ

ክርስቶስ ኢየሱስ ለእናንተ እና ለእኔ ዋጋ የከፈለው እንደራሱ ሊያፀድቅ ነው ፡፡
" እንግዲህ በክርስቶስ ኢየሱስ ላሉት አሁን ኵነኔ የለባቸውም።በክርስቶስ ኢየሱስ ያለው የሕይወት መንፈስ ሕግ ከኃጢአትና ከሞት ሕግ አርነት አውጥቶኛልና።"
(ወደ ሮሜ ሰዎች 8:1-2)

ከኛ ምን ይጠበቃል አንድ ነገር!
ሙሉ በሙሉ በኢየሱስ ክርስቶስ በማመን እና በመመካት በእግዚአብሔር ኃይል በክርስቶስ ወደ እሱ ተጠራን
" ለርኵሰት ሳይሆን እግዚአብሔር በቅድስና ጠርቶናልና።"
(1ኛ ወደ ተሰሎንቄ ሰዎች 4:7)

💯ፍቅሩን የቀመሰ እንደዚህ ይላል
" በዚህ ሁሉ ግን በወደደን በእርሱ ከአሸናፊዎች እንበልጣለን።"
(ወደ ሮሜ ሰዎች 8:37)

አስተዉሉ አሸናፊዎች አይልም ነገር ግን ከአሸናፊዎች እንበልጣለን ነው የሚለው ፡፡

መርሳት የሌለብን ነገር ከአሸናፊዎች የምንበልጠው በክርስቶስ ብቻ ነው !!ስለወደደን በመስቀል ሞት ራሱን ቀጣና አዳነን ፡፡ አሜን !
አሜን !

ለዚህ ዉለታ የምንመልሰው ምን አለ?
ምንም!ነገር ግን ህይወታችን ÷ፈቃዳችንን ÷አምልኮአችንን ለሱ ይሁን አሜን !

#General

💢💢 @PurityTube 💢💢
💢💢 @Puritytube 💢💢
🕑🕑 መቼ

የፍቅር ጓደኝነትን ለመጀመር ትክክለኛ ጊዜውን ማወቅ እጅግ በጣም አስፈላጊ ነው፡፡

የብዙ ሰዎች ጓደኝነት ትዳር ላይ ሳይደርስ ከሚፈርስባቸው ምክንያቶች ውስጥ አንዱ ያለጊዜው መጀመሩ ነው፡፡

👉 ጓደኝነትን ያለጊዜ በመጀመር ከሚደርሱት ጉዳቶች ውስጥ ደግሞ ዋነኛው የቅድስና ችግር ነው፡፡

💯 ከእነዚህ ሁሉ ችግሮች ለመዳን የፍቅር ጓደኝነትን ከመጀመራችን በፊት እውን ትክክለኛ ጊዜው ነውን? ብለን ራሳችንን መጠየቅ ይኖርብናል፤ ምን መጠየቅ ብቻ እርግጠኛ የሆነ መልሱንም ማወቅ አለብን‼️

ጊዜ አለመጠበቅ የሚያመጣውን ጉዳት በሚገባ ያስተዋልን እንደሆነ “ታዲያ እንዴት ነው ጊዜውን ማወቅ የምንችለው? 🤷‍♂የሚል ጥያቄ ወደ አእምሮአችን ይመጣል፡፡

👉የዘጠኝ ዓመት ሕፃን ልጅ ፍቅረኛ ልያዝ ወይ ብላ ብትጠይቃችሁ በእርግጠኝነት የምትመልሱላት መልስ አንቺ እኮ ገና ሕፃን ልጅ ነሽ ፍቅረኛ ለመያዝ ትንሽ ማደግ አለብሽ የሚል ነው፡፡

👉ነገር ግን አንድ የሀያ አምስት አመት ኮረዳ ተመሳሳይ ጥያቄ ብትጠይቃችሁ ህፃን ነሽ እደጊ አትሏትም ወይም ደግሞ እንዴት በሀያ አምስት ዓመትሽ አትሏትም ይልቁንም ልጁ ማነው? ክርስትያን ነው ወይ? ባሕርይው ምን ዓይነት ነው? እና ሌሎችንም ጥያቄዎችን በመጠየቅ ለማጣራት ነው የምንሞክረው፡፡

💢 ከዚህ የምንረዳው የፍቅር ጓደኝነትን መያዝ ወይም አለመያዝ የሚወሰነው በእድገታችን ነው ማለት ነው፡፡

እድገት ምንድን ነው በእድሜና በአካለመጠን የመግዘፍ ብቻ ወይስ አርቆ የማሰብና የማስተዋል መጠን ክፍል እየቆጠሩ መመረቅ ብቻ ወይስ በማህበራዊና ስነልቦዊ ዕውቀት መራቀቅ፣ እድገት ምንድን ነውስንት ዓይነት እድገት አለ


🗝እድገት የሚለካው ሁሉን አቀፍ በሆነ አዎንታዊ የለውጥ መጠን ነው፡፡ አንድ ሰው ሀያ እና ሀያ አንድ አመት ስለሞላው ብቻ አድጓል ማለት አንችልም❗️💯

🛑በትምህርት ልቆ ዶክተር ኢንጂነር ቢባል ይህ ብቻውን የእድገቱ ማሳያ ሊሆን አይችልም፡፡

👉 እድገት ዘርፈ ብዙ፣ መጠነ-ሰፊና፣ እና ሁሉን አቀፍ አዎንታዊ የለውጥ መጠን ነው፡፡

👉የፍቅር ጓደኝነትን ከመጀመራችን በፊት በቅድሚያ ሁለንተናዊ የሆነ እድገታችንን መመርመር መቻል አለብን፡፡

💢 ይህን ስናደርግ ትክክለኛ ጊዜው ይሁን አይሁን መወሰን ቀላል ይሆንልናል፡፡




ለወዳጅዎ #ሼር ያድርጉ🙏


💢💢 @PurityTube 💢💢
💢💢 @PurityTube 💢💢
_"ግን እኮ ድንግል ናት!"_____



ለእስራኤላውያን ከተሰጡት በመቶዎች የሚቆጠሩ ትዕዛዛት ይሄኛው ትኩረቴን ይስበዋል፡፡
👉"በሬንና አህያን በአንድ ቀንበር ጠምደህ አትረስ"....ዘዳ 22፥10(አዲሱ መደበኛ ትርጉም)

ሌሎች ትዕዛዛት እንደ "አትግደል" እና "አታመንዝር" ያሉትን በግልፅ እረዳቸዋለሁ፡፡
ይሄ ግን ትንሽ ግር ይለኛል"በሬንና አህያን በአንድ ላይ አትጥመድ?" ምን?

አንድ ቀን ስለዚህ ጥቅስ ፍለጋ አደረግሁና ይሄን አገኘሁ፡፡
መጀመሪያ አእምሮዬ ውስጥ የመጣው ጥያቄ
ለምንድን ነው እግዚአብሄር ህዝቡ በሁለት አይነት እንስሶች እንዲያርሱ ያልፈለገው

መልካም፡ ሌላ ቦታ ላይ ስለመጠመድ የሚናገረው በ 2ኛ ቆሮ 6 ፥ 14 ላይ "ከማያምኑ ጋር በማይመች አካሄድ አትጠመዱ፡፡"

በዘዳ 22፥10 እና በ2ኛ ቆሮ 6፥14 መካከል የሆነ ግንኙነት መኖር አለበት፡፡ አይመስላችሁም? እኔ ይመስለኛል ነገርግን ምን አይነት ግንኙነት ነው ያላቸው?

👉እነዚህ ሁለት የተለያዩ እንስሳት ፥ በሬና አህያ ፥ ሁለቱም እፅዋት ተመጋቢ ከመሆናቸው ውጪ በጣም የተለያየ ባህሪ ነው ያላቸው፡፡
አህያ ከበሬ በመጠን ያነሰ ሰውነት አለው፡፡ ከዚህም የተነሳ እርምጃዎቹ ከበሬ ያጠሩ ናቸው፡፡

👉እነዚህ ልዩነቶች ሁለቱን አንድ ላይ ጠምዶ ለማረስ ሲታሰብ ትልቅ ችግር ይፈጥራሉ፡፡ ምክንያቱም እንቅስቃሴያቸው እኩል ስለማይሆን አንዳቸው ወይም ሁለቱም መሰቃየታቸው አይቀሬ ነው፡፡

ገራሚ የሆነው የእነዚህ እነንስሳት ልዩነት ያለወው ገግን እዚህ ላይ ነው፡፡👇👇

🔑በሬ መርጦ በመብላት በኩል በጣም ንፁህ የሚባል እንስሳ ነው፡ስለራበው በብቻ ወይም እፅዋቱ መልካም መስሎ ስለታየ አይበላውም፡፡ ወደ አህያ ስንመጣ ሌላ ታሪክ ነው፡፡ አህያ ቆሻሻ ፣ መራም ሆነ መርዛማ አይመርጥም፡፡ ስለዚህ በእርግጠኝነት የአህያ አፍ መጥፎ ጠረን አለው ማለት ነው፡፡

🎇የአህያ እንዲህ መሆን ለበሬ ጉዳዩ አይደለም አንድ ላይ እስካልተጠመዱ ድረስ፡፡
ገበሬ አህያና በሬን አንድ ላይ
"መጥመድ " ከጠለ በሬ በአህያው መጥፎ ጠረን ምክንያት ይሞታል፡፡ያስቃል አይደል😀😀 (በሳይንስ የተረጋገጠ ነው🙍፡፡)

👉ስለዚህ የእግዚአብሔር ቃል "ከማያምኑ ጋር በማይመች አካሄድ አትጠመዱ " ሲል እንዲህ ማለቱ ነው ፦ "በክርስቶስ የማያምንን ሰው ለማግባት መወሰን ገዳይ ውሳኔ ነው "

󾠬ስለዚህ ዛሬ መልዕክቴ ይህ ነው
ከማያምን ሰው ጋር ለመጋባት ወይም የፍቅር ግንኙነት ለመጀመር ያቀዳችሁ ብትኖሩ እነዚህ ከላይ የተነሱትን ሁለት ጥቅሶች አስቡና
ውሳኔአችሁን ሳይረፍድባችሁ በድጋሚ አስቡት፡፡

እንዲህ አትበሉ ፦
👉"መጠጥ እኮ አይጠጣም ወደ ቤተክርስቲያን ባይሄድም ግን ኢየሱስን ይወዳል፡፡"
👉"ግን እኮ ድንግል ናት አማኝ ባትሆንም አትቃወምም እንድታምን ደግሞ እፀልይላታለሁ፡፡"
👉"ጌታ በእኔ ተጠቅሞ ወደራሱ ሊስበው ቢሆንስ?!"

ይሄን የምታነቢው/በው ምናልባት መንፈስቅዱስ በዚህ ፅሁፍ እያሳሰበሽ/ህ ይሆናልና ድምፁን ችላ አትበይ/ል፡፡

🌟በመጨረሻም በ 2ኛ ቆሮ 6፥ 14-18 ላይ ያለውን የእግዚአብሔር ቃል እንድታነቡ እጋብዛለሁ፡፡





💢💢 @PurityTube 💢💢
💢💢 @PurityTube 💢💢
🔽#Masturbation ሀጢያት ነው🔽

🔴መጀመሪያ masturbation የሚለውን ቃል ላብራራ ቀጥተኛ የአማርኛ አቻ ፍቺ እንዳለው ባላውቅም "ራስን ማስደሰት" ወይም "ራስን ማርካት" የሚል ትርጓሜ ልንሰጠው እንችላለን፡፡

በአብዛኛው ክርስቲያናዊም ሆነ ከክርስቲያናዊ ባልሆኑ የጥናት ስራወዎች ከ95-97% የሚሆኑ ታዳጊዎች የመራቢያ አካላቸውን የመነካካትና በዛም ውስጥ ጥሩ ስሜትን የሚያገኙበት ደረጃ ውስጥ እንደሚያልፉ ለማወቅ ተችሏል፡፡
ይህ ልምምድ ከ 9-12 ባለ ዕድሜ ክልል ውስጥ ሊከሰት ይችላል፡፡

ይህ ክፉ ሀሳብ የሌለበት ራስን የመነካካትና ጥሩ ስሜትን መፈለግ ቅጣት ይገባዋል ብዬ አላስብም፡፡

🔑ይልቁንም በዚህ ሰዓት ይሄ ልጅ የሚያስፈልገው አጠገቡ በመሆን ፆታዊ ጉዳዮችን ለዕድሜው በሚመጥን መልኩ የሚያስተምረው ፥ እግዚአብሄር ለምን ሰውነታችንን በዚህ መልኩ እንደፈጠረው እንዴትስ ይህን ሰውነቱን ለእግዚአብሔርም ለራሱም አእምሮ #በሚመች መልኩ መያዝ እንዳለበት የሚነግረው ወላጅ ነው፡፡(ሮሜ 12 ፥ 1-3)

🔷ያለበለዚያ ግን ይሄ ልጅ ራሱን በመነካካት ጥሩ ስሜትን ከማግኘት ያልፍና ወደ Masturbation ይሻገራል፡፡ ይሄንም በተደጋጋሚም ማድረግ ይጀምራል፡፡

👉ይሄ ድርጊቱም በተለያዩ ሰዎች ግፊት #porn ወደማየት ያድጋል፡፡
👉ይህ ልምምድ ከጊዜ በኃላ #ሱስ ይሆናል፡ በቀን ውስጥ ከ 2-14 ጊዜ ሊደጋግመው ይችላል፡፡

󾠬ይህ ሁኔታ በሂደት የሚያዩትን ወይም የተመኙትን ነገር በተግባር ለማውጣት ማለትም ግብረስጋ ግንኙነት ለመፈፀም መንገዶችን ወደ መፈለግ ይደርሳል፡፡

󾠬ይሄ ልምምድ ሁልጊዜም ፀፀት ፣ ሀዘን ፣ አሰልቺነት ፣ ጭንቀት ፣ ፍራቻና ራስን የማጥፋት ሀሳቦችን ከኃላው ያስከትላል፡፡

👉እግዚአብሄር ሁላችንንም ሲፈጥረን ፆታዊ ግንኙነትን የሚፈልግ ደግሞም ያንን ፍላጎት የሚቀሰቅስ ነገር ሲያጋጥም ምላሽ የሚሰጥ ሰውነትን #ፈጥሮልናል፡፡

👉ሆኖም እግዚአብሄር ስለ ፆታዊ ግንኙነት በራሳችን ፈልገን እንድናገኝ ዝም ብሎ አልተወንም፡፡

👉መመሪያ ወይም ብዙ ጊዜ እንደሚባለው "user manual" ሰጥቶናል፡፡ እርሱም #መፅሀፍቅዱስ ነው፡፡

💯ይህ መመሪያ እንደፈለጉ በስሜታቸው ከሚኖሩት እንስሳት ይለየናል ፡፡ የግብረስጋ ግንኙነት ፤ የእግዚአብሔር ቃል እንደሚለው ፤ በአንዲት ሴት እና በአንድ ወንድ መሀል በሚደረግ የአንድነት ጋብቻ ውስጥ #ብቻ ሊኖር የሚገባ ነው፡፡

ይህም ማለት ሚስት ለባሏ የምትሰጠው ባልም ለሚስቱ የሚሰጣት ለጋራ እርካታ የሚሆን መልካም ተግባር ነው፡፡ ይህ እግዚአብሄር ሁላችንም #ለትዳር_አጋሮቻችን #ብቻ እንሰጠው ዘንድ የሰጠን ስጦታ ነው፡፡

💥በመሆኑም በትዳር ውስጥ ያለ sex ደስታ ሰላምና ፍቅር እንጂ በምንም መልኩ ጉዳት አይፈጥርም፡፡ ልክ እንደ masturbation
ፀፀት ፣ ሀዘን ፣ አሰልቺነት ፣ ጭንቀት ፣ ፍራቻና ራስን የማጥፋት ሀሳቦችን ከኃላው አያሰከትልም ፡፡

እስከዛሬ ድረስ "እግዚአብሄር በ masturbation እየባረከኝ ነው" የሚል አንድም ሰው አላጋጠመኝም፡፡

👉ምክንያቱም ከእግዚአብሔር መንፈስ ዳግም የተወለደ ማንም ሰው ከ masturbation ጋር ተከትለው የሚመጡት እንደ ጭንቀት ፣ ፍርሃትና ብቸኝነት የመሳሰሉት ነገሮች ከእግዚአብሔር ጋር ያለውን ግንኙነት መልካም አያደርጉለትም፡፡

👉በመፅሐፍ ቅደስ ውስጥ sex ራስን ማርካት እንደሆነ ተደረጎ በየትኛውም ቦታ አልተጠቀሰም፡፡
" ባል ለሚስቱ የሚገባትን ያድርግላት፥ እንደዚሁም ደግሞ ሚስቲቱ ለባልዋ። ሚስት በገዛ ሥጋዋ ላይ ሥልጣን የላትም፥ ሥልጣን ለባልዋ ነው እንጂ፤ እንዲሁም ደግሞ ባል በገዛ ሥጋው ላይ ሥልጣን የለውም፥ ሥልጣን ለሚስቱ ነው እንጂ። "...... 1ኛ ቆሮ 7:3-4

" አዲስ ሚስትም ያገባ ሰው ወደ ጦርነት አይሂድ፥ ነገርም አይጫኑበት፤ ነገር ግን አንድ ዓመት በቤቱ በፈቃዱ ይቀመጥ፥ የወሰዳትንም ሚስቱን ደስ ያሰኛት። "
(ኦሪት ዘዳግም 24:5)

🔴አያችሁ የ sex እርካታ ባል ለሚስቱ ሚስትም ለባሏ የምትሰጠው እንጂ ሰው ከሌላ ቦታ #ከራሱም ቢሆን ሊያገኘው የሚገባ እርካታ አይደለም፡፡

󾠬የ sex እርካታ በትዳር ውስጥ ባለ መኝታ #ብቻ የሚገኝ ከእግዚአብሔር የተሰጠ ድንቅ ስጦታ ነው፡ ስለዚህ ባልና ሚስት በአንድነት ሲፀልዩ " እግዚአብሄር ሆይ ስለሰጠኸን ድንቅ ስጦታ እናመሠግንሃለን" ማለት አለባቸው፡፡

💯 ከዚህ ውጪ ያለ የፆታዊ ግንኙነት እርካታ በሙሉ #ሀጢያት ነው፡፡

👉ራስን ማርካት masturbation ይባላል፡፡
👉ከትዳር ውጪ የሚደረግ አብሮ መተኛት ማመንዘር ይባላል፡
👉ሁለት ያላገቡ ወይም ያልተጋቡ ጥንዶች አብረው ቢተኙ ግልሙትና ይባላል፡፡ ሌሎችም አሉ፡፡
በእነዚህ ነገሮች እግዚአብሄር ምንም ቦታ የለውም፡፡ ይልቁንም በዚህ ነገር ውስጥ ያለው #ዲያቢሎስና የራሳችን #የሀጢያት ተፈጥሮ ነው፡፡

🔑ስለዚህ በነዚህ ነገሮች ሁሉ ራሳችንን መግዘት አለብን፡፡
" ትዕግሥተኛ ሰው ከኃያል ሰው ይሻላል፥ በመንፈሱም ላይ የሚገዛ ከተማ ከሚወስዱ ይበልጣል። "
(መጽሐፈ ምሳሌ 16:32)

🔵ይሄ ማለት ከላይ በተነሱት ጉዳዮች ላይ ንፁህ መሆን የቻለ ሰው መልካም ባል /ሚስት ፣ መልካም አባት /እናት እንዲሁም በመንፈሳዊ ነገር ያደገ ይሆናል፡፡

የምንኖርበት ማህበረሰብና ዘመን በነዚህ ጉዳዮች ንፁህ እንድንሆን አይረዳንም፡፡ ነገርግን መፅሐፍ ቅዱስ ሲናገር " በዚህ ሁሉ ግን በወደደን በእርሱ ከአሸናፊዎች እንበልጣለን።"
(ወደ ሮሜ ሰዎች 8:37) ይላል ፡፡

ተባረኩ!!!!

#General

💢💢 @PurityTube 💢💢
💢💢 @PurityTube 💢💢
👪👪የማህፀን ፍሬ 👪👪


👉ልጆች የእግዚአብሔር ስጦታዎች ከሆኑ ምናልባት ዓለም በሙሉ ተስማምቶ ይህን ውድ ስጦታ ቢቃወም አይገርምም፡፡

👉ሰይጣን ልጆችን በፍፁም አይወድም ይህን ታውቃላችሁ? አዎ አይወድም ፡፡

👉ሁልጊዜም ልጆችን በማህፀን ሳሉም ሆነ ከተወለዱ በኃላ ሊያጠፋ የተለያዩ እቅዶችን ይነድፋል፡፡ (ሰይጣን ኢየሱስን እንዲሁም ሙሴን ሊያጠፋቸው ፈልጎ እንደነበር ልብ በሉ)

👉ስጋ የዚህን ዓለም መልዕክቶች ወደ ማመን ይወሰዳል፡፡ እነዚህ መልዕክቶችም

💥"ልጅሽን ጡት ባታጠቢ መልካም ነው አለበለዚያ ይህን ጥሩ የሰውነት ቅርፅሽን ታጪያለሽ !" ወይም
💥 "ልጅሽን ለሞግዚት ትተሽ ወደ ስራ ሂጂ ያኔ አንቺም ልጅሽም የተሻለ ኑሮ ትኖራላችሁ!"
እና የመሳሰሉት ናቸው፡፡

ከዚህ ሲከፋ ደግሞ ሰይጣን እርጉዝ በሆነች ሴት ጆሮ "አስወጪው ከዛ ትምህርትሽን ትማሪያለሽ ፣ ሀብታም ትሆኚአለሽ ፣ የፈለግሺውን መኪና ትነጂአለሽ ከዛ በኃላ ልጆች ይኖሩሻል ሰዎችም ያከብሩሻል፡፡" ወይም

💥" መፅሀፍ ቅዱስም እኮ ለሁሉም ጊዜ አለው ይላል አሁን ልጅ ለመውለድ ጊዜሽ አይደለም ግድየለሽም አስወጪው"....ወዘተ ይላል፡፡ ይሄ የዲያቢሎስ #ሽንገላ ነው ንቂበት!

🔵መፅሀፍ ቅዱስ ግን የሚለው "ልጆች የእግዚአብሔር ስጦታ ናቸው ፥ የሆድም ፍሬ የእርሱ ዋጋ ነው፡፡" የእግዚአብሔርን ስጦታ ደግሞ ከምድራዊ ነገር ጋር ልናወዳድረው አንችልም ፡፡

🔴እንደውም አንዳንድ ጊዜ እግዚአብሄር ልጆችን ወላጆቻቸውን ለመገሰፅና ለማስተማር ይጠቀምባቸዋል፡፡

ደግሞም ልጆች ሲያድጉ ማየት የሚሰጠው ደስታ ዓለም ልትሰጠው የማትችለው አይነት ደስታ ነው፡፡

🌟አንዳንድ ጊዜ ልጆች በእርግጥም የእግዚአብሔር ስጦታዎች መሆናቸውን ከተጠራጠርን እግዚአብሔር አይናችንን እንዲከፍት መፀለይ አለብን፡፡

🔑 ምክንያቱም ከእግዚአብሔር የሆነውን ነገር መረዳት የምንችለው በእግዚአብሔር መንፈስ ብቻ ስለሆነ !!

💢💢 @PurityTube 💢💢
💢💢 @PurityTube 💢💢
ከPorn ሱስ ለመውጣት ከኢየሱስ ጋር ፍቅር ሊይዝህ ግድ ይላል

👤A4P እንግዳ👤> PORN ከማየት እራሴን መጠበቅ የምችለው በምን አይነት መንገድ ነው?
A4P>አጭርና 💯 ስኬታማ የሆነውን መንገድ ነውየምትፈልገው ወይስ ረጅሙን እና ስኬታማ ላያደርግህም ሊያደርግህም የሚችለው መንገድ ነው የምትፈልገው ?

👤A4P እንግዳ👤>ከዚህ ህይወት ሊያስወጣኝ የሚል አጭርና ስኬታማ የሆነ መንገድ ከለ እሱ ይሻለኛል! ::

A4P>መልካሙን መርጠሀል!ትክክለኛ የሆነ አእምሮ (understanding )ያለው ሠው የሚመርጠውን ነው የመረጥከው፡፡ እሺ! ከporn ሱስ (addiction ) ለመውጣት አጭርና ስኬታማ መንገድ #ኢየሱስ_ክርስቶስን #በፍቅር መውደድ÷#በሱ በመደሰት ነው::

ምክንያቱም ደስታህን ከሱ ብቻና ብቻ ነው የምታገኘው::ለዘህም መፅሐፍ ቅዱስ ሲናገር

👉" በእግዚአብሔር ደስ ይበልህ፥ የልብህንም መሻት ይሰጥሃል።"ይላል ::
(መዝሙረ ዳዊት 37:4)👈

ደስታ እሱ ኢየሱስ ክርስቶስ ነው!!!

እንግዳ ፦ እሺ.... ከporn ሱስ ለመውጣት ከኢየሱስ ጋር ፍቅር ሊይዝህ ያስፈልጋል የተባለው ነገር ምንም ትርጉም አልሰጥ አለኝ፡፡እስኪ ቀለል ባለ መንገድ ?

A4P፦ ምን ማለት መሰለህ ፡፡ ከኢየሱስ ጋር ፍቅር የሚይዝህ ከኢየሱስ የበለጠ ጊዜ ሰጥተኸው ጭንቀት የወለደብህን ልምምድ ለማድረግ ስትነሳ ዝም ብለህ መፅሀፍ ቅዱስህን አውጣና አንብብ ፣ ፀሎት ለመፀለይ ሞክር ፣ መጀመሪያ ሰሞን እውነት ነው ምንም ትርጉም አይሰጥህ ይሆናል ፡፡

ሊደብርህ ሞኝነት ሊመስልህም ይችላል፡፡
ነገርግን ይሄን ሁሉ ስሜት እያለ ዝምብለህ መፅሀፍ ቅዱስን ማንበብና መፀለይህን ቀጥል፡፡
porn ለማየት በፈለግህ ጊዜ ሁሉ ይህን አድርግ፡፡

ከዛ ከጥቂት ጊዜ በኃላ አንተ ስለ porn ረስተህ ምናልባት ሰዎች ሲያወሩ ስትሰማ ምን ነክቶኝ ነው ግን ያኔ ይህን አፀያፊ ነገር ሳደርግ የነበረው😕 ብለህ አሁን ያለህበትን ሁኔታ ወደኋላ ታየዋለህ፡፡

የሆንከው ግን አንድ ነው እርሱም የልብህን ዙፋን porn ለቆ ሄዷል ኢየሱስም ቁጭ ብሎበታል፡፡
አሁን ገባህ ከኢየሱስ ጋር ፍቅር ሊይዝ ይገባል ያልኩህ ነገር?

እንግዳ ፦ አዎ ገብቶኛል ፡፡ ግን ምንድን ነው ከporn ለመውጣት ረዥሙ መንገድ?

A4P ፦ ጥሩ ጥያቄ...አሁን ከነገርኩህ መንገድ ውጪ ያሉት መንገዶች በሙሉ ረዥምና ወደ ድል ላያደርሱህ የሚችሉ ናቸው፡፡

#General

💢💢 @PurityTube 💢💢
💢💢 @PurityTube 💢💢
መልካም ዜና ስኬታማ ትዳር ለሚፈልጉ

የፍካት ስነ ልቦና ማማከር አገልግሎት ላገቡ፥ለማግባት ለሚያስቡ ህይወትን የሚቀይር ስልጠና ታህሳስ 11(ቅዳሜ) 2012 ይሰጣል፥

ቦታ፥ ቤስት ዌስተርን ሆቴል(ቦሌ ሃርመኒ ሆቴ ፊት ለፊት)

ሰአት፥11፥30(ቀድመው በመገኘት ቦታ ይያዙ)

በስልጠናው ላይ ለመሳተፍና ለመመዝገብ 6374 ላይ ok ብለው ይላኩ፥

ከትዳር አጋርዎ ወይንም ፍቅረኛዎ ጋር እንዲመጡ እንመክራለን፥

share በማድረግ ራዕያችንን ይደግፉ፥
#sex_positions

👉 Sex position ማለት በግብረ ስጋ ግንኙነት ወቅት የጥንዶች አኳኋን ወይም ከቦታ አንፃር ያለ አኳኋን ማለት እንችላለን፡፡

ማናችንም ምንም አይነት አስተሳሰብም ሆነ እምነት ብናራምድም ስለ sex position የማወቅ ጉጉት ይኖረናል፡፡

የሀይማኖት ሰዎች ከሆንን የትኛው የ sex position #ቅዱስ የትኛው ደግሞ ያልተቀደሰ ወይም #እርኩስ መሆኑን ብናውቅ ደስ ይለናል፡፡

👉እውነት ነው ለእግዚአብሄር መኖር ፣ ቀጣዩ ስራችንም መልካም እንዲሆን እንፈልጋለን ፡፡

👉በመኃልዬ መኃልዬ ዘሰሎሞን (ስለክርስቶስና ስለቤተክርስቲያን ፍቅርና አንድነት የሚስለው መፅሐፍ ) ላይ ስለ ፍቅርና ስለ ፍቅር ግንኙነት በብዛት ያወራል፡፡ከአንድ ጊዜ በላይ ስለ"sex position " ተጠቅሷል ፡፡(sex position የሚለው ቃል በትምህርተ ጥቅስ ውስጥ እኖደተቀመጠ ልብ በሉ )

👉መኃልዬ መኃልዬ ዘሰሎሞን 2፥ 6 ፣ 8፥3 እና 8፥6 ላይ ይገኛሉ፡፡
ከነዚህ ጥቅሶች ውጪ መፅሀፍ ቅዱስ ላይ ስለ "Sex position " የሚያወራ ቦታ አላውቅም፡፡

"ለምንድን ነው እግዚአብሄር በመፅሐፍ ቅዱስ ውስጥ ተቀባይነት ያላቸውን የ "sex position" አይነቶች ያልዘረዘረው ?" ብላችሁ ትጠይቁ ይሆናል፡፡

󾠬እኔ እንደማምነው ለዚህ ጥያቄ ቀጥተኛውና አጭሩ መልስ እንደዚህ የሚባል ነገር ስለሌለ ነው! የሚል ይሆናል፡፡

👉"sex position " ከሚለው ሀረግ ይልቅ "የፍቅር መግለጫ" የሚለውን መጠቀም እመርጣለሁ፡፡

እናም ይህ የፍቅር መግለጫ እንዲህ እንዲህ ተብሎ አንዱ አይነት ለሁሉም እንዲሆን ተደርጎ ሊዘረዘር አይችልም፡፡

💯 ምክንያቱም የፍቅር መግለጫ ለእያንዳንዱ ትዳር ልዩ "ሀnique" ስለሆነ ነው፡፡

🔥ይህም የሚሆነው ከጥንዶቹ ቅርርብ ፣ ፍቅርና ጤናማ ግንኙነት የተነሳ ሁለቱም ትክክለኛ ማንነታቸውን ሆነው ለመገኘት ነፃ ሲሆኑ ነው፡፡

👉ጥንዶች በጥልቀት እርስበርስ ሲተዋወቁ ፣ እግዚአብሄርንም ለትዳራቸው ጤናማነት ፍቃድ ሲሰጡት በግብረ ስጋ ግንኙነት ወቅት የሚገርምና የሚደንቅ የፍቅር መግለጫ በጋብቻቸው አልጋ ላይ ይገለጣል፡፡

💯እነዚህ የፍቅር መግለጫዎች መፅሀፍት በማንበብና የተለያዩ ነገሮችን በማየት የሚገኙ ውጤቶች አይደሉም፡፡

💯ይልቁንም የሁለቱ የተጋቡት ጥንዶች ልክ ክርስቶስ እኛን በወደደበት በተቀበለበትና በቻለበት አይነት ሁኔታ አንዳቸው አንዳቸውን ለመቻል ፣ ለማፍቀር እና ለመቀበል ካላቸው ተነሳሽነትና መሰጠት የሚመነጭ ነው፡፡

💯ይህ ማለት የናንተ ቤትና የጎረቤታችሁ የፍቅር መግለጫ አንድ አይነት ሊሆን አይችልም ማለት ነው፡፡

ስለዚህ የፍቅር መግለጫዎች ከሌላ ቦታ አይተን ወደ እኛ የምናመጣቸው ወይም የምንኮርጃቸው አይደሉም ማለት ነው፡፡💯

󾠬ብዙ ጊዜ ትዳር ውስጥ ችግር የሚፈጠረው ከሁለቱ አንዳቸው በትዳራቸው ውስጥ ላለ ቅርርብና መሰጠት የማይመጥን የፍቅር ግንኙነት ለመሞከር ጥረት ሲያደርጉ ነው፡፡

🔑እናም የዛሬውን መልዕክት እንዲህ ብለን እንዝጋው፡፡ እንደ ክርስቲያን የ "sex position" ሀሳብ ለዚች በተስፋቢስነትና ማቆሚያ በሌለው መልኩ ወሲባዊ እርካታን ያለእግዚአብሔር ለምትፈልገው ዓለም እንተወውና እኛ ትዳራችንን ለማጠናከር መስዋዕትነት ባለው ፍቅር ላይ እናተኩር፡፡

ከዛ በኋላ ከእግዚአብሄር ባርኮትና በፍቅር ውስጥ ከሚፈልቀው የፍቅር መግለጫ ውጪ ያለውን ነገር ፍለጋ የትም አንሄድም፡፡💯

#General

💢💢 @PurityTube 💢💢
💢💢 @PurityTube 💢💢
የፍካት ሁለተኛ ዙር ስልጠና በመልካም ሆኔታ በBest Western plus Hotel መሰጠቱን ስንገልጽ በደስታ ነው፥

ሁለንተናዊ ስኬትን ለመቀናጀት የሚረዳውን ቀጣይ የስነ ልቦና ስልጠና ላይ በቅርብ ቀን ለመሳተፍ ወደ 6374 ok ብለው ይላኩ፥በወር 24 ብቻ ይከፍላሉ፥
💍💍' #ፍርሃት '💍💍

👉ስሜታቸውን አሸንፈው እግዚአብሄርን ለማስደሰት የቆረጡ ብዙ ወጣቶች ወደ ትዳር ከመግባታቸው በፊት የግብረስጋ ግንኙነት ፈፅመው ስለማያውቁ የሚጋሩት አንድ የጋራ ስሜት አላቸው

እሱም 'ፍርሃት' ነው😱

👱‍♂በወንዶቹ በኩል "ምናልባት ባላረካት እንደወንድ አትቆጥረኝ ይሆን?" የሚለው የብዙዎች ፍርሃት ነው፡፡

👱‍♀️ሴቶች ደግሞ "ምናልባት ብዙ ቢያመኝ ደስታችንን ወደ ሰቀቀን እቀይረው ይሆን?" የሚለውን ፍርሃት ይጋሩታል፡፡

💯እውነቱ ግን እነዚህ ፍርሃት የሚመስሉ ስሜቶች አንድ ህፃን ልጅ ለመጀመሪያ ጊዜ ወደ ትምህርት ቤት ሲሄድ ከሚሰማው ፍርሃት የተለዩ አለመሆናቸው ነው፡፡

💢እግዚአብሄርም ቤተሰብም 'ይሁን' ባለው ነገር መጨናነቅ ተገቢ አይደለም፡፡

👉አንድ ማወቅ ያለባችሁ ነገር ቢኖር በሁለት ተጋቢዎች መሃል የግብረስጋ ግንኙነት መጣጣም ከጊዜ ወደ ጊዜ እየተሻሻለ የሚሄድ ነገር መሆኑን ነው፡፡

🔑ይልቁንም እግዚአብሄርን በማያከብርና ጊዜያዊ ስሜትን ለማርካት ሲሉ ብቻ ከጋብቻ ውጪ የግብረስጋ ግንኙነትን የተለማመዱ ሰዎች ከእርካታ ይልቅ የፍርሃት ሰለባ እንደሚሆኑ ይታመናል፡፡

🔑ምክንያቱም ገና ከመጀመሪያው ነገሩን የሚጀምሩት"ወይኔ ሃጢያት ነው እኮ!" ፣ "አረግዝ ይሆን?" ፣ "ታረግዝብኝ ይሆን?" ፣ "ቤተሰብ ቢያውቅብንስ?" ፣ "HIV ብያዝስ?" ፣ "ለጓደኞቹ/ቿ ስለእኔ መጥፎ ነገር ቢያወራስ/ብታወራስ?" እና ከመሳሰሉ አስፈሪ ሁኔታዎች ጋር ፊትለፊት በመጋጠም ነው፡፡

💯ስለዚህ እስከ ጋብቻችሁ ቀን ድረስ በድንግልናና ስሜታችሁን በመግዛት የቆያችሁ ተጋቢዎች ሁሉ ፍርሃታችሁ ተፈጥሮአዊና የሚጠበቅ ነው፡፡ ሆኖም ግን "You will be fine😉"

📌በቅርቡ ለሚያጋቡ ወዳጆቻችዎ #ሼር ያድርጉ

#couples
#General

💢💢@PurityTube 💢💢
💢💢@PurityTube 💢💢
ምኞት አይከለክልም
በደንብ ይከለከላል

ብዙን ጊዜ መፅሐፍ ቅዱስ አድርግ እና አታድርግ አይደለም የሚለው ምክንያቱም ማድረግ የመጨረሻው ደረጃ ነው፡፡

ለዚህም ነው ኢየሱስ ሲናገር

🔥 " እኔ ግን እላችኋለሁ፥ ወደ ሴት ያየ ሁሉ የተመኛትም ያን ጊዜ በልቡ ከእርስዋ ጋር አመንዝሮአል።"
(የማቴዎስ ወንጌል 5:28)የሚለው ፡፡

ደረጃው 👉ማየት መመኘት ድርጊት ነው

󾠬 ዝሙት መፈፀም ድርጊት ብቻ ሳይሆን ማየት ደግሞም መመኘት ነው ፡፡ሰው በተፈጥሮ አለማየት አልተሰጠውም ነገርግን ምኞት የእሱ ድርሻ ወይም የሱ ፍቃድ ይጠይቃል.፡፡

አብዛኛውን ጊዜ በአይን አይቶ የሚመኘው ወንድ ሲሆን ብዙውን ጊዜም ለዝሙት ይጋለጣል

👉ለዚህም ጳውሎስ በመልዕክቱ " ስለ ጻፋችሁልኝስ ነገር፥ ከሴት ጋር አለመገናኘት ለሰው መልካም ነው።

ነገር ግን ስለ ዝሙት ጠንቅ ለእያንዳንዱ ለራሱ ሚስት ትኑረው ለእያንዳንዲቱ ደግሞ ለራስዋ ባል ይኑራት።"
(1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 7:1-2)

ከጥቅሱ እንደምንረዳው ከሴት ጋር አለመገኘት በጋብቻ ቢሆንም ባይሆንም ለሰው መልካም ነው ይልና "ነገር ግን " የሚለውን ቃል በትኩረት መመልከት ያስፈልጋል::

ምክንያቱም የመጀመሪያውን ሀሳብ ትተን ቀጣዩን እንድመለከት ያደርጋል፡

ይህ ቁጥር ዝሙትን የምንከላከልበት መንገድ ይናገራል ይህም ለወንድ የሴት ሚስት ወይም ,ለሴት የወንድ ባል ይኑረው ፡፡

በቀረው ደግሞ ከዝሙት የሚዳንበትን መንገድ ያስቀምጣል እሱም ሽሽ (flee or run away )ይህንን ሲል ፈሪ ምሰል ወይም በፍጥነት ከዚያ አካባቢ ራቅ ማለት ሲሆን
" ከዝሙት ሽሹ። ሰው የሚያደርገው ኃጢአት ሁሉ ከሥጋ ውጭ ነው፤ ዝሙትን የሚሠራ ግን በገዛ ሥጋው ላይ ኃጢአትን ይሠራል።"
(1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 6:18)

🏃 መሸሽ የሚጀምረው ከትንሽ ነገር ነው ለምሳሌ
porn ካላቸው ፊልሞች መፅሃፎች> ከTV ቻናሎች መጀመር ይቻላል፡፡

📹christian movie በመመልከት
📙መፅሐፍ ቅዱስ በማንበብ
👉ለፀሎት ጊዜን በመስጠት መተካት ይቻላል!!!

#General

💢💢 @PurityTube 💢💢
💢💢 @PurityTube 💢💢
አለቀሰ😭 'ቻው' በይው👋👋

🔷ሴት ልጅ ላላገባችው ወንድ ድንግልናዋን ብትሰጠው እሷ ምታስበው ፦
እሷ ለእሱ ጣዖቱ ፣ ህልሙ ከሁሉ ይልቅ ቅድሚያ የሚሰጣት እንደምትሆን ነው፡፡

👉 የወንድ አስተሳሰብ ፣ ፆታዊና ስሜታዊ ዓለም በዚህ መልኩ አይሰራም፡፡

󾠬ሴት ልጅ ለወንድ ህልሙ የምትሆነው ለsex እንዲጠብቅ ወይም እንዲቆይ ስታደርገው #ብቻ ነው፡፡ ለራሱ ሊያደርጋት የሚፈልገውና የሚያልመው ያኔ ብቻ ነው ፡፡

ያላገባሽ ሴት ልጅ ከሆንሽ ይህን አስተውይ ወንድ ልጅ የአንዲትን ሴት ድንግልና ቢወስድ ስለራሱ እንጂ ስለእሷ ምንም ላያስብ ይችላል፡፡

🔵ምክንያቱም የእሱ sexual ዓለም እንደሴቷ አይደለም፡፡

አንድ ወንድ የሚያፈቅርሽ ከሆነ እስከትዳር ድረስ አይነካሽም ይጠነቀቅልሻል፡፡

🔗አግቢኝ ብሎ ጠየቀሽ ወይም አገባሻለሁ አለ ማለት ያገባሻል ማለት አይደለም

"ግን እኮ ከትዳር በፊት sex አናደረግም ስለው አለቀሰ!!"

በእውነት ተይው ሲፈልግ እድሜ ልኩን ያልቅስ እንባው እንዲሰብክሽ አትፍቀጂለት፡፡

የእሱን ህልውና የሚያረጋግጠው sex ከሆነ 'ቻው' በይው፡፡


💢💢 @PurityTube 💢💢
💢💢 @PurityTube 💢💢
🚺🚺የብዙ ሴቶች ስህተት🚺🚺

👉ብዙ ሴቶች እንዲህ ያስባሉ "ክርስቲያን ወንዶች ክርስቲያን ካልሆኑ ወንዶች የተለየ ወይም "የተሻለ" የsex ፍላጎት አላቸው " ብለው

👉ከዚህ የተነሳ ብዙ ጊዜ ሚስቶች ባሎቻቸው በየቀኑ sex ማድረግ በፈለጉ ጊዜ "ትክክለኛ ክርስቲያን ቢሆን ኖሮ እንዲህ አይልም ነበር!😱" በማለት ይወቅሷቸዋል፡፡

ጌታ ለነዚህ ባሎች ፀጋውን ያብዛላቸው🙏

ነገርግን እውነቱ ይህ ነው
ያመነም ሆነ ያላመነ ጤናማ ወንዶች ሁሉ ለsex ያላቸው ፍላጎት ተመሳሳይ ነው፡፡💯.......its biological


#married

💢💢 @PurityTube 💢💢
💢💢 @PurityTube 💢💢
🌱🌴 ተክል ለማደግ የፀሃይ ብርሃን 🌞፣ ውሃና ማዕድናት (አፈር)🍪 እንደሚያስፈልገው ሁሉ ፍቅርም ለማደግ #ጊዜ ያስፈልገዋል፡፡

👉ውጫዊ መስህብ ለረዥም ጊዜ አይዘልቅም💯
😍🔟󾠶󾠵 ....🔜󾠷😨

👉ፍቅር በልብ ውስጥ ስር ሰዶ እንዲያድግ #በዓላማና #በዕውቀት (በአጋጣሚ አይደለም) ለእርሱ ተብሎ የተለየ ጊዜ ይፈልጋል፡፡

#General

💢💢 @PurityTube 💢💢
💢💢 @PurityTube 💢💢
👀👀ሴት ማየት👀👀

ወንድ ልጅ የማየት ተፈጥሯዊ ባህሪ አለው፡፡
ማለትም ቆንጆ ሴት ስታልፍ አለማየት አይችልም፡፡አንዳንድ ባለትዳር ሴቶች 'ባሌ ቆንጆ ሴት ማየት የለበትም' ይላሉ፡፡

ማየት ሀጢያት እንደሆነ በመፅሐፍ ቅዱስ የትም ክፍል ላይ አልተፃፈም፡፡

👉አእምሮአችን የተለያዩ ስራዎች የሚሰሩ የተለያዩ ክፍሎች አሉት፡፡ የወንድ የእይታ ክፍል ቀጥታ ከsexual እርካታ ክፍል ጋር ይገናኛል፡፡

መፅሀፍ ቅዱስ ግን ሰው ራሱን በመግዛት በቅድስና እንዲኖር ይናገራል፡፡

" እኔ ግን እላችኋለሁ፥ ወደ ሴት ያየ ሁሉ የተመኛትም ያን ጊዜ በልቡ ከእርስዋ ጋር አመንዝሮአል።"
(የማቴዎስ ወንጌል 5:28)

የእንግሊዘኛው ትርጉም በደንብ ይገልጸዋል ፡፡
"28 But I say unto you, That whosoever looketh on a woman to lust after her hath committed adultery with her already in his heart."
(Matthew 5:28)

lust ማለት የራስ ያልሆነን ነገር መፈለግ ማለት ነው፡፡

እንግዲህ አንድ ወንድ አንድ ቆንጆ ሴት በመንገድ ስታልፍ ቢያይ ይሄ ተፈጥሮው ነው፡፡ነገርግን ካለፈች በኋላ ዞሮ በአይኑ ቢሸኛት ይሄ ችግር ነው፡፡

#General

💢💢 @PurityTube 💢💢
💢💢 @PurityTube 💢💢
👉ልባም ሴትን ማን ሊያገኛት ይችላል?👈

ብዙ ወንዶች እና ሴቶች ለራሳቸው እንደዚህ አይነት ወይም እንደዚያ አይነት ሚስት ወይም ባል እንፈልጋለን ብለው የራሳቸውን ዝርዝር አዘጋጅተው እሷን ወይም እሱን ፈለጋ🔦 ይወጣሉ ::

በዚህም ዝርዝር በአይን የሚታይ ውበት ወይም መልክ ብቻ ጠብቀው ይወጣሉ

👉ከዝርዝራቸው መሀከል ፊቷ/ቱ>ቀይ/ጠይም ፣ከኅዋላዋ > ተለቅ ያለ ፣ አንዳንዱ ደግሞ ቁመቱ ሰድስት ጫማ የሚሆን እንደሚፈልጉ ይናገራሉ ፡፡ይህ መፅሐፍ ቅዱሳዊ አይደለም

🔴በዚህ ምክንያት ብዙዎች ሴቶች እና ወንዶች ሳያገቡ ይቀራሉ ፡፡

ይህ ምድራዊ ወይም ጊዜያዊ ደስታን የሚሰጥ ጊዚያዊ ስሜት የሆነ ስጋዊ ሀሳብ ነው፡፡

💯፤መንፈሳዊ ወንድ ግን በመፅሃፍ ቅዱስ ስለሚስት ምን ይላል በማለት መፈለግ አለበት እንጂ በሴት ልጅ ውበት ብቻ ተታሎ አይሄድም

󾠬 ነገር ግን እግዚአብሔርን የምትፈራ መሆኑዋን ያረጋግጣል ። ለዚህም
(መጽሐፈ ምሳሌ 31:30)
"30፤ ውበት ሐሰት ነው፥ ደም ግባትም ከንቱ ነው፤ እግዚአብሔርን የምትፈራ ሴት ግን እርስዋ ትመሰገናለች።" ይላል....

#General

💢💢 @PurityTube 💢💢
💢💢 @PurityTube 💢💢
👉ወሲብና የፍቅር ጓደኝነት👈

🔵ዶክተር ብራንድት “Collegiate Challenge” በሚለው መጽሔት
በጻፉት መጣጥፍ ላይ በማማከር አገልግሎታቸው ውስጥ አንድ የተገነዘቡትን ነገር አስፍረዋል።

👉ይኸውም ብዙ ጊዜ ሁለት የፍቅር
ጓደኛሞች እሳቸው እኔ ጋ ምክር ፍለጋ ሲመጡ እንዲህ ይላሉ
«በመጀመሪያ ወሲብ ስንፈጽም እጅግ በጣም አስደሳች ነበር፤ ጥቂት
ቆይቼ ስለሆነው ነገር ሳስብ ስለራሴ መላቅጡ የጠፋና የንዴት ስሜት
ተሰማኝ። በጣም በጸጸት ተሞለሁ። ጥቂት ቆይቼ ስለ ፍቅር ጓደኛዬ
የተሰማኝ ስሜትም ደስ የማይልና ድብልቅልቅ ያለ ስሜት ሆነ። ከዛም
ጥቂት ቆይተን እርስ በርሳቸን መጨቃጨቅና አልፎ ተርፎም መጣላት
ጀመርን፤ በመጨረሻም ተጣላን፣ አሁን ጠላቶች ሆነናል። ብለው ይነግሩኛል። » በማለት ልምዳቸውን በመጽሔቱ ላይ አስፍረው ነበር።

ይህንን ዓይነት የሥነ ልቡና በሽታ የንጋት በሽታ ብዬዋለሁ።
ከእንቅልፋችን ብንን ብለን ከመኝታችን ስንነሳ ያ ፍቅርና መቀራረብ ዕውነት እንዳልሆነና በቦታውም እንደሌለ እንረዳለን።

🔴ከዛን ጊዜ ጀምሮ የወሲብ ግንኙነት ደስታን የሚፈጥርልን ነገር አይሆንም። መጨረሻው እንደጠበቅነው አይሆንም።

የሚሆነው ነገር ምንድነው
ሁለት የራሳቸውን ዕርካታ ብቻ ማዕከል ያደረጉ ተቃራኒ ጾታ ያላቸው ሰዎች
የየራሳቸውን ርካታ በመፈለግ ዓላማ ብቻ ተቀራርበው የሚከወነውን
ነገር ፈጽመው ተለያዩ ማለት ነው።
🔺 የሆነው ታሪክ ከዚህ ውጭ
አይደለም።
👉 እውነተኛ ፍቅርና ከልብ የሆነ መቀራረብ በአንድ አፍታና በለብለብ የሚገኝ ነገር አይደለም።

ስለዚህ በዚህ አካሄድ ሚዛናዊና
የተጣጣመ ፍለጋ ስለማይካሄድ ትርፉ የልብ ስብራትና ሃዘን አልፎም
ተርፎም ለመጥፎ የሥነልቡና ቀውስ መጋለጥ ይሆናል።


#General

💢💢 @PurityTube 💢💢
💢💢 @PurityTube 💢💢
2025/07/04 15:29:16
Back to Top
HTML Embed Code: