Telegram Web Link
አንዳንድ ክርስቲያኖች አማኝ ካልሆነ ሰው ጋር የፍቅር ግንኙነትን ለመጀመር ሲያስቡ

🙍‍♀" ምናልባት ወደ ጌታ ብስበውስ ማን ያውቃል !"
🙎‍♂ " ጌታ እኔን ተጠቅሞ ወደ ቤቱ ቢያመጣትስ ! " ይላሉ ።

🚫 የኔ ወንድም ከላይ እንደሚታየው ክሬን መኪና ከጥፋት አወጣለሁ ብሎ ወደ ጥፋት መግባት አለ !

መጀመሪያ ላይ ከዓለም እያወጣሽው እና ወደ ጌታ እየመለስሽው ሊመስልሽ ይችላል ፤ እውነቱ ግን መፅሀፍ ቀዱስ እንደሚናገረው አብ ካልሳበው በቀር ወደ ጌታ የሚመጣ አለመኖሩ ነው ። (ዩሐ 6፥44)

ወንጌልን በአፍ እና በተግባር መናገር የእኛ ስራ ነው ። ሰውን ወደ ጌታ ማምጣት ግን የእኛ ስራ አይደለም ።

👉 ሰው ወደ ጌታ መምጣት ያለበት ለመዳን ከጌታ ውጭ ሌላ መንገድ እንደሌለ ተረድቶ እንጂ ያፈቀረውን ሰው ደስ ለማሰኘት ከሆነ ሀይማኖት ቀየረ እንጂ አላመነም አልዳነም ።

" ከማያምኑ ጋር በማይመች አካሄድ አትጠመዱ፤ ጽድቅ ከዓመፅ ጋር ምን ተካፋይነት አለውና? ብርሃንም ከጨለማ ጋር ምን ኅብረት አለው?"
(2ኛ ቆሮ 6:14)

#single #couples

💢💢 @PurityTube 💢💢
💢💢 @PurityTube 💢💢
Forwarded from Purity Tube
We provide original & brand new materials for you! Shoes 👟 👞👠 clothes 👚👖👗 watches, bags & glasses 👜🕶👓 mobile phones & laptops 📱💻

U pay we provide the best

https://www.tg-me.com/joinchat-AAAAAE-nIGbcWKR82uSP9Q
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼Hello guys how are you doing? 🌼
🎇🎆NEW YEAR IS COMING🎇🎆

And we are ready to make you happy
with more gift packages.🎁🎁🎁🎁🛍🛍🛍🛍🛍🎈🎈🎈🎈
Place your orders before the time is late and surprise your family, friends, and loved ones for the new year.
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼


@Betaleo
@Benubehri

Our telegram channel @geezgiftdelivery

0915954967
0934494170
You order we deliver!
📌 ፖርኖግራፊ

ክፍል አንድ

👉 በአንድ ወቅት ‘ጉግል’ አለም ላይ አብዝተው ወሲብ (Sex) የሚለውን ቃል ፈልግልን ከሚሉኝ 5 ሐገራት መካከል እናንተ ኢትዮጵያውያን 🇪🇹 ዋነኞቹ ናችሁ ብሎን ነበር።

ይህ የሚያሳየን በሐገራችን እጅግ በጣም ብዙ ሰው የፖርኖግራፊ ተጠቃሚ ወይም በፖርኖግራፊ ሱስ የተጠቃ መሆኑን ነው።

ይህ ሱስ እንደሌሎች ሱሶች በግልጽ በሱሰኛው ላይ የማይታይ በመሆኑ እንዲሁም በማህበረሰባችን ውስጥ ስለ ጉዳዩ አሳሳቢነት በቂ መረጃ ስለሌለ የተጠቂዎች ቁጥር እጅግ ከፍተኛ እንደሆነ ይገመታል።

በቅድሚያ ግን ፖርኖግራፊ ምንድን ነው?

ፖርኖግራፊ ቃሉ የተገኘው‘πορνογραφία’ (pornographia) ከሚል የግሪክ ቃል ሲሆን በጥንት ጊዜ የቃሉ ትርጉም ስለ ሴተኛ አዳሪ ግልጽ በሆነ መንገድ የሚያትት ማናቸውም አይነት የስነ ፁህፍ ወይም የስነ ጥበብ ስራ ማለት ነው።

ነገር ግን በአሁኑ ዘመን ይህ ከጽሁፍ እና ስዕል ወደ ቪዲዮ ምስል ማደጉን እናያለን። ማንኛውም የወሲብን ስሜት የሚቀሰቅሱ ወሲባዊ ታሪኮች፣ ፊልሞች፤ ፎቶግራፎች እንዲሁም የቃላት ልውውጥ ፖርኖግራፊ ይባላል።

በአሁኑ ወቅት ሰዎች ፖርኖግራፊ ለማየት ለዚህ ከተዘጋጁ ልዩ ድህረ ገፆች ባሻገር ለዚህ አላማ ባልተዘጋጁ የማህበረሰብ መገናኛ ድህረ ገፆች ማለትም ቴሌግራም፣ ትዊተር፣ ፌስቡክ የመሳሰሉትን በመጠቀም ለፖርኖግራፊ ሱስ ተጋላጭ ይሆናሉ።

በዘመናችንም ፖርኖግራፊ በቀላሉ ሊገኝ የሚችል መሆኑም ሱሱ እንደወረሽኝ እንዲዛመት አድርጎታል።

ፖርኖግራፊ ሰዎችን በቀላሉ ሱሰኛ የማድረግ አቅም ያለው ሲሆን ሲጋራ፣ጫት እና የተለያዩ ዕፆች ሊያደርሱት ከሚችሉት ጉዳት በላይ ከባድ ችግር ሊያስከትል እንደሚችል በግልጽ ለማየት ተችሏል።

ይቀጥላል......



◅◉ @ethiotmrt ◉▻
💢💢 @PurityTube 💢💢
💢💢 @PurityTube 💢💢
​​❗️አስቸኳይ ጥሪ ለመላው ሕዝበ ክርስቲያን #share
የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን የሚያንቋሽሸው ፊልም ለእይታ እንዳይቀርብ ፊርማዎ ያስፈልገናል!

Habit የተባለ ፊልም በቅርቡ ለእይታ ሊቀረብ ነው። በፊልሙ ላየ ታዋቂዋ ተዋናይት የማይክል ጃክሰን ልጅ ፖሪስ ጃክሰን እንደ እየሱስ ክርስቶስ ሆና የምተውን መሆኖ ብቻ ሳይሆብ የምተውነው ደግሞ ግብረሰዶማዊቷ ኢየሱስን ሆና ነው ።

❗️ይህ አሳፋሪ ፊልም ለእይታ እንዳይበቃ በአሁኑ ሰዓት በአለም ላይ የፊርማ ማሰባሰብ እየተደረገ ሲሆን እርሶም ከስር በተቀመጠው ሊንክ ፊርማዎን ማኖር ባይችሉም በፀሎት በመቃወም በእግዙአብሔር ፊት በማቅረብ የበኩሎን አስተዋጽኦ ያበርክቱ።

A new blasphemous Hollywood film is predicted to come out soon depicting Jesus as a lesbian woman. The film “Habit” stars Paris Jackson who plays the role of “lesbian Jesus”.

Distributors haven’t picked it up as of yet, so let’s please spread awareness and wake people up to the Christianophobic garbage that is spread nowadays, but is somehow accepted and praised by society.

https://www.change.org/p/warner-brothers-prevent-the-distribution-of-the-film-habit?recruiter=1095770413&recruited_by_id=3dfa1350-a131-11ea-b2a6-bb05884a9cd7&utm_source=share_petition&utm_medium=copylink&utm_campaign=psf_combo_share_abi&utm_term=psf_combo_share_abi

Change.org
Sign the Petition
PREVENT THE DISTRIBUTION OF THE FILM “HABIT”

ይህ መልዕክት ለሁሉም ይድረስ ሼር ያድርጉ!
( የፌሎ እና የተለያዩ መንፈሳዊ ግሩፖች ላይ ሼር ያድርጉ )

💢💢 @PurityTube 💢💢
💢💢 @PurityTube 💢💢
ፖርኖግራፊ

ክፍል ሁለት

ጥናቶች ስለ ፖርኖግራፊ ምን ይላሉ?

◆ስለፖርኖግራፊ የተሰሩ ጥናቶች እንደሚያሳዩት ከሆነ

➝ብዙውን ጊዜ ሰዎች ለፖርኖግራፊ ተጋላጭ የሚሆኑት ከ11 ዓመታቸው ጀምሮ ነው።

➝በኢንተርኔት ውስጥ ከሚገኘው ወደ ግማሽ የሚሆነው መረጃ ፖርኖግራፊ ወይም ከፖርኖግራፊ ጋር ተያያዥ የሆነ መረጃ ነው።

➝በየቀኑ ኢንተርኔት ከሚጠቀሙ ሰዎች መካከል 25% የሚሆኑት ፖርኖግራፊ የሚመለከቱ ናቸው።

➝ከኢንተርኔት ላይ ከሚወርዱ ቪዲዮዎች መካከል 35% የሚሆነው ከፖርኖግራፊ ጋር የሚገናኙ ናቸው ።

➝34% የሚሆኑት የኢንተርኔት ተጠቃሚዎች ሳይፈልጉት በማስታወቂያዎች በራሳቸው ብቅ በሚሉ ሌሎች መረጃዎች ምክንያት ለፖርኖግራፊ ይጋለጣሉ።

➝አለም ላይ ካሉ ድህረ ገጾች መካከል 12% የሚሆነው የፖርኖግራፊ ገጾች ነው።

➝በአለማችን ላይ ከፍተኛ ገንዘብ ከሚያገኙ ሰዎች መካከል፣ በፖርኖግራፊ ኢንዱስትሪ ውስጥ ያሉ ሰዎች ይገኙበታል።

➝በሰሜን ኮሪያ በሐገሪቱ ውስጥ ፖርኖግራፊ ነክ የሆኑ ነገሮችን ማሰራጨትም ሆነ ማየት በሞት ያስቀጣል።

ይቀጥላል......

#share


◅◉ @ethiotmrt ◉▻
💢💢 @PurityTube 💢💢
💢💢 @PurityTube 💢💢
ፖርኖግራፊ

ክፍል ሶስት

ሰዎች ለምን ፖርኖግራፊ ይመለከታሉ?

ሰዎች ለምን ፖርኖግራፊን አዘውትረው ይመለከታሉ? “ችግሩን መለየት በራሱ የመፍትሄው አንድ አካል ነው” የሚለውን መርህ ይዘን ከብዙዎቹ ምክንያቶች ጥቂቶቹን ለመመልከት እንሞክር።

➊. ደስታን ፍለጋ

ለዚህ ጥያቄ ግልፅ የሆነውና የመጀመሪያው ምላሽ ሰዎች ማንኛውንም አይነት ፊልም እራሳቸውን ለማዝናናት እንደሚመለከቱት ሁሉ፣ ፖርኖግራፊንም የሚያነቃቃቸው እና ደስ የሚያሰኛቸው ነገር ከመፈለግ አንፃር ማየታቸው ነው። ከሰው መሰረታዊ ፍላጎቶች ውስጥ አንዱ ወሲብ እንደመሆኑ ሰዎች ይህንን ፍላጎት በተገቢው ሆነ ተገቢ ባልሆነ መልኩ ለማሟላት፣ በገሀዱ አለም እራሳቸው ያላደረጉትን ወይም የማያረጉትን ነገር ግን ስሜታቸው የሚፈልገውን ነገር አይተው በምናባቸው ተሳታፊ ለመሆን ፖርኖግራፊን ይመለከታሉ።


➋.በጭንቀትና ድብርት ምክንያት

ብዙውን ጊዜ በድብርት እና በጭንቀት ውስጥ ያሉ ሰዎች በፖርኖግራፊ ሱስ የሚጠቁ መሆናቸውን ጥናቶች ያሳያሉ። በአብዛኛው በፖርኖግራፊ ብቻ ሳይሆን በሌላም የዕፅ ሱሶች የሚያዙ ሰዎች ሱስ የሆነባቸውን ድርጊት ደጋግመው እንዲያረጉ የሚገፋፋቸው ወሲባዊን ደስታን ለማግኘት ያላቸው ፍላጎት ሳይሆን ውስጣቸው ከሚሰማቸው የስሜት መዋዥቅ ማለትም ጭንቀት፣ ድብርት፣ ሀዘን፣ ፍርሃት እና ሀፍረት ለማምለጥ ነው። ስለዚህ በሕይወታቸው ከባድ ጭንቀት ያለባቸውና ያልፈቱት አስጨናቂ ነገር በልባቸው ያለባቸው ሰዎች ሃዘናቸውን ለመርሳትና ጊዜያዊ ደስታ ለማግኘት ይጠቀሙበታል።

◦በስራ ቦታቸው ላይ ፖርኖግራፊ የሚመለከቱ ሰዎች ብዙውን ጊዜ ስራቸውን እየጠሉት የሚሰሩ መሆናቸው ለማወቅ ተችሏል። በትምህርት ቦታቸውም ቢሆን እንዲሁ።

➌. በብቸኝነት ምክንያት

ብዙውን ጊዜ ብቸኝነትን የሚያዘወትሩ እና በተለያየ ምክንያት ከሰዎች ጋር ህብረት ማድረግ የማይችሉ ሰዎች በዚህ ሱስ ሊጠቁ እንደሚችሉ ጥናቶች ያሳያሉ።

➍. በጓደኛ ግፊት ምክንያት

በአብዛኛው ታዳጊዎች እና ወጣቶች ስለ ወሲብ ምንነት ለማወቅ ካላቸው ጉጉት የተነሳ ወደ ፖርኖግራፊ ሊሳቡ ይችላሉ። ብዙዎች ወደሚያደርጉት ነገር ወይም ከዚያም ባለፈ በደፈናው ‘አታድርጉ!’ የሚባሉ ነገሮችን የመሞከር ዝንባሌ በወጣቶች ይስተዋላል። ታዳጊዎችና ወጣቶችም በጓደኞቻቸው ግፊት ወደዚህ ህይወት በቀላሉ ሊሳቡ ይችላሉ።

ለ10 አመት ያህል በፖርኖግራፊ ሱስ ውስጥ ያለች አንዲት እህት እንዴት ወደዚህ ሱስ እንደገባች እንዲህ ብላለች። “የዪኒቨርስቲ ተማሪ እያለሁ ዶርም ውስጥ ጓደኞቼ ተሰብስበው ፖርን ይመለከቱ ነበር። እኔ ግን ሁሌም እቃወማቸው ነበር። ከሆነ ጊዜ በኋላ ግን ሳላስበው እነሱን መቀላቀል ጀመርኩ። ከዚያ በኋላ ከነሱ የባስኩ ተመልካች ሆንኩኝ።”

ይቀጥላል......

#share

◅◉ @ethiotmrt ◉▻
💢💢 @PurityTube 💢💢
💢💢 @PurityTube 💢💢
የማስታወቂያ ሰዓት
👇👇
Forwarded from Purity Tube
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼Hello guys how are you doing? 🌼
🎇🎆NEW YEAR IS COMING🎇🎆

And we are ready to make you happy
with more gift packages.🎁🎁🎁🎁🛍🛍🛍🛍🛍🎈🎈🎈🎈
Place your orders before the time is late and surprise your family, friends, and loved ones for the new year.
🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼🌼


@Betaleo
@Benubehri

Our telegram channel @geezgiftdelivery

0915954967
0934494170
You order we deliver!
Forwarded from Purity Tube
We provide original & brand new materials for you! Shoes 👟 👞👠 clothes 👚👖👗 watches, bags & glasses 👜🕶👓 mobile phones & laptops 📱💻

U pay we provide the best

https://www.tg-me.com/joinchat-AAAAAE-nIGbcWKR82uSP9Q
Purity Tube pinned «​​❗️አስቸኳይ ጥሪ ለመላው ሕዝበ ክርስቲያን #share የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስን የሚያንቋሽሸው ፊልም ለእይታ እንዳይቀርብ ፊርማዎ ያስፈልገናል! Habit የተባለ ፊልም በቅርቡ ለእይታ ሊቀረብ ነው። በፊልሙ ላየ ታዋቂዋ ተዋናይት የማይክል ጃክሰን ልጅ ፖሪስ ጃክሰን እንደ እየሱስ ክርስቶስ ሆና የምተውን መሆኖ ብቻ ሳይሆብ የምተውነው ደግሞ ግብረሰዶማዊቷ ኢየሱስን ሆና ነው ። ❗️ይህ አሳፋሪ ፊልም…»
ፖርኖግራፊ

ክፍል አራት

ፖርኖግራፊ እንዴት ሱስ ይሆናል?

አንዳንድ ሰዎች ፖርኖግራፊን በተለያየ ምክንያት አንድ ጊዜ ወይም ከዚያ በላይ ከተመለከቱ በኋላ ሱሰኝነትን ያዳብራሉ። ''ሱስ ማለት ፈልገን የገባንበት ኋላ ግን እየጠላነውም ቢሆን የምናደርገው ነገር ነው። ማንኛውም ሱስ ሲጀምር በፍላጎት ሲሆን የሚቀጥለው ግን ያለፍላጎት ሊሆን ይችላል።ፖርኖግራፊ እንደማንኛውም አደንዛዥ ዕጽ ሰዎችን ሱሰኛ የማግረግ ከፍተኛ አቅም አለው።

ታዲያ ፖርኖግራፊ እንዴት ሱስ ሲሆን ይችላል?

“ብዙዎች ፖርኖግራፊ ሳያዩ መተኛት በማይችሉበት ሁኔታ ውስጥ ሆነው ሱስ አይሆንም ብሎ የመናገር ድፍረት አላቸው:: ነገር ግን ፖርኖግራፊ ከሌሎች ሱሶች ባልተናነሰ እንዲያውም በበለጠ መልኩ ወደ ሱስነት ያድጋል።

አንድ ሰው ፖርኖግራፊ ሲመለከት ደሙ ውስጥ የሚለቀቁ ቅመሞች (hormons) አሉ፤ እነዚህ ቅመሞች አንድ ሰው ኮኬንና ሄሮዊን የሚባሉትን አደዛዥ ዕፅ ሲጠቀም በደሙ ውስጥ የሚለቀቁ ቅመሞች ናቸው።

እኚህን ዕጾች ስንወስድ ደማችን ውስጥ የሚለቀቁት ቅመሞች ፖርኖግራፊ በምናይበት ጊዜ ከተለቀቁ ፖርኖግራፊ ሱስ አይሆንም ማለት አንችልም። ሱስ ለመባል የግድ በአፍ በኩል ወደ ውስጣችን መግባት የለበትም። አሁን ባለው መረጃ ‘Pornography is not like a drug, it is a drug’ (ፖርኖግራፊ አንደ አደንዛዥ ዕፅ ሳይሆን እራሱ አደንዛዥ ዕፅ ነው) እንዲያውም መልከ ብዙ ዕፅ ነው።

ሰው ፖርኖግራፊ ሲያይ ብዙ ዕፅ በአንድ ላይ እንደወሰደ ይቆጠራል። አንድ የኒዩሮ ሳይንቲስት (neuroscientist) ባለሙያ በፖርኖግራፊ ለመለከፍ የሚፈጅበትን ጊዜ ሲናገሩ አንድን ምስል ለግማሽ ሰከንድ ካየን በኋላ በሚቀጥሉት 5ና 10 ደቂቃ ውስጥ አንጎላችን ውስጥ መሰረታዊ የሆነ የቅርጽ ለውጥ (nerve restriction) ይፈጠራል። ይሄ አይነት ለውጥ ልክ አንድ ሰው
አደጋ ሲደርስበት የሚፈጠረውን የቅርጽ ለውጥ አይነት ነው።

በፖርኖግራፊ ለመለከፍ የሰከንድ 1/3ኛ ይበቃል እንደማለት ነው:: አስተውላችሁ ከሆነ ለሰከንድ ያየነው የፖርኖግራፊክ ምስል ለአመታት ከአይምሮአችን አይወጣም። ለምን ካላችሁ ‘epimerphine’ በተባለው ‘ሆርሞን’ ምክንያት እንዳይጠፋ ሆኖ ተቀርጿል:: ከዚህም የተነሳ ከአመታት በኋላ እንኳን አይረሳም።በዚህም ምክንያት ‘በቃ አይኔንም ስከድን ስተኛም በመንገድ ላይ ስሄድም የሚመጣብኝ እሱ ነው’ እያሉ በመንፈስ ጭንቀት የሚሰቃዩ ወጣቶች ቁጥራቸው ቀላል አይደለም።”

ይህ በቀላሉ የሚጀመሩ ነገሮች እንዴት ወደከባድ ሱስነት ሊለወጡ እንደሚችሉ አመላካች ነው።

ይቀጥላል.......

#share

◅◉ @ethiotmrt ◉▻
💢💢 @PurityTube 💢💢
💢💢 @PurityTube 💢💢
ፖርኖግራፊ

ክፍል አምስት

የፖርኖግራፊ ሱሰኝነት ምልክቶች

➀. ከፍተኛ ፍላጎት

አንድ ሰው ሱስ ደረጃ ላይ ከደረሰ ለፖርኖግራፊ ከፍተኛ ፍላጎት ይኖረዋል።በውስጡ የማያቋርጥ ፍላጎት ይቀጣጠላል። በማንኛውም ቦታ፣በማንኛውም ሁኔታ ና በማንኛውም ሰአት ፖርኖግራፊን መመልከት ይፈልጋል። ከዚህ በተጨማሪ የሚመለከትበትን ጊዜ እየጨመረ ይመጣል። በሳምንት ያይ የነበረ በቀን፤ በቀንም አንዴ ያይ የነበረው ሁለቴ ማየት ከጀመረ፣ በፖርኖግራፊም የሚያጠፋውም ጊዜ እያደገ ከመጣ፤ በሚመለከትበት ጊዜ የሚሰማው መነቃቃት እና ደስታ በሀፍረት፤ ጥፋተኝነት ስሜት እና ፀፀት ሲተካ ነገሩ ሱስ ደረጃ ላይ መድረሱን ይጠቁማል።

➁. ለማቆም አለመፈለግ እና አለመቻል

ሱስ ውስጥ የገባ አንድ ሰው ፖርኖግራፊ መመልከቱን ማቆም አይፈልግም። ሱስ እንደሆነና ችግር መሆኑን እንኳን መቀበል አይፈልግም። ይህም የሚሆነው ሱስ ውስጥ ስለገባና ከዛ ህይወት ቢወጣ ሌላ የሚያዝናናው ነገር ሊያገኝ እንደሚችል ስለማያምን ነው።

በሌላ መልኩ ደግሞ ለማቆም እየፈለጉ አለመቻልም የሱሰኝነት ማሳያ ነው። አንድ ወንድም የተናገረውን እንዋስ“እኔ ከፖርኖግራፊ ሕይወት ለመውጣት ከ100 ጊዜ በላይ ለራሴ ቃል ገብቼ ነበር፤ ነገር ግን ተመልሼ እዛው ሕይወት ውስጥ እገኛለው” ብሎአል። ይህ ንግግር የሚያሳየው ከባድ የሆነ ሱስ ውስጥ መግባቱን ሲሆን እየተጸየፍነውም የምናደርገው ነገር ሱስ እንደሆነብን ያሳያል።

➂. በሌላ ነገር ደስታ አለማግኘት

አንድ ሰው ወደዚህ ሱስ ውስጥ ከመግባቱ በፊት ያስደስቱት የነበሩትን ነገሮች ለምሳሌ ከቤተሰብና ከወዳጆች ጋር ጊዜ ማሳለፍ፣ ወደ ኃይማኖት ስፍራ መሄድ፣ ስፖርት መስራት፣ ፊልም ማየት፣ የእግር ጉዞ ማድረግ ወ.ዘ.ተ በመተው ደስታውን ሙሉ ለሙሉ በፖርኖግራፊ ላይ ካስቀመጠ ይህ ሰው የፖርኖግራፊ ሱስ ውስጥ እንደገባ ያሳያል።

➃. ከተጽኖው ጋር መቀጠል

በፖርኖግራፊ ሱስ የተጠቃ ሰው በሱሱ ምክንያት ብዙ ነገር እንዳጣ እያወቀ ህይወቱ ወደተሳሳተ አቅጣጫ እያመራ መሆኑን እየተረዳ በዛው ከቀጠለ ሱስ ደረጃ ላይ ለመድረሱን ያሳያል።

➄.ሚስጥራዊነት

በፖርኖግራፊ ሱስ ውስጥ ያለ ሰው ህይወቱን አጠገቡ ካሉ እና ከሚወዳቸው ሰዎች ሚስጥር ከማረጉ የተነሳ ድብቅ እና ሁለት ገፅታ ያለው ባይተዋር ሰው እንደሆነ ይሰማዋል። ሚስጥሩም እንዳይጋለጥ ያያቸውን ድህረ ገፆች በማጥፋት፤ የት እና ምን ያደርግ እንደነበር ቤተሰቡን እና ጓደኞቹን ሰዎችን ይዋሻል። የሚሰማውንም ሀፍረት ለመሸፈን በማስመሰል ህይወት ውስጥ ይዘፈቃል።

➅. ኃላፊነትን አለመወጣት

ብዙ ሰዓታትን በፖርኖግራፊ ከማሳለፍ የተነሳ በአግባቡ ስራን አለማከናወን፤ የቤተሰብ፤ የማህበራዊና መንፈሳዊ ሐላፊነቶችን መወጣት አለመቻል እና ገለልተኝነት ሱስ ደረጃ ላይ መደረሱን ያሳያል።

➆. የፀባይ መቀያየር

በሱስ ውስጥ ያሉ ሰዎች የሚፈልጉትን ባጡ ጊዜ በጣም ብስጩ ፤ ቁጡ እና በጥቂት ነገር የሚናደዱ ይሆናሉ። ከላይ የጠቀስናቸው ዋና የሚባሉት የሱስ ምልክቶች ሲሆን እነዚህ ምልክቶች የሚታዩባቸው ሰዎች ቆም ብለው ራሳቸውን አይተው ዕርዳታ ካልፈለጉ ለፖርኖግራፊ ሱስ መዘዞች ራሳቸውን ያጋልጣሉ።

ይቀጥላል........

#share

◅◉ @ethiotmrt ◉▻
💢💢 @PurityTube 💢💢
💢💢 @PurityTube 💢💢
◦ ፓርኖግራፊ

ክፍል ስድስት

ፖርኖግራፊ በመመልከት የሚከሰቱ ጉዳቶች

ፖርኖግራፊ መመልከት የሚያስከትለው እጅግ በጣም ብዙ መዘዞች አሉት። ጉዳቶቹም፦ መንፈሳዊ፣ስነ-ልቦናዊና ማህበራዊ ናቸው። እስኪ ጥቂቶቹን እንመልከት

➊. ድብርት እና ጭንቅት

ፖርኖግራፊ ውስጥ የገባ ሰው ያለበት ሕይወት ትክክል እንዳልሆነ ያውቃል። ስለዚህ ከባድ የሆነ ጭንቀት ይሰማዋል። ብዙ ሰዎች በዚህ ምክንያት ሀፍረት ስለሚሰማቸው በራስ መተማመናቸውን ያጣሉ። ስለዚህ በከባድ የድብርት ስሜት ውስጥ ሆነው ራሳቸውን ከሰው ያገላሉ።

➋. አቅምን ይገላል

በዚህ ሱስ የተያዘ ሰው በቀን ውስጥ በትንሹ 3 ሰዓት ፖርኖግራፊ በመመልከት ሊያጠፋ ይችላል። ምን ያህል የከበረ ጊዜውን እንደሚያጠፋም አስተውሉ! ከዚህ በተጨማሪ በዚህ ሱስ መጠቃት ኃላፊነትን ቸል ወደማለት ያደርሳል። የፈጠራ ችሎታን ይቀንሳል።

በፖርኖግራፊ ምክንያት የአፈጻጸም ብቃታቸው ወርዶ ከስራና ከትምህርት የተባረሩ ሰዎች ጥቂቶች አይደሉም። አስደናቂ ዕምቅ እና ችሎታ ያላቸው ስንቶችን በፖርኖግራፊ ምክንያት አጥተናቸዋል?

➌. ላልተፈለገ ተግባር ያጋልጣል

ጥናቶች እንደሚያሳዩት ከሆነ ሕጻናትን ከደፈሩ ሰዎች ብዙዎቹ በፖርኖግራፊ ሱስ የተጠቁ ናቸው። ከዚህ በተጨማሪ ፖርኖግራፊ የሚመለከቱ ሰዎች ከማይመለከቱት ጋር ሲነጻጸሩ በ400% ሴተኛ አዳሪዎች ጋር የመሄድ ዝንባሌ አላቸው። የተመሳሳይ ጾታ ፖርኖግራፊ በመመልከታቸው ብቻ ወደ ግብረ ሰዶማዊነት የገቡ ሰዎች እንዳሉም ለማየት ችያለው።

➍. የተሳሳተ አመለካከት

በሱሱ የተጠቁ ሰዎች ስለራሳቸው የተሳሳተ አመለካከት ይኖራቸዋል። ‘እኔ አልጠቅምም፤ እኔ ከንቱ ሰው ነኝ፤ እኔ ፈጣሪ ይጠላኛል፤ እኔ ከሰው አንሳለው፤ መቼም ከዚህ ህይወት መውጣት ስለማልችል ስኬታማ ትዳር አይኖረኝም፤ የሚሉ አሉታዊና ተስፋ የመቁረጥ አመለካከቶችን ያዳብራሉ።

እንዲህ አይነቱ ለራስ የሚሰጥ የወረደ ግምት በቶሎ ካልተቀጨ ከባድ ወደሆነ አዕምሮአዊ እና ስነ ልቦናዊ በሽታ ያመራል። ለራሱ የተሳሳተ አመለካከት ያለው ሰው ስለ ሰዎች ትክክለኛ አመለካከት ሊኖረውም አይችልም።

ሌላው የተሳሳተ አመለካከት የሚሰጠው ለተቃራኒ ጾታ ነው። እስከ ዛሬ በዚህ ጉዳይ ላይ ያማከርኳቸው ወንድሞችና እህቶች ሁሉም ለማለት በሚያስደፍረኝ ሁኔታ ለተቃራኒ ጾታ ዝቅ ያለ አመለካከት እንዳላቸው ገልጸውልኛል። ብዙውን ጊዜ በፖርኖግራፊ ምስሎች ላይ ሴቶች የወንዶች የወሲብ ፍላጎት አገልጋይ ተደርገው የተሳሉ ሲሆን ፖርኖግራፊ የሚመለከቱ ወንዶችም ልክ እንደዛው ሴቶቹን እንደሚመልከቱ ነግረውኛል። ሴቶች ደግሞ ሁሉም ወንዶች ጨካኝና ለስሜታቸው ብቻ የሚኖሩ እንደሆኑ እንዲያስቡ እንዳደረጋቸው አውርተውኛል። በዚህ የተሳሳተ አመለካከት ምክንያት ጤናማ የሆነ የፍቅር ህይወት ለመጀመር የተቸገሩ ጥቂቶች አይደሉም።

➎. ትዳርን ይበጠብጣል

አንድ ባለትዳር እንዲህ ሲል ተናግሯል፣ "እኔ በፖርኖግራፊ ሱስ ከተጠቃሁ አንድ ዓመት ሆኖኛል። በዚህ ጊዜ ውስጥ ብዙ ችግር ገጥሞኛል። በስራ ሰአቴ ላይ ረጅም ጊዜ የማጠፋው ፖርኖግራፊ በመመልከትና ግለ ወሲብ በመፈጸም በመሆኑ እቤት ስገባ ከባለቤቴ ጋር ግንኙነት የማድረግ ፍላጎት የለኝም።” የዚህ ሰው ችግር የብዙዎችም ነው። ‘ፖርኖግራፊ’ የሚመለከቱ
ሰዎች በትዳራቸው ያላቸውን እርካታ ያጡታል። የግንኙነት መቃወስም (Sexual Dysfunction) ሊያጋጥማቸው ይችላል። ይህ ደግሞ ወደ ፍቺ እና የቤተሰብ መበተን እስከማምራት ይደርሳል።

ይቀጥላል........

#share


◅◉ @ethiotmrt ◉▻
💢💢 @PurityTube 💢💢
💢💢 @PurityTube 💢💢
ፖርኖግራፊ

ክፍል ሰባት

ከፖርኖግራፊ ሱስ እንዴት መውጣት ይቻላል?

ብዙ ወጣቶች በዚህ ሱስ ውስጥ ቢኖሩም ይህን ሱስ አንደ ችግር ለሚቆጥሩት እና ለመታገል ፈቃደኛ ለሆኑት ሰዎች ከዚህ ችግር መውጣት የማይቻል ነገር አይደለም።

በዚህ ችግር ውስጥ ያላችሁ ወዳጆቼ ምን ብታደርጉ ከዚህ ሱስ መላቀቅ እንደምትችሉ እስኪ በጥቂቱ እንመልከት።

➀ ሀሳብን በሀሳብ ተዋጉ

የፖርኖግራፊ ኃጢያት ስርወ-መሰረቱ ሀሳብ አንደመሆኑ ሀሳብን ልንዋጋው የምንችለው በሌላ ሀሳብ በመተካት ብቻ ነው። አዕምሮእችንን በመልካም ሀሳብ ለመሙላት ደግሞ ዕለት ዕለት ልንሆናቸው ወደምንፈልጋቸው አላማዎቻችን ማደግ የሚያስችሉንን ነገሮች ማድረግ ያስፈልጋል። ያን ጊዜ መልካም ሀሳቦችን በአእምሮአችን መሙላት ስንጀምር መጥፎ ሀሳቦች ከእኛ እየራቁ ይመጣሉ።

➁ ለምን እንደምታዩ እወቁ

አንዲት እህት ከ 4ዓመት በፊት አስገድዶ መደፈር ደርሶባት ነበር። ሌሊት ስትተኛ ያለፈችበት እየታወሳት ትጨነቅ ነበር። ከዚህ ስቃይ ማምለጫ ያደረገችው ፖርኖግራፊ መመልከትን ነበር። ለዚህች እህት ፖርኖግራፊ መመልከት የችግሩ መገለጫ እንጂ ዋናው ችግሩ እንዳልነበር ነው። ይህች እህት ከሰዎች ጋር ቁጭ ብላ ስታወራ አሰቃቂ ከሆነ ጉዳት በኋላ ሰዎች የሚኖራቸው የስነ ልቦና መቃወስ /Post Traumatic Stress Disorder/ እንዳለባት ማረጋገጥ ተችሏል።

ፖርኖግራፊ መመልከት ሰዎች በህይወታቸው ያልፈቱት የውስጣዊ ችግር መገለጫ ሊሆን ይችላል። ጊዜ ወስዳችሁ በሕይወታችሁ የሚያስጨንቃችሁን ነገር፤ ያለፋችሁበትን ታሪክ ለመለየት ሞክሩ። ችግሩን በውስጣችንን ተጭኖ ለማስቀረት (repress) ለማድረግ መሞከር ወደ ባሰ ችግር ይወስዳልና ችግሩን ተጋፍጣችሁ መፍትሄ ለመስጠት ሞክሩ።

➂ ቀስቃሽ ነገሮችን ለዩ

ከዚህ በታች ያሉትን ጥያቄዎች ለራሳችሁ መልሱ።
◉በብዛት ፖርኖግራፊ የምታዩት የትኛው ሰአት ላይ ነው?
◉ለመጨረሻ ጊዜ ፖርኖግራፊ ያያችሁት መቼ ነው?
◉ፖርኖግራፊ ከመመልከታችሁ በፊት ምን አይነት ስሜት (mood) ላይ ነበራችሁ?
◉ቀስቃሽ ነገሮቻችሁ ምንድን ናቸው? ስሜትን የሚያነሳሱ የሙዚቃ ክሊፖች ወይንስ ፊልሞች?

አንዲት እህቴ ፖርኖግራፊ ይዘት ያላቸውን ነገሮች የምታገኘው ከፌስ ቡክ ላይ ነበር። ከዚህ ህይወትም ሙሉ ለሙሉ መውጣቷን እስክታረጋግጥ ድረስ ፌስቡክ መጠቀሟን አቆመች።

👉ከዚህ በፊት የሰበሰባችሁት ፊልምና ማንኛውም ነገር አሁኑኑ አስወግዱ።
👉ለዚህ ዓላማ የምታገኙአቸው ሰዎች ካሉ ግንኙነታችሁን አሁኑኑ አቋርጡ።

ኢንተርኔት መጠቀም ማቆም ካለባችሁ አሁኑኑ አድርጉት። የግድ መጠቀም ካለባችሁም ሰዎች በተሰበሰቡበት ቦታ ተጠቀሙ። ወይም እንደ ‘Covenant eyes’* ወይም ‘X3watch’* ያሉ ፕሮግራሞችን ተጠቀሙ ከሕይወታችሁ የሚበልጥ ምንም ነገር የለምና!

ወደ ፖርኖግራፊ የሚገፋፋችሁ ጭንቀት ከሆነ ከጭንቀት መውጫ ሌሎች መንገዶችን ፍጠሩ። ስሙን ሳልጠቅስ ታሪኩን እንዳጋራ የፈቀደልኝን የአንድ ወንድም ሕይወት ላንሳ፤ “ከሚስቴ ጋር ባለን ህይወት ደስተኛ አይደለሁም። እቤት መሄዴን ሳስብ ጭንቀት ይወረኛል። መደበሪያዬ ፖርኖግራፊ ሆኖ ለዘመናት ኖርኩኝ። የትዳሬን ችግር መፍታቴ ከፖርኖግራፊ ሱስ አስመለጠኝ”። የእናንተን ቀስቃሽ ነገርን ጻፉት።

ይቀጥላል....

#share

◅◉ @ethiotmrt ◉▻
💢💢 @PurityTube 💢💢
💢💢 @PurityTube 💢💢
📌 የወንዶች ፀጉርና ፂም ማሳደግያ Minoxidil kirkland

በቀን 2 ጊዜ ለሚጠቀሙ ሰዎች በ 1 ወር ውስጥ ውጤት የሚያሳይ

ከቆዳችን ስር የሚገኘውን ፀጉር የሚያበቅል

📌 በ"FDA" እውቅናና ማረጋገጫ የተሰጠው ደግሞም በebay ፣ amazon እና በመሳሰሉት የ online መገበያያዎች ላይ "5" ★★★★★ ኮኮብ ያገኘ ነው

✉️ከአዲስአበባ ውጪ ላላችሁ እንልካለን

For every one who have hair loss issues and want to grow beard fast .....
We have minoxidle 5% only for man

please google it for more info or look it up on youtube

@AgapeLoved
📞 0953928523
Forwarded from Purity Tube
" የኔ ቆንጆ " በላት

እኛ ሀገር አንድ ነገር የግል እስኪሆን ድረስ ማንቆለጳጰስ ማሸርገድ ከዛ የራስ ሲሆን ደግሞ ማቃለል እና ትኩረት አለመስጠት የተለመደ ነው ።

ይህ ልማድ ከትዳር በፊት ባለ የፍቅረኞች ህይወት እና ከትዳር በኋላ ባለ የባልና ሚስት አኗኗር በግልፅ ይታያል ።

ድሮ ሳይጋቡ "የኔ ፍቅር ፣ የኔ ማር ፣ የኔ ቆንጆ ፣ ወለላዬ ..... " ሲል የኖረ ወንድ በሰርጋቸው ማግስት ሳያቆላምጥ በሙሉ ስሟ መጥራት ይጀምራል ።

ሴቶች በባህሪያቸው " ቆንጆነታቸው " አሁንም አሁንም በባላቸው እንዲነገራቸው ይፈልጋሉ ። ይህ ለትዳር መቆም ምሰሶ ነው ።

ወንዶች ደግሞ "ፍቅሬን በተግባር ማሳየት እንጂ ስለፍፍ መዋል አለብኝ ? " ይላሉ ። አዎ ወንድሜ አለብህ !

በእርግጥ ፍቅር በዋናነት ድርጊት ነው ነገር ግን የፍቅር ቃላት ደግሞ የፍቅር ማጌጫዎች ናቸው ። እነዚህን የፍቅር ቃላት መጠቀም ባቆምክ ጊዜ ወደ ሚስትህ አእምሮ የሚመጡ የተለያዩ ለትዳር መሰናክል የሚሆኑ ድምፆች አሉ ። ለምሳሌ

" ሚስቱ ስለሆንኩ የትም አትሄድም ብሎ ነው ጣል ጣል ያረገኝ ? "

" ልጅ ከወለድኩ በኋላ ስለወፈርኩ አስጠላሁት ይሆን " ..... የመሳሰሉት

በእርግጥ ያንተ ምክንያቶች እነዚህ አይሆኑም ( ከሆኑ በእውነት ጥሩ ሰው አይደለህም ) ።

ነገርግን ምክንያትህ ምንም ይሁን ምንም የፍቅር ቃላት አለመጠቀምህ ለእነዚህ ድምፆች ምክንያት ከሆነ ትዳርህን ከምታሻክር ሚስትህን "የኔ ቆንጆ " በላት ። ቀላል በሆኑ ቃላት ትዳርህን የደስታ ማድረግ ትችላለህ ።

#married

💢💢 @PurityTube 💢💢
💢💢 @PurityTube 💢💢
ፖርኖግራፊ

ክፍል ስምንት

➃ በጽናት ታገሉ!

ከዚህ ሱስ መውጣት ሂደት ነው። ለማቆም ከወሰናችሁ በኋላ እንኳን መላልሳችሁ ልትወድቁ ወይም እስከ ዛሬ ያያችሁት ምስል ሀሳባችሁ ላይ እየመጣ ልትጨነቁ ትችላላችሁ። ይሄ ማለት ከዚህ ህይወት አልተላቀቃችሁም ማለት አይደለም። ቡና ለረጅም ጊዜ ጠዋት መጠጣት የለመደ ሰው እንደሚያዛጋው ማለት ነው እንጂ!

አዕምሮአችን ወደ ቀደመው ቦታ እስኪመለስ ከማንኛውም ሱስ ስንወጣ የምናልፍበት ጤናማ ሂደት ነው። ዋናው በጦርነቱ ተሸንፎ እጅ አለመስጠት ነው። ፀንታችሁ ከታገላችሁና የሚፈልገውን እስከነሳችሁት ድረስ ሱሱ በእናንተ ላይ ያለውን አቅም ያጣል። ከመገባችሁት ግን ያድግና ይውጣችኋል።

➄ ስሜቶቻችሁን ተቆጣጣሩ

ፖርኖግራፊ ማየት ሶስት ደረጃዎች አሉት። እነሱም ስሜት /Emotion/፣ ሐሳብ/Thought/ እና ተግባር/Action/ ናቸው።

ስሜት የምንለው የመጀመሪያው ደረጃ ጭንቀት፣ መከፋት ወይንም ፖርኖግራፊ የማየት ፍላጎት ሊሆን ይችላል። ይህን ተከትሎ ነው ፖርኖግራፊ የማየት ሐሳብ የሚመጣው። መጨረሻ ላይ ሁሉም ወደ ተግባር ይቀየራል። ስለዚህ ራሳችሁን መቆጣጠር የምትችሉት በሃሳብ ደረጃ ሳለ ሳይሆን ገና ስሜት ሲሰማችሁ ነው። አንዲት እህቴ ‘እንዲህ አይነት ስሜት ሲሰማኝ ከቤት ወጥቼ ሙዚቃ/መዝሙር እየሰማሁ የእግር ጉዞ ማድረግ እጀምራለሁ፤ ይህም በጣም ጠቅሞኛል’ ስትል ልምዷን አጋርታኛለች። አንድ ወንድሜ ደግሞ እንዲህ አይነት ስሜት ሲሰማው ስፖርት እንደሚሰራ አጫውቶኛል።

ይህ ስሜት ሲሰማችሁ ምን ብታደርጉ ጥሩ ነው? 3 ነገሮችን ጻፉና የሚስማማችሁን ነገር አድርጉ።

➅ ብቸኝነትን አስወግዱ

ለረጅም ሰአት ብቻችሁን ላለመሆንና ጊዜያችሁን ከቤተሰብና ከወዳጆቻችሁ ጋር ለማሳለፍ ሞክሩ። በተቻለ መጠን ቀናችሁን በተሻለና ትርጉም ሊሰጥ በሚችል ነገር ላይ አውሉት። እንደ ስፖርት መስራት መጽሐፍትን ማንበብ ቤተክርስቲያን መሄድ እና ራስን ማዝናናት ያሉ ልምዶችን አዳብሩ። ማድረግ የምትፈልጓቸውን ነገሮች ፃፏቸው።

➆ ተስፋ አትቁረጡ

ከዚህ ህይወት ለመውጣት በምታደርጉት ጥረት ውስጥ መውደቅና መነሳት ሊያጋጥማችሁ ይችላል።ተስፋ ሳትቆርጡ ከስህተታችሁ ተምራችሁ እንደ አዲስ በብሩህ ተስፋ ነገን አሻግራችሁ ተመልክቱ።

➇ ግልጽ ሁኑ

በዚህ ሱስ ውስጥ የነበሩና ከዚህ ችግር ለመውጣት የረዳቸውን ነገር ለማናገር እንዲሁም ለማንበብ ስሞክር በሁሉም ውስጥ ያገኘሁት 2 ሀሳብ ነው። አንደኛው የፈጣሪ እርዳታ ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ በችግሩ ላይ በግልጽነት ማውራቴ የሚል ነበር። ብዙ ሰው በጉዳዩ ላይ ማውራት ስለሚያሳፍረው እርዳታም ለማግኘት ይቸገራል።

ከዚህ ህይወት ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ለመውጣት ከፈለጋችሁ ሊረዳችሁ ለሚችል ለአንድ ሰው በግልጽ ችግራችሁን መናገር ይኖርባችኋል። በመናገራችሁ ብቻ፤ ሚስጥር ያደረጋችሁትን ነገር ወደ ብርሃን በማውጣታችሁ ይህ ሱስ በእናንተ ላይ ያለውን አቅም ያጣል። ስትደክሙ የሚያማክራችሁ፤ መቆማችሁን ሁሌ
የሚከታተል አንድ ሰው ማድረጋችሁ ፀንታችሁ እንድትቆሙ ብርታት ይሰጣችኋል።

ይህንን ምክር ሰምቶ የተቀበለ አንድ ወንድም ችግሩንለጓደኛው አካፈለው። መጥፎ ስሜት ሲሰማው ይደውልና 'እባክህን እየተቸገርኩ ስለሆነ ጸልይልኝ ጊዜ እናሳልፍ' ይለዋል። ልታማክሯቸው የምትችሉ ሶስት ሰዎችን ጻፉና በማስተዋል ታግዛችሁ አንዱን ሞረጡ።



◅◉ @ethiotmrt ◉▻
💢💢 @PurityTube 💢💢
💢💢 @PurityTube 💢💢
🛑 እጅግ ጠቃሚ መረጃ ነው

ፆታዊና ወሲባዊ ጥቃት ለደረሰባቸው ሰዎች (ልጆችን ጨምሮ ) ጊዜያዊ ማረፊያ የሚሰጡ ተቋማት ስም እና አድራሻ 👆👆

📌እባክዎ #ሼር በማድረግ ሀላፊነትዎን ይወጡ ።

💢💢 @PurityTube 💢💢
💢💢 @PurityTube 💢💢
📌 የወንዶች ፀጉርና ፂም ማሳደግያ Minoxidil kirkland
(Foam & liquid )
በቀን 2 ጊዜ ለሚጠቀሙ ሰዎች በ 1 ወር ውስጥ ውጤት የሚያሳይ

ከቆዳችን ስር የሚገኘውን ፀጉር የሚያበቅል

📌 በ"FDA" እውቅናና ማረጋገጫ የተሰጠው ደግሞም በebay ፣ amazon እና በመሳሰሉት የ online መገበያያዎች ላይ "5" ★★★★★ ኮኮብ ያገኘ ነው

✉️ከአዲስአበባ ውጪ ላላችሁ እንልካለን

For every one who have hair loss issues and want to grow beard fast .....
We have minoxidle 5% only for man

please google it for more info or look it up on youtube

@AgapeLoved
📞 0953928523
2025/07/08 02:56:14
Back to Top
HTML Embed Code: