❓❓ቅድመ ጋብቻ ወሲብ❓❓
(Pre Marital Sex )
🤔ታዲያ የት እንጀምር❓
🔸 እንደባልና እንደአባት ከሰዎች ጋራ ጥሩ ግንኙነቶችን መፍጠር ከፈለግህ መሥራት ልትጀምርበት የሚገባህ ጥሩ ስፍራ ቢኖር አንተው ራስህ ጋ ነው❗️
💢 ምስጢሩ ትክክለኛ ሚስት ለማግኘት ወይንም ትክክለኛ የሆኑ ልጆችን ለማፍራት ቆርጦ መነሳት አይደለም፡፡
🗝 ይልቁንም ቁልፉ ከራስህ መጀመር ነው፡፡
📌 አንተን ጥሩ ባልና አባት ሊያደርግህ የሚችል በጣም ወሳኝ የሆነ ግንኙነት ቢኖር ከእግዚአብሔር ጋራ ያለው ግንኙነትህ ነው፡፡
👉እግዚአብሔር የወሲብ፣ የፍቅርና የግንኙነቶች ሁሉ ፈጣሪ ነው፡፡ እንድንደሰትባቸው ብሎ የፈጠረልን ነገሮች ናቸው፡፡
👉 ስለአጠቃቀማቸው እርሱ ያወጣልንን ስርዓት ከተከተልን በሚገባ እንደሰትባቸዋለን፡፡
አንድ የተረዳሁት ነገር ቢኖር እግዚአብሔር የሞራል አስከባሪ በመሆን ‹‹ይህን አድርግ፣ ይህን አታድርግ!›› እያለ አለቃ ወይንም መሪ መሆኑን ለማሳየት የሚሞክር አለመሆኑን ነው፡፡
ለምሳሌ ያህል ‹‹ከጋብቻ በፊት ወሲብን አትፈጽም! ›› ሲል ለራሴ ጥቅም ብሎ ነው፡፡
👌 እርሱ ራሱ ስለሰራኝ ለእኔ የተሻለውንና የተሟላ ደስታ ሊሠጠኝ የሚችለውን ነገር ጠንቅቆ ያውቃል፡፡
🔅 እግዚአብሔርን በግል እንዴት
ማወቅ ይቻላል❓
መጽሐፍ ቅዱስ ሲናገር ኢየሱስ ክርስቶስ ራሱ እግዚአብሔር ሆኖ ሳለ በሰው አምሳል ወደ ምድር በመምጣት የእግዚአብሔርን ማንነት በግልጽ ያሳየን የእግዚአብሔር ትክክለኛ አምሳያ ነው፡፡ ባጭሩ የእግዚአብሔርን ማንነት በግልጽ አሳይቶናል፡፡
🤔ታዲያ እንዴት ነው ከርሱ ጋራ ህብረትን መፍጠር የምንችለው❓
👉እግዚአብሔር ለእኛ እውነተኛ ፍቅር ስላለው እንድናውቀው ይፈልጋል፡፡ ይሁንና ይህ እንዳይሆን ግን አንድ እንቅፋት አለ፡፡ ይኸውም ኀጢአታችን ( ማለትም ሰውንና እግዚአብሔርን በፍጹም ልብ መውደድ አለመቻላችን) በእግዚአብሔርና በእኛ መካከል ጣልቃ በመግባት ህብረትን እንዳናደርግ እንቅፋትን ፈጥሮብናል፡፡
🙏ስለሆነም እየሱስ የእኛን ሁሉ ሐጢአት በጫንቃው ላይ በመሸከም በመስቀል ላይ በፈቃዱ ሞቶልናል፡፡
👉 ይህን ያደረገው እኛ ፍጹም ይቅር እንድንባልና በእግዚአብሔርም ተቀባይነትን እንዲኖረን ነው፡፡
💢 በእኛ ፈንታ በመደብደብ በመዋረድ በመገረፍና በመሰቀል ታላቅን ዋጋ ከፍሎልናል፡፡ በሶስተኛውም ቀን ከሙታን ተነስቶአል፡፡
💢 ስለዚህ ዛሬ ለዚህ ለከፈለልን ታላቅ መስዋዕት እርሱን ወደ ህይወታችን እንዲገባ በመጋበዝ ምላሽ እንድንሰጠው ይጠብቅብናል፡፡
📌ኢየሱስ ክርስቶስ በምድር ላይ ኖረው ካለፉ ወንዶች ሁሉ የላቀ ስብዕና የነበረው ወንድ ነበር፡፡
ሰዎች ግን ይህኛውን የማንነቱን ክፍል ብዙም ትኩረት አይሰጡትም፣ ግን በጣም እውነት የሆነ ነገር ነው፡፡
🙏ስለዚህ ወደ ህይወትህ እንዲገባ ስትጋብዘው በምድር ላይ ከኖሩ ከማናቸውም ሰዎች ይልቅ ሰው መሆን ምን ማለት መሆኑን ጠንቅቆ የሚያውቀውን ሰው ነው እየጋበዝክ ያለኸው ❗️
♦️ ስለዚህ እውነተኛ ሰው እንድትሆን ይረዳሃል ፤ ይሁንና የሆሊውድ ፊልሞች የሚያሳዩንን ዓይነት ሰው ሳይሆን በህይወቱ ፍጹም የተሳካለትና ለሌሎችም ሕይወት ትርጉምን በመሥጠት በጣም ውድ የሆነ ህይወትን የሚኖር ዓይነት ሰው ያደርግሀል!
እውነተኛው ወንድ
ምን ይመስል ይሆን ❓
👌እውነተኛ ወንድ እንደተኩላ ዓይነት ሰው አይደለም፤ የራሱ ፍላጎት መርካቱን ብቻ አያስብም፡፡
📌ይልቁንም እንደ እረኛ ለሌሎች ደህንነት የሚያስብ ዐይነት ባህርይ ያለው ሰው ነው፡፡
📌ከክርስቶስ ጋራ ያለህ ህብረት ባደገ መጠን እውነተኛ ሰው ወይንም እውነተኛ ወንድ ማለት ምን ማለት እንደሆነ እየተረዳህ ትመጣለህ፡፡
ክርስቶስም ስለሴቶች ያለህን አስተሣሰብና ለእነርሱ የምታደርውን ክብካቤ ይለውጠዋል፡፡
👉 ለዘለዓለም የሚዘልቅ ግንኙነትን ከክርስቶስ ጋራ መመስረት ትችላለህ፡፡ ‹‹ በርሱ ሚያምን ሁሉ የዘላለም ህይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስኪሰጥ ድረስ ዓለምን እንዲሁ ወዶአልና፡፡››ዮሐ 3፡16 እምነት ማለት መተማመን ማለት ነው፡፡
📌 ስላንተ በተከፈለው በክርስቶስ መስዋዕት ላይ ስትተማመን የዘላለም ህይወትን ታገኛለህ፤ይህም ማለት ከእግዚአብሔር ጋራ አሁን የሚጀምርና በህይወት ዘመንህ ሁሉ የምትቀጥለው ግንኙነት ማለት ነው፡፡
💢 አሁን በልብህ እንዲህ ዓይነቱን ግንኙነት ለመጀመር ፍላጎቱ ካለህ ቀጥሎ የምታገኘውን ሀሳብ በሚመችህ መንገድ ለእግዚአብሔር ከልብህ በመናገር ግንኙነቱን መጀመር ትችላለህ፡፡
🗣 ‹‹ ውድ እግዚአብሔር አምላክ ሆይ! በሐጢአቶቼ አንተን እንደበደልኩ አውቃለሁ፡፡ ኃጢአቶቼን ሁሉ ተሸክመህ በመስቀል ላይ ስለተሰቀልክልኝም አመሰግናለሁ፡፡ይቅርታህን ለመቀበል እፈልጋለሁ፡፡ካንተ ጋራ የጠበቀ ግንኙነትን መመስረት እፈልጋለሁ፡፡ ጌታዬና አዳኜ ሆነህ ወደሕይወቴ እንድትገባ እለምንሀለሁ፡፡ አንተ የምትፈልገውን ዓይነት ሰው እንድሆንልህ እባክህን እርዳኝ፡፡ አሜን!››
📌ተጨማሪ ምክርና ርዳታን ለማግኘትና በእግዚአብሔር ዕውቀት ለማደግ ከመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እንደ ማቴዎስ፣ ማርቆስ ፣ ሉቃስና ዮሓንስ የመሳሰሉትን ወንጌላት እንድታነብ አበረታታሀለሁ፡፡
ሰላም ❗️
▪️▪️▪️▪️ አለቀ▪️▪️▪️▪️
#single #couples
💢💢 @Appeal4purity 💢💢

🔵🔵ክርስቲያን እና ፖርኖግራፊ🔵🔵
ማንኛውም ክርስቲያን እግዚአብሄር ኃጢያትን ጨምሮ ማናቸውንም ነገር ማሸነፍ እንደሚችል፤ ሁሉን ቻይ እንደሆነ እና ክርስቶስም ማናቸውንም ፈተና ልንቋቋም የምንችልበት ፀጋ እንደሰጠን ቢያምንም በፖርኖግራፊ ሱስ እየታገለ ያለ ክርስቲያን ግን ይህን እውነት መጠራጠር ይጀምራል።
👉ከብዙ ፀሎት፣ ለእግዚአብሔር እና ለራስ ከሚደረግ ከብዙ ቃለ መኃላ፤ ጥረት እና ትግል በኋላ ራሱን በሱስ ውስጥ መልሶ ወድቆ ሊያገኘው ይችላል።
💢በእርግጥ እግዚአብሔር አለ! በእርግጥ እግዚአብሔር ሁሉን ቻይ ነው!
🔶ሆኖም ግን እኛ እንደምንፈልገው ነፃ መውጣት በአንዴ ላይሆን ይችላል።
👉በዚህ ሱስም ውስጥ ያሉ ክርስቲያኖችም ከዚህ አንፃር በቤተ ክርስትያን ካለው መገፋት እና ኃፍረት የተነሳ መፍትሄን ከመፈለግ ያፈገፍጋሉ። ይህም ግለሰብ በቤተክርስትያን አገልግሎት ወይም መሪነት ቦታ ካለ ነገሮችን የበለጠ የተወሳሰቡ ይሆናሉ።
ሰው ችግሩን አምኖ የሚመጣው ይምጣ ብሎ እርዳታን መፈለግ ግን በሱሱ ዘልቆ ከሚመጣው ጉዳት አይብስም።
⛔️በኋላ እግዚአብሄር ፍርድ ፊት ከመቅረብ ዛሬ ላይ በሰው ፍርድ ውስጥ ማለፉ የተሻለ ነው።
ምንጭ:- ✍ኤርሚያስ ኪሮስ "ከፖርኖግራፊ ሱስ መውጣት ይቻላል"

Forwarded from Purity Tube
👉ጠንካራ ወጣት የሚሰማውን ሁሉ ወደ ውስጡ ዘልቆ ይገባ ዘንድ አይፈቅድም:: ☔️
👉ነገር ግን ራሱን በመግዛት ሁሉን በእርጋታ ይመረምራል 🤔
👉በእርግጥ ይህ እድሜ ፈታኝ ቢሆንም ባለቤት አለውና ውብ አድርጎ ይቀርጸው ዘንድ ዘወትር ቢፈቅድለት ኋላ የክብር እቃው ይሆናል💎
👉" ቅድስና ለእግዚአብሔር ።"(ኦሪት ዘጸአት 28 & 39
@Appeal4purity

😂ፈገግ የሚያሰኝ meme ቢሆንም ቁምነገር አዘል መልዕክት ይዟል
💯ለባል ትልቁ ንብረቱ ሚስቱ ናት❗️ 💯
♦️ ለወዳጅዎ #ሼር ያድርጉ ♦️
💢💢 @Appeal4purity 💢💢
💢💢 @Appeal4purity 💢💢
💯ለባል ትልቁ ንብረቱ ሚስቱ ናት❗️ 💯
♦️ ለወዳጅዎ #ሼር ያድርጉ ♦️
💢💢 @Appeal4purity 💢💢
💢💢 @Appeal4purity 💢💢
🔸🔸ስለ ድንግልነቷ አመስግናት🔸🔸
ብዙ ወንዶች ለሴት ልጅ ድንግልና የሚሰጡት ዋጋ እምብዛም አይደለም፡፡
🔹 ወንድ ልጅ ድንግል የሆነችን ልጅ ቢያገባ ከመጀመሪያው የወሲብ ግንኙነታቸው ከጥቂት ጊዜያት በኋላ የሚስቱ ድንግል መሆንን ከድሮ ትዝታዎቹ መዝገብ ውስጥ እንደቀላል ያስቀምጠዋል፡፡
🤷♂ይህ የብዙ ወንዶች ገሃዳዊ እውነታ ነው፡፡
👉 ለሚስቱ ግን ታሪኩ የተገላቢጦሽ ነው ፡፡ ራሷንና ድንግልናዋን ጠብቃ ስላቆየችለት እንዲያመሰግናት አጥብቃ ትፈልጋለች፡፡ ምናልባትም ሚሊዮን ጊዜ እሷን በማግኘቱ እንደተባረከ እንዲነግራት ትፈልጋለች፡፡
💢 ምክንያቱም #ድንግልናዋ ተራ የሰውነት ክፍሏ ሳይሆን #ማንነቷ_ነው ።
📌 ድንግልናዋን መስጠት ማለት ዳግም ላትወስደው የነፍሷን ክፋይ እንደመስጠት ነው፡፡
🔹 ምንም እንኳን ሴት መንፈሳዊ የሆነን ባል አግብታ ድንግልናዋን ብትሰጠው በመጀመሪያው የጫጉላ ጊዜያቸው ላይ የምትወደውን ሰው በሞት እንዳጣች ያህል ሊሰማትና ልታዝን ትችል ይሆናል፡፡
❓ አያችሁ ድንግልና ለሴት ልጅ ምን ያህል ጥልቅ ትርጉም እንዳለው❓
💔 በትክክለኛው ጊዜና ቦታ ብታጣውም እንኳን ውዷን እንዳጣች ይሰማታል፡፡
🎈ነገርግን ጥበበኛ ባል ይህን ሰሜቷን ስለ ድንግልነቷ በማመስገንና በማድነቅ ሊያረጋጋ ይችላል፡፡
#አስተውል
⛔️ይህ ማለት ግን በተገላቢጦሽ ሚስትህ ድንግል ሆና ባታገኛት ባለማስተዋል ስላደረገችው ንስሃ ገብታም እግዚአብሄር ይቅር ስላላት በደል ስትወቅሳት ኑር ማለት አይደለም‼️
#ሼር #Share📢
#couples #Married

🔵ሰው ብቻውን መሆኑ መልካም አይደለም
አሮን እራሱን ክርስቲያን ብሎ የሚጠራና ከባለቤቱጋር ሁልጊዜ ወደ ቤተክርስቲያን የሚሄድ ሰው ነው፡፡
ነገር ግን ችግር ሲያጋጥመው ለራሱ እንዲህ ይላል ፦"ዛሬ እንዴት ተስፋ አስቆራጭ ነገር እንደገጠመኝ ለባለቤቴ አልነግራትም ምክንያቱም ወንድ ነኝ ችግሬን ለማቃለል የማልችል ደካማ ሰው አድርጋ ልትቆጥረኝ አይገባም😒፡፡"
አሮን የሚከተለውን ጥቅስ ትርጉም አልተረዳም፡፡
👉"ሰው ብቻውን ይሆን ዘንድ መልካም አይደለም ፤ የሚመቸውን ረዳት እንፍጠርለት፡፡"
💢ማንኛውም ሰው ስለ ስሜቶቹ ከባለቤቱ ጋር ለመነጋገርማፈር የለበትም፡፡ አትንቀውም እንደውም የበለጠ ትወደዋለች፡፡
🔶ስሜትን እርስበርስ መነጋገር በከፍተኛ ደረጃ መግባባትን ይፈጥራል ፤ በትዳርም የከበረ ቅርበት ስለሚፈጠር ትዳር ጣፋጭ ይሆናል❤️❤️፡፡
#Married
#Couples

https://www.youtube.com/watch?v=aFcRIicf5qY
👉ጥሩ ባል ወይም ጥሩ ሚስት ለመሆን የሚያስፈልገው
💢💢 @Appeal4purity 💢💢
💢💢 @Appeal4purity💢💢
👉ጥሩ ባል ወይም ጥሩ ሚስት ለመሆን የሚያስፈልገው
💢💢 @Appeal4purity 💢💢
💢💢 @Appeal4purity💢💢
YouTube
ጥሩ ባል ወይም ጥሩ ሚስት ለመሆን የሚያስፈልገው - - - Appeal for Purity
Visit our website:
www.appealforpurity.org
Or, our Facebook page:
www.facebook.com/appealforpurity
To make an appointment for marriage/personal counseling, Email me:
[email protected]
Or, TEXT me: 240-393-8249
I give counseling service, for…
www.appealforpurity.org
Or, our Facebook page:
www.facebook.com/appealforpurity
To make an appointment for marriage/personal counseling, Email me:
[email protected]
Or, TEXT me: 240-393-8249
I give counseling service, for…
Forwarded from Purity Tube
📛📛 ዛሬ የማይታይ ዝገት ⛔️⛔️
👱♀"አንድ ልጅ አለ በጣም አስተዋይ ሰው ነው ግን በጌታ አይደለም እና እንዳገባው ጠየቀኝ ከዛ...."
👱" የምወዳት ልጅ አማኝ አይደለችም ግን ከብዙ ክርስቲያን ነን ባይ ሴቶች የተሻለ ምግባር አላት....."
👩" ይኸው ላለፉት ስምንት አመታት ከብዙ ክርስቲያን ወንዶች ጋር ግንኙነት ፈጥሬ አውቃለሁ ግን ከሶስት ወር በፊት ያወኩት አህዛብ ልጅ ግን ሁሉንም ያስንቃል...."
ከላይ ያሉትና የመሳሰሉ ተመሳሳይ ጥያቄዎች በተደጋጋሚ ይጠየቃሉ፡፡
👉 በወርቃማ ቅብ ያማረ ብረትን ጌጥ ብለህ በእጅህ ላይ ብታስረው ምናልባት እንደጌጥ ሊያገለግልህና ኮራ ብለህ በሰዎች ፊት ልታሳየው የምትችለው በጣም ውስን ለሆነ ጊዜ ነው፡፡
ከተወሰነ ጊዜ በኋላ የምትኮራበት ያ ጌጥ እራሱ የምታፍርበት መሆኑ አያጠራጥርም ፡፡ ምክንያቱም በእጅህ ላይ ያሰርከው በወርቃማ ቀለም የተሸፈነ ብረት እንጂ ወርቅ አይደለምና በላዩ የተቀባውን ቀለም አሸንፎ ዝገቱን ያጋልጣል ፡፡ የዛገን ነገር እንደጌጥ መጠቀም ማን ይመርጣል❓
ከላይ ተቀንጭበው የተጠቀሱት ታሪኮችም በወርቃማ ቀለም ከተሸፈነው ብረት የተለየ ሁኔታ የላቸውም ፡፡
▶️ "በጣም ጥሩ ሰው ነው" ፣ " ፀባዩ አንደኛ ነው" ፣ " እጅግ አስተዋይ ናት " እና የመሳሰሉት ወርቃማ ቀለሞች ምናልባት ለጊዜው በእውቀትና በእግዚአብሔር ቃል ሳይሆን በስሜት እንድንገዛ ሊጎትቱን ይችሉ ይሆናል፡፡
ጊዜያዊ ስሜታችንም እሰኪበርድ ድረስ ጥልቅ ፍስሃ ይሰጡ ይሆናል፡፡
💠ነገርግን ያ የሚያምረው ወርቃማ ቀለም ሲደበዝዝ ከታች ያለው ማለትም እንደ "ግን በጌታ አይደለም" ፣ "ግን አማኝ አይደለም " እና የመሳሰሉ ዝገቶች "ሙታን" በሚለው መፅሀፍቅዱሳዊ ቃል ማህተም ታትመው ራሳቸውን መግለጥ ሲጀምሩ ትላንት የፈጠሩትን ደስታ የሚያስረሳ ሃዘን ይዘው ይከሰታሉ፡፡
🗣 ለዚህ ምስክር ይሆን ዘንድ በስህተት ካላመኑ ሰዎች ጋር በትዳር ከተጠመዱ ሰዎች አንደበት የሚወጡ የፀፀት እና የምሬት ቃሎችን መስማት በቂ ነው፡፡
👉ለስሜት ሳይሆን ለእግዚአብሔር ቃል መታዘዝ የአስተዋይ ሰው ምርጫ ነው፡፡
#single

📛አደገኛ መረዳት⚔️
⛔️አንተና እጮኛህ 'እንደምትመቻቹ' ለማወቅ ወሲብን ከጋብቻ በፊት እየሞከራችሁ ካላችሁ ወይም ለመሞከር እያሰባችሁ ከሆነ በዚህች ዓለም የተሳሳተ መልዕክት ተሸውዳችኋል ማለት ነው
🛑"የወሲብ መጣጣም" የሚለው ሃረግ በራሱ እጅግ አሳሳች የሆነ ሃረግ ነው፡፡ ምክንያቱም የሰውን አካል በወሲብ መሞከር አይቻልምና፡፡
❌ልክ የሆነ ምግብ ቀምሰን እንደምንሞክረው ሁሉ ሰውን ሞክረን ይሆናል ወይም አይሆንም ማለት አንችልም፡፡
👉ወሲብ ለሙከራ ሳይሆን ለህይወት ዘመን ግንኙነት የተወሰነ መልካም ነገር ነው፡፡
👉 ወሲብ ትንሹ የትዳር ክፍል ነው፡፡ ሚዲያው ነው ትልቁ የትዳር ክፍል እንዲመስል ያደረገው፡፡
ግን አይደለም ቢሆን ኖሮ መፅሐፍ ቅዱስ በግልፅ በነገረን ነበር፡፡
💢 ይህ እውነት ሰርፆ እስኪገባን ድረስና ውስጣችንን እንዲያሸንፍ እስካልፈቀድንለት ድረስ ግጣማችንን ፍለጋ በየቦታው እየተኛን መቀጠላችን ነው፡፡
📛 እናም የሆነ ቀን ያን ትክክለኛ ሰው እነዳገኘን ሲሰማን በአጭር ጊዜ ውስጥ ወደ ትዳር ዘለን እንገባለን ፡፡
👉 ግን ትንሽ ቆይተን በሁሉ ነገር ( በወሲብ ፣ በመንፈሳዊ ነገር ፣ በአስተሳሰብ ፣ በስሜትና በሌሎች) እንደማንጣጣም ሲገባን አስደንጋጭ ሁኔታ ውስጥ እንዳለን ይገባናል፡፡
❓ #ከዛስ ❓
"ውይ በቃ አልተሳካም ይሄ ነገር ለአንዳንድ እድለኞች እንጂ ለኔ አይሰራም 😔 " ብለን ከትዳር ልንወጣ ነው?
💯 ቅድመ ጋብቻ ወሲብ ጎጂ ውጤቶች አሉት፡፡
ለምን❓
👉እውር የማድረግና ነገሮችን ከእግዚአብሔር ቃል አንፃር የሚያመዛዝነውን አእምሮአችንን የመዝጋት አቅም አለው፡፡
📌 ከሁሉ የተሻለው ነገር ከጋብቻ በፊት ካለ ወሲብ መራቅ ነው ፡፡(1ኛ ቆሮ 6፥ 18)
📌 አዎ ከዚህ ሃጢያት #ሽሹ #ዛሬውኑ! #አሁኑኑ!
📜 (1 ተሰ 4 )
------------
3 ይህ የእግዚአብሔር ፈቃድ እርሱም መቀደሳችሁ ነውና፤
4-5 ከዝሙት እንድትርቁ፥ እግዚአብሔርን እንደማያውቁ አሕዛብ በፍትወት ምኞት አይደለም እንጂ፥ ከእናንተ እያንዳንዱ የራሱን ዕቃ በቅድስናና በክብር ያገኝ ዘንድ እንዲያውቅ፤
6 አስቀድመን ደግሞ እንዳልናችሁና እንደ መሰከርንላችሁ፥ ጌታ ስለዚህ ነገር ሁሉ የሚበቀል ነውና ማንም በዚህ ነገር አይተላለፍ ወንድሙንም አያታልል።
#Couples #single

✨መልካም ምክር ለእህቶች✨
♦️ወሲብ በጭራሽ! የፍቅር መመዘኛ አይደለም!።
የምትወጅኝ ከሆነ በተግባር ልየዉ አንቺነትሽን ስጭኝ?
💡መልስሽ መሆን ያለበት አይሆንም🚫 አይሆንም 🚫 እና አይሆንም 🚫ነዉ።
❓መጠየቅ የሚገባሽ ነገር ስለምን ሳንጋባ በፊት ለወሲብ ትጠይቀኛለህ ? ፣ የእግዚአብሄር ፈቃድስ ይሄ ነው ወይ?
💯% በእርግጠኝነት ልትናገሪ የሚገባሽ ነገር በእጮኝነት ጊዜ ለወሲብ መጠየቅ እራስ ወዳድነት የሚያመላክት መሆኑን ነው።
🔑ቁልፍ የሆነው ነገር የወሲብ ጥማቱን ለማርካት ሲል ወደ ህይወትሽ የመጣን ሰዉ በእንቢታሽ ከፀናሽ ያለ ምንም ፀብ በአገር ሰላም እስከ መጨረሻዉ ላይመጣ ከህይወትሽ ይወጣል። ምክንያቱም ሀሳቡን ማስፈፀሚያ በመፈለግ ስለሚጠመድ።
👉 ይሄኔ ብቻሽን የቀረሽ ሊመስልሽ ይችላል። ነገር ግን የተፈጠረዉ ችግር ጊዜያዊ እና አላፊ ነዉ። እንደዉም በወሲባዊ ቅድስና እግዚአብሄርን ስላከበርሽው በመሞከር እድሜሽን እንዳትፈጂ እግዚአብሄር ትክክለኛዉን ሰዉ ወዳንቺ ሊያመጣዉ እንደሆነ ተረጂ።
#Share
© @StopAbortion

==== #ሀጢያት ነው እንዴ❓❓====
አንዳንድ ጊዜ እንደዚህ አይነት ጥያቄዎች ይጠየቃሉ ፦
⏩ "ቆይ እኔና ፍቅረኛዬ sex ሳናደርግ አብረን ብንተኛ ሀጢያት ነው? ሀጢያት ከሆነ አብረን እንዳንተኛ የሚከለክል የመፅሐፍ ቅዱስ ጥቅስ የታለ?"
⏩"መፅሀፍ ቅዱስ ውስጥ ከጋብቻ በፊት አብሮ መኖርን የሚከለክል ጥቅስ አለ?"
@Appeal4purity
⏩ "መፅሀፍ ቅዱስ ከጋብቻ በፊት sex አታድርጉ የሚለው የቱ ጋ ነው?"
⏩ "ከጋብቻ በፊት sex አድርገን ከዛ በኀላ ብንጋባስ? ይሄን የሚከለክል ትዕዛዝ በመፅሀፍ ቅዱስ ውስጥ አለ?"
እነዚህና መሠል ጥያቄዎችን ባነበብኩ ጊዜ ሁሉ መፅሀፍ ቅዱስ ውስጥ እነዚህን የሚከለክሉ ጥቅሶችን ዘርዝሬ 'ይሄው!' ለማለት እፈተናለው፡
👉ነገርግን መፅሀፍ ቅዱስ ውስጥ ያሉ ትዕዛዛት የእግዚአብሔርን ፈቃድ የመፈለግና የማድረግ ችሎታን መስጠት ቢችሉ ኖሮ ክርስቶስ ባላስፈለገን ነበር፡፡⚠⚠⚠
" ...... ጽድቅስ በሕግ በኩል ከሆነ እንኪያስ ክርስቶስ በከንቱ ሞተ።".......(ወደ ገላትያ ሰዎች 2:21). @Appeal4purity
✅ "መፅሐፍ ቅዱስ ውስጥ የቱጋ ነው እንደዚህና እንደዚያ አድርጉ አታድርጉ የሚለው?" እንደዚህ አይነት ጥያቄዎችን የምንጠይቀው በክርስቶስ ያገኘነውን ነፃነት በትክክል ሳንረዳ ስንቀር ነው፡፡
👉👉በእግዚአብሔር ቃል መሠረት በኢየሱስ የመስቀል ላይ ስራ ከሀጢያት እስራት ተፈተን ለፅድቅ ባሪያዎች እንደሆንን እንረዳለን(ሮሜ 6፥18)፡፡
👉ይህም ማለት ለእግዚአብሔር ፍቅራችንን ልንሰጠው የእርሱንም ፍቅር ለመቀበል ነፃ ሰዎች ነን ማለት ነው፡፡ምክንያቱም የእግዚአብሔር ቤተሰብ ሆነናል፡፡ @Appeal4purity
✍ አንዴ ይሄን እውነት ከተረዳን 💥 ጥያቄአችን "ይሄ ነገር (ማንኛውም "ነገር" ይሁን) ወደ እግዚአብሄር ያቀርበኛል? ከመንፈስ ቅዱስ ጋር ያለኝን ጥብቅ ግንኙነት ያሳድግልኛል?" የሚል ይሆናል፡፡
ለዚህ ጥያቄ የምናገኘው መልስም ግልፅ ይሆናል ፡፡ 💯 #አዎ ✅ ወይም #አይ ❌
#General

👉ለእህቶች ጠቅላላ እውቀት
የእርግዝና ምልክቶች እና አመጋገብ
እንድ ሴት አርግዛ ከሆነ በመጀመሪያው ሳምንት የተለያዩ ምልክቶች ያጋጥሟታል።
1. ማቅለሽለሽ
2.የጡቶች መጠን መጨመርና የህመም ሰሜት
3. ከወትሮው በተለየ ቶሎ ቶሎ መሽናት
4. ከወትሮው በበለጠ የድካም ስሜት
5. በታችኛው ሆድ አከባቢ ትንሽ ቁርጠት
*እንደገና በእርግዝና የመጨረሻዎቹ ሳምንታት ውስጥ የሚታዩ ምልክቶች፦
1.ቃር ወይም ምግብ ቶሎ አለመፈጨት
2.የሆድ ድርቀት፣ትንፋሽ ማጠር
3. የፍንጢጣ ደም ስሮች ማበጥ (የፊንጢጣ ኪንታሮት)
4.የአፍንጫ የማፈን ሰሜት እና ነስር
5.የጀርባ ህመም፣እንቅልፍ ማጣት፣ራስ ምታት
6.የድድ መድማት፣የድካም ስሜት፣የጸጉር መወፈር
7.ቶሎ ቶሎ መሽናት መፈለግ ወይም ለሊት ለሽንት መነሳት
8.ትንሽ የእግር ወይም የቁርጭምጭሚት ማበጥ
12. የጣቶች ትንሽ እብጠት እና የመደንዘዝ ስሜት
13. የዳሌ የደም ስሮች ማበጥ (Varicose veins)
14. የውሸት የምጥ ስሜት (Braxton Hicks uterine contractions)
15.የቆዳ ላይ ለውጦች ለምሳሌ ማድያት ፣ የሆድ ሸንተረር ፣ የመዳፍ መቅላት
*አደገኛ የእርግዝና ምልክቶች የሚባሉት፦
1. ከብልት ደም መፍሰስ፣ የእንሽርት ውሃ መፍሰስ
2.የጽንሱ እንቅስቃሴ መቀነስ
3.ሃይለኛ ቁርጠት ፣ከፍተኛ ድካም ወይም ማዞር
4.ትኩሳት፣ከባድ ራስ ምታት ፣ ፊት እና እግር ማበጥ ፣ ብዥታ
=>ከላይ የተጠቀሱት አደገኛ የእርግዝና ምልክቶች ከታዩ ዶክተር ማማከር ይጠበቅበዎታል።
*በእርግዝና ወቅት ንጥረ ነገር ላይ ያተኩሩ ጤናማ የእርግዝና አመጋገብ እንደ አትክልት፣ፍራፍሬ መመገብ አስፈላጊ ነው።
1.ፎሌትና እና ፎሊክ አሲድ
*ፎሌትና እና ፎሊክ አሲድ ከወሊድ ጋር ተያያዥ የሆነዉን ተፈጥሮያዊ ጉድለቶችን፣ በህብለ ሰረሰር ላይ ሊደርስ የሚችለዉን ተፈጥሮያዊ ክፍተት፣ አንዲሁም ከባድ የሆነ የአዕምሮ እና የህብለ ሰረሰር ችግሮችን ለመከላከል ይረዳል፡፡
ለምሳሌ አረንጓዴ ቅጠላማ አትክልቶች፣ ፍራፍሬዎች የቫይታሚን ቢ፣የደረቁ ባቄላና አተር በተፈጥሮ ጥሩ የፎሌት ምንጮች ናቸው፡፡
2.ካልሲየም
*ካልሲየም እርስዎ፣ለፅንሱ፣ለአጥንትና ለጥርስ ጥንካሬ፣ለደም ዝውውር፣ የጡንቻና የነርቭ ሰርዓት በአግባቡ እንዲሰሩ የሚረዳ አስፈላጊ ንጥረነገር ነዉ፡፡ለምሳሌ ወተት፣የወተት ተዋፅኦዎች፣የአበባ ጎመን፣ብዙዎቹ የፍራፍሬ ጅውስ እና ጥራጥሬዎች ጥሩ የካልሲየም ምንጮች ናቸው።
3.ቫይታሚን ዲ
*ቫይታሚን ዲ ለአጥንት ጥንካሬ መጎልበት፣ የልጅዎን አጥንትና ጥርስ ለመገንባት ይጠቅማል፡፡ለሞሳሌ ዓሳ፣ የበለፀጉ ወተቶችና የብርቱካን ጂዉስ የመሳሰሉት የቫይታሚን ዲ ምንጮች ናቸው።
4.ፕሮቲን
*ፕሮቲን እድገትን ለማፋጠን
በእርግዝናዎ ወቅት ለፅንሱ እድገት ከሚያስፈልጉ ወሳኝ ነገሮች ዉስጥ አንዱ ነዉ፡፡
ለምሳሌ ቀይ ስጋ፣ የዶሮ ስጋ፣ ዓሳና እቁላል ጥሩ የፕሮቲን ምንጮች ናቸዉ፡፡ በተጨማሪም ፕሮቲንን ከባቄላ፣ ኦቾሎኒ ከአዝርእትና አኩሪአተር ዉጤቶች ይገኛሉ፡፡
5.የብረት ማዕድን
*በብረት ማዕድን እጥረት ምክንያት የሚመጣዉን የደም ማነስ ለመከላከል ሰዉነታችን የብረት ማዕድንን ሄሞግሎቢንን ለመስራት ይጠቀምበታል፡፡ ሄሞግሎቢን ደግሞ ኦክሲጅንን ወደ ሰዉነታችን ተሸክሞ ለማድረስ ያገለግላል፡፡
* ነፍሰጡር እናቶች ነፍሰጡር ካልሆኑ እናቶች ጋር ሲነፃፀሩ የብረት ማዕድን ሁለት እጥፍ ያስፈልጋቸዋል፡፡ ይህም ለልጅዎ ኦክሲጂን ለማቅረብ ተጨማሪ ደም ስለሚያስፈልግ ይኸን ለመስራት ያገለግላል፡፡በእርግዝናዎ ወቅት በቂ የብረት ማዕድን ካላገኙ የደም ማነስ ይከሰታል፡፡ የደም ማነሱ ደግሞ ከፍተኛ ከሆነ ፅንሱ ያለግዜዉ የመወለድ አደጋ፣ ፅንሱ ሲወለድ ዝቅተኛ ክብደት እንዲኖረዉ ማድረግና ከወለዱ በኋላ ድብርት እንዲከሰት ሊያደርግ ይችላል፡፡
ለምሳሌ ቀይ ስጋ፣ የዶሮ ስጋና ዓሳ፣ ባቄላና አትክልቶች(በተለይ አረንጓዴ ቅጠላቅጠሎች) ጥሩ የብረት ማዕድን ምንጮች ናቸው።
#General
© 👉 @Doctoralle8809

●●●እራት ጭብጨባ●●●
የት/ቤት ገጓደኛዬ አንድ ነገር አጫወተቺኝ .....
የምትሰራው የአእምሮ እድገት ውስንነት (intellectual disability) ያለባችው ልጆች ማሰልጠኛ ት/ቤት ውስጥ በመምህርነት(በአሠልጣኝነት) ነው:: በምታስተምርበት ክፍል ውስጥ አብዛኛዎቹ የ down syndrome ጉዳት ያለባችው ናቸው፡፡ የማስታወስ ብቃታቸውን ለማሳደግ ሁልጊዜ ጠዋት ጠዋት memorization training በምትሰጥበት ወቅት እያንዳንዱ ልጅ እራት ምን እንደበላ(ች) ትጠይቃቸዋለች፡፡ ከተማሪዎቹ አንዱ እራት ምን እንደበላ ሲጠየቅ የሁልጊዜ መልሱ “እራት ጭብጨባ ነው” በማለት ይመልሳል፡፡ እራት ማታ የሚበላ ምግብ እንደሆነ ልታስተምረው ብትሞክርም የልጁ መልስ ሁልጊዜ “እራት ጭብጨባ ነው” የሚል ነበር፡፡
ይሄ መልሱ በጣም ስላሳሰባት ወላጆቹን ማናገር እንዳለባት ወስና ልጁ ወደሚኖርበት ቤት አመራች፡፡ ቤታቸው በጣም አነስተኛና ጎስቆል ያለ የሚባል አይነት ነው፡፡ ያገኘችው የልጁን አያት ነበር፡፡ ልጁ እናትና አባቱ በህይወት እንደሌሉና እሳቸው (አያት) እንደሚያሳድጉት ነገሯት፡፡ የኑሯቸውን ሁኔታና ልጁ እራቱን ምን እንደሚበላ ስትጠይቃቸው በጣም በችግር እንደሚኖሩና የሚመገቡት ነገር እንደሌላቸውና ልጁም ከስንት አንዴ ሲገኝ እንደሚበላ ነገሯት፡፡ እራት ጭብጨባ የሚልበትም ምክንያት አብረዋችው የሚኖሩት አጎቶቹ የእራት ሰአት ሲደርስ ስጡኝ እያለ ሲያስቸግራቸው “… እራት ጭብጨባ ነው ሶስት አጨብጭብና ተኛ…” ይሉት ነበር፡፡
ስለዚህ ይህ ልጅ ከልጅነቱ ጀምሮ አዕምሮው ላይ ያደገው ወይም የልጁ መረዳት እራት ማለት ሶስቴ አጨብጭቦ መተኛት እንደሆነ ነው፡፡ ስለዚህ ሁልጊዜ ማታ ማታ እራት ጭብጨባ እያለ ሶስቴ አጨብጭቦ ወደ መኝታው ይሄዳል፡፡ አእምሮው የተቀበለው ጭብጨባን ስለሆነ ራቱን ምግብ መብላት እንዳለበት መቀበል አቅቶት ነበር፡፡ እራት ማለት ምግብ መመገብ እንደሆነ የተረዳው ከብዙ ጊዜ ሰልጠና በኋላ ነበር፡፡ (በነገራችን ላይ የ down syndrome ጉዳት ያለባችው ልጆች የጉዳቱ ደረጃ ከፍ ያለ ሲሆን ራበኝ፤ ጠማኝ ፤ጠገብኩ፤ ደከመኝ ወዘተ… አይሉም ምክንያቱም ስሜታቸውን መረዳት ስለማይችሉ፡፡)
ይህን ካጫወተችኝ በኋላ ከጓደኞቼ ጋር በመሆን ተመሳሳይና ከዚህም የባሰ ችግር ውስጥ ያሉ ልጆችን ለመጎብኘት ወስነን ቤት ለቤት ጉብኝታችንን ጀመርን፡፡ በየቤቱ ያየነው ነገር በታም ከባድና ከጠበቅነው በላይ ነበር፡፡
… ለምሳሌ አንድ የአእምሮ እድገት ውስንነትና የመናገር ችግር ያለባት ልጅ ተደፍራ ታማ ተኝታ ነበር … የምትኖረው ከእናቷና ከእህቷ ጋር ነው፡፡ … መድሐኒት መግዣና የሚበሉት ምግብ ራሱ አልነበራቸውም ፤ ሌላው ደግሞ የ down syndrome ጉዳት ያለበት ልጅ ክእናቱ ጋር በጣም ጎስቆል ያለ የሚባል አይነት ቤት ውስጥ አገኘናቸው የሚያሳዝነው ነገር እናቱ የልብ ድካም ታማሚ ነች ሁልቱም ታመው ነው ያገኘናቸው እነሱም ተመሳሳይ የሆነ የመብል እጦት ውስጥ ናቸው፡፡
… በአጠቃላይ እኛ ካገኘናቸው ውስጥ በተመሳሳይና ከዚህም በባሰ ችግር ውስጥ ያሉ 22 ልጆች አሉ፡፡ ከ90% በላይ የሚሆኑት ብአኛ እናቶቸ (single mom) ናቸው፡፡ አብዛኛዎቹ የሚሰሩት ልብስ ማጠብ ፤ እንጀራ መጋገር ፤ ብሎኬት መሸከምና የተለያዩ የቀን ስራዎች ነው፡፡ …. ወላጆቻቸው እንዳሳወቁን ከመቼውም በላይ ከባድ ጊዜ የሚያሳልፉት በክረም ወቅት ነው፡፡ ምክንያቱም ክረምት ትምህርት ቤቱ ይዘጋል፡፡ ስለዚህ ትምህርት ቤቱ የሚሰጠው የቁርስና የምሳ አቅርቦት ይቋረጣል፡፡ በዛላይ ልጆቹ እቤት ስለሚውሉ ወላጅ ስራውን ትቶ ከነሱ ጋር መዋል ይኖርበታል ምክንያቱም እንክብካቤና የተለያዩ ቴራፒ ስለሚያስፈልጋቸው፡፡
ይህን ሁሉ ከተመለከትን በኋላ በሰኔ ወር 2009 ዓ.ም በቡድን በመሆን ለ22 ልጆች ለክረምት የሚሆናቸውን ቀለብ ለመስፈር ሞክረናል፡፡ እንዲሁም በዚሁ አመት የተለያዩ እቅዶቸን አቅደናል፡፡
የዚህ ስራ አጋር መሆን የምትፈልጉና እንዲሁም እነዚህን ወገኖች በግንባር መጎብኘትና መርዳት የምትፈልጉ inbox ወይም በዚህ ቁጥር 0962212861 ወይም
0962212862 ደውላችሁ አናግሩን፡፡
‹‹ ንጉሱም መልሶ እውነት እላችኋለሁ፤ ከሁሉ ከሚያንሱ ከእነዚህ ወንድሞቼ ለአንዱ እንኳን ስላደረጋችሁት ለእኔ አደረጋችሁት ይላቸዋል ›› ማቴ 25፤40 @eratchebecheba

👉የፍቅር ጓደኝነት በአካል ከመቀራረብ የላቀ ነው❕👈
✨የእያንዳንዳችን ሕይወት አምሥት በውል የታወቁ ክፍሎች አሉት።
እነርሱም 👉አካላዊ፣
👉ስሜታዊ
👉ሕሊናዊ
👉ማኅበራዊና መንፈሳዊ ናቸው።
⏩እነዚህ አምሥቱም የሕይወታችን ክፍሎች እርስ በርሳቸው ልክ እንደጠንካራ ገመድ ተሸራርበውና ተጣጥመው እንዲሰሩ
ተደርገው ነው የተፈጠሩት።
✨በፍቅር ጓደኝነት ፍለጋ እንቆቅልሻችን ዛሬ ወይም ቢቻል ትላንት እንዲፈታ እንፈልጋልን።
👉ከችግሮቻችን መካከል አንደኛው የአንድ አፍታ ርካታን አጥብቀን መፈለጋችን ነው።
ስለዚህ የፈለግነው ለአፍታ የምንረካበት መንገድ ወይም መፍትሄ እንጂ
እውነተኛ የፍቅር አይደለም።
✨ካሉን አምሥት የስብዕናችን ክፍሎች
ውስጥ አንዱን ብቻ ነው መርጠን መልስ ልንሰጠው የቻልነው።
የአካላችንን ፍላጎት ብቻ ነው ማስተናገድ የቻልነው።
👉ችግሩ ደግሞ ከማንም ጋር በአካል ብቻ እጅግ በጣም የቀረበ ግንኙነትን በቀላሉ መፍጠር የሚቻል ቢሆንም በሌሎቹ በአራቱ የስብዕናችን ክፍሎች ግን እንዲህ በቀላሉ የምንከውነውና እንደ ገለባ እሳት አንድደን የምናጠፋው ዓይነት አይደለም።
🔴ከአንድ ሰዓት ወይንም ከግማሽ ሰዓት
ባልበለጠ ጊዜ ውስጥ ከአንድ ተቃራኒ ጾታ ጋር ተቀራርበህ አካላዊ ውህደት መፍጠርና መቋጨት ትችላለህ፤ ።
🔴ነገሮችህን በዚህ መልክ ከቋጨህ በኋላ በደቂቃዎች ውስጥ ወሲብ ለውጭያዊ ፍላጎት ጊዜያዊ ማስተንፈሻ ብቻ እንደሆነ ትረዳለህ።
💁አሁንም ደጋግሞ እንዲገባን የሚያስፈልገው ዕውነተኛ የፍቅር ጓደኝነት ከዚህ በላቀ ሁኔታ በሂደት ውስጥ አልፎ የሚገኝ መሆኑን ማወቅ ይኖርብናል።
❓ለመሆኑ ደጋግማችሁ ወሲብ ካደረጋችሁ ፍላጎታችሁ የሚቀንስ ይመስላችኋል❓ምናልባት « ፍቅር ስለያዘኝ ነው? » ትሉ ይሆናል።
👉ውስጣችሁ ግን ባለመርካት ይታመስና ሕሊናችሁም በከባድ ጸጸት ውስጥ ይወድቃል።
♻ኮሌጆች ውስጥ የሚገኙ አያሌ ተማሪዎች እወነተኛ ፍቅር ጓደኛ ፍለጋ ከአንዱ ግንኙነት ወደሌላው ሲባዝኑ
ይስተዋላል። እየባዘኑ እያለ በእያንዳንዳቸው ግነኙነታቸው ውስጥ ራሳቸውን፡-
« ይህ እንግዲህ የመጨረሻውና ትክክለኛው ምርጫዬ ነው ፤ አሁን ግን አግኝቻታለሁ ። አሁን በቃ የነፍስ አጋሬን
አግኝቼዋለሁ» ይላሉ።
⏩እኔ እንደማምንበት ለፍለጋ የምንባዝነው ለወሲብ ሳይሆን ፍቅርን ፍለጋ ነው።
ዛሬ የፍቅር ጓደኝነት ማለት የወሲብ ጓደኝነት የሚለውን ትርጉም ይዞ
ነው የተገኘው።
✨ሆኖም ግን የፍቅር ጓደኝነት ትርጉሙ ከዚያ እጅግ ያለፈ ነው። የፍቅር ጓደኝነት ሕይወታችንና የስብዕናችን ክፍሎች
ያካትታል፤
- አዎ ! አካላዊ፣ ስሜታዊ፣ ሕሊናዊ፣ ማህበራዊና መንፈሳዊ ስብዕናችንን ይጨምራል።
👉👉እውነተኛ የፍቅር ጓደኝነት ማለት
ሕይወትን አንድም ሳያስቀሩ ማካፈል ማለት ነው።👈👈💯
✴ታዲያ ሁላችንስ ብንሆን አንድም ሳናስቀር ህይወታችንን ለሌላው የማካፈል ስሜት
ውልብ አላለብንም❓

👉" ክርስቶስም ካልተነሣ እንግዲያስ ስብከታችን ከንቱ ነው እምነታችሁም ደግሞ ከንቱ ናት፤"
(1ኛ ወደ ቆሮንቶስ ሰዎች 15:14)
የጌታችን ትንሳኤ ለሚያምንበት ሁሉ ከታሪክ የዘለለ ትርጉም ያለው የክርስትና ማዕከላዊ አጀንዳ ነው።
👉 ከሙታን በመነሳቱ አብረነው ተነስተናል።
👉በሰማያዊ ስፍራ ከርሱ ጋር ተቀምጠናል።
👉 በማይሻር ኪዳን በማይጠፋ ህይወት ዳግም ተወልደናል።
👉ተወዳጆች ስብከታችን ታሪክ ትረካ ሳይሆን ሞት አቅም ያጣበት የትንሳኤ እውነት ነውና መንፈስ ቅዱስ ይህን በልባችን አድምቆ ይሳል።
ፅጋ ይብዛላችሁ።

=======የጠፋው ማስረጃ======
ዳኛው ተሰይሟል ፤ ተከሳሽ ሰው በሸንጎው ፊት በተከሳሾች መቆሚያ ቆሟል ፤ ከሳሽ ሰይጣን በደስታ ቆሟል
ተከሳሽ ሰው እራሱ ጥፋተኛ እንደሆነ ፣ ፍርዱንም እንደማይችለው አውቆ አዝኗል
ሰይጣን የሰውን ሀዘን እያየ ይስቃል፡፡
በዚህ ሁኔታ ነበር ጠበቃው ኢየሱስ የቀረበው
ኢየሱስ ፦ አንተ ዲያቢሎስ ሰው ሞት ይገባዋል ነው የምትለው?
ሰይጣን ፦ አዎ ሰው ሀጢያትን ሰርቷል ስለዚህ የገሃነም እሳት ፍርድ ይገባዋል!!
ኢየሱስ ፦ ማስረጃ አለህ?
ሰይጣን ፦ እንዴ አዎ ለዚያውም ብዙ
ኢየሱስ ፦ ማስረጃህ የታል??
ሰይጣን ማስረጃውን ፈለገው የለም ፤ ላይ ወጣ ታች ወረደ ማስረጃው ግን የለም ፡፡ ከሳሹ ደነገጠ ተከሳሽ ሰው ፈገግ አለ የሀዘኑ ደመና ገሸሽ አለ፡፡
ያለማስረጃ ፍርድ የለም ሰው ነፃ ሆነ ዲያቢሎስ አፈረ፡፡
ማስረጃው ግን የት ሄደ??
የሆነው እንዲህ ነው የኃጢያታችን ማስረጃ ተደምስሷል!! ኢየሱስ ሁሉንም ሰብስቦ በመስቀል ላይ ቸንክሮ ደምስሶታል!!
አሜን!!
፠ እናንተም በበደላችሁና ሥጋችሁን ባለመገረዝ ሙታን በሆናችሁ ጊዜ፥ ከእርሱ ጋር ሕይወትን ሰጣችሁ። በደላችሁን ሁሉ ይቅር አላችሁ። በእኛ ላይ የነበረውን የሚቃወመንንም በትእዛዛት የተጻፈውን የዕዳ ጽሕፈት ደመሰሰው። እርሱንም በመስቀል ጠርቆ ከመንገድ አስወግዶታል።
ወደ ቆላስይስ ሰዎች 2 : 13-14
#share